Sunday, 17 November 2013
ወያኔ የግንቦት ሰባት መሪዎችን ለመግደል ያሰሬዉ ሴራ በመክሸፉ የኢትዮጵያ ህዝብ ደስተዉን እየገለጸ ነዉ
በወያኔው መረጃና ደህንነት ሃለፊ ጌታቸው አሰፋ እና በሃይለማሪያም ደሳለኝ
አማካሪ ጸጋየ በርሄ ቁጥጥር የተመራና በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌና በግንቦት7
ህዝባዊ ሀይል መሪዎች ላይ የተቀነባበረው የግድያ ሙከራ መክሸፉን ተከትሎ
ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ከሚገመተው በላይ ሰርጎ ገቦችን ለመከላከል የሚያስችል
የሰውም ሆነ የቴክኖሎጂ አቅም ያለው መሆኑን አስመስክሯል የሚሉ
ተበራክተዋል። ይህን ሃሳብ የሚደግፉ ወገኖች ባንድ በኩል የፋሽስት ወያኔ
አመራሮች ምንም እንኳ ከፍተኛ የስልጣን እርከን ላይ ነው ያለነው ቢሉም ምን
ያህል የተዋረደና የቀለለ ስራ ለመስራት እንደሚደፍሩ በግልጽ በራሳቸው አንደበት
የሰማንበትና ያወቅንበት ነው ሲሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል
ራሱን ለመከላከል የሚያስችለውን ቴክኖሎጂያዊ አቅም መገንባቱንና ይህም
ለሀገራችንና ነጻነት ለጠማው ሕዝባችን ታላቅ ተስፋ ሰጭ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
ሌሎች በጉዳዩ የተደሰቱ ወገኖች ደግሞ ፋሽስት ወያኔ ከዚህ በፊትም ለገንዘብና
ለስልጣን የሚጓጋጉ ለሕዝብ ልእልና ደንታ የሌላቸው እና ለማይገኝ ባዶ ምኞት
የሞቱ ሆዳሞችን በመግዛት ስንት የሕዝብ ተሰፋ እንቅስቃሴዎችን እንዳደናቀፉ
አስታውሰው ይህ ግን ልዩ ነበር ካሉ በሗላ ወያኔዎች የት ደረጃ ላይ እንዳሉና
አቅማቸውም እስከምን ድረስ እንደሆነ አወቅንበት ይላሉ። ከዚህ በፊት በተለይ
በ1997 ዓ/ም የነበረውን ምርጫ ቅንጅት ቢያሸንፍም ፋሽስት ወያኔ ገልብጦ ሁሉን
ለራሱ በማድረግ እንዲጫወት እገዛ ያደረጉለት የሕዝብ ወገን ነን እያሉ በመደለል
በሆዳቸውና በሌሎች ጥቅማጥቅሞች የተገዙ ከሃዲዎች እንደነበሩ አይዘነጋም። source ginbot7.org
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment