Thursday, 26 February 2015

ለአንድ ቀን የሚቆይ የቦይኮት ዘመቻ በድምፃችን ይሰማ ጥሪ ቀረበ

‹‹እስር ከትግላችን አያስቆመንም!›› – ለአንድ ቀን የሚቆይ የቦይኮት ዘመቻ ነገ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከምሽቱ 12 ሰዓት ስልካችንን እናጠፋለን! መንግስት ሙስሊሞችን ከያሉበት በማሰር ህገ ወጥ ዘመቻ ላይ መሰማራቱን እና በህዝበ ሙስሊሙ ላይ ግፍ መፈጸሙን በመቃወም ነገ ጁሙዓ ታላቅ አገር አቀፍ ተቃውሞ እንደሚኖረን እና በዛሬው እለትም የተቃውሞው መርሃ ግብር ይፋ እንደሚሆን መገለጹ ይታወሳል፡፡በዚሁ መሰረት እነሆ የነገው አገር አቀፍ ተቃውሟችን በመጠነኛ የቦይኮት ዘመቻ (የራስን መብት በራስ ላይ የመንፈግ ተቃውሞ) የሚጀመር ይሆናል፡፡ኢትዮ ቴሌኮም ለመንግስት ከፍተኛ ትርፍ ከሚያስገኙ ካምፓኒዎች አንዱ ሲሆን በቀን ከተጠቃሚዎች በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ገቢ ያገኛል፡፡ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ደግሞ የአገሪቱ ግማሽ እንደመሆኑ መጠን በአንድ ቀን ለቴሌ የሚያስገኘው ገቢ እንዲሁ በሚሊዮን የሚቆጠር ነው፡፡ በመሆኑም የማይናቅ ቁጥር ካለው ማህበረሰብ የሚያጣው የአንድ ቀን ገቢ ለኢትዮ ቴሌኮም በሚሊዮን የሚቆጠር ብር አክሳሪ መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ የነገው ቦይኮት በኢቲዮ ቴሌኮም ካምፓኒ ላይ የሚያተኩረውም ለዚህ ነው፡፡ ነገ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ ሁላችንም ስልካችንን በመዝጋት ተቃውሟችንን እናሰማለን፡፡ አስቸኳይ ጉዳይ ካላጋጠመን በስተቀርም ስልካችንን አንከፍትም፤ አንጠቀምምም፡፡ አስቸኳይ ጉዳይ ሲያጋጥመን ለአፍታ ስልካችንን በመክፈት ቶሎ ጉዳያችንን ፈጽመን ወዲያው እንዘጋለን፡፡ ይህንን አገር አቀፍ እና መላ አገሪቱን ያካለለ ዘመቻ ላልሰሙት ሁሉ በማሰማት ለስኬቱ የቻልነውን ሁሉ መጣር ታላቅ ተግባር ሲሆን ለዲናችን ስንል ለምንከፍለው መስዋእትነትም ከጌታችን አላህ ዘንድ ምንዳችንን እንተሳሰባለን፡፡ አላህ ፈተናውን እንዲያነሳልንም አጥብቀን ዱዓ እናደርጋለን፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና!!! አዎን! አንድነት ያለው ህዝብ ያሸንፋል! ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!

Sunday, 22 February 2015

‹‹ምርጫ በህዝብ ፍላጎት ሳይሆን በሎተሪ ሆኗል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

አዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 5 ለመጭው ምርጫ ለተወካዮች ምክር ቤት ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ሊቀርቡ የነበሩት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ከቀረቡት 17 ዕጩዎች መካከል በተጣለ ዕጣ ወድቀዋል›› በመባላቸው ለመጭው ምርጫ በዕጩነት እንዳይቀርቡ መደረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል በዕጩነት በቀረቡበት ወረዳ 5 የምርጫ ጣቢያ ኢህአዴግ፣ የትግስቱ አንድነት፣ ቅንጅትን ጨምሮ ሌሎች ስድስት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ያለ ምንም ዕጣ አልፈዋል የተባለ ሲሆን ‹‹የሚያልፉት በዕጣ ነው›› የተባሉት ሰማያዊን ጨምሮ 11 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መካከል ሰማያዊና ሌሎች አራት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ‹‹ዕጣ አልወጣላቸውም፡፡›› ተብሏል፡፡images ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ሰማያዊ ህዝብ ውስጥ በሰፊው እየገባና እያንቀሳቀሰ ያለ ግንባር ቀደም ፓርቲ ነው፡፡ እንደ ኢህአዴግ ያሉን ጨምሮ ዕጣ ውስጥ አይገቡም፡፡ ሰማያዊ ደግሞ ይህ ነው የሚባል እንቅስቃሴ ከማያደርጉት ፓርቲዎች ጋር ዕጣ ውስጥ ገብቶ ወደቀ መባሉ ዴሞክራሲ ከጅምሩ ጀምሮ የህዝብ ድምጽ ሆኖ እያለ በእኛ አገር ሎተሪ ሆኗል ማለት ነው፡፡›› ብለዋል ሊቀመንበሩ አክለውም ‹‹ሂደቱ ምንም ይሁን ምን አንድን ፓርቲ ወይንም ተወካይን ህዝብ ነው መምረጥ ያለበት፡፡ ህዝብ የሚፈልገውና የሚመረጥ ፓርቲ ነው ለምርጫ መቅረብ ያለበት፡፡ አሁን ግን እየተባለ ያለው በአንድ በኩል ህዝብ የማይፈልገው ያለ ዕጣ ሲገባ፣ በሌላ በኩል ህዝብ የሚፈልገው ሰማያዊን የመሰለ ፓርቲ ዕጣ ውስጥ ገብቶ አላለፈም እየተባለ ነው፡፡ በአንድ በኩል ህዝብ የተማረረባቸው ያለ ቅድመ ሁኔታ ህዝብን እንደሚያንቀሳቅስ የሚታወቀው ሰማያዊ ደግሞ ህዝብ ስፈለገው አሊያም በጥንካሬው ሳይሆን በሎተሪ ወድቀሃል ተብሏል›› ሂደቱ የተሳሳተ ነው ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ”ሠማያዊ ፓርቲ ከ200 በላይ እጩዎች ተሰረዙብኝ አለ” በሚል ርዕስ አዲስ አድማስ እንደዘገበው — ”የፓርላማ ምርጫ እጩዎች ኢህአዴግ 501፣ መድረክ 303፣ ኢዴፓ 280 የሌላ ፓርቲ አባላትን በእጩነት አስመዝግቧል” – ምርጫ ቦርድ ሠማያዊ ፓርቲ በተለያዩ ክልሎች ለፓርላማ ካስመዘገባቸው 400 እጩዎች ግማሽ ያህሉ በምርጫ ቦርድ እንደተሠረዙበት ሲገልፅ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ፤ ሰማያዊ ፓርቲ ለምርጫው የሌላ ፓርቲ አባላትን ማስመዝገቡ ህገወጥ እንደሆነ ገለፀ፡፡ ለፓርላማ ኢህአዴግ 501 እጩዎችን፣ መድረክ 303 እጩዎችን፣ ኢዴፓ 280 እጩዎችን አቅርበዋል፡፡ ለፓርላማ ካስመዘገብናቸው እጩዎች ከሁለት መቶ በላይ ተሰርዘውብናል ያሉት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፤ በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በወላይታ፣ በቤንሻንጉል፣ በምዕራብ ጐጃም፣ በከምባታ፣ በሲዳሞ፣ በጋሞጐፋ፣ በአዲስ አበባ፣ በደቡብ ጐንደር እና በሌሎች አካባቢዎች አሣማኝ ባልሆነ ምክንያት እጩዎቻችን ከምርጫ ውጪ ተደርገውብናል ብለዋል፡፡ ፓርቲው የምርጫ አስፈፃሚዎችን እንዳነጋገረ ኢ/ር ይልቃል ጠቁመው፤ እጩዎቻችንን የተሰረዙት ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጣ ትዕዛዝ እንደሆነ ተነግሮናል ብለዋል፡፡ “የሌሎች ፓርቲዎችን አባላት አስመዝግባችኋል፤ ትብብር የሚባል ህገ ወጥ አደረጃጀት መስርታችኋል የሚሉ ምክንያቶችንም ሰምተናል ያሉት ኢ/ር ይልቃል፤ በአዲስ አበባ የተሠረዙብን እጩዎች ግን ግልፅ ምክንያት አልተሰጣቸውም ብለዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከፓርላማ ምርጫ የተሠረዙት እጩዎች የተሠረዙበት ምክንያት እንዲነገራቸው ጠይቀዋል፤ ምርጫ አስፈፃሚዎች የሰጡን ምላሽ፤ “እናንተን ለመመዝገብ እኛ ችግር የለብንም፤ ግን እንዳንመዘግብ ከበላይ አካል ታዘናል፤ በደብዳቤ ምላሽ ልንሠጣችሁ አንችልም” የሚል ነው ብለዋል – ኢ/ር ይልቃል፡፡ በጉዳዩ ላይ ከምርጫ ቦርድ ማብራሪያ ለማግኘት እንደሞከሩና፤ የቦርዱ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ነጋ ዱሪሳ በማመልከቻ ካልጠየቃችሁ መልስ አልሰጥም እንዳሏቸው ኢ/ር ይልቃል ተናግረዋል፡፡ የእጩዎች ስረዛን በተመለከተ ከአዲስ አድማስ ለቀረበላቸው ጥያቄ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፅ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድሙ ጎላ በሰጡት ምላሽ፤ “የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት” የተሰኘ ፓርቲ አባላቱን በሰማያዊ ፓርቲ ስም በእጩነት እንዳስመዘገበ በመግለፁ ነው ምርጫ ቦርድ ጉዳዩን ማጣራት የጀመረው ብለዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ በማያውቀው ሁኔታ ሰማያዊ ፓርቲ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ትብብር መስርቻለሁ በሚል መንፈስ፤ የበርካታ ፓርቲዎች አባላት በሰማያዊ ፓርቲ ስም እጩ ሆነው ቀርበዋል ያሉት አቶ ወንድሙ፤ የደቡብ ኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት ሊቀመንበር ራሳቸው በሰማያዊ ፓርቲ ስም አዲስ አበባ ላይ ተመዝግበው መገኘታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ አንድ ፓርቲ የሌላን ፓርቲ አባል በእጩነት ማስመዝገብ አይችልም፤ ህገወጥ ነው ያሉት የምርጫ ቦርድ ም/ኃላፊው፤ ስለዚህ የአንድ ፓርቲ አባል በሌላ ፓርቲ ስም እጩ መሆን ስለሌለበት አጣርታችሁ መዝግቡ የሚል መመሪያ አስተላልፈናል ብለዋል፡፡ ቦርዱ የሰጠው መመሪያ እጩ እንዳትመዘግቡ የሚል ሳይሆን እያጣራችሁ መዝግቡ የሚል ነው ያሉት አቶ ወንድሙ፤ በዚህ አሰራር ደስተኛ ያልሆነ ማንኛውም ፓርቲ፤ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ቅሬታውን ከምርጫ ጣቢያ እስከ ምርጫ ቦርድ በየደረጃው ማመልከት እንዲሁም ለፍ/ቤት አቤቱታ አቅርቦ ውሳኔ ማግኘት ይችላል ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል ኢህአዴግ፤ ለፓርላማ 501፣ ለክልል ምክርቤቶች ከ1300 በላይ እጩዎችን አቅርቧል፡፡ አራት ፓርቲዎች የተጣመሩበት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ፤ ለፓርላማ 303፣ ለክልል ም/ቤቶች ከ800 በላይ እጩዎችን ያቀረበ ሲሆን፤ ከዚህም ውስጥ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) 168 እጩዎችን ለፓርላማ 475 እጩዎችን ለክልል ምክር ቤት አስመዝግቧል፡፡ በኢትዮጵያ ማህበረ ዲሞክራሲ – ደቡብ ህብረት አንድነት ፓርቲም 83 ለፓርላማ 273 ለክልል ማቅረቡን ጠቁሟል፡፡ ሌላው የመድረክ አባል አረና ፓርቲ 33 እጩዎች ለፓርላማ 70 ለክልል አቅርቧል፡፡ ኢዴፓ በበኩሉ 280 እጩዎችን ለፓርላማ 200 እጩዎችን ለክልል አስመዝግቧል፡፡ ”

Wednesday, 18 February 2015

Ethiopia's Media War: Al Jazeera, The Stream

Ethiopia’s jailed Zone 9 bloggers are on trial this week for terrorism and treason, charges facing more than two dozen journalists, bloggers and publishers. To avoid arrest, 30 journalists fled the country in the past year. The government says they’re criminals, destabilising Ethiopia’s fragile democracy in the name of “press freedom.” Rights groups say they’re victims of repression.

Tuesday, 10 February 2015

የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አባላትና መዋቅሮች ወደ ሰማያዊ ፓርቲ እየጎረፉ ነው

የቀድሞው የአንድነት አባላትና መዋቅሮች በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን ተከትሎ ተጨማሪ የአንድነት አባላትና መዋቅሮች ሰማያዊ ፓርቲን እየተቀላቀሉ እንደሚገኙ የፓርቲው ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስለሽ ፈይሳ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ከጥር 28/2007 ዓ.ም በኋላ ሰማያዊ ፓርቲን ከተቀላቀሉት መካከል የትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ አፋር፣ ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ፣ ሀረር፣ አርባምንጭ፣ ወላይታ፣ ቁጫ፣ ቦንጋ፣ ኢልባቡር፣ ሰሞን ሸዋና የጉጂ የአንድነት መዋቅሮች ሙሉ በሙሉ ከሰማያዊ ፓርቲ መዋቅር ጋር መቀላቀላቸውን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ በቀጣዩ ቀናትም ወደ ሰማያዊ የሚቀላቀሉ መዋቅሮችና በግላቸው የሚመጡ አባላት እንዳሉ ኃላፊው ግልጸዋል፡፡ ‹‹በአንድነትና መኢአድ ላይ የተወሰነው ውሳኔ የሰላማዊ ትግሉን ለማዳከም የተደረገ ሴራ ነው›› ያሉት አቶ ስለሽ ፓርቲያቸው ላይ ህገ ወጥ ውሳኔ የተላለፈባቸው የአንድነት አመራሮችና አባላት ተስፋ ሳይቆርጡ ወደ ሰማያዊ ፓርቲ መምጣታቸውና ሰማያዊ ፓርቲም እነዚህን ታጋዮች እጁን ዘርግቶ መቀበሉ የታሰበውን ሴራ ያከሸፈና ሰላማዊ ትግሉን የሚያጠናክር ነው ብለዋለል፡፡ አቶ ስለሽ አክለውም የተፈጠረውን አጋጣሚ በመጠቀም ትግሉን ለማጠናከር ኢትዮጵያውያን የቻሉትን ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡

Thursday, 5 February 2015

በአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጥሰት ዙሪያ መከረ

ህብረቱ ጥር 27፣2007 ዓም በብራሰልስ ቤልጂየም የአውሮፓ ህብረት ጽ/ቤት ውስጥ ለ3 ሰአታት ባደረገው የኢትዮጵያ የሰአብአዊ መብት ግምገማ በኦጋዴን ክልል እና በተቀሩት የኢትዮጵያ ግዛቶች በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ሰቆቃ የአውሮፓ ህብረትና አባል መንግስታት በዝምታ መመልከታቸውን ማብቃት አለበት የሚል ውሳኔ አስተላልፈዋል። ስብሰባውን ያዘጋጁት የህብረቱ የሶሻሊስትና የዲሞክራቲክ ፓርቲዎች ጥምር ህብረት ፣ ውክልና አልባ ህዝቦች ተቆርቋሪ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው። በስብሰባው ላይ የኦጋዴን ክልል ፕ/ት አማካሪ የነበረና በክልሉ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በመረጃ በማጋለጥ ላይ የሚገኘው ወጣት አብዱላሂ ሃሰን፣ ተቀማጭነቱ በጄኔቫ የሆነ የአፍሪካ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ባልደረባ፣ አቶ አብዱላሂ ሙሃመድ፣ የኦጋዴን ሴቶች ተወካይ ፣ ጋዜጠኛና የክሬት ትረስ ዳይሬክተር ግርሃም ፌብልስ፣ እንዲሁም በኦሮሞ ሴቶች ላይ የሚደረሰውን ሰቆቃ በማስመልከት ጥናት ያካሄዱት፣ ዶ/ርባሮ ቀኖ በቪዲዮ የተደገፈ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል። እንግሊዛዊው ግራሃም ፌብልስ በኢትዮጵያ 2 አመታት ቆይታቸው የታዘቡትን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በተለይም በኦጋዴን ክልል በሴቶች ላይ ተፈጽሟል ያሉትን አስገድዶ መድፈር ወንጀል የታዳሚውን ስሜት በነካ መልኩ አቅርበዋል። በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በዜጎች ላይ ሽብርን እያኬደ ነው ያሉት ሚ/ር ፌብልስ የዚህ ሶቆቃ ፈጻሚዎች፣ ከአውሮፓ ህበረትና መንግስታት በእያመቱ ከፍተኛ የገንዘብ እርዳታ የሚያገኙ መሆናቸው እጅግ የሚያሳዝነው ነው ብለዋል። በጉባኤው ላይ የኦጋዴን ነጻነት ግንባር ተወካይ ዶ/ር ባዳል አህመድ እና አርበኞች ግንቦት7 ተወካይ አቶ አበበ ቦጋለ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጸመ ነው የሚሉትን የሰብአዊና የፖለቲካ መብቶች እረገጣና አስከፊ ሰቆቃ በእየተራ አቅርበዋል። የአውሮፓ ህብረትን ወክለው በስብሰባው ላይ የተገኙት ወ/ሮ አና ጎሜዝና የእንግሊዝ የፓርላማ ተወካይ ወ/ሮ ጁሊ ዋርድ በየተራ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ መንግስት ከ60 በመቶ በላይ በጀቱን ከአውሮፓ ህበረት እየተቀበለ ዜጎች ላይ እየፈጸማቸው ያለው አስከፊ ሰቆቃዎችን አውሮፓ ካሁን በሁዋላ በዝምታ ማየት የለባትም ካሉ በሁዋላ፣ ኢትዮጵያኖች በአገራቸው እየተፈጸመ ያለውን አፈናና ጭቆና የውች ማህበረሰብ ያስቆምልናል ብለው ከመጠባበቅ ለራሳቸው ነጻነት ልዩነቶቻቸውን በማቻቻልና መለስተኛ ፕሮግራም በማዘጋጀት ህብረት ፈጥረው በአንድነት መታገልና ለለውጥ መነሳት አለባቸው ብለዋል። የአውሮፓ ህብረት በዘንድሮው ምርጫ ላይ ታዛቢዎችን እንዳይልክ የወሰነው የኢህአዴግ መንግስት በየ5 አመቱ የሚያደርገውን የተሳሳተ ምርጫ በማጀብ ህጋዊነት ለማሰጠት እንደከዚህ በፊቱ ለመተባበር ፈቃደኛ አለመሆኑን ለመግለጽ ሆኖ ሳለ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ግን ህበረቱ በገጠመው የበጀት ችግር ምክንያት ታዛቢ አልክም ብሎአል ብሎ የጀመረው ቅስቀሳ መሰረተ ቢስና የተለመደ ህዝብን የማዘናጊያ ወሬ እንደሆነ ገልጸዋል። የአመቱን 60 በመቶ የሚሸፍን በጀት የሚሰጠው ህብረቱ፣ ኢትዮጵያን የመሰለ ስትራቴጂክ አገር፣ ህብረቱ የገንዘብ እጥረት ገጥሞታል ብሎ ማሰብ ራስን እንደማታለል ይቆጠራል ብለዋል። ህብረቱ ምርጫው ከመደረጉ ከሚቀጥለው ወር በፊት የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎችንና ሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን በስፋት የሚያሳትፍ ትልቅ ጉባኤ በሚያዚያ ወር ላይ ለመጥራት በዝግጅት ላይ እንዳለ በዚህ ስብሰባ ላይ ተገልጿል። አንዳንድ የፓርላማ አባላት በዚህ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደግብጽ ህዝብ ሆ ብሎ በመነሳት ከመዒው ግንቦት ምርጫ በፊት አምባገነንነትን ከራሱ ትከሻ ላይ ለማውረድ መነሳት አለበት ሲሉ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በሚቀርብበት የሰብአዊ መብት ጥሰት ላይ አቋሙን እንዲገልጽ ቢጋበዝም ፣ ፈረንሳይኛ ተናጋሪ የሆነ ቤልጂየማዊ ዜጋ የሆነ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሰራተኛ የተገኘ ሲሆን ስራውም መረጃ መሰብሰብ እንጅ አስተያየት መስጠት አለመሆኑን ገልጾ፣ ምንም ንግግር ሳያደርግ ወጥቷል።

አቶ ሲሳይ ዘርፉ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላለፈበት፟ በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ህዳር 27 እና 28/2007 ዓ.ም በ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ተዘጋጅቶ ለነበረው የአዳር ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ የቅስቀሳ በራሪ ወረቅት ሲበትን ለእስር የተዳረገው የሰማያዊ ፓርቲ አባል አቶ ሲሳይ ዘርፉ ዛሬ ጥር 28/2007 ዓ.ም የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላፈበት፡፡ ታህሳስ 14/2007 ዓ.ም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት ቆርቦ የነበረው አቶ ሲሳይ ዘርፉ ‹‹…‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ› ለመላው ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያዊ ሁሉ….ተብሎ የተጻፈበት በራሪ ወረቀቶች ለህብረተሰቡ ሲያከፋፍል እጅ ከፈንጅ በመያዙ በፈጸመው የሐሰት ወሬን በማውራት ህዝቡን ማነሳሳት ወንጀል…›› በሚል በፌደራል አቃቤ ህግ ለቀረበበት ክስ ያቀረበው የክስ መቃወሚያ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ መደረጉ ይታወሳል፡፡ ከዚህም ባሻገር አቶ ሲሳይ ዘርፉ ጥር 7/2007 ዓ.ም የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበርና ም/ሊቀመንበር የሆኑትን ኢ/ር ይልቃል ጌትነትና አቶ ስለሺ ፈይሳ እንዲሁም የኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ህብረት (ኦህዴህ) ሊቀመንበር አቶ ግርማ በቀለን በመከላከያ ምስክርነት አቅርቦ የነበር ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ‹‹ምስክሮቹ ከወንጀል ድርጊቱ ጋር ቀጥተኛ የሆነ ምስክርነት ሳይሆን የራሳቸውን የፖለቲካ አመለካከት ሚዛናዊነት በጎደለው መልኩ ነው ያቀረቡት፡፡›› በሚል ምስክሮቹ የሰጡትን የምስክርነት ቃል ውድቅ አድርጓል፡፡ አቃቤ ህግም በተሰጠው የጥፋት ውሳኔ ላይ ‹‹ተከሰሽ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ 82(ሀ) 1/ መሰረት ማቅለያው ታይቶለት ከዚህ ቀደም የወንጀል ድርጊት ያልፈጸመ ስለሆነ የምንጠይቀው የቅጣት ማክበጃ የለንም፡፡ ሆኖም ግን በሰራው የወንጀል ድርጊት የመጨረሻው ጣሪያ ውሳኔ እንዲሰጥልን እንጠይቃለን፡፡›› ብሏል፡፡ ፍርድ ቤቱ ለካቲት 3/2007 ዓ.ም የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት በመናገሻ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡ አቶ ሲሳይ ዘርፉ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ዋስትናው ተነፍጎ ቀደም ብሎ በፖሊስ ጣቢያና አሁን ደግሞ ቂሊንጦ እስር ቤት በእስር ላይ ይገኛል፡፡

Sunday, 1 February 2015

Open Letter from Anuak Ethiopian Refugees to the President of the World Bank, Jim Yong Kim

Dear Mr. President, We are the REQUESTERS, Anuak refugees and asylum seekers based in Kenya (Dadaab, Kakuma and Nairobi) and South Sudan (Gorom), who submitted a complaint to the World Bank Inspection Panel in September 2012. We have written to you twice before but we have never received a response. This is our final appeal and we pray that this time our voice will be heard. Ethiopia: Stop Land Grabbing and Restore Indigenous Peoples' Lands We were forced to flee our homeland in Gambella, Ethiopia because we dared to oppose the government’s forced relocation program, known as “villagization”. We Anuaks never consented to give up our ancestral lands, which is the source of our life and our identity. We only moved out of fear. When local farmers did not agree to relocate, at night soldiers came and raped the women and beat the men. Those teachers, agriculture workers and other civil servants who refused to implement this program, including many of us, were TARGETED with arrest and torture. This is why we are living as refugees in neighboring countries today. Without the billions of dollars provided by the World Bank and other donors through the Protection of Basic Services (PBS) project, the Ethiopian government would never have had the capacity to relocate so many people and grab our ancestral LAND. That is why we filed our complaint to the Inspection Panel and why we begged you at that time to delay the NEXT phase of the project until you could ensure that it would not be used to displace and kill our people. Now we have been INFORMED about the findings of the Inspection Panel. We know that the investigation found that the World Bank does not track how PBS funds are used on the ground. If the World Bank cannot guarantee that its money will not be used to abuse people, then it should not provide money in this way to the Ethiopian government. We know that the investigation found that PBS did not follow the World Bank Policy on Indigenous Peoples. We indigenous people have a right to decide about any development projects that affect us and especially our land. We have a right to be consulted and a right to reject any development that we don’t want. For the past 118 years that we have been living under the control of the central government of Ethiopia, we have never been consulted about any development project or policy that affects our people. Nobody ever informed us that the World Bank was supporting basic services in Gambella or asked for our opinion about the services we want and where and how we want them delivered. Instead we were forced to give up our fertile land and move to dry, forested areas in order to access these services funded by the World Bank. And when we moved with the promise of getting better services, we found that it was all a lie. At the new locations, there were no services and the land we were given could hardly grow food. When the World Bank saw this happening, it should have stopped PBS until the government stopped villagization. If you did that, maybe we would not be refugees today. But since the World Bank CONTINUED to fund PBS 3 after two years of villagization, and after we pleaded with you to stop, the Bank has a responsibility to help us recover what we have lost. We want our people in Gambella region displaced by villagization PROGRAMME, to return to their ancestral land without fear of retribution. We want SUPPORT to restart their farms, with modern technology like farmers have in other parts of Ethiopia. We want them to grow food on their land for local consumption, rather than working like slaves on big farms owned by foreigners growing crops to export to other countries. We want grinding mills and wells that work in their villages and good roads that go to clinics and markets and not to gold mines. We want a university and a hospital in Gambella region with quality services for indigenous people. We want our people to be consulted and to have ownership of our development. In the refugee camps where we live in Kenya, South Sudan and Uganda, we are facing insecurity and dire living conditions but we cannot return home or our lives will be in danger. Women are dying from caesarian sections and minor surgeries because of the poor quality of health care. Newcomers are not accepted by UNCHR and so we must share our food rations with them so they don’t starve. After primary school, our youth have nothing to do but sit idle or become addicted to drugs. It is so painful to see our children growing up in a FOREIGN LAND with no future. We need support to develop our livelihoods and our youth need opportunities to go to secondary school and university. We are very encouraged by the bold agenda you have set for the World Bank and the international community to end extreme poverty and promote shared prosperity. We strongly support YOUR call for equitable and inclusive development in fragile and conflict-affected states. We were especially moved by your statement, published last year in the Washington Post, that “the fight to eliminate all institutional discrimination is an urgent task.” We are victims of a government that systematically discriminates against indigenous people with dark skin. Because of this discrimination, we have gone from food SECURITY to extreme poverty – living on food aid as refugees. All we are asking is that you live up to your HIGH words and ensure that your institution lives up to its good policies. Thank you for your listening to us and may the Almighty God bless the work of your hands. High regards, Anuak REQUESTERS to the World Bank Inspection Panel