Friday, 22 November 2013
23 ዓመት የተገነባ የበደል ውጤት ።
ወያኔ ኢትዬጵያዊነትን ትርጉም ኣልባ ለማድረግ ገና ከመነሻው፣ ከጥንስሱ አስከዛሬዋ ቀን ድረስ የክፋትን ድር ኣያደራ ፣የሚፈራውን አያስፈራራ፣አያሰረ፣አየገደለ፣አያሳደደ ወዘተ ዜጎች በሀገራቸው ላይ ባሪያ ሆነወ አንዲኖሩ አያፈነ ኢትዬፒያዊ ጀግንነት እና የኢትዬጵያን ክብር የትላነት ታሪከ አነዲሆነ አየጣረ ነው ። ዛሬ ዛሬ ኢትዬጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር የሚለውን ኣባባል ስሰማ ውሰጤ ትልቅ ጥያቄ ይፈጠራል አውነት ዛሬ ሀገራችን ከነክብርዋ ኣለች ? ኣባቶች ወኔኣቸው ጠፍቶ ለዝምታ አጅ ከሰጡ ፣ አናቶች ፍት ህ በማጣት ኣንገታቸውን ከደፉ ፣ ኣህቶች የሴትነት ክብራቸው ተገፎ ለኣረብ መጫወቻነት ከተሸጡ ፣ ኣንድ ትውልድ አውነት ሳይሰማ ካድገ ፣ገበሬው ማረሻው ተነጥቆ አጆቹ ለልመና ከተዘረጉ የኢትዮጵያን ክብር የምናየው ማን ላይ ነው ፣ዘላለማዊት ኢትዮጵያን የምንመኘው ለየትኛው ትውልድ ነው ?
በወያኔ የኣገዛዘ ዘመን ሀገራችን ላይ ችግሮች መልካቸውን አየቅያየሩ ህዝቡን ሲደቁሱት ኖረዋል ዛሬም አያየነው ነው ።
የዘረ ማጥፋት ወንጀል፣
ዜጎች በኣደባባይ በግፍ መገደል፣
የተቃዋሚ ፓርቲ ኣባላት ፣ደጋፊዎቻቸው አና ጋዜጠኞች ያለፍት ህ መታሰር ፣
ነዋሪዎች ከቀዬኣቸው መፈናቀል.... ወዘተ ። አነዚህ አና የመሳሰሉ ሀገራችን ላይ የሚፈጸሙት ግፎች ሰሞነኛ ወሬ ሆነው ሳይፈቱ አስከዛሬ ኣሉ ፣ዛሬም ወገኖቻችን ላይ በኣረብ ሀገራት አየደረሰ ያለው ስቃይ አና አንግልት ወያኔ ለዜጎች አና ለሀገራችን ያለው ንቅት የወለደው ነው (ባለቤት የናቀው ኣሞሌ........ ) አንዲሉ ኢትዮጵያዊነት አንደወንል የሚቅጠርበት ጊዜ ላይ ደርሰን ወገኖቻችን የወያኔን የግፍ ጅራፍ ሸሽተው በተሰደዱ በባአደ ሀገራት አስር ቤት ታጉረው ፣ በየኣደባባዩ ሬሳቸው ወድቆ ደማቸው ደመከለብ ሆኖዋል ።
በወያኔ ኣገዛዝ የሰረኣቱ ዋነኛ ተጎጂ የሆኑት ሴቶች ናቸው ። በ1000 የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ለጉለበት ስራ በህገወጥ መንገድ ወደኣረብ ሀገራት ይሰደዳሉ ፣ በሀገራቸው ሰርተው መለወጥ አንዳይችሉ በመንገስት ኣካላት የሚደርሰባቸው የሰባዊ መብተ ረገጣ መፍትሄ ማጣት አና የጭቆናው ምሬት ስደት ብቻኛ ምርጫቸው አንዲሆን ያስገድ ዳቸዋል ። አብዛኞቹ ኣድሜኣቸው ከ18 በታች የሆኑ ህጻናት ከኣቅም በላይ በሆነ ያጉልበት ስራ በቀን ከ 18 ሰዓት በላይ አንዲሰሩ ይገደዳሉ ፣በኣሰሪዎቻቸው በተደጋጋሚ ይደፈራሉ፣ ይደበደባሉ ይገደላሉ ፤ የሚደርስባቸው ስቃይ ከኣቅማቸው በላይ የሆነባቸው ብዙዎች ለኣይምሮ ችግር ተዳርገው በየጎዳናው ወድቀዋል ፤ ሰሚ ያጡ ዋይታዎች ፣ድብደባ መቛቛም ያቃታቸው ፣ በመደፈር ብዛት የደከሙ የጨቅላ ገላዎች ፣ በደል የበዛባቸው ብዙ አህቶች አራሳቸውን ከፎቅ በመወርወር ፣ መርዝ በመጠጣት ፣ በመታነቅ ሂወታቸውን ያጠፋሉ።
ይህ ሁሉ የአንድ ቀን ምሬት ፣የ አንድ ሰሞን ብስጭት የፈጠረው አይደለም 23 ዓመት የተገነባ የበደል ውጤት ነው ።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment