Friday, 30 January 2015

US urges Ethiopia to ensure fair trial to bloggers and journalists

January 30, 2015 (U.S. Department of State) The United States is concerned by the Ethiopian Federal High Court’s January 28, 2015, decision to proceed with the trial of six bloggers and three independent journalists on charges under the Anti-Terrorism Proclamation. The decision undermines a free and open media environment—critical elements for credible and democratic elections, which Ethiopia will hold in May 2015.US on Ethiopian bloggers We urge the Ethiopian government to ensure that the trial is fair, transparent, and in compliance with Ethiopia’s constitutional guarantees and international human rights obligations. We also urge the Ethiopian government to ensure that the trial is free of political influence and continues to be open to public observation. The use of the Anti-Terrorism Proclamation in previous cases against journalists, activists, and opposition political figures raises serious questions about the implementation of the law and about the sanctity of Ethiopians’ constitutionally guaranteed rights to freedom of the press and freedom of expression. Freedom of expression and freedom of the press are fundamental elements of a democratic society. We call on the government of Ethiopia to support freedom of expression and freedom of the press to demonstrate its commitment to democracy as it approaches its May 2015 national elections.

Tuesday, 20 January 2015

ወያኔ የሚመለመል ወታደር አጣ

ወያኔን የሚከዱ ወታደሮች በየቦታው እየተሰማ ባለበት ባሁኑ ሰዓት የሚመለመል ወታደር መጥፍቱ ምናልባትም ወያኔዎቹ ከፍተኛ የራስ ምታት ሳይሆንባቸው አይቀርም፡፡ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በተደጋጋሚ የአዲስ ቅጥረኛ ወታደር ማስታወቂያ ቢያወጡም፣ አይደለም የሚመለመል ወታደር ቀርቶ የሚመዘገብ ጠፋ፡፡ እናም ይህንን ችግር ለመፍታት ወያኔ አዲስ ዘዴ ቀየሰ፡፡ ከከተማ እስከ ገጠር ቀበሌ፣ በብረታብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ስም አማላይ ማስታወቂያዎችን አስለጠፈ፡፡ ይህ በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የወጣው ማስታወቂያ የሚመለምለው በሚከተሉት የሙያ ዘርፎች እንደሆነ ይዘረዝራል፡፡ ጄኔራል መካኒክ ኤሌክትሪክሲቲ/ ኢንዱስትሪያል ኤሌክትሪክ ሲቲ/ ኤሌክትሮኒክ /ማካትሮኒክ/ ማሽን ቴክኖሎኪ አውቶ መካኒክ አውቶ ኤሌክትሪክ *የምልመላ መስፈርቱ ‹‹በመከላከያ ሚኒስቴር ለአዲስ ምልመላ ወታደሮች ያስቀመጣቸው የቅበላ መስፈርቶች እንደተጠበቁ ናቸው›› ይላል፡፡ ይህን የማታለያ ዘዴ (አታሎ ወታደር የማድረግ) ወያኔ ብዙ ጊዜ ተጠቅሞበታል፡፡ በኢትዮ – ኤርትራ ጦርነት ጊዜ አስራ ሁለተኛ ክፍል የጨረሱ ተማሪዎችን ‹‹ኑ እናስተምራችሁና ስራ እናስቀጥራችሁ›› ብለው አታለው ከወሰዷቸው በኋላ ጦርነት ውስጥ ማገዷቸው፡፡ ብዙ እናቶችም የደም እንባ አነቡ፡፡ ዘንድሮ ግን ይህ የማታለያ ዘዴ ፈጽሞ ሊሰራላቸው አልቻለም፡፡ ምክንያቱም ይህችን የወያኔ ጨዋታ ህዝቡ በልቷታል፡፡ በገጠር ቀበሌዎች ማስታወቂያውን የለጠፉት አብዛኛውን ፖሊሶች ናቸው፡፡ በስተ-እግር መንገዳቸውም እለቱ እሁድ ስለነበር፣ የተሰበሰቡትን ገበሬዎች ልጆቻቸውን እንዲሰዱ እና ይህ እድልም እንዳያልፋቸው ሰበካ አድርገው ነበር፡፡ ከሰባኪያን ፖሊሶች አንዱ ያለው ግን በጣም ያስቃል፡፡ እንዲህ ነበር ያለው ‹‹እኔ ይህን እድል ባገኜው ኖሮ፣ ዳግም የተፈጠርሁ ያህል እቆጥረው ነበር›› ነበር ያለው፡፡ ያኔ ሁሉም ገበሬዎች ሳቁልሃ! አንዳንዶቹም ‹‹ታዲያ ለምን አትሄድም?›› ሲሉ አሾፉበት፡፡ ጋሽ ፖሊሱ በመጣበት መንገድ አፍሮ ተመለሰ፡፡ በከተማ ማስታወቂያውን ካድሬዎች ሲለጥፉ የከተማው ወጣቶች ከበው ያዩዋቸው ነበር፡፡ አብዛኛዎቹ ስራ አጥ ስለሆኑ የስራ ማስታወቂያ መስሏቸው ነበር ሰፍ ብለው ለጣፊውን ካድሬ ክብብ ያደረጉት፡፡ ማስታወቂያውን አንብበው እንኳ ሳይጨርሱ ‹‹አንተ ለምን አትሄድም›› ሲሉ አምባረቁበት፡፡ እኒህ ወጣቶችና ማስታወቂያውን የለጠፈው ካድሬ ማታ ካራንቡላ ቤት ተገናኙ፡፡ ስለ ማስታወቂው ወሬ ተጀመረ፡፡ እናም ካድሬው ማንንም ሳይፈሩ ‹‹እብድ ይሂድ እንጂ ማንም እንዲሄድ አልመክርም›› ብለውት እርፍ አሉ፡፡ በነገራችን በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ከወጣት እስከ ሽማግሌ ከመንግስት ሰራተኛ እስከ ገበሬዎች የወያኔን የጦር ካምፕ ሳይሆን የአማጺያንን ካምፕ እየተቀላቀሉ ነው፡፡ - See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/3825#sthash.w0PHu4Pi.dpuf

Saturday, 10 January 2015

ሰው በላውን ወያኔን እናጠፋዋለን!!! -ከ-አዲስ ብርሃኑ

ከ-አዲስ ብርሃኑ andargacew Tsigeአንዳርጋቸውን ሳስበው ውስጤ ያለው የኢትዮጵያዊነት ወኔ ይቀጣጠልብኛል። ብርሃን ካለ ጨለማ የለም ብርሃን ከሌለ ግን ጨለማ አለ። አንዳርጋቸው ማለት ለኢትዮጵያዊያን በሙሉ ብርሃን ማለት ነው። የለኮሰው ብርሃን በኢትዮጵያ በሙሉ የሚበራ ብርሃን ነው። አንድአርጋቸው በኢትዮጵያ የለኮሰው ብርሃን የሰላም ብርሃን ነው፣ የፍቅር ብርሃን ነው፣ የቆራጥነት ብርሃን ነው፣ የጀግንነት ብርሃን ነው፣ የአንድነት ብርሃን ነው፣ የትግል ብርሃን ነው። በዚህ ብርሃን ውስጥ የማይጓዝ ማንም ኢትዮጵያዊ የለም። አንድአርጋቸው የኢትዮጵያ ብርሃን!!!የእውነት ብርሃን ጥቅም ያለወጠህ ብርሃን የለኮስከው የነጻነት የትግል ሻማ አንተ ሻማ ሆነህ እየቀለጥክ ብርሃንነትን የለበስክ የኢትዮጵያ ብርሃናዊ ጀግና አንተ ነህ። ወያኔ የፈራው ስራህን ብቻ ሳይሆን ስምህንም ጭምር ነው። አንድነት ለወያኔ አይመቸውም አንድነትን ይፈራል ህብረትን ይጠላል ለያይቶ እና ከፋፍሎ መግዛትን ነው የሚፈልገው። ስለዚህ አንድአርጋቸው ሲባል ያባንነዋል።ወያኔ ለዘረፋው አንድነት አይመቸውም ለተንኮል ስራው አይመቸውም ስለዚህ እንኳን ስራህን ስምህንም አይወዱትም። በኢትዮጵያዊያን ግን ስምህም ተግባርህም ይወደዳል። እዚህ ጋር ነው ቁም ነገሩ በህዝብ መወደድ እና መከበር። የኢትዮጵያ ህዝብ የሰላም ብርሃን የለኮሱትን እና ወደ ብርሃን የሚወስዱትን ብርቅዬ ታጋይ በማይጠፋው በኢትዮጵያዊ መዝገብ ውስጥ ጽፈው ያስቀምጧቸዋል ። ወያኔ እና ከነግብርአበሮቹ ግን ከነስራቸው ይጠፋሉ። ስለ አንዳርጋቸው ጽጌ የተለቀቀውን ቪዲዮ አይቼ በጣም ነውያፈርኩት በቪዲዮ መግቢያው ላይ ምዕራባዊያን የእስር አያያዝ ላይ ትችት ሲያቀርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን የእስረኛ አያያዝ በሰላም እንደሆነ እጅ እጅ ያለውን ወሬአቸውን በተለመደ የውሸት ቋንቋቸው ዛሬም ሲደግሙት አይናቸውን በጨው አጥበው በመቅረብ አንዳርጋቸው የሚናገረው ንግግር እራሱ ፈልጎ እንደሆነ አድርጋችሁ አቀረባችሁ። ቪዲዮው ስንመለከት ግን 14 ደቂቃ ባልሞላች ንግግር ውስጥ የአንድአርጋቸው የለበሰው ልብስ በየደቂቃው የቀያየራል ቪዲዮው በየደቂቃው ይቆራረጣል ይበጣጠሳል በዛ ላይ የተላለፈው መልእክት ምን እንደሆነ የማይገባ። ይህንን ቪዲዮ እንደ ኢትዮጵያዊ ሆኜ ሳስበው በጣም አሳፋሪ ነው እንደ ወያኔ አውሬነት ሳየው ደግሞ የምጠብቀው ስለሆነ አይደንቅም የሚገርመው የካድሬዎች ጫጫታ ነው ተንጫጩ እኮ ወይ መንጫጫት በዚህ ዘምን የሚታለል ወይም የወያኔን ስራ የማያውቅ ማንም ኢትዮጵያዊ የለም ኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስት አቸባሪ ነው ያስቸገረው። አንዳርጋቸው የለኮሰው የትግል ብርሃን ወያኔን ጥሎ ካልሆነ በስተቀር መቆሚያ የለውም። ወያኔ የአንድአርጋቸውን ጽጌ ቪዲዮ የለቀቀው ግራ ገብቶት ነው ወያኔ ሲጨንቀው ሲጨንቀው ማስተንፈሻ ይፈልጋል ሰሞኑን 3ት የአየር ሃይል አብራሪዎች ከነ ሄልኮፕተር ወደ ኤርትራ መግባታቸው ወያኔን መካዳቸው ያስደነገጠው በተጨማሪም 4ት የአየር ሃይል የተዋጊ አብራሪዎች ወደ ኬኒያ መግባታቸው እና የመከላከያ ሰራዊት ከነ ትጥቁ እየከዳቸው ስለሆነ የመውደቂያው ዋዜማ ላይ መሆኑን ስላወቀው ስለደነገጠ ማስተንፈሻ ስለፈለገ የህዝቡን ሃሳብ ለመበተን በጣም አሳፋሪ እና የተቆራረጠ በዛ ላይ ሃሳቡ ግልጽ ያልሆነ ቪዲዮ ለመልቀቅ ተገደዋል። አሁን ወያኔ በሚደሰኩረው ዲስኩር ዲስኩር ተታሎ ግዜ ሰጥቶ የሚያወራ ቢኖር ወያኔ እና ካድሬዎች ብቻ ናቸው። እኛ ግን አንዳርጋቸው በለኮሰው የብርሃን የትግል ጉዞ ተጉዘን ወያኔን ለመደምሰስ ቆርጠን ተነስተናል። ወያኔ ሆይ አሁን የዘራኽውን ማጨጃህ ሰዓት ላይ ነህ። የኢትዮጵያ ህዝብ የተገደለበት የቆሰለበት የተደበደበበት የተሰደደበት የተረገጠበት የተናቀበት ግዜ አብቅቶ ኢትዮጵያዊው ቁጭቱን ለከፍል ቆርጦ ተነስቷል። ህዝብ ያቸንፋል ወያኔ እና ካድሬዎች ለአንደ እና ለመጨረሻ ግዜ ይጠፋሉ። ድል ለኢትዮጵያዊያን!!!

Thursday, 25 December 2014

በነ ሀብታሙ አያሌው የክስ ጉዳይ የተሰየመው ችሎት ‹አስገራሚ› ውሎ

∙ተከሳሾቹ ‹‹ዘረፋ›› ተፈጽሞብናል ብለዋል ∙‹‹ለማን አቤት ይባላል?›› ሀብታሙ አያሌው በላይ ማናዬ ዛሬ ታህሳስ 15 ቀን 2007 ዓ.ም በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮችን ጨምሮ 10ሩም ተከሳሾች በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛው ወንጀል ምድብ ችሎት ቀርበው ነበር፡፡ የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና አቶ አብርሃ ደስታ እንዲሁም አንደኛ ተከሳሽን ጨምሮ ስድስት ተከሳሾች ተሟልተው ፍርድ ቤት ተገኝተዋል፡፡ ችሎቱ የተሰየመው ታህሳስ 9 ቀን 2007 ዓ.ም በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ ወቅት ተከሳሾች በቀረበባቸው የሽብር ክስ ላይ የሰጡትን መልስ በተመለከተ 7ኛ ተከሳሽ መልስ በዕለቱ ባለማቅረባቸው አሟልተው እንዲቀርቡ ነበር፡፡ በተጨማሪም ተከሳሾች በእስር ላይ ባሉበት ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሊጎበኟቸው የሚሄዱ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው ወደ እስር ቤቱ ሲገቡ በተለየ መዝገብ እንዲመዘገቡ እየተደረጉ መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበው ስለነበር ይህን በተመለከተ ማረሚያ ቤቱ ማብራሪያ እንዲሰጥ በታዘዘው መሰረት ማብራሪያውን ለመስማት ነበር፡፡ የተከሳሾች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች በጥየቃ ወቅት በተለየ መዝገብ ይመዘገባሉ የተባለውን አቤቱታ በተመለከተ፣ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በደብዳቤ መልስ መስጠቱ የተገለጸ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ‹‹ማረሚያ ቤቱ በሰጠው መልስ እስረኞች ከሌሎች በተለየ የደረሰባቸው ችግር የለም›› ማለቱን ገልጾ ይህንኑ መልስ ሙሉ ለሙሉ መቀበሉን አስታውቋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን በዛሬው የችሎቱ ውሎ ላይ ተከሳሾች ለየት ያለ አቤቱታ በጠበቆቻቸው በኩል አቅርበዋል፡፡ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ለችሎቱ እንዳስረዱት ደንበኞቻቸው ከሌሎች በተለየ መልኩ ከፍተኛ በደል እየተፈጸመባቸው ነው፡፡ አቶ ተማም አባቡልጉ በታህሳስ 12 ለ13 ቀን 2007 ዓ.ም አጥቢያ ሌሊት ስምንት ሰዓት ጀምሮ ደንበኞቻቸው ላይ ድንገተኛ ፍተሻ ተደርጎ የግል ማስታወሻዎቻቸው፣ ገንዘብ እና በተከሰሱበት ጉዳይ ላይ እያዘጋጁት የነበረው መቃወሚያና መከራከሪያ ተወስዶባቸዋል ብለዋል፡፡ ‹‹ደንበኞቼ ላይ እየተደረገ ያለው ጉዳይ ለህይወታቸውም የሚያሰጋቸው ነው፡፡ በማረሚያ ቤቱ በሌሊት ፍተሻ ያደረጉባቸው ሰዎች ቀደም ሲል በምርመራ ወቅት ‹ህገ-ወጥ› ተግባራት ሲፈጽሙባቸው የነበሩ የፌደራል ፖሊስና የደህንነት አባላት ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህን ሰዎች ደንበኞቼ ያውቋቸዋል፡፡ ስለሆነም ፍተሻው የተከናወነው በማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች አልነበረም ማለት ነው፡፡ ድርጊቱ የተፈጸመው የተለየ የስም ዝርዝር ተይዞ ከሌሎች በተለየ መልኩ ነው፡፡ ለአብነት ደንበኞቼ አቶ አብርሃ ደስታና በሌላ የክስ መዝገብ የተከሰሰው አብዱራዛቅ አክመድ ላይ የሆነው ከሌሎቹ በተለየ መልኩ ነው፡፡ ፍተሻው ስለት ነገር አልያም ሌላ ህገ-ወጥ ቁሳቁስ ለመያዝ የተደረገ አለመሆኑን ከተወሰዱት ንብረቶች ማየት ይቻላል›› ሲሉ አቶ ተማም ለፍርድ ቤቱ በደንበኞቻቸው ላይ የተፈጸመውን ድርጊት አስረድተዋል፡፡ ይህን በተመለከተ አስተያየት የሰጡት የፌደራል አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ በበኩላቸው፣ ‹‹ማረሚያ ቤቱ መንግስት ዜጎች ታንጸው እንዲወጡ ያሰራው ነው፡፡ ይህን አሰራር ለመጠበቅም የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር የተለያዩ ስራዎችን ሊሰራ ይችላል፡፡ እየቀረበ ያለው አቤቱታም ከዚህ አኳያ መታየት ያለበት ነው›› ብለዋል፡፡ ጠበቃ ተማም የደንበኞቻቸውን አቤቱታ ከህግ አንጻር ያስረዱ ሲሆን፣ ‹‹በመሰረቱ ፍተሻ ሊካሄድ መቻሉ ላይ አይደለም አቤቱታው፡፡ የተካሄደው ፍተሻ ግን ህገ-ወጥ ነው፤ ምክንያቱም ፍተሻው የተከናወነበት ሰዓት ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ባለው ጊዜ ሳይሆን ሌሊት 8 ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡ ይህ ህገ-ወጥ ነው፡፡ በሌላ በኩልም ፍተሻው በማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች አይደለም የተከናወነው፡፡ በደህንነቶችና የፌደራል ፖሊሶች ነው ፍተሻው የተደረገው፡፡ ይህም ማረሚያ ቤቱ ደንበኞቼን ለመጠበቅ ፍላጎቱም ሆነ ብቃቱ እንደሌለው ያሳያል፡፡ ስለሆነም ፍርድ ቤቱ ይህን መሰል ድርጊት የፈጸሙት አካላትና በማን ትዕዛዝ እንደተፈጸመ ምርመራ እንዲካሄድ ትዕዛዝ እንዲሰጥልን እንጠይቃለን›› ብለዋል፡፡ ጠበቃ ተማም በተጨማሪ ከደንበኞቻቸው ላይ በፍተሻው ወቅት የተወሰዱባቸው ንብረቶችና ማስታወሻዎች እንዲመለሱላቸው ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው አመልክተዋል፡፡ ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ ‹‹የተለየ ከፍተኛ በደል ደርሶብኛል›› በሚል ለፍርድ ቤቱ እንዲያስረዱ ዕድል እንዲሰጣቸው ጠይቀው የነበሩት 3ኛ ተከሳሽ አቶ ዳንኤል ሺበሺ የጠየቁት የመናገር እድል ሳይፈቀድላቸው ቀርቷል፡፡ በጠበቆቹ አማካኝነት የቀረበው አቤቱታን በተመለከተ ችሎቱ አስተያየት የሰጠ ሲሆን በተለይ ጠበቃ ተማም አቤቱታውን ባቀረቡበት ወቅት ‹‹ማረሚያ ቤቱ ደንበኞቼን ለመጠበቅ ፍላጎትም ብቃትም የለውም›› ያሉት አገላለጽ ተገቢ ስላልሆነ እንዲታረሙ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡ ይህንኑ ጉዳይ በቃል የገለጹት የመሐል ዳኛው፣ ‹‹እንዲህ አይነት አገላለጽ ማረሚያ ቤቱ የበቀል እርምጃ እንዲወስድ የሚገፋፋ እንዳይሆን…›› በማለት ሌላ አስገራሚ መነጋገሪያ ከፍተዋል፡፡ ይህን የዳኛውን ንግግር ተከትሎ 2ኛ ተከሳሽ አቶ ሀብታሙ አያሌው የመናገር እድል ከተደጋጋሚ ጥያቄ በኋላ ለአጭር ጊዜ ተፈቅዶለታል፡፡ እናም፣ ‹‹እርስዎ እያሉት ያለው ነገር ተገቢ አይደለም፡፡ በህይወቴ ላይ የደህንነት ስጋት አለብኝ ነው እያልኩ ያለሁት፡፡ ይህንን ስጋቴን ለችሎት እያስረዳሁ ነው፡፡ ግን እርስዎ ‹የበቀል እርምጃ› እንዲወሰድብን ማሳሰቢያ እየሰጡ ነው፡፡ ይህ ተገቢ አይደለም፡፡ በእርግጥ አሁንም የበቀል እርምጃ እንደማይወሰድብን ማረጋገጫ የለንም፡፡ እሺ ለማን አቤት ይባላል? የደረሰብንን በደል ለፍርድ ቤት ከማስረዳት ውጭ ለማን አቤት እንላለን….አሁን እኮ ፍርድ ቤቱ ከማረሚያ ቤቱ ጋር መወገኑን ነው እያየን ያለነው፡፡ ፍርድ ቤቱ የእኛን አቤቱታ እየሰማ አይደለም፡፡ ከፍርድ ቤት ውጭ ለማን አቤት እንበል?›› ሲል አቤቱታውን በስሜት ውስጥ ሆኖ አስረድቷል፡፡ የሀብታሙን ንግግር አዳምጠው አንደኛ ዳኛ ‹‹እኛ ሳንሆን ህጉ ነው ይህን እንድንል የሚያደርገን›› በማለት አጭር መልስ ሰጥተዋል፡፡ በዚህ መልኩ ቀጥሎ የዋለው ችሎት በተከሳሾች በኩል የቀረበውን አቤቱታ መርምሮ ፍርድ ቤቱ ይህን ጉዳይ የማየት ስልጣን አለው ወይስ የለውም በሚለው ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት፣ እና መደበኛ ክሱን ለማየት ለታህሳስ 24 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተጥቷል፡፡

Monday, 1 December 2014

ከ40 በላይ የአንድነት አባላትና አመራሮች በቃሊቲ እስር ቤት ታገቱ

የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አስራት አብርሃን ጨምሮ ከአርባ በላይ የሚሆኑ የፓርቲው አባላት ቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ ታገቱ፡፡ አንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለህሊና እስረኞች በሚል መሪ ቃል ከህዳር 14 ጀምሮ እያካሄደያለው የማህበራዊ ሚዲያ ንቅናቄ አካል የሆነውን የህሊና እስረኞችን የመጎብኘት መርሀ-ግብር ለመሳተፍ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ያቀኑት የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አስራት አብርሃ እና የፓርቲው የአዲስ አበባ ሰብሳቢ አቶነገሰ ተፋረደኝን ጨምሮ 40 የአንድነት ፓርቲ አባላት ለግዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሰበብ በእስር ቤቱ ግዜያዊ ማቆያ እንዲገቡ መደረጋቸውን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ከስፍራው ዘግበዋል፡፡ አንድነት የሚሊዮኖች ድምፅ ለህሊና እስረኞች በሚል መሪቃል በዚህ ሳምንት እያካሄደ ያለው ንቅናቄ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን ትኩረት ማግኘቱ ገዢውን ቡድን ማስቆጣቱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ዘግይቶ የደረሰን ዜና እንዳመለክተው ከሆነ ደግሞ; የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ነገሰ ተፈረደኝ፣ ንዋይ ገበየሁ፣ ዳንኤል ሙላትና አቶ ብርሐኑና ትግስት ክራውን ሆቴል አካባቢ አሁንም ታስረው እንደሚገኙ ምንጮች ገለጹ፡፡ ስማቸው ከላይ የተጠቀሱት ግለሰቦች የታሰሩ የህሊና እስረኞችን ለመጠየቅ ወደቃሊቲ አምርተው ከነበሩት ሰዎች መካከል ይገኛሉ፡፡

Wednesday, 26 November 2014

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አመራሩ ድብደባ እንደተፈጸመበት ገለፁ።

አንድ ወር የትግል መርሃ ግብር ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎችና ህዝባዊ የለውጥ ንቅናቄዎችን በገዥው ፓርቲ አፈና እና ማስፈራሪያ እንደማይቆም ትብብሩ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡ ህዳር 7/2007 ዓ.ም የትብብሩ ህዝባዊ የአደባባይ ስብሰባ በኃይል መበተኑን፣ ይህንኑ አስመልክቶ ህዳር 7/2007 ዓ.ም ለሰማያዊ ፓርቲ ማስጠንቀቂያ መጻፉን እና ለህዳር 21 ለሚደረገው ስብሰባ የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ደብዳቤ በፖስታና በአካል ቢላክለትም ማሳወቂያ ክፍሉ አልቀበልም ማለቱን የገለጸው መግለጫው ስርዓቱ የትብብሩን የትግል መርሃ ግብር ለማስቆም እየጣረ መሆኑን ገልጾአል፡፡ በተጨማሪም የትብብሩ አንድ አባል እና ትብብሩ ህዳር 21/2007 ዓ.ም የሚያደርገውን የአደባባይ ስብሰባ የሚያስተባብረው መኢዴፓ ሊቀመንበርና የትብብሩ ገንዘብ ያዥ የሆኑትን አቶ ኑሪ ሙደሲር ላይ የድብደባ ወንጀል እንደተፈጸመባቸው አመራሩ ገልጸዋል፡፡ ትብብሩ በዛሬው ዕለት ‹‹ማስፈራራትና አፈና የዴሞክራሲ ጥያቄዎችንና ሠላማዊ ሕዝባዊ የለውጥ ንቅናቄዎችን አይቀለብስም›› በሚል በሰጠው መግለጫ የተገኙት አቶ ኑሪ ሙደሲር ከሁለት ሳምንት በፊት ጀምሮ ወከባ እንደተፈጸመባቸው ገልጸዋል፡፡ አቶ ኑሪ ‹‹መኪናችን ገጨህብን ባሉ 10 ሰዎች ነው የተደበደብኩት፡፡ ከአሁን ቀደምም ፖሊሶች ምንም አይነት ችግር ሳላደርስ ገጨህብን ብለው አዋክበውኛል፡፡ ሰሞኑን መኪናዬን ቢሰብሩብኝም በስህተት የተመታ መስሎኝ ነበር፡፡ አሁን ከደበደቡኝ መካከል ተክለኃይማኖት አካባቢ የሚገኙ ካድሬዎችና ደንብ አስከባሪዎች ይገኙበታል፡፡ መጀመሪያ ላይ ፖሊሶች ‹ቢገጭስ እንዴት 10 ሆናችሁ አንድ ሰው ትደበደርባላችሁ?› ካሉ በኋላ እንደገና ካድሬዎች መሆናቸውን ሲያውቁ እነሱን ትተው እኔን ይወቅሳሉ፡፡ ይህም የሚያሳየው ሆን ተብሎ የተደረገ ነገር መሆኑን ነው›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ህዳር 21/2007 ለሚደረገው የአደባባይ ስብሰባ በአካልም ሆነ በፖስታ ደብዳቤ ቢላክም የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍሉ ባለመቀበሉ የትብብሩ ደብዳቤ በፋክስ እንዲደርሰው እንደተደረገ የትብብሩ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ገልጸዋል፡፡ ሆኖም በፋክስ የተላከውን ደብዳቤ አልቀበል ካለ የትብብሩ አመራሮች በጋራ ደብዳቤውን ለማድረስ እንደሚሄዱ፣ የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍሉ ይህንም አልቀበልም ካለ ሁነቱን በቪዲዮና በፎቶ በመቅረጽ ለህዝብ በማሳወቅ ስብሰባውን እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡ በሂደቱም የሚከፈለውን መስዋዕትነት ሁሉ ለመክፈል እንደተዘጋጁ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ገልጸዋል፡፡