Wednesday, 30 September 2015
አገር የምትኖረው በ3 ነገር ነው በወታደር በገበሬ እና በመምህር ። – ከአዲስ ብርሃኑ ፡
ethiopiaአገር ለማፍረስ ቆርጦ የተነሳው ወያኔ ኢትዮጵያ የምትባለው አገር እንድትኖር በመሰሪ ሃሳቡ ሌት ተቀን የማይቆፍረው ግድጓድ የለም የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። ነገር ግን እንደ አሳቡ ሊሆንለት አልቻሉም ዘር ከዘር ሊያጋጭ ብዙ ጣረ አልተሳካለትም፤ ሐይማኖት ከሃይማኖት ሞከረ ይሄም አልሰራ አለው ሃሳቡ ሁሉ መና ሲቀርበት እራሱ ከሳሽ እራሱ ፈራጅ በሆነበት ፍርድ ቤት የብዙሃን ነጽሃን ሰው መሰቃያ ወደ ሆነው ወህይኒ እየወረወረ ባልሰራበት ወንጀል ባላደረጉት ድርጊት ንጽሐኑን ማሰቃየት ከጀመረ ድፍን 24 አመት አለፈ። -መምህር….. አንድ አገር ከሚያስፈልጋት ዋናው መሰረታዊ ነገር መምህር ነው። መምህር ከሌለ የተማረን ህብረተሰብ ማግኝት አይቻልም። መምህር በጠመኔው ለአገር የሚሆን ፍሬ ለህዝብ የሚጠቅም ዘር በሰው አእምሮ ውስጥ የሚዘራ እና ብዙ ጥበቦች ባለ ብዙ እውቀት ባለቤት አገርን በጥበብ የሚመራ ላገሩ በእውቀት የሚያገለግል ለአገር የሚጠቅመውን ካመነበት የሚሰራ ካላመነበት ደግሞ እንቢ የሚል ማንኛውንም ነገር ሰለ ህዝብ ብሎ ስለ አገር ብሎ ማድረግ የሚቻል ዜጋን የሚቀርጹት መምህራናን ናቸው። ዛሬ ወያኔ እያደረገ ያለው እኔ የምላቹሁን አድረጉ እኔ የምላቹሁን አስተምሩ እኔ የምላቹሁን መመርያ ተቀበሉ ብሎ አገርን የሚያጠፋ ሆኖ ሰላገኙት የወያኔ ደጋፊ ባለመሆናቸው ብቻ አገርን የሚያቀኑን መምህራን ትውልድን የሚቀርጹ መምህራን በካድሬ በመተካት የተማረ እንዳይበቅልባት ያወቀ እንዳይወጣባት ትምህርት ቤቶችና ዪንቨርስቲዎች ያቃጣሪወች መናህርያ አድርጓታል። እንግዲህ ወገኔ የመምህራን መነካት የኢትዮጵያ አንዱ መሰረቱ እየተናጋ ነውና ልትነቃ እና የወያኔ አገር አጥፊነቱን አውቀን በቃህ ልንለው ይገባል። ገበሬ…… አገር የምትኖረው ገበሬው አምርቶ በሚያበቅለው ምርት ነው ገበሬው ጠንክሮ በማረስ አገርን በመመገቡ ሂደት የአገርን መሰረት ነው። ዛሬ ገበሬው ከመሬቱ በማፈናቀል ለውጪ ባለሃብት ለኢንቬስተር በመስጠት እንዲሁም በግድ ማደበርያ እንዲወስድ እያደረጉት ባለ እዳ በማድረግ እዳውን መክፈል ሳይችል ሲቀር መሬቱን ጥሎ እንዲሄድ በማድረግ ተሳዳጅ አድርገውታል። ገበሬ የለም ማለት አገር የለችም ማለት ነው ።ገበሬው በማሰቃየት እረፍት በመንሳት እስመርረውት ያሉት ወያኔወች ሃሳባቸውም ራያቸውም ሰለ ኢትዮጵያ እና ሰለ ሕዝቧ ስላልሆነ ስለሚያደርጉት ነገር መጸጸት እንኳን አያሳዩም ስለዚህ ገበሬው ሲነካ የአገር መሰረት መነካት ነውና ወገኔ እንግዲህ ንቃ። ወታደር….. አገር የምትጠበቀው በወታደር ነው አንድ አገር ጠንካራ የወታደር ከሌላት ጠላት በቀላሉ ይዳፈራታል። ስለዚህ ጠንካር የወታደር ተቋም ለአገር አጥርም መሰረት ነው። ዛሬ ግን ወያኔ እየሰራ ያለው የወታደር ተቋም በወታደራዊ ስልጠና እንዲሁም ትምርት በብቃት የሚበልጣቸው እያሉ ትግሬ በመሆኑ ብቻ አዛዥ ቦታ ላይ እንዲቀመጥ ይደረጋል ይሄ አካሄድ ለወያኔወች የአገር ማፍረስ አላማቸው ስለሆነ ምንም አይሰማቸው ለትግሬወች ግን ጊዚያዊ ሹመት ሲሰጣቸው ሁሉንም ቦታ ያለ እውቀታቸው ቦታውን እንዲይዙት ሲደረግ ለምን ብላቹ መጠየቅ ሲገባቹሁ የተሰጣችሁን ስልጣን ተቀብላቹ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ላይ በደልና ጫና የምትፈጥሩ እንግዲህ እዳው በእጃቹ ነው። የወያኔ ባለስልጣን ባንተ ስም የአገርን ንብረት እየዘረፉ እያሸሹ ይገኛሉ አንተ ግን ከህብረተሰቡ ጋር የትም አትሄድም ያኔ በሰፈሩት መስፈርያ እንዳይሆንባቹሁ የትግሬ ተወላጆች በወታደር ላይ የምታደርጉትን በደል ታቆሙ ዘንድ ያስፈልጋል። እንተም ከጥቂት የአገር አጥፊ እና ዘረፊ ጋር ባለመወገን አንድነታቹሁን የምታሳዩበት ጊዜ በጣም አጭር ነውና ይታሰብበት። ካለበለዚያ ግን ወደ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ደምና ጉልበት እንዲሁም በኢትዮጵያ ሕዝብና ሃብት እንደፈለጋቹ እየሆናቹ የምትኖሩበት ጊዜ ማብቂያው ይመጣል። ወታደሩም እራሱንና አገሩን ሕዝቡን የመጠበቅ ነጻ የማውጣት ሃላፊነት እንዳለበት ወያኔ የሚያውቅበት ጊዜ ቅርብ ነው። ወያኔወች የመከላከያ ሰራዊት የሃገር መሰረት ስለሆነ ይህንም ለማፍረስ እና ለመበተን ሌት ተቀን እየሰሩ ነው። እውነት ነው መምህሩም ወደቀድሞ ቦታቸው ተመልሰው ባላቸው እውቀት ጠመኔን ይዘው ያለምንም ተጽእኖ ዜጋን የሚያፈሩበት ጊዜ ቅርብ ነው። እውነት ነው ገበሬው ሞፈሩን አንስቶ እርሻውን አስፍቶ በትራክተር አርሶ ሕዝቡን የሚመግብበት ቅርብ ነው ። እውነት ነው ወታደሩ ወያኔን የተባለ ወንበዴን አጥፍቶ ለሕዝቡና ለአገሩ ዘብ የሚቆምበት ጊዜ ቅርብ ነው ። ሞት ለወያኔ!!! አዲስ ብርሃኑ -
Friday, 14 August 2015
በአገራችን በሰሜን ምስራቅ እና በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ መጠኑ እየጨመረ መጥቷል፡፡
በአገራችን በሰሜን ምስራቅ እና በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ መጠኑ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ጉዳዩ ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው ተመሳሳይ ድርቅ በመጪው አመት 2008 ዓ.ም በጥቅምት እና በህዳር ወር ሊከሰት እንደሚችል ባለሙያዎች እየጠቆሙ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ገዥው መንግሰት አሁንም የችግሩን አሳሳቢነት ወደ-ጎን በማድረግ ፤የስራዓቱ ደጋፊ እና አቀንቃኝ ከሆኑ ዲያስፖራ ጋር “አስረሽ ሚቺው” እያለ ከበሮ እየደለቀ ይገኛል፡፡
ሆኖም በአገራችን በተለይ በሰሜን ምስራቅ የተከሰተው ድርቅ እንስሳቶችን በከፍተኛ ሁኔታ እየገደለ የሚገኝ ሲሆን ፣በሰው ሕይወት ላይ ቁጥሩ ቀላል የማይባል የሞት አደጋ እያንዣበበ ይገኛል፤በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎች በሰውንት መዳከም እና እስን ተከትሎ በሚመጣ በሽታ እየተጠቁ ናቸው፡፡ ይህ እውነት ከባለፉት ቀናት ዛሬ ላይ ከኢትዮጵያ አልፎ በአለም ላይ መረጃው እየተሰራጨ ይገኛል፤ ይሄን ተከትሎ ገዥው መንግሰት መረጃውን ደብቆ የመያዝ ፍላጎቶ ሊከሽፍበት ችሎአል ፡፡
የመንግሰት ውጥን ሣይሳካ ሲቀር፣ የመንግሰት ኮሚኒኪሽን ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሬዲዋን ሁሴን “ሰባት ሞቶ ሚሊይን ብር በጀት የያዝን በመሆኑ ችግሩን መቆጣጠር እንችላለን” በማላት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ነገሩን ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው እንደሳቸው ገለፃ “ምንም አይነት የዉጪ እርዳታ አያስፈልገንም፣ የዚህን ያህል አሳሳቢ ደረጃ አልደረሰም” ማለታቸው ነው፡፡ እሳቸው ይሄን ይበሉ እንጂ አሁን ላይ የተከሰተው ድርቅ እና በቀጣይ አመት ይከሰታል ተብሎ የተገመተው ድርቅ፣ ከመንግሰት ቅድመ ዝግጅት ማነስ እና የእርዳታ ድርጅቶች መንግሰት በተለመደው መንገድ እየተከላከለ የሚቀጥል ከሆነ፤ አገራችን አስከፊ ሁኔታ ውስጥ የሚከት ነው፡፡ መንግሰት 7መቶ ሚሊየን ብር መደብኩ ይበል እንጂ፣በመንግስት የአሰራር ብልሹነት እና ስር ከሰደደው ሙሱና አንፃር ችጉሩን የቱንም-ያህል ፈቀቅ እንደማያደርገው እውን ነው ፡፡
መንግሰት በተለያየ ወቅት ኢትዮጵያ በምግብ እራሷን ችልለች ይበል እንጂ፣ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ጾም አዳሪ ነው፡፡ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ድርቅ ተከስቶ መንግስት እርዳታ አያስፈልግም ችግሩን መቋቋም እችላለለው በማለቱ፤ አለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ድጋፍ ማድረጋ ባለመቻላቸው በሰው እና በእንስሳ ላይ ቁጥሩ ቀላል የማይባል ሞት ተከስቷል፡፡
ድርቁ ሊከሰት የቻለበት ዋና ምክንያት ከአለም አቀፍ የአይር ንብረት ለውጥ ጋር በተገናኘ ነው፡፡ በጠንካራ የመንግሰት አስተዳደር እራሳቸውን ላዋቀሩ በሌሎች አገራት፣ ይህ አይነቱ ድርቅ በሚከሰትበት ወቅት ከመንግሰት የመጠባበቂያ በጀት እና የእህል ክምችት በመጠቀም ችግሩን ለመቋቋም ጥረት ይደረጋል፡፡ እንዲህ አይነቱ መሠረት የሌለው መንግሰት እና ሕዝብ ደግሞ በለጋሽ አገራት የገንዘብ ድጎማና የምግብ እርዳታ ይደረጋል ፡፡ በተለይ ደግሞ አምባገነን መንግስታት በሚመሩት አገር የደርቅ ችግር በሚከሰትበት ወቅት ችግሩን አፍኖ መያዝ ዋንኛ መገለጫቸው ነው፡፡ እንደምክንያትነት የሚነገረው “እረዳት አያስፈልገንም እራሳችን ችለናል” የሚል ባዶ ቀረርቶ ነው፡፡
Saturday, 18 July 2015
አሜሪካኖቹ ዲፕሎማቶች የኢትዮጵያ መንግስትን አስጠነቀቁ
**የኦባማ ጉብኝት ለውይይት እንጂ ወንጀለኛን መንግስት ለማጽደቅ እንዳልሆነ አስረዱ
** “የተፈቱት የዞን ዘጠኝ ጋዜጠኞች ፓስፖርታቸው እንኳን እንዳልተመለሰ እናውቃለን:: መጀመርያውኑ መታሰር እልነበረባቸውም:: ሲፈቱም አፈታታቸው ሙሉ አይደለም”
ዛሬ እዚህ ዋሺንገተን ዲሲ ላይ ጠንካራ ውይይት ሲካሄድ ነበር:: ውይይቱ የኦባማን የምስራቅ አፍሪካ ጉዞ በተመለከተ ሲሆን : አሜሪካኖቹ መራር መልሶችን ሲመልሱ ተደምጠዋል::
የኦባማ ጉብኝት ለአምባገነኖች ሽፋን መስጠት ሳይሆን ሌሎች በርካታ ዓላማዎች እንዳሉትም አስረድተዋል::
በውይይቱ የዞን ዘጠኝ ጋዜጠኞች አስር ፈጽሞ ያልተገባ መሆኑን ጠቅሰው: ሲፈቱም ሙሉ ነጻነት እንዳልተሰጣቸው ፓስፖርታቸው እንኳን እንዳልተመለሰላቸው አስረድተዋል::ከዚሁም ጋር በተያያዘ ሰሞኑን አቶ ኃይለማርያም ኤርትራን ስለመምታት የተናገሩትን ዛቻ በተመለከተ ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል:: ኢትዮጵያ የኤርትራን ድንበር ጥሳ እንዳትገባና ብትገባ ግን አሜሪካ እንደምታወግዘው ገልጸዋል::
ሌሎችም ሌሎችም ውይይቱ ይህን ይመስል ነበር ::
Friday, 22 May 2015
የወያኔ በጉልበት የምረጡኝ ዘመቻ (ከ አዲስ ብርሃኑ)
ንብን ምረጡ ማለት ከጀመሩ ሰነባብተዋል ። ለአገር እድገት፤ ለብለጽግና ፤ለእኩልነት ፤የተጀመረውን እድገት፤ ለማስቀጠል እያሉ...... እያሉ.... መንገድ ተሰራ፤ ህንጻ ተሰራ ፤ስልጣኔ ገባ ፤ይህን ሁሉ በዘመነ ኢህአዲግ ነው ብለው ይናግሩናል። ይህን ማለታቸው ጥሩ። ምንም ተቃውሞ የለኝም ።
አንድ ኢትዮጵያዊ የፈለገውን የመከተል እና የማመን ጉዳይ ነው ። ሌላም ሌላም ይጨምሩ ስለነሱ ማውራት ሳይሆን ለኛም እድል ስጡን እኛም ስለ ኢትዮጵያ የምነለው ነገር አለ ስለ ወያኔም የምንነቅፈው ነገር አለን ይህ ነው ቁምነገሩ ፍርድ እና ውሳኔውን ለሕዝብ በመተው ሕዝብ የመረጠውን እንዲመራው ማድረግ ግድ ይላል።
ወያኔ ኢትዮጵያን ማስተዳደር ከጀመረ የማይታወቁና የማይፈለጉ ሃሳቦች እና ነገሮች ገብተዋል። ያም ህዝብ ወዶ ሳይሆን በግድ የህዝብ ሃሳብ ተጥሶ የአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ሃሳብ እና አላማ እየተንጸባረቀ ነው። ባንዲራው ላይ ከተለጠፈችው ኮከብ ብንጀምር ከ90%
በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን የኮከብ ምልእክት አርማ ያለውን ባንድራ አይቀበለውም ።የኮከቡ ትርጋሜውም ወይም አላማው ሌላ ነው። ኮከባ የምትገልጸው የስይጣንን አምላኪወችን ሲሆን በኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ የተለጠፈው ኮከብ ሶስት ትረጔሜ አለው እነሱም እንደሚከተሉት ናቸው።
1 የኢትዮጵያን ህዝብ በሰይጣናዊ ሃይል ለማፍዘዝ ፦
2 ስይጣን ፍቅር ስለማያውቅ መለያየት እና መጣላት በኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ ለማስረጽ፦
3 የኢትዮጵያ ህዝብ አውቆም ሆነ ሳያውቅ የሰይጣን ምልክት የሆነውን የሰይጣንን ምልክት እንዲያውቅ እና ክፋታዊ የሰይጣንን አሰራር እንዲለማመድ ለማድረግ ነው።
በዚህ ዙርያ ትንሽ ብዬ ወደ ወያኔ ወደሆነችው አርማ እሄዳለው
በኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔ ከገባ ጀምሮ የአገሬ ህዝብ ውስጥ ብዙ ክፋት አብሮ ገብቱአል። ለዚህም ኮከባ የወለደችው ወይም ያፈራችው ፍሬ ስናይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ፍቅር ጠፍታል ። የኢትዮጵያ ህዝብም ብርን እና ጥቅምን አምላኪ ከመሆኑ የተነሳ ወንድም ወንድሙን ፤እህት እህቷን፤ ወላጆች ልጆቻቸውን ፤አሳልፈው ይስጣሉ። ሁሉም ስልጣን ናፋቂወች ሆነዋል። አባት ከልጁ፤ እህት ከወንድም፤ ዘር ከዘር ፤ጎሳ ከጎሳ ፤ሃይማኖት ከሃይማኖት፤ ኢትዮ ጵያ ውስጥ ከእለት ወደ እለት ግጭቶ ች እየተበራቱ ጥላቻወች በሰፊው እየታዩ ነው። እናት ሌባ ልጅ ቀማኘ የሚለው ቢሄል (አባባል) በአሁን በዘመነ ወያኔ እያየነው ነው። መሪዎች ተብዬዎች ሌባ ሎሌዎች ደግሞ ቀማኞች የሆነች ሐገር ከመሰለች ሰነባብታልብ ።የጠፋው ፍቅር እንዲመለስ እና የተወሰድብን ክብር እንዲመጣ የወያኔ አዚም የሆ ነችውን ኮ ከብ ከኢትዮጵያ ምድር ማጥፋት መቻል አለብን። ይህ ኮከብ ቢሄር ቤሄረስቦችን የሚወክል ሳይሆን ጥላቻና መለያየትን የሚያሰፍን ፍቅርን የሚያጠፋ የሰይጣንን ስረአት የመከተል እና የሠይጣንን አርማ ከፍ አድርጎ የማሳየት ስራ ነው።
ወደ ንብ ስንመጣ ደሞ ንብን ምረጡ... ንብን ምረጡ ...እያሉ መለፍለፍ ከጀመሩ ሰንብተዋል መረዟን ብቻ እንጂ ማሯን የማናየውን ንብን ፤በየአገሩ እየዞረች እሾኴን የምታራግፈዋን ንቧን፤ ማሯን ለንጉሶቻ ብቻ የምታበላዋን ንቧን ፤ህብረተሰባን ማሯን ታበላን ይሆን ብሎ የሚጠብቃት ተስፈኘዋን ንቧን ፤ይችን ንብ ነው ምረጡ የሚሉን።
የንብ በሀሪ የአንድ ቀፎ ንብ ከሌላ ቀፎ ንብ ጋር በፍጹም አይሰማማም ተሳስታ አንዷ ንብ ወደሌላ ቀፎ ከሄደች ይገድሏታል። ወያኔም ልክ የንብ በሀሪ ነው ያለው። ከወያኔወች ድርጅት ውጪ የሌላ ድርጅት የሆነ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲኖር አይፈለግም ።
ንቦች ማራችውን የሚሰሩት ለራሳችው እና ለንጉሳ ቸው ብቻ ነው። ወያኔዎችም የሚሰሩት ለራሳችው እና ለሹማምቶቻችው ብቻ ነው።
ንቦች ለማር መስሪያ እንዲሁም ለቀፎ አገልግሎት የሚሆነውን በሙሉ የሚጠቀሙት ክቀፎአቸው ወጥተው በሰአት 100 ኪ. ሜ ያህል
በመብረር ከአካባቢያችው ስብሰበው ወደቀፎአቸው የገባሉ። ወያኔዎቸም የኢትዮጵያን ንብረት በሙሉ በሁሉም አቅጣጫ በመዘዋወር እየዘረፉ ለራሳቸው ያክማቻሉ። ንቦች የራሳቸው ባልሆነ ነገር ማራቸውን እየሰሩ የሌላ ቀፎ ንብ ግን ወደነሱ ቀፎ እንድትገባ አይፈልጉም ወያኔም ምንም ቅሬታ በሌላችው ስዎች የሌላውን ህብረተሰብ ሃብት ለመጠቀም ይስበሰባሉ። ሊላው ህብረተሰብ ወደ እነሱ ሲጠጋ ግን ያጠፉታል ።ስለዚህ የንብን ማር መብላት የሚችለው የቀፎወቹ ንቦች ብቻ ናቸው። የኢትዮጵያንን ሃብት እየበላ እና እየተጠቀመ ያለው ብቻውን ወያኔ ነው።
ኢትዮጵያ ማር ነች ማርን ደግሞ ሁሉም ይፈልጉታል አንድም ለመብላት አንድም ለመድሃኒት። ማር መብላት ካማሮት ወደ ንብ ቀፎ ባዶ እጅ አይኬድም እንደጭስ ያለ መከላከያ እና ማሩን መቁረጫ ቢላ ያስፈልጋል። ካለበለዝያ ግን በመርዝ ተወግተው ይሞታሉ። ወያኔም እንደዚሁ ነው የኢትዮጵያን ሃብትና ንብረትን የብቻው አድርጎ ማስተዳደር ከጀመረ ሰንብታል ስለዚህ ኢትዮጵያ የምትባለው አገር የወያኔ ብቻ መስሎ ከታያቸው ሰንብታል። የኢትዮጵያ ሃብት የኢትዮጵያን እንጂ የጥቂቶች ብቻ አይደለችም ብሎ ለመጠቀም እና ለሁሉም ለማዳረስ ባዶ እጅ ተኪዶ አይሆንም ።በባዶ እጅ ከተኬደ በመረዛቸው ወግተው ስለሚገሉ መከላከያ አድርገን ኢትዮ ጵያን ማዳን ግድ ይለናል። ስለዚህም ምርጫ ..ምርጫ.... የሚለው የወያኔ የማደናገርያ ዘዴ ነው እና ይህ ምርጫ አልጫ እንደሆነ እና ትርጉም የሌለው መሆኑን ልንረዳው ይገባል። አልጫ የሆነው ምርጫ የሚለወጠው አልያም የጣፈጠ የሚሆነው የሁሉም ኢትዮጵያዊ የነቃ ተሳትፎ ሲያደርግ ነው። ንብን በማጥፋት በመርዙ ከመወጋት እና ከመሞት የኢትዮጵያ ሕዝቡ ነጻ ሁኑ። ባንዲራው ላይ ያለችውን ኮከብ በማስወገድ የሰይጣንን መንፈስ የኢትዮጵያ አርማ ከመሆን እንከላከል እላለው።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!!!!
ከ አዲስ ብርሃኑ
Email.. berhanu.addis@yahoo.com
Friday, 15 May 2015
በፍርሃት ውስጥ ያለው የኢሕአዴግ ሥርዓት የማዕከላዊ ዕዝ ወታደሮች ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ መመሪያ አወረደ!
የኢህአዴግ ስርአት የማእከላዊ እዝ ወታደሮች ከቦታ ወደ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ መምሪያ እንዳወረዱላቸው ምንጮቻችን ገለፁ ሲል የደህሚት ድምጽ ዘገበ:: በአዲ-ኮኮብ የሰፈሩት የማእከላዊ እዝ የበታች አመራር ወታደሮችና ተራ ወታደሮች ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር እንዳይገናኙና ወደ አዲ-ዳዕሮና ሸራሮ እንዳይንቀሳቀሱ ተከልክለው እንደሚገኙ የገለጸው የደህሚት ድምጽ እነዚህ የበላይ አመራሮች ሰራዊቱን በመሰብሰብ በአዲ-ዳዕሮ፤ አዲ ነብሪ ኢድ፤ አዲ-ሃገራይ፤ ሸራሮና አካባቢው በአጠቃላይ በአካባቢው የሚገኝ ህብረተሰብ የትህዴን አባል ሰለሆነ የምናጣራው ነገር አለን መንቀሳቀስ ክልክል ነው በማለት ትእዛዝ እንዳወረዱላቸው ለማወቅ ተችሏል። በተጨምሪም- ወታደሮቹ በአካባቢው ህብረተሰብ ላይ ጥላቻ እንዲያሳድሩና ከሱ ጋር እንዳይወግኑ የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ቅስቀሳ ሲሰጥ የሰነበተ ሲሆን ስርአቱ ከህዝብ ተነጥሎ በጠምንጃ ሃይል ብቻ የቆመ እንደሆነ በሚገባ ሰለሚያውቅ ወታደሮቹ ደግሞ ስርአቱን በመተው ከህዝባቸው ጋር እንዳይወግኑ በመስጋት የመነጨ መሆኑን ወታደሮቹ በሚገባ እንደተረዱት ለመረጃ ምንጩ የደረሰው መረጃ አስረድቷል።
Thursday, 7 May 2015
የቁልቁለቱን ጉዞ እናስቁም፤ ውርደት ይብቃን!!!
የህወሓት አገዛዝ ፋሽስታዊ ባህርያት እያደር መረን እያጣ፤ ነውረኛ እየሆነ መጥቷል። በአሳለፍነው ሣምንት ብቻ እንኳን አስነዋሪ ይዘት ያላቸው ሁለት ፋሽስታዊ ክስተቶችን አስተውለናል።
አንዱ በምርመራ ስም በታሳሪዎች ላይ የሚደረገው አሳፋሪ ሰቆቃ ነው። በገላቸው በሚያፌዙና በሚሳለቁ ተቃራኒ ፆታ መርማሪዎች ፊት ለሰዓታት ተመርማሪዎች ራቁታቸውን እንዲሆኑ የሚደረግበት እና እየተፌዘባቸው የሚደበደቡበት ሥርዓት መኖሩ የጉዳቱ ሰለባዎች ይፋ ሲያወጡ እፍረቱ ለመርማሪዎቹ ብቻ ሳይሆን ይህንን ጉድ ተሸክመን ለኖርነው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ነው። በተለይም ደግሞ እንዲህ ዓይነት ክብረነክ ሰቆቃ በሴቶች ላይ እየተፈፀመ መሆኑን ስንሰማ አገራዊ ውርደቱ ያሸማቅቀናል። እንዲህ ዓይነቶችን በሰው ስቃይና እፍረት የሚዝናኑ ጉዶችን ተሸክመን የምኖር መሆናችን ሁላችንን ያዋርደናል። ይህንን አስነዋሪ “የምርመራ ዘዴ” ያጋለጡት የዞን 9 ብሎገሮች፣ ጋዜጠኞችና ፓለቲከኞች ክብርና ሞገስ የሚገባቸው ጀግኖች ሲሆኑ የተዋረዱት እነሱ ሳይሆኑ እኛ ኢትዮጵያዊያን መሆናችን ሊሰማንና “ውርደት በቃ” ልንል ይገባናል።
ሁለተኛው አሳፋሪ ድርጊት ደግሞ ወገኖቻችንን በግፍ ባረደው አይሲስ በተሰኘው አሸባሪ ድርጅት ላይ የህወሓት አገዛዝ የተለሳለሰ አቋም ወስዷል ብለው ራሱ ህወሓት በጠራው ሰልፍ ላይ ተቃውሞዓቸውን ባሰሙ ወጣቶች ላይ አገዛዙ የወሰደው የኃይል እርምጃና ከዚያም ወዲህ እየተደረገ ያለው ነገር ነው። አገዛዙ ለፕሮፖጋንዳው ይጠቅመኛል ብሎ በጠራው ሰልፍ ወጥተው ተቃውሞዓቸውን የገለፁ ወጣቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተደብድበዋል፤ በጅምላ ወደ እስር ቤቶች ተግዘዋል። የአገዛዙ ካድሬዎች ወገኖቻችንን የፈጀውን አይሲስን በመቃወም ፋንታ የራሱ የህወሓትን ውል አልባ ህግ አክብረው በመንቀሳቀስ ላይ ያሉትን ሰማያዊ ፓርቲ፣ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን እና አረና ፓርቲን እየወነጀሉ መሆኑ አጅግ አሳፋሪ ነገር ነው። የአይሲስን አረመኔአዊ ድርጊት ከኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ጋር ለማገናኘት በህወሓት የደህንነት ቢሮ አማካይነት እንቅስቃሴ መጀመሩ እየተሰማ ነው። ለወጣቱ በብዛት መሰደድ በምክንያትነት የሚያቀርቡት ደላሎችን መሆኑ አላዋቂነት ሳይሆን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ቅራኔው በኢትዮጵያዊያን መካከል እርስ በርስ እንዲሆን ያለመ መሠሪነት ነው። ከዚህም አልፎ የትግራይ ወጣቶችን ነጥሎ በመሰብሰብ “ትምክህተኞች ሊበሉህ ነውና ታጥቀህ ሳይቀድሙህ ቅደም” እያሉ መቀስቀስ በመንግሥት ደረጃ የእርስ በርስ እልቂትን ከማደራጀት ተለይቶ አይታይም። የሥርዓቱ ይሉኝታ ቢስነት የደረሰበት ዝቅጠት ገላጭ ከሆኑ ነገሮች አንዱ “እስከምርጫ መጨረሻ ድረስ ልጆቻችሁን አስረን እናቆይላችሁ” እያሉ ወላጆችን እስከመጠየቅ መድፈራቸው ነው።
ከላይ በአጭሩ የተዘረዘሩት ኩነቶች የሚያረጋግጡት ህወሓት የተማከለ አመራር አጥተው መንገድ የጠፋቸው፤ ሆኖም ግን እጃቸው ውስጥ የገባው ስልጣንና ሀብት ላለማጣት ምንም ነገር ከማድረግ የማይመለሱ አውሬዎች ስብስብ መሆኑ ነው። እንዲህ ዓይነቱን የአውሬዎች ስብስብ የሚገዛው የህግም ሆነ የሥነ-ምግባር ገደብ የለም። ህወሓት እስር በርሳችንን አባልቶ አገራችንንና ሕዝቧን ወደ ማንወጣው አዘቅት ከመክተቱ በፊት ራሱ ህወሓትን ማስወገድ እና በምትኩት ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን መገንባት የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው። ይህ ካላደረግን አሁን በወህኒ ቤቶች የሚደረገው ዜጎችን ልብስን አስወልቆ የማዋረድ አስነዋሪ ተግባር ነገ በአደባባዮች የማይደረግ ስለመሆኑ ምንም ማረጋገጫ የለንም። ይህ ትውልድ ኃላፊነቱ ካልተወጣ ህግን አክብረው ከአገዛዙ የተለየ ሀሳብ እናራምዳለን የሚሉ ወገኖቻችን በሙሉ አደጋ ውስጥ ናቸው። በህወሓት መሠሪ ተግባራት ሳቢያ በክርስትናና እስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን መካከል ያለው መግባባት እንዲሻክር እየተደረገ ነው። ዜጎችን በማዋረድ የሚደሰት አገዛዝና ለመዋረድ የፈቀደ ሕዝብ እስካለ ድረስ የቁልቁለቱ ጉዞ መጨረሻ የለውም። ይህንን ማስቆም ያለብን እኛ ሁላንችንም ነን። በአደባባይ መደራጀት ሲከለከል በምስጢር መደራጀትን መልመድ የኛ ኃላፊነት ነው። የኢትዮጵያ አርበኞች ድል መታሰቢያ በዓልን ስናከብር ከቀደምቶቻችን ልንወርስ ከሚገቡን እሴቶች አንዱ ለክብራችን ዋጋ መክፈል ያለብን መሆኑን ጭምር ነው። የኢትዮጵያዊያን ክብር በወያኔ ሲዋረድ እያየን ዝምታን ከመረጥን ከዚህም የባሰ እንዲመጣ መፍቀዳችንን እንወቀው።
አርበኞች ግንቦት 7:የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የዜጎችና የአገር ውርደት ይብቃ! በተባበረ ክንድ ህወሓት ይወገድ፤ በምትኩም ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመመሥረት መሠረት እንጣል፤ ይህንን ታላቅ ኃላፊነት ለመወጣት በኅብረት እንነሳ ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
Source www.patriotg7.org
Monday, 6 April 2015
ወቅቱ የተግባራዊ ትግል ነው!
ለገዛ ራሱ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና ለኢትዮጵያ ቅን የሚመኝ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ህወሓትን ለማስወገድ ተግባራዊ ትግል ውስጥ መሳተፍ የሚኖርበት ወቅት ላይ እንገኛለን። በዚህ ወሳኝ ወቅት ከዳር ሆኖ መታዘብ ዘረኛውን፣ አምባገነኑን፣ ፋሽስቱን ህወሓት እንደመደገፍ ይቆጠራል።
ዛሬ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ህሊናውና አቅሙ በሚፈቅድለት የትግል ዘርፍ የመሰማራት ሰፊ እድል ተፈጥሮለታል። በዚህም መሠረት የህወሓትን አፈና በጠነከረ ክንድ ለመመከት የቆረጡ ኢትዮጵያዊያን ወደ በረሃዎችና ተራራዎች አቅንተዋል። ብዙዎች በመንገዱ ላይ ያሉ ጋሬጣዎችን ተቋቁመው እየተቀላቀሏቸው ነው። በደል የመረራቸው ሌሎች በርካታ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በቡድን ለነፃነታቸው ዘብ ቆመው በህወሓትና አገልጋዮቹ ላይ እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል። ይህ የሚበረታታ እና ተቀናጅቶ ሊጠናከር የሚገባው ጉዳይ ነው።
አሁን ያለንበት ጊዜ ልዩ የትግል ወቅት ነው። ትናንት በከተሞች ይካሄድ የነበረው ፀረ ወያኔ ትግል ዓይነተኛ መታወቂያው ሕዝባዊ ተቃውሞ ነበር። ዛሬ ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሯል። በተለይ በአገዛዙ ፈቃድ የሚደረጉ ተቃውሞዎች ፋይዳ ቢስ ሆነዋል። በአገዛዙ ፈቃድ በሚደረጉ ተቃውሞዎች ለውጥ እንደማይመጣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በማያሻማ ሁኔታ ተረድቷል። ስለሆነም ትግሉ ወደ ሕዝባዊ እምቢተኝነት አድጓል።
ዛሬ ከዚህ በፊት ያልተሞከሩ የትግል ስልቶች ተግባራዊ እየሆኑ ነው። በዚህ ረገድ የሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የተቀናጁ ርምጃዎች በአርዓያነት የሚጠቀሱና የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ የሚሹ ናቸው። እነዚህ የሕዝባዊ እምቢተኝነት ተግባራት የእምነት አጥር ሳይለያየን ፍትህ የተጠማን ዜጎች ሁሉ ልንተገብራቸው የሚገቡ ናቸው።
ለምሳሌ፣ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን በተወሰኑ ቀናት መዝጋት በተቀናጀ ሁኔታ ከተደረገ ከፍተኛ ውጤት ሊያመጣ የሚችል፤ በሙስሊም ወገኖቻችን ግንባር ቀደም መሪነትና አስተባባሪነት ተሞክሮ በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል መሆኑ የታየ አንድ የትግል ስልት ነው።
በአሁኑ ወቅት ተግባራዊ በመደረግ ላይ ያለው ሣንቲሞችን የመሰብሰብ ዘመቻም ሌላ ከዚህ በፊት ያልተሞከረ፤ በተጨማሪ እርምጃዎች ከታገዘ ህወሓት መራሹ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን ገንዘብ መቆጣጠር የማይችልበት ደረጃ ላይ ሊያደርስ የሚችል ጉልበት ያለው ስልት ነው። ውሳኔው ሣንቲሞችን ብቻ ሳይሆን የወረቀት ኖቶችንም ሲያካትት በዝውውር ላይ የሚኖረውን ገንዘብ ብዛት የሚቆጣጠረው ህወሓት ሳይሆን በደል ያንገሸገሸው ሕዝብ ይሆናል። በባንኮች ያለ ተቀማጭ ገንዘብ በማውጣትም የህወሓት የፋይናንስ ተቋማትን ማሽመድመድ ሌላ ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል ስልት ነው። በእነዚህ እርምጃዎች የተለማመደ ሕዝብም ወደ ግዢ እቀባ፤ ለተወሰኑ ቀናት ከቤት አለመውጣት ብሎም “ግብር አልከፍልም” ወደማለት ሊሸጋገር ይችላል።
እንዲህ ዓይነቱ ስልቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ግን የመላው ሕዝብ ተሳትፎ እና የተቀናጀ አሠራርን ይፈልጋል። ለምሳሌ፣ ሰብስቡ ሲባል መሰብሰብን፤ በትኑ ሲባል መበተን ይጠይቃል። እንዲህ ዓይነት የተቀናጁ የጋራ እርምጃዎች በአምባገኑ የህወሓት አገዛዝ ላይ ከሚያደርሱት ጥቃት በተጨማሪ በኢትዮጵያዊያን መካከል ያለውን መግባባት ያጠናክራሉ። እንዲህ ዓይነት የተቀናጁ የጋራ እርምጃዎች በማኅበረሰብ ቡድኖች መካከል አዎንታዊ መስተጋብር ለመፍጠር የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ ነው።
አሁን አገራችን የምትገኝበት ሁኔታ በጥሞና ሲጤን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይነጋገር መግባባት፣ እርስ በርሱ መናበብ የሚችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑ መረዳት ይቻላል። ይህ ስነልቦናዊ ዝግጅት ደረጃ በደረጃ ጠንከር ያሉ እርምጃዎችን ለመውሰድ ያዘጋጀናል።
በማናቸውም የጋራ እርምጃዎች ለግል ጥቅሞቻቸው ቅድሚያ የሚሰጡ፤ ራሳቸው “ብልጥ” አድርገው በማየት በተፈጠረው ሁኔታ መጠቀም የሚፈልጉ፤ በሌላው ድካም ለማትረፍ የሚሯሯጡ ሰዎች መኖራቸው የማይቀር ነው። ህወሓት ለሃያ አራት ዓመታት ኮትኩቶ ያሳደገው የአድርባይነት ባህልም ሌላው እንቅፋት ሊሆን እንደሚችል መገመት ቀላል ነው። ድህነት ደግሞ በገዢዎች ላይ ጨክነን የመነሳት አቅማችንን እንደሚያዳክም የታወቀ ነው። ሆኖም ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፊቱ የቀረበለት ምርጫ “ባርነት ወይስ ነፃነት” መሆኑን የተገነዘበበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።
በዚህም ምክንያት ለህወሓት ባርነት ከመገዛት ነፃነትን የሚመርጥ ዜጋ ሁሉ ዋጋ ለመክፈል መዘጋጀት ይኖርበታል። ለሁላችንም የሚሆን የትግል ዘርፍ መኖሩ የሕዝቡን ተሳትፎ ከፍ ያደርገዋል። የሁለገብ ትግል ስትራቴጂ ጥቅሙም እዚህ ላይ ነው። ማንም የማንም ነፃ አውጭ አይደለም። ሁላችንም ተባብረን ሁላችንንም ነፃ እናወጣለን።
አርበኖች ግንቦት 7፡ የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ “ትግላችን ዘርፈ ብዙ ነው፤ ተግባራዊ ትግል የሚደረገውን በሁሉም ቦታዎች ነው፤ እርጃዎቻችን እናቀናጅ፤ ወቅቱ የተግባራዊ ትግል ነው” ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
Friday, 27 March 2015
የኛ የኢትዮጵያውያን ጥያቄ ስር ነቀል አብዮታዊ ለውጥ ጥያቄ ነው
ኢትዮጵያውያን ለነጻነታችን ዋጋ መክፈል የጀመርነው ከጥንት ጀምሮ መሆኑ ይታወቃል:: በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶየሚገኘው የዘረኛውና ቡድናዊው አገዛዝ በዜጎች ላይ ከፍተኛ በደል በማድረስ ላይ ይገኛል:: ከዚህ ጨቋኝ አገዛዝ ለመገላገልበአንድነትና በመተባበር ለነጻነታችን መታገል አለብን:: ላለፉት 24 አመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተቀመጠውንዘራፊውን እና ጨቋኙን የወያኔ ጁንታን ለመቅበር የአንድነት እና የለውጥ ሃይሎች ልዩነቶቻችንን በማቻቻል በጋራ ልንታገልየሚገባና ለውጥ ልናመጣ የሚገባ ችላ የማይባል ዋነኛ ጉዳይ ነው። በህዝባችን ላይ ከፍተኛ እንግልት፣ እስር፣ ሰቆቃ፣ ግድያወዘተ እየፈጸመ የሚገኘው የህዝባችንና የሃገራችን ጠላት ወያኔ እና ወያኔ ብቻ ነው::
ባሳለፍናቸው መራር የትግል አመታት ውስጥ በቅርቡ እንዳየነው የተቃዋሚዎች በመዋሃድና አንድነትን ከመፍጠር ይልቅ እርስበእርስ መፈራረጅና መወነጃጀል ለስልጣን መሮጥ እንዲሁም ለስም እና ለዝና መትጋት ነው:: ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተረፈው ነገርቢኖር ከጭቆና ወደ ባሰ ጭቆና ማቅ ውስጥ ከመዘፈቅ ውጪ ፍጹም የናፈቀውን የነጻነት አየር እንዲተነፍስ አላደረግነውም።የተቃዋሚ ሃይሎች ጥንካሬ እንዲጎለብት በየድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እንከኖች በማጥራት በጋራ እና በተመቻቸ የሃሳብ መግባባትተቻችሎ እና ተግባብቶ የትግል ስትራቴጂን ከግብ ለማድረስ ህብረ-ብሄር የሆኑት የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር እና ግንቦት7 እንዳደረጉት ለአንድነትና ለትብብር ተግቶ መስራት ይጠበቅብናል። በአሁኑ ወቅት ይህንን ዘረኛ ስርዓት ለማውረድ በውስጥምሆነ በውጭም ትግሉ በስፋት ቀጥሎ ይገኛል:: ወያኔ እስኪወድቅና ህዝባችን ድል እስኪቀዳጅ ድረስ ሊቀጥል የሚገባው ትግልእንደመሆኑ መጠን ከበፊቱ በተሻለ ሁኔታ የተያዘው ትግል በአሁኑ ሰአት ወያኔን እያፍረከረከ በፍርሃት እንዲሸበር አድርጎታል::
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል! የኛ የኢትዮጵያውያን ጥያቄ አብዮታዊ የለውጥ ጥያቄ ነው። የፖለቲካ አስተዳደር ለውጥ ፣የኑሮ ውድነት የሚያላቅቅ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ለውጥ፣ በጋራ ህብረተሰባዊነትና እኩልነት ላይ የተመሰረተ አገዛዝ ወይንም መንግስትእንደምናገኝ የሚያረጋግጥልን ለውጥ እንፈልጋለን፡፡ የማህበራዊና ፍትህ እኩልነት ለውጥ፣ የነጻነት እና የመብት ማግኘት ጥያቄ፣ከመንግስት ነጻ የሆነ ፍርድ ቤት፣ በሃገራችን ተዘዋውረን በፈለግነው ቦታ የመስራት እና የመኖር ጥያቄ የሚያረጋግጥልን ለውጥእንፈልጋለን፡፡ በሃገራችን ላይ የሃገራችን ባለቤቶች ስንሆን የሚገኘው ብልጽግና እና እድገት ባለቤት መሆናችንን የሚያረጋግጥልንለውጥ እንፈልጋለን፡፡ ይህ ሳይታለም የተፈታ እና የሁሉም የነጻነት ፈላጊ ሃይሎች ጥያቄ ነው። ሰብአዊ መብቶች ለዲሞክሪያሲያዊስርአት ግንባታና ለአንድ ሀገር ልማትና ብልፅግና መሰረታዊ ነገሮች ተደርገው የሚወሰዱ ናቸው፡፡ ዜጎች የሃገራቸው ሃብትባለቤትና የመጠቀምም መብት እንዲሁም ሃሳባቸውን በነጻነት የመግለጽ መብት ሊኖረን ይገባል::
በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉትን ፓርቲዎች መዋቅሮቻቸውን በማጠናከር የውስጥ ድክመቶቻቸውንም በመቅረፍእንዲጠነክሩ የማድረግ ግዴታ ከሁላችንም ከለውጥ ፈላጊ ሃይሎች ይጠበቃል።ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
Sunday, 15 March 2015
ሰማያዊ ፓርቲ ቅስቀሳ እንዳያደርግ እንቅፋት እየተፈጠረበት ነው
ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ቅስቀሳ እንዳያደርግ በፖሊሶች ክልከላና ወከባ እየደረሰበት እንደሚገኝ የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ጉዳይ ኃላፊና ም/ሊቀመንበሩ አቶ ስለሽ ፈይሳ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ዛሬ መጋቢት 5/2007 ዓ.ም ፓርቲው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ቅስቀሳ ያደረገ ሲሆን በባህርዳርና ወላይታ ዞን ፖሊስ የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር ቅስቀሰውን ማደናቀፉን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
ዛሬ ሰማያዊ ፓርቲ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ቅስቀሳ በሚያደርግበት ወቅት የከተማው ፖሊስ ‹‹የምርጫ ቅስቀሳ አልተጀመረም›› ብሎ ያዋከበ ሲሆን የፓርቲው አመራሮችና አባላት ቅስቀሳ መጀመሩን ገልጸው ስራቸውን እያከናወኑ በነበሩበት ወቅት ‹‹ህገ ወጥ ሰላማዊ ሰልፍ›› አድርጋችኋል በሚል ሌላ ክስ 8 የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችንና ሌሎች አባላትን በማሰር ቅስቀሳውን እንዳደናቀፈ የወላይታ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ታደመ ፈቃዱ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ በባህርዳር ከተማ ፖሊስ ‹‹በሞንታርቮ ለመቀስቀስ ፈቃድ ስላላመጣችሁ መቀስቀስ አትችሉም፡፡›› በሚል ፓርቲው ሊያደርገው የነበረውን የምርጫ ቅስቀሳ እንዳደናቀፈ የፓርቲው የምዕራብ ጎጃም ዞን ጊዜያዊ አስተባባሪ አቶ አዲሱ ጌታነህ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ‹ለምን ትከለክሏቸዋላችሁ?› በሚል ህዝቡ ፖሊሶቹን በማፋጠጡ በድምፅ መቀስቀስ ባንችልም በህዝቡ ድጋፍ የቅስቀሳ ወረቀቶችን በማሰራጨት የተሳካ ቅስቀሳ አድርገናል›› ሲሉ አቶ አዲሱ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በዚህ ወቅት ቅስቀሳ ለማድረግ ምንም አይነት ፈቃድ እንደማያስፈልግ የገለፁት አቶ ስለሽ ፖሊስ የሚፈጥረው እንቅፋት ሆን ተብሎ ሰማያዊ ወደ ህዝብ እንዳይደርስ የተቀየሰ ስልት ነው ብለዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም ‹‹የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን በመሰረዝ ፓርቲው ምርጫው ላይ የሚፈጥረውን ጫና ለመቀነስ ጥረዋል፡፡ ይህ አልበቃ ሲልም የቅስቀሳ መልዕክቶቻችን በተደጋጋሚ በሚዲያ እንዳይተላለፉ እያደረጉ ነው፡፡ አሁን ደግሞ ወደ ህዝብ እንዳንደርስ በህገ ወጥ መንገድ በፖሊስ ማስቆም ጀምረዋል›› ብለዋል፡፡
በሌላ ዜና የጅማ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ባልታወቁ ግለሰቦች መዘረፉን የምርጫ ጉዳይ ኃላፊው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹በ02/07/07 ሁለት ሰዓት ላይ አራት ግለሰቦች ጽ/ቤቱን በመስበርና የጽ/ቤቱን ጥበቃ አስፈራርተው በማባረር ለቅስቀሳ የተላከ 6 ሺህ ኦሮምኛ በራሪ ወረቀት እንዲሁም 3 ሺህ አማርኛ በራሪ ወረቀት፣ አንድ የፎቶ ካሜራ፣ አንድ ባነር፣ ለሸካ ዞን ሊላክ የተዘጋጀ 5 ሺህ በራሪ ወረቀት፣ 50 ፖስተር፣ አንድ የእጅ ሜጋ ፎን፣ ሁለት ባነር፣ በርካታ ጋዜጦችና መጽሔቶች ሲዘርፉ የጽ/ቤቱን ኮምፒውተርም ሰብረዋል›› ሲሉ ኃላፊው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡
Wednesday, 4 March 2015
በአገር ሙሉ ጀግና ሞልቶ ወያኔን ጀግና አሉት።
ሀገራችን የጀግና ደሀ አይደለችም ጀግኖች የሞሉባት ሀገር ናት። በየተሰለፍንበት መሰኩ አለምን ያስደመመ ጀግኖች ያፈራች አገር ነች።በትምህርቱ ዘርፍ እስከ ሳይንቲስት የደረሱ የትምህርት ጀግኖች አሉ። በሰዕሉ እስከ የአለም ሎሬት የደረሱ የስእል ባለሞያ ጀግኖች አሉን። በስፖርቱም እስከ ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሌያና የአለምን ክብረ ወሠን የሚሰብሩ ጀግኖች ልጆችን ያፈራች አገር ነች። በኪነ ጥበቡ ጥግ ድረስ የደረሱ የኪነ ጥበብ ጀግኖች አሉን። በምርምሩም አዳዲስ ፈጣሪዎችን የሚፈጥሩ ድንቅዬ እና ብርቅዬ ልጆች አሉን። መቼም ጀግና አጥተን የጀግና ደሀ ሆና አታዉቅም አገራችንን የሚያኮሩዋት ጀግኖች አሉዋት የጀግናም ጀግና። - ወያኔን ጀግና አሉት! በTPLF የትግል ድርሻ ያለው እና ታጋዮች ጭምር ተወዳጅ የሆነውን ታጋይ ኃየሎም አርአያ በትግል ግዜ ሁሌም ካጠገባቸዉ እንዳይለይ የሚፈልጉት በቆራጥነቱ እና በችሎታዉ ታጋዬች በሙሉ የሚተማመኑበት ሀየሎም አርአያ ቀድሞም የጀኔሪል ማእረግ የተሰጠዉ ሰራዊቱ በጣም ስለሚወደዉ አና ስለሚያከብረዉ የተሸበሩት የTPLF መሪ ተብዬዎች ነገ ትልቅ ቦታ እንደሚይዝ እና የወያኔዎችን ኃሳብ ሊቀበላቸዉ እንደማይችል ስለሚያቁ ያንን ከባድ ጊዜያቶችን አሳልፎ የመጣዉን ታጋይ እየተዝናና ባለበት ሰአት አንድ ተራ የወያኔ ካድሬ በበላዮቹ TPLF ሰዎች ትእዛዝ ተሰጥቶት ሳያስበዉ በመሳሪያ ተኩሶ በመምታት ገደለውታል። ይሄ ነዉ የወያኔ ጀግንነት?
በትግሉ ሰአት አብሮአቸዉ የነበሩት የትግራይ ሰዎች ትግሉንም በድል ያጠናቀቁትን የትግራይ ልጆች ከድል በኋላ ከወያኔ ጋር የሀሳብ ልዩነት በመኖራቸዉ ብቻ በድብቅ አየተከታተሉ ከሰላሳ ስድስት ሺህ በላይ ታጋዬችን የገደሉ እንግዲህ እዚህን ገዳዬች ነዉ ጀግኖች የምትሉት?
ሀዉዜን ላይ የወረደዉ የቦብ ዝናብ በደርግ ባለስልጣን ዉስጥ ሆኖ ትዕዛዝ ያስላለፈዉ አና ይህንን ምስኪን ሕዝብ ለድብቅ አላማቸዉ የሰዉ ሀይል ለማግኛ ተበዳይ ለመምሰል ወደ ሀዉዜን ገበያ የወያኔ ወታደር በሙሉ ገብተዋል ተብሎ እንዲነገር አስደርገዉ የትግራይን ሕዝብ ዳር ቆመው ያስፈጁትን ወያኔን ጀግና አሉት።
አዲስ አበባ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ ምንም የጦር መሳሪያ ባልያዙ ንፁሀን ዜጎጀ ላይ የፈሪ ዱላ አንደሚባለው በያዙት መሳሪያ ያለምንም ርህራሄ ህዝቡን የፈጁት ነዉ እንግዲህ ጀግና የምትሉን?
ጋንቤላ ላይ ከመሬታችን አታፈናቅሉን በመሬታችን መኖር እንፈልጋለን ብለዉ መሬታችንን ለባዕዳን አትስጡብን ብለዉ ተቃዉሞ ባሰሙት ንፁሁን የጋቤላ ተወላጆች ላይ ብረት አንስግቶ የፈጀዉና በግዳጅ ከመሬታቸዉ አፈናቅሎ ለባድ የሚሰጠዉን ነው ዉያኔን ጀግና የምትሉት?
በአኝዋከ ህዝብ ላይ መሬታቸዉን በመፈለግ የአኝዋከ ህብረተሰብን ዘግናኝ በሆነ መልኩ የዘር ማጥፋት እልቂት ከደረሰ በኋላ በጅምላ ወደ አንድ ጉድጓድ የከተተዉን ነዉ ጀግና ብላቹ የምትጠሩት?
በኦጋዴን ዉሰ በሱማሌ ተወላጆች ህብረተሰብ ላይ በአየር ቦምብ በማዝነብ የዘር ማጥፋት የፈፀመዉን እና እንደ ሃውዜን ውስጥ እንዳደረጉት ጭካኔ የተሞላበት ስራቸውን የደገሙትን ነዉ ጀግና ያላችኋተው?
አንቦ ላይ በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን መሰረት ተቃዉሞ የወጣዉን የአምቦ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የታጠቀ ወታደር አሰማርቶ ተማሪዎችን መግደል ነዉ እንዴ ወያኔን ጀግና ያሰኘዉ?
ባህር ዳር ላይ ስለሀይማኖት ብለዉ የወጡት ሰላማዊ ሕዝብ ላይ አነጣጥሮ ተኩሶ መግደል ነዉ ጀግና ያሰኛቸዉ ታድያ ጀግና ያሰኛቸዉ ምንድን ነዉ?
ብዕር የያዘ ጋዜጠኛ አንተ አሸባሪ ነህ ብሎ ወደ እስር መጣል ነዉ ጀግንነት? ወይስ የፖለቲካ ሰዎችን ባላቸዉ የፖለቲካ አቋም በመፍራት ብቻ የአሸባሪ ታፔላ እየለጠፉ ወደ ወይኒ መወርወር ነዉ ጀግንነት? ወይስ የተማረዉንም ያልተማረዉንም ሰዉ በኛ መስመር ግባ ካልገባህ መኖር አትችልም ብለዉ ማዋከብ ነዉ ጀግና ያሰኛቸዉ?
ጀግና ማለት በፍቅር ታግሎ በፍቅር የሚያሸንፍ ነዉ። ጀግና ማለት ከባርነት ቀንበር አላቆ ነፃነትን የሚያወርስ እና በነፃነት እንዲኖሩ ማድረግ ነዉ።ጀግና ማለት ስራዉ ከሚናገዉ በበጠ ጏልቶ የሚታይ እና በሰዉም ዘንድ ተቀይነትን ያገኘ ነዉ።
ጀግና ማለት እንደ ዉሻ ላበላዉ የሚጮህ ሳይሆን ለእዉነት የቆመ ለእዉነት የተሸነፈ ለእዉነት የሚኖር እሱ ነዉ ጀግና። መሳርያ ስለያዘ ብቻ ከኔ በላይ ማን አለብኝ ብሎ እየተኯሰ ሰላማዊ ሰዉን የሚገል እሱ ጀግና ሳይሆን አረመኔ ነዉ አረመኔን ደሞ ጀግኖች ያጠፉታል።
ጀግና ማለት ለነሱ የታጠቀ ኃይል በሰላማዊ ሰዉ ላይ ተኩሶ መግደል ከመሰላቸዉ፡ ጀግና ማለት ለነሱ ብዕር የያዙትን ብዕራዉያንን በብረት አስረዉ ማሰቃየት ከሆነ፡ ጀግና ማለት ለነሱ የፓለቲካ ሰዎችን በአአስከፊ ቅጣት መቅጣት ከመሠላው፡ እኔ ግን እላለዉ እነዚህ ጀግና ሳይሆኑ ፈሪ እና እውቀት የጏደላቸዉ ናቸዉ። እነዚህ ጀግና ሳይሆኑ የጨነቃቸዉ ናቸዉ እላለዉ። ፈሪና የጨነቀዉ ሰዉ የሚያደርገዉን ድርጊት እያደረጉት ያሉት።
ጀግናማ ፍቅርን አስተማሪ ነዉ። ጀግናማ ለህዝብ የቆመ ነዉ። ጀግናማ ለሆዱ ያልቆመ ነዉ። ጀግናማ ኢትዮጵያዊው ነው።
To Addis Berhanu
03.03.2015
Email- berhanu.addis@yahoo.com
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/5049#sthash.m7pSsFra.dpuf
Thursday, 26 February 2015
ለአንድ ቀን የሚቆይ የቦይኮት ዘመቻ በድምፃችን ይሰማ ጥሪ ቀረበ
‹‹እስር ከትግላችን አያስቆመንም!›› – ለአንድ ቀን የሚቆይ የቦይኮት ዘመቻ
ነገ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከምሽቱ 12 ሰዓት ስልካችንን እናጠፋለን!
መንግስት ሙስሊሞችን ከያሉበት በማሰር ህገ ወጥ ዘመቻ ላይ መሰማራቱን እና በህዝበ ሙስሊሙ ላይ ግፍ መፈጸሙን በመቃወም ነገ ጁሙዓ ታላቅ አገር አቀፍ ተቃውሞ እንደሚኖረን እና በዛሬው እለትም የተቃውሞው መርሃ ግብር ይፋ እንደሚሆን መገለጹ ይታወሳል፡፡በዚሁ መሰረት እነሆ የነገው አገር አቀፍ ተቃውሟችን በመጠነኛ የቦይኮት ዘመቻ (የራስን መብት በራስ ላይ የመንፈግ ተቃውሞ) የሚጀመር ይሆናል፡፡ኢትዮ ቴሌኮም ለመንግስት ከፍተኛ ትርፍ ከሚያስገኙ ካምፓኒዎች አንዱ ሲሆን
በቀን ከተጠቃሚዎች በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ገቢ ያገኛል፡፡ ሙስሊሙ
ማህበረሰብ ደግሞ የአገሪቱ ግማሽ እንደመሆኑ መጠን በአንድ ቀን ለቴሌ
የሚያስገኘው ገቢ እንዲሁ በሚሊዮን የሚቆጠር ነው፡፡ በመሆኑም የማይናቅ
ቁጥር ካለው ማህበረሰብ የሚያጣው የአንድ ቀን ገቢ ለኢትዮ ቴሌኮም
በሚሊዮን የሚቆጠር ብር አክሳሪ መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ የነገው
ቦይኮት በኢቲዮ ቴሌኮም ካምፓኒ ላይ የሚያተኩረውም ለዚህ ነው፡፡
ነገ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ ሁላችንም ስልካችንን
በመዝጋት ተቃውሟችንን እናሰማለን፡፡ አስቸኳይ ጉዳይ ካላጋጠመን በስተቀርም
ስልካችንን አንከፍትም፤ አንጠቀምምም፡፡
አስቸኳይ ጉዳይ ሲያጋጥመን ለአፍታ ስልካችንን በመክፈት ቶሎ ጉዳያችንን ፈጽመን ወዲያው እንዘጋለን፡፡
ይህንን አገር አቀፍ እና መላ አገሪቱን ያካለለ ዘመቻ ላልሰሙት ሁሉ በማሰማት ለስኬቱ የቻልነውን ሁሉ መጣር ታላቅ ተግባር ሲሆን ለዲናችን ስንል ለምንከፍለው
መስዋእትነትም ከጌታችን አላህ ዘንድ ምንዳችንን እንተሳሰባለን፡፡ አላህ ፈተናውን
እንዲያነሳልንም አጥብቀን ዱዓ እናደርጋለን፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ
አይደለምና!!!
አዎን! አንድነት ያለው ህዝብ ያሸንፋል!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
Sunday, 22 February 2015
‹‹ምርጫ በህዝብ ፍላጎት ሳይሆን በሎተሪ ሆኗል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
አዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 5 ለመጭው ምርጫ ለተወካዮች ምክር ቤት ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ሊቀርቡ የነበሩት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ከቀረቡት 17 ዕጩዎች መካከል በተጣለ ዕጣ ወድቀዋል›› በመባላቸው ለመጭው ምርጫ በዕጩነት እንዳይቀርቡ መደረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል በዕጩነት በቀረቡበት ወረዳ 5 የምርጫ ጣቢያ ኢህአዴግ፣ የትግስቱ አንድነት፣ ቅንጅትን ጨምሮ ሌሎች ስድስት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ያለ ምንም ዕጣ አልፈዋል የተባለ ሲሆን ‹‹የሚያልፉት በዕጣ ነው›› የተባሉት ሰማያዊን ጨምሮ 11 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መካከል ሰማያዊና ሌሎች አራት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ‹‹ዕጣ አልወጣላቸውም፡፡›› ተብሏል፡፡images
ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ሰማያዊ ህዝብ ውስጥ በሰፊው እየገባና እያንቀሳቀሰ ያለ ግንባር ቀደም ፓርቲ ነው፡፡ እንደ ኢህአዴግ ያሉን ጨምሮ ዕጣ ውስጥ አይገቡም፡፡ ሰማያዊ ደግሞ ይህ ነው የሚባል እንቅስቃሴ ከማያደርጉት ፓርቲዎች ጋር ዕጣ ውስጥ ገብቶ ወደቀ መባሉ ዴሞክራሲ ከጅምሩ ጀምሮ የህዝብ ድምጽ ሆኖ እያለ በእኛ አገር ሎተሪ ሆኗል ማለት ነው፡፡›› ብለዋል
ሊቀመንበሩ አክለውም ‹‹ሂደቱ ምንም ይሁን ምን አንድን ፓርቲ ወይንም ተወካይን ህዝብ ነው መምረጥ ያለበት፡፡ ህዝብ የሚፈልገውና የሚመረጥ ፓርቲ ነው ለምርጫ መቅረብ ያለበት፡፡ አሁን ግን እየተባለ ያለው በአንድ በኩል ህዝብ የማይፈልገው ያለ ዕጣ ሲገባ፣ በሌላ በኩል ህዝብ የሚፈልገው ሰማያዊን የመሰለ ፓርቲ ዕጣ ውስጥ ገብቶ አላለፈም እየተባለ ነው፡፡ በአንድ በኩል ህዝብ የተማረረባቸው ያለ ቅድመ ሁኔታ ህዝብን እንደሚያንቀሳቅስ የሚታወቀው ሰማያዊ ደግሞ ህዝብ ስፈለገው አሊያም በጥንካሬው ሳይሆን በሎተሪ ወድቀሃል ተብሏል›› ሂደቱ የተሳሳተ ነው ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ”ሠማያዊ ፓርቲ ከ200 በላይ እጩዎች ተሰረዙብኝ አለ” በሚል ርዕስ አዲስ አድማስ እንደዘገበው —
”የፓርላማ ምርጫ እጩዎች ኢህአዴግ 501፣ መድረክ 303፣ ኢዴፓ 280
የሌላ ፓርቲ አባላትን በእጩነት አስመዝግቧል” – ምርጫ ቦርድ
ሠማያዊ ፓርቲ በተለያዩ ክልሎች ለፓርላማ ካስመዘገባቸው 400 እጩዎች ግማሽ ያህሉ በምርጫ ቦርድ እንደተሠረዙበት ሲገልፅ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ፤ ሰማያዊ ፓርቲ ለምርጫው የሌላ ፓርቲ አባላትን ማስመዝገቡ ህገወጥ እንደሆነ ገለፀ፡፡
ለፓርላማ ኢህአዴግ 501 እጩዎችን፣ መድረክ 303 እጩዎችን፣ ኢዴፓ 280 እጩዎችን አቅርበዋል፡፡ ለፓርላማ ካስመዘገብናቸው እጩዎች ከሁለት መቶ በላይ ተሰርዘውብናል ያሉት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፤ በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በወላይታ፣ በቤንሻንጉል፣ በምዕራብ ጐጃም፣ በከምባታ፣ በሲዳሞ፣ በጋሞጐፋ፣ በአዲስ አበባ፣ በደቡብ ጐንደር እና በሌሎች አካባቢዎች አሣማኝ ባልሆነ ምክንያት እጩዎቻችን ከምርጫ ውጪ ተደርገውብናል ብለዋል፡፡
ፓርቲው የምርጫ አስፈፃሚዎችን እንዳነጋገረ ኢ/ር ይልቃል ጠቁመው፤ እጩዎቻችንን የተሰረዙት ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጣ ትዕዛዝ እንደሆነ ተነግሮናል ብለዋል፡፡ “የሌሎች ፓርቲዎችን አባላት አስመዝግባችኋል፤ ትብብር የሚባል ህገ ወጥ አደረጃጀት መስርታችኋል የሚሉ ምክንያቶችንም ሰምተናል ያሉት ኢ/ር ይልቃል፤ በአዲስ አበባ የተሠረዙብን እጩዎች ግን ግልፅ ምክንያት አልተሰጣቸውም ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከፓርላማ ምርጫ የተሠረዙት እጩዎች የተሠረዙበት ምክንያት እንዲነገራቸው ጠይቀዋል፤ ምርጫ አስፈፃሚዎች የሰጡን ምላሽ፤ “እናንተን ለመመዝገብ እኛ ችግር የለብንም፤ ግን እንዳንመዘግብ ከበላይ አካል ታዘናል፤ በደብዳቤ ምላሽ ልንሠጣችሁ አንችልም” የሚል ነው ብለዋል – ኢ/ር ይልቃል፡፡
በጉዳዩ ላይ ከምርጫ ቦርድ ማብራሪያ ለማግኘት እንደሞከሩና፤ የቦርዱ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ነጋ ዱሪሳ በማመልከቻ ካልጠየቃችሁ መልስ አልሰጥም እንዳሏቸው ኢ/ር ይልቃል ተናግረዋል፡፡
የእጩዎች ስረዛን በተመለከተ ከአዲስ አድማስ ለቀረበላቸው ጥያቄ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፅ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድሙ ጎላ በሰጡት ምላሽ፤ “የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት” የተሰኘ ፓርቲ አባላቱን በሰማያዊ ፓርቲ ስም በእጩነት እንዳስመዘገበ በመግለፁ ነው ምርጫ ቦርድ ጉዳዩን ማጣራት የጀመረው ብለዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ በማያውቀው ሁኔታ ሰማያዊ ፓርቲ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ትብብር መስርቻለሁ በሚል መንፈስ፤ የበርካታ ፓርቲዎች አባላት በሰማያዊ ፓርቲ ስም እጩ ሆነው ቀርበዋል ያሉት አቶ ወንድሙ፤ የደቡብ ኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት ሊቀመንበር ራሳቸው በሰማያዊ ፓርቲ ስም አዲስ አበባ ላይ ተመዝግበው መገኘታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ አንድ ፓርቲ የሌላን ፓርቲ አባል በእጩነት ማስመዝገብ አይችልም፤ ህገወጥ ነው ያሉት የምርጫ ቦርድ ም/ኃላፊው፤ ስለዚህ የአንድ ፓርቲ አባል በሌላ ፓርቲ ስም እጩ መሆን ስለሌለበት አጣርታችሁ መዝግቡ የሚል መመሪያ አስተላልፈናል ብለዋል፡፡
ቦርዱ የሰጠው መመሪያ እጩ እንዳትመዘግቡ የሚል ሳይሆን እያጣራችሁ መዝግቡ የሚል ነው ያሉት አቶ ወንድሙ፤ በዚህ አሰራር ደስተኛ ያልሆነ ማንኛውም ፓርቲ፤ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ቅሬታውን ከምርጫ ጣቢያ እስከ ምርጫ ቦርድ በየደረጃው ማመልከት እንዲሁም ለፍ/ቤት አቤቱታ አቅርቦ ውሳኔ ማግኘት ይችላል ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል ኢህአዴግ፤ ለፓርላማ 501፣ ለክልል ምክርቤቶች ከ1300 በላይ እጩዎችን አቅርቧል፡፡ አራት ፓርቲዎች የተጣመሩበት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ፤ ለፓርላማ 303፣ ለክልል ም/ቤቶች ከ800 በላይ እጩዎችን ያቀረበ ሲሆን፤ ከዚህም ውስጥ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) 168 እጩዎችን ለፓርላማ 475 እጩዎችን ለክልል ምክር ቤት አስመዝግቧል፡፡
በኢትዮጵያ ማህበረ ዲሞክራሲ – ደቡብ ህብረት አንድነት ፓርቲም 83 ለፓርላማ 273 ለክልል ማቅረቡን ጠቁሟል፡፡ ሌላው የመድረክ አባል አረና ፓርቲ 33 እጩዎች ለፓርላማ 70 ለክልል አቅርቧል፡፡ ኢዴፓ በበኩሉ 280 እጩዎችን ለፓርላማ 200 እጩዎችን ለክልል አስመዝግቧል፡፡ ”
Wednesday, 18 February 2015
Ethiopia's Media War: Al Jazeera, The Stream
Ethiopia’s jailed Zone 9 bloggers are on trial this week for terrorism and treason, charges facing more than two dozen journalists, bloggers and publishers. To avoid arrest, 30 journalists fled the country in the past year. The government says they’re criminals, destabilising Ethiopia’s fragile democracy in the name of “press freedom.” Rights groups say they’re victims of repression.
Tuesday, 10 February 2015
የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አባላትና መዋቅሮች ወደ ሰማያዊ ፓርቲ እየጎረፉ ነው
የቀድሞው የአንድነት አባላትና መዋቅሮች በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን ተከትሎ ተጨማሪ የአንድነት አባላትና መዋቅሮች ሰማያዊ ፓርቲን እየተቀላቀሉ እንደሚገኙ የፓርቲው ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስለሽ ፈይሳ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ከጥር 28/2007 ዓ.ም በኋላ ሰማያዊ ፓርቲን ከተቀላቀሉት መካከል የትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ አፋር፣ ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ፣ ሀረር፣ አርባምንጭ፣ ወላይታ፣ ቁጫ፣ ቦንጋ፣ ኢልባቡር፣ ሰሞን ሸዋና የጉጂ የአንድነት መዋቅሮች ሙሉ በሙሉ ከሰማያዊ ፓርቲ መዋቅር ጋር መቀላቀላቸውን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ በቀጣዩ ቀናትም ወደ ሰማያዊ የሚቀላቀሉ መዋቅሮችና በግላቸው የሚመጡ አባላት እንዳሉ ኃላፊው ግልጸዋል፡፡
‹‹በአንድነትና መኢአድ ላይ የተወሰነው ውሳኔ የሰላማዊ ትግሉን ለማዳከም የተደረገ ሴራ ነው›› ያሉት አቶ ስለሽ ፓርቲያቸው ላይ ህገ ወጥ ውሳኔ የተላለፈባቸው የአንድነት አመራሮችና አባላት ተስፋ ሳይቆርጡ ወደ ሰማያዊ ፓርቲ መምጣታቸውና ሰማያዊ ፓርቲም እነዚህን ታጋዮች እጁን ዘርግቶ መቀበሉ የታሰበውን ሴራ ያከሸፈና ሰላማዊ ትግሉን የሚያጠናክር ነው ብለዋለል፡፡ አቶ ስለሽ አክለውም የተፈጠረውን አጋጣሚ በመጠቀም ትግሉን ለማጠናከር ኢትዮጵያውያን የቻሉትን ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡
Thursday, 5 February 2015
በአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጥሰት ዙሪያ መከረ
ህብረቱ ጥር 27፣2007 ዓም በብራሰልስ ቤልጂየም የአውሮፓ ህብረት ጽ/ቤት ውስጥ ለ3 ሰአታት ባደረገው የኢትዮጵያ የሰአብአዊ መብት ግምገማ በኦጋዴን ክልል እና በተቀሩት የኢትዮጵያ ግዛቶች በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ሰቆቃ የአውሮፓ ህብረትና አባል መንግስታት በዝምታ መመልከታቸውን ማብቃት አለበት የሚል ውሳኔ አስተላልፈዋል።
ስብሰባውን ያዘጋጁት የህብረቱ የሶሻሊስትና የዲሞክራቲክ ፓርቲዎች ጥምር ህብረት ፣ ውክልና አልባ ህዝቦች ተቆርቋሪ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው።
በስብሰባው ላይ የኦጋዴን ክልል ፕ/ት አማካሪ የነበረና በክልሉ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በመረጃ በማጋለጥ ላይ የሚገኘው ወጣት አብዱላሂ ሃሰን፣ ተቀማጭነቱ በጄኔቫ የሆነ የአፍሪካ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ባልደረባ፣ አቶ አብዱላሂ ሙሃመድ፣ የኦጋዴን ሴቶች ተወካይ ፣ ጋዜጠኛና የክሬት ትረስ ዳይሬክተር ግርሃም ፌብልስ፣ እንዲሁም በኦሮሞ ሴቶች ላይ የሚደረሰውን ሰቆቃ በማስመልከት ጥናት ያካሄዱት፣ ዶ/ርባሮ ቀኖ በቪዲዮ የተደገፈ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል።
እንግሊዛዊው ግራሃም ፌብልስ በኢትዮጵያ 2 አመታት ቆይታቸው የታዘቡትን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በተለይም በኦጋዴን ክልል በሴቶች ላይ ተፈጽሟል ያሉትን አስገድዶ መድፈር ወንጀል የታዳሚውን ስሜት በነካ መልኩ አቅርበዋል። በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በዜጎች ላይ ሽብርን እያኬደ ነው ያሉት ሚ/ር ፌብልስ የዚህ ሶቆቃ ፈጻሚዎች፣ ከአውሮፓ ህበረትና መንግስታት በእያመቱ ከፍተኛ የገንዘብ እርዳታ የሚያገኙ መሆናቸው እጅግ የሚያሳዝነው ነው ብለዋል።
በጉባኤው ላይ የኦጋዴን ነጻነት ግንባር ተወካይ ዶ/ር ባዳል አህመድ እና አርበኞች ግንቦት7 ተወካይ አቶ አበበ ቦጋለ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጸመ ነው የሚሉትን የሰብአዊና የፖለቲካ መብቶች እረገጣና አስከፊ ሰቆቃ በእየተራ አቅርበዋል።
የአውሮፓ ህብረትን ወክለው በስብሰባው ላይ የተገኙት ወ/ሮ አና ጎሜዝና የእንግሊዝ የፓርላማ ተወካይ ወ/ሮ ጁሊ ዋርድ በየተራ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ መንግስት ከ60 በመቶ በላይ በጀቱን ከአውሮፓ ህበረት እየተቀበለ ዜጎች ላይ እየፈጸማቸው ያለው አስከፊ ሰቆቃዎችን አውሮፓ ካሁን በሁዋላ በዝምታ ማየት የለባትም ካሉ በሁዋላ፣ ኢትዮጵያኖች በአገራቸው እየተፈጸመ ያለውን አፈናና ጭቆና የውች ማህበረሰብ ያስቆምልናል ብለው ከመጠባበቅ ለራሳቸው ነጻነት ልዩነቶቻቸውን በማቻቻልና መለስተኛ ፕሮግራም በማዘጋጀት ህብረት ፈጥረው በአንድነት መታገልና ለለውጥ መነሳት አለባቸው ብለዋል።
የአውሮፓ ህብረት በዘንድሮው ምርጫ ላይ ታዛቢዎችን እንዳይልክ የወሰነው የኢህአዴግ መንግስት በየ5 አመቱ የሚያደርገውን የተሳሳተ ምርጫ በማጀብ ህጋዊነት ለማሰጠት እንደከዚህ በፊቱ ለመተባበር ፈቃደኛ አለመሆኑን ለመግለጽ ሆኖ ሳለ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ግን ህበረቱ በገጠመው የበጀት ችግር ምክንያት ታዛቢ አልክም ብሎአል ብሎ የጀመረው ቅስቀሳ መሰረተ ቢስና የተለመደ ህዝብን የማዘናጊያ ወሬ እንደሆነ ገልጸዋል። የአመቱን 60 በመቶ የሚሸፍን በጀት የሚሰጠው ህብረቱ፣ ኢትዮጵያን የመሰለ ስትራቴጂክ አገር፣ ህብረቱ የገንዘብ እጥረት ገጥሞታል ብሎ ማሰብ ራስን እንደማታለል ይቆጠራል ብለዋል።
ህብረቱ ምርጫው ከመደረጉ ከሚቀጥለው ወር በፊት የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎችንና ሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን በስፋት የሚያሳትፍ ትልቅ ጉባኤ በሚያዚያ ወር ላይ ለመጥራት በዝግጅት ላይ እንዳለ በዚህ ስብሰባ ላይ ተገልጿል።
አንዳንድ የፓርላማ አባላት በዚህ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደግብጽ ህዝብ ሆ ብሎ በመነሳት ከመዒው ግንቦት ምርጫ በፊት አምባገነንነትን ከራሱ ትከሻ ላይ ለማውረድ መነሳት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት በሚቀርብበት የሰብአዊ መብት ጥሰት ላይ አቋሙን እንዲገልጽ ቢጋበዝም ፣ ፈረንሳይኛ ተናጋሪ የሆነ ቤልጂየማዊ ዜጋ የሆነ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሰራተኛ የተገኘ ሲሆን ስራውም መረጃ መሰብሰብ እንጅ አስተያየት መስጠት አለመሆኑን ገልጾ፣ ምንም ንግግር ሳያደርግ ወጥቷል።
አቶ ሲሳይ ዘርፉ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላለፈበት፟ በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
ህዳር 27 እና 28/2007 ዓ.ም በ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ተዘጋጅቶ ለነበረው የአዳር ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ የቅስቀሳ በራሪ ወረቅት ሲበትን ለእስር የተዳረገው የሰማያዊ ፓርቲ አባል አቶ ሲሳይ ዘርፉ ዛሬ ጥር 28/2007 ዓ.ም የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላፈበት፡፡
ታህሳስ 14/2007 ዓ.ም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት ቆርቦ የነበረው አቶ ሲሳይ ዘርፉ ‹‹…‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ› ለመላው ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያዊ ሁሉ….ተብሎ የተጻፈበት በራሪ ወረቀቶች ለህብረተሰቡ ሲያከፋፍል እጅ ከፈንጅ በመያዙ በፈጸመው የሐሰት ወሬን በማውራት ህዝቡን ማነሳሳት ወንጀል…›› በሚል በፌደራል አቃቤ ህግ ለቀረበበት ክስ ያቀረበው የክስ መቃወሚያ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ መደረጉ ይታወሳል፡፡
ከዚህም ባሻገር አቶ ሲሳይ ዘርፉ ጥር 7/2007 ዓ.ም የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበርና ም/ሊቀመንበር የሆኑትን ኢ/ር ይልቃል ጌትነትና አቶ ስለሺ ፈይሳ እንዲሁም የኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ህብረት (ኦህዴህ) ሊቀመንበር አቶ ግርማ በቀለን በመከላከያ ምስክርነት አቅርቦ የነበር ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ‹‹ምስክሮቹ ከወንጀል ድርጊቱ ጋር ቀጥተኛ የሆነ ምስክርነት ሳይሆን የራሳቸውን የፖለቲካ አመለካከት ሚዛናዊነት በጎደለው መልኩ ነው ያቀረቡት፡፡›› በሚል ምስክሮቹ የሰጡትን የምስክርነት ቃል ውድቅ አድርጓል፡፡
አቃቤ ህግም በተሰጠው የጥፋት ውሳኔ ላይ ‹‹ተከሰሽ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ 82(ሀ) 1/ መሰረት ማቅለያው ታይቶለት ከዚህ ቀደም የወንጀል ድርጊት ያልፈጸመ ስለሆነ የምንጠይቀው የቅጣት ማክበጃ የለንም፡፡ ሆኖም ግን በሰራው የወንጀል ድርጊት የመጨረሻው ጣሪያ ውሳኔ እንዲሰጥልን እንጠይቃለን፡፡›› ብሏል፡፡ ፍርድ ቤቱ ለካቲት 3/2007 ዓ.ም የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት በመናገሻ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡
አቶ ሲሳይ ዘርፉ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ዋስትናው ተነፍጎ ቀደም ብሎ በፖሊስ ጣቢያና አሁን ደግሞ ቂሊንጦ እስር ቤት በእስር ላይ ይገኛል፡፡
Sunday, 1 February 2015
Open Letter from Anuak Ethiopian Refugees to the President of the World Bank, Jim Yong Kim
Dear Mr. President,
We are the REQUESTERS, Anuak refugees and asylum seekers based in Kenya (Dadaab, Kakuma and Nairobi) and South Sudan (Gorom), who submitted a complaint to the World Bank Inspection Panel in September 2012. We have written to you twice before but we have never received a response. This is our final appeal and we pray that this time our voice will be heard.
Ethiopia: Stop Land Grabbing and Restore Indigenous Peoples' Lands
We were forced to flee our homeland in Gambella, Ethiopia because we dared to oppose the government’s forced relocation program, known as “villagization”. We Anuaks never consented to give up our ancestral lands, which is the source of our life and our identity. We only moved out of fear. When local farmers did not agree to relocate, at night soldiers came and raped the women and beat the men. Those teachers, agriculture workers and other civil servants who refused to implement this program, including many of us, were TARGETED with arrest and torture. This is why we are living as refugees in neighboring countries today.
Without the billions of dollars provided by the World Bank and other donors through the Protection of Basic Services (PBS) project, the Ethiopian government would never have had the capacity to relocate so many people and grab our ancestral LAND. That is why we filed our complaint to the Inspection Panel and why we begged you at that time to delay the NEXT phase of the project until you could ensure that it would not be used to displace and kill our people.
Now we have been INFORMED about the findings of the Inspection Panel. We know that the investigation found that the World Bank does not track how PBS funds are used on the ground. If the World Bank cannot guarantee that its money will not be used to abuse people, then it should not provide money in this way to the Ethiopian government.
We know that the investigation found that PBS did not follow the World Bank Policy on Indigenous Peoples. We indigenous people have a right to decide about any development projects that affect us and especially our land. We have a right to be consulted and a right to reject any development that we don’t want.
For the past 118 years that we have been living under the control of the central government of Ethiopia, we have never been consulted about any development project or policy that affects our people. Nobody ever informed us that the World Bank was supporting basic services in Gambella or asked for our opinion about the services we want and where and how we want them delivered. Instead we were forced to give up our fertile land and move to dry, forested areas in order to access these services funded by the World Bank. And when we moved with the promise of getting better services, we found that it was all a lie. At the new locations, there were no services and the land we were given could hardly grow food. When the World Bank saw this happening, it should have stopped PBS until the government stopped villagization. If you did that, maybe we would not be refugees today. But since the World Bank CONTINUED to fund PBS 3 after two years of villagization, and after we pleaded with you to stop, the Bank has a responsibility to help us recover what we have lost.
We want our people in Gambella region displaced by villagization PROGRAMME, to return to their ancestral land without fear of retribution. We want SUPPORT to restart their farms, with modern technology like farmers have in other parts of Ethiopia. We want them to grow food on their land for local consumption, rather than working like slaves on big farms owned by foreigners growing crops to export to other countries. We want grinding mills and wells that work in their villages and good roads that go to clinics and markets and not to gold mines. We want a university and a hospital in Gambella region with quality services for indigenous people. We want our people to be consulted and to have ownership of our development.
In the refugee camps where we live in Kenya, South Sudan and Uganda, we are facing insecurity and dire living conditions but we cannot return home or our lives will be in danger. Women are dying from caesarian sections and minor surgeries because of the poor quality of health care. Newcomers are not accepted by UNCHR and so we must share our food rations with them so they don’t starve. After primary school, our youth have nothing to do but sit idle or become addicted to drugs. It is so painful to see our children growing up in a FOREIGN LAND with no future. We need support to develop our livelihoods and our youth need opportunities to go to secondary school and university.
We are very encouraged by the bold agenda you have set for the World Bank and the international community to end extreme poverty and promote shared prosperity. We strongly support YOUR call for equitable and inclusive development in fragile and conflict-affected states. We were especially moved by your statement, published last year in the Washington Post, that “the fight to eliminate all institutional discrimination is an urgent task.”
We are victims of a government that systematically discriminates against indigenous people with dark skin. Because of this discrimination, we have gone from food SECURITY to extreme poverty – living on food aid as refugees. All we are asking is that you live up to your HIGH words and ensure that your institution lives up to its good policies.
Thank you for your listening to us and may the Almighty God bless the work of your hands.
High regards,
Anuak REQUESTERS to the World Bank Inspection Panel
Friday, 30 January 2015
US urges Ethiopia to ensure fair trial to bloggers and journalists
January 30, 2015
(U.S. Department of State) The United States is concerned by the Ethiopian Federal High Court’s January 28, 2015, decision to proceed with the trial of six bloggers and three independent journalists on charges under the Anti-Terrorism Proclamation. The decision undermines a free and open media environment—critical elements for credible and democratic elections, which Ethiopia will hold in May 2015.US on Ethiopian bloggers
We urge the Ethiopian government to ensure that the trial is fair, transparent, and in compliance with Ethiopia’s constitutional guarantees and international human rights obligations. We also urge the Ethiopian government to ensure that the trial is free of political influence and continues to be open to public observation.
The use of the Anti-Terrorism Proclamation in previous cases against journalists, activists, and opposition political figures raises serious questions about the implementation of the law and about the sanctity of Ethiopians’ constitutionally guaranteed rights to freedom of the press and freedom of expression.
Freedom of expression and freedom of the press are fundamental elements of a democratic society. We call on the government of Ethiopia to support freedom of expression and freedom of the press to demonstrate its commitment to democracy as it approaches its May 2015 national elections.
Tuesday, 20 January 2015
ወያኔ የሚመለመል ወታደር አጣ
ወያኔን የሚከዱ ወታደሮች በየቦታው እየተሰማ ባለበት ባሁኑ ሰዓት የሚመለመል ወታደር መጥፍቱ ምናልባትም ወያኔዎቹ ከፍተኛ የራስ ምታት ሳይሆንባቸው አይቀርም፡፡ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በተደጋጋሚ የአዲስ ቅጥረኛ ወታደር ማስታወቂያ ቢያወጡም፣ አይደለም የሚመለመል ወታደር ቀርቶ የሚመዘገብ ጠፋ፡፡
እናም ይህንን ችግር ለመፍታት ወያኔ አዲስ ዘዴ ቀየሰ፡፡ ከከተማ እስከ ገጠር ቀበሌ፣ በብረታብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ስም አማላይ ማስታወቂያዎችን አስለጠፈ፡፡ ይህ በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የወጣው ማስታወቂያ የሚመለምለው በሚከተሉት የሙያ ዘርፎች እንደሆነ ይዘረዝራል፡፡
ጄኔራል መካኒክ
ኤሌክትሪክሲቲ/ ኢንዱስትሪያል ኤሌክትሪክ ሲቲ/
ኤሌክትሮኒክ /ማካትሮኒክ/
ማሽን ቴክኖሎኪ
አውቶ መካኒክ
አውቶ ኤሌክትሪክ
*የምልመላ መስፈርቱ ‹‹በመከላከያ ሚኒስቴር ለአዲስ ምልመላ ወታደሮች ያስቀመጣቸው የቅበላ መስፈርቶች እንደተጠበቁ ናቸው›› ይላል፡፡
ይህን የማታለያ ዘዴ (አታሎ ወታደር የማድረግ) ወያኔ ብዙ ጊዜ ተጠቅሞበታል፡፡ በኢትዮ – ኤርትራ ጦርነት ጊዜ አስራ ሁለተኛ ክፍል የጨረሱ ተማሪዎችን ‹‹ኑ እናስተምራችሁና ስራ እናስቀጥራችሁ›› ብለው አታለው ከወሰዷቸው በኋላ ጦርነት ውስጥ ማገዷቸው፡፡ ብዙ እናቶችም የደም እንባ አነቡ፡፡ ዘንድሮ ግን ይህ የማታለያ ዘዴ ፈጽሞ ሊሰራላቸው አልቻለም፡፡ ምክንያቱም ይህችን የወያኔ ጨዋታ ህዝቡ በልቷታል፡፡
በገጠር ቀበሌዎች ማስታወቂያውን የለጠፉት አብዛኛውን ፖሊሶች ናቸው፡፡ በስተ-እግር መንገዳቸውም እለቱ እሁድ ስለነበር፣ የተሰበሰቡትን ገበሬዎች ልጆቻቸውን እንዲሰዱ እና ይህ እድልም እንዳያልፋቸው ሰበካ አድርገው ነበር፡፡ ከሰባኪያን ፖሊሶች አንዱ ያለው ግን በጣም ያስቃል፡፡ እንዲህ ነበር ያለው ‹‹እኔ ይህን እድል ባገኜው ኖሮ፣ ዳግም የተፈጠርሁ ያህል እቆጥረው ነበር›› ነበር ያለው፡፡ ያኔ ሁሉም ገበሬዎች ሳቁልሃ! አንዳንዶቹም ‹‹ታዲያ ለምን አትሄድም?›› ሲሉ አሾፉበት፡፡ ጋሽ ፖሊሱ በመጣበት መንገድ አፍሮ ተመለሰ፡፡
በከተማ ማስታወቂያውን ካድሬዎች ሲለጥፉ የከተማው ወጣቶች ከበው ያዩዋቸው ነበር፡፡ አብዛኛዎቹ ስራ አጥ ስለሆኑ የስራ ማስታወቂያ መስሏቸው ነበር ሰፍ ብለው ለጣፊውን ካድሬ ክብብ ያደረጉት፡፡ ማስታወቂያውን አንብበው እንኳ ሳይጨርሱ ‹‹አንተ ለምን አትሄድም›› ሲሉ አምባረቁበት፡፡ እኒህ ወጣቶችና ማስታወቂያውን የለጠፈው ካድሬ ማታ ካራንቡላ ቤት ተገናኙ፡፡ ስለ ማስታወቂው ወሬ ተጀመረ፡፡ እናም ካድሬው ማንንም ሳይፈሩ ‹‹እብድ ይሂድ እንጂ ማንም እንዲሄድ አልመክርም›› ብለውት እርፍ አሉ፡፡
በነገራችን በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ከወጣት እስከ ሽማግሌ ከመንግስት ሰራተኛ እስከ ገበሬዎች የወያኔን የጦር ካምፕ ሳይሆን የአማጺያንን ካምፕ እየተቀላቀሉ ነው፡፡
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/3825#sthash.w0PHu4Pi.dpuf
Saturday, 10 January 2015
ሰው በላውን ወያኔን እናጠፋዋለን!!! -ከ-አዲስ ብርሃኑ
ከ-አዲስ ብርሃኑ
andargacew Tsigeአንዳርጋቸውን ሳስበው ውስጤ ያለው የኢትዮጵያዊነት ወኔ ይቀጣጠልብኛል። ብርሃን ካለ ጨለማ የለም ብርሃን ከሌለ ግን ጨለማ አለ። አንዳርጋቸው ማለት ለኢትዮጵያዊያን በሙሉ ብርሃን ማለት ነው። የለኮሰው ብርሃን በኢትዮጵያ በሙሉ የሚበራ ብርሃን ነው። አንድአርጋቸው በኢትዮጵያ የለኮሰው ብርሃን የሰላም ብርሃን ነው፣ የፍቅር ብርሃን ነው፣ የቆራጥነት ብርሃን ነው፣ የጀግንነት ብርሃን ነው፣ የአንድነት ብርሃን ነው፣ የትግል ብርሃን ነው። በዚህ ብርሃን ውስጥ የማይጓዝ ማንም ኢትዮጵያዊ የለም። አንድአርጋቸው የኢትዮጵያ ብርሃን!!!የእውነት ብርሃን ጥቅም ያለወጠህ ብርሃን የለኮስከው የነጻነት የትግል ሻማ አንተ ሻማ ሆነህ እየቀለጥክ ብርሃንነትን የለበስክ የኢትዮጵያ ብርሃናዊ ጀግና አንተ ነህ።
ወያኔ የፈራው ስራህን ብቻ ሳይሆን ስምህንም ጭምር ነው። አንድነት ለወያኔ አይመቸውም አንድነትን ይፈራል ህብረትን ይጠላል ለያይቶ እና ከፋፍሎ መግዛትን ነው የሚፈልገው። ስለዚህ አንድአርጋቸው ሲባል ያባንነዋል።ወያኔ ለዘረፋው አንድነት አይመቸውም ለተንኮል ስራው አይመቸውም ስለዚህ እንኳን ስራህን ስምህንም አይወዱትም። በኢትዮጵያዊያን ግን ስምህም ተግባርህም ይወደዳል። እዚህ ጋር ነው ቁም ነገሩ በህዝብ መወደድ እና መከበር። የኢትዮጵያ ህዝብ የሰላም ብርሃን የለኮሱትን እና ወደ ብርሃን የሚወስዱትን ብርቅዬ ታጋይ በማይጠፋው በኢትዮጵያዊ መዝገብ ውስጥ ጽፈው ያስቀምጧቸዋል ። ወያኔ እና ከነግብርአበሮቹ ግን ከነስራቸው ይጠፋሉ።
ስለ አንዳርጋቸው ጽጌ የተለቀቀውን ቪዲዮ አይቼ በጣም ነውያፈርኩት በቪዲዮ መግቢያው ላይ ምዕራባዊያን የእስር አያያዝ ላይ ትችት ሲያቀርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን የእስረኛ አያያዝ በሰላም እንደሆነ እጅ እጅ ያለውን ወሬአቸውን በተለመደ የውሸት ቋንቋቸው ዛሬም ሲደግሙት አይናቸውን በጨው አጥበው በመቅረብ አንዳርጋቸው የሚናገረው ንግግር እራሱ ፈልጎ እንደሆነ አድርጋችሁ አቀረባችሁ። ቪዲዮው ስንመለከት ግን 14 ደቂቃ ባልሞላች ንግግር ውስጥ የአንድአርጋቸው የለበሰው ልብስ በየደቂቃው የቀያየራል ቪዲዮው በየደቂቃው ይቆራረጣል ይበጣጠሳል በዛ ላይ የተላለፈው መልእክት ምን እንደሆነ የማይገባ። ይህንን ቪዲዮ እንደ ኢትዮጵያዊ ሆኜ ሳስበው በጣም አሳፋሪ ነው እንደ ወያኔ አውሬነት ሳየው ደግሞ የምጠብቀው ስለሆነ አይደንቅም የሚገርመው የካድሬዎች ጫጫታ ነው ተንጫጩ እኮ ወይ መንጫጫት በዚህ ዘምን የሚታለል ወይም የወያኔን ስራ የማያውቅ ማንም ኢትዮጵያዊ የለም ኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስት አቸባሪ ነው ያስቸገረው። አንዳርጋቸው የለኮሰው የትግል ብርሃን ወያኔን ጥሎ ካልሆነ በስተቀር መቆሚያ የለውም።
ወያኔ የአንድአርጋቸውን ጽጌ ቪዲዮ የለቀቀው ግራ ገብቶት ነው ወያኔ ሲጨንቀው ሲጨንቀው ማስተንፈሻ ይፈልጋል ሰሞኑን 3ት የአየር ሃይል አብራሪዎች ከነ ሄልኮፕተር ወደ ኤርትራ መግባታቸው ወያኔን መካዳቸው ያስደነገጠው በተጨማሪም 4ት የአየር ሃይል የተዋጊ አብራሪዎች ወደ ኬኒያ መግባታቸው እና የመከላከያ ሰራዊት ከነ ትጥቁ እየከዳቸው ስለሆነ የመውደቂያው ዋዜማ ላይ መሆኑን ስላወቀው ስለደነገጠ ማስተንፈሻ ስለፈለገ የህዝቡን ሃሳብ ለመበተን በጣም አሳፋሪ እና የተቆራረጠ በዛ ላይ ሃሳቡ ግልጽ ያልሆነ ቪዲዮ ለመልቀቅ ተገደዋል። አሁን ወያኔ በሚደሰኩረው ዲስኩር ዲስኩር ተታሎ ግዜ ሰጥቶ የሚያወራ ቢኖር ወያኔ እና ካድሬዎች ብቻ ናቸው። እኛ ግን አንዳርጋቸው በለኮሰው የብርሃን የትግል ጉዞ ተጉዘን ወያኔን ለመደምሰስ ቆርጠን ተነስተናል። ወያኔ ሆይ አሁን የዘራኽውን ማጨጃህ ሰዓት ላይ ነህ። የኢትዮጵያ ህዝብ የተገደለበት የቆሰለበት የተደበደበበት የተሰደደበት የተረገጠበት የተናቀበት ግዜ አብቅቶ ኢትዮጵያዊው ቁጭቱን ለከፍል ቆርጦ ተነስቷል። ህዝብ ያቸንፋል ወያኔ እና ካድሬዎች ለአንደ እና ለመጨረሻ ግዜ ይጠፋሉ።
ድል ለኢትዮጵያዊያን!!!
Subscribe to:
Posts (Atom)