Tuesday, 10 December 2013
2007 የምርጫ ቁማር ይብቃ!!
***ምርጫ***
2007 የምርጫ ቁማር ይብቃ!!
የህውሃት ልሳን የሆነው ሬዲዮ ፋና የወሬ ዱለታ ይብቃ ለማለት ነው ይህችን ጹሁፍ ጫር ያደረኩት
ጠቅላይ ተብዬው ሀይለማሪያም እርሳቸውም እንደ ማህረቤን ያያችሁ ጨዋታ ዙሪያውን ተሽከርክረው ተሽከርክረው “እኛ ምስል ባናሳይም ድምፅ ባናሰማም ህዝባችን ያምነናል ውጪ ሀገር ያለው ህዝብ ነው የማያምነው እርሱ ደግሞ የራሱ ጉዳይ” ብለዋል።
እውነትም ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው።
ለምሳሌ በ97 ቱ ምርጫ የምርጫውን ውጤት ተቀብሎ “ላጥ” ይላል ብለን አምነን ነበር። ግን አልታመነም በጥይት አሳመመን እንጂ… አሁንም ለምሳሌ በ2002 ቱ ምርጫ ፍትሀዊ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ያደርጋል ብለን አምነነው ነበር ነገር ግን በተቃራኒው ሆነ ታመምንም። አሁንም ለምሳሌ የዛሬ ሃያ አመት ከአስር አመት በኋላ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በቀን ሶስቴ ይበላል ተብለን አምነነን ነበር። ነገር ግን ከሃያ አመት በኋላ እንኳን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በርሃብ እንደተጠቁ ከራሱ የመንግስት ሚዲያ ሰምተን ታመናል።
ደግሞ ካሁኑ ዱለታው 2007 ምርጫ
አዎን አውቃለሁ፣ የምን ምርጫ ነው ትሉ ይሆናል፡ ይህም የኔም ጥያቄ ነው የእናንተ ብቻ ሳይሆን። የህውሃት/ወያኔ አገዛዝ እስካለ ድረስ በኢትዮጵያ ዳግም ትክክለኛ የሆነ ምርጫ ሊደረግ እንደማይችልና እንደማይኖር ብዙዎች የተነበዩት ነው። የሕዝብን ድምፅ አክብሮ በተሸናፊነት አምኖ ወያኔ ሥልጣኑን የመልቀቁ ጉዳይ ያከተመለት ይመስላል። ይህም ቀድሞ የተደረጉትን ወከባዎች፣ ግለሰቦችን ማስፈራራትን እና መድብደብን፣ ያልሆነ ምክንያት በመደርደር መወንጀልና በእስር ማንገላታቱን ሳንጨምር፣ ሰሞኑን የተቃዋሚ ፓርቲ በሚካሄደው ሴራና ድብደባ እስሩ የወያኔ ካድሬዎችና ጀሌዎቻቸው የፈጸሙት አሳፋሪ ተግባር ሐገራችን በምን አይነት ራሳቸውን መንግሥት ነን በሚሉ ተራ ግለሰቦች እየተመራች መሆኑን ነው የሚያሳየን። በእርግጥ የሰውን ሕይወት ለማጥፋት በጭራሽ ወደ ሗላ የማይል የወያኔ አስተዳደር ይህንን ተግባር ለመፈጸም ቢነሳሳ የሚያስገርም አይሆንም።
ወያኔ በ1997ቱ ምርጫ ባላወቀውና ባልተገነዘበው ሁኔታ በዋነኛነት ደግሞ ለምእራባውያን ጌቶቹ ታማኝነቱን ለማሳየት ሲል ብቻ በኢትዮጵያ ዲሞክራሲ አለ ተብሎ እንዲነገርለትና በሌላም በኩል ሕዝብን ሊያስተባበር የሚችል ጠንካራ ተቃዋሚ ስለሌለ ድሉ የኔ ነው በሚል የተሳሳተ ስሌት ተነሳስቶ ጥሩ ምርጫ እንዲደረግ እድሉን ከፍቶ ነበር። ይህም በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ መሆኑ ማንም የሚክደው አይደለም። በሰጠው እድል ተቃዋሚዎችም በሚገባ ተጠቅመውበት በምርጫውለት ድሉ ወደ ተቃዋሚዎች በመዞሩ ምን ያህል መደናገጡን፣ ተደናግጦም የፈጸመውን አስጸያፊ ድርጊት አለም በሙሉ ያየው እና የተረዳው ነው፡ ለዚህም የመርማሪ ኮሚሽኑ ሪፖርት በአቢይነት ሊጠቀስ የሚችል ምስክር ነው።
እንግዲህ ከዚህ በሗላ ነው ድጋሚ ስህተትን ላለመፍጠርና ያ በዲሞክራሲ ተሸፍኖ የነበረው የወያኔ የአውሬ መልኩ አንዴ መጋለጡ ከታወቀ ወያኔ ስልጣኑን በምንም አይነት መንገድ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንደማይለቅ ማሳወቅ የጀመረው። ይኸውም ከምርጫ 97 ጀምሮ ተቃዋሚዎችን ከማሰር፣ ማስፈራራትና ሕዝብን ወጥተው እንዳያስተባብሩ፣ ጽሕፈት ቤቶችን የመክፈት ሥራቸውን አድካሚና አሰልቺ በማድረግ፣ የተከፈቱትንም ጽሕፈት ቤቶች የተለያዩ ምክንያቶችን በመፈብረክ እንዲዘጉ የማድረግ ተግባራትን በመፈጸም ፣ሰብአዊ መብትን የሚገፍ አዳዲስ ሕጎችን በማውጣት፣ የሕዝብን የቁጣ ትኩሳት በመጨመር ላይ ይገኛል።
ከምርጫ 97 በሗላ በሰላማዊ መንገድ ታግሎና በምርጫ አሸንፎ ወያኔን ከሥልጣን የማስወገዱ መንገድ ሙሉ በሙሉ መዘጋቱን በማመን ተስፋው የተሟጠጠ መሆኑን ቀድመው የተረዱ የቀድሞ ተቃዋሚዎች ገሚሶቹ ሰላማዊ ትግል አያዋጣም በማለት በሌሎች በሚያዋጡን መንገዶች ሁሉ እንታገላለን በማለት ትግል ስልታቸውን ቀይረው የተነሱ አሉ። ገሚሶቹ ደግሞ በፍርሃትም ይሁን ለሆዳቸው በማደር ተለጣፊ ፓርቲዎቻቸውን ከወያኔ አሰጠግተው በስመ ተቃዋሚ ሕዝብን ክደውና ንቀው ለወያኔ ፍርፋሪ በማደር በሐገሪቱ ዲሞክራሲ አለ እንዲባል በማስመሰል ፓርላማ ውስጥ ተሰግስገው ሊቀመጡ እራሳቸውን ከአውሬው አስተካክለዋል።
ከዚሁ ከምርጫ 97 በሗላም በሺሕና በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች በተለያዩ የሐገሪቱ ክፍል እስር ቤቶች ታምቀው ይገኛሉ። ከነዚህም ውስጥ የአንድነትን ፓርቲ ለማዳከምና የሚያደርገውን ሰላማዊ ትግል ለመግታት ታስቦበትና ተጠንቶበት የተደረገው የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ወደ ቃሊቲ መወርወር በእውነት የፖለቲካ ምሕዳሩ ምን ያህል እንደጠበበ እና ሰላማዊው ትግል እንደሞተ የሚያሳይ ጥሩ ምስክር ሊሆን የሚችል ሲሆን፣ ከአሁን በሗላም በቀረችው ግዜ ተቀይረው ወያኔ ለሰላም እና ለዲሞክራሲ ተገዝቶ እንከንየለሽ የሆነ ምርጫ ይደረጋል ማለት የማይታለም ነው።
ህውሃት/ወያኔ አሁንም ስለምርጫው በሰፊው በማውራት ላይ ይገኛል፡ ሕዝብን በእህልና በምግብ አቅርቦት፡ በሥራ እድልና በመሳሰሉት እንደ ቀብድ በማስያዝ፡ በፓርቲው ስር ካልታቀፉ በሐገሪቱ ውስጥ ሊያገኟቸውና ሊጠቀሙባቸው የሚገባቸውን ሰብዓዊ መብቶች በመግፈፍ በውዴታ ሳይሆን በግዴታ የፓርቲውን የአባልነት ፎርም በማስሞላት ላይ ይገኛል። በቀደመው ምርጫ ድምጻቸውን ለተቃዋሚዎች የሰጡትን ግለሰቦች ከስራቸው እንዲባረሩ ወይም ሐገር ለቀው እንዲወጡ ለመጪውም ምርጫ እንቅፋት የማይሆኑበትን መንገድ በመቀየስ አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል፡ ለማንኛውም ባለፈው የክልል ምርጫዎች እንደተደረገው አሁንም ምርጫው የሚካሄደው ወያኔ ከራሱ ከወያኔ ጋር ይሆናል እንጂ በዚህ ሁካታና የመብት መጣስ በሰፊው በተንሰራፋበት ሁኔታ ጠንካራ ተቃዋሚ ገብቶ ሥነሥርዓት ባለው ሁኔታ ምርጫ ይካሄዳል ማለት ፈጽሞ የማይታሰብ ነው። ለዚህም ነው 2002 ምርጫ ሲሉን የምን ምርጫ የሚለው ጥያቄ ሲያስተጋባ የምንሰማው። እውነት ግን የምን ምርጫ ከአሁን በኋላ?
ከሰብኣዊ
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment