Friday, 27 March 2015
የኛ የኢትዮጵያውያን ጥያቄ ስር ነቀል አብዮታዊ ለውጥ ጥያቄ ነው
ኢትዮጵያውያን ለነጻነታችን ዋጋ መክፈል የጀመርነው ከጥንት ጀምሮ መሆኑ ይታወቃል:: በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶየሚገኘው የዘረኛውና ቡድናዊው አገዛዝ በዜጎች ላይ ከፍተኛ በደል በማድረስ ላይ ይገኛል:: ከዚህ ጨቋኝ አገዛዝ ለመገላገልበአንድነትና በመተባበር ለነጻነታችን መታገል አለብን:: ላለፉት 24 አመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተቀመጠውንዘራፊውን እና ጨቋኙን የወያኔ ጁንታን ለመቅበር የአንድነት እና የለውጥ ሃይሎች ልዩነቶቻችንን በማቻቻል በጋራ ልንታገልየሚገባና ለውጥ ልናመጣ የሚገባ ችላ የማይባል ዋነኛ ጉዳይ ነው። በህዝባችን ላይ ከፍተኛ እንግልት፣ እስር፣ ሰቆቃ፣ ግድያወዘተ እየፈጸመ የሚገኘው የህዝባችንና የሃገራችን ጠላት ወያኔ እና ወያኔ ብቻ ነው::
ባሳለፍናቸው መራር የትግል አመታት ውስጥ በቅርቡ እንዳየነው የተቃዋሚዎች በመዋሃድና አንድነትን ከመፍጠር ይልቅ እርስበእርስ መፈራረጅና መወነጃጀል ለስልጣን መሮጥ እንዲሁም ለስም እና ለዝና መትጋት ነው:: ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተረፈው ነገርቢኖር ከጭቆና ወደ ባሰ ጭቆና ማቅ ውስጥ ከመዘፈቅ ውጪ ፍጹም የናፈቀውን የነጻነት አየር እንዲተነፍስ አላደረግነውም።የተቃዋሚ ሃይሎች ጥንካሬ እንዲጎለብት በየድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እንከኖች በማጥራት በጋራ እና በተመቻቸ የሃሳብ መግባባትተቻችሎ እና ተግባብቶ የትግል ስትራቴጂን ከግብ ለማድረስ ህብረ-ብሄር የሆኑት የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር እና ግንቦት7 እንዳደረጉት ለአንድነትና ለትብብር ተግቶ መስራት ይጠበቅብናል። በአሁኑ ወቅት ይህንን ዘረኛ ስርዓት ለማውረድ በውስጥምሆነ በውጭም ትግሉ በስፋት ቀጥሎ ይገኛል:: ወያኔ እስኪወድቅና ህዝባችን ድል እስኪቀዳጅ ድረስ ሊቀጥል የሚገባው ትግልእንደመሆኑ መጠን ከበፊቱ በተሻለ ሁኔታ የተያዘው ትግል በአሁኑ ሰአት ወያኔን እያፍረከረከ በፍርሃት እንዲሸበር አድርጎታል::
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል! የኛ የኢትዮጵያውያን ጥያቄ አብዮታዊ የለውጥ ጥያቄ ነው። የፖለቲካ አስተዳደር ለውጥ ፣የኑሮ ውድነት የሚያላቅቅ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ለውጥ፣ በጋራ ህብረተሰባዊነትና እኩልነት ላይ የተመሰረተ አገዛዝ ወይንም መንግስትእንደምናገኝ የሚያረጋግጥልን ለውጥ እንፈልጋለን፡፡ የማህበራዊና ፍትህ እኩልነት ለውጥ፣ የነጻነት እና የመብት ማግኘት ጥያቄ፣ከመንግስት ነጻ የሆነ ፍርድ ቤት፣ በሃገራችን ተዘዋውረን በፈለግነው ቦታ የመስራት እና የመኖር ጥያቄ የሚያረጋግጥልን ለውጥእንፈልጋለን፡፡ በሃገራችን ላይ የሃገራችን ባለቤቶች ስንሆን የሚገኘው ብልጽግና እና እድገት ባለቤት መሆናችንን የሚያረጋግጥልንለውጥ እንፈልጋለን፡፡ ይህ ሳይታለም የተፈታ እና የሁሉም የነጻነት ፈላጊ ሃይሎች ጥያቄ ነው። ሰብአዊ መብቶች ለዲሞክሪያሲያዊስርአት ግንባታና ለአንድ ሀገር ልማትና ብልፅግና መሰረታዊ ነገሮች ተደርገው የሚወሰዱ ናቸው፡፡ ዜጎች የሃገራቸው ሃብትባለቤትና የመጠቀምም መብት እንዲሁም ሃሳባቸውን በነጻነት የመግለጽ መብት ሊኖረን ይገባል::
በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉትን ፓርቲዎች መዋቅሮቻቸውን በማጠናከር የውስጥ ድክመቶቻቸውንም በመቅረፍእንዲጠነክሩ የማድረግ ግዴታ ከሁላችንም ከለውጥ ፈላጊ ሃይሎች ይጠበቃል።ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
Sunday, 15 March 2015
ሰማያዊ ፓርቲ ቅስቀሳ እንዳያደርግ እንቅፋት እየተፈጠረበት ነው
ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ቅስቀሳ እንዳያደርግ በፖሊሶች ክልከላና ወከባ እየደረሰበት እንደሚገኝ የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ጉዳይ ኃላፊና ም/ሊቀመንበሩ አቶ ስለሽ ፈይሳ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ዛሬ መጋቢት 5/2007 ዓ.ም ፓርቲው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ቅስቀሳ ያደረገ ሲሆን በባህርዳርና ወላይታ ዞን ፖሊስ የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር ቅስቀሰውን ማደናቀፉን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
ዛሬ ሰማያዊ ፓርቲ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ቅስቀሳ በሚያደርግበት ወቅት የከተማው ፖሊስ ‹‹የምርጫ ቅስቀሳ አልተጀመረም›› ብሎ ያዋከበ ሲሆን የፓርቲው አመራሮችና አባላት ቅስቀሳ መጀመሩን ገልጸው ስራቸውን እያከናወኑ በነበሩበት ወቅት ‹‹ህገ ወጥ ሰላማዊ ሰልፍ›› አድርጋችኋል በሚል ሌላ ክስ 8 የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችንና ሌሎች አባላትን በማሰር ቅስቀሳውን እንዳደናቀፈ የወላይታ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ታደመ ፈቃዱ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ በባህርዳር ከተማ ፖሊስ ‹‹በሞንታርቮ ለመቀስቀስ ፈቃድ ስላላመጣችሁ መቀስቀስ አትችሉም፡፡›› በሚል ፓርቲው ሊያደርገው የነበረውን የምርጫ ቅስቀሳ እንዳደናቀፈ የፓርቲው የምዕራብ ጎጃም ዞን ጊዜያዊ አስተባባሪ አቶ አዲሱ ጌታነህ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ‹ለምን ትከለክሏቸዋላችሁ?› በሚል ህዝቡ ፖሊሶቹን በማፋጠጡ በድምፅ መቀስቀስ ባንችልም በህዝቡ ድጋፍ የቅስቀሳ ወረቀቶችን በማሰራጨት የተሳካ ቅስቀሳ አድርገናል›› ሲሉ አቶ አዲሱ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በዚህ ወቅት ቅስቀሳ ለማድረግ ምንም አይነት ፈቃድ እንደማያስፈልግ የገለፁት አቶ ስለሽ ፖሊስ የሚፈጥረው እንቅፋት ሆን ተብሎ ሰማያዊ ወደ ህዝብ እንዳይደርስ የተቀየሰ ስልት ነው ብለዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም ‹‹የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን በመሰረዝ ፓርቲው ምርጫው ላይ የሚፈጥረውን ጫና ለመቀነስ ጥረዋል፡፡ ይህ አልበቃ ሲልም የቅስቀሳ መልዕክቶቻችን በተደጋጋሚ በሚዲያ እንዳይተላለፉ እያደረጉ ነው፡፡ አሁን ደግሞ ወደ ህዝብ እንዳንደርስ በህገ ወጥ መንገድ በፖሊስ ማስቆም ጀምረዋል›› ብለዋል፡፡
በሌላ ዜና የጅማ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ባልታወቁ ግለሰቦች መዘረፉን የምርጫ ጉዳይ ኃላፊው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹በ02/07/07 ሁለት ሰዓት ላይ አራት ግለሰቦች ጽ/ቤቱን በመስበርና የጽ/ቤቱን ጥበቃ አስፈራርተው በማባረር ለቅስቀሳ የተላከ 6 ሺህ ኦሮምኛ በራሪ ወረቀት እንዲሁም 3 ሺህ አማርኛ በራሪ ወረቀት፣ አንድ የፎቶ ካሜራ፣ አንድ ባነር፣ ለሸካ ዞን ሊላክ የተዘጋጀ 5 ሺህ በራሪ ወረቀት፣ 50 ፖስተር፣ አንድ የእጅ ሜጋ ፎን፣ ሁለት ባነር፣ በርካታ ጋዜጦችና መጽሔቶች ሲዘርፉ የጽ/ቤቱን ኮምፒውተርም ሰብረዋል›› ሲሉ ኃላፊው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡
Wednesday, 4 March 2015
በአገር ሙሉ ጀግና ሞልቶ ወያኔን ጀግና አሉት።
ሀገራችን የጀግና ደሀ አይደለችም ጀግኖች የሞሉባት ሀገር ናት። በየተሰለፍንበት መሰኩ አለምን ያስደመመ ጀግኖች ያፈራች አገር ነች።በትምህርቱ ዘርፍ እስከ ሳይንቲስት የደረሱ የትምህርት ጀግኖች አሉ። በሰዕሉ እስከ የአለም ሎሬት የደረሱ የስእል ባለሞያ ጀግኖች አሉን። በስፖርቱም እስከ ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሌያና የአለምን ክብረ ወሠን የሚሰብሩ ጀግኖች ልጆችን ያፈራች አገር ነች። በኪነ ጥበቡ ጥግ ድረስ የደረሱ የኪነ ጥበብ ጀግኖች አሉን። በምርምሩም አዳዲስ ፈጣሪዎችን የሚፈጥሩ ድንቅዬ እና ብርቅዬ ልጆች አሉን። መቼም ጀግና አጥተን የጀግና ደሀ ሆና አታዉቅም አገራችንን የሚያኮሩዋት ጀግኖች አሉዋት የጀግናም ጀግና። - ወያኔን ጀግና አሉት! በTPLF የትግል ድርሻ ያለው እና ታጋዮች ጭምር ተወዳጅ የሆነውን ታጋይ ኃየሎም አርአያ በትግል ግዜ ሁሌም ካጠገባቸዉ እንዳይለይ የሚፈልጉት በቆራጥነቱ እና በችሎታዉ ታጋዬች በሙሉ የሚተማመኑበት ሀየሎም አርአያ ቀድሞም የጀኔሪል ማእረግ የተሰጠዉ ሰራዊቱ በጣም ስለሚወደዉ አና ስለሚያከብረዉ የተሸበሩት የTPLF መሪ ተብዬዎች ነገ ትልቅ ቦታ እንደሚይዝ እና የወያኔዎችን ኃሳብ ሊቀበላቸዉ እንደማይችል ስለሚያቁ ያንን ከባድ ጊዜያቶችን አሳልፎ የመጣዉን ታጋይ እየተዝናና ባለበት ሰአት አንድ ተራ የወያኔ ካድሬ በበላዮቹ TPLF ሰዎች ትእዛዝ ተሰጥቶት ሳያስበዉ በመሳሪያ ተኩሶ በመምታት ገደለውታል። ይሄ ነዉ የወያኔ ጀግንነት?
በትግሉ ሰአት አብሮአቸዉ የነበሩት የትግራይ ሰዎች ትግሉንም በድል ያጠናቀቁትን የትግራይ ልጆች ከድል በኋላ ከወያኔ ጋር የሀሳብ ልዩነት በመኖራቸዉ ብቻ በድብቅ አየተከታተሉ ከሰላሳ ስድስት ሺህ በላይ ታጋዬችን የገደሉ እንግዲህ እዚህን ገዳዬች ነዉ ጀግኖች የምትሉት?
ሀዉዜን ላይ የወረደዉ የቦብ ዝናብ በደርግ ባለስልጣን ዉስጥ ሆኖ ትዕዛዝ ያስላለፈዉ አና ይህንን ምስኪን ሕዝብ ለድብቅ አላማቸዉ የሰዉ ሀይል ለማግኛ ተበዳይ ለመምሰል ወደ ሀዉዜን ገበያ የወያኔ ወታደር በሙሉ ገብተዋል ተብሎ እንዲነገር አስደርገዉ የትግራይን ሕዝብ ዳር ቆመው ያስፈጁትን ወያኔን ጀግና አሉት።
አዲስ አበባ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ ምንም የጦር መሳሪያ ባልያዙ ንፁሀን ዜጎጀ ላይ የፈሪ ዱላ አንደሚባለው በያዙት መሳሪያ ያለምንም ርህራሄ ህዝቡን የፈጁት ነዉ እንግዲህ ጀግና የምትሉን?
ጋንቤላ ላይ ከመሬታችን አታፈናቅሉን በመሬታችን መኖር እንፈልጋለን ብለዉ መሬታችንን ለባዕዳን አትስጡብን ብለዉ ተቃዉሞ ባሰሙት ንፁሁን የጋቤላ ተወላጆች ላይ ብረት አንስግቶ የፈጀዉና በግዳጅ ከመሬታቸዉ አፈናቅሎ ለባድ የሚሰጠዉን ነው ዉያኔን ጀግና የምትሉት?
በአኝዋከ ህዝብ ላይ መሬታቸዉን በመፈለግ የአኝዋከ ህብረተሰብን ዘግናኝ በሆነ መልኩ የዘር ማጥፋት እልቂት ከደረሰ በኋላ በጅምላ ወደ አንድ ጉድጓድ የከተተዉን ነዉ ጀግና ብላቹ የምትጠሩት?
በኦጋዴን ዉሰ በሱማሌ ተወላጆች ህብረተሰብ ላይ በአየር ቦምብ በማዝነብ የዘር ማጥፋት የፈፀመዉን እና እንደ ሃውዜን ውስጥ እንዳደረጉት ጭካኔ የተሞላበት ስራቸውን የደገሙትን ነዉ ጀግና ያላችኋተው?
አንቦ ላይ በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን መሰረት ተቃዉሞ የወጣዉን የአምቦ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የታጠቀ ወታደር አሰማርቶ ተማሪዎችን መግደል ነዉ እንዴ ወያኔን ጀግና ያሰኘዉ?
ባህር ዳር ላይ ስለሀይማኖት ብለዉ የወጡት ሰላማዊ ሕዝብ ላይ አነጣጥሮ ተኩሶ መግደል ነዉ ጀግና ያሰኛቸዉ ታድያ ጀግና ያሰኛቸዉ ምንድን ነዉ?
ብዕር የያዘ ጋዜጠኛ አንተ አሸባሪ ነህ ብሎ ወደ እስር መጣል ነዉ ጀግንነት? ወይስ የፖለቲካ ሰዎችን ባላቸዉ የፖለቲካ አቋም በመፍራት ብቻ የአሸባሪ ታፔላ እየለጠፉ ወደ ወይኒ መወርወር ነዉ ጀግንነት? ወይስ የተማረዉንም ያልተማረዉንም ሰዉ በኛ መስመር ግባ ካልገባህ መኖር አትችልም ብለዉ ማዋከብ ነዉ ጀግና ያሰኛቸዉ?
ጀግና ማለት በፍቅር ታግሎ በፍቅር የሚያሸንፍ ነዉ። ጀግና ማለት ከባርነት ቀንበር አላቆ ነፃነትን የሚያወርስ እና በነፃነት እንዲኖሩ ማድረግ ነዉ።ጀግና ማለት ስራዉ ከሚናገዉ በበጠ ጏልቶ የሚታይ እና በሰዉም ዘንድ ተቀይነትን ያገኘ ነዉ።
ጀግና ማለት እንደ ዉሻ ላበላዉ የሚጮህ ሳይሆን ለእዉነት የቆመ ለእዉነት የተሸነፈ ለእዉነት የሚኖር እሱ ነዉ ጀግና። መሳርያ ስለያዘ ብቻ ከኔ በላይ ማን አለብኝ ብሎ እየተኯሰ ሰላማዊ ሰዉን የሚገል እሱ ጀግና ሳይሆን አረመኔ ነዉ አረመኔን ደሞ ጀግኖች ያጠፉታል።
ጀግና ማለት ለነሱ የታጠቀ ኃይል በሰላማዊ ሰዉ ላይ ተኩሶ መግደል ከመሰላቸዉ፡ ጀግና ማለት ለነሱ ብዕር የያዙትን ብዕራዉያንን በብረት አስረዉ ማሰቃየት ከሆነ፡ ጀግና ማለት ለነሱ የፓለቲካ ሰዎችን በአአስከፊ ቅጣት መቅጣት ከመሠላው፡ እኔ ግን እላለዉ እነዚህ ጀግና ሳይሆኑ ፈሪ እና እውቀት የጏደላቸዉ ናቸዉ። እነዚህ ጀግና ሳይሆኑ የጨነቃቸዉ ናቸዉ እላለዉ። ፈሪና የጨነቀዉ ሰዉ የሚያደርገዉን ድርጊት እያደረጉት ያሉት።
ጀግናማ ፍቅርን አስተማሪ ነዉ። ጀግናማ ለህዝብ የቆመ ነዉ። ጀግናማ ለሆዱ ያልቆመ ነዉ። ጀግናማ ኢትዮጵያዊው ነው።
To Addis Berhanu
03.03.2015
Email- berhanu.addis@yahoo.com
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/5049#sthash.m7pSsFra.dpuf
Thursday, 26 February 2015
ለአንድ ቀን የሚቆይ የቦይኮት ዘመቻ በድምፃችን ይሰማ ጥሪ ቀረበ
‹‹እስር ከትግላችን አያስቆመንም!›› – ለአንድ ቀን የሚቆይ የቦይኮት ዘመቻ
ነገ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከምሽቱ 12 ሰዓት ስልካችንን እናጠፋለን!
መንግስት ሙስሊሞችን ከያሉበት በማሰር ህገ ወጥ ዘመቻ ላይ መሰማራቱን እና በህዝበ ሙስሊሙ ላይ ግፍ መፈጸሙን በመቃወም ነገ ጁሙዓ ታላቅ አገር አቀፍ ተቃውሞ እንደሚኖረን እና በዛሬው እለትም የተቃውሞው መርሃ ግብር ይፋ እንደሚሆን መገለጹ ይታወሳል፡፡በዚሁ መሰረት እነሆ የነገው አገር አቀፍ ተቃውሟችን በመጠነኛ የቦይኮት ዘመቻ (የራስን መብት በራስ ላይ የመንፈግ ተቃውሞ) የሚጀመር ይሆናል፡፡ኢትዮ ቴሌኮም ለመንግስት ከፍተኛ ትርፍ ከሚያስገኙ ካምፓኒዎች አንዱ ሲሆን
በቀን ከተጠቃሚዎች በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ገቢ ያገኛል፡፡ ሙስሊሙ
ማህበረሰብ ደግሞ የአገሪቱ ግማሽ እንደመሆኑ መጠን በአንድ ቀን ለቴሌ
የሚያስገኘው ገቢ እንዲሁ በሚሊዮን የሚቆጠር ነው፡፡ በመሆኑም የማይናቅ
ቁጥር ካለው ማህበረሰብ የሚያጣው የአንድ ቀን ገቢ ለኢትዮ ቴሌኮም
በሚሊዮን የሚቆጠር ብር አክሳሪ መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ የነገው
ቦይኮት በኢቲዮ ቴሌኮም ካምፓኒ ላይ የሚያተኩረውም ለዚህ ነው፡፡
ነገ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ ሁላችንም ስልካችንን
በመዝጋት ተቃውሟችንን እናሰማለን፡፡ አስቸኳይ ጉዳይ ካላጋጠመን በስተቀርም
ስልካችንን አንከፍትም፤ አንጠቀምምም፡፡
አስቸኳይ ጉዳይ ሲያጋጥመን ለአፍታ ስልካችንን በመክፈት ቶሎ ጉዳያችንን ፈጽመን ወዲያው እንዘጋለን፡፡
ይህንን አገር አቀፍ እና መላ አገሪቱን ያካለለ ዘመቻ ላልሰሙት ሁሉ በማሰማት ለስኬቱ የቻልነውን ሁሉ መጣር ታላቅ ተግባር ሲሆን ለዲናችን ስንል ለምንከፍለው
መስዋእትነትም ከጌታችን አላህ ዘንድ ምንዳችንን እንተሳሰባለን፡፡ አላህ ፈተናውን
እንዲያነሳልንም አጥብቀን ዱዓ እናደርጋለን፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ
አይደለምና!!!
አዎን! አንድነት ያለው ህዝብ ያሸንፋል!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
Sunday, 22 February 2015
‹‹ምርጫ በህዝብ ፍላጎት ሳይሆን በሎተሪ ሆኗል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
አዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 5 ለመጭው ምርጫ ለተወካዮች ምክር ቤት ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ሊቀርቡ የነበሩት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ከቀረቡት 17 ዕጩዎች መካከል በተጣለ ዕጣ ወድቀዋል›› በመባላቸው ለመጭው ምርጫ በዕጩነት እንዳይቀርቡ መደረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል በዕጩነት በቀረቡበት ወረዳ 5 የምርጫ ጣቢያ ኢህአዴግ፣ የትግስቱ አንድነት፣ ቅንጅትን ጨምሮ ሌሎች ስድስት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ያለ ምንም ዕጣ አልፈዋል የተባለ ሲሆን ‹‹የሚያልፉት በዕጣ ነው›› የተባሉት ሰማያዊን ጨምሮ 11 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መካከል ሰማያዊና ሌሎች አራት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ‹‹ዕጣ አልወጣላቸውም፡፡›› ተብሏል፡፡images
ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ሰማያዊ ህዝብ ውስጥ በሰፊው እየገባና እያንቀሳቀሰ ያለ ግንባር ቀደም ፓርቲ ነው፡፡ እንደ ኢህአዴግ ያሉን ጨምሮ ዕጣ ውስጥ አይገቡም፡፡ ሰማያዊ ደግሞ ይህ ነው የሚባል እንቅስቃሴ ከማያደርጉት ፓርቲዎች ጋር ዕጣ ውስጥ ገብቶ ወደቀ መባሉ ዴሞክራሲ ከጅምሩ ጀምሮ የህዝብ ድምጽ ሆኖ እያለ በእኛ አገር ሎተሪ ሆኗል ማለት ነው፡፡›› ብለዋል
ሊቀመንበሩ አክለውም ‹‹ሂደቱ ምንም ይሁን ምን አንድን ፓርቲ ወይንም ተወካይን ህዝብ ነው መምረጥ ያለበት፡፡ ህዝብ የሚፈልገውና የሚመረጥ ፓርቲ ነው ለምርጫ መቅረብ ያለበት፡፡ አሁን ግን እየተባለ ያለው በአንድ በኩል ህዝብ የማይፈልገው ያለ ዕጣ ሲገባ፣ በሌላ በኩል ህዝብ የሚፈልገው ሰማያዊን የመሰለ ፓርቲ ዕጣ ውስጥ ገብቶ አላለፈም እየተባለ ነው፡፡ በአንድ በኩል ህዝብ የተማረረባቸው ያለ ቅድመ ሁኔታ ህዝብን እንደሚያንቀሳቅስ የሚታወቀው ሰማያዊ ደግሞ ህዝብ ስፈለገው አሊያም በጥንካሬው ሳይሆን በሎተሪ ወድቀሃል ተብሏል›› ሂደቱ የተሳሳተ ነው ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ”ሠማያዊ ፓርቲ ከ200 በላይ እጩዎች ተሰረዙብኝ አለ” በሚል ርዕስ አዲስ አድማስ እንደዘገበው —
”የፓርላማ ምርጫ እጩዎች ኢህአዴግ 501፣ መድረክ 303፣ ኢዴፓ 280
የሌላ ፓርቲ አባላትን በእጩነት አስመዝግቧል” – ምርጫ ቦርድ
ሠማያዊ ፓርቲ በተለያዩ ክልሎች ለፓርላማ ካስመዘገባቸው 400 እጩዎች ግማሽ ያህሉ በምርጫ ቦርድ እንደተሠረዙበት ሲገልፅ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ፤ ሰማያዊ ፓርቲ ለምርጫው የሌላ ፓርቲ አባላትን ማስመዝገቡ ህገወጥ እንደሆነ ገለፀ፡፡
ለፓርላማ ኢህአዴግ 501 እጩዎችን፣ መድረክ 303 እጩዎችን፣ ኢዴፓ 280 እጩዎችን አቅርበዋል፡፡ ለፓርላማ ካስመዘገብናቸው እጩዎች ከሁለት መቶ በላይ ተሰርዘውብናል ያሉት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፤ በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በወላይታ፣ በቤንሻንጉል፣ በምዕራብ ጐጃም፣ በከምባታ፣ በሲዳሞ፣ በጋሞጐፋ፣ በአዲስ አበባ፣ በደቡብ ጐንደር እና በሌሎች አካባቢዎች አሣማኝ ባልሆነ ምክንያት እጩዎቻችን ከምርጫ ውጪ ተደርገውብናል ብለዋል፡፡
ፓርቲው የምርጫ አስፈፃሚዎችን እንዳነጋገረ ኢ/ር ይልቃል ጠቁመው፤ እጩዎቻችንን የተሰረዙት ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጣ ትዕዛዝ እንደሆነ ተነግሮናል ብለዋል፡፡ “የሌሎች ፓርቲዎችን አባላት አስመዝግባችኋል፤ ትብብር የሚባል ህገ ወጥ አደረጃጀት መስርታችኋል የሚሉ ምክንያቶችንም ሰምተናል ያሉት ኢ/ር ይልቃል፤ በአዲስ አበባ የተሠረዙብን እጩዎች ግን ግልፅ ምክንያት አልተሰጣቸውም ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከፓርላማ ምርጫ የተሠረዙት እጩዎች የተሠረዙበት ምክንያት እንዲነገራቸው ጠይቀዋል፤ ምርጫ አስፈፃሚዎች የሰጡን ምላሽ፤ “እናንተን ለመመዝገብ እኛ ችግር የለብንም፤ ግን እንዳንመዘግብ ከበላይ አካል ታዘናል፤ በደብዳቤ ምላሽ ልንሠጣችሁ አንችልም” የሚል ነው ብለዋል – ኢ/ር ይልቃል፡፡
በጉዳዩ ላይ ከምርጫ ቦርድ ማብራሪያ ለማግኘት እንደሞከሩና፤ የቦርዱ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ነጋ ዱሪሳ በማመልከቻ ካልጠየቃችሁ መልስ አልሰጥም እንዳሏቸው ኢ/ር ይልቃል ተናግረዋል፡፡
የእጩዎች ስረዛን በተመለከተ ከአዲስ አድማስ ለቀረበላቸው ጥያቄ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፅ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድሙ ጎላ በሰጡት ምላሽ፤ “የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት” የተሰኘ ፓርቲ አባላቱን በሰማያዊ ፓርቲ ስም በእጩነት እንዳስመዘገበ በመግለፁ ነው ምርጫ ቦርድ ጉዳዩን ማጣራት የጀመረው ብለዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ በማያውቀው ሁኔታ ሰማያዊ ፓርቲ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ትብብር መስርቻለሁ በሚል መንፈስ፤ የበርካታ ፓርቲዎች አባላት በሰማያዊ ፓርቲ ስም እጩ ሆነው ቀርበዋል ያሉት አቶ ወንድሙ፤ የደቡብ ኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት ሊቀመንበር ራሳቸው በሰማያዊ ፓርቲ ስም አዲስ አበባ ላይ ተመዝግበው መገኘታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ አንድ ፓርቲ የሌላን ፓርቲ አባል በእጩነት ማስመዝገብ አይችልም፤ ህገወጥ ነው ያሉት የምርጫ ቦርድ ም/ኃላፊው፤ ስለዚህ የአንድ ፓርቲ አባል በሌላ ፓርቲ ስም እጩ መሆን ስለሌለበት አጣርታችሁ መዝግቡ የሚል መመሪያ አስተላልፈናል ብለዋል፡፡
ቦርዱ የሰጠው መመሪያ እጩ እንዳትመዘግቡ የሚል ሳይሆን እያጣራችሁ መዝግቡ የሚል ነው ያሉት አቶ ወንድሙ፤ በዚህ አሰራር ደስተኛ ያልሆነ ማንኛውም ፓርቲ፤ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ቅሬታውን ከምርጫ ጣቢያ እስከ ምርጫ ቦርድ በየደረጃው ማመልከት እንዲሁም ለፍ/ቤት አቤቱታ አቅርቦ ውሳኔ ማግኘት ይችላል ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል ኢህአዴግ፤ ለፓርላማ 501፣ ለክልል ምክርቤቶች ከ1300 በላይ እጩዎችን አቅርቧል፡፡ አራት ፓርቲዎች የተጣመሩበት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ፤ ለፓርላማ 303፣ ለክልል ም/ቤቶች ከ800 በላይ እጩዎችን ያቀረበ ሲሆን፤ ከዚህም ውስጥ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) 168 እጩዎችን ለፓርላማ 475 እጩዎችን ለክልል ምክር ቤት አስመዝግቧል፡፡
በኢትዮጵያ ማህበረ ዲሞክራሲ – ደቡብ ህብረት አንድነት ፓርቲም 83 ለፓርላማ 273 ለክልል ማቅረቡን ጠቁሟል፡፡ ሌላው የመድረክ አባል አረና ፓርቲ 33 እጩዎች ለፓርላማ 70 ለክልል አቅርቧል፡፡ ኢዴፓ በበኩሉ 280 እጩዎችን ለፓርላማ 200 እጩዎችን ለክልል አስመዝግቧል፡፡ ”
Wednesday, 18 February 2015
Ethiopia's Media War: Al Jazeera, The Stream
Ethiopia’s jailed Zone 9 bloggers are on trial this week for terrorism and treason, charges facing more than two dozen journalists, bloggers and publishers. To avoid arrest, 30 journalists fled the country in the past year. The government says they’re criminals, destabilising Ethiopia’s fragile democracy in the name of “press freedom.” Rights groups say they’re victims of repression.
Tuesday, 10 February 2015
የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አባላትና መዋቅሮች ወደ ሰማያዊ ፓርቲ እየጎረፉ ነው
የቀድሞው የአንድነት አባላትና መዋቅሮች በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን ተከትሎ ተጨማሪ የአንድነት አባላትና መዋቅሮች ሰማያዊ ፓርቲን እየተቀላቀሉ እንደሚገኙ የፓርቲው ም/ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስለሽ ፈይሳ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ከጥር 28/2007 ዓ.ም በኋላ ሰማያዊ ፓርቲን ከተቀላቀሉት መካከል የትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ አፋር፣ ደቡብ ወሎ፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ፣ ሀረር፣ አርባምንጭ፣ ወላይታ፣ ቁጫ፣ ቦንጋ፣ ኢልባቡር፣ ሰሞን ሸዋና የጉጂ የአንድነት መዋቅሮች ሙሉ በሙሉ ከሰማያዊ ፓርቲ መዋቅር ጋር መቀላቀላቸውን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ በቀጣዩ ቀናትም ወደ ሰማያዊ የሚቀላቀሉ መዋቅሮችና በግላቸው የሚመጡ አባላት እንዳሉ ኃላፊው ግልጸዋል፡፡
‹‹በአንድነትና መኢአድ ላይ የተወሰነው ውሳኔ የሰላማዊ ትግሉን ለማዳከም የተደረገ ሴራ ነው›› ያሉት አቶ ስለሽ ፓርቲያቸው ላይ ህገ ወጥ ውሳኔ የተላለፈባቸው የአንድነት አመራሮችና አባላት ተስፋ ሳይቆርጡ ወደ ሰማያዊ ፓርቲ መምጣታቸውና ሰማያዊ ፓርቲም እነዚህን ታጋዮች እጁን ዘርግቶ መቀበሉ የታሰበውን ሴራ ያከሸፈና ሰላማዊ ትግሉን የሚያጠናክር ነው ብለዋለል፡፡ አቶ ስለሽ አክለውም የተፈጠረውን አጋጣሚ በመጠቀም ትግሉን ለማጠናከር ኢትዮጵያውያን የቻሉትን ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)




.jpg)
