Saturday, 30 November 2013

“ዜጐች የተሰደዱት መንግስት የሥራ ዕድል ባለመፍጠሩ ነው”

መንግስት ከሣውዲ የሚመለሱ ዜጐች ቁጥር አስቀድሞ ከተገመተው በላይ መሆኑን ገልጿል። ቀድሞ የተመላሾቹ ቁጥር 28 ሺህ እንደሚሆን ቢገመትም አሁን ወደ 80ሺህ እንደሚደርስ ተነግሯል፡፡ በስደተኞቹ ላይ እየደረሰ ያለውን እንግልት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፤ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ከማውገዝ አልተቆጠቡም፡፡ ጉዳዩ በሰከነና የዲፕሎማሲ መርሁ በሚፈቅደው መንገድ መያዙንም ገልፀዋል፡፡ መንግስት ከዚህ በላይ በዲፕሎማሲው ርቆ ሊሄድባቸው የሚችልበት አማራጮች እንደሌሉ የሠሞኑ መግለጫዎቹ ያመለክታሉ፡፡ ይሁን እንጂ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሣይንስ ምሁሩ ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ መንግስት የዜጐቹን መብት በማስከበርም ሆነ የሃገርን ክብር በማስጠበቅ ረገድ ምንም አልተራመደም ይላሉ – ተመላሾቹን ከመቀበል የዘለለ ዲፕሎማሲያዊ እርምጃዎች መውሰድ አለመቻሉን በመግለፅ፡፡ ዶ/ር መረራ ጉዲና በጉዳዩ ዙሪያ የሰጡንን አጭር ማብራሪያ እነሆ:- በሣውዲ አረቢያ በዜጐቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ተከትሎ መንግስት ጉዳዩን የያዘበትን መንገድ እንዴት ገመገሙት? ሁለት ሶስት ነገሮች አሉ፡፡ አንደኛው አሜሪካ፣ ጀርመን፣ ስዊድን በመሳሰሉት ሃገሮች ያሉ ኢትዮጵያውያን በሣውዲ አረቢያ ላይ ተቃውሞ ሲያሰሙ እየፈቀዱላቸው፣ እዚህ መከልከሉ በዜጐች ላይ ተጨማሪ ወንጀል መስራት ነው፡፡ ሁለተኛው በተለያየ መንገድ እየሰማን እንዳለው አሁንም ቢሆን በ40ሺህ የሚቆጠሩ ዜጐች እየተንገላቱ ነው፡፡ እሪታና የይድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ የሚያወራው ሌላ ነው፡፡ መደብኩ እንኳን ያለው 50 ሚሊየን ብር አንድ እነሱ “የመንግስት ሌባ” የሚሉት የሚሠርቀው እኮ ነው። 50 ሚሊየን ብር ለ70ሺህ ሰው ነው የመደቡት። ነገር ግን በሙስና የተከሰሱት ሰዎቻቸው እኮ የዚያን ሶስት እጥፍ ሰርቀዋል ተብሏል፡፡ በእውነቱ የተመደበው ገንዘብ በጣም ትንሽ ነው፡፡ ሌላው ደጋግመው የሚያሰሙት፤ የሣውዲ አረቢያ መንግስትን ድርጊት የሚኮንን ሳይሆን ወዳጅነት እንዳይበላሽ ትልቅ ስጋት ያላቸው የሚያስመስላቸው ነው፡፡ ከዜጐች ድብደባ፣ ግድያና እንግልት ይልቅ የሣውዲ መንግስት ፍቅር የያዛቸው ነው የሚመስለው፡፡ ስለዚህ በሚፈለገው መንገድ ለጉዳዩ ምላሽ እየሰጡ አይደለም የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡ ድሮውንም ቢሆን እነዚህ ዜጐች የተሰደዱት የኢትዮጵያ መንግስት የስራ እድል መፍጠር ባለመቻሉ ነው፡፡ ሃገሪቷን የስደት ሃገር ያደረገው ራሱ መንግስት ነው፡፡ በሃላፊነትም ያስጠይቀዋል፡፡ ስለዚህ መንግስት በቀን ይሄን ያህል ሰው መለስኩ ከሚል፣ በመሠረታዊነት ዜጐች የማይሰደዱባት ሃገር መፍጠር አለበት፡፡ የስራ እድል ሊኖርና የሰብአዊ መብት ሊከበር ይገባል፡፡ መንግስት በዜጐቹ ላይ ለተፈፀመው ግፍ፣ በአለማቀፍ ፖለቲካዊ ዲፕሎማሲው ምን ድረስ ነው ሊሟገት የሚችለው? መንግስት እኮ ደጋግሞ የሚነግረን በህገወጥ መንገድ ከሃገር የወጡ ናቸው እያለ ነው፡፡ እንኳን በዚህ ዘመን ቀርቶ በጥንት ዘመንም ስደተኞች ክብር አላቸው፡፡ ዝም ብሎ ይገደሉ፣ ይፈለጡ፣ ይቆረጡ አይባልም፡፡ ስለዚህ ሣውዲ አረቢያ ኋላቀር በሆነ መንገድ ዜጐቻችንን ስታንገላታ በህግ መክሰስም ይቻላል፡፡ ሌላ አማራጭ ከተፈለገም እንደወዳጅ መንግስትና የንግድ ሸሪክ ብዙ ተጽእኖ ማድረግ ይቻላል፡፡ ይልቁንስ የኢትዮጵያ መንግስት እያየ ያለው፣ እዚህ ያሉ ተቃዋሚዎች ምን አሉ የሚለውን ብቻ ነው፡፡ ተቃዋሚዎች ከሰሱን፣ አጣጣሉን የሚለው ላይ ነው ያተኮረው፡፡ ከዚያም ሲያልፍ ሌት ተቀን እንደ መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረን ዜጐቹ በህገወጥ መንገድ መሄዳቸውን ነው፡፡ ዋናው ጉዳይ መጀመሪያ የዜጐችን ነፍስ ማዳን ነው፤ ሌላው ደግሞ ለስደት የዳረገንን የኢኮኖሚ ችግር በመፍታት፣ ኢትዮጵያን ከስደት ሀገርነት ዝርዝር ለማውጣት መንቀሳቀስ አለበት፡፡ ግን አሁን ባለው ሁኔታ የዚህ አዝማሚያ እምብዛም እየታየ አይደለም፡፡ መንግስት በሣውዲ አረቢያ ላይ ይከተል የነበረውን የዲፕሎማሲ አቅጣጫ ለመፈተሽና ለመቀየር የእነዚህ ዜጐች እንግልት ምክንያት ሊሆን ይችላል ብለው ያስባሉ? አሁን እኮ መንግስት ጠንከር ያለ መግለጫ እንኳ አላወጣም፡፡ በመኮነን ደረጃ እንኳ ደፍሮ መግለጫ ማውጣት አልቻለም፡፡ ሌሎች ሀገሮች እኮ ቢያንስ በዜጐቻቸው ላይ በደል ሲፈፀም በመንግስት ደረጃ የመረረ ጩኸት ያሰማሉ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ግን ከህዝቡ ጋር አብሮ ሊጮህ ቀርቶ፣ የህዝቡንም ድምጽ እያፈነ ነው፡፡ ለዚህ ነው በተለይ በፖለቲካ ዲፕሎማሲው በኩል እየተወሰደ ያለው እርምጃ በቂ አይደለም የምለው፡፡ መንግስት ዜጐቹን ከሃገሪቱ ከማስወጣት ባለፈ እርምጃ ያልወሰደው የኢኮኖሚ ጥገኝነት ጉዳይ ስላለ ነው፤ የኢትዮጵያ ዋነኛዋ የውጪ ንግድ ሸሪክ ሣውዲ በመሆኗ ነው የሚሉ አስተያየቶችንስ እንዴት ያዩዋቸዋል? በእርግጥ የኢኮኖሚ ጥገኝነቱ አለ፡፡ እናውቃለን። ታላላቅ የሣውዲ አረቢያ ከበርቴዎች በዚህች አገር ኢንቨስት ያደርጋሉ፡፡ ነገር ግን ለኢኮኖሚ ሲባል የዜጐችን መብትና ብሔራዊ ጥቅምን አሣልፎ መስጠት በየትኛውም የፖለቲካ አማራጭ ፈጽሞ አይመከርም፡፡ ከምንም በላይ የዜጐች መብትና የሃገር ክብር ይቀድማል፡፡ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሰው እየተንገላታ ለኢኮኖሚ ጥገኝነቱ ሲባል ዝምታን መምረጥ እንዲሁም የዜጐችን ጩኸት ወደማፈኑ መሄድ ተገቢ አይደለም፡፡ አንድ መንግስት በሌላ ሀገር የሚኖሩ ዜጐቹን መብት ለማስከበር ከአለማቀፍ ህግና ፖለቲካ ተመክሮ አንፃር ምን ያህል ርቀት ነው ሊጓዝ የሚችለው? ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ጨርሶ እስከማቋረጥ ይደርሳል፡፡ ከዲፕሎማሲ ግንኙነት ማቋረጥ ባለፈም ችግሩን ለአለማቀፉ ህብረተሰብ በጩኸት ማሰማትም ይገባል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ግን አፉን ሞልቶ ‘በዜጐቻችን ላይ እየተሰራ ያለውን ግፍ እንኮንናለን’ ለማለት እንኳ እየጨነቀው ነው፡፡ እዚህ ያለውን ኤምባሲ እንኳ ሲያነጋግሩ፣ ዋናውን አምባሳደር አይደለም፡፡ በሰለጠኑትን ሃገሮች ደረጃ ቢሆን በ30ሺህ፣ 60ሺህ የሚቆጠሩ ዜጐች እንዲህ ያለ እንግልት ሲደርስባቸው ቀላል ጉዳይ አድርገው አይመለከቱትም፡፡ የህንድ፣ የፊሊፒንስ እና የሌሎች ሃገሮች ዜጐች ከኢትዮጵያውያኑ በተለየ ክብራቸው ተጠብቆ ነው ከሃገር የወጡት፡፡ ይሄ ለምን ሆነ ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡ የስደተኞቹ ስቃይ ለፖለቲካ መጠቀሚያነት እንዳይውል መንግስት ጠይቋል፡፡ በእርግጥ ለፖለቲካ መጠቀሚያነት ውሏል? የኢትዮጵያ ዜጐች በያሉበት ብሶት እያሰሙ ነው። በተለያዩ መንገዶች በየሃገራቱ በኢትዮጵያውያኑ ላይ የሚፈፀሙት በደሎች ሲሰሙ ይዘገንናሉ፡፡ እኛ እኮ እየጠየቅን ያለነው የእነዚህ ኢትዮጵያውያንን መብት ነው፡፡ ነገር ግን መንግስት ጉዳዩን በሌላ እየተረጐመው እኮ ነው የተቸገረው፡፡ Source-adissadmas.com

Friday, 29 November 2013

ADDIS STANDARD’S EXCLUSIVE INTERVIEW WITH ANA GOMES

Ana Gomes is coordinator and spokesperson of the foreign affairs committee for her political group, the Social-Democrat. With 200 members the Social-Democrat is the second largest group within the European Parliament. For Ethiopia and Ethiopians though Ana Gomes is best remembered for her role as the leader of the EU election observers’ team during the 2005 crisis-induced general election in Ethiopia. She has had a troubled relationship with Ethiopia’s late Prime Minister Meles Zenawi, who she still calls “a dictator,” after she published her report in which wrote the election was massively rigged. Eight years later, Ana Gomes came to Ethiopia to participate in the just concluded 26th ACP-EU parliamentary meeting. Her arrival in Addis Ababa caught many, who thought she would never be allowed to set foot in Ethiopia, by a surprise. Addis Standard’s deputy-editor-in-chief Tesfaye Ejigu met Ana Gomes during the meeting and held an exclusive interview. Excerpts: AS - Your question to the development commissioner Andris Piebalgs was on Ethio-Djibouti road project funded by the EU. The commissioner replied EU no longer funds road projects in Ethiopia because construction work is given to companies without auction or given to friendly companies. What happened to the Ethio-Djibouti road project at the end? Ana- Gomes - I don’t know if it was the auction. I raised the issue because some very concerned European friends told me about that because there is a lot of money from the European taxpayers which was supposed to be directed to development that was diverted. I only talked about the road. But I just confirmed with the EU commission representative that it’s indeed two contracts; one, a railway between Addis Ababa and Djibouti; the EU funding was around 45 million Euros, and two, 50 water tunnels project, by the same company worth 20 million Euros. The company was an Italian company called CONSTAT. That company adds Ethiopian Contractors/subcontractors. Obviously it was chosen by the ministry of finance with EU agreement. It’s a project that has gone very wrong because nothing has been achieved, and the money has been deviated. EU has started investigation, arbitration is going on; it also involved your government. And support has been cancelled. They are apparently trying to recover the money from the company. But the money has gone, so the investigation goes on. I was promised for the details by the European commission. It doesn’t mention road. It’s a bit weird however that the EU development commissioner mentioned road construction. And the EU signing new agreement to fund road projects in Ethiopia is contradictory. I think it’s important to clarify all these contradictions for the sake of taxpayers in Europe and also for the Ethiopian people. I am heartened by the fact that PM Hailemariam [Desalegn] has started taking measures even against the high officials who are involved in corruption. So I have to find out. In fighting corruption the main element is transparency. So this element has to be put out for the people to know. There are some things to be checked.qoute2 AS - EU funded hydropower project-Gilgel gibe 3 was given without auction to Salini Construction, an Italian company. A few months after it went operational part of it caved in and was closed. The EU criticized openly the handing out of the construction without auction. But it didn’t decide not to fund hydropower projects. Ana Gomes - I am very interested to learn about that. I need to note down that information. I will find out about it and ask the EU. I am glad you asked this. I have not been able to follow in detail all this development processes because I was not in the EU development committee. AS - ACP-EU joint parliamentary assembly has democratic agenda. The speaker of the house of people’s representative of Ethiopia Abadula Gemeda said, “we have achieved a lot in building democracy, peace and good governance.” Do you buy that? Do you think a lot has been achieve? Ana Gomes - No! In many respect I see a lot of the old ways. Meles was an expert in using jargons such as good governance, the rule of law, democracy, sustainable development, but in practice doing just the opposite. It was a smart leadership which uses politically correct languages for Europeans and Americans consumption. But the practice was really oppressive. What I saw during Meles Zenawi was a dictatorship. I have lived in dictatorship in my own country. I believe this persists in the mind set of many authorities. But at the same time, I realize there is indeed some opening, some realization [that] Ethiopia can’t continue this way. Ethiopia needs change. Even some of the people who have that politically correct speech that everything has been achieved in Ethiopia in public, in private conversation with me they acknowledged that Ethiopia needs change, and that it is the time to really promote important, drastic changes. In that sense I welcome the move that the PM Hailemariam has initiated the prosecution of high officials, even a minister charged with corruption. I hope this will be the first step in the right direction. At the debate we were discussing the independence of the judiciary. I used the debate to say that Judicial Independence doesn’t exist in Ethiopia, although it’s stated. I recalled the judges who flee the country in 2005 because they refuse to tamper with the conclusion on the inquiry about the massacre in 2005. They were pressed by the [late] PM and the government to do that. These were very courageous people who put all their lives and their families [at risk]. I also highlighted that trials of all political prisoners but in particular journalists Eskinder Nega, Wubeshet Taye, Riyot Alemu and others like DebebeEshetu; [political] leaders Andualem Arage e.t.c. were not fair; all the people [including] Europeans who were able to be present at some of these trials said they [the prosecutors] never produced any significant evidence against them and indeed the trials were not fair. So I hope I have made this appeal today here. AS - But they faced terrorism charges…? These terrorist charges are not credible, so I appeal for their liberation in the spirit of openness. You have now a sort of dual register. In public it said one thing in private it acknowledges that Ethiopia must change. Or Ethiopia needs support to change. In that context, indeed bold decisions should be taken to liberate these people, because some of these people are icons of the younger generation. Very educated, qualified generation which Ethiopia needs to develop itself. I receive a mail, a standard letter everyday from an Ethiopian who manages to flee the country and who is somewhere in Kenya, Uganda ….Nigeria asking me to write a letter to the UNHCR saying they need political asylum. So I know Ethiopia looses the best, most qualified generation not only because of lack of jobs but because there is politically closed environment with which these young qualified people cannot live. I know Ethiopia faces serious terrorist threat as we all do, Ethiopia in particular because of the neighborhood and the tension that has been built up by Meles Zenawi between Muslims and Christians inside Ethiopia which was not an issue in 2005 but in the meantime became a big source of concern. If the government continues the old ways repressing this bright, younger people who are now connected to the world in a way the regime cannot control them via the twitter, and facebook, and so on. Obviously many of these young people will be driven into the hands of radicals and extremists. Even to be recruited by terrorists. It is what we see happening in other countries in the region. So, it is very important to open up democratically for the security of the country. AS - in 2015 Ethiopia will hold a general election. Do you think it will be democratic, free and fair given the situation now? qoute1 Ana Gomes - I don’t know, but I hope it could be good. Meles died, he was the source of the repression;his own supporting group are divided. They are fighting with each other. There is indeed an opportunity to see Ethiopia change progressively, peacefully. Nobody wants to see Ethiopia destabilized. But to create the conditions for the election to be held democratically it requires the opposition to be allowed to operate, which is not the case in the moment. In the moment you have only one member of the opposition [in the parliament]. I recall in 2005 at least there were some results that were not disputed. And these are the results of Addis Ababa where all the 23 seats went in a shocking landslide victory to the opposition. Well, where are these people? In exile. They say the opposition is weak, of course it is weak. “it is weak, it is fragmented, it is not loyal…” are the same kind of things that I used to hear in 2005 from Meles Zenawi. But any opposition in that condition in any country would be weak. In my own country do you think the opposition in the days of the dictator was stronger? No! Most of it was underground. In order to have the conditions to operate I believe it is important to allow the opposition to operate, not just those inside the country but also those forced into exile. They need guarantee to operate. There is no media freedom, only an opening seen. I read the Ethiopian herald and it’s all the same thing only better because PM Meles Zenawi is not writing now. There is no condition for NGOs or civil societies to operate. I believe EU will not accept to come back and observe election and give its temp of credibility unless basic elements are met; such as liberating political prisoners or allowing the judiciary to operate independently. AS - “Europe could definitely make the difference for democracy in Ethiopia. Instead, current European leaders are choosing to fail it. In doing so they are not just failing Ethiopians. They are also failing Europe.” This is taken from a letter you wrote to AP. By this do you mean Europeans aren’t trustworthy? They don’t like democracy to thrive in Ethiopia? Ana Gomes - No! European citizens, European taxpayers, European Parliamentarians care about Ethiopia, democracy, development in Ethiopia, the efficiency of development assistance but the problem is they don’t know what happens in Ethiopia. They are fooled by the leaders; leaders in the council of ministers and in the European commission. And also the development industry prevailing should continue without trouble. That is their vested interest. The tragedy is many people don’t understand what is happening in Ethiopia. I was very happy that finally EU human rights sub-committee came last July. They are very serious, knowledgeable colleagues of mine. It was eye opener. They asked to visit Kalite Prison and the PM allowed them but was rudely treated by the Prison administration. That is an eye opener. AS - EU and Ethiopia are development partners today as well as then. When you were not on good terms with the regime in 2005 did EU stand by your side? Ana Gomes - The then commissioner in charge of foreign affairs and human rights stood by me always. She was not from my party but very serious. I appreciated. But the then development commissioner Mr. Louis Michel didn’t support me. Some people from his services in Brussels even tried to rewrite my report to water it down. I didn’t accept that. Several moments, my views were attacked. They supported the campaign against me which the government of MelesZ enawi spread. But Meles has gone! This is a new timing. I am pleased I was granted visa without preconditions. AS - You were lobbying with the EU member states accusing the Ethiopian government of violating human rights. Do you think the situation has improved now? Ana Gomes - I know it was not easy for the new PM to assert his role as PM. I know there was a lot of internal fighting within the power. He is not a Tigrian. I value the visa I was given. I value the move against corruption. I sense some change. AS - I saw you with the speaker of the house of people’s representative, AbadulaGemeda and Ambassador Teshome Toga. You had lunch with them may be. But you were not on good terms with them? Ana Gomes - There was nothing personal; even with Meles Zenawi. Even these professionals who were instrumental, I have nothing personal against them. I don’t pretend to know well this country. Ethiopian people really marveled me. Ethiopia has a great resonance in my country. My ancestors 500 years ago were looking for Prester John. However, Ethiopia has a magical resonance in my childhood. Ethiopia is special. Ethiopia is a civilization; not any country. It is a civilization. Anna Gomez AS – You said “the EU is not only misusing European taxpayer’s money, but supporting an illegitimate status-quo, letting down all those who fight for justice and democracy and increasing the potential for conflict in Ethiopia and Africa.” But conflict in Ethiopia rises sometimes due to terrorist threats. Do you agree? Ana Gomes - Not only the Muslim-Christian conflict Meles Zenawi fueled by trying to interfere in the Muslim community leadership but also in Ogaden. All the report we receive in the EU are disastrous, horrendous and I am very sorry to see the Ethiopian army involved in all of that. Terrorism is an excuse; subversion was in the days of the dictatorship in my country. Now the buzzword is terrorism. It serves to excuse, and to erase any rules, principles and values. I don’t accept it. I am very conscience of the terrorist threat. It is strong democratic societies who are better empowered to fight terrorism, not those with high level of poverty, unemployment and of internal conflict. That is the situation in Ethiopia now. I hope this can be sorted out. AS - “Western leaders resist speaking up against Zenawi’s regime by invoking stability interests. Besides attempting to depict Ethiopia as a success story of development assistance, EU and the US like to portray their ‘aid darling’ as a partner in the fight against terrorism and a crucial actor for stability in the horn Africa,” do you still believe in this statement of yours? Ana Gomes - I hope Ethiopian people will be able to make the distinction between this bankrupt leadership in Europe which brought us into the big economic crises which is also political crises and the people of Europe who really are serious about democracy, human rights and the rule of law. AS - Do you think the EU and the USA still see the regime as a partner and a crucial actor for stability or do you see any change in their position? Ana Gomes - I think they do. But on the other hand they also appreciate the limits of that partnership in the sense that they understand the big tensions that have been developing in Ethiopia and in the region; namely lack of effectiveness in fighting terrorism and deterring terrorism to infiltrate. I think the Americans understand it better. Within the Obama administration there is a realization that you cannot have security without real development, not fake development and numbers but without democracy. The Americans were much more effective in getting people out of jail. The American’s pressure had political prisoners freed; opposition leaders and Birtukan Medeksa and others. They realized these three elements are linked, although they have their own flout in fighting terrorism. I was told the new American ambassador to Ethiopia is outspoken about human rights. I hope it translates into a more principled approach on the part of the Obama administration. AS – a lot of Ethiopians respect you. They gave you an Ethiopian name. Ethiopians like honesty. Are you aware of your name? Do you know what it means? Ana Gomes - Yes! I am aware of it. Ethiopian friends told me about it. They told me “Ana Gobeze” I am flattered, I don’t deserve it. They told me that ‘Gobez’ means brave. I have been happy meeting Ethiopian community in different countries and also received fantastic ‘Kaba’ as a gift from Ethiopians inSweden.

talaku rucha

Thursday, 28 November 2013

በሽብርተንነት ስም የህዝብ መብቶችን ማፈን ይቁም!

ፀረ -ሽብርተኝነት ለአምባገነኖች ሁለት ጥቅም ያስገኝላቸዋል፡፡ አንደኛ በፀረ- ሽብርተኝነት ስም ከምዕራባውያን ኃያላን ጎን በአጋርነት በመቆማቸው በጥሬ ገንዘብም ሆነ በዓይነት (ለምሳሌ በመሣሪያ፣ በፖለቲካ ድጋፍ) ዳጎስ ያለ ጥቅም ያገኛሉ፡፡ ሁለተኛ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ስም የሚያወጡት ሕግ የውስጥ የሥልጣን ተቀናቃኞቻቸውን ለማጥቃት የሚያስችላቸውን ሕጋዊ ሽፋን ይሰጣቸዋል፡፡ ስለዚህ ነው ፀረ -ሽብርተኝነት ለአምባገነኖች ከሰማይ የወረደ የተቀናቃኝ ማጥቂያ መሣሪያ ነው የሚባለው፡፡ ይህንን ያልኩበት አብይ ጉዳይ ዛሬ ሃገራችንንና ህዝቧን እያስጨነቀ ያለው የወያኔ አገዛዝ የፀረ ሽብርተኝነት ህግን ከለላ በማድረግ በሰላማዊ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው የመብት ረገጣ፤ እጅግ የከፋ ደረጃ በመድረሱ ነው። በሰላማዊ ትግል ዴሞክራሲያዊ የመንግስት ለዉጥ ለማምጣት የሚታገሉ ሰላማዊ ዜጎችን አግባብ ባልሆነና ባልተጨበጠ ክስና ዉንጀላ ማሰር፣ አፍኖ መሰወር፣ ንብረትን ማዉደምና መዉረስ እንዲሁም የአደባባይ ግድያ ባለፉት 22 የወያኔ የአገዛዝ ዘመናት የተለመዱ ተግባሮች ሆነዉ ቆይተዋል። አሁን ደግሞ ይህ አምባገነናዊና ኢፍትሀዊ ተግባር በህግ ሽፋን ተጠናክሮ ቀጥሏል። ለገዥዉ ስርአት የአፈናና የጥርነፋ መዋቅር ተባባሪ ያልሆኑና ለመብታቸዉ መከበር የሚታገሉ ዜጎች በአሸባሪነት ስም በጅምላ እየታፈሱና እየታሰሩ ይገኛሉ። ታፍነዉ የተወሰዱና ያሉበት ቦታ የማይታወቀዉም ጥቂቶች አይደሉም። ባለፉት ጥቂት አመታት ብቻ በሽዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በሽብርተኝነት ተወንጅለዉ ታስረዋል። ሰብአዊ መብታቸዉም በማንአለብኝነት እየተረገጠ ይገኛል። ከነዚህ ንፁሀን ዜጎች ዉስጥ ብዙዎቹ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላቶች፤ የእምነት መሪዎችና ለሞያቸዉ ታማኝ የሆኑ ጋዜጠኞች መሆናቸዉን ስናይ ደግሞ ዘመቻዉ በሀገራችን ተጠናክሮ የህዝብን የስልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥ የሚደረገዉን ሰላማዊ ትግል ለመጨፍለቅና ህዝብን ከትክክለኛ መረጃ አርቆና አፍኖ ለመግዛት ታስቦበትና ሆነ ተብሎ የተያዘ ስልት መሆኑን ግልፅ ነው። በሽብርትኝነት ያለመከሰስ መብቱን በጠመንጃ ያስከበረው ወያኔ ግን ሰላማዊውን ህዝቡ በተለያዩ መንገዶች እያሸበረ የስልጣን ቆይታውን ለማርዘም ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል። ዜጐችን በማፈናቀል፤ በእምነት ውስጥ ጣልቃ በመግባትና የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት በመከፋፈል እያፋጀ የሽብር ሴራውን እየፈፀመ ይገኛል። ሰላማዊ ዜጋውን ፣አርሶ አደሩን፣ አርብቶ አደሩን በልማት ስም ተወልዶ ባደገበት እትብቱ ከተቀበረበት ሃገር እያፈናቀለ ለስደት እየዳረገው ይገኛል፡፡ ለዚህም የሽብር ሴራው ሰለባ የሆኑት፤ የሚበሉት፤ የሚጠጡት እና በመጠለያ እጦት በየአደባባዩ ሰፍረው የድረሱልኝ ጥሪ እያሰሙ የሚገኙት የአማራ ብሔረሰብ ወገኖቻችን ናቸው፤ እነዚህ ወገኖቻችን በሃገሪቱ አራቱም ማዕዘናት እየተፈናቀሉና እየተዋከቡ ይገኛሉ። ማፈናቀለ አልበቃ ያለው የወያኔ የሽብር መረብ ወደ እምነት ቦታዎችም በመዛመት ዋልድባን እና የተለያዩ የሃይማኖት ቦታዎችን በማፈራረስ በአለም ደረጃ እውቅና እና አድናቆት የተሰጣቸውን የሃገሪቱን የሃይማኖት፤ የታሪክ ቅርሶች በማውደም፤ ኢትዮጵያውያን በቀደምትነት በምንታወቅበት እምነታችን ላይ አደጋ በመፍጠር፤ አዋራጅ ድርጊቶችን በንቀት እና በጥላቻ እየፈፀሙ ይገኛሉ፡፡ ከእምነት ቦታዎች ባሻገር በአለም ደረጃ እውቅናን ካገኙት ታሪካዊ ቦታዎች ውስጥ ተጠቃሹ የታችኛው አዋሽ እና ኦሞ ሸለቆዎች አንዱ ነው፡፡ ይህ ታሪካዊ ቦታ ያራዊቶች እና የተለያዩ የደኖች ስብስብ ያለበት ሰፊ የሃገራችን ቅርስ የነበረው ሲሆን ዛሬ ላይ ግን ወያኔዎች በልማት ስም ለውጭ ባለሃብቶች አስረክበውት ድብዛው እየጠፋ ነው፡፡ አምባገነኑ ወያኔ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ያነሱትን የመብት ጥያቄ ወደ ጎን በመተው በእኔ አውቅላችኋለሁ እብሪት የተሞላ አስተሳሰብ በማፈን ንፁሃኑን ሙስሊም እየገደሉ ብሎም በሽብርተኝነት በመወንጀል እያሰቃዩት ይገኛሉ። ሙስሊሙ ህብረተሰብ የተቃውሞ ድምፁን ያሰማበትን አላማ ምንድነው? ችግሩስ ከምን የመነጨ ነው? ብሎ እልባት ከመስጠት ይልቅ ጥያቄአቸውን በማንቋሸሽ እና በማጥላላት በጠመንጃ አፈ ሙዝ የሚመልሱት ይመስል ህዝበሙስሊሙን ለከፋ መከራና ስቃይ ዳርገውታል። ለዚህ ድርጊታቸው ደግሞ ሚስጥሩ ንፁሃኑ ህዝበ ሙስሊም ላይ የሃሰት ታርጋ በመለጠፍ አሸባሪነትንና አክራሪነትን እየተዋጋው ነው በሚል የማስመሰልና የማታለል ስራው የምዕራባውያን ሃገራትንና የአሜሪካ ቀልብ ለመሳብና እርዳታ ለማጋበስ ነው። ቢያውቁት ግን ይህ ድርጊታቸው አውሬ እንጅ ሰው አለመሆናቸውን ቁልጭ አድርጐ ያሳያል። ለገንዘብ ሲባል ሰውን ያክል ፍጡር መግደል፤ ማሰርና ማሰቃየት ከአንድ ሰው የሆነ ሰብአዊ ፍጡር አይጠበቅምና። ሌላው ወያኔዎች 22 ዓመታት በጠመንጃ ስልጣን ላይ ከወጡበት ጊዜ አንስቶ ሲጠነስሱት የነበረው ሽብር የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት በመከፋፈልና በማፋጀት የኢትዮጵያን ህልውና አንድነትን፣ ማንነትን በማናወጥ፤ የስልጣን እድሜያቸውን ማርዘም ነው። ይህ ስራቸው ከምን ጊዜውም በላይ በአሁኑ ሰአት እያፋፋሙትና፤ ሰላማዊውን ህዝብ በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት በማጋጨት የሽብር ሴራቸውን እያስፋፉ ይገኛሉ። ዳሩ ግን ለወያኔዎች ህዝብን መከፋፈል የሚበጅ ቢመስላቸውም የዚህ የሽብር ድራማቸው ተጠቂዎች ግን በፍፁም ልንሆን አልቻልንም፤ ወደፊትም ልንሆን አንችልምም። ምክንያቱም መቻቻል እና በፍቅር አብሮ መኖር መለዬ ባህላችንን በፍፁም ይህ ሰይጣናዊ ድርጊታቸው ሊያመክነው ስለማይችል ነው። ይህንን አንድነታችንን፤ ፍቅራችንን የመቻቻል ባህላችንን የበለጠ በማጎልበት፤ ባህላችንን፣ አንድነታችንን፣ ሃይማኖታችንን እየተፈታተነ ያለው የወያኔን የሽብር ስልት በማክሸፍ፤ ለበለጠ ድል እስክንበቃ ትግላችንን ማጠናከር ይኖርብናል። በመጨረሻም የወያኔ ባለስልጣናት በፈረጠመ አምባገነናዊ ክንድ ህዝብን በማሸበርና በማፈን የስልጣን ዘመንን ለማራዘም መሞከር አወዳደቅን ማክፋት መሆኑን ካለፉት አምባገነናዊ ስርአቶች ሊማሩ ይገባል! አሁንም በድጋሚ ወያኔዎች ጠንቅቀው ሊያውቁት የሚገባ እውነት የኢትዮጵያ ህዝብ ሽብኝነትን በጽናትና በቁርጠኝነት ይቃወማል፤ ያወግዛልም፡፡ በፀረ -ሽብርተኝነት ሽፋን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን እየጣሰ ያለውን የወያኔ አገዛዝንም በተመሳሳይ ጽናትና ቁርጠኝነት ይቃወማል፤ ይታገላልም!!! ድል ለጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ!

Wednesday, 27 November 2013

የግንቦት7 እና አክራሪ የእስልምና ሀይሎች በኢህአዴግ አባላት ስም ፓርላማውን በመቆጣጠር ኢህአዴግን ሊጎዱት ይችላል ሲሉ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ተናገሩ

ኢሳት ዜና :-ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ይህን የተናገሩት ” በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደው የፖለቲካ እንቅስቃሴ የመንግስት ቀጣዩ የምርጫ ፈተና” በሚል ርእስ ለኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ባቀረቡት ጽሁፍ ነው።ኢሳት የሚኒስትሩን ሙሉ ንግግር የያዘ ሰነድ የደረሰው ሲሆን፣ በሰነዱ ግርጌ ላይ ” ለመደበኛ አባላት የማይነገር፣ ለከፍተኛ አመራሮች ብቻ” የሚል ተጽፎበት ይታያል። በዚህ ርእስ ስር ደግሞ ” ቀጣዩ የምክር ቤት አባላት ምርጫ የግንቦት ሰባት እና አክራሪ እስልምና ሀይሎችን የሚያስቀጥሉ አባላት ወንበሩ በኢህአዴግ አባላት ስም ሊነጠቅ ይችላል። ” ብሎአል። ሚኒስትሩ ለዚህ አስተሳሰባቸው የምርጫ 97ትን ሁኔታ እንደማጠቃሻ ተጠቅመዋል። ” የ97 የቅንጅት አሸናፊት አካሄድ ስልት ማለትም የተቃዋሚ አባላት ሁነው በህቡእ ተደራጅተው በኢህአዴግ የአባላትን ካርድ ሙሉ በሙሉ ፓርቲውን ሊጎዱት ይችላሉ” ሲሉ ሚኒስትሩ ጽፈዋል። ሚኒስትሩ በዚህ ጽሁፋቸው፣ ቅንጅት በ97 ምርጫ ማሸነፉን እንዲሁም የኢህአዴግ አባላት ሆነው ለቅንጅት በውስጥ ይሰሩ የነበሩ ሰዎች እንደነበሩ ጠቅሰዋል። በክርስትና እና በእስልምና ሀይማኖት ሽፋን የሚካሄደውን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ሚኒሰትሩ በዝርዝር አቅርበዋል። Image በክርስትና ሀይማኖት በኩል ” መንግስት በሃይማኖት አባቶች ሹመት ላይ እጁን ያስገባል፤ የዋልድባ ገዳም ተደፈረ፤ አልፎ አልፎ በአጋጣሚ ቤተክርስታያን ባለበት አካባቢ ከድርቅ ጋር ተያይዞ በሚነሳ ቃጠሎ ሆነ ተብሎ እንደተደረገ ማስወራት፤ ይህን የሚያግዝ የውጭ ሚዲያ መኖር ኢሳት በቀዳሚኒት ፣ የደርግ ስርዓት ደጋፊዎች የሆኑት ቪኦኤ በቀጣይነተወ የሚያራግቡት አካሄደ ጉዳዩን ትኩረት እንዲያገኝ ” ማድረጉን ሚኒስትሩ ገልጸዋል። የሙስሊሙ እንቅስቃሴንም በተመለከተ ሚኒሰትሩ ሲገልጹ” ከቅንጅት እስከ ህብረት፣ ከቪኦኤ እስከ ቲቪ አፍሪካ፣ ከጀርመን ድምጽ እስከ ቢላል ሬዲዮ፣ ከጅሃዳዊ ሀረካት እስከ ግንቦት ሰባት፣ ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች ዓለም አቀፍ እስከ መድረክ እስከ ስደተኛው ሲኖዶስ ያሉ ሀይሎች በተናጠልና በህብረት” ተሳትፈውበታል ብለዋል። የሙስሊሙ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ፍጥነት በመዳከም ሂደት ውስጥ የገባው በቡድኑ ቀንደኛ መሪዎች ላይ ህጋዊ ስርአቱን ተከትሎ የእስራት እርምጃ ከተወሰደ በሁዋላ ነው ብለዋል። በሃይማኖት ሽፋን የሚካሄዱ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ውለው አድረው እየተጋለጡና እየተዳከሙ መሄዳቸው ባይቀርም ባለፉት ሁለት ዓመታት ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን በሀይል ለመፈታተን ከሞከሩት የሁከት ሀይሎች ዋነኞቹ ነበሩ ማለት ይቻላል ብለዋል ሚኒሰትሩ። “በሃይማኖት ስም የሚካሄደውን ንግድ ውጤታማ እንዲሆን በማድረግ ረገድ የድህነት መንሰራፋትና የመልካም አስተዳደር እጦት ወይም ጉድለት ተጠቃሽ ናቸው” የሚሉት ዶ/ር ሽፈራው በተለይ ከድህነትና ኋላቀርነት መውጫውን ትክክለኛ መንገድ የሚያመላክት መሪ ድርጅት በሌለበት ፣ በሃይማኖት ሽፋን የሚነግዱ የፖለቲካ ሀይሎች አንዱን በሌላው ላይ ማነሳሳት የፅድቅ መንገድ እንደሆነ አስመስለው በማቅረብ ዜጐችን ወደጥፋት ይመራሉ” ብለዋል። መሪ ድርጅቱም ኖሮ በአመራርም ሆነ በአባላት ደረጃ በአንድ በኩል ከፀረ ድህነትና ኋላቀርነት ትግሉ ላይ ጽናትና ብቃት ያለው አመራር መስጠት ካልተቻለ፣ በሌላ በኩል ደግም የፓርቲና የመንግስት መሪዎች ስራቸውን ከየትኛውም ሃይማኖት ገለልተኛ በሆነ መንገድና ሁሉን ሃይማኖቶች እኩል በሚያስተናግድ አግባብ ካልፈፀሙ ይኸው ችግር ተባብሶ መቀጠሉ አይቀርም ሲሉ ዶ/ር ሽፈራው አስጠንቅቀዋል። አሁንም ድህነትና ኋላቀርነት በመኖሩ፣ በፓርቲና በመንግስት አመራራችን የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ጉድለቶች በመኖራቸውና የእምነት ጉዳይ ለሚዛናዊ አስተሳሰብ ያለው ተጋላጭነት ዝቅተኛ በመሆኑ አልፎ አልፎ የተካረረ ፍጥጫ እያጋጠመ መሆኑንም ሚኒስተሩ በጽሁፋቸው አብራርተዋል። ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ለኢህአዴግ ባለስልጣናት ያቀረቡትን ሙሉ ጽሁፍ በድረገጻችን መመልከት የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን። በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደው የፖለቲካ እንቅስቃሴ የመንግስት ቀጣዩ የምርጫ ፈተና ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም ህዳር 2006 ዓ.ም አዲስ አበባ 1. በክርስትና ሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደው የፖለቲካ እንቅስቃሴና ቀጣይ አዝማሚያዎቹ፣ ü በክርስትና ሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደው እንቅስቃሴ በዋነኛነት ኢትዮጵያ የክርስትና ሃይማኖት የበላይነት ሊኖርባት ይገባል በሚል ኋላቀርና ዘመን የሻረው አስተሳሰብና ሀይል የሚመራ ነው፡፡ ü በዚህ መሠረት ይህ ኋላቀር ሀይል መነሻና መድረሻውን የክርስትና ሃይማይማኖትን የበላይነት አድርጐ ይህን ሊያረጋግጡልኝ ይችላሉ የሚላቸውን መፈክሮች ጐላ አድርጐ ያሰማል፡፡ ü በዚህ ረገድ “ኢትዮጵያ የክርስትና ደሴት ነች”፣ “አንድ አገር አንድ ሃይማኖት” የሚሉ መፈክሮቹ የአስተሳሰቡን ጭብጥ የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ü በዚህ ሀይል አስተሳሰብ መሠረት አገራችን በርካታ ሃይማኖቶችን ያስተናገደችና በማስተናገድ ላይ የምትገኝ አገር መሆኗ ቀርቶ የክርስቲያን ደሴት ብቻ ተደርጋ ትቀርባለች፡፡ ü እራሱ አንድ አገር አንድ ሃይማኖት የሚለው አስተሳሰብም በተመሳሳይ መልኩ በኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ሃይማኖት ብቻ እንዳለ ወይም ሊኖር እንደሚገባ የሚሰብክ ኋላቀር የፀረ እኩልነት አስተሳሰብ ነው፡፡ ü እነዚህ ሀይሎች አንደንዶቹ የሃይማኖት ጉዳይ ህብረተሰቡን በቀላሉ ሊያደናግርልን ይችላል ብለው የሚያምኑ ተቃዋሚ የፖለቲካ ሀይሎች ሲሆኑ ü ከፊሎቹ ደግሞ ከሃይማኖት አኳያ የኦርቶዶክስ እምነት መንግስታዊ ሃይማኖት መሆኑ ቀርቶ ከሌሎች ሃይማኖቶች በእኩልነት የሚታይና የሚከበር መሆኑን ያልተቀበሉ በትላንቱ ዓለም የሚኖሩ ሀይሎች ናቸው፡፡ ü የፖለቲካ ሀይሎቹ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የክርስትና ሀይማኖትን መጠለያ በማድረግ የተለያዩ ቀስቃሽና ስሜትን የሚኮረኩሩ የፈጠራ አጀንዳዎችን ለማራገብ የሚሞክሩ ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- መንግስት በሃይማኖት አባቶች ሹመት ላይ እጁን ያስገባል፤ የዋልድባ ገዳም ተደፈረ፤ አልፎ አልፎ በአጋጣሚ ቤተክርስታያን ባለበት አካባቢ ከድርቅ ጋር ተያይዞ በሚነሳ ቃጠሎ ሆነ ተብሎ እንደተደረገ ማስወራት፤ ይህን የሚያግዝ የውጭ ሚዲያ መኖር ኢሳት በቀዳሚኒት እና ቪኦኤ /የደርግ ስርዓት ደጋፊዎች/ የሚያራግቡት አካሄደ ጉዳዩን ትኩረት እንዲያገኝ አድርግውታል፡፡ ፤ ü በራሳቸው ፖለቲካዊ መስፈርት የቤተ ክርስቲያኒቱን መሪዎችና ሀላፊዎች መሾምና መሻር የሚፈልጉ ተቃዋሚ ሀይሎች በተለይም ደግሞ በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚ ሀይሎች የራሳቸውን ሰው አዘጋጅተው ለማስመረጥ ብዙ ጥረት አድርገዋል፡፡ ü በዛሬማ ሸለቆ አካባቢ የስኳር ልማቱ የሚካሄደው በጣም ዝቅተኛና ቆላ ላይ ሲሆን፤ የዋልድባ ገዳም መሬት ደግም በደጋና ወይናደጋ ቦታዎች ላይ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሃቁ ይህ ሆኖ ሳለ በገዳሙና በስኳር ማሳው መካከል ያለውን ከፍተኛ የመልክዓምድር ልዩነት በቅርቡ ለማያውቁ የክርስትና ምዕመናን ሁሉ ገዳሙ ተደፈረ የሚለው ቃል እልህና የቁጣ ስሜት ይፈጥርባቸዋል ብሎ በማመን ሰፊ ዘመቻ ሲካሄድበት ከርሟል፡፡ ü የዚህ ዘመቻ ፊታውራሪዎች በአሜሪካን ድምጽ ሬዲዮ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ የቀድሞ የኢህአፓዎችና የቅንጅት ትርፍራፊዎች ናቸው፡፡ ü በአንድ ወቅት በምዕራብ ኢትዮጵያ ጅማ አካባቢ በኻዋርጃ ስም የሚታወቁ አክራሪዎች በክርስቲያኖች ላይ ያደረሱትን ግድያ መጠጊያ በማድረግ “ክርስቲያኖች እየተጨፈጨፉ ነው ስለዚህም አፀፋው ሊመለስ ይገባዋል” በሚል ቅኝት መንቀሳቀስ ጀምረው ነበር፡፡ ü አልፎ አልፎ እንደምናየውም ከድርቅ ጋር በተያያዘ ምክንያት በሚነሳ ቃጠሎ አንድ ቤተ ክርስትያን ወይም ገዳም ባለበት አካባቢ በአጋጣሚ ቃጠሎ ከተነሳ ይህንኑ ሆን ተብሎና በክርስትና ላይ ጥቃት ለመፈፀም ሲባል እንደተደረገ አስመስሎ የማቅረብ፣ ü እንዲሁም ለቤተ ክርስትያን መስሪያ ተብሎ ባልተሰጠ ቦታ የቤተክርስትያን ግንባታ መጀመርና ህገ ወጥ ግንባታ እንዲቆም ሲጠየቅ በክርስትና ሃይማኖት ላይ ተዘመተ ብሎ የእኩልነት ጥያቄ ማንሳት አዘውትረው የሚጠቀሙባቸው ስልቶች ናቸው፡፡ ü ከመንግስትና ድርጅት ሀላፊዎች ውጭ ባሉ የተሳሳተ አስተሳሰብ ባላቸው ዜጐች የሚራመዱት እነዚህ ኋላቀርና ፀረ እኩልነት አስተሳሰቦች እንደተጠበቁ ሆኖ ሃይማኖታዊ አዝማሚያ ባልተለያቸውና በመንግስታዊ ሀፊነትና በእምነታቸው መካከል ያለውን ልዩነት በውል መገንዘብ የተሳናቸው ሀላፊዎች ደግሞ የየራሳቸውን ስህተት ሲሰሩ ማስተዋል የተለመደ ነው፡፡ ü በአጠቃላይ ሲታይ ወቅታዊና ለፖለቲካ ንግድ የሚያመች እንዲህ አይነት አጀንዳ ሲፈጠር አጋጣሚውን ለመጠቀም ምን ጊዜም ወደ ኋላ አይሉም፡፡ ü በክርስትና ስምና ሽፋን የሚነግዱ ፖለቲከኞች አነዚህን የመሳሰሉ መሠረተ ቢስ አጀንዳዎችን በመቅረጽና በማራገብ ክርስትና ሃይማኖት ተከብሮና ተቻችሎ በሚኖርባት አዲሲቷ ኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ክብርና ሞገሱን የተገፈፈ አስመስለው ያቀርባሉ፡፡ ü ለእምነቱ ክብርና ሞገስ የሌላቸው ራሳቸው በሃይማኖቱ ሽፋን የፖለቲካ ንግድ የሚያካሂዱት ü ሀይሎች መሆናቸውን ደብቀው መንግስትና ስርዓቱን በመሰረተ ቢስ ወንጀል ይከሳሉ፡፡ 2. በእስልምና ሀይማኖት ሽፋን የሚካሄደው የፖለቲካ እንቅስቃሴና ቀጣይ አዝማሚያዎቹ፤ በክርስትና ሀይማኖት ሽፋን ከሚካሄደው እንቅስቃሴ ባልተናነሰ ይልቁንም አልፎ አልፎ በራሱ ባህሪ ከዚያም በከፋ ሁኔታ በእስልምና ሀይማኖት ስም ሚካሄድ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚታይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ü እንቅስቃሴው ውስጥ ውስጡን ሲካሄድ ቆይቶ ከቅርብ አመታት ወዲህ አክራሪነትን ለመታገል እንቅስቃሴ ሲጀመር ነው በግልጽ ፀረ ህገመንግስታዊ መልክ ይዞ መታየት የጀመረው፡፡ ü ከ20 ዓመታት በፊት በጨቋኙ ስርዓት ይደርስባቸው ከነበረው ግፍና በደል በዲሞክራሲያዊ ትግል ተላቀው የሃይማኖታቸውን እኩልነት ባስከበሩባት አዲሲቷ ኢትዮጵያ የሃይማኖት የበላይነትን በማስፈን ቅኝትና ከሌሎች ሃይማኖት ተከታይ ወንድሞቻቸው ጋር በመቻቻልና በእኩልነት የመኖር እድልን በሚዘጋ ሁኔታ የሚንቀሳቀሱ አክራሪ ዝንባሌዎች መታየት ጀምረዋል፡፡ ü እነዚህ አክራሪ እንቅስቃሴዎች በዋኛነት ከሰሜን አፍሪካና ከመካከለኛው ምስራቅ አገሮች አክራሪ ሀይሎች የመነጩ፤ በአንድ በኩል የእስልምናን የበላይነት በአካባያችን ለማስፈን የሚካሄደው እቅድ ማስፈጸሚያ፤ በሌላ በኩል በሃይማኖቱ በሚነግዱ ግለሰቦችና ቡድኖች በሃገሪቱ የተፈጠረውን የእኩልነት ስርዓት በመፃረር የበላይነትን ለማሰፈን የሚካሄደው እንቅስቃሴ መገለጫዎች ናቸው፡፡ ü በእነዚህ አክራሪ አስተሳሰቦች የሚመሩ ጽንፈኞች መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባ በመገንዘብ በሀይማኖት ሽፋን የዜጐችን ሰብዓዊ መብቶች የሚረግጡ በርካታ አስነዋሪ ተግባራትን ፈጽመዋል፡፡ ነባር መስጊዶችን አቃጥለዋል፣ ነባርና ኢትዮጵያዊ መሠረት አላቸው የሚሏቸውን የሃይማኖት መጽሃፍት አቃጥለዋል፡፡ ü ይህን በመቃወም ለማስቆም የሞከሩ ዜጐችና የሃይማኖት ትምህርት ቤቶችንና መስጊዶችን የአመራር ቦታዎች በጉልበት ነጥቀዋል፣ ይህን የተቃወሙ ዜጐችን ሁሉ ከቤት ንብረታቸው አፈናቅለዋል፡፡ ይህ ከሞላ ጐደል አክራሪዎቹ በደረሱባቸው ቦታዎች ሁሉ የተካሄደ ነው፡፡ ü የመጀመሪያው ሙከራ ያነጣጠረው በኢትዮጵያ ያሉ ብዙዎቹ ነባር ሃይማኖቶች ሁሉ መሠረታቸው መካከለኛው ምስራቅ መሆኑ እየታወቀ መንግስት አህባሽ የሚባል ሃይማኖት ከውጭ አመጣብን የሚለው መከራከሪያ ውሃ የማይቋጥር ቢሆንም መንግስት ይህኛውን ወይም ያኛውን ሃይማኖት ከዚህኛው ወይም ከዚያኛው አገር በብድር የሚያመጣበት ምክንያትም ሆነ ሎጂክ አልነበረውም፣ የለውምም፡፡ ሃቁ ይህ ሆኖ ሳለ በውጭ ገንዘብ ድጐማ የሚንቀሳቀሱት እነዚህ ሀይሎች ባላቸው አቅመ ሁሉ በመታገዝ ü መንግስት አህባሽ የሚባል የውጭ እምነት አምጥቶ /በሃጂ አብዲላሂ መምህርነት የተስፋፋውን/ ሙስሊሙን ህብረተሰብ ሊጭንበት እየተንቀሳቀሰ ነው የሚል መሠረተ ቢስ ጉዳዮችን እያመጡ መንግስት በሃይማኖታችን ጉዳይ ጣልቃ ገባ ብለው ሲከሱ ሰንብተዋል፡፡ ቀላል ያልሆነ የህብረተሰብ ክፍል በተለይም ወጣት አደናግረዋል፡፡ ü የአስተምህሮ መሰረታቸው ብቻ ሳይሆን የየፋይናንስ ምንጫቸውም የውጭ ሀይል ለዚያውም በጣም በቅርቡ የምናውቀው መካከለኛው ምስራቅ በሆነበት ሁኔታ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ ገብነት ለመክሰስ የሚያስችላቸው ሞራላዊ ብቃት እንዴት ሊጐናፀፉ ቻሉ? ü ገንዘብን በመጠቀም ነባሩን የሱፊ እምነት ለመገለባበጥ ያደረጉት ጥረትና በተወሰነ ደረጃ ያገኙት ውጤት የልብ ልብ ስለሰጣቸው ብቻ ራሳቸውን ምሉዕ በኩልሄ አገር በቀል ሌላውን ደግሞ መጤ ለማስመሰል እስከመሞከር ደርሰዋል፡፡ ü ደግነቱ በዚህች ዴሞክራሲያዊት ምድር አገር በቀል መሆን ወይም አለመሆን እምነትን ለማስተማር ቦታ የሌለው መሆኑ እንጅ አገር በቀል ያልሆነ እምነት ሁሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ቦታ ሊኖረው አይገባም ቢባል ማን ይቀራል፤ ü ነገር ግን አዲሱቱ ኢትዮጵያ የሃይማኖት መለኪያዋ የዜጐች ምርጫ መሆን አለመሆኑ ነው፡፡ መሠረቱ ኢትዮጵያዊ፣ አፍሪካዊ ወይም የሌላ ዓለም መሆን አለመሆኑ አይደለምና ከመካከለኛው ምስራቅ አንዳንድ አገሮች በቅርቡ የገቡትን ሌሎች አስተምህሮዎች ያልከለከለችውን ያክል አህባሽም ሆነ ሌላ አስተምህሮ የዜጐች ምርጫ እስከሆነ ድረስ እንዳይገባ የምትከለክልበት አንዳችም ምክንያት አልነበረም፡፡ ü በዚህ ጉዳይ ላይ መንግስት ጉዳዩን አቃሎ በመመልከት ሰፊና አጥጋቢ ማብራሪያ ባለመስጠቱ ግን አክራሪዎቹ ፈቃጅና ከልካይ ሆነው አህባሽ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት የለበትም የሚል አስተምህሯቸው የብዙዎቹን ወጣት ሙስሊሞች አዕምሮ እንዲበርዝ እድል አገኘ፡፡ ü ሌላው መጠቀሚያ ሊያደርጉት የሞከሩት እና የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምርጫ ነበር፡፡ ü መንግስት ከት/ቤቱ የፈለገው ሃይማኖትና ፖለቲካ የተነጣጠሉ መሆናቸውን በመቀበል ከማናቸውም አይነት የፖለቲካ አስተምህሮ በፀዳ አኳኋን ተግባሩን እንዲፈጽም ብቻ ነው፡፡ ü ተቋሙ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን አክብሮ ከመንቀሳቀስ ይልቅ ለማንም ተጠያቂነት በሌላቸው ወገኖች እየተመራ ከሃይማኖታዊ ጉዳዮች በራቁና ለአክራሪዎች በተመቹ አጀንዳዎች ተጠምዶ ጊዜውን ሲያሳልፍ ቆይቷል፡፡ በመሆኑም ይህንኑ መነሻ በማድረግ ድርጅቱ በእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሚመራና ተጠያቂነት ያለበት ተቋም እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ü የሙስሊሙ ማህበረሰብ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤቶችን እንደ አዲስ መርጦ ማደራጀት እንደሚፈልግ ግልጽ ነበር – ከየአቅጣጫው በሚነሱ ጥያቄዎች፡፡ በዚህመ ሠረት ምክር ቤቶቹ በአፋጣኝ በሚካሄድ ምርጫ እንዲዋቀሩ ጥያቄ አቅርቦ ነበር፡፡ ይህ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ህገ መንግስታዊ መብት በመሆኑ መንግስት ይህንኑ ተቀብሎ፤ ምክር ቤቶቹ ለዚህ የህዝብ ጥያቄ አወንታዊ ምላሽ እንዲሰጡ ከእርሱ የሚጠበቀውን ምክር ለግሷል፡፡ ምክር ቤቶቹ በአፋጣኝ በሚካሄድ ምርጫ እንዲዋቀሩ የማድረጉን ዴሞክራሲይዊ አሰራርም ደግፏል፡፡ ü ልክ መንግስት ጣልቃ እንደገባና ያለሙስሊሙ ህዝብ ፍላጐት መራጮች በላዩ ላይ እንደተጫኑበት በማስመሰል ሲቀሰቅሱ ከቆዩ በኋላ ከዚህ ታላቅ የዴሞክራሲ ተግባር አቋርጠው ወጡ፡፡ ü በውጤቱም ህዝቡ ከአክራሪነት የፀዱ የሚላቸውን ሰዎች መምረጡን አረጋግጧል፡፡ ነገር ግን ይህ ምርጫ ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ ሆኖ መካሄዱ ያንገሸገሻቸው አክራሪ ሀይሎች ገና ከምርጫው ዋዜማ ጀምሮ ይህንኑ ለመቃወም ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል፡፡ ü ድምፃችን ይሰማ በማለት አርብ አርብ በአንዋር መስጊድና አልፎ አልፎም በሌሎች መስጊዶች ከመንግስት ጋር በከፍተኛ ደረጃ ሲፋጠጡ ከርመዋል፡፡ ü ከውጭ ሚዲያዎች ጋር በተቀናጀ አኳኋን በእስልምና ሃይማኖት ላይ ጥቃት የደረሰ በማስመሰል ለማነሳሳት ብዙ ጥረት አድርገዋል፡፡ ü በፖሊስና ፀጥታ አስከባሪ ሀይሎች ትዕግስት ወደ መካረርና ግጭት እንዳይመራ ተደረገ እንጂ ከሞላ ጐደል ለአንድ ዓመት ተኩል ያክል አክራሪዎቹ መንግስትን ወደ ግጭትና ደም መፋሰስ ለማስገባት ያላደረጉት ጥረት አልነበረም፡፡ ü በአፍሪካ ህብረት ዓመታዊ ስብሰባ ወቅት ያልተፈቀደ የሚሊዮን ሰዎች ሰልፍ ለማድረግና የአዲስ አበባን መንገዶች በመዘጋጋት አደጋ ለመፍጠር ሙከራ አድርገው ነበር፡፡ እንደዚሁም ባለፈው ክረምት አንድ ሌሊት ላይ ከቢላል መስጊድ በመነሳት አዲስ አበባ ከተማን ለማተራመስ ሞክረው ነበር፡፡ ü እራሱን ጀሃዳዊ ሃረካት በሚል ስያሜ ለማስተዋወቅ ጥረት ያደረግ ከነበረ የአሸባሪዎች ድርጅት ጋር በመቀናት የአንዋር መስጊዱንም ሆነ ሌሎች መሰል የነውጥ ሙከራዎች በሽፋንነት መጠቀም መርጠው ነበር፡፡ ü ይህም ሆኖ መንግስት ረጀም ጊዜ ወስዶ ባካሄደው ጥናትና በሰበሰባቸው ማስረጃዎች ላይ በመመስረት በቡድኑ ቀንደኛ መሪዎች ላይ ህጋዊ ስርዓቱን ተከትሎ የእስራት እርምጃ ወስዷል፡፡ ü ከዚህ ጊዜ በኋላ ነው ንቅናቄው በከፍተኛ ፍጥነት በመዳከም ሂደት ውስጥ የገባው፡፡ ü በሌላ በኩል ደግም ሃይማኖትን በሽፋንነት ለመጠቀም የሞከረው ይኸው ሀይል በተለይ በውጭ ከሚገኙ ደጋፊዎቹ ጋር በመቀናጀት አሉ የተባሉትን ፀረ ኢትዮጵያ ሚዲያዎች ከመጠቀሙም ባሻገር ከግንቦት 7 እስክ ስደተኛው ሲኖዶስ ባለ የትምክህት ሀይሎች ለመደገፍና ብርቱ ጥረት አድርጓል፡፡ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው በሚል ፈሊጥ እርስ በእርስ ተሳስረውና ተደጋግፈው ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል፡፡ ü በማጠቃለል ሲታይ በሃይማኖት ሽፋን የሚካሄዱ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ውለው አድረው እየተጋለጡና እየተዳከሙ መሄዳቸው ባይቀርም ባለፉት ሁለት ዓመታት ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን በሀይል ለመፈታተን ከሞከሩት የሁከት ሀይሎች ዋነኞቹ ነበሩ ማለት ይቻላል፡፡ ü በሀይማኖት ሽፋን የሚካሄደው እንቅስቃሴ በጽንፈኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች በቀጥታ ከተደረገው የነውጥ ማነሳሰት በእጅጉ የላቀ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ü ምንም እንኳን ነውጠኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከ97 ውድቀታቸው በኋላ በተመሳሳይ ደረጃ ወደሚገለጽ የጐዳና ላይ ነውጥ ለማምራት በከፍተኛ ደረጃ እየተቸገሩ ቢሆኑም በሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደውን እንቅስቃሴ በመደገፍና ነዳጅ በማርከፍከፍ ለማቀጣጠል ያደረጉትን ጥረት ጨምሮ የወቅቱ ፀረ ህገ መንግስታዊ ንቅናቄ መገለጫ የሃይማኖት ልባስ ይዞ የሚካሄደው እንቅስቃሴ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ü በሃይማኖት ሽፋን ለመንቀሳቀስ የተመረጠበትን ዋነኛና ደጋፊ ምክንያቶች መለየትና ከዚህም አኳያ መሠረታዊ መፍትሄ ማበጀት ይገባል፡፡ 3. ሃይማኖትን በሽፋንነት ለመጠቀም የተመረጠባቸው ምክንያቶች፣ ü ሃይማኖትን በሽፋንነት በመጠቀም የፖለቲካ እንቅስቃሴውን ማካሄድ የመረጡት ሀይሎች የተለያየ መጠሪያ ያላቸው ነገር ግን በመሰረቱ የትምክህት ወይም የጠባብነት መፈክሮችን አንግበው ለመፋለም የሞከሩ የፖለቲካ ሀይሎች እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ ü ከቅንጅት እስከ ህብረት፣ ከቪኦኤ እስከ ቲቪ አፍሪካ፣ ከጀርመን ድምጽ እስከ ቢላል ሬዲዮ፣ ከጀሃዳዊ ሃረካት እስከ ግንቦት ሰባት፣ ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች ዓለም አቀፍ እስከ መድረክ እስከ ስደተኛው ሲኖዶስ ወዘተ ያሉ ሀይሎች በተናጠልና በህብረት የተሳተፉበት ነው፡፡ ü ሁሉም ያነገቡትን ዓላማ በተለያዩ ፀረ ህገ መንግስታዊ ስልቶች በመታገዝ ለማስፈፀም ሞክረው የከሸፈባቸው ሀይሎች ናቸው፡፡ ü እነዚህ አላማቸውን በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ በማራመድ ለስኬት መብቃት ያቃታቸው ድርጅቶችና ሀይሎች ከፍ ሲል እንደተመለከትነው የፖለቲካ ዓላማቸውን በሃይማኖት ሽፋን ማራመድ የመረጡት ይህ ስልት ምን ዓይነት እድል ቢሰጣቸው ነው ብሎ ጥያቄ ማንሳትና ጉዳዩን መመርመር በዚሁ ዙሪያ በቀጣይነት መካሄድ ያለበትን ትግል በትክክል ለመወሰን አስፈላጊ ነው፡፡ ü በድሃና ኋላቀር ህብረተሰብ ውስጥ በእምነት ጉዳይ ዜጐችን ብዥታ ውሰጥ መክተት ይህን ስልት ለመረጡ ወገኖች በቀላሉ ያለመጋለጥ እድል ያጐናጽፈናል፡፡ ከዚህም አለፍ ሲል ለድል ያበቃናል ብለው ማመናቸው ነው፡፡ ü የእምነት ጉዳይ ለሚዛናዊ አስተሳሰብ ያለው ተጋላጭነት በተነፃፃሪ አነስተኛ ከመሆኑ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ü በሃይማኖት ለሚመራ ሰው ወደ ማንኛውም ድርጊት ለማምራት ማመን ብቻውን በቂ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ü “በእምነትህ የመጣ ነው” ተብሎ የቀረበለትን ጉዳይ ያለማንገራገር ተቀብሎ ወደ ድርጊት ማምራት በብዙ የሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ የሚታይ ክስተት ነው፡፡ ü ስለሆነም ይህ አካሄድ በሃይማኖታቸው ቀናዒ የሆኑ ሰዎች በሃይማኖት ሽፋን የሚራመዱ የፖለቲካ አጀንዳዎች ሰለባ ለማድረግ የተሻለ እድል ይፈጥርልናል በማለት ነው፡፡ ü በበለፀገው ዓለምም በአሸባሪነትም ሆነ በፀረ አሸባሪነት ጐራ ተሰልፈው የሚፋለሙ ሀይሎች ሃይማኖታዊ ጥሪ በማስተላለፍ የፖለቲካ ዓላማቸውን በሃይማኖት ግጭት መልክ ሲያስኬዱ ማየት የተለመደ ነው፡፡ ü የትኛውንም ጎራ በመሠረተ ቢስ እምነት ነክ ውንጀላዎች በቀላሉ በስሜት በማነሳሳት ሌላውን እንዲገጥሙ ማድረግ ይቻላል ተብሎ ይታመናል፡፡ ü በመሆኑም የከሰሩ ፖለቲከኞች ሁሉ ሃይማኖትን በሽፋንነት በመጠቀም መንቀሳቀሳቸው የእምነት ጉዳይ ለሚዛናዊ አስተሳሰብ ያለው ተጋላጭነት በተነፃፃሪ አነስተኛ ከመሆኑ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ü በሃይማኖት ስም የሚካሄደውን ንግድ ውጤታማ እንዲሆን በማድረግ ረገድ አጋዥ ሚና የሚጫወቱ ችግሮች ደግሞ ይኖራሉ፡፡ በዚህ ረገድ የድህነት መንሰራፋትና የመልካም አስተዳደር እጦት ወይም ጉድለት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ü በተጨባጭ እንደሚታየው በበለፀገና ሰርቶ የመጠቀም እድል በሰፋበት ማህበረሰብ ውስጥ ለጽንፈኝነት መሠረት የሚሆን ተስፋ መቁረጥ አይገኝም፡፡ ሰርቶ መክበርና ማደግ ስለሚቻል ለተስፋ መቁረጥ ምክንያት የሚሆን ችግር አይኖርም፡፡ ü መልካም አስተዳደር በሰፈነበት ሁኔታ ዜጐችና ህዝቦች በደስታና በስምምነት ይኖራሉ፡፡ በአንፃሩ ድህነትና ኋላቀርነት በተስፋፋበት ህብረተሰብ ውስጥ ተስፋ መቁረጥ ያይላል፡፡ ዜጐች የምድራዊ ኑሯቸውን ከሲኦል ያልተለየ አድርገው በመውሰድ በሃይማኖት ስም ለሚቀርቧቸው ሃሳዊ መሲሆች ሁሉ አመኔታቸውን ሊሰጡ ይገደዳሉ፡፡ ኢትዩጵያ በመጭው ምርጫ ፈተና ይሆንብናል፡፡ ü በተለይ ከድህነትና ኋላቀርነት መውጫውን ትክክለኛ መንገድ የሚያመላክት መሪ ድርጅት በሌለበት በሃይማኖት ሽፋን የሚነግዱ የፖለቲካ ሀይሎች አንዱን በሌላው ላይ ማነሳሳት የፅድቅ መንገድ እንደሆነ አስመስለው በማቅረብ ዜጐችን ወደጥፋት ይመራሉ፡፡ ü መሪ ድርጅቱም ኖሮ በአመራርም ሆነ በአባላት ደረጃ በአንድ በኩል ከፀረ ድህነትና ኋላቀርነት ትግሉ ላይ ጽናትና ብቃት ያለው አመራር መስጠት ካልተቻለ፣ በሌላ በኩል ደግም የፓርቲና የመንግስት መሪዎች ስራቸውን ከየትኛውም ሃይማኖት ገለልተኛ በሆነ መንገድና ሁሉን ሃይማኖቶች እኩል በሚያስተናግድ አግባብ ካልፈፀሙ ይኸው ችግር ተባብሶ መቀጠሉ አይቀርም፡፡ ü ከዚህ አኳያ ሲታይ ድህነትና ኋላቀርነነት እንዲሁም እነዚህን ለማስወገድ የሚያስችል ብቃት ያለው አመራር እጦት የፖለቲካ ጽንፈኝነትና የሃይማኖት አክራሪነት የሚስፋፋባቸው ለም አፈሮች ብቻ ሳይሆኑ በሃይማኖት ሽፋን የሚነግዱ ፖለቲከኞችም እንደመልካም አጋጣሚ የሚመለከቷቸው ናቸው፡፡ ü በመሆኑም እነዚህን ችግሮች በመፍታት በሃይማኖት ሽፋን ለሚነግዱ ፖለቲከኞች መንቀሳቀሻ አድማሱን ማጥበብ እጅግ ተፈላጊ ሆኖ ይገኛል፡ IV. በሃይማኖት ሽፋን የሚካሄደውን የፖለቲካ ንግድ በአስተማማኝ ደረጃ ለማሸነፍ ምን እንስራ? ü ከፍ ሲል እንደገለጽነው ፈጣንና ህዝብ የሢቀምበት ለውጥና ብዝሃነነትን በአግባባ የማስተናገድ ችሎታተ የያለው ህብረተሰብ በመፈጠሩሪ ምክንያት በሀይማኖት ሽፋንም ሆነ በግላጭ ሲካሄድ የቆየው ጽንፈኛ እንቅስቃሴ የህዝብ ይሁንታን ሊያገኘ ባለመቻሉ ትርጉም ያለው ሁከትና ብጥብጥን ለመቀስቀስ ሳይቻለው ቆይቷል፡፡ ü ይህ መሠረታዊ ሃቅ አንደተጠበቀ ሆኖ አሁንም ድህነትና ኋላቀርነት በመኖሩ፣ በፓርቲና በመንግስት አመራራችን የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ጉድለቶች በመኖራቸውና የእምነት ጉዳይ ለሚዛናዊ አስተሳሰብ ያለው ተጋላጭነት ዝቅተኛ በመሆኑ አልፎ አልፎ የተካረረ ፍጥጫ የሚያጋጥመን ሆኖ ቆይቷል፡፡ ü ይህ ፍጥጫ በተለይ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከሞላ ጐደል ሁሉንም ተፋላሚ ሀይሎች በሁለት ጐራ ከፍሎ ያፋጠጠ ሆኖ ከርሟል፡፡ ü ምንም እንኳን ችግሩ ለጊዜውም ቢሆን በመንግስት ታጋሽነትና አርቆ አስተዋይነት እንዲሁም በሰላም ወዳዱ ህዝብ ብርቱ ትግል የከሸፈም ቢሆን ለችግሩ መቀስቀስ ምክንያት የሆኑት ጉዳዮች በሙሉ ዛሬም በተጨባጭ ይገኛሉና ይህንን ታሳቢ ያደረገ የመፍትሄ ሃሳብ ማመላከት ተገቢ ይሆናል፡፡ 1. ፀረ- ድህነትና ፀረ-ኋላቀርነት ትግላችንን እናፋፍም፣ ü በድህነት የተጐዳ ህብረተሰብ ሁሌም በምሬት ውስጥ የሚኖርና ከዚህ ችግር የሚያላቅቀው ትክክለኛ አማራጭ ካልቀረበለት በስተቀር በሌሎች ጽንፈኛና መሰረተ ቢስ አማራጮች ሊማለል የሚችል ነው፡፡ ü በተለይ ደግም በምድራዊው ህይወቱ ያላለፈለትን ህዝብ በሰማይ ቤት ያልፍልሃልና ማንኛውንም ጽንፈኛ አቋም ተግባራዊ አድርግ ለሚሉ አይነት ቅስቀሳዎች ተጋላጭ ይሆናል፡፡ ü ኋላቀርነትም እንደዚሁ አንድን ህብረተሰብ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር እድል በመንፈግ ለተስፋ መቁረጥና ጽንፈኝነት ሊዳርገው ይችላል፡፡ ü ምሬቱ የከፋና ተስፍ የቆረጠ ህዝብ ባለበት ሁሉ ጽንፈኝነት ሲስፋፋ የምንመለከተው በዚህ ምክንያት ነው፡፡ ü ይህ አዲስ ግኝት ሳይሆን ድርጅታችን ቀደም ሲል ጀምሮ የተገነዘብነውና ለመፍትሄውም የታገለለት ጉዳይ ነው፡፡ ü ድርጅታችንና በርሱም የሚመራው ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ድህነትና ኋላቀርነት ጽንፈኝነትንና፣ ፀረ እኩልነት የሆኑ የትምክህትና ጠባብነት አዝማሚያዎችን ወዘተ ሊሸከም የሚችል ለም አፈር መሆኑን ታሳቢ በማድረግ በድህነትና ኋላቀርነት ላይ ጦርነት ካወጀ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ü ፈጣንና ብዙሃኑ ህዝቦች የሚቀጠሙበትን ልማት አስፋፍቷል፡፡ ü መሠረተ ሰፊና አሳታፊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ገንብቷል፡፡ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ቀጣይ ትግል አካሂዶ በመስኩ ከፍተኛ ድሎችን አስመዝግቧል፡፡ ü ይህም በመሆኑ ዛሬ አገራችን ከመቼውም ጊዜ በተለየ ሁኔታ በፈጣንና ህዝብ በሚጠቀምበት ዴሞክራሲያዊ የእድገት አቅጣጫ እየገሰገሰች ትገኛለት፡፡ ü እድገታችን ፈጣንና መሰረተ ሰፊ በመሆኑም የህዝቡን ተስፋ አለምልሟል፡፡ ü ዴሞክራሲያችን ብዝሃነትን በማወቅና በማክበር ላይ የተመሰረተ በመሆኑ በህዝቦች መካከል ፍቅርን መከባበርና መቻቻልን አጐልብቷል፡፡ ü የእርስ በርስ መናቆርና ከዚህም ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችል ተስፋ መቁረጥ መሰረት ተንዷል፡፡ ብዙ አገሮች በቀለም አብዮቶች ሲናጡና ከቀውስ ወደ ቀውስ ሲረማመዱ በአገራችን ሰላምና መረጋጋት እንደሰፈነ የቀጠለው በዚህ ምክንያት ነው፡፡ 2. ወጣቱን ከስራ አጥነትና ተስፋ መቁረጥ እንታደግ? ü አብዛኛውን ጊዜ በስሜት የሚያነሳሱ ጉዳዮች በቀላሉ ተጽዕኖ የሚያሳርፉት በወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ላይ ነው፡፡ ü በተለይ ወጣቱ ለስራ አጥነት፣ ጥራት ለሌለው ትምህርት፣ ከተደራጀ ፖለቲካዊ ተሳትፎ መገለልና ለመልከም አስተዳደር የሚያመች ሁኔታ ባልገጠመው ወቅት ስሜት ቀስቃሽ የሆኑ አቀራረቦች በደካማ ጐኑ ለመግባት የተሻለ እድል ያገኛሉ፡፡ ü በአገራችን በተለይ ከ97 ዓ/ም ድህረ ምርጫ ቀውስ በመማር የወጣቱን የልማትና የተጠቃሚነት፣ የመልካም አስተዳደርና የተሳትፎ ጥያቄዎች ለመመለስ ጥረት ያደረግነውና የተሳካ ውጤት ያገኘነውም በመሰረቱ ለስራ አጥነትና ለተስፋ መቁረጥ የተጋለጠ ወጣት ሊኖርበት የሚችለውን ተጋላጭነት በማስወገድ ንቁ የአገር ገንቢ ለማድረግ ነው፡፡ ü ወጣቱ ያለበትን የመነሻ ካፒታል ችግር በከፊልና የራሱን ተሳትፎ ባረጋገጠ አኳኋን ልንቀርፍለት፣ የመስሪያና የመሸጫ ቦታዎችን ገንብተን በማቅረብ ለልማታዊ ጥረቱ የተሻለ ሁኔታ ልናመቻችለት ይገባናል፡፡ ü በገጠርም በግብርናና ከግብርና ውጭ በሚካሄዱ ልማታዊ ሰራዎች ተሳትፎውንና ተጠቃሚነቱን ማረጋገጥ ይገባናል፡፡ ü ከዚህ ጐን ለጐን ወጣቱ ትውልድ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን በሚካሄደው ትግል ዋነኛ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ ተጠናከሮ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ ü ይህ ሲሆን ብቻ ነው ወጣቱ ሚዛናዊ አስተሳሰብ እንዲይዝ ለማድረግ የምናደርገውን አስተምህሮ በቅን ልቦና ተመልክቶ ሊቀበል የሚችለው፡፡ 3. የመንግስትና ፓርቲ አመራርን ሃይማኖታዊ ገለልተኝነት እናጠናክር፣ ü ህዝቡ ለመብቱና ለጥቅሙ የሚያደርገውን ትግል በትክክለኛ መስመር ለመምራት የተነሳው ድርጅታችንም ሆነ ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስታችን የብሄርና የሃይማኖት ልዩነት ሳያደርግ አላማውን የተቀበሉና መንግስታዊ ተልዕኮን ለመፈፀም ዝግጁ የሆኑ ታጋዮችንም ያሰባስባል፡፡ ü ይህም በመሆኑ ድርጅታችንም ሆነ ልማታዊ መንግስታችን የተለያዩ እምነቶች ተከታዮች የሚሳተፉባቸው ተቋማት እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡ ü ይህ መሠረታዊ የግል እምነትን የማክበርና የማስከበር ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ ድርጅታዊ አመራርን የማረጋገጥም ሆነ መንግስታዊ አገልግሎትን የመስጠት ጉዳይ ከሃይማኖት /ከራስህም እምነት ጭምር/ ገለልተኛ በሆነ መንገድ መካሄዱን ማረጋገጥ ይገባል፡፡ ü ዜጐችና የተለያዩ እምነት ተከታዮች ከድርጅት የሚያገኙት አመራርና ከመንግስት የሚያገኙት አገልግሎት በእኩልነት ከሀይማኖት ገለልተኛ በሆነ መንገድ ሊፈፀም ይገባዋል፡፡ ü በየደረጃው የሚገኙ ሀላፊዎች ከዚህ አኳያ በተጨባጭ ከሚፈፀሙ ገለልተኝነትን ለድርድር ከሚያቀርቡ ስህተቶች መጽዳታቸውን ማረጋገጥ ይገባል፡፡ 4. የህገ መንግስታዊና ሚዛናዊ አስተሳሰብ ትምህርትን ማስፋፋት፣ ü ሆን ብለውና እያወቁ በሀይማኖት ሽፋን የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ጥረት የሚያደርጉ ወገኖችን ከተሳሳተ አቅጣጫቸው በትምህርት መመለስ አይቻልም፡፡ ü እነዚህ ጥቅማቸውን በጥገኛ ወይም የኪራይ ሰብሳቢ መንገድ ለማሳካት የሚንቀሳቀሱና ለዚህም የቆረጡ ናቸው፡፡ ü ስለሆነም ተጋልጠው የፖለቲካ ተፅዕኖ የማሳረፍ አቅማቸው እንዲዳከምና የማታ ማታ ደግሞ ተነጥለው ወደ ዳርቻ እንዲገፉ /marginalized/ ማድረግ ብቻ የሚጠይቁ ወይም የሚፈልጉ ናቸው፡፡ ስለሆነም ስለህገ መንግስታዊና ሚዛናዊ አስተሳሰብ አስተምህሮ ስናነሳ ለእነዚህ እንደማይሆን በመገንዘብ ጭምር ነው፡፡ ü ህገ መንግስታዊና የሚዛናዊ አስተሳሰብ ትምህርት ከማንም በላይ የሚያስፈልገውና የሚጠቅመው ከልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ሂደቱ ተጠቃሚ ለሆኑት ብዙሃን ህዝቦች ነው፡፡ ü ስለሆነም ለራሳችን ማህበራዊ መሰረቶች በህገ መንግስታዊ ስርዓታችን ላይ ግልጽነት፣ እምነትና ስርዓቱን ከአደጋ የመጠበቅ ቁርጠኝነት እንዲያዳብሩ የሚያግዝ ትምህርት ልንሰጥ ይገባናል፡፡ ü እያንዳንዱ ዜጋ በማንኛውም ጉዳይ ላይ አቋም ከመውሰዱ በፊት ለምን? ለማንና መቼ? እንዴትና የት? ወዘተ የሚሉ መሠረታዊ ጥያቄዎችን በማንሳት መመርምር እንደሚገባው ማስተማር ይገባናል፡፡ ü እነዚህን ጥያቄዎች በማንሳት የህዝብንና የአገርን ጥቅም የሚጐዳን ማናቸውም ጉዳይ መቃወም፣ የሚጠቅመን ጉዳይ ደግሞ መደገፈ እንዳሚገባ ማስተማር ይገባል፡፡ ü ሌላው ሰው አድርጐታል በማለትና በመንጋ ቅኝት በመመራት አቋም መውሰድ እንደማይገባ ይልቁንም አያንዳንዱ ሰው ራሱን ችሎና በህሊናው አመዛዝኖ አቋም መውሰድ እንዳለበት ማስተማር ይገባናል፡፡ ü በአንድ በኩል ከእያንዳንዱ ሚዛናዊ አቋምና ተግባር በሌላ በኩል ደግሞ ከእያንዲንዱ ሚዛናዊነት የጐደለው አስተሳሰብና ተግባር ተፈላጊውን ትምህርት መስጠትና የሚዛናዊ አስተሳሰብን የበላይነት ማረጋገጥ ይገባናል፡፡ 5. በሃይማኖት ሽፋን የሚነግዱትን ሀይሎች በቀጣይነት ማጋለጥና መሰረት ማሳጣት፣ ü እነዚህ ተግባራት በትክክል ከተፈፀሙ አክራሪነትንና ጽንፈኝንት ከማሸነፍ አኳያ ረጅም ርቀት እንደሚወስዱን አያጠያይቅም፡፡ ይህም ሆኖ ብቻቸውን በቂ ናቸው ሊባሉ የሚችሉ አይደሉም፡፡ በሃይማኖት ሽፋን የሚነግዱ ጽንፈኞችን ሁሉ በማጋለጥ ትግል ሊደገፉ የሚገባቸው ናቸው፡፡ ከዚህ ትግል ውጭ የምናገኛቸው ውጤት ምሉዕነት ሊኖረው የሚችል አይደለም፡፡ ü ህዝቡ ህይወቱን በሚመለከቱ መሠረታዊ ጉዳያች ላይ ሁሉ ብቁ፣ ዝርዝርና ወቅታዊ መረጃ እንዲኖረው ማድረግ ነው፡፡ ü የመንግስትን እቅዶችና አፈፃፀም እንዲሁም በአፈፃፀም ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችና መልካም አጋጣሚዎችን የሚመለከት መረጃ ለህዝቡ በፍጥነትና በግልጽ ማቅረብ ይገባናል፡፡ ü ከዚህ አኳያ በየመስሪያ ቤቱና በየድርጅት ጽ/ቤቱ ያሉትን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊዎች አደረጃጀቶች በብቃት ማንቀሳቀስ ይጠበቅብናል፡፡ ü ይህን የማጋለጥና መሠረታቸውን የመናድ ስራ እየሰራን አስፈላጊ ሆኖ በተገኘበት ደረጃና መጠን ደግም ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ይገባናል፡፡ ü እነዚህን በተናጠልና በድምር በመፈፀም በሃይማኖት ሽፋን የሚካሄዱ አፍራሽና አክራሪ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን በተሟላ አኳኋን አይሳነንም፡፡

Monday, 25 November 2013

የዚህ ፅሁፍ ማጠንጠኛ የፖለቲካ አመለካከትን መተቸት አይደለም፤ ከዋና ዋና ሀገራዊ አጀንዳዎች ወረድ ያሉ የጉልበታሙን ስርዓት የሥራ አፈፃፀሞችን ማብጠልጠልም አይደለም፤ የተቀናቃኝ ፓርቲዎችን ስንክሳር መንቀስም… አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊ (አል-ሀበሽ) መሆን ለፈተና፣ ለመከራ፣ ለሰቆቃ… መዳረጉ የወለደው ብሶት እንጂ፤ መመረር-ማምረር ነው፡፡ …ይህ የእኛ ዕጣ ፈንታ የሆነበትን ምስጢር መመርመር ነው፡፡ ሰሞኑን የሳውዲ አረቢያ መንግስት ታጣቂዎች እና በድጎማ የሚያድሩ የሀገሬው ተወላጆች በመሰረቱት የጥፋት ግንባር ጉልበታቸውን ገብረው፣ በላብ በወዛቸው በሚያድሩ ስደተኛ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመው አረመኔያዊ ወንጀል፣ የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ልብ በከባድ ሀዘን የሰበረ፣ በቁጭት ያንገበገበ አሳዛኝ ፍፃሜ ሆኗል፡፡ ጭፍጨፋው ሃይማኖታዊው ጀሀድ ያወጀው አይደለም፤ ኢትዮጵያዊነት ባመጣው ዕዳ በድሃ ወንድም-እህቶቻችን ጀርባ ላይ ያረፈ ምህረት የለሽ ብትር እንጂ፡፡ …ይህ ግን ለምን ሆነ? ጥያቄ ነው፡፡ ርግጥ ነው፣ እንዲህ አይነቱ የእልቂት ነጋሪት መጎሰም ከጀመረ ዓመታት ነጉደዋል፤ መነሻ ሀገሩ ግን ሳውዲ አረቢያ ወይም ሊቢያ አይደለም፤ እዚሁ ኢትዮጵያችን ምድር ላይ እንጂ… ዘ-ፍጥረት… የየካቲቱ አብዮት ድንብዥታ (ሀንግኦቭር) ዛሬም ድረስ ዘመን ተጋሪዎቼን እያሳደደና እያሰደደ ይገኛል፡፡ ያኔ ያ ትውልድ ‹ኑ እንነሳ፣ ከተማውን እንውረር፤ አሮጌውንም ቅፅር በጩኸት አፍርሰን፣ አዲሱን እንፍጠር!› የሚል መለከት መንፋቱ ሙሉ ለሙሉ ስህተት ባይሆንም ‹የተጠሩ ብዙዎች፣ የተመረጡ ጥቂቶች› እንዲል መፅሀፉ፣ እፍኝ ለማይሞሉ ‹ምርጥ ወታደራዊ መኮንኖች› የተናጠል አሸናፊነት፣ የወል ተጠያቂ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ ስለምን ቢሉ? ስለተከሰተው ታሪክ ይሆናል መልሱ፡፡ በርግጥም ‹ፓርቲ› የሚባል የ‹ጦስ ዶሮ› ባነበረው ልዩነት በጥይት ደብድበው ሲያበቁ፣ አፈር ፈጭቶ፣ ውሃ ተራጭቶ ባደገበት መንደር እንደ መናኛ በየመንገዱ አስጥቶ ማዋል፣ ለግብዓተ መሬቱ የጥይት ዋጋ ማስከፈል፣ ወላጆችን እርም መከልከል… ከዚህ የከፋ ምን ሊያመጣ ኖሯል? …ከተኛበት አልጋ እያነቁ መስቀል፣ ከገሀነም በከፋው ቅጣት ‹ወፌ-ላላ› ገልብጦ ማሰቃየት፣ በአንድ ጉድጓድ ስልሳውን አነባብሮ መቅበር… ከዚህ ሌላ ምን ሊያስገኝ ኖሯል? …የሆነውም ይህ ነበር፡፡ እነሆም ያ ትውልድ የፀነሰው የተገነባውን መናድ፣ የተሰራውን ማፍረስ፣ በራስ ወገን ላይ መከራ ማዝነብን የሚመክረው የዘ-ፍጥረት መፅሀፍ ምዕራፍ እዚህ ጋ ነበረ የጀመረው፡፡ አዲስ ታሪክ አልተሰራም! ‹አዲስ ንጉስ እንጂ፣ ለውጥ መቼ መጣ!› እንዳለው ከያኒው፣ ታጋዮቹ በወታደሮቹ ቦታ ከተቀመጡ በኋላ የነበረው-እንደነበረው ነው የቀጠለው፤ ‹ባለሙያ› ገራፊዎች በአሸናፊዎቹ ከመተካታቸው በቀር፣ ማሰቃያ ጎሮኖቹ ዛሬም ወደ ሙዚየምነት አልተቀየሩም፣ መገረፊያው፣ መገልበጫው፣ መግደያው፣ መጋዣው… አሁንም የቀድሞውን ግልጋሎታቸውን እየሰጡ ነው፡፡ ማን ያውቃል? ነገም በዚሁ ይቀጥሉ ይሆናል፤ ለአጎራባች መንደሮች መቀጣጫ በሚል የጭካኔ ፈሊጥ፣የአማፅያን ኮሽታ የተሰማበትን መንደር ሁሉ ዶግ አመድ ማድረግም፣ የጄነራሎቻችን የጦር ‹ጠበብ›ነት መገለጫ ሆኖ ቀጥሏል፤ በሀውዜን፣ አርባ ጉጉ፣ አርሲ፣ ሐረር፣ ጋምቤላ፣ አዋሳ፣ ኦጋዴን፣ ቀብሪ-ደሀር፣ ደገ-ሀቡር… የፈሰሰው የግፉአን ደም፣ የተከሰከሰው የንፁሀን አጥንት ታሪክ ነጋሪ ጥቁር ሀውልት መሆኑን ማን ይክዳል? ይህንን ሁሉ ምድራዊ ፍዳ፣ ዓለም እንደ ማንኛውም አሳዛኝ ዜና ሰማው እንጂ፣ ሰለባዎቹን ለመታደግ ያደረገው እዚህ ግባ የሚባል እንቅስቃሴ አልነበረም፤ በራስ መንግስት፣ በራስ ወገን መናቅ፣ ክብር መነፈግ፣ ለ‹ምርኮኛ ሕግ› ማደር… ክፋቱ እዚህ ላይ ነው፡፡ የዛሬዎቹ አረቦቹም በወገኖቻችን ላይ የጭካኔ እጃቸውን እንዲያነሱ የልብ ልብ የሰጣቸው፣ ይኸው የእኛው የእርስ በእርስ አለመደጋገፍና አለመከባበር ነው፡፡ ትላንትና በጉራ ፈርዳና ቤንች ማጂ ዞን ጎሳ መመዘኛ ሆኖ ‹ውጡ የክልሉ ተወላጅ አይደላችሁም› በሚል በገዛ ወገኖቻቸው እንደጠላት ሀገር ሰው በጦር መሳሪያ ተከበው፣ ንብረታቸውን ሜዳ በትነው ስለተባረሩ ኢትዮጵውያኖች፣ የሰሙ አረቦች ‹ሳወዲያ አረቢያን ልቀቁና ውጡ› ብለው ይህ አይነቱን መዓት ቢያወርዱ ምን ይደንቃል? የባዕድ ሀገር ሰው የትንኝ ነፍስ ያህል እንኳ ሳይጨነቅ እንደዘበት ህይወታችንን ቢነጥቀን በእርሱ ላይ መፍረድ እንዴት ይቻለናል? አሳልፈው የሰጡን እነማን ሊሆኑ ነው? እመነኝ፣ በሳውዲ አረቢያ ጎዳናዎች የሰው ራስ ቅል እንደ በግ በመጥረቢያ ሲከሰከስ፣ እንደ ጦስ ዶሮ ተጋድሞ ሲታረድ፣ በቁሙ እሳት ሲለቀቅበት፣ ህፃናት የወታደር መለዮ በለበሱ አረመኔዎች ሲረገጡ… ልብህ እያለቀሰ፣ ፊትህ በእንባ እየታጠበ ያየኸው አይነት ጭካኔ ምንጩ ይህ ነው፤ ይህም ነው የኢትዮጵያን ሰው በአልባሌ ምክንያት መግደል፣ እያፏጩ ጉዞን የመቀጠል ያህል ያቀለለው፤ ለዚህም ነው በሙስሊሞች ቅድስቲቷ መዲና ላይ በድንጋጤ የጨው አምድ የሆነ አካለ-ቁመና፣ በሽብር ተውጣ አቅሏን የሳተች እህት፣ ስጋት ያናጠበው ወንድም ተመልክተህ በሀዘን የተቆራመድከው፤ ‹‹ወይኔ ወገኔ!›› ብለህ ደም እንባ የተራጨኸው፡፡ …እናስ! ለዚህ ሁሉ ጥፋት ተመጣጣኝ ዋጋ መክፈል ያለበት ማን ነው? ንጉሥ አብደላና ዕኩይ ተከታዮቹ ብቻ? ወይስ እንዲህ የፊጥኝ አስሮ ለአረብ ሀገራት መቀለጃ የዳረገህ መንግስትህም ጭምር? ከችጋርና ጭቆና ያልተፋታ ሕዝብ ዳቦና ነፃነት ፍለጋ እግሩ ወዳደረሰው ሀገር ተሰዶ መኖሩ በእኛ የተጀመረ አይደለም፤ እንዲያውም ስደተኞችን ካስተናገዱ ከመጀመሪያዎቹ ጥቂት የዓለም ሀገራት መካከል በግንባር ቀደምነት የምትጠቀሰው የእኛዋ የአቢሲኒያ ምድር ኢትዮጵያ ነች፡፡ የሩቁን ትተን እስከ የኃ/ስላሴ ስርዓት ፍፃሜ ድረስ የነበረውን ተጨባጭ ሁነት ብንመለከት እንኳ፣ ‹አረብ ቤት› በሚል ተቀፅላ የሚታወቁት ብዙዎቹ ሱቆችና የንግድ መደብሮች፣ በስደት መጥተው እኩል እንደ ዜጋ ሀገራችን መኖር በቻሉ አረቦች የተያዙ ነበሩ፡፡ የዛሬን አያድርገውና ይህች ገናና ሀገር ለሌሎች ሀገራት ሕዝቦች የነፃነትና የክብር ተምሳሌትም ነበረች፡፡ በመፅሀፍ ቅዱስም ሆነ በቅዱስ ቁርአን ውስጥ በፈሪሐ እግዚአብሔርነቷ፣ በፍትሐዊነቷና በርትዓዊነቷ ስሟ ተደጋግሞ የተወሳና የተመሰከረላት፣ የታላቅ ሕዝብ ታላቅ ሀገር ነበረች፡፡ ዛሬ በተፈጥሮ ማዕድን በልፅጋ የሀበሻ ስደተኞች መናኸሪያ ለመሆን በበቃችው ሳውዲ አረቢያ የተወለዱት ነብዩ መሀመድ የዛሬ 1400 ዓመታት ገደማ በስደት መጠለያነት የመረጧት፣ ሀገሪቷም ተከታዮቻቸውን እጇን ዘርግታ በመቀበል ከራሷ ዜጋ እኩል ተንከባክባ ያኖረቻቸው ስልጡን ሀገር ነበረች፡፡ ማን ነበረ ‹ወርቅ ላበደረ…› ያለው? እነሆም ዘመኑ ተቀያየረና ‹‹የኋላኞቹ ፊተኞች፣ የፊተኞቹ ኋለኞች›› ይሆኑ ዘንድ ግድ በማለቱ ዛሬ አብዛኞቹ የአረብ ሀገራ ኢኮኖሚያዊ ልዕልና እየተጎነፀፉ ሲመጡ፣ እኛ የኋሊት ተንሸራተን ቁልቁል ለመውረድ በቃን፡፡ ምንም እንኳ እነዛ ሁሉ መልካም መገለጫዎቻችን ዛሬም ድረስ ባናጣቸውም፣ በብሔር ክፍፍልና በእርስ በእርስ ሹኩቻ የተነሳ ግን በደህነት ማጥ ውስጥ ተዘፍቀን፣ እኛም በተራችን መሰደድ ዕጣ ክፍላችን ሆኖ ቀረ፡፡ ዛሬ አብዛኛው ወጣት በሀገሩ የመኖር ተስፋው በመሟጠጡ፣ በስደት ወጀብ የሚንገላታ፣ ማረፊያ እንዳጣች ወፍ ሲናወዝ መሽቶ የሚነጋለት ብኩን ሆኗል፡፡ በሀገሩ እጅግ ከመመረሩም የተነሳ ራሱን ለሻርክ ጥርስ፣ ለእንግልት፣ ለግርፊያና ለበልዓ-ሰቦች አሳልፎ እስከ መስጠት በሚያደርሰው የስደት ጉዞ ለማለፍ የማያመነታ ትውልድ ለመሆን ተገዷል፡፡ ይህ ከድህነት ወለል ስር ያሳደረን የዘመን ግርሻ፣ ይህ ከመንግስት ጋር አይንና ናጫ ያደረገን አምባገነናዊ አገዛዝ፣ ለዚህ ሁሉ አሳረ-መከራ ዳርጎን፣ ከሀፍረት ጋር አንገታችንን እስደፋን… ውለታን ከማስረሳቱም በላይ ለከፋ በደል አጋልጦ ቁጭት አስታቀፈን፡፡ ሰሞኑን ‹‹የበላችበትን ወጪት…›› ከሰበረችው ሳውዲ አረቢያ የተሰማው አሰቃቂ ዜናም የእዚህ የኢትዮጵያን ስደተኞች ተከታታይ ፍዳ ጉትያ ነው፡፡ እርግጥ አብዛኛው የአረብ ሀገራት መሬቱ ሰለጠነ እንጂ ሕዝቡ ገና ጨለማ ዘመን ውስጥ ነው፤ ሌላ ሌላውን ወደጎን ብለን የሰሞኑን አውሬአዊ ባህሪያቸው እንኳን እንደ አይነተኛ ማሳያ ልንወስደው እንችላለን፤ ይህ ድርጊትም እንሰሳዊ ባህሪያቸው የስነ-ዝግመት ለውጥን ገና አለማገባደዱን ያመለከተ ነው፡፡ ከአንድ ክፍለ ዘመን በፊት ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ምኒሊክ አድዋ ላይ፣ ያውም ሀገራቸውንና ዙፋናቸውን በጦር ኃይል ለመንጠቅ የጎመዠችው ሮም ያዘመተቻቸው ወታደሮች፣ እልፍ አእላፍ ሠራዊታቸውን ፈጅተው፣ የቅርብ ወዳጆቻቸው የሆኑ የጦር አበጋዞቻቸውን ገድለው የማታ ማታ የሽንፈትን ፅዋ አስጎንጭተው ከማረኳቸው በኋላ በርህራሄ ተንከባክበው እንደያዟቸው የዓለም ታሪክ ያውቀዋል፡፡ በሀገሩ ኑሮ አልቃና ብሎት፣ በሰው ምድር የሰው አደፋ አፅድቶ፣ ቆሻሻ ለቅሞ… ፋታ የማይሰጠውን የእህል ውሃ ጥያቄ ለመሙላት በማሰነ፣ ሆድቃን በሳንጃ መዘርገፍና የዱር አውሬ እንኳ የማይፈፅመው የጋርዮሽ ሴት ደፈራ መፈፀም… ምን አይነት ‹ኢብሊሳዊ› (ሠይጣናዊ) ተግባር ነው? የተቸነፈን መልሶ ማቸነፍ፣ የወደቀን መርገጥስ ‹ከመክፈር› (ፈጣሪን ከመካድ) በምን ይለያል? አሁንም እደግመዋለሁ፡- ይህ ፖለቲካ አይደለም፤ እየፈሰሰ ስላለ የንፁሀን ደም፣ የወላድ መሀን ስለሆኑ እናቶች፣ ጧሪ ቀባሪ ስላጡ የተራቡ አባቶች፣ አሳዳጊ አልባ ስለሆኑ ህፃናት፣ ያለሚስት ስለቀሩ አባወራዎች፣ ባላቸውን ስለተነጠቁ የቤት እመቤቶች … የሰቆቃ እሪታ ነው፡፡ በወጡበት ሰው ሀገር ላይ ወድቀው ስለሚቀሩ ወገኖቻችን ዋጋ ስለመጠየቅ ነው፤ ለነጋዴው መንግስታችን ኢትዮጵያዊው ዜጋ ዋጋው ስንት እንደሆነ የመሞገት ጉዳይ ነው፡፡ ሀገር ምን ማለት ነው? ‹ሀገር› የሚለውን ቃል የኢህአዴግ መራሹ-መንግስት መዝገበ ቃላት ምን ፍቺ ሰጥቶት ይሆን? ሉዓላዊነትስ በ‹አብዮታዊ ዲሞክራሲ› ቀዩ መፅሀፍ አንደምታው ምን ይሆን? …ቀለብ ሰፍረን የምናሳድረውን ሠራዊት ሞቋዶሾ ድረስ ልኮ፣ የባራክ ኦባማን ስጋት ማቃለል? በ‹ተባበሩት መንግስታት› ስም የሲ.አይ.ኤ ቅጥረኛ ሆኖ በሱዳናዊያን የውስጥ ችግር ላይ-ታች እንዲማስን ማድረግ? የሕዝብ ደህንነት መ/ቤትስ ኃላፊነቱ የእናንተንና የቅምጦቻችሁን ደህንነትና ምቾት መጠበቅ ነውን? የአምባሳደሮቻችን የሥራ ድርሻ ፓስፖርት ማደስና የመግቢያ ፍቃድ መስጠት ብቻ ነው? በስደተኛ ወገኖቻችን ላይ ‹ጊንጥ ሰላይ› መሆን? ቦንድ መሸጥ? ‹ኢህአዴግ ጌታ ነው› እያሉ መስበክ? …ወይስ የዜጎችንም ደህንነት መከታተልና መጠበቅንም ጭምር? …ይህ ነው የወቅቱ ዓብይ ጥያቄ፡፡ የዲፕሎማሲ ግንኙነትስ ምን ማለት ነው? አገዛዙ በአንድ ወቅት ተቀማጭነቱ ኳታር-ዶሀ የሆነው ‹አልጄዚራ› ቴሌቪዥን ‹ስሜን አጠፋ› በሚል የኳታርን ኢምባሲ እንደ ዘጋው አይነት ስራን ብቻ የሚመለከት ይሆን? ከዋነኞቹ ለጋሽ ሀገራት በግንባር ቀደምነት የምትመደበው ኖርዌይስ ኢምባሲዋ የተዘጋው ለማን ትርፍ ነበር? ለብሔራዊ ጥቅም መቆርቆርስ ‹ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት አልተከበረም› ብለው ዘገባ ባወጡ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ላይ ያንን ሁሉ አቧራ ማስነሳት ይሆን? ሌላው ቢቀር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለምን እንደ ተመሰረተ ይዘነጋል? አባቶቻችን ኮሪያና ኮንጎ ድረስ የዘመቱት ለዓለም ዜጎች ሰላም መሆኑስ እንዴት ይረሳል? የድርጅቱ አባል ሀገራት የፈረሙት ስምምነትስ የሳውዲ አረቢያን ሽፍትነት እንኳ ለመከላከል አቅም አይኖረውም? በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት እልፍ አእላፍ ወታደሮቻችን ካለቁብን በኋላ ከባረንቱ የተመለስነው፣ ባድሜ ላይ የቆምነው፣ በዛላንበሳ የታገድነው… የማንን ሕግ አክብረን ነበር? ያውም ‹በስለላ ስራ ሊሰማሩ ይችላሉ› ተብለው የተጠረጠሩ ኤርትራውያን እንዲያ በክብርና በእንክብካቤ ወደ ትውልድ ሀገራቸው የተሸኙት፣ በጦር ሜዳ የተሸነፈው ሻዕቢያ ተፈርቶ ነበር እንዴ? …ይህ ነው እንቆቅልሹ፡፡ ዛሬስ መንግስታችን የስደተኛ ዜጎችን ደህንነት በምልዓት የማይከታተለውና የድረሱልኝ ጩኸታቸውን ሰምቶ ፈጥኖ እጁን የማይዘረጋላቸው ለምን ይሆን? ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ ሆኖበት? ወይስ በለመደው የንቀት መነፅር አይቶ እንዳላየ በቸልተኛነት አልፎት ነውን? በርግጥ ይህንን የበደል ማማ ካለፈው ታሪኩ አንፃር ከገመገምነው ምክንያቱ ሀገራዊ ስሜቱ ደካማና ከሥልጣኑ ሌላ ምንም የሚያሳስበው ነገር ባለመኖሩ ብቻ እንደሆነ ይገባናል፡፡ ሌላው ቀርቶ ሠማያዊ ፓርቲ የአረቦቹን ወደር የለሽ ጭካኔ ለማውገዝ በሳውዲ አረቢያ ኢምባሲ በር አጠገብ የጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ ያገደው ‹ይህ አይነቱ ሀገራዊ መቆርቆር ነገ ደግሞ መስቀል አደባባይን በሕዝብ ሱናሚ ለማጥለቅለቅ መነቃቃት የሚፈጥር ገፊ ምክንያት ሊሆን ይችላል› ብሎ በስጋት ስለተጠፈነገ ይመስለኛል፡፡ የሆነው ሆኖ የመንግስት ህልውናም ሆነ አቅም በእንዲህ አይነቱ ወቅት ነውና የሚፈተነው ኢህአዴግም በዚህ ተግባሩ ዜጎቹን የመታደግ ገት እንዳሌለው አስመስክሯል፡፡ መቼም በሲ.አይ.ኤ ተላላኪነቱ በ‹ዋይት ሀውስ› ማህደረ-መዝገብ ውስጥ ከጊዜ ጊዜ እየዳጎሰ የመጣው የ‹ውለታ›ው ዶሴ ለእንዲህ አይነቱ ፈታኝ ወቅት መሆን ይሳነዋል ማለት ይከብዳል፡፡ ሼክ መሀመድ አላሙዲንን ጨምሮ ጥቂት የማይባሉ የሳውዲ ነጋዴዎች፣ ሀገራችን ውስጥ በበርካታ የንግድ ዘርፎች ተሰማርተው አትርፈው ማደራቸው፣ በሰፋፊ እርሻዎች ዘርተው ማጨዳቸውስ እንደምን ተዘነጋ? ይህ ቢያንስ በነፍስ-ውጪ ነፍስ-ግቢ ለተያዙ ወገኖቻችን እንዴት የመደራደሪያ ጉልበት መፍጠር ሳይችል ቀረ? …በርግጥ መለስ ዜናዊ በ2004 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ከጎራ ፈርዳ ስላፈናቀላቸው አማርኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን በተጠየቀበት ጊዜ ‹‹ደን ጨፍጫፊዎች ናቸው›› ሲል የስላቅ መልስ እንደሰጠው ሁሉ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኀኖምም የሳውዲውን እልቂት በተመለከተ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርቦ ‹‹የማባረር ሥራው በኢትዮጵያውያን ላይ ብቻ ያነጣጠረ እንዳልነበረ ተረድተናል›› በማለት መቀለዱ፣ ስርዓቱ ‹አስተዳድረዋለሁ› ከሚለው ሕዝብ ይልቅ ሥልጣኑንና ተያይዘው የሚመጡ ጥቅሞቹን በዜጎች ሕይወት ጭምር ተደራድሮ ከማስከበር እንደማይመለስ የሚያሳይ ይመስለኛል፡፡ እንደ መንግስት በሀገር ሀብት እንደአሻው እየተምነሸነሸ፣ ‹ግዴታዬ የባቡር መንገድና ኮንዶሚንየም ቤት መስራት ብቻ ነው› ማለቱ ይህንኑ ይመሰክራል፡፡ አሊያማ ፋሺስቱ ጣሊያን እንዲያ በርካታ ድልድዮች፣ መንገዶች፣ ቤቶች… ገንብቶ ሲያበቃ፣ ‹ሀገር› ማለት ሕዝብ የሰፈረበት ሉዓላዊ ግዛት ማለት ነው ተብሎ ያ ሁሉ መስዕዋትነት ተከፍሎ በኃይል እንዲባረር ባልተደረገ ነበር፡፡ ‹ሕዝቤን ልቀቅ!› በዘመነ-ኦሪት በግብፅ ዙፋን ላይ በተፈራረቁ ፈርኦኖች፣ ለባርነት የተዳረጉ ዕብራዊያንን ነፃ ያወጣ ዘንድ በፈጣሪ ተመርጦ የተላከው ሙሴ ‹‹እግዚአብሄር ‹ያመልከኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ!› ብሎሀል›› ማለቱ በቅዱሳት መፃህፍት መገለፁ እውነት ነው፡፡ በዚህ ዘመን ደግሞ ራሱን ‹ኢህአዴግ› ሲል በሚጠራው ‹አምሳለ-ፈርኦን› ለመከራና ለሀፍረት የተዳረጉ ሕዝቦች አርነት ይጎናፀፉ ዘንድ ‹የሙሴ ያለህ!› የሚለው ጩኸታቸው ከተራራ ተራራ እያስተጋባ መሆኑ ሌላ እውነታ ነው፡፡ በሳውዲ አረቢያ የግፍ ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵውያን ደምም ዋይታ እየተበራከተ ነው፤ ስርዓቱ እንዲህ አይነቱ ሰቆቃን ለፖለቲካ ትርፍ እየተጠቀመበት መሆኑንም ሰሞኑን የመንግስት እና ደጋፊዎቹ ሚዲያዎች የሚያሰራጩትን ዘገባ መመልከት በቂ ነው፡፡ መቼም መሬት ልሰው፣ አፈር ቅመው ያፈሩትን ንብረት ተነጥቀው፣ ባዶአቸውን እየተመለሱ ያሉ ስደተኞችን ‹በሀገራችን መስራት ይሻለን ነበር› እንዲሉ ማስገደድ ለርካሽ ፖለቲካዊ ትርፍ ካልሆነ በቀር ሌላ ትርጉም የለውም፡፡ አስከፊው ድህነታችን ጉርሻ እስከ መግዛት፣ ከቆሻሻ ገንዳ ውስጥ ቅልጥም እስከ መምጠጥ፣ የወደቀ ምግብ ከውሻ ጋር ተጋፍቶ እስከ መመገብ… በደረሰበት በዚህ የችጋር ዘመናችን ላይ በምን አመክንዮ፣ ከየትኛው ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ተመዝኖ ሊታመን ይችላል ተብሎ ነው ‹ሀገር ውስጥ ሰርቶ በሰላም መኖር ይቻላል› የሚለው ተራ ፕሮፓጋንዳ ነጋ-ጠባ የሚደሰኮረው? ምንድር ነውስ የሚሰራው? እዚህ እኛ ሀገር የማንን መፀዳጃ ቤት ንጽህና መጠበቅ ይሆን የአረቦቹን ያህል ዳጎስ ያለ ክፍያ ማስገኘት ቀርቶ፣ በቀን ሁለቴ ለመብላት የሚያግደረድረው? ቅጥ አንባሩን ያጣው የግብር ፖሊሲያችን፣ እንጀራ ቸርቻሪዎችን ሳይቀር አሳድዶ የእለት ጉርሻቸውን እየነጠቀና በተንሰራፈው ድህነት ላይ ተጨማሪ እልቂት አውጆ ድሆችን ለማጥፋት ሰይፉን በሚያወናጭፍበት በዚህ ወቅት፣ ወጣቱ እንዴት ብሎ ነው በሀገሩ ሰርቶ መኖር ይችላል የሚባለው? ገና ጀንበር ከማዘቅዘቋ ጎዳናውን የሚያጥለቀልቁት ህፃናት ሴተኛ አዳሪዎችንስ ምን እንበላቸው? የትኛው ተቀጣሪስ ነው በደሞዙ የወር ቀለቡን ሳይሳቀቅ መሸመት የቻለው? …ሁላችንም የመዳፋችንን ያህል አብጠርጥረን የምናውቀው በመሬት ያለው ተጨባጭ እውነታ ይህ ነው፡፡ እነሆም በመጨረሻ እንዲህ ማለት ወደድኩ፡- ስርዓቱ ሰባኪው እንዳለው ‹የከንቱ ከንቱ፣ ከንቱ› ቢሆንም፣ አቶ መለስ ዜናዊ በኤርትራ የመጀመሪያው የነፃነት ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ ተገኝቶ በአስመራ ሳባ ስታዲዮም ለተሰበሰበው ህዝብ በደርግ የደረሰባቸውን በደል በማስታወስ ‹‹በእናንተ ጀርባ ላይ ያለው ጠባሳ በእኛም ላይ አለ›› ሲል ሀዘኑንና መቆርቆሩን እንደገፀላቸው ሁሉ፣ በሳውዲ አረቢያ የግፍ ሰለባ የሆናችሁ ወንድም-እህቶቼ ሆይ! የእናንተ ሰቆቃና በደል፣ በእኛም ግንባር ላይ ተቸክችኮ ሀፍረታችችንና ውድቀታችንን የጋራ እንዳደረገው የታሪክ ፍርድን መጠበቁ አይቀሬ ነው፡፡ እመኑኝ ያች ዕለትም አብረን የምንነሳበት፣ ከፍ ብለን የምንበርበት ትሆናለች፡፡› ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

Sunday, 24 November 2013

What the heck was that ? Are they serious ?shame on you all!!!!

“እኔ ራሴ ስድስት ያበዱ ሴቶችን ይዤ መጥቻለሁ..” ራውዳ ጀማል – ከሳዑዲ ተመላሽ ኢትዮጵያዊት (ቃለ ምልልስ)

በሃገር ቤት እየታተመ የሚወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሃገራቸው ከተመለሱ ኢትዮጵያውያን ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል። ቃለ ምልልሱ ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም ትዘግባቸው የነበሩ የሳዑዲ ሕይወቶችን የሚያጠናክሩ በመሆናቸው ጋዜጠኛ አበባየሁ ገበያው ያደረገችውን ቃለምልልስ ለአንባቢዎቻችን እንደወረደ ይኸው፦ ራውዳ ጀማል ትባላለች፡፡ የሃያ ዓመት ወጣት ናት፡፡ ስለራስዋም ሆነ በሳኡዲ ስላሉ ኢትዮጵያውያን ወቅታዊ ሁኔታ ስታወራ እያለቀሰችና እየተወራጨች ነው፡፡ ለማነጋገር ስቀርባት “ወንድ ከሆናችሁ ጋዜጠኞች ነን፣ የህዝብ አፍ ነን ካላችሁ፤ እዚህ ተቀምጣችሁ፣ “ሁለት ሰው ሞተ” እያላችሁ ከምታቅራሩ ሳኡዲ ሂዱና በየቀኑ ሁለት ሶስት ሰው የሚሞትበትን እልቂት ተመልከቱ፣ “ሰዎቹን ምን እየሰራችሁ ነው?” ብላችሁም ጠይቁልን” አለችኝ። መቅረፀ ድምፄን ሶስት አራት ጊዜ ያስጠፋችኝ ቢሆንም በመጨረሻ ግን ለቃለ ምልልስ ፈቃደኛ ሆነችልኝ፡፡ ስንት ዓመት ቆይተሽ መምጣትሽ ነው? ከሁለት ዓመት በኋላ ነው የመጣሁት፡፡ እስከ አስረኛ ክፍል የተማርኩት አዲስ አበባ ቢሆንም፤ የኮምቦልቻ ልጅ ነኝ፡፡ እንዴት ነበር የሄድሽው? በፓስፖርት… በኮንትራት ነበር የሄድኩት … ካላስ! የሰውየው ልጆች ግን “የማይሆን” ፊልም ተመልከቺ እያሉ ያስቸግሩኝ ነበር፡፡ ሲመረኝ ጠፍቼ ወጣሁ፡፡ ከዚያም ከጓደኞቼ ጋር በነፃነት ቤት ተከራይተን እየኖርን፣ በ1800 ሪያል ተቀጥሬ መስራት ጀመርኩኝ፡፡ ቤተሰቤንም ገንዘብ እየላኩ እረዳ ነበር፡፡ ወደ አገርሽ እንዴት ተመለስሽ? ውጡ ሲባል… ረብሻ ሲነሳ.. ጓደኞቻችን ሲሞቱ.. ሲደፈሩብን.. ‘ድሮም ስደተኛ ክብር የለውም’ ብዬ ተመልሼ መጣሁ..ከሚገሉኝ ከሚያበለሻሹኝ ብዬ እጄን ሰጠሁ፡፡ ብዙ ኢትዮጵውያኖች ችግር ላይ ናቸው.. እባካችሁ ድረሱላቸው፡፡ ብርዱም ፀሃዩም ሲፈራረቅባቸው.. ያሳዝናሉ፡፡ ብዙ ያልመጡ አሉ፤ መምጣት እየፈለጉ፡፡ ስቃይ ላይ ናቸው፡፡ እኔ አሁን አስራ ሶስት ቀን ታስሬ ነው የመጣሁት፡፡ እስቲ ስለ እስሩ ንገሪኝ … ሁለት ቀን ያለ ምግብ ያለ ውሃ ነው የታሰርነው። ከዛ በኋላ ግን ጥሩ ምግብ ሰጥተውናል፣ ጥሩ መኝታም አግኝተናል፡፡ ብዙዎቹ ግን ከእኛ የባሰ ችግር ላይ ናቸው፡፡ መጠለያ ያላገኙ አሉ… ኤምባሲያችንም አይሰማም እንጂ ስንት ጊዜ ደውለን ተናግረናል መሰለሽ፡፡ ግን የሚሰማ የለም፡፡ ከአገራችን ውጡ ካሉ በኋላ ትዕግስት ያጡና መልሰው ይዩዙናል፡፡ በዛን ጊዜ አበሻው፣ ሻንዛ/ጩቤ ይመዛል፡፡ ፖሊስ ራሱን ለማዳን ይተኩሳል። እኔ እንደውም ደህና ነኝ፤ እዛ ላሉት ድረሱላቸው። በምድረ ዱርዬ እየተደፈሩ ነው ያሉት /ለቅሶ/ ስንት ህፃናት አሉ የሚሞቱ፣ የሚታመሙ፡፡ ስንመጣ ደሞ፤ ሻንጣ አትያዙ ተብለን ተመናጭቀን…በጥፊ ተመትተን..መከራችንን በልተናል፡፡ ወንዶችና ሴቶች ለብቻ ነበር የተቀመጣችሁት? የተቀመጣችሁት አትበይ! የታሰራችሁት በይ፡፡ … የሴት እስር ቤት ለብቻው ነው በሴቶችና በህፃናት ለቅሶ የተሞላ ነው፡፡ እኔ ራሴ ስድስት ያበዱ ሴቶችን ይዤ መጥቻለሁ…/ለቅሶ/ አሁን ቤተሰብ እየጠበቅሽ ነው? ነበረ ግን ሻንጣዬ ጠፋብኝ፡፡ በርግጥ ጤነኛ ሆኖ መምጣትም ቀላል አይደለም፡፡ እዛ ያሉትን ጥለናቸው ስንመጣ እያለቀስን ነው፡፡ እስር ቤቱ ውስጥ አንድ እርጉዝ ሞታብናለች፡፡ እዛው እስር ቤት እያለን ምጥዋ መጣ፤ ግን የህክምና እርዳታ ባለማግኘትዋ ሞተች፡፡ እስር ቤት ያሉት ምን ያህል ይሆናሉ? ሰማኒያ ክፍል አለ..በየክፍሉ ስልሳ አምስት ስልሳ አምስት ሰው ነው ያለው፡፡ መካሲመሺ እስር ቤት ይባላል፡፡ የወንድና የሴት እስር ቤት የተራራቀ ነው፡፡ በጣም ረጅም ከመሆኑ የተነሳ በመኪና እንጂ በእግር አይሞከርም፡፡ በአሁኑ ሰዓት በከተማው ያለው እስር ቤት ሞልቶ የመዝናኛና የስብሰባ አዳራሹን ሁሉ እስር ቤት አድርገውታል፡፡ የተደፈሩት የሞቱት..ሴቶች ብዙ ናቸው፡፡ አንዷን እርጉዝ ለሶስት ሲደፍሯት ሞታለች፡፡ የሌሎች አገር ስደተኞችም እየወጡ ነው ተብሏል… አዎ፡፡ ኢትዮጵያዊው ከበደሉ ብዛት የተነሳ እየተናነቀው እኮ ነው ግጭቱ የሚከረው፡፡ ሚስቱን እህቱን ከእጁ መንትፈው ሊወስዱበት ሲሉ ነው ጦርነት የሚነሳው፡፡ አበሻ ወንድ እየሞተ ያለው ‹‹ሴቶቻችንን አትንኩብን..›› ስለሚል እኮ ነው፡፡ ኤምባሲው ሊደርስላቸው ይገባል፡፡ ምንጭ ዘ-ሐበሻ

Ethiopian migrants victimised in Saudi Arabia

The recent appalling events in Saudi Arabia have brought thousands of impassioned Ethiopians living inside the country and overseas onto the streets. ethi.migr.in saudi Racism and hate running through the streets In the last 10 days persecution of Ethiopian migrant workers in Saudi Arabia has escalated. Men and women are forced from their homes by mobs of civilians and dragged through the streets of Riyadh and Jeddah. Distressing videos of Ethiopian men being mercilessly beaten, kicked and punched have circulated the Internet and triggered worldwide protests by members of the Ethiopian diaspora as well as outraged civilians in Ethiopia. Women report being raped, many repeatedly, by vigilantes and Saudi police. Ethiopian Satellite Television (ESAT), has received reports of fifty deaths and states that thousands living with or without visas have been detained awaiting repatriation. Imprisoned, many relay experiences of torture and violent beatings. Earlier this year the Saudi authorities announced plans to purge the kingdom of illegal migrants. In July, King Abdullah extended the deadline for them to “regularize their residency and employment status” [from 3 rd July] to November 4th [HRW]. Obtain the correct visa documentation, or risk arrest, imprisonment and/or repatriation. On 6th November, Inter Press Service (IPS) reports, Saudi police, “rounded up more than 4,000 illegal foreign workers at the start of a nationwide crackdown,“ undertaken in an attempt (the authorities say), to reduce the 12% unemployment rate “creating more jobs for locals”. Leading up to the “crackdown” many visa-less migrants left the country: nearly a million Bangladeshis, Indians, Filipinos, Nepalis, Pakistanis and Yemenis are estimated to have left the country in the past three months. More than 30,000 Yemenis have reportedly crossed to their home country in the past two weeks,” and around 23,000 Ethiopian men and women have “surrendered to Saudi authorities” [BBC]. Most news sources are funded by corporations and investors. Their goal is to drive people to advertisers while pushing the corporate agenda. NationofChange is a 501(c)3 organization funded almost 100% from its readers–you! Our only accountability is to the public. Click here to make a generous donation. The police and civilian vigilante gangs are victimizing Ethiopian migrants, residing with and without visas; the “crackdown” has provided the police and certain sectors of the civilian population with an excuse to attack Ethiopians. Press TV reports that “Saudi police killed three Ethiopian migrant workers in the impoverished neighborhood of Manfuhah in the capital, Riyadh, where thousands of African workers, mostly Ethiopians, were waiting for buses to take them to deportation centers.” Hundreds have been arrested and report being tortured: “we are kept in a concentration camp, we do not get enough food and drink, when we defend our sisters from being raped, they beat and kill us,” a migrant named Kedir, told ESAT TV. Women seeking refuge within the Ethiopian consulate tell of being abducted from the building by Saudi men and raped. ESAT, reports that several thousand migrants have been transported by trucks to unknown destinations outside the cities. Whilst the repatriation of illegal migrants is lawful, the Saudi authorities do not have the right to act violently; beating, torturing and raping vulnerable, frightened people: people, who wish simply to work in order to support their families. The abuse that has overflowed from the homes where domestic workers are employed onto the streets of the capital reflects the wide-ranging abuse suffered by migrant workers of all nationalities in Saudi Arabia and throughout the Gulf States. Trail of abuse This explosion of state sponsored violence against Ethiopians highlights the plight of thousands of migrant workers in Saudi Arabia. They tell of physical, sexual and psychological abuse at the hands of employers, agents and family members. The draconian Kafala sponsorship system, (which grants ownership of migrants to their sponsor), together with poor or non-existent labour laws, endemic racism and gender prejudice, creates an environment in which extreme mistreatment has become commonplace in the oil-rich kingdom. There are over nine million migrant workers in Saudi Arabia, that’s 30% of the population. They come from poor backgrounds in Sri Lanka, the Philippines, Indonesia and Ethiopia and make up “more than half the work force. The country would grind to an embarrassing stand still without their daily toil. “Many suffer multiple abuses and labor exploitation [including withholding of wages, excessive working hours and confinement], sometimes amounting to slavery-like conditions”, Human Rights Watch (HRW) states. The level of abuse of domestic workers is hard to judge: their isolation combined with total control exerted by employers, together with government indifference, means the vast majority of cases go unreported. Until August this year there was no law covering domestic abuse. Legislation has been passed: however, the authorities, HRW reports “are yet to make clear which agencies will police the new law…without effective mechanisms to punish domestic abuse, this law is merely ink on paper.” All pressure needs to be exerted on the rulers of Saudi Arabia to ensure the law is implemented and enforced so victims of domestic violence feel it is safe to come forward. Ethiopian governments negligence Whilst thousands of its nationals are detained, beaten, killed and raped, the Ethiopian government hangs its negligent head in silence in Addis Ababa, does not act to protect or swiftly repatriate their nationals, and criminalises those protesting in Addis Ababa against the Saudi actions. Although freedom to protest is enshrined within the Ethiopian constitution (a liberal minded, largely ignored document written by the incumbent party), dissent and public demonstrations, if not publicly outlawed, are actively discouraged by the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) regime. In response to the brutal treatment meted out by the Saudi police and gangs of vigilantes in Riyadh and Jeddah, outraged civilians in Addis Ababa staged a protest outside the Saudi Embassy, only to be confronted by their own police force, wielding batons and beating demonstrators. Al Jazeera reports that police “arrested dozens of people outside the Saudi embassy [in Addis Ababa] in a crackdown on demonstrators protesting against targeted attacks on Ethiopians in Saudi Arabia.” A senior member of The Blue Party, Getaneh Balcha was one of over 100 people arrested for peacefully protesting. The government’s justification, rolled out to defend yet another suppressive response to a democratic display, was to assert that the protest “was an illegal demonstration, they had not got a permit from the appropriate office”: petty bureaucraticnonsense, hiding the undemocratic truth that the government does not want public protests of any kind on the streets of its cities: effectively, freedom of assembly is banned in Ethiopia. The protestors, he said, “were fomenting anti-Arab sentiments here among Ethiopians.” Given the brutal treatment of Ethiopians in Saudi Arabia, anger and anti-Saudi sentiment (not anti Arab) is, one would imagine understandable, and should be shared by the Ethiopian government. The people of Ethiopia are living under a duplicitous highly repressive regime. The EPRDF consistently demonstrates it’s total indifference to the needs and human rights of the people. Freedom of expression, political dissent and public assembly is denied by a regime that is committing a plethora of human rights violations in various parts of the country, atrocities constituting in certain regions crimes against humanity. In fact, according to Genocide Watch, the Ethiopian government is committing genocide in the Somali region, as well as on the “Anuak, Oromo and Omo” ethnic groups (or tribes). The recent appalling events in Saudi Arabia have brought thousands of impassioned Ethiopians living inside the country and overseas onto the streets. This powerful worldwide action presents a tremendous opportunity for the people to unite, to demand their rights through peaceful demonstrations and to call with one voice for change within their beloved country. The time to act is now, as a wise man has rightly said, “nothing happens by itself, man must act and implement his will”.

Friday, 22 November 2013

23 ዓመት የተገነባ የበደል ውጤት ።

ወያኔ ኢትዬጵያዊነትን ትርጉም ኣልባ ለማድረግ ገና ከመነሻው፣ ከጥንስሱ አስከዛሬዋ ቀን ድረስ የክፋትን ድር ኣያደራ ፣የሚፈራውን አያስፈራራ፣አያሰረ፣አየገደለ፣አያሳደደ ወዘተ ዜጎች በሀገራቸው ላይ ባሪያ ሆነወ አንዲኖሩ አያፈነ ኢትዬፒያዊ ጀግንነት እና የኢትዬጵያን ክብር የትላነት ታሪከ አነዲሆነ አየጣረ ነው ። ዛሬ ዛሬ ኢትዬጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር የሚለውን ኣባባል ስሰማ ውሰጤ ትልቅ ጥያቄ ይፈጠራል አውነት ዛሬ ሀገራችን ከነክብርዋ ኣለች ? ኣባቶች ወኔኣቸው ጠፍቶ ለዝምታ አጅ ከሰጡ ፣ አናቶች ፍት ህ በማጣት ኣንገታቸውን ከደፉ ፣ ኣህቶች የሴትነት ክብራቸው ተገፎ ለኣረብ መጫወቻነት ከተሸጡ ፣ ኣንድ ትውልድ አውነት ሳይሰማ ካድገ ፣ገበሬው ማረሻው ተነጥቆ አጆቹ ለልመና ከተዘረጉ የኢትዮጵያን ክብር የምናየው ማን ላይ ነው ፣ዘላለማዊት ኢትዮጵያን የምንመኘው ለየትኛው ትውልድ ነው ? በወያኔ የኣገዛዘ ዘመን ሀገራችን ላይ ችግሮች መልካቸውን አየቅያየሩ ህዝቡን ሲደቁሱት ኖረዋል ዛሬም አያየነው ነው ። የዘረ ማጥፋት ወንጀል፣ ዜጎች በኣደባባይ በግፍ መገደል፣ የተቃዋሚ ፓርቲ ኣባላት ፣ደጋፊዎቻቸው አና ጋዜጠኞች ያለፍት ህ መታሰር ፣ ነዋሪዎች ከቀዬኣቸው መፈናቀል.... ወዘተ ። አነዚህ አና የመሳሰሉ ሀገራችን ላይ የሚፈጸሙት ግፎች ሰሞነኛ ወሬ ሆነው ሳይፈቱ አስከዛሬ ኣሉ ፣ዛሬም ወገኖቻችን ላይ በኣረብ ሀገራት አየደረሰ ያለው ስቃይ አና አንግልት ወያኔ ለዜጎች አና ለሀገራችን ያለው ንቅት የወለደው ነው (ባለቤት የናቀው ኣሞሌ........ ) አንዲሉ ኢትዮጵያዊነት አንደወንል የሚቅጠርበት ጊዜ ላይ ደርሰን ወገኖቻችን የወያኔን የግፍ ጅራፍ ሸሽተው በተሰደዱ በባአደ ሀገራት አስር ቤት ታጉረው ፣ በየኣደባባዩ ሬሳቸው ወድቆ ደማቸው ደመከለብ ሆኖዋል ። በወያኔ ኣገዛዝ የሰረኣቱ ዋነኛ ተጎጂ የሆኑት ሴቶች ናቸው ። በ1000 የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ለጉለበት ስራ በህገወጥ መንገድ ወደኣረብ ሀገራት ይሰደዳሉ ፣ በሀገራቸው ሰርተው መለወጥ አንዳይችሉ በመንገስት ኣካላት የሚደርሰባቸው የሰባዊ መብተ ረገጣ መፍትሄ ማጣት አና የጭቆናው ምሬት ስደት ብቻኛ ምርጫቸው አንዲሆን ያስገድ ዳቸዋል ። አብዛኞቹ ኣድሜኣቸው ከ18 በታች የሆኑ ህጻናት ከኣቅም በላይ በሆነ ያጉልበት ስራ በቀን ከ 18 ሰዓት በላይ አንዲሰሩ ይገደዳሉ ፣በኣሰሪዎቻቸው በተደጋጋሚ ይደፈራሉ፣ ይደበደባሉ ይገደላሉ ፤ የሚደርስባቸው ስቃይ ከኣቅማቸው በላይ የሆነባቸው ብዙዎች ለኣይምሮ ችግር ተዳርገው በየጎዳናው ወድቀዋል ፤ ሰሚ ያጡ ዋይታዎች ፣ድብደባ መቛቛም ያቃታቸው ፣ በመደፈር ብዛት የደከሙ የጨቅላ ገላዎች ፣ በደል የበዛባቸው ብዙ አህቶች አራሳቸውን ከፎቅ በመወርወር ፣ መርዝ በመጠጣት ፣ በመታነቅ ሂወታቸውን ያጠፋሉ። ይህ ሁሉ የአንድ ቀን ምሬት ፣የ አንድ ሰሞን ብስጭት የፈጠረው አይደለም 23 ዓመት የተገነባ የበደል ውጤት ነው ።

ኦባንግ – ከዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር እየሠራሁ ነው አሉ

በሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ፈር የለቀቀ አስነዋሪ ግፍ ዓለምአቀፍ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ሌሎች ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ጋር እየሠሩ መሆናቸውን አቶ ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ፡፡ የሳዑዲ ልዑል ሰብዓዊነት የረገፈበትንና በግፍ የተሞላ የወሮበላ ተግባር የሚፈጸምበትን አሰቃቂ ተግባር የሚከናውኑትን አንጋቾች አሞካሹ፡፡ ያለ አንዳች ልዩነት ኢትዮጵያውያን በኅብረት ድምጻቸውን በማሰማት እየተቃወሙት ያለውን ኢሰብዓዊ ተግባር አስመልክቶ በተለያዩ መንገዶች ይፋ ከሆኑት በተጨማሪ ድብቅ መረጃዎች እየተሰበሰቡ መሆናቸውን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አስታውቀዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ የጋራ ንቅናቄው ከዓለምአቀፍ የመብት ተቋማት ጋር በቅርበት እየተሰራ ስላለው ዝርዝር ጉዳይ ግን ከሁኔታው ምስጢራዊነት አኳያ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ “አልዘገዩም” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም “አኢጋን ችግር በተከሰተ ቁጥር የሚቋቋምና የሚፈርስ የዕቁብ ይዘት ያለው ድርጅት አይደለም፡፡ ወይም እሣት ሲነሳ ድምጽ እያሰማ እንደሚከንፍ የእሣት አደጋ መኪና የሚመሰል ድርጅት አይደለም” በማለት የጋራ ንቅናቄውን የተጠና አካሄድ በመጠቆም የመለሱት አቶ ኦባንግ ይህ ችግር እንደሚከሰት አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡ ችግሩ አስቀድሞ እንደሚከሰት ቢታወቅም ምላሽ የሚሰጥ ብቃት ያለው አካል ባለመኖሩ አንገት የሚያስደፋና ኃፍረት የሚላብስ፤ “አገር አለኝ ወይ?” የሚል ጥያቄ የሚያስነሳ በኢትዮጵያ ታሪክ ተሰምቶና ታይቶ የማይታወቅ ኃፍረት ሊደርስብን ችሏል፡፡ “ይሁን እንጂ” አሉ ኦባንግ “ይህ መራር ዜና ከተሰማበት ሰዓት ጀምሮ የጋራ ንቅናቄው የበኩሉን” ሲያደርግ መቆየቱን አመልክተዋል፡፡ “ከተለያዩ ዓለምአቀፋዊ ተቋማት፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ አግባብ ካላቸው መንግሥታዊ አካላትና በተለያየ ደረጃ ላይ ከሚገኙ የሳዑዲ ባለስልጣናት ጋር ተነጋግረናል” በማለት አቶ ኦባንግ ተናግረዋል፡፡ ለዓብነት ያህልም የሳዑዲ ም/ጠ/ሚ/ር እና የመከላከያ ሚ/ር፣ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር፣ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚ/ር፣ የፍትሕ ሚ/ር እና ሌሎች ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን የመንግሥት መ/ቤቶችን ጨምሮ በአውሮጳና በሰሜን አሜሪካ የሚገኙትን የሳዑዲ ኤምባሲዎችን እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽነርን፣ የአፍሪካ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ACHPR)፣ ወዘተ ማነጋገራቸውንና በየደረጃውም ምላሽ ማግኘታቸውን አመልክተዋል፡፡ በመላው የመካከለኛው ምስራቅ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ዕረፍት የሚሰጥ እንዳልሆነ የጠቆሙት “ጥቁሩ ሰው” ሳዑዲ ካላትና ከምትከተለው “የበርህን ዝጋ ፖሊሲ” አንጻር በአካል በቦታው ላይ ከመገኘት ይልቅ አቅም ካላቸው ዓለምአቀፋዊ አካላት ጋር በአፋጣኝና በቅርበት መሥራቱ ድርጅታቸው የወሰደው አማራጭ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የሎጂስቲክሱ ጉዳይ መስመር ሲይዝም የጋራ ንቅናቄው ከዚህ በፊት በየአገራቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይ ሲያስፈጽምበት የነበረውንና በውጤታማነቱ የሚታወቀውን አማራጭ እንደሚተገብር ጨምረው ገልጸዋል፡፡ ኢህአዴግ አገርን እንደሚያስተዳድር ድርጅት በዜጎቹ ላይ እየደረሰ ያለውን አስነዋሪ ተግባር ትኩረት ሰጥቶ አለመመከቱ ተቃውሞ አስነስቷል፡፡ ይህንኑ አስመልክቶ አቶ ኦባንግ ሜቶ “ወገኖቻችንን ድንበር በማሻገርና ኤጀንሲ ከፍተው ወደ አረብ አገራት ሲልኩ የነበሩት ሁሉ ሕግ ፊት ቀርበው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ የተለያዩ ተግባራት” እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ alamudi-ሼክ መሐመድ አላሙዲ የሠራተኛ ኃይል ወደ ሳዑዲ እንዲላክ ከኢህአዴግ ጋር በይፋ ስምምነት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡ ኢንቨስትመንትን በተመለከተ ከሚፈልጉበት ክልል መሬት ለመውሰድ፣ ከሚፈልጉበት ባንክ ኮሪደር ገንዘብ ለመበደር ገደብ የሌላቸውና በሞቀበት ሁሉ ባለመጥፋት በጀት መድበው በሚያስተዳድሯቸው ሚዲያዎች እንዲሁም አንደበታቸውን በሙስና ላሰሯቸው ባለሥልጣናት “ኢትዮጵያዊ ነኝ” እያሉ በተገኙበት ቦታ ሁሉ ለሚዲያ ፍጆታ የሚደሰኩሩትና ግጥም የሚያስደረድሩት ሼክ መሐመድ አላሙዲ፣ “ወገኔ” የሚሉት ሕዝብ በአባታቸው አገር ወሮበሎች ሲያልቅና ሲጨፈጨፍ ዝም ማለታቸው ኢንቨስትመንቶቻቸውን ጥያቄ ውስጥ ከትቷል፡፡ አንዳንዶች እንደሚሉት ይህ አሰቃቂ ድርጊት መስመር ለቅቆ ከመውጣቱ በፊት የሳዑዲ አረቢያ ዜጎችን ከርስ እንዲሞላ በኢትዮጵያ የተቋቋመው ሳዑዲ ስታር ኩባንያ በገንዘብ እጥረት ሊዘጋ እንደሚችል መዘገቡ የሚታወስ ነው፡፡ በወቅቱ ሪፖርተር ባወጣው ዘገባ ሳዑዲ ስታር በኪሣራ ወደ መዘጋት መድረሱ የኩባንያው “ባለቤት የሆኑትን ሼክ ሙሐመድ አል አሙዲንና የሳዑዲ ዓረቢያን ስም የሚያጎድፍ ከመሆኑም ባሻገር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እስኪታክት የተወራለት ይህ ፕሮጀክት መና መቅረቱ ሁለቱን አካላት በሕዝቡ ዘንድ ለከፍተኛ ትችትና ወቀሳ እንደሚያጋልጣቸውም” ጠቁሞ ነበር፡፡ mohammed bin nayef ልዑል ሞሐመድ ቢን ናይፍ በአሁኑ ጊዜ “ሕገወጥ ናችሁ” በሚል ሰብዓዊነት የጎደው እርምጃ እየተወሰደባቸው ያለው የበርካታ አገራት ዜጎች በተለይም ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመውን ሰቅጣጭ ተግባር ሕገወጦችን የማባረር “ዘመቻ” በማለት ያቃለሉት የሳዑዲው አገር ውስጥ ሚ/ር ልዑል ሞሐመድ ቢን ናይፍ ወንጀለኛ ሬንጀር ለባሾችን፣ ፖሊሶችንና ወሮበሎቹን ሸባቦች አደፋፍረዋል፡፡ “ዘመቻው ይቀጥላል … በተወሰነ ጊዜ የተገደበ አይደለም” በማለት “እስክንጨርስ እንጨርሳችኋለን” የሚመስል የማፊያ መሪ መሰል መልዕክት ለአንጋቾቻቸው አስተላልፈዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን በሕጋዊነት የሚኖሩትም ጭምር በሳዑዲ ያለው ሁኔታ አሳሳቢነት ወደፊት ችግር ውስጥ ሊከትታቸው እንደሚችል በመገመት ወደ አገራቸው መመለስ ይፈልጋሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት ለከፍተኛ ሰቆቃ የተጋለጡት ኢትዮጵያውያን “ቤት አለን ቤታችን መልሱ” እያሉ የሰቆቃና የድረሱልን ጥሪ በሚያስተላልፉበት ወቅት ሰብዓዊነት የጎደላቸው የኢህአዴግ መሪዎች ይህ ነው የሚባል አፋጣኝ ምላሽ መስጠት አለመቻላቸው “በእርግጥ ኢትዮጵያውያን አገር አላቸው?” ብሎ የሚያስጠይቅ እንደሆነ በርካታዎች የሚጋሩት ነው፡፡ አቶ ኦባንግ በበኩላቸውም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአንድ ሳምንት ሥራውን አቋርጦ እንኳን ቢሆን ስደተኞቹን ባፋጣኝ የማመላለስ ተግባር መፈጸም ይገባው ነበር በማለት ቁጭታቸውን ተናግረዋል፡፡ ዜጎች በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ህይወታቸው እየተቀጠፈ “3ሺህ ዛሬ ገቡ … ድምሩ 10ሺህ ሆኗል …” የሚል የሞላ ጎደለ ቁማር ዓይነት ጨዋታ በትዊተር መጫወት የቴድሮስ አድሃኖምን ዘመነኛነት ሳይሆን ለሰውልጅ ህይወት ያላቸውን ደንታቢስነት የሚያሳይ መሆኑን ሁኔታው ያስቆጣቸው አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ አቶ ኦባንግም “ቤቴ መልሱኝ” ብሎ ለሚለምን አንድ ዜጋ የተከፈለው ተከፍሎ ትራንፖርት በማቅረብ ክቡር ህይወትን በአስቸኳይ ለመታደግ አለመቻል ለትውልድ የሚተላለፍ የታሪክ ጠባሳ መሆኑን በአጽዕኖት ተናግረዋል፡፡ ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

በሳዉዲ የኢትዮጵያውን ስቃይ ያስነሳዉ ተቃዉሞ

ሳዉድ አረቢያ በሚገኙ ዜጎች ላይ የሚፈፀመዉን ጥቃት በመቃወም ከመላ ጀርመን የተሰባሰቡ በርካታ ኢትዮጵያውያን ዛሬ በበርሊን ከተማ ሰልፍ አካሄዱሰልፈኞቹ የሳውዲ መንግሥት የወሰደውን ርምጃ የሚያወግዙ መፈክሮች በማሰማት ርምጃው እንዲያበቃ ጠይቀዋል። ከሰልፉ አዘጋጂዎች መካከል አንዱ የሆኑትን አቶ በላይነህ ተሾመን ስለሰልፉ በስልክ አነጋግሬያቸዋለሁ። የፓሪሱንም ሰልፍ ወኪላችን ሀይማኖት ጥሩነህ ተከታትላዋለች።

ሰማያዊ ፓርቲ፣ የዜጎችን ሰቆቃ እና በደል ችላ ማለት ከግፈኞች ጋር እንደመተባበበር ይቆጠራል!!

ሰማያዊ ፓርቲ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎቻችን ላይ የሳውዲ መንግስት እያደረሰ ያለውን እስራት፣ ስቃይ እና ግድያ በመቃወም እና ህይወታቸው ላለፈ፣ ለተደበደቡ እንዲሁም የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ህዝቡ ሃዘኑን እንዲገልጽ በመጪው እሁድ በሚደረገው ታላቁ ሩጫ ላይ የሚሮጡ ተሳታፊዎች ጥቁር ሪቫን አድርገው እንዲሮጡ ጥሪ ማስተላለፉ የሚታወቅ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የታላቁ ሩጫ አስተባባሪዎች ይህንን ጥሪ እንደሚቃወሙት እና በፕሮግራሙም ላይ ጥቁር ሪቫን ያሰረ ተሳታፊን እንደተሳታፊ እንደማይቆጥሩ መናገራቸው ፓርቲያችንን እጅግ አሳዝኖታል፡፡ ፓርቲያችን ይህንን ጥሪ ሲያስተላልፍ አላማው ፍጹም ፖለቲካዊ አንድምታ የሌለው ሲሆን ጥያቄውም በዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እና ግድያ እንዲቆም እና ፍትሃዊ እርምጃም እንዲወሰድ ለመጠየቅ ብቻ እና ብቻ እንጂ ሌላ አላማ እንደሌለው እየታወቀ የታላቁ ሩጫ አስተባባሪዎች ግን ጉዳዩ ከፖለቲካ ጋር ለማያያዝ መሞከራቸው የሚያስተዛዝብ እና ህዝባዊ ወገንተኝነታቸውን ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው፡፡ ስፖርት ሰላማዊ ነገር የሚሰበክበት እንዲሁም እኩይ ተግባራት የሚወገዙበት መድረክ ነው፡፡ በአለማችን ላይ በተለያዩ ጊዜያት በተከሰቱ አሰቃቂ ሰው ሰራሽ አደጋዎች በተለያዩ ስፖርታዊ ዝግጅቶች ላይ ሲወገዙ እንዲሁም ለሰለባዎች ሃዘን የመግለጽ ስነ ስርዓትና የህሊና ጸሎት ሲደረግ መመልከት የተለመደ ነው፡፡ ታዲያ በጠራራ ፀሀይ በአደባባይ እናት ልጆችዋ ፊት እንዲሁም ሴት ልጅ ቤተሰቦችዋ ፊት ስትደፈር ከማየት የዘለለ ምን እኩይ ተግባርስ ሊኖር ነው? ታዲያ ስፖርት ይህንን ካላወገዘ ምንን ሊያወግዝ ነው? በመጨረሻም የታላቁ ሩጫ አስተባባሪዎች የፓርቲውን ጥሪ መቃወማቸው ፓርቲያችንን ያሳዘነ እና ያስቆጣ መሆኑን እየገለጽን አሁንም ፓርቲያችን በድጋሜ በዝግጅቱ ላይ ተሳታፊዎች ጥቁር ሪቫን አድርገው እንዲሮጡ እየጠየቀ ጥቁር ሪቫኖችን ማግኘት ለማትችሉ በሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ተገኝታችሁ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡ ክብር ለዜጎቻችን ይሁን!!

Thursday, 21 November 2013

አሁንም የድረሱልን ጥሪ ከሳዑዲ አረቢያ እስር ቤት (Video)

(ዘ-ሐበሻ) ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን እንዳጓጓዘ ቢገልጽም አሁንም በሳዑዲ ያሉ እህቶች በቪድዮ የተደገፈ ስቃያቸውን ለዓለም እያሰሙ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ይድረስልን እያሉ የሚናገሩት እነዚሁ እህቶች ለ2 እና ለ3 ወራት እስር ቤት እንደቆዩም ይናገራሉ። አንዳንድ የደረሱን መረጃዎች ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት ቅድሚያ ሰጥቶ ወደ ሃገር እያሳፈረ ያለው የስርዓቱ ደጋፊ የሆኑ፣ ኢምባሲው በሚጠራቸው ስብሰባዎች የሚገኙ፣ ገንዘብ በሙስና ለሚከፍሉ ነው የሚሉና ሌሎችም ናቸው። አንድ ዜጋ የመንግስትን አገልግሎት ለማግኘት የግድ የመንግስት ስብሰባዎች ላይ መገኘትና የነርሱን ፖለቲካ አቀንቃኝ መሆን የለበትም፤ መንግስትን መደገፍም መቃወምም የሰው ልጅ መብት ሲሆን መንግስት ደግሞ የሚጠላውንም የሚወደውንም የማገልገል ሃላፊነት አለበት። ሕሊና ያለው መንግስት የሚያስበው ይህን ነው። የእህቶቻችንን ጥሪ ይመልከቱ፦ http://www.zehabesha.com/

ልበ ሙሉ ጀግና

http://www.ginbot7.org/Audio/audio/Zemene_Kasse_with_G7_radio_nov2013.mp3

Wednesday, 20 November 2013

ዶ/ር ቴዎድሮስና ሌሎቹ – ግርማ ጌታቸው ካሳ

ኢሕአዴግን እንደ አንድ የሚመለከቱ፣ ሁሉን አባላቶቹን በጅምላ የሚፈርጁ ጥቂቶች አይደሉም። ነገር ግን ኢሕአዴግ ውስጥ የተለያዩ ቡድኖች አሉ። አንዱ የገነባውን አንዱ ያፈርሳል። አንዱ ሲያነሳ አንዱ ይጥላል። አንዱ ሰላማዊ ሰልፍ ሲፈቅድ፣ አንዱ በጎን የዜጎችን ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት ይጋፋል። አንዱ የታሰሩ የሕሊና እስረኖች እንዲፈቱ ሲፈልግ፣ ሌላው “እዚያው ቃሊቲ ይበስብሱ” ይላል። አንዱ በጎና ቀና ሕሊና ሲኖረው፣ ሌላው ደግሞ የጠመመና የጫካ አስተሳሰብ ያለው ሆኖ ይገኛል። በኢሕአዴግ ውስጥ ያለው ተቃርኖ ሰሞኑን በጉልህ ለማየት ችያለሁ። ነገሩ እንዲህ ነው። በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን አሳዛኝ ግፍ ለመቃወም፣ በአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያውያን ወደ ሳዑዲ ኤምባሲ ያመራሉ። ወዲያው የደህንነት ሰራተኞች ባዙቃቸውን እና ዱላቸውን ይዘው፣ ሰልፉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከማድረግ ይልቅ፣ ሰልፈኞችን መደብደብ ጀመሩ። ብዙዎች ታሰሩ። ሰልፉ፣ የደህንነት ሰራተኞችና ፖሊሶች ሳይቀሩ ሊቀላቀሉት የሚገባ ሰልፍ ነበር። በሰልፉ የተነሳው ጉዳይ፣ ኢትዮጵያውያንን በሙሉ ያዋረደ ጉዳይ ነው። ነገር ግን፣ የዜጎቻችን መብት ተረግጦ በሳዑዲ የተፈጸመውን ድብደባ ለመቃወም፣ በአገሩ የወጣው ሕዝባችን ተደብድቦ ተመለሰ። በዚህ ጉዳይ ላይ፣ አልጀዚራ እንደዘገበው፣ የኢሕአዴግ መንግሥት ቃለ አቀባይ፣ አቶ ሽመለስ ከማል፣ አስተያየት ሰጥተውበታል። “ሰላማዊ ሰልፉ ሕገ-ወጥ ነው። ፍቃድ አልተሰጣቸውም። በኢትዮጵያዊያን መካከል ፀረ-ዐረብ ስሜት (anti-Arab sentiments) እንዲኖር ለማድረግ እየሞከሩ ነው። ስለዚህ ፖሊስ እርምጃ ወስዷል” ነበር ያሉት።(1) አቶ ሽመልስ እንዲህ ማለታቸውን ከአልጀዚራ ዘገባ ሳነብ፣ ልክ ወላፈን በፊቴ ያለፈ ይመስል በጣም ደነገጥኩኝ። ለማመን አልቻልኩም። ደቂቃዎች እያለፉ፣ ፍም ላይ እንደተጣደ ምጣድ፣ ውስጤ መንደድ ጀመረ። የኢትዮጵያውያን ስሜት ተጎድቶ ባለበት ወቅት፣ ቆስለን ባለንበት ወቅት፣ ግፍ ለፈጸሙብን ዐረቦች ስሜት የምንቆረቆርበት ጊዜ ነውን? ይህ አይነቱ የኢትዮያውያንን ስሜት ክፉኛ የሚጎዳ አስተያየት ከአንድ ኢትዮጵያዊ ነኝ ከሚል፣ ያውም የመንግሥት ባለሥልጣን፣ ይጠበቃልን? በእውኑ እንዲህ አይነት፣ ለሕዝብ ስሜትና ክብር ፍጹም ደንታ የሌላቸው ሰዎች ናቸውን የሚገዙን? “በቂ የጥበቃ ኃይል እንዲኖር ዝግጅት ስላላደረግን፣ ሕዝቡም በንዴት ውስጥ ስለሆነ፣ የሳዑዲ ኤምባሲን የማቃጠል ተግባር ሊፈጸም ይችላል” የሚል ስጋት ኖሯቸው ሊሆን ይችላል፣ ሰልፉን በኃይል ያስቆሙት። ነገር ግን አንድ የዘነጉት ጉዳይ ቢኖር የኢትዮጵያ ሕዝብ ጨዋ ሕዝብ መሆኑን ነው። ላለፉት 5 ወራት በተለያዩ የአገራችን ግዛቶች በርካታ ሰልፎች መደረጋቸውን ማስታወስ እፈልጋለሁ። አንድም ድንጋይ አልተወረወረም። አንዲትም ንብረት አልጠፋችም። እንደውም በደሴ ሰልፈኞቹ ለፖሊስ አበባ ያድሉ ነበር። በርግጥ ሕዝባችን የተከበረ፣ የሚያኮራ፣ ጨዋ ህዝብ ነው። አገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎች ሰልፍ ለማድረግ፣ በሕጉ መሰረት ባለሥስልጣናት ቢያሳውቁም፣ አሁንም ሕገ መንግሥቱ ተንዶ፣ ሰልፍ ማድረግ እንደማይችሉ ነው በደብዳቤ የተነገራቸው። እንኳን ሌሎች ድርጅቶች ሰልፍ ሲጠሩ መከልከል ቀርቶ፣ በዚህ አንገብጋቢ አገራዊ ጉዳይ፣ እራሱ ኢሕአዴግ ሰልፍ መጥራት ነበረበት። የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር የሆኑት አቶ ሰይፉ ኃይሉ፣ በቅርቡ በለቀቁት ጽሁፍ “why not the government has arranged even public demonstration at least in our major cities to condemn the event and send message to the world?” ሲሉ ነበር የጠየቁት።(2) አሁን ደግሞ ወደ ሌላ የኢሕአዴግ ባለሥልጣን ልውሰዳችሁ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድርስ አዳኖም። ኅዳር 6 ቀን 2006 ዓ.ም. ዶ/ር ቴዎድሮስ፣ ከሳዑዲ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን ጊዜያዊ ማረፊያ ድረስ በመሄድ እንዳጽናኑና እንዳበረታቱ ፋና ዘግቧል። በርግጠኝነት ማረጋገጥ አልቻልኩም፣ ግን ዶክተሩ፣ ስደተኞች፣ የአገራቸውን መሬት በአይሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው እንደተቀበሏቸው የሚገልጹ አንዳንድ አስተያየቶች ፌስቡክ ላይ አንብቤያለሁ። ከአጥር አልፎ ሕዝብ ጋር መቀላቀል ማለት ይሄ ነው!! ቅዳሜ ኅዳር 7 ቀን ዶ/ር ቴዎድሮስ፣ አዲስ አበበ በተደረገ ሦስተኛው የዓለም አቀፍ ፋሚሊ ፕላኒንግ ኮንፍራንስ ላይ ያደረጉትን ንግግርም ማንሳት እፈልጋለሁ። “ዜጎቻችን ወደ አገር ሲመለሱ፣ ነገሮች በተስተካከለ ሁኔት እንዲሄዱ ለማድረግ እንሞክራለን። ሳዑዲዎች ሕገ-ወጥ ናቸው (ከአገር ውጡልን) ቢሏቸው፣ ግድ የለም፤ የሚሄዱበት አገር አላቸው። አጠንክሬ ላረጋግጥላችሁ፣ ዜጎቻችን በአክብሮት እንቀበላቸዋለን” ነበር ያሉት። ከአንድ ጨዋ፣ የተማረ፣ በሳል መሪ የሚጠበቅ ግሩም ንግግር! በአቶ ሽመልስ ከማል አይነቶቹ የደማው ልቤ ትንሽ ታደሰ። ምን አለ ኢሕአዴግ እራሱን ከሽመልስ ከማሎች አጽድቶ ቴዎድሮስ አዳኖሞችን ቢያበዛ? ምን አለ ባለሥልጣናቱ የሚሰብርና ለሕዝብ ንቀት የሞላበት ንግግር ከሚናገሩ፣ የሚያሰባብስ፣ የሚያንጽ፣ የሚገነባ ንግግር ቢናገሩ? ምን አለ ዜጎችን በማሰቃየት፣ በመደብደብ፣ ሽብርተኞች እያሉ በማሰር፣ በማንገላታት ከሚደሰቱ፣ ዜጎች ሲጠቁ ማዘን ቢጀመሩ? ምን አለ እንደ እንስሳ ከሚሆኑ እንደ ሰው ቢሆኑ? እንግዲህ እነቴዎዶሮስ አዳኖም የሚያረጉትን እያበረታታን፣ የተለየ ትዕዛዝ እየላኩ፣ ዜጎችን የሚያስደበድቡ፣ የዜጎችን መብት የሚረግጡና በዜጎች መጎሳቆል የሚደሰቱ፣ የአገዛዙ ባለሥልጣናትን ለማጥራት ሁላችንም ተባብረን መስራት ይኖርብናል። እነዚህ ግለሰቦች ለኢሕአዴግም ሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እርግማን ናቸው!!!! አገራችንን እንዲያምሱና እንዲያወኩ ሊፈቀድላቸው አይገባም። በተለይም የኢሕአዴግ ደጋፊዎች እነዚህ ሰዎች የድርጅታቸው ጠንቅ፣ ድርጅታቸው የበለጠ እንዲጠላ የሚያደርጉ መሆናቸውን አውቀቁ፣ እነርሱ ላይ ዘመቻ እንዲጀምሩ አሳስባለሁ። በመጨረሻ አንድ ነገር ጣል ላድርግና ላቁም። በዚህ ወቅት የ”ጠቅላይ ሚኒስትራችን” ኃይለማርያም ደስአለኝ መሰወር ነው። እኝህ ሰው ዝምታን ለምን መረጡ? ጋዜጠኛ ወሰንሰገድ፣ “አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ “እስረኛ” ናቸው” በሚል አውራምባ ታይምስ ላይ ባወጣው ጽሁፉ፣ ጠቅላይ ሚኒስተሩ የሕዝብን ትርታ እንዲያዳምጡ፣ ከአማካሪዎቻቸው አጥር እንዲወጡ፣ እንደመሪ አገር መምራት እንዲጀምሩ ጥሪ አቅርቧል።(3) ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም በ3ኛው የአፍሮ-ዐረብ ስብሰባ ላይ ለመገኘት (ሳዑዲዎችም ያሉበት) ወደ ኩዌት ትላንት ኅዳር 10 ቀን 2006 ዓ.ም. አምርተዋል። ከዚያ በኋላ ደግሞ በቀጥታ የተባበሩት መንግሥት ክላይሜት ቼንጅ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ወደ ዋርሶው ፖላንድ ያመራሉ። (የዓለማችን የአየር ሁኔታ በወገኖቻችን ላይ ከደረሰው ግፍ በልጦ ማለት ነው) አቶ ኃይለማርያም የተማሩ ሰው ናቸው። በዚህ ወቅት ከአገር ምንም አይነት መግለጫ ሳይሰጡ፣ ሕዝቡን ሳያበረታቱ፣ ከአገር ውጭ መውጣታቸው፣ ምን ያህል ተሰሚነታቸውን እንደሚጎዳ ያጡታል ብዬ አላስብም። ታዲያ ምን ነክቷቸው ነው እራሳቸውን እንደዚህ የሚያገምቱት? ወደፊት በስፋት የምንነጋገርበት ይሆናል። ግርማ ጌታቸው ካሳ muziky68@yahoo.com ኅዳር 11 ቀን 2006 ዓ.ም (1) http://ethioforum.org/arrests-at-anti-saudi-protest-in-ethiopia-aljazeera/ (2) http://aigaforum.com/articles/what-we-learn-saudi-ethio.php (3) http://www.awrambatimes.com/?p=10948

Sunday, 17 November 2013

ወያኔ የግንቦት ሰባት መሪዎችን ለመግደል ያሰሬዉ ሴራ በመክሸፉ የኢትዮጵያ ህዝብ ደስተዉን እየገለጸ ነዉ

በወያኔው መረጃና ደህንነት ሃለፊ ጌታቸው አሰፋ እና በሃይለማሪያም ደሳለኝ አማካሪ ጸጋየ በርሄ ቁጥጥር የተመራና በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌና በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል መሪዎች ላይ የተቀነባበረው የግድያ ሙከራ መክሸፉን ተከትሎ ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ከሚገመተው በላይ ሰርጎ ገቦችን ለመከላከል የሚያስችል የሰውም ሆነ የቴክኖሎጂ አቅም ያለው መሆኑን አስመስክሯል የሚሉ ተበራክተዋል። ይህን ሃሳብ የሚደግፉ ወገኖች ባንድ በኩል የፋሽስት ወያኔ አመራሮች ምንም እንኳ ከፍተኛ የስልጣን እርከን ላይ ነው ያለነው ቢሉም ምን ያህል የተዋረደና የቀለለ ስራ ለመስራት እንደሚደፍሩ በግልጽ በራሳቸው አንደበት የሰማንበትና ያወቅንበት ነው ሲሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ራሱን ለመከላከል የሚያስችለውን ቴክኖሎጂያዊ አቅም መገንባቱንና ይህም ለሀገራችንና ነጻነት ለጠማው ሕዝባችን ታላቅ ተስፋ ሰጭ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። ሌሎች በጉዳዩ የተደሰቱ ወገኖች ደግሞ ፋሽስት ወያኔ ከዚህ በፊትም ለገንዘብና ለስልጣን የሚጓጋጉ ለሕዝብ ልእልና ደንታ የሌላቸው እና ለማይገኝ ባዶ ምኞት የሞቱ ሆዳሞችን በመግዛት ስንት የሕዝብ ተሰፋ እንቅስቃሴዎችን እንዳደናቀፉ አስታውሰው ይህ ግን ልዩ ነበር ካሉ በሗላ ወያኔዎች የት ደረጃ ላይ እንዳሉና አቅማቸውም እስከምን ድረስ እንደሆነ አወቅንበት ይላሉ። ከዚህ በፊት በተለይ በ1997 ዓ/ም የነበረውን ምርጫ ቅንጅት ቢያሸንፍም ፋሽስት ወያኔ ገልብጦ ሁሉን ለራሱ በማድረግ እንዲጫወት እገዛ ያደረጉለት የሕዝብ ወገን ነን እያሉ በመደለል በሆዳቸውና በሌሎች ጥቅማጥቅሞች የተገዙ ከሃዲዎች እንደነበሩ አይዘነጋም። source ginbot7.org

Friday, 15 November 2013

የኢትዮጵያን መንግስት ለፍርድ ለማቅረብ ከተነሱት ስዊድናዊ ጠበቃ ጋር ውይይት ተደረገ

ቅዳሜ ኖቬምበር 2 ቀን 2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ መድረክ በስዊድን የወያኔን መንግስት በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለማቅረብ የተጀመረውን ክስ መነሻ በማድረግ የክሱን ሂደት ከሚመሩት ከስዊድናዊው ጠበቃ ከስቴላ ያርዴና ከሌሎች እንግዶች ጋር በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ወይይት አደረገ። million ም/ኢኒስፔክተር ሚሊዮን ብሩ ውይይቱ ከቀኑ 14፡00 ሰዓት የተጀመረ ሲሆን ውይይቱን የከፈቱት የመድረኩ ሊቀ መንበር ም/ኢኒስፔክተር ሚሊዮን ብሩ ናቸው። ኢኒስፔክተር ሚሊዮን በንግግራቸው መክፈቻ ጥሪ የተደረገላቸውን እንግዶችና ተሰብሳቢውን ህዝብ አመስግነው መድረኩ የተቋቋመበት ዓላማ በሀገር ውስጥና በውጪ የሚደረገውን የነጻነት ትግል የተደራጀ መልክ ይዞ የሚጓዝበት መንገድ ለማመቻቸትና በየጊዜውም ይህንን መሰል ውይይት በማድረግ ትግሉን ለመርዳት መሆኑን ገልጸው የዛሬውንም ስብሰባ የዚህ መነሻ እንደሆነ አስታውቀዋል። ዶ/ር ሙሉዓለም አዳም ዶ/ር ሙሉዓለም አዳም ከሳቸው በመቀጠል መድረኩን እንዲመሩ የተጋበዙት ጋዜጠኛ ወንድማገኝ ጋሹ፤ ዶ/ር ሙሉዓለም አዳምን የመጀመሪያው ተናጋሪ አድርገው ጋብዘዋል። ዶ/ር ሙሉዓለም የመድረኩን አዘጋጆች አመስግነው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በአስከፊ ሁኔታ ላይ መውደቁን ሙስናውም እያደረ መባባሱን የመንግስት ባለስልጣኖች ወደ ውጪ የሚያሸሹት ገንዘብ እየናረ መሄዱን ገልጸዋል። እንዲሁም የዘር ፖለቲካ እየተስፋፋ መሄዱን፣ የስለላ መዋቅሩም መጠናከሩንና ህዝቡን መግቢያ መውጫ ማሳጣቱን ከዚያም አልፎ በውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ድረስ መዝለቁን አስረድተዋል። የወቅቱን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርንም ንግግር በመጥቀስ በሰላማዊ ሁኔታ የሚደረገው ትግል አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንደወደቀ አመላክተዋል። ሁለተኛው ተናጋሪ የመድረክ መሪው ጋዜጠኛ ወንድማገኝ ጋሹ ሲሆኑ እርሳቸውም በሀገራችን ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ የሰው ልጅን የሰውነት ደረጃ ያቃለለ፣ ሙሉ ለሙሉ ያዋረደና መብት የገፈፈ መሆኑን ጠቅሰው፣ ለሃያ ደቂቃ የቆየ ይህንኑ የሚያመላክት ፊልም አሳይተዋል። wendmagegne ጋዜጠኛ ወንድማገኝ ጋሹ ቀጥሎም የተነሱበትን አላማ እንዲያስረዱ በጉጉት ይጠበቁ የነበሩት ስዊድናዊው ጠበቃ ስቴላ ያርዴ ንግግር እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል። ጠበቃ ስቴላ ያርዴ የስዊድን ቴሌቪዥን ባሳየው ዘጋቢ ፍልም ስሚታቸው እንደተነካ ገልጸው ይሄንን አሰቃቂ ወንጀል የፈጸመውን የወያኔን መንግስት ለፍርድ ለማቅረብ እንደተነሱ አስረድተዋል። በፊልሙ ላይ የታዩት የወንጀል ድርጊቶች ለተነሳንበት ክስ አሳማኝ መረጃ ከመሆኑም በላይ በተለይ በእስር ላይ ያሉ ስዎችን የመድፈርና የማስወለድ ድርጊት ወንጀሉን የሚያከብደው ሲሆን በቅርባችን ባሉት ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ላይም የተፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰትና በደል ክሱን እንደሚያጠናክርው ገልጸዋል። ሁኔታውን ሲያብራሩም አሁን ያሉንን መረጃዎች ይዘን ለሚመለከተው አካል አመልክተናል። ወደ ቀጣዩ እርምጃ ለማለፍ የነሱን ውሳኔ መጠበቅ ይኖርብናል። የስዊድን ፖሊስም ለዚህ ጉዳይ ትብብሩን አልነፈገንም ብለዋል። stellan-yarde ጠበቃ ስቴላ ያርዴ ከተሰብሳቢው ህዝብም ክሳችሁ ትኩረት ይዞ የተነሳው በኦጋዴን በታየው በደል ብቻ ነው ወይስ በሌሎችም ክልሎች የተፈጸመውን አጠቃሎ ይይዛል? ለተባሉት ሲመልሱ በሌሎች ክልሎች የተፈጸመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ድርጊቱን በሚያስረዳ መልክ ማስረጃ አሰባስበን መያዝ የመጀመሪያ ስራችን ይሆናል ብለዋል። ማስረጃ ልንሰጣችሁ ብንፈልግ በምን መልኩ ማቅረብ እንችላለን ለተባለው ጥያቄ ደግሞ ሲመልሱ ማስረጃ ለመስጠት በተናጠል እኔን ማግኘት አያስፈልጋችሁም ከተለያየ ሰውና ቦታ የምታገኙትን መረጃ ይህንን የሚያሰባስብ የመረጃ ቡድን አቋቁማችሁ ቡድኑ መረጃዎችን አጣርቶና አሰባስቦ ቢሰጠን የተሻለ ይሆናል ብለዋል። ye afar tenagareየአፋር ሰብዓዊ መብት ተወካይ በስብሰባው ላይ የተገኙት የአፋር ህዝብ ብሄራዊ ክልል የሰብዓዊ መብት ተወካይ በበኩላቸው በአፋር ህዝብ ላይ እየተደረገ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ከሌላው ክልል የማይተናነስ መሆኑን ገልጸው በእጃቸው የሚገኘውን መረጃ ለጠበቃ ስቴላ ያርዴ ሰጥተዋል። የመጨረሻው ተናጋሪ መቶ አለቃ አበረ አዳሙ ሲሆኑ እርሳቸውም ‹‹ድርጅታዊ ዘረኝነት›› በሚል ርዕስ የተሰብሳቢውን ህዝብ ስሜት የሳበ ንግግር አድርገዋል። በዚሁ ንግግራቸው እንዳብራሩት የኢትዮጵያ መንግስት የድርጅታዊ ዘረኛነትን አገዛዝ አጥብቆ ለመያዝ የክልልና የፌዴራል ፖሊስን፣ የደህንንነት መምሪያውን፣ የመከላከያ ሰራዊቱን፣ የስራ ፈጻሚ ክፍሎች እንዲሁም የገንዘብ ገቢ የሚያስገኙ ተቋማትን በአንድ ዘር በማደራጀት ሃላፊዎች መድቦ ምንም አይነት ቀዳዳ ሳይከፍት ሁሉን ነገር ከቁጥጥሩ ስር በማድረግ tesebsabe hezb ተሰብሳቢው ህዝብ በከፊል ድርጅታዊ ዘረኝነቱን ለማጠናከር ችሏል ብለዋል። በመሆኑም ተቃዋሚ የሆንን ሁሉ ይህንን ድርጅታዊ ዘረኝነት አውቀን ትግላችንን ማጠናከር ይገባናል ለዚህም የሚያገለግለን መተባበርና እርስ በርሳችን መተሳሰር ሲሆን ይህን የአፈና መዋቅርም ማፍረስ የምንችለው በተጠናከረ የአንድነት ትግል ብቻ ነው በማለት ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋል። የመቶ አለቃ አበረ ንግግር በብዙዎች ታዳሚዎች ዘንድ ለለውጥ የሚያነሳሳ ስሜት ፈጥሮ ነበር። በመጨረሻም የውይይት መድረኩ ለወደፊትም ከልዩ ልዩ እንግዶች ጋር በዚህ መልክ ወይይቶች እንደሚደረግ ገልጾ ውይይቱ 18፤00 ስዓት ላይ ተጠናቋል። (ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የተጠናቀረው ዘገባ ወለላዬ ከስዊድን)

በወያኔ ሎሌነት ከመማቀቅ አንድ ቀን ነፃ ሆኖ መኖር ይሻላል

በወያኔ ግፈኛ ስርአት መከራቸውን ከሚያዩ ዜጎች ውስጥ ራሱ ሥርአቱ ለራሱ መገልገያ የሰበሰባቸውና ያሰማራቸው ዜጎች ይገኙበታል። ከእጅ ወደ አፍ እንኳን ለማትሆን ደመዎዝ በሰራዊቱ ውስጥ በተራ ወታደርነትና በበታች ሹማምንት የሲኦልና የጉስቅልና ኖሮ እንደሚኖሩ እናውቃለን። በየዞኑና በየወረዳው በካድሬነት ወያኔ ለገላጋይነት ያሰማራቸው ሰራተኞችና የድርጅቱ አባሎች ከህዝቡ የጥላቻ ሰለባነት ባልተናነሰ በኑሮአቸው ለራሳቸውም ለቤተሰቦቻቸውም ሳያልፍላቸው እንደሚኖሩ እናውቃለን። ይልቁንስ የወያኔው የአመራር ጉጅሌ ነገ የት እንደሚያደርሳቸው በማያውቁት ጨለማ ውስጥ ነው የሚዳክሩት ሚስጥርና የዳጎሰ ጥቅም ከነሱ ዘንድ አይደርስም። በቀድሞ ጊዜ የነበሩት የባላባት ሎሌዎች እንኳን ክብር አላቸው። በዚህ ላይ ሁሉም አስተማማኝ ሎሌ መሆኑን ወያኔ ለማረጋገጫ የሚጠቀምበት ግምገማ አለ። የወያኔ ግምገማ የበታች አባላትና ደጋፊዎቹን በማስፈራራት ያላቋረጠ ድጋፍ እንዲሰጡት የሚያደርግበት በመሰረቱ ከውሻ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የማይለይ ተቋም ነው። የትምህርት እድል የስራ እድገትና የደመወዝ ጭማሪ የወያኔው ጉጅሌ የባርነት መደለያዎች ናቸው። ግንቦት 7 ከጥቂት ከመንገዳቸው እያወጡ ህዝብ ከሚያሰቃዩት የወያኔ ታዛዥ ሎሌዎች በቀር የሀገርና የወገን ጠላት ናቸው ብሎ አያምንም። ትግላችን ለነሱም ነጻነት ነው። እነዚህ ወገኖቻችን ባገኙት አጋጣሚና እድል ሁሉ ትግሉን ያግዛሉ ብሎም ያምናል። የሚያግዙም አሉ። እርግጥ ነው ባሽከርነት ኑሮ የተንገፈገፉ የሰራዊቱ አባላትና ለህሊናቸው ክብር ያላቸው በርካታ የስርአቱ አገልጋዮች ትግላችንን እየተቀላቀሉ ነው። ግንቦት 7 ንቅናቄ ዛሬም እንደሁሌው ለነዚህ ወገኖች ኑ ተቀላቀሉን የሚል ጥሪውን ያቀርባል። ሁላችንም ከነክብራችን ሆነን ሰዎችን ሳይሆን ውዲቱን ሀገራችንና ህዝባችንን በፈቃደኝነት በነጻነት የምናገለግልበት ጊዜ እየቀረበ ነው፡፡ ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!source ginbot7.org

ወያኔ የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎችን አሰረ፤ ሰልፉም እንዳይደረግ ከለከለ፤ በሰልፉ ላይ የነበሩ የአንድነት ፓርቲ አባላትም መታሰራቸው ታውቋል

የሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ለመሳተፍ የወጡ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ታሰሩ፡፡ ከጽ/ቤታቸው ተነስተው ወደ ሰላማዊ ሰልፉ ቦታ ሲሄዱ 4 ኪሎ የኦሮሚያ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ጎን በሚገኘው ወታደራዊ ገራዥ መታሰራቸውን ዘጋቢያችን ከቦታው አድርሶናል፡፡ ከመታሰራው ቀደም ብሎ ከፖሊስ ጋር እንሂድ አትሄዱም በሚል ጭቅጭቅ ላይ እንደነበሩ ሰምተናል፡፡ ሌሎች የፓርቲው አባላትና አመራሮች ተበታትነው ወደ ሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ እየሄዱ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል፡፡ ዘግየቶ በደረሰን ዜና ደግሞ በኤምባሲው በተገኙ ሰዎች ላይ ፌዴራል ፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ ማድረሱ ታውቋል፡፡ በተጨማሪም በሰልፉ ላይ የነበሩ የአንድነት ፓርቲ አባላትም መታሰራቸው ታውቋል፡፡ በተለይ አንዲ ሴት ክፉኛ በመመታቷ ለህይወቷ እንዲያሰጋ ለማወቅ ችለኛል፡፡ አንድ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው “በሰው አገር ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ለመቃወም ወጥተን ተመሳሳይ ስቃይ አስተናገድን” ብለዋል፡፡

Tuesday, 12 November 2013

በስደት ለሚሰቃየው ኢትዩዺያዊ ተተያቂው ማነው?

ሀገር እያለው ሀገር እንደሌለው በሞት ለሚቀጣው ህዝብስ ተተያቂው ማነው? በድብደባ በእስር ለሚገላታው ወገን አረ ማንነው ተተያቂው? ለዚህ ሁሉ ተተያቂው ማነው? አረ ወገኖች የሀገር የወገን ያለ! እያለ ነው፡ ህዝባችን ግን ማን አለን ሀገር መሪ ቢኖረን ወገኖች በሳውዲ ሲሰቃዩ ሲገደሉ ሲቆረጡ መንግስት ለህዝቡ መብት መቆም አልቻለም::
ላለፉት ሁለት አስርት አመታት በማን አለብኝነት ህዝብን ማሰር ማሰቃየት መግደል ግለሰቦችንና ቡድኖችን ማንቃሸሽ መሳደብ ስልጣንን ተገን አድርጎ የሀገርና የህዝብን ሀብት መዝረፍ ለግላቸው ጥቅምና ስልጣን የሀገርንና የህዝብን ጥቅም አሳልፎ መስጠትና የመሳሰሉትን ወንጀሎች ሲፈፅሙ ቆይተዋል:: ልክ ከዚህ በፊት እንዳየናቸው አምባገነን አፍሪካዊያን መሪዎች በስልጣን ለመቆየትና የህዝብንና የሀገርን ሀብት ንብረት ለመዝረፍ ሲሉ የወያኔ መንግስት የፈፅሙዋቸውና ያስፈፅሙዋችው ኢ-ሰብአዊና ኢ-ፍታዊ ድርጊቶች: የዘር ማጥፋት: የግለሰቦችን ነብስ ማጥፋት ወንጀሎች: ሁሉም የመንግስት ባለስልጣናት በከፍተኛ ሙስና የጠገቡ ባለሀብቶች መሆን: ሀገሪቱዋ እስካሁን በምግብ እራስን ለመቻል ተቀረዑ የተባሉት እስትራቴጂዎች ምንም ውጤታማ ሳይሆኑ ቀርተው በአስር ሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን በተደጋጋሚ በከፍተኛ በርሀብ አለንጋ ከመገረፍ አለማዳናቸው: የህዝቡን ጥያቄ በአግባቡ ባለመመለሳቸው የወያኔ መንግስት ወደ ስነልቦናዊ አእምሮአዊና ፖለቲካዊ ችግር ውስጥ ተዘፍቀዋል:: የወያኔ መንግስት ለስሙ ሀይማኖትና መንግስት ጣልቃ አይገባቡም እያለ ጆሮችንን በየቀኑ ያደነቁረናል ነገር ግን በኦርቶዶክስና በእስልምና እምነት ድርጅቶች ውስጥ በቀጥታ እጁን አስገብቶ በመጀመሪያ ለዘመናት ተቻችለውና ተከባብርው የኖሩትን ከላይ የተጠቀሱትን የሁለቱን እምነቶች ተከታዮችን ጣልቃ በመግባት እርስ በርሱ እንዲተላለቁ ለማድረግ ብዙ ስራዎች ተሰርተው ነበረ ነገር ግን ህብረተሰቡ ይህ ተግባር የወያኔ አኩይ ስራ እንደነበረ ስለተረዳ በትዝብት ተመልክቶታል:: በሁለተኛ ደረጃ ወያኔ በእምነቶች ውስጥ ጣልቃ መግባቱ ገሀድ የወጣበት በኦርቶዶክስ እምነት ውስጥ የሚገኙትን ከፍተኛ የስልጣን ቦታዎችን የፈጣሪን የሚመለክባቸው ሳይሆን የወያኔን ጥቅም ለሚያስከብሩ ከአንድ ብሄር ለተሰበሰቡ ግለሰቦች አስረከበ:: የወያኔ መንግስት ህዝባዊ አመፅ የሚያስነሱ ናቸው በማለት በውሸት በተቀነባበረ ክስ በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎች የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት አባላቶች ደጋፊዎች የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች በሰብአዊ መብትና በማህበረሰብ ልማት ላይ የተሰማሩትን መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የግል ጋዜጣ ባለቤቶችና አምደኞች በየእስር ቤቶቹ እያጎረ ነው። እነዚህ በየማጎሪያ ቤቶቹ የሚገኙትን እስረኞች ቁጥር በእጅጉ ከመጨመሩም በላይ ታስረው በሚገኙበት ቦታ የሚፈጸመው እንግልት እና ስቃይ እጅግ በጣም ተባብሷል:: ሆኖም ግን ወያኔ የህዝቡን አመለካከት እና የወቅቱን የፓለቲካ እንቅስቃሴ ለመለወጥ ሲል በአሸባሪዎች በማሳበብ ብዙ ሽብሮችን እየፈጠረ የፓለቲካውን ሂደት እንዲለውጥ በማድረግ ይሞክራል። ሆኖም ግን በተደጋጋሚ በመደረጉ በህዝቡ አመኔታን ከማጣቱ የተነሳ ተቀባይነት ሊያገኝ አልቻለም። አሁን የወያኔ አባላቶችና ደጋፊዎች የሚይዙትን የሚጨብጡትን ያጡበት ሰአት ላይ ይገኛሉ። ትልቁ ችግራቸው እስካሁን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሱትን ወንጀሎች ኢተፈጥሮአዊና ኢሰብአዊ ድርጊቶች የሀገርና የህዝብ ሀብትና ንብረት ዘረፋ ብሎም የግለሰቦችን የብሄርንና የሀገርን ስምና ታሪክ ማጥፋትና ማበላሸትና የመሳሰሉ የውንብድና ተግባሮቻቸውን እንዴት ማጥፋት እንደሚችሉ የሚቻላቸውን ሁሉ ጥረት እያደረጉ ነው። ነገር ግን የሄ የመንግስት የሀይል እርምጃ ፉከራ ድንፋታ መደነባበር የህዝባችንን የፍትህ የእኩልነትና የነፃነት ትግል ማቆም አያስችለውም::

Sunday, 10 November 2013

ኢሕአዴግ እና የሃይማኖት ነጻነት

(ፋክት መጽሔት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፱ ጥቅምት ፳፻፮ ዓ.ም.) ተመስገን ደሳለኝ … ኢሠፓ መራሹ መንግሥት በኢሕአዴግ ከተተካ ጥቂት ወራት ቢያልፈውም፣ የተራዘመው የእርስ በርስ ጦርነት ያልደረሰባቸው በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙ አንዳንድ ከተሞችን ገና በቅጡ አልተቆጣጠራቸውም፤ በአናቱም በኢሠፓ መንግሥት ሽንፈት ሳቢያ እንዲበተን ከተገደደው የአገሪቱ መደበኛ ወታደር አብዛኛው ከእነትጥቁ የትውልድ መንደሩንና ቤተሰቡን መቀላቀሉ በአገሪቱ ላይ ከባድ ፍርሃት አንብሯል፡፡ በሰላም ወጥቶ ለመመለስ ርግጠኛ መኾን የማይቻልበት ከባቢያዊ አየርም አስፍኗል፡፡ በበርካታ ቦታዎች ተጠንተውና ታቅደው የሚፈጸሙ ወንጀሎችም ከአምስት እስከ ዐሥራ አምስት በሚደርሱ ወታደሮች የተደራጁ ልዩ ልዩ ሕገ ወጥ ቡድኖች በየማዕዘኑ እያቆጠቆጡ መኾኑን አመላክትዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የዐዲስ አበባ ቆዳ ስፋትና የነዋሮዎቿ የአኗኗር ዘይቤን በቀላሉ ለመልመድ የተቸገሩ ተጋዳላዮች ለትንሽ ለትልቁ ግርግር ጠመንጃን እንደ መፍትሔ መምረጣቸው ችግሩን አባብሶታል፡፡ ጉዳዩ እያሳሰባቸው የሄደው የኢሕአዴግ ዋነኛ መሪዎችም እንዲህ ዐይነቱን አለመረጋጋትና ሥርዐተ አልበኝነት ለመቆጣጠር የመንፈሳዊ መሪዎች አስተዋፅኦ ወሳኝ ስለ መኾኑ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል(እንደ ቀደሙት ሥርዐቶች ኹሉ ለቅቡልነት ከሚጠቀሙበት በተጨማሪ ማለት ነው)፡፡ ይኹንና በመንበሩ ላይ የነበሩት ፓትርያርኩ አቡነ መርቆሬዎስ አገር ለቀው እንዲወጡ በመደረጉ ክፍተት ተፈጥሯል፡፡ ይህ ጊዜ ነው ከ፲፱፻፸፬ ዓ.ም. ጀምሮ [ከኢየሩሳሌም ተሰደው] መኖርያቸውን አሜሪካን አገር ያደረጉ አንድ መንፈሳዊ አባት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ የተወሰነው፤ በጥሪው መሠረትም ወደ አገራቸው ሲገቡ መንግሥት የክብር አቀባበል አደረገላቸው፡፡ እኚኽ አባት ዛሬ በመንበረ ፕትርክናው የተሠየሙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ነበሩ፡፡ ኾኖም ከሳምንት ሽር ጉድ በኋላ አቡነ ‹‹የኢዲዩ አባል ነበሩ›› የሚል ወሬ በአመራሩ አካባቢ በስፋት መሰራጨቱ ያልተጠበቀ ዱብ ዕዳ አስከተለ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ኢሕአዴግ እና ኢዲዩ በ፲፱፻፸ዎቹ መጀመርያ ትግራይ እና ጎንደር ውስጥ በርካታ መሥዋዕትነት ያስከፈለ ውጊያ ማድረጋቸው ብቻ አልነበረም፡፡ የመጀመርያዎቹ ሊቀ መንበሮች ስሁል ገሰሰ እና መሐሪ ተኽሌ(ሙሴ) ‹‹የተገደሉት በኢዲዩ ነው›› የሚለው ወሬ በድርጅቱ ውስጥ ከጫፍ ጫፍ የተናኘና የታመነበት ጉዳይ መኾኑ ነበር፡፡ በዚህም ላይ የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ግራ ዘመምነት ተደማምሮ አቡነ ማትያስ በወቅቱ ወደ ታሪክነት ከተቀየረ ዓመታትን ባስቆጠረው ኢዲዩ ተፈርጀው ከታጩበት የፕትርክና መንበር ተገፈተሩ፡፡ ከዚህ በኋላ ነበር አብላጫውን የትጥቅ ትግል ዘመን በአሜሪካ ያሳለፉት አሰፋ ማሞ እና ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ ‹‹ዉድብ›› የሰጠቻቸውን ተልእኮ ተቀብለው ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ያመሩት፤ እናም ቀድሞም ትውውቅ ወደነበራቸው ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ ዘንድ ሄደው ለፕትርክና ወንበር መታጨታቸውን አበሠሯቸው፡፡ በእንዲህ ያለ መንገድ መንግሥት የቀባቸው አቡነ ጳውሎስም እስከ ኅልፈታቸው ድረስ አወዛጋቢ መሪ ኾነው ዘልቀዋል፡፡ (በነገራችን ላይ በአሜሪካ ለመጀመርያ ጊዜ ከሲኖዶሱ ተነጥሎ የቆመ ቤተ ክርስቲያን የመሠረቱት አቡነ ጳውሎስ እንደነበሩ ይነገራል፡፡ አቡኑ ደርግ ለጥቂት ዓመታት አስሮ ከለቀቃቸው በኋላ ወደ አሜሪካ ሄደው የፈጣሪያቸውን ሰማያዊ መንግሥት ሲሰብኩ ቆይተው የህወሓት ሠራዊት ክንዱ እየበረታ በቁጥጥሩ ሥር ያዋላቸው ከተሞችም እየበዙ ሲሄዱ እርሳቸውም ስብከታቸውን ወደ ትግርኛ ቋንቋ ከመቀየራቸውም በላይ ለ‹ነጻ አውጭ›ው ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ ያሰባስቡ ጀመር፡፡ የሥርዐት ለውጥ መደረጉን ተከትሎም በፖሊቲከኞች በተቀነባበረ ሤራ ከአቡነ ጳውሎስ ጋራ ቦታ የተለዋወጡት አቡነ መርቆሬዎስም፣ እዚያው አሜሪካ ‹ተተኪ›ያቸው የጀመሩትን ብሔር ተኮርና ከሲኖዶሱ የተገነጠለ ቤተ ክርስቲያን አስፋፍተው ዛሬ ለደረሰበት ‹የጎንደሬ ማርያም›፣ ‹የትግሬ ገብርኤል›. . .ለተሰኘ አሳፋሪ ክፍፍል ዳርገውታል፡፡ በርግጥ ለአቡኑ[አቡነ መርቆሬዎስ] ከአገር መውጣት የኢሕአዴግ እጅ እንዳለበት እንድናምን የሚያስገድደን በቅርቡ ታምራት ላይኔ ‹‹በእኔ ፊርማ ነው ያባረርናቸው›› ማለቱን ዊኪሊክስ ካደረሰን መረጃ በተጨማሪ በትጥቅ ትግሉ ዘመን ህወሓት በተቆጣጠራቸው በትግራይና ወሎ ነጻ መሬቶች በሚገኙ ከተሞች ያሉ ነዋሪዎችን ቀስቅሶና አደራጅቶ ፓትርያርኩ ላይ ‹‹ሽጉጥ ታጣቂ ጳጳስ››፣ ‹‹ቀይ ደብተር ያለው/ለኢሠፓ አባላት የሚሰጥ/ የሸንጎ ተወካይ››. . .የመሳሰሉትን መፈክሮች እያሰሙ በተቃውሞ ሰልፍ እንዲያወግዟቸው ማስተባበሩን ስናስታውስ ነው)፡፡ ዛሬስ የሃይማኖት ነጻነት የት ድረስ ነው? ከላይ ታሪክን ወደ ኋላ መለስ ብዬ በደምሳሳው ለመጠቃቀስ እንደሞከርኹት፣ ኢሕአዴግ በሃይማኖት ጉዳይ እጁን ጣልቃ ማስገባት የጀመረው ክንዱ ሳይፈረጥም ገና በረሓ ላይ ሳለ ነበር፡፡ በዚህ ኹኔታ የተጀመረው ጣልቃ ገብነት ዛሬም ድረስ ተባብሶ ቀጥሏል፤ ምንም እንኳ በሃይማኖት ጉዳዮች ጣልቃ እንደማይገባ በደፈናው ከሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፲፩ን በመጥቀስ በተደጋጋሚ ለማስተባበል ቢሞክርም ያለፉት ዓመታት ተጨባጭ ተግባሮቹ የሚመሰክሩት ግልባጩን ነው፡፡ ድርጅቱ ራሱም ቢኾን ጥያቄው በተነሣ ቁጥር ከሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፲፩ን የሚጠቅሰው ለስሙ እንጂ ሕጉ ተግባራዊ አለመኾኑን ሳይረዳ ቀርቶ አይደለም፤ አቶ ተፈራ ዋልዋም በ፲፱፻፺፰ ዓ.ም. ኅዳር/ታኅሣሥ ወር ከታተመችው ሐመር መጽሔት ጋራ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ጉዳዩን አስመልክቶ የሰጡት አስተያየት የኢሕአዴግን አጭበርባሪነት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፡- ‹‹ኢሕአዴግ እኮ የሚመራው መንግሥት በደርግም ጊዜ፣ በኃይለ ሥላሴም ጊዜ እንደሚታወቀው ‹የቤተ ክርስቲያን ሥራ አስኪያጅ ሹምልን› ተብሎ ተጠይቆ ‹የለም ራስዋ ቤተ ክርስቲያኒቱ ትሾማለች እንጂ እንደ ቀድሞው መንግሥት አይሾምላችኁም› የሚል መልስ የሰጠ መንግሥት ነው፡፡›› በሕዝበ ሙስሊሙ ተመርጦ ለእስር የተዳረጉት የኮሚቴ አባላትም በአንድ ወቅት ለሚመለከተው የመንግሥት ባለሥልጣን የጻፉት ደብዳቤ ጣልቃ ገብነቱን በግልጽ ያሳያል፡- ‹‹መንግሥት እንደ መንግሥት ሕዝቡ ተበድዬአለኹ፤ ምርጫ ይካሔድ፤ የመጅሊሱን አመራር አላመንኹበትም፤ ውክልና የለውምና ሕገ ወጥ ነው ያለውን አካል ሕገ ወጥነቱ እንዲረዝም ምርጫውን እርሱው እንዲያካሒድ መወሰን ሕዝብን ግራ አጋቢ ነው፡፡›› ሥርዐቱ በሃይማኖት ጉዳዮች ላይ ጣልቃ እንደማይገባ ለማሳመን ይህን ያህል ቢዳክርም በቅርቡ ‹‹የፀረ አክራሪነት ትግል የወቅቱ ኹኔታና ቀጣይ አቅጣጫዎች›› በሚል ርእስ የተዘጋጀው ባለ 44 ገጽ ሰነድ፣ መንግሥት በዘወርዋራ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን ሙሉ በሙሉ የሚያምን ኾኖ አግኝቸዋለኹ፤ ‹‹የመንግሥት መዋቅራትን ሴኩላር መንግሥት መኾናችንን ዐውቆ የመንግሥትን መዋቅር ተጠቅሞ የራሱን ሃይማኖት መሠረት ያደረገ አገልግሎት ከመስጠት ሙሉ በሙሉ ያልጸዳ መኾኑን የተለያዩ ጥቂት የማይባሉ ገሃድ የወጡ መገለጫዎች አሉ፡፡ እንዲያውም የትኛውም አክራሪ ኃይል ከመዋቅር(ከመንግሥት) አካል በርታ ሳይባልና ሽፋን ሳይሰጠው የሚንቀሳቀስ እንደሌለ አማኞቹ በገሃድ ይገልጻሉ፡፡›› መቼም ይህን ያነበበ ዜጋ መረጃው የተገኘው በመንግሥት ከተዘጋጀ ሰነድ ሳይኾን በኒዮሊበራሊስት›ነት ከተፈረጁት እነ‹‹ሂዩማን ራይትስዎች›› እና ‹‹አምንስቲ ኢንተርናሽናል›› ቢመስለው አይደንቅም፡፡ ሐቁ ግን ይኸው ነው፡፡ አገዛዙ ላለፉት ኻያ ሁለት ዓመታት መንግሥት እና ሃይማኖት እንዲለያዩ ማድረጉን ሲለፍፍ ከመቆየቱም በላይ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን የዘገቡ ጋዜጠኞችን ከሥሦ ዛሬም ድረስ ፍርድ ቤት እያመላለሳቸው እንደኾነ ይታወቃል፡፡ ከዚህ አንጻር ይመስለኛል ዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን በእስር ላይ የሚገኙት የእነ አቡበበከር መሐመድ ክሥ፣ የሼኽ ኑር ሑሴን ግድያ፣ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ እየተሰነዘሩ ያሉ ውንጀላዎችንና መሰል ፍረጃዎችን አምኖ ለመቀበል የተቸገሩት፡፡ ያም ኾነ ይህ ሃይማኖትን ብቻ ሳይኾን ዕድርና ዕቁብንም ሳይቀር ‹ካልተቆጣጠርኹ ሞቼ እገኛለኹ› በሚል የቁጥጥር ልክፍት የተያዘው ኢሕአዴግ፣ በተለይም 99.6 ድምፅ አግኝቼ አሸንፌአለኹ ብሎ ካወጀበት ከምርጫ ፳፻፪ ማግሥት ጀምሮ ‹‹አናት ላይ ከተቀመጡ መሪዎቻቸው በቀር ሙሉ በሙሉ አልተቆጣጠርናቸውም›› የሚላቸውን የኦርቶዶክስ ክርስትና እና የእስልምና እምነቶችን ዋነኛ አጀንዳ አድርጎ እየሠራ ለመኾኑ በርካታ መረጃዎች አሉ፡፡ በ፳፻፫ ዓ.ም. ኅዳር ወር ‹‹የአምስት ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድና የኢትዮጵያ ሕዳሴ›› በሚል ርእስ በአቶ መለስ ዜናዊ ተሰናድቶ የተሰራጨው ጥራዝ፣ የሥርዐቱን ቀጣይ አካሔድና ይህን ኹናቴ የሚያሳይ ከመኾኑም በተጨማሪ ዛሬም ድረስ በሃይማኖት ጉዳዮች ላይ መንግሥት የሚያዘጋጃቸው ሥልጠናዎችም ኾኑ ጥናታዊ ጽሑፎች መነሻ ሐሳባቸው ይኸው ዳጎስ ያለ ጥራዝ እንደኾነ ይነገራል፡፡ ጥራዙ የእምነት ተቋማትን በተመለከተ ከገጽ 128 – 132 ያካተተው ሐሳብ፣ ለኪራይ ሰብሳቢነት ዋነኛው ምክንያት ‹‹የሃይማኖት አክራሪነት›› መኾኑን ከጠቃቀሰ በኋላ ችግሩን ‹‹ተኪ የኾነ ልማታዊ አስተሳሰብ›› በማምጣት ማስወገድ እንደሚቻል ይመክራል፡፡ ይህን ከግብ ለማድረስ ደግሞ ሚዲያዎችንና ተያያዥነት ያላቸውን ማኅበራት መጠቀሙ አዋጭ እንደኾነ ይተነትናል፡፡ የኢሕአዴግ አባላት በየእምነት ተቋሞቻቸው ያሉ ማኅበራትን በዐይነ ቁራኛ መከታተል እንዳለባቸውም ያሳስባል፡- ‹‹[የግንባሩ አባላት] ከእምነት ተቋማት ውጭ ባላቸው አደረጃጀት አማካይነት በሰፊው መሥራት አለብን››፡፡ በርግጥም የእስልምና እምነት ተከታዮች ‹‹የሃይማኖት ነጻነት ይከበር›› የሚል ተቃውሟቸውን ባጠናከሩበት ሰሞን፣ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ሙስሊም አባላቱን ለብቻ እየሰበሰበ እንቅስቃሴውን የማክሸፍ ሥራ መሥራት ግዴታቸው መኾኑን የሰበከው ከዚኹ አቶ መለስ ዜናዊ አዘጋጅተውት ከነበረው ጥራዝ ነው ብሎ መከራከር ይቻላል፡፡ ከጣልቃ ገብነት ወደ ጠቅላይ ተቆጣጣሪነት በዘወርዋራም ቢኾን በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን ሙሉ በሙሉ የሚያምነው ከላይ የተጠቀሰው ሰነድ በአገሪቱ ‹‹የሃይማኖት አክራሪነት›› መከሠቱን ካተተ በኋላ ዋነኛ ተጠያቂዎች አድርጎ ያቀረበው እንደወትሮው ኹሉ ለተደጋጋሚ መሸማቀቅ የተዳረጉትን መንፈሳዊ መሪዎችንና ማኅበራትን ሳይኾን የመንግሥት መዋቅርን ነው፡- ‹‹የመንግሥት መዋቅራችን አካል ኾነው አክራሪነቱን በድብቅም በገሃድም የሚደግፍ አካል በፌዴራልም በክልልም ከሞላ ጎደል የሚታወቁ ናቸው፡፡ እነዚኹ አካላት በተቻላቸው ኹሉ በመድረክ ጤናማ እየመሰሉ የሚኖሩ ናቸው፡፡ የፀረ አክራሪነቱን ትግል ማጧጧፍ የሚፈልገውን መዋቅር አካልም ይኹን የሕዝብ አካል በተደራጀና በመረባቸው አማካይነት ከፍተኛ ጫና የሚያሳድሩ፣ የተቋማቸውን ምቹ ኹኔታ ተጠቅመው በፀረ አክራሪነት የሚንቀሳቀሱትን አካል የሚቀጡ፣ አሉባልታ እየፈጠሩ የሚያሸማቅቁ፣ ኾን ብለው ድጋፍ የሚነፍጉና በሐሰት ምስክርም ጭምር ዜጎችን የሚያሳስሩ ናቸው፡፡ የመንግሥትን አቅሞች ተጠቅመው አክራሪነትን የሚያስፋፉና ከአክራሪነት እንቅስቃሴ ጋራ በተለያዩ ጥቅሞች የተሳሰሩ ናቸው፡፡›› እነኾም በእንዲህ ዐይነቱ የውንብድና ተግባር የተሠማሩ ባለሥልጣናት የተሰባሰቡበት፣ ውንብድናው መኖሩንም የሚያምን መንግሥት አንድም ተጠያቂዎቹን ለሕግ አሳልፎ አለመስጠቱ፣ አልያም ሥልጣኑን በፈቃዱ አለመልቀቁ በአገር ላይ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ ለመረዳት ነቢይነትን አይጠይቅም፡፡ በአናቱም ሥርዐቱ ለሕግ የበላይነት ተገዥ አለመኾኑን የሚያሳየው በዚህ ደረጃ ‹‹ችግሩን ተረድቸዋለኹ›› እያለም እንኳ፣ ዛሬም የቅጣት ብትሩን ያሳረፈው ከመዋቅሩ ጋራ አንዳችም ንክኪ በሌላቸው መንፈሳዊ መሪዎች ላይ መኾኑ ነው፡፡ በርግጥም ይህ ዐይነቱ አሠራር ከዐምባገነን አስተዳደር መገለጫዎች አንዱ ነው፡፡ ኢሕአዴግም ያለፉትን አራት ምርጫዎች ጨምሮ በተለያየ ጊዜ የዴሞክራሲም ኾነ የሰብአዊ መብትን በዐደባባይ መጣስ፣ የሐሰት ክሦችንና ፍረጃዎችን እንደ ምክንያት መጠቀም ነባር ስልቱ እንደኾነ ይታወቃል፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ እየዘረዘረ ያለው የፈጠራ ውንጀላ እና ለሙስሊሙ ‹‹መፍትሔ አፈላላጊ›› ተብለው በተመረጡት የኮሚቴ አባላት ላይ የወሰደው ዕመቃ መግፍኤ ይኸው ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ከዚህ ቀደም በተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ ስለሚፈጸመው የግፍ ግድያዎች ይሰጥ የነበረውን ምክንያት በመንፈሳዊ ሰዎችም ላይ ያለአንዳች የይዘት ለውጥ ለመጠቀም አላመነታም፡፡ እንደሚታወሰው በድኅረ ምርጫ – ፺፯ በአምቦና በኢተያ በታጣቂዎች የተገደሉትን የኦሕኮ አባላት ከተፈጥሮ ሕመም ጋራ አያይዞት ነበር፡፡ በያዝነው ዓመት ጥቅምት ወር መጀመርያ ላይ በተካሔደው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ደግሞ የምዕራብ ወለጋና አሶሳ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ኄኖክ ‹‹ቤጊ›› ወረዳ በመንግሥት ባለሥልጣናት ተፈጸመ ያሉትን ግድያ ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ተወካይ፡- ‹‹በቤተ ክርስቲያን 70 ሜትር ርቀት ላይ የሌላ እምነት ተከታዮች የራሳቸውን ቤተ ክርስቲያን እንዲሠሩ መፈቀዱን ከተቃወሙት መካከል አንድ ዲያቆን ተደብድቦ በሦስተኛው ቀን ሕይወቱ ሲያልፍ ‹በወባ በሽታ ነው የሞተው› ተብሎ ለፍርድ ቤቱ የሐሰት ማስረጃ ከዶክተሩ እንዲቀርብ ታዘዘ›› ማለታቸውን መጥቀሱ ለጉዳዩ አስረጅነት በቂ ይመስለኛል፡፡ የኾነው ኾኖ አገዛዙ በዘረጋው ግዙፍ መዋቅሩ ውስጥ ያልታቀፉ ማኅበራትንም ኾነ የሃይማኖት ተቋማትን የስጋት ምንጭ አድርጎ ማየቱ፣ በእምነት ነጻነት ላይ ጣልቃ ለመግባትም ኾነ ምንም ዐይነት ገለልተኛ ተቋማት እንዳይኖሩ ዕንቅልፍ ዐጥቶ መሥራቱን ያሳያል ብዬ አስባለኹ፤ በሚቆጣጠራቸው የኤሌክትሮኒክስና የኅትመት ሚዲያዎች ቀን ከሌት የፕሮፓጋንዳ ከበሮ የሚመታበት የ‹አክራሪነት› ፍረጃም መነሾው ይኸው ይመስለኛል፡፡ ሰነዱን ከዚህ ቀደም ካየናቸው ለየት የሚያደርገው፣ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ አሉ ከሚላቸው ወንበዴዎች በተጨማሪ የሚከሥሣቸውን መንፈሳውያን ማኅበራት በደፈናው ‹‹በክርስትና እምነት ውስጥ ያሉ›› ብሎ አለማለፉ ነው፤ ቃል በቃል እንዲህ ይላልና፡- ‹‹በማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ የመሸጉ የትምክህት ኃይሎች ጽንፈኛ የፖሊቲካ ኃይሎች አካል በመኾን በጋዜጣና በመጽሔት ሕዝባችንን ለዐመፅና ለሁከት ለማነሣሣት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡. . .በራሳችንም ኃይል እንደሌላው ሰልፍ ልንወጣ ይገባል በሚል የዐመፅና የሁከት ቅስቀሳ ለማድረግ ይፈልጋሉ፡፡›› ይህ ኹኔታ መንግሥት መንፈሳውያን ማኅበራትን ጠቅልሎ ለመቆጣጠር በመፈለጉ ለተቃዋሚዎች ያሠመረውን ‹ቀይ መሥመር› መጣሱን ያሳያል፡፡ አስገራሚው ጉዳይ ደግሞ የሃይማኖት ተቋማትን የፖሊቲካ መሣርያ አድርጎ መጠቀሙ አልበቃ ብሎት ወደ መንፈሳውያን ማኅበራቱ መዞሩ ነው፡፡ በገሃድ እንደሚታወቀው የክርስትና ይኹን የእስልምና እምነት መሪዎች በተለያየ ጊዜ ከሥርዐቱ ጎን ተሰልፈው ‹ናዳን ለመግታት› ያደረጉት አበርክቶ በቀላሉ የሚገመት አለመኾኑ ነው፡፡ በርግጥም ‹‹የቄሣርን ለቄሣር›› በሚል አስተምህሮ የሚያድሩ፣ ደመወዛቸው በምድር ያልኾኑት መንፈሳውያን አባቶች በድኅረ ምርጫ – ፺፯ ሕፃናትን ሳይቀር በጥይት የፈጀውን ሥርዐት ማውገዝ ቀርቶ መምከር ያለመፈለጋቸው ምክንያት ፍርሃት ብቻ ሳይኾን የግል ጥቅምን ታሳቢ ያደረገው ግንኙነታቸው ያሳደረው ተጽዕኖ ይመስለኛል፡፡ ከቅዱሳን መጻሕፍት ይልቅ አብዮታዊ ዴሞክራሲን ‹አዳኝ› አድርገው የመቀበላቸው መግፍኤ ይኸው ነው፡፡ ኢሕአዴግም ‹ነገረ መለኰት›ን ለሲኖዶሱና ለመጅሊሱ እስከ ማስተማር ድረስ የደፈረው የእነርሱ ለሁለት ጌታ መገዛት ነው – ለገንዘብ እና ለጌታ፡፡ የሲኖዶሱ እና የመንግሥት ፍጥጫ በኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ሕገ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ከፍተኛውን ሥልጣን የሚይዝ ሲኾን ፓትርያርክንም የመሾምና የመሻር ሥልጣን አለው፡፡ ኾኖም ይህ የላዕላይ መዋቅር እስከ አቡነ ጳውሎስ ኅልፈት ድረስ ለእርሳቸውም ኾነ ለሥርዐቱ ሰጥ ለጥ ብሎ የሚገዛ ጥርስ የሌለው አንበሳ በመኾኑ ለትችት ከመዳረጉም በላይ በምእመናን ዘንድ ለመንፈሳውያን አባቶች የሚሰጠው ክብርም ተነስቶት ቆይቷል፡፡ ይኹንና በያዝነው ዓመት ጥቅምት ወር መጀመርያ በተካሄደው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ፴፪ኛ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ከመንግሥት የተወከሉ ሓላፊዎች÷ ‹‹የብዝኃነት አያያዝ አክራሪነት/ጽንፈኝነት ዝንባሌዎቹና መፍትሔዎቹ›› በሚል ርእስ ያቀረቡትን ጥናት ተከትሎ ስድስት ጳጳሳት ቀድሞ ባልታየ መልኩ ጠንካራ ተቃውሞ ማቅረባቸው፣ በብዙዎች ዘንድ የሃይማኖት መሪዎች ለመንፈስ ልዕልና ሊገዙ ይኾን? ከምድራዊው ይልቅ ሰማያዊውን ሊመርጡ ይኾን? ‹‹እመን እንጂ አትፍራ›› የሚለውን አስተምህሮአቸውን ሊተገብሩ ይኾን? የሚል ጥያቄ አጭሯል፡፡ በዕለቱ የመጀመርያው ተናጋሪ የነበሩት የሰሜን ወሎና ዋግ ኽምራ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቄርሎስ በጥናቱ ላይ መቻቻል አስመልክቶ የቀረበውን ድምዳሜ እንዲህ ሲሉ ነበር ያጣጣሉት፡- ‹‹ይኼ አክራሪነት፣ ጽንፈኝነት የሚለውን ቋንቋ እናንተው ናችኹ ያሰማችኹን፤ ከዚህ በፊትም አይታወቅም፣ በደርግም ይኹን በሌላ፡፡ እንደገና ደግሞ ብዙ ጊዜ ጽንፈኝነት፣ አክራሪነት እያላችኹ ዕድሜ ሰጥታችኹ ያበለጸጋችኋቸው እናንተው ናችኹ፡፡›› በርግጥም አቡኑ የተቹት ሥርዐቱ የፕሮፓጋንዳው ፋሽን ያደረገውን ‹‹መቻቻል››ን ብቻ አይደለም፤ ‹‹በመቃብሬ ላይ ነው የሚሻሻለው›› የሚለውን የመሬት ፖሊሲንም ነው፡፡. . . ‹‹በፊት መሬትም ሕዝብም የነገሥታቱ ነበር፤ አሁንስ የማን ነው? ይልቁንም ከአንድ ቤት ‹ግድግዳው የቤቱ ባለቤት ነው፤ ሳሎኑ የመንግሥት ነው› የሚለው ዐዋጅ የአሁን አይደለም እንዴ? ለኢትዮጵያዊነቱ ዋስትና የለውም፤ ይኼ የእኔ ነው የሚለው ከሌለ ምንድን ነው? ይህች የእኔ የኢትዮጵያዊነቴ መገለጫ ናት ካላለ ምንድን ነው ኢትዮጵያዊነት? አሁንም መሬቱም ሕዝቡም የእናንተው ኹኖ ሳለ ለፊቱ፣ ለነገሥታቱ መስጠታችኹ በምን ተመልክተውት ነው?›› የደቡብ ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ እንድርያስም በሚያስተዳድሩት አካባቢ ያለውን የመንግሥት ጣልቃ ገብነትና ተጽዕኖን ከዘረዘሩ በኋላ ለተሰነዘረው ፍረጃና ማሸማቀቂያ እንዲህ የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡- ‹‹የተበደለ ሰው ሲናገር ‹ፖሊቲካ ተናገረ› እየተባለ የውሸት ውሸት ሲያተራምሱን የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው፡፡. . .እንዴ! የመንግሥት ሥልጣን የተረከቡ ወንድሞች የእኛን አፍ፣ የእኛን አንደበት ብቻ ነው እንዴ የሚጠብቁት፤ ለሌሎች ሞራል ይሰጣሉ ማለት ነው?. . .ለምንድን ነው ግን በሽፋንነት የምትጠቀሙብን? መንግሥት እኛን ሽፋን አድርጎ ነው ሲበዘብዘን የምንኖረው፡፡ ሌባውም ቀጣፊውም ሰርጎ ገቡም ሲያጭበረብረን ሲያታኩሰን መንግሥትን ሽፋን አድርጎ ነው፡፡›› የወላይታ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅም በተመሳሳይ መልኩ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን ቤተ ክርስቲያኗ ስትቃወም ጉዳዩን ወደ ፖሊቲካ እየቀየሩ ማስፈራራቱ እንደተለመደና ለቀብር ማስፈጸሚያ የሚኾን መሬት ከመስተዳድሩ በሚጠየቅበት ጊዜ የሚሰጠው መልስ በሐሰት መወንጀል እንደኾነ ከገለጹ በኋላ ጉዳዩ መፍትሔ ካላገኘ ሊከተል ስለሚችለው ስጋታቸውን ተናግረዋል፡- ‹‹ ‹የፖሊቲካ ጉዳይ ነው፤ ሕዝብን በሃይማኖት ሽፋን ታንቀሳቅሳላችኹ› እየተባልን እየተሸማቀቅን ያለንበት ኹኔታ ነው ያለው፡፡ ይህን እንዴት ታዩታላችኹ? መቻቻልስ የሚመጣው ከምን አኳያ ነው? ዝም ብለን የምንቀመጥ ከኾነ ምናልባት ሓላፊነት ለመውሰድ ስለሚከብደን ይህን ወርዳችኹ እንድትፈትሹ ለማለት ነው፡፡›› (በነገራችን ላይ የአጠቃላይ ጉባኤው ዓመታዊ ስብሰባ በተጠናቀቀ ማግሥት ከማኅበረ ቅዱሳን አመራር ሦስት አባላት ወደ ፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ተጠርተው ዶ/ር ሽፈራውን ጨምሮ ከሚመለከታቸው ሓላፊዎች ጋራ ውይይት ማድረጋቸውን ከመሥሪያ ቤቱ ምንጮቼ ሰምቻለኹ፡፡ ሚኒስትሩ ከማኅበሩ አመራሮች ጋራ ለመወያየት የተገደዱት ካልተጠበቀው የሲኖዶሱ አባላት ድፍረት ጀርባ ‹የማኅበረ ቅዱሳን እጅ አለበት› የሚል ጥርጣሬ በመያዙ ነው፡፡ በውይይቱም ላይ የተንጸባረቀው የአባላቱ መለሳለስ፣ ማኅበሩን አክራሪ ብለው እንደማያምኑና ከዚህ ቀደም የተሰራጩት ወንጃይ ሰነዶችን ሳይቀር ‹አናውቃቸውም› እስከማለት የደረሰ እንደነበር አረጋግጫለኹ፡፡ ይኹንና ይህ እሳት ማጥፊያ ስልት ከሥርዐቱ ጋራ የቆየ መኾኑ ይታወቃል፤ የማኅበሩ አመራርም ይህ ይጠፋዋል ብዬ ባላስብም፤. . .) የኾነው ኾኖ [በአጠቃላይ ጉባኤው ዓመታዊ ስብሰባ] ከፌዴራል ጉዳዮች ከመጡት ሦስት ተወካዮች መካከል አቶ ገዛኽኝ ጥላሁን አብዛኛውን ጥያቄ በተመለከተ የሰጡት ምላሽ የወከሉት መንግሥት ዛሬም በተሳሳተ ታሪክ ንባብ እያሸማቀቀ፣ እያስፈራራ፣ ሕግን እየጠመዘዘ፣ እስር ቤት እየከተተ. . . የፖሊቲካ ጥቅሙን ማስከበር ላይ ያተኮረ መኾኑን ያሳያል፡፡ ሓላፊው ማስጠንቀቂያውን ያስተላለፉት እንዲህ በማለት ነው፡- ‹‹መጀመርያ ግንዛቤ ላይ እንሥራ በሚል ርምጃ አልወሰድንም፡፡ ኮሽ ባለ ቁጥር ወደ ቃሊቲ መፍትሔ አይኾንም፡፡›› . . .‹ቃሊቲ›ን ምን አመጣው? መቼም ለጣልቃ ገብነቱ ከዚህ የበለጠ ማሳያ መፈለግ ‹ዐውቆ የተኛን. . .› እንደመኾን ነው፡፡ ‹‹መንግሥት እና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው›› ብሎ መከራከሩም ጊዜ ያለፈበት ፕሮፓጋንዳ ይመስለኛል፡፡ እናም የተሻለው መንገድ ከላይ በጠቀስኹት ሰነድ ‹‹በየማእከላዊ ኮሚቴው በሚካሄደው የስምሪት ተግባር በፀረ አክራሪነት ትግል ላይ ያለው የእያንዳንዱ ግለሰብ ቁመና መፈተሽ አለበት›› ተብሎ የተገለጸውን ማሳሰቢያ በፍጥነት በመተግበር፣ በቅድሚያ ራስን ከአክራሪነትና አሸባሪነት ማራቅ ነው፡፡ ማረጋገጫ የማይቀርብበትን አፈ ታሪክንም እየለቃቀሙ በአንድ ሃይማኖት ላይ መለጠፉ አስተማሪ አይመስለኝም፡፡ ከዚህ ባለፈ ‹‹የሃይማኖት ኮማንድ ፖስት አቋቁመን ለችግሩ እልባት እንሰጣለን›› የምትሉት ጉዳይ በቀጥታ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ እጁን ማስገባቱን በዐደባባይ ከማመን ያለፈ የፖሊቲካ ጠቀሜታ አይኖረውም፡፡ ጳጳሳቱም ኾኑ ሼኾቹ ሓላፊነትና ግዴታቸው ሰማያዊውን መንግሥት መስበክ እንጂ ከሰላይ አለቆችና ከፖሊስ አዛዦች ጋራ ቢሮ ዘግተው የመንፈስ ልጆቻቸውን ‹‹ትምክህተኛ››፣ ‹‹አሸባሪ››፣ ‹‹አክራሪ››. . .እያሉ እንዲፈርጁ መፈታተኑ ያልታሰበ ሕዝባዊ ቁጣ መቀስቀሱ አይቀርም፡፡