Wednesday, 30 September 2015

አገር የምትኖረው በ3 ነገር ነው በወታደር በገበሬ እና በመምህር ። – ከአዲስ ብርሃኑ ፡

ethiopiaአገር ለማፍረስ ቆርጦ የተነሳው ወያኔ ኢትዮጵያ የምትባለው አገር እንድትኖር በመሰሪ ሃሳቡ ሌት ተቀን የማይቆፍረው ግድጓድ የለም የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። ነገር ግን እንደ አሳቡ ሊሆንለት አልቻሉም ዘር ከዘር ሊያጋጭ ብዙ ጣረ አልተሳካለትም፤ ሐይማኖት ከሃይማኖት ሞከረ ይሄም አልሰራ አለው ሃሳቡ ሁሉ መና ሲቀርበት እራሱ ከሳሽ እራሱ ፈራጅ በሆነበት ፍርድ ቤት የብዙሃን ነጽሃን ሰው መሰቃያ ወደ ሆነው ወህይኒ እየወረወረ ባልሰራበት ወንጀል ባላደረጉት ድርጊት ንጽሐኑን ማሰቃየት ከጀመረ ድፍን 24 አመት አለፈ። -
መምህር….. አንድ አገር ከሚያስፈልጋት ዋናው መሰረታዊ ነገር መምህር ነው። መምህር ከሌለ የተማረን ህብረተሰብ ማግኝት አይቻልም። መምህር በጠመኔው ለአገር የሚሆን ፍሬ ለህዝብ የሚጠቅም ዘር በሰው አእምሮ ውስጥ የሚዘራ እና ብዙ ጥበቦች ባለ ብዙ እውቀት ባለቤት አገርን በጥበብ የሚመራ ላገሩ በእውቀት የሚያገለግል ለአገር የሚጠቅመውን ካመነበት የሚሰራ ካላመነበት ደግሞ እንቢ የሚል ማንኛውንም ነገር ሰለ ህዝብ ብሎ ስለ አገር ብሎ ማድረግ የሚቻል ዜጋን የሚቀርጹት መምህራናን ናቸው። ዛሬ ወያኔ እያደረገ ያለው እኔ የምላቹሁን አድረጉ እኔ የምላቹሁን አስተምሩ እኔ የምላቹሁን መመርያ ተቀበሉ ብሎ አገርን የሚያጠፋ ሆኖ ሰላገኙት የወያኔ ደጋፊ ባለመሆናቸው ብቻ አገርን የሚያቀኑን መምህራን ትውልድን የሚቀርጹ መምህራን በካድሬ በመተካት የተማረ እንዳይበቅልባት ያወቀ እንዳይወጣባት ትምህርት ቤቶችና ዪንቨርስቲዎች ያቃጣሪወች መናህርያ አድርጓታል። እንግዲህ ወገኔ የመምህራን መነካት የኢትዮጵያ አንዱ መሰረቱ እየተናጋ ነውና ልትነቃ እና የወያኔ አገር አጥፊነቱን አውቀን በቃህ ልንለው ይገባል። ገበሬ…… አገር የምትኖረው ገበሬው አምርቶ በሚያበቅለው ምርት ነው ገበሬው ጠንክሮ በማረስ አገርን በመመገቡ ሂደት የአገርን መሰረት ነው። ዛሬ ገበሬው ከመሬቱ በማፈናቀል ለውጪ ባለሃብት ለኢንቬስተር በመስጠት እንዲሁም በግድ ማደበርያ እንዲወስድ እያደረጉት ባለ እዳ በማድረግ እዳውን መክፈል ሳይችል ሲቀር መሬቱን ጥሎ እንዲሄድ በማድረግ ተሳዳጅ አድርገውታል። ገበሬ የለም ማለት አገር የለችም ማለት ነው ።ገበሬው በማሰቃየት እረፍት በመንሳት እስመርረውት ያሉት ወያኔወች ሃሳባቸውም ራያቸውም ሰለ ኢትዮጵያ እና ሰለ ሕዝቧ ስላልሆነ ስለሚያደርጉት ነገር መጸጸት እንኳን አያሳዩም ስለዚህ ገበሬው ሲነካ የአገር መሰረት መነካት ነውና ወገኔ እንግዲህ ንቃ። ወታደር….. አገር የምትጠበቀው በወታደር ነው አንድ አገር ጠንካራ የወታደር ከሌላት ጠላት በቀላሉ ይዳፈራታል። ስለዚህ ጠንካር የወታደር ተቋም ለአገር አጥርም መሰረት ነው። ዛሬ ግን ወያኔ እየሰራ ያለው የወታደር ተቋም በወታደራዊ ስልጠና እንዲሁም ትምርት በብቃት የሚበልጣቸው እያሉ ትግሬ በመሆኑ ብቻ አዛዥ ቦታ ላይ እንዲቀመጥ ይደረጋል ይሄ አካሄድ ለወያኔወች የአገር ማፍረስ አላማቸው ስለሆነ ምንም አይሰማቸው ለትግሬወች ግን ጊዚያዊ ሹመት ሲሰጣቸው ሁሉንም ቦታ ያለ እውቀታቸው ቦታውን እንዲይዙት ሲደረግ ለምን ብላቹ መጠየቅ ሲገባቹሁ የተሰጣችሁን ስልጣን ተቀብላቹ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ላይ በደልና ጫና የምትፈጥሩ እንግዲህ እዳው በእጃቹ ነው። የወያኔ ባለስልጣን ባንተ ስም የአገርን ንብረት እየዘረፉ እያሸሹ ይገኛሉ አንተ ግን ከህብረተሰቡ ጋር የትም አትሄድም ያኔ በሰፈሩት መስፈርያ እንዳይሆንባቹሁ የትግሬ ተወላጆች በወታደር ላይ የምታደርጉትን በደል ታቆሙ ዘንድ ያስፈልጋል። እንተም ከጥቂት የአገር አጥፊ እና ዘረፊ ጋር ባለመወገን አንድነታቹሁን የምታሳዩበት ጊዜ በጣም አጭር ነውና ይታሰብበት። ካለበለዚያ ግን ወደ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ደምና ጉልበት እንዲሁም በኢትዮጵያ ሕዝብና ሃብት እንደፈለጋቹ እየሆናቹ የምትኖሩበት ጊዜ ማብቂያው ይመጣል። ወታደሩም እራሱንና አገሩን ሕዝቡን የመጠበቅ ነጻ የማውጣት ሃላፊነት እንዳለበት ወያኔ የሚያውቅበት ጊዜ ቅርብ ነው። ወያኔወች የመከላከያ ሰራዊት የሃገር መሰረት ስለሆነ ይህንም ለማፍረስ እና ለመበተን ሌት ተቀን እየሰሩ ነው። እውነት ነው መምህሩም ወደቀድሞ ቦታቸው ተመልሰው ባላቸው እውቀት ጠመኔን ይዘው ያለምንም ተጽእኖ ዜጋን የሚያፈሩበት ጊዜ ቅርብ ነው። እውነት ነው ገበሬው ሞፈሩን አንስቶ እርሻውን አስፍቶ በትራክተር አርሶ ሕዝቡን የሚመግብበት ቅርብ ነው ። እውነት ነው ወታደሩ ወያኔን የተባለ ወንበዴን አጥፍቶ ለሕዝቡና ለአገሩ ዘብ የሚቆምበት ጊዜ ቅርብ ነው ። ሞት ለወያኔ!!! አዲስ ብርሃኑ -

Friday, 14 August 2015

በአገራችን በሰሜን ምስራቅ እና በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ መጠኑ እየጨመረ መጥቷል፡፡

በአገራችን በሰሜን ምስራቅ እና በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ መጠኑ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ጉዳዩ ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው ተመሳሳይ ድርቅ በመጪው አመት 2008 ዓ.ም በጥቅምት እና በህዳር ወር ሊከሰት እንደሚችል ባለሙያዎች እየጠቆሙ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ገዥው መንግሰት አሁንም የችግሩን አሳሳቢነት ወደ-ጎን በማድረግ ፤የስራዓቱ ደጋፊ እና አቀንቃኝ ከሆኑ ዲያስፖራ ጋር “አስረሽ ሚቺው” እያለ ከበሮ እየደለቀ ይገኛል፡፡ ሆኖም በአገራችን በተለይ በሰሜን ምስራቅ የተከሰተው ድርቅ እንስሳቶችን በከፍተኛ ሁኔታ እየገደለ የሚገኝ ሲሆን ፣በሰው ሕይወት ላይ ቁጥሩ ቀላል የማይባል የሞት አደጋ እያንዣበበ ይገኛል፤በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎች በሰውንት መዳከም እና እስን ተከትሎ በሚመጣ በሽታ እየተጠቁ ናቸው፡፡ ይህ እውነት ከባለፉት ቀናት ዛሬ ላይ ከኢትዮጵያ አልፎ በአለም ላይ መረጃው እየተሰራጨ ይገኛል፤ ይሄን ተከትሎ ገዥው መንግሰት መረጃውን ደብቆ የመያዝ ፍላጎቶ ሊከሽፍበት ችሎአል ፡፡ የመንግሰት ውጥን ሣይሳካ ሲቀር፣ የመንግሰት ኮሚኒኪሽን ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሬዲዋን ሁሴን “ሰባት ሞቶ ሚሊይን ብር በጀት የያዝን በመሆኑ ችግሩን መቆጣጠር እንችላለን” በማላት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ነገሩን ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው እንደሳቸው ገለፃ “ምንም አይነት የዉጪ እርዳታ አያስፈልገንም፣ የዚህን ያህል አሳሳቢ ደረጃ አልደረሰም” ማለታቸው ነው፡፡ እሳቸው ይሄን ይበሉ እንጂ አሁን ላይ የተከሰተው ድርቅ እና በቀጣይ አመት ይከሰታል ተብሎ የተገመተው ድርቅ፣ ከመንግሰት ቅድመ ዝግጅት ማነስ እና የእርዳታ ድርጅቶች መንግሰት በተለመደው መንገድ እየተከላከለ የሚቀጥል ከሆነ፤ አገራችን አስከፊ ሁኔታ ውስጥ የሚከት ነው፡፡ መንግሰት 7መቶ ሚሊየን ብር መደብኩ ይበል እንጂ፣በመንግስት የአሰራር ብልሹነት እና ስር ከሰደደው ሙሱና አንፃር ችጉሩን የቱንም-ያህል ፈቀቅ እንደማያደርገው እውን ነው ፡፡ መንግሰት በተለያየ ወቅት ኢትዮጵያ በምግብ እራሷን ችልለች ይበል እንጂ፣ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ጾም አዳሪ ነው፡፡ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ድርቅ ተከስቶ መንግስት እርዳታ አያስፈልግም ችግሩን መቋቋም እችላለለው በማለቱ፤ አለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ድጋፍ ማድረጋ ባለመቻላቸው በሰው እና በእንስሳ ላይ ቁጥሩ ቀላል የማይባል ሞት ተከስቷል፡፡ ድርቁ ሊከሰት የቻለበት ዋና ምክንያት ከአለም አቀፍ የአይር ንብረት ለውጥ ጋር በተገናኘ ነው፡፡ በጠንካራ የመንግሰት አስተዳደር እራሳቸውን ላዋቀሩ በሌሎች አገራት፣ ይህ አይነቱ ድርቅ በሚከሰትበት ወቅት ከመንግሰት የመጠባበቂያ በጀት እና የእህል ክምችት በመጠቀም ችግሩን ለመቋቋም ጥረት ይደረጋል፡፡ እንዲህ አይነቱ መሠረት የሌለው መንግሰት እና ሕዝብ ደግሞ በለጋሽ አገራት የገንዘብ ድጎማና የምግብ እርዳታ ይደረጋል ፡፡ በተለይ ደግሞ አምባገነን መንግስታት በሚመሩት አገር የደርቅ ችግር በሚከሰትበት ወቅት ችግሩን አፍኖ መያዝ ዋንኛ መገለጫቸው ነው፡፡ እንደምክንያትነት የሚነገረው “እረዳት አያስፈልገንም እራሳችን ችለናል” የሚል ባዶ ቀረርቶ ነው፡፡

Saturday, 18 July 2015

አሜሪካኖቹ ዲፕሎማቶች የኢትዮጵያ መንግስትን አስጠነቀቁ

**የኦባማ ጉብኝት ለውይይት እንጂ ወንጀለኛን መንግስት ለማጽደቅ እንዳልሆነ አስረዱ ** “የተፈቱት የዞን ዘጠኝ ጋዜጠኞች ፓስፖርታቸው እንኳን እንዳልተመለሰ እናውቃለን:: መጀመርያውኑ መታሰር እልነበረባቸውም:: ሲፈቱም አፈታታቸው ሙሉ አይደለም” ዛሬ እዚህ ዋሺንገተን ዲሲ ላይ ጠንካራ ውይይት ሲካሄድ ነበር:: ውይይቱ የኦባማን የምስራቅ አፍሪካ ጉዞ በተመለከተ ሲሆን : አሜሪካኖቹ መራር መልሶችን ሲመልሱ ተደምጠዋል:: የኦባማ ጉብኝት ለአምባገነኖች ሽፋን መስጠት ሳይሆን ሌሎች በርካታ ዓላማዎች እንዳሉትም አስረድተዋል:: በውይይቱ የዞን ዘጠኝ ጋዜጠኞች አስር ፈጽሞ ያልተገባ መሆኑን ጠቅሰው: ሲፈቱም ሙሉ ነጻነት እንዳልተሰጣቸው ፓስፖርታቸው እንኳን እንዳልተመለሰላቸው አስረድተዋል::ከዚሁም ጋር በተያያዘ ሰሞኑን አቶ ኃይለማርያም ኤርትራን ስለመምታት የተናገሩትን ዛቻ በተመለከተ ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል:: ኢትዮጵያ የኤርትራን ድንበር ጥሳ እንዳትገባና ብትገባ ግን አሜሪካ እንደምታወግዘው ገልጸዋል:: ሌሎችም ሌሎችም ውይይቱ ይህን ይመስል ነበር ::

Friday, 22 May 2015

የወያኔ በጉልበት የምረጡኝ ዘመቻ (ከ አዲስ ብርሃኑ)

ንብን ምረጡ ማለት ከጀመሩ ሰነባብተዋል ። ለአገር እድገት፤ ለብለጽግና ፤ለእኩልነት ፤የተጀመረውን እድገት፤ ለማስቀጠል እያሉ...... እያሉ.... መንገድ ተሰራ፤ ህንጻ ተሰራ ፤ስልጣኔ ገባ ፤ይህን ሁሉ በዘመነ ኢህአዲግ ነው ብለው ይናግሩናል። ይህን ማለታቸው ጥሩ። ምንም ተቃውሞ የለኝም ። አንድ ኢትዮጵያዊ የፈለገውን የመከተል እና የማመን ጉዳይ ነው ። ሌላም ሌላም ይጨምሩ ስለነሱ ማውራት ሳይሆን ለኛም እድል ስጡን እኛም ስለ ኢትዮጵያ የምነለው ነገር አለ ስለ ወያኔም የምንነቅፈው ነገር አለን ይህ ነው ቁምነገሩ ፍርድ እና ውሳኔውን ለሕዝብ በመተው ሕዝብ የመረጠውን እንዲመራው ማድረግ ግድ ይላል። ወያኔ ኢትዮጵያን ማስተዳደር ከጀመረ የማይታወቁና የማይፈለጉ ሃሳቦች እና ነገሮች ገብተዋል። ያም ህዝብ ወዶ ሳይሆን በግድ የህዝብ ሃሳብ ተጥሶ የአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ሃሳብ እና አላማ እየተንጸባረቀ ነው። ባንዲራው ላይ ከተለጠፈችው ኮከብ ብንጀምር ከ90% በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን የኮከብ ምልእክት አርማ ያለውን ባንድራ አይቀበለውም ።የኮከቡ ትርጋሜውም ወይም አላማው ሌላ ነው። ኮከባ የምትገልጸው የስይጣንን አምላኪወችን ሲሆን በኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ የተለጠፈው ኮከብ ሶስት ትረጔሜ አለው እነሱም እንደሚከተሉት ናቸው። 1 የኢትዮጵያን ህዝብ በሰይጣናዊ ሃይል ለማፍዘዝ ፦ 2 ስይጣን ፍቅር ስለማያውቅ መለያየት እና መጣላት በኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ ለማስረጽ፦ 3 የኢትዮጵያ ህዝብ አውቆም ሆነ ሳያውቅ የሰይጣን ምልክት የሆነውን የሰይጣንን ምልክት እንዲያውቅ እና ክፋታዊ የሰይጣንን አሰራር እንዲለማመድ ለማድረግ ነው። በዚህ ዙርያ ትንሽ ብዬ ወደ ወያኔ ወደሆነችው አርማ እሄዳለው በኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔ ከገባ ጀምሮ የአገሬ ህዝብ ውስጥ ብዙ ክፋት አብሮ ገብቱአል። ለዚህም ኮከባ የወለደችው ወይም ያፈራችው ፍሬ ስናይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ፍቅር ጠፍታል ። የኢትዮጵያ ህዝብም ብርን እና ጥቅምን አምላኪ ከመሆኑ የተነሳ ወንድም ወንድሙን ፤እህት እህቷን፤ ወላጆች ልጆቻቸውን ፤አሳልፈው ይስጣሉ። ሁሉም ስልጣን ናፋቂወች ሆነዋል። አባት ከልጁ፤ እህት ከወንድም፤ ዘር ከዘር ፤ጎሳ ከጎሳ ፤ሃይማኖት ከሃይማኖት፤ ኢትዮ ጵያ ውስጥ ከእለት ወደ እለት ግጭቶ ች እየተበራቱ ጥላቻወች በሰፊው እየታዩ ነው። እናት ሌባ ልጅ ቀማኘ የሚለው ቢሄል (አባባል) በአሁን በዘመነ ወያኔ እያየነው ነው። መሪዎች ተብዬዎች ሌባ ሎሌዎች ደግሞ ቀማኞች የሆነች ሐገር ከመሰለች ሰነባብታልብ ።የጠፋው ፍቅር እንዲመለስ እና የተወሰድብን ክብር እንዲመጣ የወያኔ አዚም የሆ ነችውን ኮ ከብ ከኢትዮጵያ ምድር ማጥፋት መቻል አለብን። ይህ ኮከብ ቢሄር ቤሄረስቦችን የሚወክል ሳይሆን ጥላቻና መለያየትን የሚያሰፍን ፍቅርን የሚያጠፋ የሰይጣንን ስረአት የመከተል እና የሠይጣንን አርማ ከፍ አድርጎ የማሳየት ስራ ነው። ወደ ንብ ስንመጣ ደሞ ንብን ምረጡ... ንብን ምረጡ ...እያሉ መለፍለፍ ከጀመሩ ሰንብተዋል መረዟን ብቻ እንጂ ማሯን የማናየውን ንብን ፤በየአገሩ እየዞረች እሾኴን የምታራግፈዋን ንቧን፤ ማሯን ለንጉሶቻ ብቻ የምታበላዋን ንቧን ፤ህብረተሰባን ማሯን ታበላን ይሆን ብሎ የሚጠብቃት ተስፈኘዋን ንቧን ፤ይችን ንብ ነው ምረጡ የሚሉን። የንብ በሀሪ የአንድ ቀፎ ንብ ከሌላ ቀፎ ንብ ጋር በፍጹም አይሰማማም ተሳስታ አንዷ ንብ ወደሌላ ቀፎ ከሄደች ይገድሏታል። ወያኔም ልክ የንብ በሀሪ ነው ያለው። ከወያኔወች ድርጅት ውጪ የሌላ ድርጅት የሆነ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲኖር አይፈለግም ። ንቦች ማራችውን የሚሰሩት ለራሳችው እና ለንጉሳ ቸው ብቻ ነው። ወያኔዎችም የሚሰሩት ለራሳችው እና ለሹማምቶቻችው ብቻ ነው። ንቦች ለማር መስሪያ እንዲሁም ለቀፎ አገልግሎት የሚሆነውን በሙሉ የሚጠቀሙት ክቀፎአቸው ወጥተው በሰአት 100 ኪ. ሜ ያህል በመብረር ከአካባቢያችው ስብሰበው ወደቀፎአቸው የገባሉ። ወያኔዎቸም የኢትዮጵያን ንብረት በሙሉ በሁሉም አቅጣጫ በመዘዋወር እየዘረፉ ለራሳቸው ያክማቻሉ። ንቦች የራሳቸው ባልሆነ ነገር ማራቸውን እየሰሩ የሌላ ቀፎ ንብ ግን ወደነሱ ቀፎ እንድትገባ አይፈልጉም ወያኔም ምንም ቅሬታ በሌላችው ስዎች የሌላውን ህብረተሰብ ሃብት ለመጠቀም ይስበሰባሉ። ሊላው ህብረተሰብ ወደ እነሱ ሲጠጋ ግን ያጠፉታል ።ስለዚህ የንብን ማር መብላት የሚችለው የቀፎወቹ ንቦች ብቻ ናቸው። የኢትዮጵያንን ሃብት እየበላ እና እየተጠቀመ ያለው ብቻውን ወያኔ ነው። ኢትዮጵያ ማር ነች ማርን ደግሞ ሁሉም ይፈልጉታል አንድም ለመብላት አንድም ለመድሃኒት። ማር መብላት ካማሮት ወደ ንብ ቀፎ ባዶ እጅ አይኬድም እንደጭስ ያለ መከላከያ እና ማሩን መቁረጫ ቢላ ያስፈልጋል። ካለበለዝያ ግን በመርዝ ተወግተው ይሞታሉ። ወያኔም እንደዚሁ ነው የኢትዮጵያን ሃብትና ንብረትን የብቻው አድርጎ ማስተዳደር ከጀመረ ሰንብታል ስለዚህ ኢትዮጵያ የምትባለው አገር የወያኔ ብቻ መስሎ ከታያቸው ሰንብታል። የኢትዮጵያ ሃብት የኢትዮጵያን እንጂ የጥቂቶች ብቻ አይደለችም ብሎ ለመጠቀም እና ለሁሉም ለማዳረስ ባዶ እጅ ተኪዶ አይሆንም ።በባዶ እጅ ከተኬደ በመረዛቸው ወግተው ስለሚገሉ መከላከያ አድርገን ኢትዮ ጵያን ማዳን ግድ ይለናል። ስለዚህም ምርጫ ..ምርጫ.... የሚለው የወያኔ የማደናገርያ ዘዴ ነው እና ይህ ምርጫ አልጫ እንደሆነ እና ትርጉም የሌለው መሆኑን ልንረዳው ይገባል። አልጫ የሆነው ምርጫ የሚለወጠው አልያም የጣፈጠ የሚሆነው የሁሉም ኢትዮጵያዊ የነቃ ተሳትፎ ሲያደርግ ነው። ንብን በማጥፋት በመርዙ ከመወጋት እና ከመሞት የኢትዮጵያ ሕዝቡ ነጻ ሁኑ። ባንዲራው ላይ ያለችውን ኮከብ በማስወገድ የሰይጣንን መንፈስ የኢትዮጵያ አርማ ከመሆን እንከላከል እላለው። ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!!!! ከ አዲስ ብርሃኑ Email.. berhanu.addis@yahoo.com

Friday, 15 May 2015

በፍርሃት ውስጥ ያለው የኢሕአዴግ ሥርዓት የማዕከላዊ ዕዝ ወታደሮች ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ መመሪያ አወረደ!

የኢህአዴግ ስርአት የማእከላዊ እዝ ወታደሮች ከቦታ ወደ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ መምሪያ እንዳወረዱላቸው ምንጮቻችን ገለፁ ሲል የደህሚት ድምጽ ዘገበ:: በአዲ-ኮኮብ የሰፈሩት የማእከላዊ እዝ የበታች አመራር ወታደሮችና ተራ ወታደሮች ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር እንዳይገናኙና ወደ አዲ-ዳዕሮና ሸራሮ እንዳይንቀሳቀሱ ተከልክለው እንደሚገኙ የገለጸው የደህሚት ድምጽ እነዚህ የበላይ አመራሮች ሰራዊቱን በመሰብሰብ በአዲ-ዳዕሮ፤ አዲ ነብሪ ኢድ፤ አዲ-ሃገራይ፤ ሸራሮና አካባቢው በአጠቃላይ በአካባቢው የሚገኝ ህብረተሰብ የትህዴን አባል ሰለሆነ የምናጣራው ነገር አለን መንቀሳቀስ ክልክል ነው በማለት ትእዛዝ እንዳወረዱላቸው ለማወቅ ተችሏል። በተጨምሪም- ወታደሮቹ በአካባቢው ህብረተሰብ ላይ ጥላቻ እንዲያሳድሩና ከሱ ጋር እንዳይወግኑ የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ቅስቀሳ ሲሰጥ የሰነበተ ሲሆን ስርአቱ ከህዝብ ተነጥሎ በጠምንጃ ሃይል ብቻ የቆመ እንደሆነ በሚገባ ሰለሚያውቅ ወታደሮቹ ደግሞ ስርአቱን በመተው ከህዝባቸው ጋር እንዳይወግኑ በመስጋት የመነጨ መሆኑን ወታደሮቹ በሚገባ እንደተረዱት ለመረጃ ምንጩ የደረሰው መረጃ አስረድቷል።

Thursday, 7 May 2015

የቁልቁለቱን ጉዞ እናስቁም፤ ውርደት ይብቃን!!!

የህወሓት አገዛዝ ፋሽስታዊ ባህርያት እያደር መረን እያጣ፤ ነውረኛ እየሆነ መጥቷል። በአሳለፍነው ሣምንት ብቻ እንኳን አስነዋሪ ይዘት ያላቸው ሁለት ፋሽስታዊ ክስተቶችን አስተውለናል። አንዱ በምርመራ ስም በታሳሪዎች ላይ የሚደረገው አሳፋሪ ሰቆቃ ነው። በገላቸው በሚያፌዙና በሚሳለቁ ተቃራኒ ፆታ መርማሪዎች ፊት ለሰዓታት ተመርማሪዎች ራቁታቸውን እንዲሆኑ የሚደረግበት እና እየተፌዘባቸው የሚደበደቡበት ሥርዓት መኖሩ የጉዳቱ ሰለባዎች ይፋ ሲያወጡ እፍረቱ ለመርማሪዎቹ ብቻ ሳይሆን ይህንን ጉድ ተሸክመን ለኖርነው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ነው። በተለይም ደግሞ እንዲህ ዓይነት ክብረነክ ሰቆቃ በሴቶች ላይ እየተፈፀመ መሆኑን ስንሰማ አገራዊ ውርደቱ ያሸማቅቀናል። እንዲህ ዓይነቶችን በሰው ስቃይና እፍረት የሚዝናኑ ጉዶችን ተሸክመን የምኖር መሆናችን ሁላችንን ያዋርደናል። ይህንን አስነዋሪ “የምርመራ ዘዴ” ያጋለጡት የዞን 9 ብሎገሮች፣ ጋዜጠኞችና ፓለቲከኞች ክብርና ሞገስ የሚገባቸው ጀግኖች ሲሆኑ የተዋረዱት እነሱ ሳይሆኑ እኛ ኢትዮጵያዊያን መሆናችን ሊሰማንና “ውርደት በቃ” ልንል ይገባናል። ሁለተኛው አሳፋሪ ድርጊት ደግሞ ወገኖቻችንን በግፍ ባረደው አይሲስ በተሰኘው አሸባሪ ድርጅት ላይ የህወሓት አገዛዝ የተለሳለሰ አቋም ወስዷል ብለው ራሱ ህወሓት በጠራው ሰልፍ ላይ ተቃውሞዓቸውን ባሰሙ ወጣቶች ላይ አገዛዙ የወሰደው የኃይል እርምጃና ከዚያም ወዲህ እየተደረገ ያለው ነገር ነው። አገዛዙ ለፕሮፖጋንዳው ይጠቅመኛል ብሎ በጠራው ሰልፍ ወጥተው ተቃውሞዓቸውን የገለፁ ወጣቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተደብድበዋል፤ በጅምላ ወደ እስር ቤቶች ተግዘዋል። የአገዛዙ ካድሬዎች ወገኖቻችንን የፈጀውን አይሲስን በመቃወም ፋንታ የራሱ የህወሓትን ውል አልባ ህግ አክብረው በመንቀሳቀስ ላይ ያሉትን ሰማያዊ ፓርቲ፣ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን እና አረና ፓርቲን እየወነጀሉ መሆኑ አጅግ አሳፋሪ ነገር ነው። የአይሲስን አረመኔአዊ ድርጊት ከኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ጋር ለማገናኘት በህወሓት የደህንነት ቢሮ አማካይነት እንቅስቃሴ መጀመሩ እየተሰማ ነው። ለወጣቱ በብዛት መሰደድ በምክንያትነት የሚያቀርቡት ደላሎችን መሆኑ አላዋቂነት ሳይሆን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ቅራኔው በኢትዮጵያዊያን መካከል እርስ በርስ እንዲሆን ያለመ መሠሪነት ነው። ከዚህም አልፎ የትግራይ ወጣቶችን ነጥሎ በመሰብሰብ “ትምክህተኞች ሊበሉህ ነውና ታጥቀህ ሳይቀድሙህ ቅደም” እያሉ መቀስቀስ በመንግሥት ደረጃ የእርስ በርስ እልቂትን ከማደራጀት ተለይቶ አይታይም። የሥርዓቱ ይሉኝታ ቢስነት የደረሰበት ዝቅጠት ገላጭ ከሆኑ ነገሮች አንዱ “እስከምርጫ መጨረሻ ድረስ ልጆቻችሁን አስረን እናቆይላችሁ” እያሉ ወላጆችን እስከመጠየቅ መድፈራቸው ነው። ከላይ በአጭሩ የተዘረዘሩት ኩነቶች የሚያረጋግጡት ህወሓት የተማከለ አመራር አጥተው መንገድ የጠፋቸው፤ ሆኖም ግን እጃቸው ውስጥ የገባው ስልጣንና ሀብት ላለማጣት ምንም ነገር ከማድረግ የማይመለሱ አውሬዎች ስብስብ መሆኑ ነው። እንዲህ ዓይነቱን የአውሬዎች ስብስብ የሚገዛው የህግም ሆነ የሥነ-ምግባር ገደብ የለም። ህወሓት እስር በርሳችንን አባልቶ አገራችንንና ሕዝቧን ወደ ማንወጣው አዘቅት ከመክተቱ በፊት ራሱ ህወሓትን ማስወገድ እና በምትኩት ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን መገንባት የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው። ይህ ካላደረግን አሁን በወህኒ ቤቶች የሚደረገው ዜጎችን ልብስን አስወልቆ የማዋረድ አስነዋሪ ተግባር ነገ በአደባባዮች የማይደረግ ስለመሆኑ ምንም ማረጋገጫ የለንም። ይህ ትውልድ ኃላፊነቱ ካልተወጣ ህግን አክብረው ከአገዛዙ የተለየ ሀሳብ እናራምዳለን የሚሉ ወገኖቻችን በሙሉ አደጋ ውስጥ ናቸው። በህወሓት መሠሪ ተግባራት ሳቢያ በክርስትናና እስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን መካከል ያለው መግባባት እንዲሻክር እየተደረገ ነው። ዜጎችን በማዋረድ የሚደሰት አገዛዝና ለመዋረድ የፈቀደ ሕዝብ እስካለ ድረስ የቁልቁለቱ ጉዞ መጨረሻ የለውም። ይህንን ማስቆም ያለብን እኛ ሁላንችንም ነን። በአደባባይ መደራጀት ሲከለከል በምስጢር መደራጀትን መልመድ የኛ ኃላፊነት ነው። የኢትዮጵያ አርበኞች ድል መታሰቢያ በዓልን ስናከብር ከቀደምቶቻችን ልንወርስ ከሚገቡን እሴቶች አንዱ ለክብራችን ዋጋ መክፈል ያለብን መሆኑን ጭምር ነው። የኢትዮጵያዊያን ክብር በወያኔ ሲዋረድ እያየን ዝምታን ከመረጥን ከዚህም የባሰ እንዲመጣ መፍቀዳችንን እንወቀው። አርበኞች ግንቦት 7:የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የዜጎችና የአገር ውርደት ይብቃ! በተባበረ ክንድ ህወሓት ይወገድ፤ በምትኩም ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመመሥረት መሠረት እንጣል፤ ይህንን ታላቅ ኃላፊነት ለመወጣት በኅብረት እንነሳ ይላል። ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ! Source www.patriotg7.org

Monday, 6 April 2015

ወቅቱ የተግባራዊ ትግል ነው!

ለገዛ ራሱ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና ለኢትዮጵያ ቅን የሚመኝ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ህወሓትን ለማስወገድ ተግባራዊ ትግል ውስጥ መሳተፍ የሚኖርበት ወቅት ላይ እንገኛለን። በዚህ ወሳኝ ወቅት ከዳር ሆኖ መታዘብ ዘረኛውን፣ አምባገነኑን፣ ፋሽስቱን ህወሓት እንደመደገፍ ይቆጠራል። ዛሬ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ህሊናውና አቅሙ በሚፈቅድለት የትግል ዘርፍ የመሰማራት ሰፊ እድል ተፈጥሮለታል። በዚህም መሠረት የህወሓትን አፈና በጠነከረ ክንድ ለመመከት የቆረጡ ኢትዮጵያዊያን ወደ በረሃዎችና ተራራዎች አቅንተዋል። ብዙዎች በመንገዱ ላይ ያሉ ጋሬጣዎችን ተቋቁመው እየተቀላቀሏቸው ነው። በደል የመረራቸው ሌሎች በርካታ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በቡድን ለነፃነታቸው ዘብ ቆመው በህወሓትና አገልጋዮቹ ላይ እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል። ይህ የሚበረታታ እና ተቀናጅቶ ሊጠናከር የሚገባው ጉዳይ ነው። አሁን ያለንበት ጊዜ ልዩ የትግል ወቅት ነው። ትናንት በከተሞች ይካሄድ የነበረው ፀረ ወያኔ ትግል ዓይነተኛ መታወቂያው ሕዝባዊ ተቃውሞ ነበር። ዛሬ ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሯል። በተለይ በአገዛዙ ፈቃድ የሚደረጉ ተቃውሞዎች ፋይዳ ቢስ ሆነዋል። በአገዛዙ ፈቃድ በሚደረጉ ተቃውሞዎች ለውጥ እንደማይመጣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በማያሻማ ሁኔታ ተረድቷል። ስለሆነም ትግሉ ወደ ሕዝባዊ እምቢተኝነት አድጓል። ዛሬ ከዚህ በፊት ያልተሞከሩ የትግል ስልቶች ተግባራዊ እየሆኑ ነው። በዚህ ረገድ የሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የተቀናጁ ርምጃዎች በአርዓያነት የሚጠቀሱና የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ የሚሹ ናቸው። እነዚህ የሕዝባዊ እምቢተኝነት ተግባራት የእምነት አጥር ሳይለያየን ፍትህ የተጠማን ዜጎች ሁሉ ልንተገብራቸው የሚገቡ ናቸው። ለምሳሌ፣ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን በተወሰኑ ቀናት መዝጋት በተቀናጀ ሁኔታ ከተደረገ ከፍተኛ ውጤት ሊያመጣ የሚችል፤ በሙስሊም ወገኖቻችን ግንባር ቀደም መሪነትና አስተባባሪነት ተሞክሮ በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል መሆኑ የታየ አንድ የትግል ስልት ነው። በአሁኑ ወቅት ተግባራዊ በመደረግ ላይ ያለው ሣንቲሞችን የመሰብሰብ ዘመቻም ሌላ ከዚህ በፊት ያልተሞከረ፤ በተጨማሪ እርምጃዎች ከታገዘ ህወሓት መራሹ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን ገንዘብ መቆጣጠር የማይችልበት ደረጃ ላይ ሊያደርስ የሚችል ጉልበት ያለው ስልት ነው። ውሳኔው ሣንቲሞችን ብቻ ሳይሆን የወረቀት ኖቶችንም ሲያካትት በዝውውር ላይ የሚኖረውን ገንዘብ ብዛት የሚቆጣጠረው ህወሓት ሳይሆን በደል ያንገሸገሸው ሕዝብ ይሆናል። በባንኮች ያለ ተቀማጭ ገንዘብ በማውጣትም የህወሓት የፋይናንስ ተቋማትን ማሽመድመድ ሌላ ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል ስልት ነው። በእነዚህ እርምጃዎች የተለማመደ ሕዝብም ወደ ግዢ እቀባ፤ ለተወሰኑ ቀናት ከቤት አለመውጣት ብሎም “ግብር አልከፍልም” ወደማለት ሊሸጋገር ይችላል። እንዲህ ዓይነቱ ስልቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ግን የመላው ሕዝብ ተሳትፎ እና የተቀናጀ አሠራርን ይፈልጋል። ለምሳሌ፣ ሰብስቡ ሲባል መሰብሰብን፤ በትኑ ሲባል መበተን ይጠይቃል። እንዲህ ዓይነት የተቀናጁ የጋራ እርምጃዎች በአምባገኑ የህወሓት አገዛዝ ላይ ከሚያደርሱት ጥቃት በተጨማሪ በኢትዮጵያዊያን መካከል ያለውን መግባባት ያጠናክራሉ። እንዲህ ዓይነት የተቀናጁ የጋራ እርምጃዎች በማኅበረሰብ ቡድኖች መካከል አዎንታዊ መስተጋብር ለመፍጠር የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ ነው። አሁን አገራችን የምትገኝበት ሁኔታ በጥሞና ሲጤን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይነጋገር መግባባት፣ እርስ በርሱ መናበብ የሚችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑ መረዳት ይቻላል። ይህ ስነልቦናዊ ዝግጅት ደረጃ በደረጃ ጠንከር ያሉ እርምጃዎችን ለመውሰድ ያዘጋጀናል። በማናቸውም የጋራ እርምጃዎች ለግል ጥቅሞቻቸው ቅድሚያ የሚሰጡ፤ ራሳቸው “ብልጥ” አድርገው በማየት በተፈጠረው ሁኔታ መጠቀም የሚፈልጉ፤ በሌላው ድካም ለማትረፍ የሚሯሯጡ ሰዎች መኖራቸው የማይቀር ነው። ህወሓት ለሃያ አራት ዓመታት ኮትኩቶ ያሳደገው የአድርባይነት ባህልም ሌላው እንቅፋት ሊሆን እንደሚችል መገመት ቀላል ነው። ድህነት ደግሞ በገዢዎች ላይ ጨክነን የመነሳት አቅማችንን እንደሚያዳክም የታወቀ ነው። ሆኖም ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፊቱ የቀረበለት ምርጫ “ባርነት ወይስ ነፃነት” መሆኑን የተገነዘበበት ጊዜ ላይ ደርሰናል። በዚህም ምክንያት ለህወሓት ባርነት ከመገዛት ነፃነትን የሚመርጥ ዜጋ ሁሉ ዋጋ ለመክፈል መዘጋጀት ይኖርበታል። ለሁላችንም የሚሆን የትግል ዘርፍ መኖሩ የሕዝቡን ተሳትፎ ከፍ ያደርገዋል። የሁለገብ ትግል ስትራቴጂ ጥቅሙም እዚህ ላይ ነው። ማንም የማንም ነፃ አውጭ አይደለም። ሁላችንም ተባብረን ሁላችንንም ነፃ እናወጣለን። አርበኖች ግንቦት 7፡ የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ “ትግላችን ዘርፈ ብዙ ነው፤ ተግባራዊ ትግል የሚደረገውን በሁሉም ቦታዎች ነው፤ እርጃዎቻችን እናቀናጅ፤ ወቅቱ የተግባራዊ ትግል ነው” ይላል። ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!