Friday, 20 December 2013
እባክዎን ይንን መልዕክት ያስተላልፉ!!!!
እባክዎን ይንን መልዕክት ያስተላልፉ!!!! እስከ መጨረሻው ያንብቡት እኔ በተወለድኩበት ትግራይ ክፍለሃገር ውስጥ የትግራይ ሪፑብሊክ ለመመስረት መነሻ አድርጐ ያሰራጫቸው መግለጫዎቹ መሰረት በማድረግ “ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ” ብሎ እራሱን ሰይሞ ወደ ጫካ በመግባት ከደርግ ወታደራዊ መንግሥት ጋር ባካሄደው የትጥቅ ትግል በተለያዩ ምክንያቶች “በለስ ቀንቶት” ደርግን አሸንፎ የመንግሥት መንበር ከተቆጣጠረ ወዲህ ኢትዮጵያን እንደ ደቡብ አፍሪካ ዘረኛው የነጮች መንግሥት በጐሳ/በቋንቋ አስተዳደር አዋቅሮ “ጸረ አማራ” ሕብረተሰብ እና “ጸረ አገር” ዕቅድ ነድፎ ሕዝቧን እና አንድነቷን ለማበጣበጥ የተመሰረተ የፖለቲካ ድርጅት እንደሆነ በተለያዩ ጊዜያት በጽሑፍም በቃለ መጠይቅም በመጽሐፍቶቼም ገልጫለሁ። አሁን በስልጣን ላይ እየባለገ ያለው “ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ” በታሪካችን ውስጥ ለጆሮ እና ለዓይን የሚከብዱ፤ በሕዝባችን እና በአገራችን ሉአላዊ ክብር ላይ ብዙ አስነዋሪ ወንጀሎች የፈጸመ ቢሆንም፤ ለዓይን እና ለጀሮ ጐልቶ የሚታየው ጥቃት በአማራ ሕብረተሰብ ሕይወት ላይ ፈጽሟል። ይህ የአማራ ጥቃት ከመላ የተለያዩ የአገሪቱ ጐሳዎች ሁሉ በይበልጥ የጥቃት ማሕደሩ የተከመረው በአማራው ላይ ነው። በዚህ ጎሳ (ዘር/ሀረግ) ላይ ያነጣጠረው የወያኔ ጥቃት በምንም መለኪያው በማንኛውም ጎሳ ላይ የደረሰውጉዳት ሲነጻጸር የት የሌለ ነው። አማራው ለዘመናት ሲኖርባቸው አካባቢዎች ውጣ እየተባለ ከነቤተሰቦቹ ሲባረር፤ኦሮሞው፤ትግሬው፤አደሬው፤ሶማሌው፤ አፋሩ፤ጋምቤለው፤ወላይታው፤ወዘተ…ወዘተ… አልተባረረም። ከነ ነብሱ ወደገደል ተገፍትሮ አልተጨፈጨፈም።በዚህ-ከተማመንን፤አማራው ለምን ለብቻው ጥቃቱ አንዲነገርለት ተፈለገ ብለው ለሚጠይቁን ዜጎች ለምን አንድንጮክለት እንደተፈለገ ግልጽ ይሆንላቸዋል። ከላይ አንደገለጽኩት የዚህ ሕብረተሰብ ጥቃት እና መፍትሔው ምን መሆን እንዳለበት ለመግለጽ በአካል ስላልተገኘሁ በጽሑፍ መዘርዘሩ ቦታ ስለማይበቃ፤ ይህንኑ ገለጻ ለወንድሞቼ በመተው አድማጩን ለማስገንዘብ የምፈልገው ነገር አለኝ የምለው ነገር የሚከተለው አጭር ማስገንዘብያ ነው። ይኸውም፤ ይህ ጉባኤ ለምን በአማራ ጥቃት ላይ ማተኮር አንዳለበት ቅሬታቸውን በማሰማት በግል ‘በቴክስት’ መልእክት እና በስልክ በጉባው ላይ እንዳልሳተፍ በማስጠንቀቅያ መልክ ያስጠነቀቁኝ ወገኖች እና የአማራው ልዩ ጥቃት ሁኔታው መረዳት የተሳናቸው ግብዝ ወገኖች አንዳሉ ለማስገንዘብ እፈልጋለሁ። እነኚህ ግለሰቦች ያልተረዳቸው ሁኔታ ‘አማራው’ ከማንኛውም ኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ተለይቶ“በሻዕቢያ”፤ “በወያኔ” ፤ “በኦነግ”፤ ዓረባዊ ነኝ በሚለው “ኦብነግ” እና በተቃዋሚው ክፍል የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ የዜና ማሰራጫዎች፤በተለይ በውጭ አገር የተቃዋሚውን መልሕቅ የተቆጣጠረው ከኤርትራ ሻዕቢያው ቡድን ጋር የተቆራኘው ግንቦት 7 ብሎ እራሱን የሚጠራው “ጸረ አማራ” ኤሊቱ ክፍል በአማራ ሕብረተሰብ ላይ የአካል እና የስነ ልቦና ስብራት አድረሰውበታል። የተጠቀሱት ክፍሎች በመጽሐፋቸው “ቀጥቅጠውታል” (የአንዳርጋቸው ጽጌ ‘የአማራ ሕዝብ ከየት ወዴት” መጽሐፍ- ልብ ይለዋል)። በጥይት ረሽነውታል። እርጉዝ እናቶች እና እህቶች ከነህይወታቸው ወደ ገድል ተወርውረዋል። ከሚኖሩበት አካባቢ በጉልበት ተገፍተው ንብረታቸው ሳይዙ እና ከቤተሰቦቻቸው እየተነጠሉ ፡ አንዳንዶቹ ከመቅጽበት አንዳንዶቹ ደግሞ በ24 ወይንም በ48 ሰዓት የጊዜ ገበዶቦች ተሰጥቷቸው አንዲባረሩ ተደርጓል። በጥቂት አመታት ልዩነት የሌሎቹ ጎሳዎች የሕዝብ ቁጥር ሲጨምር አማራው ግን 2 ሚሊዮን አማራ ሕብረተስብ ከምድረገጽ መጥፋቱ በእኛ ጥናት ብቻ ሳይሆን በወያኔ ስታትስቲክ ጭምር ወያኔ በፓርላማው አምኖ ገልፆታል። በወጣት እናቶች እና በአዛውንቶች ክብር ላይ ጥቃት ተፈጽሟል። ‘ዓይነስውራን’ ወንዶች አዛውንቶች ‘ብልታቸው’፤እናቶች ደግሞ ‘ጡታቸው’ በቢላዋ ተሰልበዋል። ህፃናት በትምህርት ገበታ ላይ አንዳሉ አንዳይወጡ የየክፍሎቻቸውን መዝግያዎች ተቆልፎባቸው ከነ ነብሳቸው ተቃጥለው እንዲሞቱ እሳት ተለኩሶባቸው አልቀዋል። እናቶች አንዳይወልዱ ማሕጸናቸው አንዲደርቅ መርዝ አንዲወጉ ተደርጓል። አሁንም ጥቃቱ አላባራም። ግብዦቹ ‘ይህንን ጥቃት’ ነው “አታጋልጡ” የሚሉን። በዚህ ጉባኤ ስለ አማራ ጥቃት እና ውረደት ስቃይና መከራ ለሕብረተሰብ መንገር “ጸረ ኢትዮጵያዊነት” ነው እያሉ የአማራው ሕብረተሰብ ጥቃት ተሸፍኖ እንዲቀጥል በማወቅም ባለማወቅም አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ወገኖች አንዳሉ ለመግለጽ እወዳለሁ። በተለይ ለምን አንደዚህ አንደሚሉ ጥቂት ልበል። ስለ አማራ ሕብረተሰብ ጥቃት ማጋለጥ፤መፈትሄ ማፈላለግ ማለት የወያኔ የጐሳ አወቃቀር ፖለቲካ መከተል ነው በማለት “ጐሰኝነት” ነው ይሉታል። ይህ “ጥርቅም” ያለ “ድንቁርና” ለወያኔዎች እና ለመሳሰሉ ለጸረ አማራ ቡድኖች የሚያመቻች ተጨማሪ ጥቃት ነው።እኛ አማራው “ይገንጠል” የራሱ ክልል ይከልል፤ በአካባቢው የሚኖሩ ትግሬዎች፤ኦሮሞዎች፤የደቡብ ሕዝብ ጎሳዎች ከአማራ አከባቢ መሬቶች ይባረሩ፤ ይገደሉ፤ የሚል ቅስቀሳ እና አጀንዳ የለንም። እኛ እና ወያኔ በጎሰኛነት በመወንጀል የሚያያይዙን “ደንቆሮዎች” የዘር ማጥፋት ወንጀሉና ሰበቡ አላጠኑም ወይንም ሆን ብለው የአማራው ጥቃት አንዲቀጥል የመሰሪ ቡድኖች ተላላኪዎች ናቸው ማለት ነው። በጣም የሚገርማችሁ ደግሞ፤ በቴክስት እና በስልክ ያስጠነቀቀኝ ግለሰብ “ዶክተር አስፋ፤ ዳኛ ከተማ ደኔ እና አንተ አቶ ጌታቸው ረዳ፤ ስለ አማራ ሕብረተሰብ ጥቃት ስትናገሩ ‘አማራ’ ወክሎናል የምትሉት የምስክር ወረቀት አሳዩን ማለቱ “በጣም አስገራሚ ድንቁርና ከመሆን አልፎ፤ ስለ ትግሬ ወይንም ስለ ኦሮሞ ጥቃት ስንናገር ወይንም “ታሪክ፤ባሕል፤ ጦርነት፤ፖለቲካ” አንስተን ስንተነትን ይህ አነጋጋር ‘ወያኔዎች’ አንዲሁም ‘ኦነጐች’ ስለ ጎሳችን ‘እኛ’ እንጂ አንናተ አያገባችሁም፤ስለ እኛ ወክለህ ተናገርልን ብሎ የሰጣችሁ ፈቃድ አሳዩን፤ እያሉ በጠባብ ሕሊና የሚንቀዠቀዡት የጠባብ ቡድኖች ቅጂ ቅስቀሳ ነው። ለነገሩ ወያኔም እኮ “ዲያስፖራ ተቃዋሚው ስለ አገር ላለው ሕዘብ መናገር አትችሉም። ውክልና ወረቀት አምጡ እያለ ድንቁርናውን እያስተጋባብን ነው።ታዲያ የኛ የምንላቸው ተቃዋሚዎች ተመሳሳይ ሲጠጥቁን ከወያኔ ድንቁርና በምን ይሻላሉ?፡ ማን ወከላችሁ? ብሎ ለጠየቀኝ ሰው መልሱ ጥቃት የደረሰበት “አማራ ሕብረተሰብ” ስለ እሱ እንድንናገርለት ጥሪ አድርጎልናል።ይህንን የቴፕ ድምፅ ለማስረጃ አንዲደመጥ ልኬአለሁ። 45 ደቂቃ የፈጀ ዝርዘር በኢትዮጵያን ሰማይ አውድዮ ቪድዮ ክፍል ተለጥፎ ዠይገኛል። ድረሱል ያሉንን ጥሪ ግን ባጭሩ ይኼው። እነሆ ከ4 አመት በፊት ጥሪው በጀርመን ራዲዩ ። Active ethnic cleasning in Ethiopia http://youtu.be/aJDyueu2Kek ከተጠቂዎቹ በድምፅ መልእክቱ እንዳዳመጣችሁት፤ መልእክቱ የሚለው “ለሚመለከተው ክፍል እባሃችሁ ስለ እኛ ስም ሆናችሁ አነጋግሩልን አደራ! አደራ! አደራ!” የሚለው የአደራ መልእክት ተንተርሰን ነው እኛም የተጠቂዎቹ አደራ ላለመብላት እዚሁ እየተነጋገርን ያለብበት እና ያስገደደን ምክንያት። ስለዚህ ስለ አማራው ሕብረተሰብ እንደትናገሩ ማን ወከላችሁ? የውክልና የፈቃድ ወረቀት አሳዩን በማለት የሚዘላብዱ እና ስለ አማራ ሕብረተሰብ እናቶች እና አባቶች ጥቃት ‘ትንፍሽ’ አትበሉ የሚሉን “ጥርቅም” ያሉ “ደናቁርት” -የአጥቂዎቹ ተባባሪዎች ከመሆናቸውበፊት ልቦና አንዲገዙ አጋጣሚውን ተጠቅሜ ልመክራቸው እፈልጋለሁ ። በዚህ አጋጣሚ በተጓዝኩበት አካባቢ አመች ሆኖ ካገኘሁት ከናንተው ጋር ለመቀላቀል እሞክራለሁ፡ ካልሆነልኝ ግን ባለመገኘቴ እያዘንኩ፤ የዚህ ሕብረተሰብ ጥቃት ተጠንቶ አጥቂዎቹ ወደ ሕግ የሚቀርቡበት ሁኔታ ማመቻቸት አስፈላጊ መሆኑን የተጠቂዎቹ ልሳን አደራ ብሎናል እና በርቱ። የአማራው ሕብረተሰብ ጥቃት ሰሚ ጀሮ አንዳያገኝ የሚጥሩ ሁሉ እናወግዘለን። የአማራ እናቶች ማህፀን ቢመክንም ከአጥቂዎቹ እጅ ያማለጣችሁ የአማራ ተወላጆች ሁሉ የእናቶቻችሁ እና እህቶቻችሁ ትኩስ እምባ እንዲቆም የማድረግ ሃላፊነት በናንተው በአማራዎች ብቻ ሳይሆን በሌሎች ኢትዮጵያዊያንም ዘንድ የዜግነት ግዳታ አንዲወጡ ጥሬየን አቀርባለሁ። በዚህ አጋጣሚ ከአማራ ሕብረተሰብ የተወለዱ ውጭ አገር እና ውስጥ አገር የሚኖሩ የሕግ ጠበቆች በየድረገጹ የሚያቀርቧቸው ሳምንታዊ/ወርሃዊ “የፖለቲካ ጅላጅል ትንተናቸውን” አቁመው የወላጆቻቸው እና የእህቶቻቸውን የድረሱልን ጥሪ “ኢትዮጵያዊያን ኦጋዴን ሶማሌ ተቃዋሚዎች” እያደረገት አንዳደሉት ሁሉ እናንተም የወላጆቻችሁ እና የእህቶቻችሁን አምባ ማድረቅ እና ወንጀለኞቹን ወደ ሕግ ማቅረብ ሃላፊነት ከናንተው ይጠበቃል።ይህ የክህደት ዘመን በመንደላቀቅ እና በምቾት ኑሮ በውጭም በውስጥም አገር ጆሮውን ደፍኖ ሰምቶ አንዳልሰማ ያጠረመመው ‘አማራው ልሂቅም ’ ሆነ በግንቦት 7 ስም ከኤርትራው ቡድን ጋር ትከሻ ለትከሻ እየተሻሸ ያለው አማራው ሊሂቅ እና ተከታየቹ ብቻ ሳይሆኑ ይህንን ጐሳ ያጠቁትና በመጽሀፍቶቻቸው እና በሕዝባዊ ንግግራቸው የዘለፉት እና የከዱት፦ የንጉሥ ተፈሪ የልጅ ልጆች ነን የሚሉን ውጭ አገር እና በውስጥ አገር የሚኖሩ መሳፍንቶች እና ልዑላኖች አማራን እያጠቃ ካለው የወያኔ ቡድን እና መሪያቸው ጋር በመተባባር አሳፋሪ የሆኑ የክህድት ተግባሮች ፈጽመዋል። ለመግለጽ የፈለግኩት ጥንቃቄ የጎደለበት በውጭ አገር የስለላ መረቦች እየታገዘ የፖለቲካ ቁማር እየተጫወተ ያለው ያለው የምሁሩ ክፍል ብቻ ሳይሆን የንጉሱ የልጅ ልጆች ሳይቀሩ ስለ አማራ ጥቃት ከመጤፍ ያለመቁጠራቸው አንዱ አሳዛኝ እና መራራ ያደረገው ገጽታው ስታዘብ ሃዘኔ እጅግ የበረታ ያደረገዋል። ይህ የክህደት ዘመን ስትመለከቱ “ለአማራው” ማን ያልቅስ? ስለ አማራው ጥቃት አንድትነጋገሩ “በስሜ አንድትነገሉኝ ወክያችሗለሁ ብሎ የሰጣችሁ የምስክር ወረቀት ውክልና አሳዩን” የሚሉ ተቃዋሚ ነን የሚሉን የአማራ ተወላጆችም ሆኑእንዲሁም “አማራ ብቻ ስለ አማራ ቢናገር ያምርበታል፡ትግሬ የሆናችሁ ተቃዋሚዎች በዚህ ላይ አያምርባችሁም” የሚሉን የወያኔ ሰዎች እና ተቃዋሚዎች ጉባው እንዲነጋገርበት አሳስባለሁ። ስለ አማራው ጥቃት መነጋጋር ማለት ስለ ኢትዮጵያ ጥቃት መነጋጋር አይደለም ወይ? ስለ አማራው ጥቃት እና አንዴት ይቁም የሚለው መነጋጋር እንዴት “ጐሰኝነት” ነው ያስብላል? ስለ አማራ ጥቃት መቆርቆር በአገር በታኝነት የሚከሱን ወገኖች ሁሉ ካለው ከባድ ቅሬታዬ ተጨማሪ ሆኖ እጅግ አክብደውታል።የሕብረሰተቡም ግፍ አንዲቀጥል ተጨማሪ ጫና ሆነውታል። ይህ ማሳሰቢያ ባጭሩ ጉባኤው እንዲነጋገርበት ይህ መልእክት እያሳለፍኩ ፡ ጉባኤው አንዲሳካ ምኞቴ ነው።ትግሉ ረዢም እና መራራ ቢሆንም፤ በመጨረሻ ግን የተጠቃው ሕዝብ ባሸናፊነት በድል ተራራ ላይ ቆሞ የተነጠቀው ክብሩን እና ሰንደቃላማው እንደገና ያውለበልባል። አመሰግናለሁ። አቶ ጌታቸው ረዳ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment