Tuesday, 10 December 2013
2007 የምርጫ ቁማር ይብቃ!!
***ምርጫ***
2007 የምርጫ ቁማር ይብቃ!!
የህውሃት ልሳን የሆነው ሬዲዮ ፋና የወሬ ዱለታ ይብቃ ለማለት ነው ይህችን ጹሁፍ ጫር ያደረኩት
ጠቅላይ ተብዬው ሀይለማሪያም እርሳቸውም እንደ ማህረቤን ያያችሁ ጨዋታ ዙሪያውን ተሽከርክረው ተሽከርክረው “እኛ ምስል ባናሳይም ድምፅ ባናሰማም ህዝባችን ያምነናል ውጪ ሀገር ያለው ህዝብ ነው የማያምነው እርሱ ደግሞ የራሱ ጉዳይ” ብለዋል።
እውነትም ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው።
ለምሳሌ በ97 ቱ ምርጫ የምርጫውን ውጤት ተቀብሎ “ላጥ” ይላል ብለን አምነን ነበር። ግን አልታመነም በጥይት አሳመመን እንጂ… አሁንም ለምሳሌ በ2002 ቱ ምርጫ ፍትሀዊ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ያደርጋል ብለን አምነነው ነበር ነገር ግን በተቃራኒው ሆነ ታመምንም። አሁንም ለምሳሌ የዛሬ ሃያ አመት ከአስር አመት በኋላ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በቀን ሶስቴ ይበላል ተብለን አምነነን ነበር። ነገር ግን ከሃያ አመት በኋላ እንኳን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በርሃብ እንደተጠቁ ከራሱ የመንግስት ሚዲያ ሰምተን ታመናል።
ደግሞ ካሁኑ ዱለታው 2007 ምርጫ
አዎን አውቃለሁ፣ የምን ምርጫ ነው ትሉ ይሆናል፡ ይህም የኔም ጥያቄ ነው የእናንተ ብቻ ሳይሆን። የህውሃት/ወያኔ አገዛዝ እስካለ ድረስ በኢትዮጵያ ዳግም ትክክለኛ የሆነ ምርጫ ሊደረግ እንደማይችልና እንደማይኖር ብዙዎች የተነበዩት ነው። የሕዝብን ድምፅ አክብሮ በተሸናፊነት አምኖ ወያኔ ሥልጣኑን የመልቀቁ ጉዳይ ያከተመለት ይመስላል። ይህም ቀድሞ የተደረጉትን ወከባዎች፣ ግለሰቦችን ማስፈራራትን እና መድብደብን፣ ያልሆነ ምክንያት በመደርደር መወንጀልና በእስር ማንገላታቱን ሳንጨምር፣ ሰሞኑን የተቃዋሚ ፓርቲ በሚካሄደው ሴራና ድብደባ እስሩ የወያኔ ካድሬዎችና ጀሌዎቻቸው የፈጸሙት አሳፋሪ ተግባር ሐገራችን በምን አይነት ራሳቸውን መንግሥት ነን በሚሉ ተራ ግለሰቦች እየተመራች መሆኑን ነው የሚያሳየን። በእርግጥ የሰውን ሕይወት ለማጥፋት በጭራሽ ወደ ሗላ የማይል የወያኔ አስተዳደር ይህንን ተግባር ለመፈጸም ቢነሳሳ የሚያስገርም አይሆንም።
ወያኔ በ1997ቱ ምርጫ ባላወቀውና ባልተገነዘበው ሁኔታ በዋነኛነት ደግሞ ለምእራባውያን ጌቶቹ ታማኝነቱን ለማሳየት ሲል ብቻ በኢትዮጵያ ዲሞክራሲ አለ ተብሎ እንዲነገርለትና በሌላም በኩል ሕዝብን ሊያስተባበር የሚችል ጠንካራ ተቃዋሚ ስለሌለ ድሉ የኔ ነው በሚል የተሳሳተ ስሌት ተነሳስቶ ጥሩ ምርጫ እንዲደረግ እድሉን ከፍቶ ነበር። ይህም በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ መሆኑ ማንም የሚክደው አይደለም። በሰጠው እድል ተቃዋሚዎችም በሚገባ ተጠቅመውበት በምርጫውለት ድሉ ወደ ተቃዋሚዎች በመዞሩ ምን ያህል መደናገጡን፣ ተደናግጦም የፈጸመውን አስጸያፊ ድርጊት አለም በሙሉ ያየው እና የተረዳው ነው፡ ለዚህም የመርማሪ ኮሚሽኑ ሪፖርት በአቢይነት ሊጠቀስ የሚችል ምስክር ነው።
እንግዲህ ከዚህ በሗላ ነው ድጋሚ ስህተትን ላለመፍጠርና ያ በዲሞክራሲ ተሸፍኖ የነበረው የወያኔ የአውሬ መልኩ አንዴ መጋለጡ ከታወቀ ወያኔ ስልጣኑን በምንም አይነት መንገድ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንደማይለቅ ማሳወቅ የጀመረው። ይኸውም ከምርጫ 97 ጀምሮ ተቃዋሚዎችን ከማሰር፣ ማስፈራራትና ሕዝብን ወጥተው እንዳያስተባብሩ፣ ጽሕፈት ቤቶችን የመክፈት ሥራቸውን አድካሚና አሰልቺ በማድረግ፣ የተከፈቱትንም ጽሕፈት ቤቶች የተለያዩ ምክንያቶችን በመፈብረክ እንዲዘጉ የማድረግ ተግባራትን በመፈጸም ፣ሰብአዊ መብትን የሚገፍ አዳዲስ ሕጎችን በማውጣት፣ የሕዝብን የቁጣ ትኩሳት በመጨመር ላይ ይገኛል።
ከምርጫ 97 በሗላ በሰላማዊ መንገድ ታግሎና በምርጫ አሸንፎ ወያኔን ከሥልጣን የማስወገዱ መንገድ ሙሉ በሙሉ መዘጋቱን በማመን ተስፋው የተሟጠጠ መሆኑን ቀድመው የተረዱ የቀድሞ ተቃዋሚዎች ገሚሶቹ ሰላማዊ ትግል አያዋጣም በማለት በሌሎች በሚያዋጡን መንገዶች ሁሉ እንታገላለን በማለት ትግል ስልታቸውን ቀይረው የተነሱ አሉ። ገሚሶቹ ደግሞ በፍርሃትም ይሁን ለሆዳቸው በማደር ተለጣፊ ፓርቲዎቻቸውን ከወያኔ አሰጠግተው በስመ ተቃዋሚ ሕዝብን ክደውና ንቀው ለወያኔ ፍርፋሪ በማደር በሐገሪቱ ዲሞክራሲ አለ እንዲባል በማስመሰል ፓርላማ ውስጥ ተሰግስገው ሊቀመጡ እራሳቸውን ከአውሬው አስተካክለዋል።
ከዚሁ ከምርጫ 97 በሗላም በሺሕና በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች በተለያዩ የሐገሪቱ ክፍል እስር ቤቶች ታምቀው ይገኛሉ። ከነዚህም ውስጥ የአንድነትን ፓርቲ ለማዳከምና የሚያደርገውን ሰላማዊ ትግል ለመግታት ታስቦበትና ተጠንቶበት የተደረገው የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ወደ ቃሊቲ መወርወር በእውነት የፖለቲካ ምሕዳሩ ምን ያህል እንደጠበበ እና ሰላማዊው ትግል እንደሞተ የሚያሳይ ጥሩ ምስክር ሊሆን የሚችል ሲሆን፣ ከአሁን በሗላም በቀረችው ግዜ ተቀይረው ወያኔ ለሰላም እና ለዲሞክራሲ ተገዝቶ እንከንየለሽ የሆነ ምርጫ ይደረጋል ማለት የማይታለም ነው።
ህውሃት/ወያኔ አሁንም ስለምርጫው በሰፊው በማውራት ላይ ይገኛል፡ ሕዝብን በእህልና በምግብ አቅርቦት፡ በሥራ እድልና በመሳሰሉት እንደ ቀብድ በማስያዝ፡ በፓርቲው ስር ካልታቀፉ በሐገሪቱ ውስጥ ሊያገኟቸውና ሊጠቀሙባቸው የሚገባቸውን ሰብዓዊ መብቶች በመግፈፍ በውዴታ ሳይሆን በግዴታ የፓርቲውን የአባልነት ፎርም በማስሞላት ላይ ይገኛል። በቀደመው ምርጫ ድምጻቸውን ለተቃዋሚዎች የሰጡትን ግለሰቦች ከስራቸው እንዲባረሩ ወይም ሐገር ለቀው እንዲወጡ ለመጪውም ምርጫ እንቅፋት የማይሆኑበትን መንገድ በመቀየስ አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል፡ ለማንኛውም ባለፈው የክልል ምርጫዎች እንደተደረገው አሁንም ምርጫው የሚካሄደው ወያኔ ከራሱ ከወያኔ ጋር ይሆናል እንጂ በዚህ ሁካታና የመብት መጣስ በሰፊው በተንሰራፋበት ሁኔታ ጠንካራ ተቃዋሚ ገብቶ ሥነሥርዓት ባለው ሁኔታ ምርጫ ይካሄዳል ማለት ፈጽሞ የማይታሰብ ነው። ለዚህም ነው 2002 ምርጫ ሲሉን የምን ምርጫ የሚለው ጥያቄ ሲያስተጋባ የምንሰማው። እውነት ግን የምን ምርጫ ከአሁን በኋላ?
ከሰብኣዊ
Monday, 9 December 2013
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ ሰራዊት በጋራ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀሙ ..
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ ሰራዊት በጋራ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀሙ .................
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ ሰራዊት በጋራ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀሙ
የጋራ ትግል አስፈላጊ መሆኑን በፅኑ የሚያምኑት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር /ኢሕአግ/
እና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ /ጋሕነን/ በሕዳር 13/2006 ዓ.ም በሁመራ ሉግዲ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1፡00 ለሶስት ሰዓት ያህል በወሰደው ውጊያ የወያኔው 24ኛ ክፍለ ጦር ድባቅ ተመቷል።
ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በ24ኛው ክፈለ/ ጦር ላይ በተመሳሳይ ሥፍራከፍተኛ ድል መቀዳጀቱ ይታወሳል።
በሕዳር 13/2006 ዓ.ም የኢሕአግና የጋህነን ሰራዊት በወሰዱት ድንገተኛ ወታደራዊ ጥቃት 66 /ስልሳ ስድስት/ ገድለው 113 /አንድ መቶ አስራ ሶስት/ በማቁሰል እንዲሁም ቁጥራቸው የበዛ የጦር መሳሪያዎችን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ማርከዋል።
ሁለቱ ድርጅቶች በጋራ በተለያየ የትግል መስክ ሲተጋገዙና ሲተባበሩ ቆይተዋል የግንኙነታቸውን እድገትና ለውጥ የሚያሳይ ወታደራዊ ጥቃትም ፈፅመዋል።
ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመኘውና የሚፈልገው የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ስምምነትና አንድነት መገለጫ ሊሆን የሚችል አኩሪ ጥቃት መሆኑ ይታመንበታል ። በጥቃቱ የተካፈሉ የሁለቱ ድርጅቶች ታጋዮች እንዳብራሩት ዛሬ በጋራ የጀመርነው ወታደራዊ ጥቃት በዚሁ የሚያበቃ ሳይሆን የጋራ ዓላማና ራዕይ እስካለን ድረስ ወደኋላ የማይቀለበስ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ከዚህም አክለው የዚህ ወታደራዊ ዘመቻ ዓላማ አገር እንደሌለው ሁሉ በሰው አገር ፍዳውን እያየና እየተሰቃየ እንዲሁም ለሞት እየተዳረገ የሚገኙውን በሳውዲ አርቢያ ለተፈፀመው በደል ለመበቀልና ሕዝባዊ ወገንተኝነታችንን ለማሳየት ታስቦ የተወሰደ ወገናዊ እርምጃ ነው በማለት አብራርተዋል።
በውጊያው ከሞት ተርፎ ለከባድ ቁስልና የአካል ጉዳት የተዳረገው የወያኔው ቅጥረኛ የ24ኛ ክፈለ ጦር አባላትን ከሁመራ አንስቶ እስከ ትግራይ የሕክምና ማዕከሎች ማጋጋዝ ዋነኛ ተግባሩ ሆኗል።
ይህንን የጀግና ጥቃትና ድል የተመለከቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ሰራዊቱን እንኳን ደህና መጣችሁ ብሎ በመቀበልና ስንቅና ትጥቅ በማቅረብ አጋርነቱን ያስመሰከረ ሲሆን የተጀመረው ወታደራዊ ጥቃት በተለያዩ አካባቢዎች ላይ እንዲደገም ያላቸውን ልባዊ ምኞት ገልፀው በንፁሃን ላይ ያለ አግባብ ሲወሰድ የነበረው የቅጥረኞች እርምጃ አንጀቱ ላረረው ሕዝብ እምባ ያበሰ እንደሆነም ተናግረዋል።
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር/ ኢሕአግ/ እና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ /ጋህነን/ ወያኔ ለ22 ዓመት ያህል አገሪቷን ሲበዘብዝና ሕዝቡ የዲሞክራሲያዊ መብቱ ተጠቃሚ እንዳይሆን በሃይል የመግዛቱ ሂደት እንዲያከትም የተቻላቸውን ሁሉ ለማድረግ ቆርጠው መነሳታቸውን አስታውቀዋል።
የጋራ ትግል አስፈላጊ መሆኑን በፅኑ የሚያምኑት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር /ኢሕአግ/
እና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ /ጋሕነን/ በሕዳር 13/2006 ዓ.ም በሁመራ ሉግዲ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1፡00 ለሶስት ሰዓት ያህል በወሰደው ውጊያ የወያኔው 24ኛ ክፍለ ጦር ድባቅ ተመቷል።
ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በ24ኛው ክፈለ/ ጦር ላይ በተመሳሳይ ሥፍራከፍተኛ ድል መቀዳጀቱ ይታወሳል።
በሕዳር 13/2006 ዓ.ም የኢሕአግና የጋህነን ሰራዊት በወሰዱት ድንገተኛ ወታደራዊ ጥቃት 66 /ስልሳ ስድስት/ ገድለው 113 /አንድ መቶ አስራ ሶስት/ በማቁሰል እንዲሁም ቁጥራቸው የበዛ የጦር መሳሪያዎችን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ማርከዋል።
ሁለቱ ድርጅቶች በጋራ በተለያየ የትግል መስክ ሲተጋገዙና ሲተባበሩ ቆይተዋል የግንኙነታቸውን እድገትና ለውጥ የሚያሳይ ወታደራዊ ጥቃትም ፈፅመዋል።
ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመኘውና የሚፈልገው የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ስምምነትና አንድነት መገለጫ ሊሆን የሚችል አኩሪ ጥቃት መሆኑ ይታመንበታል ። በጥቃቱ የተካፈሉ የሁለቱ ድርጅቶች ታጋዮች እንዳብራሩት ዛሬ በጋራ የጀመርነው ወታደራዊ ጥቃት በዚሁ የሚያበቃ ሳይሆን የጋራ ዓላማና ራዕይ እስካለን ድረስ ወደኋላ የማይቀለበስ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ከዚህም አክለው የዚህ ወታደራዊ ዘመቻ ዓላማ አገር እንደሌለው ሁሉ በሰው አገር ፍዳውን እያየና እየተሰቃየ እንዲሁም ለሞት እየተዳረገ የሚገኙውን በሳውዲ አርቢያ ለተፈፀመው በደል ለመበቀልና ሕዝባዊ ወገንተኝነታችንን ለማሳየት ታስቦ የተወሰደ ወገናዊ እርምጃ ነው በማለት አብራርተዋል።
በውጊያው ከሞት ተርፎ ለከባድ ቁስልና የአካል ጉዳት የተዳረገው የወያኔው ቅጥረኛ የ24ኛ ክፈለ ጦር አባላትን ከሁመራ አንስቶ እስከ ትግራይ የሕክምና ማዕከሎች ማጋጋዝ ዋነኛ ተግባሩ ሆኗል።
ይህንን የጀግና ጥቃትና ድል የተመለከቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ሰራዊቱን እንኳን ደህና መጣችሁ ብሎ በመቀበልና ስንቅና ትጥቅ በማቅረብ አጋርነቱን ያስመሰከረ ሲሆን የተጀመረው ወታደራዊ ጥቃት በተለያዩ አካባቢዎች ላይ እንዲደገም ያላቸውን ልባዊ ምኞት ገልፀው በንፁሃን ላይ ያለ አግባብ ሲወሰድ የነበረው የቅጥረኞች እርምጃ አንጀቱ ላረረው ሕዝብ እምባ ያበሰ እንደሆነም ተናግረዋል።
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር/ ኢሕአግ/ እና የጋምቤላ ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ /ጋህነን/ ወያኔ ለ22 ዓመት ያህል አገሪቷን ሲበዘብዝና ሕዝቡ የዲሞክራሲያዊ መብቱ ተጠቃሚ እንዳይሆን በሃይል የመግዛቱ ሂደት እንዲያከትም የተቻላቸውን ሁሉ ለማድረግ ቆርጠው መነሳታቸውን አስታውቀዋል።
Sunday, 8 December 2013
በወያኔ ስርዓት ውስጥ በሙስና ያልተጨማለቀ ሰው ቢኖር እኔ ነኝ ዓሉ ወ/ሮ አዜብ
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኛ የነበሩት አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ከሁለት ቤተሰቦቻቸው ጋር በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ተጨማሪ ክስ ተመሰረተባቸው። “የአቶ ወልደስላሴ እህት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን ፥ ምንም አይነት የገቢ ምንጭ የሌላት እንደሆነች ነው በክስ መዝገቡ የተገለጸው…ግለሰቧ በ 81 ሺ ዩሮ የተገዛ አንድ ስካቫተር ፣ አውቶሞቢል መኪና፣ በአዲስ አበባ ቦሌና የካ ክፍለ ከተሞች እንዲሁም በለገጣፎ ፣ በመቀሌና አክሱም ከተሞች 3 ሺህ 266 ካሬ ሜትር ቦታዎች በስሟ ተመዝግቧል ፤ በተለያዩ ባንኮችም ከ 8 ሚሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብም እንዲሁ ተመዝግቧል።
…….” ተከሳሾቹ አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል፣ የመከላከያ ሚኒስቴር ባልደረባ የነበሩት ወንድማቸው ዘርአይ ወልደሚካኤል፣ እህታቸው ወይዘሪት ትርሃስ ወልደሚካኤልና የቅርብ ጓደኛቸው ዶሪ ከበደ ናቸው ።ተከሳሹ በ 2002 ዓ.ም ቱሪዝም ኢን ኢትዮዽያ ኤንድ ዘ ሆርን ኦፍ አፍሪካ የተሰኘ መጽሃፍ ያሳተሙ ሲሆን ፥ ይህንን መጽሃፋቸውን በስፖንሰር ለማሳተም ባደረጉት እንቅስቃሴም የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ በየነ ገብረስላሴ የነበራቸውን ቀና አስተሳሰብ ተጠቅመው ያለአግባብ በልጽገዋል ነው የሚለው የክስ መዝገቡ። መጽሃፉ በመስሪያቤታቸው ስም እንደተዘጋጀ በሚያስመስል ሁኔታ አቶ በየነ የሚመሯቸው የቦሌ፣ የብርሃንና ሰላምና የአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት ሃላፊዎች በጋራ የአቶ ወልደስላሴን 3 ሺህ መጻህፍት በ124 ሺህ ብር እንዲያሳትሙ ተደርጓል ነው የሚለው ክሱ።
ማተሚያ ቤቶቹ በርካሽ ያሳተሙት አቶ ወልደስላሴ ከነበራቸው ተሰሚነትና ስልጣን መነሻነት መሆኑንና ይህንን መጽሃፍ ኢትዮ ቴሌኮም ምንም በማይመለከተው 10 ሺህ መጻህፍት የሚታተሙበትን የ385 ሺህ ብር ክፍያ ለአቶ ወልደስላሴ እንዲከፍልም መደረጉንም ነው የክስ መዝገቡ የሚያስረዳው። አቶ ወልደስላሴ የሙገር ሲሚንቶ ኢንተርፕራይዝና የአትክልትና ፍራፍሬ ገበያ ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ በነበሩበት ጊዜ ሃላፊነታቸውነ ተጠቅመው ፥ ሁለቱ ድርጅቶች 310 ኮፒዎችን በግድ እንዲገዙ መደረጉም ተመልክቷል። 26 የሚሆኑ ግለሰቦችና ድርጅቶችም እያንዳንዳቸው ከ 25 እስከ 1ሺህ 500 ፥ በጥቅሉ ከ73 ሺህ የሚልቁ ኪፒዎችን ሳይወዱ በግድ እንዲገዙ መደረጉ ፣ ይሄ ሁሉ ሲደረግ ተቋማቱ ለመጻህፍቱ ገንዘብ ከፍለው መጻህፍቱን አለመረከባቸውም ጭምር ነው በክስ መዝገቡ የተዘረዘረው። ተከሳሹ አቶ ወልደስላሴ ባልደረባቸወ የሆኑ አንዲት ሴት ጋር በነበራቸው መቀራረብ የመስሪያቤቱን መኪና በህገ ወጥ መንገድ ነዳጅ እያስሞሉ ግለሰቧ እንደልባቸው በአዲስ አበበባና ከከተማ ውጪ እንዲጠቀሙበት አስደርገዋል የሚለውም ተጠቅሶባቸዋል።
ተከሳሹ ከ2003 እስከ 2004 ዓ.ም አቶ ሳቢር አርጋው የተሰኙ ነጋዴን ለምሰራው ቤት ሴራሚክ ስለጎደለኝ የጣሊያን ስሪት ገዝተህ ስጠኝ በማለት ፥ በስልጣናቸው አስፈራርተዋቸው የ65 ሺህ ብር ሴራሚክ ተቀብለዋል ፣ ከ 2001 እስከ 2005 ባሉት የግብር አመታት አሳትሞ ከሸጣቸው መጻህፍት ካገኘው ገቢ ላይ መክፈል የነበረበትን ከ496 ሺህ ብር በላይ ለመንግስት አስታውቆ አለመክፈሉም ተጠቅሷል። ተከሳሹ ባለ4 ፎቅ የግል ቤቱን ወንድሙ ለሆነው ሁለተኛ ተከሳሽ ዘርአይ ወልደስላሴ ውክልና ሰጥቶና ከመኖሪያ ቤት ውጭ ለሆነ አገልግሎት እንዲውል አድርጎ በ14 ወራት ውስጥ 790 ሺህ ብር ገቢ አግኝቷል ፤ ከገቢው 126 ሺህ ብር የሚሆነው የመንግስት ግብርን ለግብር አስገቢው መስሪያቤት ሃሰተኛ መግለጫ በማቅረብ ሳይከፍል መቅረቱም በክሱ ተመልክቷል። ከዚሁ ቤት ኪራይ መንግስት ከተርን ኦቨር ታክስ ማግኘት የነበረበትን ከ119 ሺህ ብር በላይ ገቢ ሳያገኝ መቅረቱና ተከሳሹ በህገ ወጥ መነገድ ያገኘውን ገንዘብ ማንም እንዳያውቅበት ለማድረግ በሰኔ 28 1998 ዓ.ም ለሁለተኛው ተከሳሽ (ወንድም) ዘርአይ ወልደሚካኤል ሙሉ ውክልና መስጠቱ ተዘርዝሯል።
እንዲሁም ምንም አይነት የገንዘብ ልውውጥ ሳያደርጉ ከ3ኛዋ ተከሳሽ እህቱ ትርሃስ ጋር መጋቢት 24፣ 2005 ዓ.ም የብድር ውል ማድረጋቸውም ተጠቅሷል።በተጨማሪም ተከሳሹ ከእህቱና ወንድሙ ጋር ያለአግባብ አፈሯቸው የተባሉ የገንዘብና የአይነት ሃብቶች በክስ መዝገቡ ተጠቅሰዋል። 1ኛው ተከሳሽ ወልደስላሴ ወደሚካአል ከ1983 እስከ የካቲት 2005 ዓ.ም የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የውስጥ ሰራተኛ ሆኖ ሲሰራ ፥ ወርሀዊ ደመወዙ ከ 1,600 እስከ 6,000 ብር የነበር ሲሆን ፥ ነገር ግን ስልጣኑን እና የነበረውን ተሰሚነት በመጠቀም በፈጸመው የሙስና ወንጀል ከባለ4 ደረጃ ህንጻ ውጪ ፣ ከ3 ሚሊየን ብር በላይ በተለያዩ የግልና የመንግስት ባንኮች ተቀማጭ ማድረጉም ተመልክቷል። 2ኛ ተከሳሽ አቶ ዘርአይ ወልደስላሴ ከመከላከያ ሚኒስቴር በጡረታ እስከሚገለል ድረስ ወርሀዊ ደመወዙ 532 ብር የነበር ሲሆን ፥ በክስ መዝገቡ ተከሳሹ በተለያዩ ባንኮች 5 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ማስቀመጡ ፣ በአዲስ አበባ ቤቴል ቁጥር 3 በተባለ አካባቢ በ74 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ መሰረት የተጀመረበት ቦታ ፣ በአፋር ክልል ከ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ሁለት የእርሻ ኢንቨስትመንቶችና 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው ሁለት ሎደር ማሽነሪዎችም በስሙ መኖራቸው ተመዝግቧል ።
3ኛዋ ተከሳሽ የአቶ ወልደስላሴ እህት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን ፥ ምንም አይነት የገቢ ምንጭ የሌላት እንደሆነች ነው በክስ መዝገቡ የተገለጸው።ግለሰቧ በ 81 ሺ ዩሮ የተገዛ አንድ ስካቫተር ፣ አውቶሞቢል መኪና፣ በአዲስ አበባ ቦሌና የካ ክፍለ ከተሞች እንዲሁም በለገጣፎ ፣ በመቀሌና አክሱም ከተሞች 3 ሺህ 266 ካሬ ሜትር ቦታዎች በስሟ ተመዝግቧል ፤ በተለያዩ ባንኮችም ከ 8 ሚሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብም እንዲሁ ተመዝግቧል።
Saturday, 7 December 2013
ወያኔን በማስወገድ ፍትሀዊ አመራር ማስፈን : ግንቦት 7
አሁንም በሳውዲ አረቢያ እና አካባቢው አገሮች የሚገኙ ወገኖቻችን የድረሱን ጥሪዎች እያሰሙ ነው። የወገኖቻችን ዋይታና ሰቆቃ አልበረደም። ዛሬም እህቶቻን እየተደፈሩ፣ እየተዋረዱ፣ እየተገደሉ ናቸው። በጥጋብ አገር ውስጥ ሆነው ኢትዮጵያዊያን ሕፃናት በረሀብና በጥም እየሞቱ ነው። በርካታ ኢትዮጵያዊያን ለከፋ የአዕምሮ ህመም እየተዳረጉ ነው።
በተለያዩ የዓለም አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ ወገኖቻቸውን ሕመም እየታመሙ፤ ስቃያቸውን እየተሰቃዩ ይገኛሉ። አስቸኳይ እርዳታ ለማድረስም አቅማቸው የቻለውን ሁሉ ለማድረግ በመረባረብ ላይ ናቸው።
ባለፉት ጥቂት ሣምንታት ኢትዮጵያዊያን ባደረጓቸው ብርቱ ጥረቶች ጥቂት አበረታች ውጤቶች ተገኝተዋል። ከደረሰባቸው የመብት ረገጣ ጋር ፈጽሞ ተመጣጣኝ ባይሆንም ቢቢሲን ጨምሮ አንዳንድ የዓለም ዓቀፍ የዜና አውታሮች በወገኖቻችን ላይ ስለሚደርሰው በደል እንዲዘግቡ ማድረግ ተችሏል። እስካሁን ምን ያህል ወገኖቻችን እድሉን እንዳገኙ ማረጋገጥ ባይቻልም የሳውዲ መንግሥት ሙሉ የትራንስፓርት ወጪ ችሎ ወገኖቻችን ማጓጓዝ ጀምሯል። ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅቶች ለኢትዮጵያዊያን መብት መከራከር ጀምረዋል።
በአንፃሩ ግን አሁንም ሕሊናን የሚረብሹ ነገሮች እየተሰሙ ነው።
ከሳውዲ እየታፈሱ የመን ድንበር ላይ የተጣሉ፤ የደረሱበት የማይታወቁ ኢትዮጵያን ቁጥር በየእለቱ እየጨመረ ነው። እነዚህ ወገኖቻችን በየመን በረሀ ላይ የሚደርስባቸው ሰቆቃ ሳውዲ ውስጥ ከነበረው የባሰ ነው።
አሁንም በሳውዲ ተደብቀው የሚገኙ፤ “እጃቸውን ለመንግሥት ሰጥተው” እንደ ወንጀለኛ በእስር ቤቶች የሚማቅቁ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን አሉ። እነዚህ ወገኖቻችን ያሉበት ሁኔታ ሕሊና ሊሸከመው ከሚችል በላይ ነው።
ከዚህ ሁሉ በላይ ኢትዮጵያዊያንን እየረበሸ ያለው የወያኔ ባህርይ ነው።
ወያኔ በእንዲህ ዓይነት የመከራ ወቅትም በወገኖቻችን ላይ ዘርፈ ብዙ ንግድ እያጧጧፈ ነው። በሳውዲ አረቢያ መንግሥት ወጪ የተመለሰሉትን ወገኖቻችን ለምርጫ ቅሰቀሳ ፕሮፖጋንዳ ሥራ እየተጠቀሙባቸው መሆኑ ሳያንስ ለእለት ጉርስ የሚሰጣቸው የእርዳታ ገንዘብ በወያኔ እየተዘረፉ ነው። ገንዘብ ባለበት ሁሉ ወያኔ አለ። ወያኔ ለተመላሽ ስደተኞች የእለት ጉርስ የተሰጠውንም እርዳታ እየቀማ የሚበላ እኩይ ኃይል ነው።
ድሆች ኢትዮጵያዊያን ወደ አረብ አገራት ሲሰደዱ ለወያኔ ድርጅቶች ገንዘብ ከፍለው ነው። እዚያ በነበሩበት ጊዜም ለወያኔ ገንዘብ እንዲከፍሉ ይደረግ ነበር። በግፍ ተፈናቅለው፤ ሀብታቸው ተዘርፎ ባዶ እጃቸውን ሲመለሱም ለወያኔ የእርዳታ ገንዘብ መለመኛ ሆነዋል። ወያኔ በድሆች ኢትዮጵያዊያን ድህነት የሚከብር በታሪካችን ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ስግብግብ ነው። ወያኔ ኢትዮጵያዊያን ፈጽሞ ሊጠየፉት የሚገባ ነው ስብስብ ነው።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በችግር ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን ከመርዳት ጎን ዓይኖቻችንን ከወያኔ እንዳንነቅል በአጽንዖት ያሳስባል። ወያኔ ከሥልጣን ሳይወገድ ችግሮቻችንን መፍታት አንችልም። የኢትዮጵያዊያን ችግሮች ለወያኔ የገቢ ምንጮች ናቸና ወያኔ እስካለ ድረስ ችግሮችን መፍጠሩና ማስፋፋቱ አይቀርም።
የኛ የኢትዮጵያዊያን ችግሮች የመፍትሔ ቁልፍ ያለው ወያኔን በማስወገድ ፍትሀዊ አመራር ማስፈን ላይ በመሆኑ የጋራ ትኩረታችን እዚያ ላይ እንዲሆን ግንቦት 7 ያሳስባል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
Thursday, 5 December 2013
የካርቱም ድራማ፡ እነ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሕዝቡን ስብሰባ ጠርተው እነርሱ ቀሩ
አብርሃ በላይ ከመቀሌ
(ከካርቱም የተላከልኝ መረጃ ነው፤ እንዳለ ለጥፌዋለሁ።) ትላንት ማክሰኞ (ህዳር 24, 2006 ዓም) በኢትዮጵያ ስዓት አቖጣጠር ልክ ከ10:00ጀምሮ ለተለያዩ የማህበራት አመራሮችና እድሮች ዛሬ ሮብ ለሚደረግ ስብሰባ ሰዉ እንዲጠሩ መልዕኽት ተላለፈ። መልዕክቱ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለች የሚመሩትና ሌሎች ሚንስትሮች የሚገኙበት በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ5:00 የሚጀመር ስብሰባስላል ከየማህብራችሁ 200 ሰዉ እንድትጋብዙ የሚል በስልክ መደወል ተጀመረ። በተሰጠዉ መምሪያ መሰረት ሁሉም አመራሮች ወደ አባሎቻቸዉ መደወል ያዙ። በአካል ያገኙትም ለሌላዉ እንዲናገር ወሬው ድፍን ካርቱም እንዲዳረስ አደረጉ። የሚገርመዉ ከሃይለማሪያም ደሳለኝ ውጭ ሌሎች ሚኒስትሮች ከባለፈዉ ዓርብ ጀምሮ መግባት ጀምረዋል። እስከ ትላንትና ቀን ሁሉም በየመጡበት ፊና የተለያዩ ስራዎች ሲያከናዉኑ ቆይተዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደግሞ ትላንት ማክሰኞ ምሽት ላይ ካርቱም ገቡ። አይነጋ የለ ለሊቱ ነጋ። በካርቱም የሚገኙው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ስትገባ የመጀመሪያዉ በር ስታልፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ/ማህበረሰብ/ ሬስቶራንት አለ ከዛ አልፎ ሌላ ሁለተኛ በር ልዩ ፍተሻ የሚደረግበት አልፎ ኤምባሲዉ ትገባለህ።
ዛሬ ሮብ ይደረጋል ተብሎ የኮሚኒቲዉ ሰራተኞች ሁሉም ከጥዋቱ 2:00 ስራ ገብተዉ ግቢዉን ሲያፀዱ ዉለዉ ረፋድ ላይ በኢትዮጵያ ስዓት አቆጣጠር 6:00 ዛሬ ስራ ስለሌለ ወደ ቤታችሁ ሂዱ ተባሉ። ጊዜዉ እየገፋ ነዉ ስዓቱ እየተቃረበ ነዉ። ስብሰባዉ በማህበረሰቡ ውስጥ በሚገኙዉ መናፈሻ ይደረጋል ተብሎ ሲጠበቅ ነበር። ምክንያቱ ሁሌም የተለያዩ ፖለቲካዊ ና ሃይማኖታዊ በዓላት የሚደረጉት በዚሁ አከባቢ ነበር። ዛሬ ግን ሌላ ነገር ተደረገ። ለታዳሚዉ የሚሆኑ ወንበሮች በኤምባሲው ግቢ ዉስጥ በለችሁ ትንሽ ሚዳና ዛፎች ስር ተደረደሩ። ስዓቱ ገፋ ኤምባሲዉ ውስጥ የሚገኙ ሰራተኞ ከዉትረዉ ለየት ባለ አለባበስ ግማሾች ሱፍ በከራቫታ ግማሾቹ ደግሞ ነጭ ቲሸርት በክራቫታ ለብሰዉ ውር ውር ማለት ጀመሩ። የደህንነት ሰዎች ግቢዉን ሁሉ መመርመር ጀመሩ። የተወሰኑ የፀጥታ ሰዎች ከተመደቡ በኋላ ልክ በኢትዮጵያ ስዓት አቆጣጠር 10:30 ወደ ውስጥ መግባት ተጀመረ። ህዝቡ ቀስ ያለ መምጣት ጀመረ። ኤምባሲዉም ሆነ የኮሚኒቲ ሬስቶራንቱ በሱዳን ፖሊሶች ተከቧል። የመጀመሪያዉ በር ፍተሻ ላይ ሰዉ በማህበሩ ወይ በእድሩ እየተጠየቀ ሞቫይሉን በትልቅ ፌስታል ዉስጥ በማስቀመጥ ተፈትሾ ባዶ እጁን ወደ ግቢዉን ይገባል። ከዛም በተጨማሪ የኤምባሲዉ መግቢያ ሁለተኛ በር ጋር ድጋሜ ተፈትሾ ወደ ውስጥ ይገባል። በስተግራ ወደ ተዘጋጁት ወንበሮች ሁሉ ገብቶ ቦታ ቦታዉን መያዝ ይጀምራል። እንድህ እንዲህ እየተባለ እስከ 12:00 በኢትዮጵያ አቆጣጠር ሁሉም ገብቶ ቁጭ ይላል። ሌላዉ የሚገርመዉ ትዕይንት ደግሞ የገዛ ኢምባሲያችን ህንፃ ላይ ተራ ፖሊሶች ወጥተዉ አከባቢዉን እየቃኙ ጠበቃዉን ተያይዘዉታል። በተጨማሪም በኤምባሲዉ ዙርያ በሚገኙት ህንፃዎች የተለያዩ ፖሊሶች ተመደቡ። በተለይ ከኤምባሲዉ አጠገቢ በሚገኝ ሲንድያን ሆቴል አከባቢ ትንሽ እንግዶች በመስኮት ወጣ ገባ ሲሉ በፖሊሶች አርፈዉ እንዲቀመጡ ተነገራቸዉና ተደበቁ። ህዝቡ ተሰብስቦ ዝምታ ሰፍነዋል። መድረክ አከባቢ ለሚኒስትሮችና የተወሰኑ ዲፕሎማቶች ተብሎ 15 ቪ ኣይ ፒ ወንበሮች ተቀምጠዋል። ከነሱም አለፍ ብሎ ሶስት ጠቅላይ ሚኒስትሩና የመድረኩ መሪዎች ይቀመጡባቸዋል ተብለዉ ከነ ጠሬጲዛና ማይክሮፎን የተዘጋጁተዉ ነበሩ። ሁሉም የእንግዶችን መምጣት መጠባበቅ ጀመረ። አንዴ የኤምባሲዉ ደህንነቶች ወደዚህ ወደዚያ ይላሉ። ምንም የማያዉቁ የሱዳን ቦዲጋርዶች /አጃቢዎች/ ገብተዉ ወደዚ ወደዚያ ይላሉ። በመሃል ከተሰበሰበዉ ህዝብ 3 ኤርትራዉያን ተይዘዉ እንዲወጡ ተደረጉ። አሁን ስዓቱ ሄደ ልክ 1:30 ሆነ። እንግዶች አሁንም አልመጡም። ሁኔታዉ ያላማራቸዉ የኤምባሲዉ ዲፕሎማቶች ግራ ተጋቡ። በዚህ መሃል የአምባሳደር አባዲ ዘሞ አማካሪ የሆኑት ወ/ሮ ፍረወይኒ እና የኤምባሲዉ ፋይናንስና አስተዳደር አቶ ቀለሙ የሃይለማርያምንና የመድረክ መሪዎች ወንበር ያዙ። ወ/*ሮ ፍረወይኒ ትንሽ ማይክሮፎኑን መታመታ በማድረግ “ሚኒስትሮቹ ወደዚህ አገር የመጡት ዋና አላማ ከሱዳን መንግስት ጋር በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነትን ለማጠናከር ነበር የመጡት። ለዚህም ጉዳይ ዛሬ ጥዋት በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2:00 ወደ ገዳሪፍ /የሱዳን ሌላዉ ከተማ / ሄደዋል። የሄዱበት አላማ ደግሞ የሱዳን መንግስት ከኢትዮጵያ የ200 ኪሎዋት የኤሌትሪክ ሃይል ለመዉሰድ ለማስወረቅ ነዉ። እዛ ዉለዉ ከዛ በኋላ በሱዳን ወደ ሚሰራዉ መርሃዊ በተባለዉ ቦታ ያለዉ ትልቁ ግድብ ለመጎብኘት ሄደዋል። የዛሬዉ ፕሮግራም እነሱ በፈለጉት መስረት ከህዝቡ ጋር መገናኘት እንፈልጋለን ይህንን ስዓት ያዙልን ብለዉን ነዉ ስንጠብቃቸዉ የዋልነዉ። እስከ ቅርብ ስዓት ድረስ ስንደዉልላቸዉ ነበር። እንደሚመጡ ነግረዉን ነበር። አሁን ከትንሽ ደቂቃዎች በፊት ግን በኢትዮጵያ መንግስት ስም ህዝቡን ይህንን ያህል ስዓት ስላስቆየነዉ ይቅርታ ጠይቁልን ብለዋል። እኔም የመንግስት አካል ስለሆንኩኝ ይቅርታዉ እያስተላለፍኩ ነዉ” ሲሉ ተስብሳቢዉ የተወሰነ ማለትም 10% ሲያጨበጭብ 90% ማጉረምረምና በስሜት መናገር ጀመረ። በዚህ መሃል ፍረወይኒ ንግግርዋን በመቀጠል ይቅርታ ነገ ደሞ ወደ ፈረንሳይ ይበራሉ ስለዚህ 80 ሚሊዮን ህዝብ ሃላፊነት ተሸክመዉ እየዞሩ ነው ስለዚ ምናልባት ለመናገር የምትፈልጉት ነገር ካላችሁ አንድ ሁለት ሰዉ እድል ልስጥ ትላለች። በዚህ ግዜ የመጀመሪያ እጅ አዉጥቶ ዕድል የተሰጠዉ ሼክ ዳዉድ የአማራ ልማት ማህበር ሊቀመንበር እንዲሁም በባለፈዉ ዓመት በሱዳን የኮሚኒቲው ወክሎ ከሌላ አገራት የዲያስፖራ አካላት ጋር በመሆን የህዳሴን ግድብን ጎብኝቶ የመጣ ሰዉ ነዉ። ሼክ ዳዉድ ሲናገር ፥- እኔ በበኲሌ ይህ ይቅርታ በምንም ታአምር አልቀበለዉም ብሎ ሲናገር ህዝቡን ሁሉ አጨበጨበ ንግግሩን በመቀጠል , በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም እና ዶ/ር ቴድሮስ አድሐኖም አለመምጣታቸዉ ለማመኑ በሚያስቸግር ሁኔታ ከብዶኛል፡ ይህ ንቀት ነዉ። የሰዉ አገር 200 ሜጋ ዋት ሃይል እሰጡ እየረዱ የኛ ችግር አልታይ ብሎዋቸዉ ነዉ ወይ በጣም በጣም ያሳዝናል። መንግስታችን የሰዉ አገር ፀጥታ እያስከበረ የኛን መብት ማስከብር አለመቻሉ ጉልበት ስላጣ አይመስለኝም በጣም በጣም አዝኛለሁኝ በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፊት ለመጠየቅ ከያዝኩዋቸዉ ጥያቄዎች አንዱ በቅርቡ እምዱርማን ተብሎ በካርቱም በሚገኙዉ ሰፈር ሰሙኑን አንድ ማዚን የሚባል የሱዳን ጦር መሪ የኢትዮጵያ መንግስት ፍቃድ ሰጥቶኛል እያለ ወረቀት እያሳየ ሰዎች ከቤታቸዉ እያስወጣ ወደ እስርቤት እየወረወረ ነዉ። ይህ ለምን ይሆናል። ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ ጭብጨባ በዛ በመቀጠል መኪ ያተባለ የጉራጌ ልማት ማህበር ሊቀ መንበር ሲናገር ችግሩ የኛ ነዉ ሌላ ጊዜ ወደ ኢምባሲ አንመጣም ባለስልጣን ሲመጣ ግን እንዲህ ለምን እንመጣለን ለምን በማህበር አትደራጁም ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ ህዝቡ ማጉረምረም እና አንዳንዶችን መሳደብ ጀመሩ። ጩሆት ሆነ በዚህ ማሃል ወ/ሮ ፍረወይኒ እንዲህ ቀጠለች “ ጠላ ቤት አይደለም ኤምባሲ ነዉ እንደፈለጋችሁት አትጭሁ ስነስርዕእት ስነስርዓት እንደማመጥ። መኪ ያለዉን ትክክል ነዉ። እስቲ እንነጋገር በእዉነት እናንተ በአገራችሁ ከፍቶዋችሁ ነዉ የመጣችሁ? ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ መጥፎ ስለሆነች ነው ወይ? በማለት ህዝቡን ለማግባባት ብትሞክርም ህዝቡ ማጉረምረሙ ቀጠለ በመጨረሻም ስብሰባዉ ያለፍሬ በይቅርታ ተበተነ። የሚገርመዉ ሰዉ ሲገባ ሞቫይል በፊስታል ነበር የተሰበሰበዉ። ከስብሰባዉ ሁሉ ሲወጣ ሌላ ግርግር ሆነ። ሁሉም እስኪወጣ ድረስ 2:30 ሆነ፡ ድራማዉ በእንዲህ ተጠቃለለ:: ምንጭ ፥ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/10472
‹‹መለስ ዛሬ የለም፡፡ አዲስ ጊዜ ነው፡፡ ደስ ብሎኛል፤ ቪዛዬም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተሰጥቶኛል፡፡››...አና ጎሜዝ
‹‹መለስ ዛሬ የለም፡፡ አዲስ ጊዜ ነው፡፡ ደስ ብሎኛል፤ ቪዛዬም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተሰጥቶኛል፡፡››...
(… Meles has gone! This is a new timing. I am pleased I was granted visa without preconditions.)
ይህንን ያሉት በምርጫ በ1997 የአውሮፓ ኅብረት ምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ሆነው የመጡት ሚስስ አና ጎሜዝ ሰሞኑን ከአዲስ ስታንዳርድ መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው፡፡
የአፍሪካ መዲና አዲስ አበባ መሰንበቻውን ካስተናግደችው ጉባኤዎች መካከል የአፍሪካ ካሪቢያን፣ የፓስፊክና አውሮፓ የጋራ የፓርላማ ስብሰባ አንዱ ነበር፡፡ ጉባኤው የመንግሥት ሚዲያ ቀልብ ይሳብ እንጂ የሕዝቡን ቀልብ የሳበው ግን ሌላ ነው፡፡ ሪፖርተርን ጨምሮ የግሉን ሚዲያና የሕዝቡን ቀልብ የሳበው የሚስስ አና ጎሜዝ ወደ አዲስ አበባ መምጣት ነው፡፡
ከዘጠኝ ዓመት በፊት ከመንግሥት ጋር የተወዛገቡት የአና ጎሜዝ መምጣት የበለጠ አስገራሚ ያደረገው እሳቸው በዚሁ ጉባኤ በአዲስ አበባ መገኘታቸው ብቻ አይመስልም፡፡ እሳቸው በአባልነታቸው የሚታወቁበት አውሮፓ ኅብረት ፓርላማ ለኢትዮጵያ 5.5 ቢሊዮን ብር በዕርዳታ መልክ መለገሱን ኢቲቪ ዘግቧል፡፡ በአመዛኙ የምርጫ 97ን ተከትሎ የፖለቲካ ምህዳሩ መጥበቡን ቢናገሩም፤ ከአንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ግልጽ ውይይት ማድረጋቸውና አዲስ የለውጥ ነፋስ አየሁ ማለታቸውም ሌላው አነጋጋሪ አጀንዳ ሆኗል፡፡
አና ጎሜዝና ምርጫ 97
ኢትዮጵያ ከደርግ ውድቀት በኋላ ቢያንስ በመርህ ደረጃ የሕዝብ ይሁንታ የሚረጋገጥበት ሕዝባዊ ሥልጣን በምርጫ የሚያዝበት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ታውጇል፡፡ ኢሕአዴግ አብዛኛው የፓርላማ መቀመጫውን በምርጫ ስም (ገለልተኛ ታዛቢዎች እንደሚሉት) መቆጣጠር ይዞት የመጣው ባህል፣ በሦስተኛው ዙር የ1997ቱ አገራዊ ምርጫ ተሰብሮ ነበር፡፡ በወቅቱ እንደ አሸን የፈሉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁለት አውራ ጥምረቶች (ኅብረትና ቅንጅት) በመፍጠር ገዥውን ፓርቲ ኢሕአዴግ በሰላማዊ መንገድ መፈታተን ችለው ነበር፡፡ ኋላ ኋላ ጉዳዩ ላይ ጥናት ያካሄዱት ምሁራን እንደሚሉት በሙያ ሥነ ምግባር ጉድለት ምክንያት፣ የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨት አደገኛነቱ የሚያመዝን ቢሆንም፣ የግል ሚዲያው በአገሪቱ ታሪክ ተጠናክሮ የመጣበት ወቅትም ነበር፡፡ መንግሥት የሰነዘራቸው ከፍተኛ ትችቶች ሳይዘነጉም የአገር በቀልና የውጭ ሲቪክ ማኅበራትም በፖለቲካው የላቀ ሚናቸውን ተጫውተዋል፡፡
ይኸው የ97ቱ ምርጫ በአንዳንድ የኅብረተሰብ ክፍል ላይ የራሱ የሆነ የማይረሳ መጥፎ ጠባሳ ጥሎ አልፏል፡፡ በመንግሥትና በተቃዋሚዎች ግንኙነት ላይ ያስከተለው ሕመምም አሁንም ድረስ አልተፈወሰም፡፡ ምርጫውን ተከትሎ ለተፈጠረው ቀውስም፣ በዋና ተዋናዮቹ ሁለቱ ወገኖች ብቻ የተወሰነ አልነበረም፡፡
ኢሕአዴግ እንደሚለው፣ አንዳንድ የፖለቲካ ሰዎች የራሳቸው የፖለቲካ አጀንዳ ይዘው የተንቀሳቀሱ የ‹‹ኒዮሊበራል›› ኃይሎች በገንዘብም ሆነ በሞራል ጫና ለመፍጠር ክፍተቱን ተጠቅመው ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ይህ በማናቸውም አገሮች የሚፈጠር ቀውስ ለውጭ ኃይሎች በር መክፈቱ ግን በኢትዮጵያም በሌሎች አገሮችም እንግዳ አይደለም፡፡ በምርጫም ሽፋንም ሆነ በኃይል በመፈንቅለ መንግሥት፣ በተለይ ምዕራባውያን ኃይሎች የማይፈልጉትን አካል ለመጣልና የሚፈልጉትን ወገን ደግሞ ለማንገሥ ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ ጣልቃ ገብነት ከማድረግ አይቦዝኑም፡፡ የሚያስከትለው ውጤት ከአገር አገር ይለይ እንጂ፣ በተለይ በድሀ አፍሪካ አገሮች የእነዚህ ኃይሎች እጅ ረዘም ያለ ነበር፡፡ ዋና አጀንዳቸው ባይሆንም ለዲሞክራሲ መስፋፋት ምንም ዓይነት ፋይዳ አይኖራቸውም ግን አይባልም፡፡
ከምርጫ 97 ጋር በተያያዘ ስማቸው በቀላሉ ከሕዝብ አእምሮ ከማይጠፋው ጥቂት የፖለቲካ ሰዎች እኩል የሚታየው፣ የውጭ ሰዎች ግንባር ቀደሙ ደግሞ የሚስስ አና ጎሜዝ ነው፡፡ ለዚህም ይሆናል ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተደረገው ዓለም አቀፍ ጉባኤና ከአውሮፓ ኅብረት ከፍተኛ ዕርዳታም በላይ፣ የብዙዎችን ቀልብ የሳበ የሚመስለው፡፡ ወይዘሮዋ በአሁኑ ወቅት በተለይ የአዲስ አበባን ነዋሪዎች ቀልብ የሳቡት ከምርጫው ቀውስ ዘጠኝ ዓመት በኋላ ወደ ከተማይቱ ሲመጡ ለመጀመርያ ጊዜ በመሆኑ ብቻ አይመስልም፡፡ ያሳዩት የአቋም ለውጥ ጭምር እንጂ፡፡
የአና ጎሜዝ ልብ ዛሬ ወዴት ነው?
ከሁለት ዓመት እስር በኋላ በይቅርታ የተፈቱ የቅንጅት አመራሮች፣ የሚዲያና የሲቪክ ማኅበራት የፖለቲካ አራማጆችም፣ በምርጫው ወቅት ያሳዩትን ጉልበት ይዘው መቀጠል አልቻሉም፡፡ በተቃዋሚዎች ላይ ተስፋ የቆረጡት ግን የአሜሪካ መንግሥት (ቀጥሎ የመጣው የኦባማ አስተዳደር) እና የአውሮፓ ኅብረት ብቻ አልነበሩም፡፡ በምርጫ ውጤት እንደታየው፣ መራጩ ሕዝብ በተቃዋሚዎች ላይ ተስፋ መቁረጡን በግልጽ አሳይቷል፡፡ ማሳያው በ1997 ምርጫ መቶ በመቶ ቅንጅትን የመረጠው የአዲስ አበባው ሕዝብ፣ ከአንድ ወንበር በስተቀር በ2002 ዓ.ም. ኢሕአዴግን መርጧል፡፡ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት፣ የፖለቲካ ቁርጠኝነት የትግል ጽናት የላቸውም ብሎ ተስፋ የቆረጠባቸው የተቃዋሚዎች አመራሮች ‹‹ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ ተንቀሳቅሰናል›› በሚል ይቅርታ መጠየቃቸው ብቻም አይመስልም፡፡ መሪዎቹ ከእስር ከወጡ በኋላ በሁለት እግሩ መቆም የሚችል ድርጅት ይዘው መቀጠል አለመቻላቸውም ጭምር ነው፡፡ ይህንን በማድረግ ምትክ፣ በመካከላቸው በተፈጠረው አለመግባባት ወደተራ ድብድብ እስከመግባት የደረሱ ነበሩ፡፡ መንግሥት ይህንን ክስተት ለፕሮፖጋንዳ በስፋት ተጠቅሞት ነበር፡፡
በቅርቡ አዲስ አበባ የመጡት አና ጎሜዝ ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝተው ግልጽ የሆነ ውይይት ማድረጋቸው ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ ከተቃዋሚዎች ጋር ምንም ንግግር አለማድረጋቸው ይነገራል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ድንገተኛ ሕልፈት አገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ሽግግር እንድታደርግ እንደ መልካም አጋጣሚ የተመለከቱት አና ጎሜዝ፣ በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ መሠረታዊ የሆነ ለውጥ ለማየት የጓጉ ይመስላሉ፡፡
በዚሁ ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፣ ‹‹አዲስ ነፋስ አለ›› ያሉት መንግሥት ለእሳቸው ያለምንም መንገላታትና እንቅፋት ቪዛ ስለሰጣቸው የአወንታዊው ለውጥ ምልከታቸው ቀዳሚ ነው፡፡ አሁንም ከ97 በኋላ የፖለቲካ ምህዳሩን በተመለከተ ችግሮች መኖራቸው አስረግጠው የተናገሩት አና ጎሜዝ፣ በአጠቃላይ ግን አገሪቱ በተለየና አዲስ አመራር ውስጥ መሆኗን ይናገራሉ፡፡ ያዩዋቸው ለውጦች ምን ምን እንደሚያካትቱ በዝርዝር ባያስረዱም፡፡ አንድ ትልቅ ለውጥ የተመለከቱት የሶሻል ሚዲያ መስፋፋት ሲሆን፣ ያንንም ከመንግሥት ቁጥጥር በላይ በመሆኑ ነው ይላሉ፡፡ በሙሰኞች ላይ የተወሰደ ዕርምጃም አድንቀዋል፡፡ ‹‹በኢትዮጵያ ላይ እኔ ምንም የኢኮኖሚ ሆነ ምንም ግላዊ ፍላጎት የለኝም›› የሚሉት አና ጎሜዝ፣ አንዳንድ ባለሥልጣናት በግልጽ ለመነጋገር መፍቀዳቸውንም እንደ ለውጥ ሳይመለከቱት አልቀሩም፡፡ ‹‹እኔን ለመስማት መፈለጋቸው ራሱ ጥሩ ይመስለኛል›› ብለዋል፡፡ ‹‹በሽብርተኝነት የታሠሩት ጋዜጠኞች እንጂ አሸባሪዎች አይደሉም›› ለሚለው ሙግታቸው ማስረጃ እንዲያቀርቡ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ ‹‹ጋዜጠኞች መሆናቸውን ነው የማውቀው›› ከማለት ውጪ የማቀርበው ማስረጃም የለኝም ብለዋል፡፡
በወቅቱ ከቅንጅት አመራሮች አንዱ የነበሩት ዶክተር ኃይሉ አርአያ፣ የአና ጎሜዝን መምጣት በበጎ ጎን አይተውታል፡፡ ‹‹መቀራረቡ በእኔ በኩል ገንቢ ነገር ነው፤›› የሚሉት ዶክተር ኃይሉ፣ ‹‹በአገሪቱ ተለውጧል ያሉትን ነገር ግን እሳቸው ብቻ ናቸው የሚያውቁት፡፡ እሳቸው በወቅቱ ይዘውት ከነበረው አቋም አሁን ምንም የተለወጠ ነገር አላየሁም፡፡ አቋማቸውን የሚያስለውጥ መሠረታዊ ለውጥ አላየሁም፤›› ብለዋል፡፡ ዶክተር ኃይሉ እንደሚሉት፣ በአገሪቱ እሳቸውም የማይክዱት ልማት እየመጣ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ‹‹ከዚያ ውጪ ግን በፖለቲካ መስክ ምንም የመጣ ለውጥ የለም፡፡ ቪዛ ስለተሰጣቸው ብቻ አዲስ ለውጥ አለ ማለት ግን አግባብ አይደለም፤›› ይላሉ፡፡
የቀድሞ አምባሳደር ተስፋዬ ሀቢሶ በበኩላቸው በ1997 ዓ.ም. በካምፓላ (ኡጋንዳ) አምባሳደር የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩን በቅርበት ይከታተሉ እንደነበር ይናገራሉ፡፡ አና ጎሜዝ በወቅቱ በኢትዮጵያ ላይ የያዙት አቋም የግላቸው እንዳልነበር በአጠቃላይ የምዕራባውያን መንግሥታት አቋም እንደነበር ይናገራሉ፡፡ በተለይ ደግሞ፣ ኒዮሊበራሊዝምን አክርረው የሚቃወሙት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስን እንደ ‹‹የወገብ ቅማል›› አድርገው ነበር የሚያዩዋቸው ብለዋል፡፡ በወቅቱ ከኢትዮጵያ የተባረሩት አራት የውጭ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችም የተቃውሞ እንቅስቃሴውን በገንዘብ ሲደግፉ እንደነበር ለአብነት ይጠቅሳሉ፡፡ አና ጎሜዝ ብቻም ሳይሆኑ እነ ክርስቶፈር ክላፋም፣ ክሪስ ቦርና የኤችአር 2003 ሕግ አርቃቂ ዶናልድ ፐይን የመሳሰሉትም በተመሳሳይ ይጠቅሳሉ፡፡ እሳቸውም እንደ ዶክተር ኃይሉ ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ አቋም የሚያስለውጥ ምንም የተለወጠ ነገር የለም፤›› በሚለው ሐሳብ ይስማማሉ፡፡
አና ጎሜዝ ከመንግሥት ጋር መታረቅ የፈለጉበት ምክንያት ግን ‹‹ታክቲክ›› እንደሚሆን በመገመት፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ ላይ ያለው አቋም መለወጡን ተስፋ እንዳስቆረጣቸው ይገምታሉ፡፡ ‹‹ከወደቀ ጋር መሆን ማን ይፈልጋል?›› በማለት፡፡ ‹‹አሁን በ60 ዲግሪ አቋማቸው ተለውጧል ያሉት አምባሳደር ተስፋዬ፣ ግለሰቦች የራሳቸው ሚና ቢኖራቸውም ያው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የተዉት ፖሊሲና ርዕዮተ ዓለም እየተተገበረ ስለሆነ ምንም አቋም የሚያስለውጥ ነገር የለም፤›› ይላሉ፡፡ ‹‹ስህተታቸውን አምነው፣ ለውጡ ከልብ ተቀብለውት ከሆነ ግን መልካሙን እመኝላቸዋለሁ›› ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሰላምና ልማት ተቋም ተመራማሪው አቶ አቤል አባተ በበኩላቸው፣ ‹‹የአና ጎሜዝ መለሳለስ ከአውሮፓ ውስጥ የደረሰባቸው መገለል ውጤት ነው፤›› ይላሉ፡፡ ከ1997 ምርጫ በኋላ የኢሕአዴግ መጠናከርና መንግሥት በልማት ላይ ያሳያቸው ተጨባጭ ዕድገቶች የተቺዎቹን አፍ እየዘጋለት እንደሆነ በመግለጽ፡፡ ለዚህም ከአቶ መለስ ሕልፈት በኋላ ምንም ዓይነት የፖሊሲም ሆነ የስትራቴጂ ለውጥ ባልታየበት የአና ጎሜዝ መለሳለስ ጥሩ ማሳያ ነው ብለውታል፡፡
‹‹ቀደም ሲል ከተቃዋሚ አመራሮች ጋር የነበራቸው መጥፎ ስም ለማደስ ፈልገው ይሆናል፡፡ ለአቋማቸው መለወጥ ዋነኛ ምክንያት ግን መገለላቸውና በአውሮፓ ኅብረት ውስጥ ምንም ዓይነት ተሰሚነትና ተአማኒነት ማጣታቸው ነው፡፡››
የባከኑ ስምንት ዓመታት
አና ጎሜዝ ሰሞኑን እዚሁ አዲስ አበባ እስከታዩ ድረስ፣ በተገኙ አጋጣሚዎች በሙሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ሲከሱ፣ ሲወነጅሉና ሲያጣጥሉ ቆይተዋል፡፡
ከይቅርታ ጠያቂዎቹ መካከል ወደ አሜሪካና አውሮፓ የገቡ አንዳንድ አመራሮች ከውጭ በመሆን ከእነ ሚስስ አና ጎሜዝና ዶናልድ ፔይን (ከሦስት ዓመት በፊት ሕይወታቸው ያለፈው) ጋር በመሆን ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል፡፡ መንግሥትን በኃይል ለመጣል ከዳያስፖራ ድጋፍ እያሰባሰበ የሚገኘውና በመንግሥት በአሸባሪነት የተፈረጀው ግንቦት ሰባት ሊቀመንበሩ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ (በአገር ክህደት ክስ በሌሉበት ሞት የተፈረደባቸው) ጋር በቅርበት ሲሠሩ ከቆዩት መካከል፣ አሁን ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ‹‹ግልፅ›› ውይይት ማድረጋቸውን የሚናገሩት ሚስስ አና ጎሜዝ ናቸው፡፡ በአውሮፓ ኅብረት አስተባባሪነት ኢትዮጵያን በሚመለከቱ መድረኮች፣ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ የተለያዩ ተቃውሞአቸውን እንዲገልጹም ከማመቻቸት ባሻገር ራሳቸው በተለያዩ ወቅቶች ኅብረቱ በኢትዮጵያ ላይ እንዲጨክን ድምፃቸውን ሲያሰሙ ኑረዋል፡፡ በኢትዮጵያ በሽብርተኝነት ክስ ተፈርዶባቸው በእስር የሚገኙት ግለሰቦች በአስቸኳይ እንዲፈቱ፣ መንግሥት ያፀደቃቸውን ሕጎች እንዲከልስ፣ ኅብረቱ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው ዕርዳታም ሆነ ብድር እንዲያቋርጥ በተለያዩ መንገዶች ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ የእሳቸው ጥረት፣ በአጠቃላይ የአውሮፓ ኅብረትና አባል አገሮች ሥልጣን ላይ ባለው መንግሥት ዕውቅና እንዲነፍጉ የሚጠይቅ ነው፡፡ ከዚያም አልፈው ወይዘሮዋ፣ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ባለው የድንበር ግጭትም ጭምር አስተያየት የሚሰጡ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የሄጉ ፍርደ ገምድል ውሳኔ ተፈጻሚ እንዲያደርግ ለዚህም ኅብረቱ ጫና እንዲፈጥር ይጠይቃሉ፡፡
በተለይ አምና መጋቢት ወር ላይ ለኅብረቱ ባቀረቡት ስሞታ፣ የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የሆኑት ጆሴ ማኑኤል ባሮሶ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝን በሚያነጋግሩዋቸው ወቅት፣ አገሪቱ ‹‹የፖለቲካ›› እስረኞቿን በአስቸኳይ እንድትፈታ የድንበር ውሳኔው በአስቸኳይ እንዲተገበርና በሶማሊያ የምታደርገውን ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት እንድታቆም ጫና እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡ ‹‹በእርግጥ እሳቸው ማምጣት የሚችሉት ለውጥ እምብዛም ነው›› ያሉዋቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያምንም የሥልጣን ሽግግር እንዲያደርጉ ፕሬዚዳንቱ ጫና ይፈጥሩ ዘንድ ተማጽነው ነበር፡፡ አውሮፓ ኅብረት ምርጫ 97ን ተከትሎ ያደረገው ለውጥ ካለ፣ ለአገሪቱ የሚሰጠው ዕርዳታ በመንግሥት በኩል መሆኑ ቀርቶ በፕሮጀክቶች አማካይነት በቀጥታ ለዜጎች እንዲውል ማድረጉ ነው፡፡ ከዚያ ውጪ በሶማሊያም ጉዳይ ሆነ በአካባቢው ደኅንነትና የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ዙርያ በጋራ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ ይህ ግን ለአና ጎሜዝ ፍፁም ተቀባይነት የለውም፡፡ ኅብረቱ በኢትዮጵያ ላይ የሚከተለው ፖሊሲ እስካሁንም አይዋጥላቸውም፡፡
በመጀመርያ አካባቢ የአውሮፓ ኅብረት በተለይ ደግሞ የኅብረቱ ዋና አከርካሪ ከሆኑት አባል አገሮች ግንባር ቀደም ከሆኑት መካከል እንግሊዝ በኢትዮጵያ ላይ የዕርዳታና ብድር ለኢትዮጵያ መንግሥት በቀጥታ እንዳይሰጥ በመከልከል የተሳካላት ቢመስልም የኋላ ኋላ ነገሮች እየተቀየሩ መጥተዋል፡፡ የአውሮፓ ኅብረትም ሆነ የአሜሪካ መንግሥት፣ ተስፋ የጣለባቸው ተቃዋሚዎችና ‹‹አክቲቪስቶች›› ወደ እስር ቤት በመግባታቸው ተፅዕኖዋቸው እየቀጨጨ በመሄዱ የውጭ ኃይሎችም ተስፋ እየቆረጡ መጥተዋል፡፡ ወይዘሮዋም ‹‹አይዟችሁ›› ሲሉዋቸው የነበሩ አመራሮችን ከእስር አላዳኑዋቸውም፡፡
እንደ የፖለቲካ ተመራማሪዎች ትንተና፣ በአገሪቱ የተፈጠረው የፖለቲካ ቀውስና መንግሥት የሰጠው አሉታዊ ምላሽ፣ የአገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ጉዞን ወደ ኋላ እንዲያፈገፍግ ምክንያት ቢሆንም፣ የውጭ ኃይሎች ግን ተስፋ የተጣለውን ያህል ተቃዋሚዎች የዲሞክራሲ ጉዞውንም የሚታደጉ አልነበሩም፡፡ ከውጭ ተፅዕኖ በአንጻራዊነት ነፃ መሆኑን የሚያምነው ኢሕአዴግም ሊቀመንበሩ አቶ መለስም፣ ክፍተቱን ተጠቅመው በኢትዮጵያ ላይ እጃቸውን የሰደዱ ኃይሎች በቀላሉ መቋቋም ችለዋል፡፡
የአና ጎሜዝ ድምዳሜና መዘዙ
የመለስ ዜናዊ አጠቃላይ ትንተና የአውሮፓ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን በ1997ቱ የኢትዮጵያ ምርጫ ላይ ሐቀኛ ሪፖርት አላቀረበም የሚል ነው፡፡ በተለይ የምርጫ ታዛቢ ቡድኑን በመሩት ፖርቱጋላዊቷ አና ጎሜዝ ላይ ጠንከር ያለ ተቃውሞን ከመሰንዘር ባሻገር ዘለፋ አከል አነጋገሮችን ተጠቅመዋል፡፡ በኢትዮጵያን ሔራልድ ጋዜጣ ለመጀመርያ ጊዜ በስማቸው ባወጡት ጽሑፍ ቡድኑ በሪፖርቱ ያካተታቸው ጥሬ ሐቆች ያሉት ቢሆንም፣ ድምዳሜው ሁሉ መሠረታዊ ችግር ያለበት መሆኑን ይጠቁማሉ፡፡ በሪፖርቱ በተካተቱ የምርጫ ጣቢያዎች ሁሉ ተስተዋሉ የተባሉትን ችግሮች በዝርዝር በማስታወስ ለችግሮቹ መንስዔ የሆኑትንና ሪፖርቱ በውል ያላጤናቸውን ነገሮች በመዘርዘር የሪፖርቱን ኢ-ሚዛናዊነት ያስቀምጣሉ፡፡ በተለይ በቡድን መሪዋ ላይ ካነሷቸው አበይት ነጥቦች መካከል ግለሰቧ የምርጫውን ሒደት ከመታዘብና ከመዘገብ ኃላፊነት አልፈው በድህረ ምርጫው በተነሱት ያለመግባባት ጥያቄዎች የመፍትሔ ሐሳብ ጠቋሚ ሆነው ቀርበዋል የሚል ነው፡፡ አና ጎሜዝ በሪፖርታቸው ምርጫው በተቃዋሚዎች አሸናፊነት መጠናቀቁን ገልጸው የተጋረጠውን አደጋ መመለስ የሚቻለው መንግሥትና ተቃዋሚዎች ወደ ጥምር መንግሥት የሚያመራቸውን የጋራ ስምምነት ማድረግ ሲችሉ እንደሆነ የሚገልጽ ንድፈ ሐሳብ ነበራቸው፡፡
በእነዚህና በሌሎችም ተጨማሪ ጉዳዮች የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ‹‹በሪፖርቱ ያልተካተተ ነገር ግን የሪፖርቱ ችግር ምንጭ›› ያሉት አና ጎሜዝን የሚሸነቁጡ ንግግሮችንና ዘለፋዎችን ሰንዝረዋል፡፡ በምላሻቸው ማጠናቀቂያ ላይ የቡድን መሪዋን የመፍትሔ ሐሳብ ላቅርብ ባይነትን በነገር ሲወጉ ‹‹የተከበሩት ወይዘሮዋ ከምርጫው ጋር ተያያዥነት የለውም ብለው እንጂ ዘንድሮ ስላገኘነው ጥሩ የዝናብ መጠንም አስተያየት መስጠት ይችሉ ነበር፤›› ሲሉ መልሰዋል፡፡
ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ምላሽ የብዙዎችን ቀልብ የሳበው በጽሑፋቸው መጨረሻ ያሰፈሩት፣ ‹‹What’s love got to do with it›› የታዋቂዋ አፍሪካ አሜሪካዊት ዘፋኝ ቲና ተርነር ዘፈን ወይዘሮዋን ሸንቆጥ ማድረጋቸው ነበር፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ጽሑፍ እስካሁን በወይዘሮዋ ላይ ያሳደረው ተፅዕኖ ከፍተኛ ይመስላል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ኅልፈት ያደረባቸውን ስሜት እስከመግለጽ ደርሰዋል፡፡
አና ጎሜዝ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ በእጅጉ መበሳጨታቸውን በመግለጽ ‹‹ከተቃዋሚዎች የገንዘብ ድጋፍ እንደተደረገልኝና ሌላ ሌላ አስመስለው ነው የገለጹኝ፡፡ በጣም ምርጥ ጭንቅላት ያለው ሰው ቢሆንም የሰው ሐሳብ የማምታታት ችሎታ የነበረው መሪ ነው፤›› ሲሉ ነው የገለጿቸው፡፡
ቪዛ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ማግኘታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ መሞት ያገናኙት አና ጎሜዝ የብሔር ጉዳይም ማንሳታቸው በኢትየጵያ ስላዩት መሻሻል እንዲነግሩት ለጠየቃቸው አዲስ ስታንዳርድ መጽሔት፣ በሰጡት ምላሽ ‹‹አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሚናውን ለመጫወት ቀላል አይሆንም፡፡ በውስጣቸው የሥልጣን ሽኩቻ እንደነበርም አውቃለሁ፤ እሱ ከትግራይ አይደለማ፡፡ የተሰጠኝን ቪዛ ትልቅ ትርጉም እሰጠዋለሁ፤›› ብለዋል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)

.jpg)


