Friday, 15 November 2013

የኢትዮጵያን መንግስት ለፍርድ ለማቅረብ ከተነሱት ስዊድናዊ ጠበቃ ጋር ውይይት ተደረገ

ቅዳሜ ኖቬምበር 2 ቀን 2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ መድረክ በስዊድን የወያኔን መንግስት በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለማቅረብ የተጀመረውን ክስ መነሻ በማድረግ የክሱን ሂደት ከሚመሩት ከስዊድናዊው ጠበቃ ከስቴላ ያርዴና ከሌሎች እንግዶች ጋር በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ወይይት አደረገ። million ም/ኢኒስፔክተር ሚሊዮን ብሩ ውይይቱ ከቀኑ 14፡00 ሰዓት የተጀመረ ሲሆን ውይይቱን የከፈቱት የመድረኩ ሊቀ መንበር ም/ኢኒስፔክተር ሚሊዮን ብሩ ናቸው። ኢኒስፔክተር ሚሊዮን በንግግራቸው መክፈቻ ጥሪ የተደረገላቸውን እንግዶችና ተሰብሳቢውን ህዝብ አመስግነው መድረኩ የተቋቋመበት ዓላማ በሀገር ውስጥና በውጪ የሚደረገውን የነጻነት ትግል የተደራጀ መልክ ይዞ የሚጓዝበት መንገድ ለማመቻቸትና በየጊዜውም ይህንን መሰል ውይይት በማድረግ ትግሉን ለመርዳት መሆኑን ገልጸው የዛሬውንም ስብሰባ የዚህ መነሻ እንደሆነ አስታውቀዋል። ዶ/ር ሙሉዓለም አዳም ዶ/ር ሙሉዓለም አዳም ከሳቸው በመቀጠል መድረኩን እንዲመሩ የተጋበዙት ጋዜጠኛ ወንድማገኝ ጋሹ፤ ዶ/ር ሙሉዓለም አዳምን የመጀመሪያው ተናጋሪ አድርገው ጋብዘዋል። ዶ/ር ሙሉዓለም የመድረኩን አዘጋጆች አመስግነው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በአስከፊ ሁኔታ ላይ መውደቁን ሙስናውም እያደረ መባባሱን የመንግስት ባለስልጣኖች ወደ ውጪ የሚያሸሹት ገንዘብ እየናረ መሄዱን ገልጸዋል። እንዲሁም የዘር ፖለቲካ እየተስፋፋ መሄዱን፣ የስለላ መዋቅሩም መጠናከሩንና ህዝቡን መግቢያ መውጫ ማሳጣቱን ከዚያም አልፎ በውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ድረስ መዝለቁን አስረድተዋል። የወቅቱን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርንም ንግግር በመጥቀስ በሰላማዊ ሁኔታ የሚደረገው ትግል አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንደወደቀ አመላክተዋል። ሁለተኛው ተናጋሪ የመድረክ መሪው ጋዜጠኛ ወንድማገኝ ጋሹ ሲሆኑ እርሳቸውም በሀገራችን ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ የሰው ልጅን የሰውነት ደረጃ ያቃለለ፣ ሙሉ ለሙሉ ያዋረደና መብት የገፈፈ መሆኑን ጠቅሰው፣ ለሃያ ደቂቃ የቆየ ይህንኑ የሚያመላክት ፊልም አሳይተዋል። wendmagegne ጋዜጠኛ ወንድማገኝ ጋሹ ቀጥሎም የተነሱበትን አላማ እንዲያስረዱ በጉጉት ይጠበቁ የነበሩት ስዊድናዊው ጠበቃ ስቴላ ያርዴ ንግግር እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል። ጠበቃ ስቴላ ያርዴ የስዊድን ቴሌቪዥን ባሳየው ዘጋቢ ፍልም ስሚታቸው እንደተነካ ገልጸው ይሄንን አሰቃቂ ወንጀል የፈጸመውን የወያኔን መንግስት ለፍርድ ለማቅረብ እንደተነሱ አስረድተዋል። በፊልሙ ላይ የታዩት የወንጀል ድርጊቶች ለተነሳንበት ክስ አሳማኝ መረጃ ከመሆኑም በላይ በተለይ በእስር ላይ ያሉ ስዎችን የመድፈርና የማስወለድ ድርጊት ወንጀሉን የሚያከብደው ሲሆን በቅርባችን ባሉት ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ላይም የተፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰትና በደል ክሱን እንደሚያጠናክርው ገልጸዋል። ሁኔታውን ሲያብራሩም አሁን ያሉንን መረጃዎች ይዘን ለሚመለከተው አካል አመልክተናል። ወደ ቀጣዩ እርምጃ ለማለፍ የነሱን ውሳኔ መጠበቅ ይኖርብናል። የስዊድን ፖሊስም ለዚህ ጉዳይ ትብብሩን አልነፈገንም ብለዋል። stellan-yarde ጠበቃ ስቴላ ያርዴ ከተሰብሳቢው ህዝብም ክሳችሁ ትኩረት ይዞ የተነሳው በኦጋዴን በታየው በደል ብቻ ነው ወይስ በሌሎችም ክልሎች የተፈጸመውን አጠቃሎ ይይዛል? ለተባሉት ሲመልሱ በሌሎች ክልሎች የተፈጸመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ድርጊቱን በሚያስረዳ መልክ ማስረጃ አሰባስበን መያዝ የመጀመሪያ ስራችን ይሆናል ብለዋል። ማስረጃ ልንሰጣችሁ ብንፈልግ በምን መልኩ ማቅረብ እንችላለን ለተባለው ጥያቄ ደግሞ ሲመልሱ ማስረጃ ለመስጠት በተናጠል እኔን ማግኘት አያስፈልጋችሁም ከተለያየ ሰውና ቦታ የምታገኙትን መረጃ ይህንን የሚያሰባስብ የመረጃ ቡድን አቋቁማችሁ ቡድኑ መረጃዎችን አጣርቶና አሰባስቦ ቢሰጠን የተሻለ ይሆናል ብለዋል። ye afar tenagareየአፋር ሰብዓዊ መብት ተወካይ በስብሰባው ላይ የተገኙት የአፋር ህዝብ ብሄራዊ ክልል የሰብዓዊ መብት ተወካይ በበኩላቸው በአፋር ህዝብ ላይ እየተደረገ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ከሌላው ክልል የማይተናነስ መሆኑን ገልጸው በእጃቸው የሚገኘውን መረጃ ለጠበቃ ስቴላ ያርዴ ሰጥተዋል። የመጨረሻው ተናጋሪ መቶ አለቃ አበረ አዳሙ ሲሆኑ እርሳቸውም ‹‹ድርጅታዊ ዘረኝነት›› በሚል ርዕስ የተሰብሳቢውን ህዝብ ስሜት የሳበ ንግግር አድርገዋል። በዚሁ ንግግራቸው እንዳብራሩት የኢትዮጵያ መንግስት የድርጅታዊ ዘረኛነትን አገዛዝ አጥብቆ ለመያዝ የክልልና የፌዴራል ፖሊስን፣ የደህንንነት መምሪያውን፣ የመከላከያ ሰራዊቱን፣ የስራ ፈጻሚ ክፍሎች እንዲሁም የገንዘብ ገቢ የሚያስገኙ ተቋማትን በአንድ ዘር በማደራጀት ሃላፊዎች መድቦ ምንም አይነት ቀዳዳ ሳይከፍት ሁሉን ነገር ከቁጥጥሩ ስር በማድረግ tesebsabe hezb ተሰብሳቢው ህዝብ በከፊል ድርጅታዊ ዘረኝነቱን ለማጠናከር ችሏል ብለዋል። በመሆኑም ተቃዋሚ የሆንን ሁሉ ይህንን ድርጅታዊ ዘረኝነት አውቀን ትግላችንን ማጠናከር ይገባናል ለዚህም የሚያገለግለን መተባበርና እርስ በርሳችን መተሳሰር ሲሆን ይህን የአፈና መዋቅርም ማፍረስ የምንችለው በተጠናከረ የአንድነት ትግል ብቻ ነው በማለት ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋል። የመቶ አለቃ አበረ ንግግር በብዙዎች ታዳሚዎች ዘንድ ለለውጥ የሚያነሳሳ ስሜት ፈጥሮ ነበር። በመጨረሻም የውይይት መድረኩ ለወደፊትም ከልዩ ልዩ እንግዶች ጋር በዚህ መልክ ወይይቶች እንደሚደረግ ገልጾ ውይይቱ 18፤00 ስዓት ላይ ተጠናቋል። (ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የተጠናቀረው ዘገባ ወለላዬ ከስዊድን)

በወያኔ ሎሌነት ከመማቀቅ አንድ ቀን ነፃ ሆኖ መኖር ይሻላል

በወያኔ ግፈኛ ስርአት መከራቸውን ከሚያዩ ዜጎች ውስጥ ራሱ ሥርአቱ ለራሱ መገልገያ የሰበሰባቸውና ያሰማራቸው ዜጎች ይገኙበታል። ከእጅ ወደ አፍ እንኳን ለማትሆን ደመዎዝ በሰራዊቱ ውስጥ በተራ ወታደርነትና በበታች ሹማምንት የሲኦልና የጉስቅልና ኖሮ እንደሚኖሩ እናውቃለን። በየዞኑና በየወረዳው በካድሬነት ወያኔ ለገላጋይነት ያሰማራቸው ሰራተኞችና የድርጅቱ አባሎች ከህዝቡ የጥላቻ ሰለባነት ባልተናነሰ በኑሮአቸው ለራሳቸውም ለቤተሰቦቻቸውም ሳያልፍላቸው እንደሚኖሩ እናውቃለን። ይልቁንስ የወያኔው የአመራር ጉጅሌ ነገ የት እንደሚያደርሳቸው በማያውቁት ጨለማ ውስጥ ነው የሚዳክሩት ሚስጥርና የዳጎሰ ጥቅም ከነሱ ዘንድ አይደርስም። በቀድሞ ጊዜ የነበሩት የባላባት ሎሌዎች እንኳን ክብር አላቸው። በዚህ ላይ ሁሉም አስተማማኝ ሎሌ መሆኑን ወያኔ ለማረጋገጫ የሚጠቀምበት ግምገማ አለ። የወያኔ ግምገማ የበታች አባላትና ደጋፊዎቹን በማስፈራራት ያላቋረጠ ድጋፍ እንዲሰጡት የሚያደርግበት በመሰረቱ ከውሻ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የማይለይ ተቋም ነው። የትምህርት እድል የስራ እድገትና የደመወዝ ጭማሪ የወያኔው ጉጅሌ የባርነት መደለያዎች ናቸው። ግንቦት 7 ከጥቂት ከመንገዳቸው እያወጡ ህዝብ ከሚያሰቃዩት የወያኔ ታዛዥ ሎሌዎች በቀር የሀገርና የወገን ጠላት ናቸው ብሎ አያምንም። ትግላችን ለነሱም ነጻነት ነው። እነዚህ ወገኖቻችን ባገኙት አጋጣሚና እድል ሁሉ ትግሉን ያግዛሉ ብሎም ያምናል። የሚያግዙም አሉ። እርግጥ ነው ባሽከርነት ኑሮ የተንገፈገፉ የሰራዊቱ አባላትና ለህሊናቸው ክብር ያላቸው በርካታ የስርአቱ አገልጋዮች ትግላችንን እየተቀላቀሉ ነው። ግንቦት 7 ንቅናቄ ዛሬም እንደሁሌው ለነዚህ ወገኖች ኑ ተቀላቀሉን የሚል ጥሪውን ያቀርባል። ሁላችንም ከነክብራችን ሆነን ሰዎችን ሳይሆን ውዲቱን ሀገራችንና ህዝባችንን በፈቃደኝነት በነጻነት የምናገለግልበት ጊዜ እየቀረበ ነው፡፡ ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!source ginbot7.org

ወያኔ የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎችን አሰረ፤ ሰልፉም እንዳይደረግ ከለከለ፤ በሰልፉ ላይ የነበሩ የአንድነት ፓርቲ አባላትም መታሰራቸው ታውቋል

የሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ለመሳተፍ የወጡ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ታሰሩ፡፡ ከጽ/ቤታቸው ተነስተው ወደ ሰላማዊ ሰልፉ ቦታ ሲሄዱ 4 ኪሎ የኦሮሚያ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ጎን በሚገኘው ወታደራዊ ገራዥ መታሰራቸውን ዘጋቢያችን ከቦታው አድርሶናል፡፡ ከመታሰራው ቀደም ብሎ ከፖሊስ ጋር እንሂድ አትሄዱም በሚል ጭቅጭቅ ላይ እንደነበሩ ሰምተናል፡፡ ሌሎች የፓርቲው አባላትና አመራሮች ተበታትነው ወደ ሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ እየሄዱ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል፡፡ ዘግየቶ በደረሰን ዜና ደግሞ በኤምባሲው በተገኙ ሰዎች ላይ ፌዴራል ፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ ማድረሱ ታውቋል፡፡ በተጨማሪም በሰልፉ ላይ የነበሩ የአንድነት ፓርቲ አባላትም መታሰራቸው ታውቋል፡፡ በተለይ አንዲ ሴት ክፉኛ በመመታቷ ለህይወቷ እንዲያሰጋ ለማወቅ ችለኛል፡፡ አንድ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው “በሰው አገር ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ለመቃወም ወጥተን ተመሳሳይ ስቃይ አስተናገድን” ብለዋል፡፡

Tuesday, 12 November 2013

በስደት ለሚሰቃየው ኢትዩዺያዊ ተተያቂው ማነው?

ሀገር እያለው ሀገር እንደሌለው በሞት ለሚቀጣው ህዝብስ ተተያቂው ማነው? በድብደባ በእስር ለሚገላታው ወገን አረ ማንነው ተተያቂው? ለዚህ ሁሉ ተተያቂው ማነው? አረ ወገኖች የሀገር የወገን ያለ! እያለ ነው፡ ህዝባችን ግን ማን አለን ሀገር መሪ ቢኖረን ወገኖች በሳውዲ ሲሰቃዩ ሲገደሉ ሲቆረጡ መንግስት ለህዝቡ መብት መቆም አልቻለም::
ላለፉት ሁለት አስርት አመታት በማን አለብኝነት ህዝብን ማሰር ማሰቃየት መግደል ግለሰቦችንና ቡድኖችን ማንቃሸሽ መሳደብ ስልጣንን ተገን አድርጎ የሀገርና የህዝብን ሀብት መዝረፍ ለግላቸው ጥቅምና ስልጣን የሀገርንና የህዝብን ጥቅም አሳልፎ መስጠትና የመሳሰሉትን ወንጀሎች ሲፈፅሙ ቆይተዋል:: ልክ ከዚህ በፊት እንዳየናቸው አምባገነን አፍሪካዊያን መሪዎች በስልጣን ለመቆየትና የህዝብንና የሀገርን ሀብት ንብረት ለመዝረፍ ሲሉ የወያኔ መንግስት የፈፅሙዋቸውና ያስፈፅሙዋችው ኢ-ሰብአዊና ኢ-ፍታዊ ድርጊቶች: የዘር ማጥፋት: የግለሰቦችን ነብስ ማጥፋት ወንጀሎች: ሁሉም የመንግስት ባለስልጣናት በከፍተኛ ሙስና የጠገቡ ባለሀብቶች መሆን: ሀገሪቱዋ እስካሁን በምግብ እራስን ለመቻል ተቀረዑ የተባሉት እስትራቴጂዎች ምንም ውጤታማ ሳይሆኑ ቀርተው በአስር ሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን በተደጋጋሚ በከፍተኛ በርሀብ አለንጋ ከመገረፍ አለማዳናቸው: የህዝቡን ጥያቄ በአግባቡ ባለመመለሳቸው የወያኔ መንግስት ወደ ስነልቦናዊ አእምሮአዊና ፖለቲካዊ ችግር ውስጥ ተዘፍቀዋል:: የወያኔ መንግስት ለስሙ ሀይማኖትና መንግስት ጣልቃ አይገባቡም እያለ ጆሮችንን በየቀኑ ያደነቁረናል ነገር ግን በኦርቶዶክስና በእስልምና እምነት ድርጅቶች ውስጥ በቀጥታ እጁን አስገብቶ በመጀመሪያ ለዘመናት ተቻችለውና ተከባብርው የኖሩትን ከላይ የተጠቀሱትን የሁለቱን እምነቶች ተከታዮችን ጣልቃ በመግባት እርስ በርሱ እንዲተላለቁ ለማድረግ ብዙ ስራዎች ተሰርተው ነበረ ነገር ግን ህብረተሰቡ ይህ ተግባር የወያኔ አኩይ ስራ እንደነበረ ስለተረዳ በትዝብት ተመልክቶታል:: በሁለተኛ ደረጃ ወያኔ በእምነቶች ውስጥ ጣልቃ መግባቱ ገሀድ የወጣበት በኦርቶዶክስ እምነት ውስጥ የሚገኙትን ከፍተኛ የስልጣን ቦታዎችን የፈጣሪን የሚመለክባቸው ሳይሆን የወያኔን ጥቅም ለሚያስከብሩ ከአንድ ብሄር ለተሰበሰቡ ግለሰቦች አስረከበ:: የወያኔ መንግስት ህዝባዊ አመፅ የሚያስነሱ ናቸው በማለት በውሸት በተቀነባበረ ክስ በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎች የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት አባላቶች ደጋፊዎች የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች በሰብአዊ መብትና በማህበረሰብ ልማት ላይ የተሰማሩትን መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የግል ጋዜጣ ባለቤቶችና አምደኞች በየእስር ቤቶቹ እያጎረ ነው። እነዚህ በየማጎሪያ ቤቶቹ የሚገኙትን እስረኞች ቁጥር በእጅጉ ከመጨመሩም በላይ ታስረው በሚገኙበት ቦታ የሚፈጸመው እንግልት እና ስቃይ እጅግ በጣም ተባብሷል:: ሆኖም ግን ወያኔ የህዝቡን አመለካከት እና የወቅቱን የፓለቲካ እንቅስቃሴ ለመለወጥ ሲል በአሸባሪዎች በማሳበብ ብዙ ሽብሮችን እየፈጠረ የፓለቲካውን ሂደት እንዲለውጥ በማድረግ ይሞክራል። ሆኖም ግን በተደጋጋሚ በመደረጉ በህዝቡ አመኔታን ከማጣቱ የተነሳ ተቀባይነት ሊያገኝ አልቻለም። አሁን የወያኔ አባላቶችና ደጋፊዎች የሚይዙትን የሚጨብጡትን ያጡበት ሰአት ላይ ይገኛሉ። ትልቁ ችግራቸው እስካሁን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሱትን ወንጀሎች ኢተፈጥሮአዊና ኢሰብአዊ ድርጊቶች የሀገርና የህዝብ ሀብትና ንብረት ዘረፋ ብሎም የግለሰቦችን የብሄርንና የሀገርን ስምና ታሪክ ማጥፋትና ማበላሸትና የመሳሰሉ የውንብድና ተግባሮቻቸውን እንዴት ማጥፋት እንደሚችሉ የሚቻላቸውን ሁሉ ጥረት እያደረጉ ነው። ነገር ግን የሄ የመንግስት የሀይል እርምጃ ፉከራ ድንፋታ መደነባበር የህዝባችንን የፍትህ የእኩልነትና የነፃነት ትግል ማቆም አያስችለውም::

Sunday, 10 November 2013

ኢሕአዴግ እና የሃይማኖት ነጻነት

(ፋክት መጽሔት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፱ ጥቅምት ፳፻፮ ዓ.ም.) ተመስገን ደሳለኝ … ኢሠፓ መራሹ መንግሥት በኢሕአዴግ ከተተካ ጥቂት ወራት ቢያልፈውም፣ የተራዘመው የእርስ በርስ ጦርነት ያልደረሰባቸው በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙ አንዳንድ ከተሞችን ገና በቅጡ አልተቆጣጠራቸውም፤ በአናቱም በኢሠፓ መንግሥት ሽንፈት ሳቢያ እንዲበተን ከተገደደው የአገሪቱ መደበኛ ወታደር አብዛኛው ከእነትጥቁ የትውልድ መንደሩንና ቤተሰቡን መቀላቀሉ በአገሪቱ ላይ ከባድ ፍርሃት አንብሯል፡፡ በሰላም ወጥቶ ለመመለስ ርግጠኛ መኾን የማይቻልበት ከባቢያዊ አየርም አስፍኗል፡፡ በበርካታ ቦታዎች ተጠንተውና ታቅደው የሚፈጸሙ ወንጀሎችም ከአምስት እስከ ዐሥራ አምስት በሚደርሱ ወታደሮች የተደራጁ ልዩ ልዩ ሕገ ወጥ ቡድኖች በየማዕዘኑ እያቆጠቆጡ መኾኑን አመላክትዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የዐዲስ አበባ ቆዳ ስፋትና የነዋሮዎቿ የአኗኗር ዘይቤን በቀላሉ ለመልመድ የተቸገሩ ተጋዳላዮች ለትንሽ ለትልቁ ግርግር ጠመንጃን እንደ መፍትሔ መምረጣቸው ችግሩን አባብሶታል፡፡ ጉዳዩ እያሳሰባቸው የሄደው የኢሕአዴግ ዋነኛ መሪዎችም እንዲህ ዐይነቱን አለመረጋጋትና ሥርዐተ አልበኝነት ለመቆጣጠር የመንፈሳዊ መሪዎች አስተዋፅኦ ወሳኝ ስለ መኾኑ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል(እንደ ቀደሙት ሥርዐቶች ኹሉ ለቅቡልነት ከሚጠቀሙበት በተጨማሪ ማለት ነው)፡፡ ይኹንና በመንበሩ ላይ የነበሩት ፓትርያርኩ አቡነ መርቆሬዎስ አገር ለቀው እንዲወጡ በመደረጉ ክፍተት ተፈጥሯል፡፡ ይህ ጊዜ ነው ከ፲፱፻፸፬ ዓ.ም. ጀምሮ [ከኢየሩሳሌም ተሰደው] መኖርያቸውን አሜሪካን አገር ያደረጉ አንድ መንፈሳዊ አባት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ የተወሰነው፤ በጥሪው መሠረትም ወደ አገራቸው ሲገቡ መንግሥት የክብር አቀባበል አደረገላቸው፡፡ እኚኽ አባት ዛሬ በመንበረ ፕትርክናው የተሠየሙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ነበሩ፡፡ ኾኖም ከሳምንት ሽር ጉድ በኋላ አቡነ ‹‹የኢዲዩ አባል ነበሩ›› የሚል ወሬ በአመራሩ አካባቢ በስፋት መሰራጨቱ ያልተጠበቀ ዱብ ዕዳ አስከተለ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ኢሕአዴግ እና ኢዲዩ በ፲፱፻፸ዎቹ መጀመርያ ትግራይ እና ጎንደር ውስጥ በርካታ መሥዋዕትነት ያስከፈለ ውጊያ ማድረጋቸው ብቻ አልነበረም፡፡ የመጀመርያዎቹ ሊቀ መንበሮች ስሁል ገሰሰ እና መሐሪ ተኽሌ(ሙሴ) ‹‹የተገደሉት በኢዲዩ ነው›› የሚለው ወሬ በድርጅቱ ውስጥ ከጫፍ ጫፍ የተናኘና የታመነበት ጉዳይ መኾኑ ነበር፡፡ በዚህም ላይ የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ግራ ዘመምነት ተደማምሮ አቡነ ማትያስ በወቅቱ ወደ ታሪክነት ከተቀየረ ዓመታትን ባስቆጠረው ኢዲዩ ተፈርጀው ከታጩበት የፕትርክና መንበር ተገፈተሩ፡፡ ከዚህ በኋላ ነበር አብላጫውን የትጥቅ ትግል ዘመን በአሜሪካ ያሳለፉት አሰፋ ማሞ እና ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ ‹‹ዉድብ›› የሰጠቻቸውን ተልእኮ ተቀብለው ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ያመሩት፤ እናም ቀድሞም ትውውቅ ወደነበራቸው ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ ዘንድ ሄደው ለፕትርክና ወንበር መታጨታቸውን አበሠሯቸው፡፡ በእንዲህ ያለ መንገድ መንግሥት የቀባቸው አቡነ ጳውሎስም እስከ ኅልፈታቸው ድረስ አወዛጋቢ መሪ ኾነው ዘልቀዋል፡፡ (በነገራችን ላይ በአሜሪካ ለመጀመርያ ጊዜ ከሲኖዶሱ ተነጥሎ የቆመ ቤተ ክርስቲያን የመሠረቱት አቡነ ጳውሎስ እንደነበሩ ይነገራል፡፡ አቡኑ ደርግ ለጥቂት ዓመታት አስሮ ከለቀቃቸው በኋላ ወደ አሜሪካ ሄደው የፈጣሪያቸውን ሰማያዊ መንግሥት ሲሰብኩ ቆይተው የህወሓት ሠራዊት ክንዱ እየበረታ በቁጥጥሩ ሥር ያዋላቸው ከተሞችም እየበዙ ሲሄዱ እርሳቸውም ስብከታቸውን ወደ ትግርኛ ቋንቋ ከመቀየራቸውም በላይ ለ‹ነጻ አውጭ›ው ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ ያሰባስቡ ጀመር፡፡ የሥርዐት ለውጥ መደረጉን ተከትሎም በፖሊቲከኞች በተቀነባበረ ሤራ ከአቡነ ጳውሎስ ጋራ ቦታ የተለዋወጡት አቡነ መርቆሬዎስም፣ እዚያው አሜሪካ ‹ተተኪ›ያቸው የጀመሩትን ብሔር ተኮርና ከሲኖዶሱ የተገነጠለ ቤተ ክርስቲያን አስፋፍተው ዛሬ ለደረሰበት ‹የጎንደሬ ማርያም›፣ ‹የትግሬ ገብርኤል›. . .ለተሰኘ አሳፋሪ ክፍፍል ዳርገውታል፡፡ በርግጥ ለአቡኑ[አቡነ መርቆሬዎስ] ከአገር መውጣት የኢሕአዴግ እጅ እንዳለበት እንድናምን የሚያስገድደን በቅርቡ ታምራት ላይኔ ‹‹በእኔ ፊርማ ነው ያባረርናቸው›› ማለቱን ዊኪሊክስ ካደረሰን መረጃ በተጨማሪ በትጥቅ ትግሉ ዘመን ህወሓት በተቆጣጠራቸው በትግራይና ወሎ ነጻ መሬቶች በሚገኙ ከተሞች ያሉ ነዋሪዎችን ቀስቅሶና አደራጅቶ ፓትርያርኩ ላይ ‹‹ሽጉጥ ታጣቂ ጳጳስ››፣ ‹‹ቀይ ደብተር ያለው/ለኢሠፓ አባላት የሚሰጥ/ የሸንጎ ተወካይ››. . .የመሳሰሉትን መፈክሮች እያሰሙ በተቃውሞ ሰልፍ እንዲያወግዟቸው ማስተባበሩን ስናስታውስ ነው)፡፡ ዛሬስ የሃይማኖት ነጻነት የት ድረስ ነው? ከላይ ታሪክን ወደ ኋላ መለስ ብዬ በደምሳሳው ለመጠቃቀስ እንደሞከርኹት፣ ኢሕአዴግ በሃይማኖት ጉዳይ እጁን ጣልቃ ማስገባት የጀመረው ክንዱ ሳይፈረጥም ገና በረሓ ላይ ሳለ ነበር፡፡ በዚህ ኹኔታ የተጀመረው ጣልቃ ገብነት ዛሬም ድረስ ተባብሶ ቀጥሏል፤ ምንም እንኳ በሃይማኖት ጉዳዮች ጣልቃ እንደማይገባ በደፈናው ከሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፲፩ን በመጥቀስ በተደጋጋሚ ለማስተባበል ቢሞክርም ያለፉት ዓመታት ተጨባጭ ተግባሮቹ የሚመሰክሩት ግልባጩን ነው፡፡ ድርጅቱ ራሱም ቢኾን ጥያቄው በተነሣ ቁጥር ከሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፲፩ን የሚጠቅሰው ለስሙ እንጂ ሕጉ ተግባራዊ አለመኾኑን ሳይረዳ ቀርቶ አይደለም፤ አቶ ተፈራ ዋልዋም በ፲፱፻፺፰ ዓ.ም. ኅዳር/ታኅሣሥ ወር ከታተመችው ሐመር መጽሔት ጋራ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ጉዳዩን አስመልክቶ የሰጡት አስተያየት የኢሕአዴግን አጭበርባሪነት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፡- ‹‹ኢሕአዴግ እኮ የሚመራው መንግሥት በደርግም ጊዜ፣ በኃይለ ሥላሴም ጊዜ እንደሚታወቀው ‹የቤተ ክርስቲያን ሥራ አስኪያጅ ሹምልን› ተብሎ ተጠይቆ ‹የለም ራስዋ ቤተ ክርስቲያኒቱ ትሾማለች እንጂ እንደ ቀድሞው መንግሥት አይሾምላችኁም› የሚል መልስ የሰጠ መንግሥት ነው፡፡›› በሕዝበ ሙስሊሙ ተመርጦ ለእስር የተዳረጉት የኮሚቴ አባላትም በአንድ ወቅት ለሚመለከተው የመንግሥት ባለሥልጣን የጻፉት ደብዳቤ ጣልቃ ገብነቱን በግልጽ ያሳያል፡- ‹‹መንግሥት እንደ መንግሥት ሕዝቡ ተበድዬአለኹ፤ ምርጫ ይካሔድ፤ የመጅሊሱን አመራር አላመንኹበትም፤ ውክልና የለውምና ሕገ ወጥ ነው ያለውን አካል ሕገ ወጥነቱ እንዲረዝም ምርጫውን እርሱው እንዲያካሒድ መወሰን ሕዝብን ግራ አጋቢ ነው፡፡›› ሥርዐቱ በሃይማኖት ጉዳዮች ላይ ጣልቃ እንደማይገባ ለማሳመን ይህን ያህል ቢዳክርም በቅርቡ ‹‹የፀረ አክራሪነት ትግል የወቅቱ ኹኔታና ቀጣይ አቅጣጫዎች›› በሚል ርእስ የተዘጋጀው ባለ 44 ገጽ ሰነድ፣ መንግሥት በዘወርዋራ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን ሙሉ በሙሉ የሚያምን ኾኖ አግኝቸዋለኹ፤ ‹‹የመንግሥት መዋቅራትን ሴኩላር መንግሥት መኾናችንን ዐውቆ የመንግሥትን መዋቅር ተጠቅሞ የራሱን ሃይማኖት መሠረት ያደረገ አገልግሎት ከመስጠት ሙሉ በሙሉ ያልጸዳ መኾኑን የተለያዩ ጥቂት የማይባሉ ገሃድ የወጡ መገለጫዎች አሉ፡፡ እንዲያውም የትኛውም አክራሪ ኃይል ከመዋቅር(ከመንግሥት) አካል በርታ ሳይባልና ሽፋን ሳይሰጠው የሚንቀሳቀስ እንደሌለ አማኞቹ በገሃድ ይገልጻሉ፡፡›› መቼም ይህን ያነበበ ዜጋ መረጃው የተገኘው በመንግሥት ከተዘጋጀ ሰነድ ሳይኾን በኒዮሊበራሊስት›ነት ከተፈረጁት እነ‹‹ሂዩማን ራይትስዎች›› እና ‹‹አምንስቲ ኢንተርናሽናል›› ቢመስለው አይደንቅም፡፡ ሐቁ ግን ይኸው ነው፡፡ አገዛዙ ላለፉት ኻያ ሁለት ዓመታት መንግሥት እና ሃይማኖት እንዲለያዩ ማድረጉን ሲለፍፍ ከመቆየቱም በላይ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን የዘገቡ ጋዜጠኞችን ከሥሦ ዛሬም ድረስ ፍርድ ቤት እያመላለሳቸው እንደኾነ ይታወቃል፡፡ ከዚህ አንጻር ይመስለኛል ዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን በእስር ላይ የሚገኙት የእነ አቡበበከር መሐመድ ክሥ፣ የሼኽ ኑር ሑሴን ግድያ፣ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ እየተሰነዘሩ ያሉ ውንጀላዎችንና መሰል ፍረጃዎችን አምኖ ለመቀበል የተቸገሩት፡፡ ያም ኾነ ይህ ሃይማኖትን ብቻ ሳይኾን ዕድርና ዕቁብንም ሳይቀር ‹ካልተቆጣጠርኹ ሞቼ እገኛለኹ› በሚል የቁጥጥር ልክፍት የተያዘው ኢሕአዴግ፣ በተለይም 99.6 ድምፅ አግኝቼ አሸንፌአለኹ ብሎ ካወጀበት ከምርጫ ፳፻፪ ማግሥት ጀምሮ ‹‹አናት ላይ ከተቀመጡ መሪዎቻቸው በቀር ሙሉ በሙሉ አልተቆጣጠርናቸውም›› የሚላቸውን የኦርቶዶክስ ክርስትና እና የእስልምና እምነቶችን ዋነኛ አጀንዳ አድርጎ እየሠራ ለመኾኑ በርካታ መረጃዎች አሉ፡፡ በ፳፻፫ ዓ.ም. ኅዳር ወር ‹‹የአምስት ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድና የኢትዮጵያ ሕዳሴ›› በሚል ርእስ በአቶ መለስ ዜናዊ ተሰናድቶ የተሰራጨው ጥራዝ፣ የሥርዐቱን ቀጣይ አካሔድና ይህን ኹናቴ የሚያሳይ ከመኾኑም በተጨማሪ ዛሬም ድረስ በሃይማኖት ጉዳዮች ላይ መንግሥት የሚያዘጋጃቸው ሥልጠናዎችም ኾኑ ጥናታዊ ጽሑፎች መነሻ ሐሳባቸው ይኸው ዳጎስ ያለ ጥራዝ እንደኾነ ይነገራል፡፡ ጥራዙ የእምነት ተቋማትን በተመለከተ ከገጽ 128 – 132 ያካተተው ሐሳብ፣ ለኪራይ ሰብሳቢነት ዋነኛው ምክንያት ‹‹የሃይማኖት አክራሪነት›› መኾኑን ከጠቃቀሰ በኋላ ችግሩን ‹‹ተኪ የኾነ ልማታዊ አስተሳሰብ›› በማምጣት ማስወገድ እንደሚቻል ይመክራል፡፡ ይህን ከግብ ለማድረስ ደግሞ ሚዲያዎችንና ተያያዥነት ያላቸውን ማኅበራት መጠቀሙ አዋጭ እንደኾነ ይተነትናል፡፡ የኢሕአዴግ አባላት በየእምነት ተቋሞቻቸው ያሉ ማኅበራትን በዐይነ ቁራኛ መከታተል እንዳለባቸውም ያሳስባል፡- ‹‹[የግንባሩ አባላት] ከእምነት ተቋማት ውጭ ባላቸው አደረጃጀት አማካይነት በሰፊው መሥራት አለብን››፡፡ በርግጥም የእስልምና እምነት ተከታዮች ‹‹የሃይማኖት ነጻነት ይከበር›› የሚል ተቃውሟቸውን ባጠናከሩበት ሰሞን፣ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ሙስሊም አባላቱን ለብቻ እየሰበሰበ እንቅስቃሴውን የማክሸፍ ሥራ መሥራት ግዴታቸው መኾኑን የሰበከው ከዚኹ አቶ መለስ ዜናዊ አዘጋጅተውት ከነበረው ጥራዝ ነው ብሎ መከራከር ይቻላል፡፡ ከጣልቃ ገብነት ወደ ጠቅላይ ተቆጣጣሪነት በዘወርዋራም ቢኾን በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን ሙሉ በሙሉ የሚያምነው ከላይ የተጠቀሰው ሰነድ በአገሪቱ ‹‹የሃይማኖት አክራሪነት›› መከሠቱን ካተተ በኋላ ዋነኛ ተጠያቂዎች አድርጎ ያቀረበው እንደወትሮው ኹሉ ለተደጋጋሚ መሸማቀቅ የተዳረጉትን መንፈሳዊ መሪዎችንና ማኅበራትን ሳይኾን የመንግሥት መዋቅርን ነው፡- ‹‹የመንግሥት መዋቅራችን አካል ኾነው አክራሪነቱን በድብቅም በገሃድም የሚደግፍ አካል በፌዴራልም በክልልም ከሞላ ጎደል የሚታወቁ ናቸው፡፡ እነዚኹ አካላት በተቻላቸው ኹሉ በመድረክ ጤናማ እየመሰሉ የሚኖሩ ናቸው፡፡ የፀረ አክራሪነቱን ትግል ማጧጧፍ የሚፈልገውን መዋቅር አካልም ይኹን የሕዝብ አካል በተደራጀና በመረባቸው አማካይነት ከፍተኛ ጫና የሚያሳድሩ፣ የተቋማቸውን ምቹ ኹኔታ ተጠቅመው በፀረ አክራሪነት የሚንቀሳቀሱትን አካል የሚቀጡ፣ አሉባልታ እየፈጠሩ የሚያሸማቅቁ፣ ኾን ብለው ድጋፍ የሚነፍጉና በሐሰት ምስክርም ጭምር ዜጎችን የሚያሳስሩ ናቸው፡፡ የመንግሥትን አቅሞች ተጠቅመው አክራሪነትን የሚያስፋፉና ከአክራሪነት እንቅስቃሴ ጋራ በተለያዩ ጥቅሞች የተሳሰሩ ናቸው፡፡›› እነኾም በእንዲህ ዐይነቱ የውንብድና ተግባር የተሠማሩ ባለሥልጣናት የተሰባሰቡበት፣ ውንብድናው መኖሩንም የሚያምን መንግሥት አንድም ተጠያቂዎቹን ለሕግ አሳልፎ አለመስጠቱ፣ አልያም ሥልጣኑን በፈቃዱ አለመልቀቁ በአገር ላይ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ ለመረዳት ነቢይነትን አይጠይቅም፡፡ በአናቱም ሥርዐቱ ለሕግ የበላይነት ተገዥ አለመኾኑን የሚያሳየው በዚህ ደረጃ ‹‹ችግሩን ተረድቸዋለኹ›› እያለም እንኳ፣ ዛሬም የቅጣት ብትሩን ያሳረፈው ከመዋቅሩ ጋራ አንዳችም ንክኪ በሌላቸው መንፈሳዊ መሪዎች ላይ መኾኑ ነው፡፡ በርግጥም ይህ ዐይነቱ አሠራር ከዐምባገነን አስተዳደር መገለጫዎች አንዱ ነው፡፡ ኢሕአዴግም ያለፉትን አራት ምርጫዎች ጨምሮ በተለያየ ጊዜ የዴሞክራሲም ኾነ የሰብአዊ መብትን በዐደባባይ መጣስ፣ የሐሰት ክሦችንና ፍረጃዎችን እንደ ምክንያት መጠቀም ነባር ስልቱ እንደኾነ ይታወቃል፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ እየዘረዘረ ያለው የፈጠራ ውንጀላ እና ለሙስሊሙ ‹‹መፍትሔ አፈላላጊ›› ተብለው በተመረጡት የኮሚቴ አባላት ላይ የወሰደው ዕመቃ መግፍኤ ይኸው ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ከዚህ ቀደም በተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ ስለሚፈጸመው የግፍ ግድያዎች ይሰጥ የነበረውን ምክንያት በመንፈሳዊ ሰዎችም ላይ ያለአንዳች የይዘት ለውጥ ለመጠቀም አላመነታም፡፡ እንደሚታወሰው በድኅረ ምርጫ – ፺፯ በአምቦና በኢተያ በታጣቂዎች የተገደሉትን የኦሕኮ አባላት ከተፈጥሮ ሕመም ጋራ አያይዞት ነበር፡፡ በያዝነው ዓመት ጥቅምት ወር መጀመርያ ላይ በተካሔደው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ደግሞ የምዕራብ ወለጋና አሶሳ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ኄኖክ ‹‹ቤጊ›› ወረዳ በመንግሥት ባለሥልጣናት ተፈጸመ ያሉትን ግድያ ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ተወካይ፡- ‹‹በቤተ ክርስቲያን 70 ሜትር ርቀት ላይ የሌላ እምነት ተከታዮች የራሳቸውን ቤተ ክርስቲያን እንዲሠሩ መፈቀዱን ከተቃወሙት መካከል አንድ ዲያቆን ተደብድቦ በሦስተኛው ቀን ሕይወቱ ሲያልፍ ‹በወባ በሽታ ነው የሞተው› ተብሎ ለፍርድ ቤቱ የሐሰት ማስረጃ ከዶክተሩ እንዲቀርብ ታዘዘ›› ማለታቸውን መጥቀሱ ለጉዳዩ አስረጅነት በቂ ይመስለኛል፡፡ የኾነው ኾኖ አገዛዙ በዘረጋው ግዙፍ መዋቅሩ ውስጥ ያልታቀፉ ማኅበራትንም ኾነ የሃይማኖት ተቋማትን የስጋት ምንጭ አድርጎ ማየቱ፣ በእምነት ነጻነት ላይ ጣልቃ ለመግባትም ኾነ ምንም ዐይነት ገለልተኛ ተቋማት እንዳይኖሩ ዕንቅልፍ ዐጥቶ መሥራቱን ያሳያል ብዬ አስባለኹ፤ በሚቆጣጠራቸው የኤሌክትሮኒክስና የኅትመት ሚዲያዎች ቀን ከሌት የፕሮፓጋንዳ ከበሮ የሚመታበት የ‹አክራሪነት› ፍረጃም መነሾው ይኸው ይመስለኛል፡፡ ሰነዱን ከዚህ ቀደም ካየናቸው ለየት የሚያደርገው፣ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ አሉ ከሚላቸው ወንበዴዎች በተጨማሪ የሚከሥሣቸውን መንፈሳውያን ማኅበራት በደፈናው ‹‹በክርስትና እምነት ውስጥ ያሉ›› ብሎ አለማለፉ ነው፤ ቃል በቃል እንዲህ ይላልና፡- ‹‹በማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ የመሸጉ የትምክህት ኃይሎች ጽንፈኛ የፖሊቲካ ኃይሎች አካል በመኾን በጋዜጣና በመጽሔት ሕዝባችንን ለዐመፅና ለሁከት ለማነሣሣት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡. . .በራሳችንም ኃይል እንደሌላው ሰልፍ ልንወጣ ይገባል በሚል የዐመፅና የሁከት ቅስቀሳ ለማድረግ ይፈልጋሉ፡፡›› ይህ ኹኔታ መንግሥት መንፈሳውያን ማኅበራትን ጠቅልሎ ለመቆጣጠር በመፈለጉ ለተቃዋሚዎች ያሠመረውን ‹ቀይ መሥመር› መጣሱን ያሳያል፡፡ አስገራሚው ጉዳይ ደግሞ የሃይማኖት ተቋማትን የፖሊቲካ መሣርያ አድርጎ መጠቀሙ አልበቃ ብሎት ወደ መንፈሳውያን ማኅበራቱ መዞሩ ነው፡፡ በገሃድ እንደሚታወቀው የክርስትና ይኹን የእስልምና እምነት መሪዎች በተለያየ ጊዜ ከሥርዐቱ ጎን ተሰልፈው ‹ናዳን ለመግታት› ያደረጉት አበርክቶ በቀላሉ የሚገመት አለመኾኑ ነው፡፡ በርግጥም ‹‹የቄሣርን ለቄሣር›› በሚል አስተምህሮ የሚያድሩ፣ ደመወዛቸው በምድር ያልኾኑት መንፈሳውያን አባቶች በድኅረ ምርጫ – ፺፯ ሕፃናትን ሳይቀር በጥይት የፈጀውን ሥርዐት ማውገዝ ቀርቶ መምከር ያለመፈለጋቸው ምክንያት ፍርሃት ብቻ ሳይኾን የግል ጥቅምን ታሳቢ ያደረገው ግንኙነታቸው ያሳደረው ተጽዕኖ ይመስለኛል፡፡ ከቅዱሳን መጻሕፍት ይልቅ አብዮታዊ ዴሞክራሲን ‹አዳኝ› አድርገው የመቀበላቸው መግፍኤ ይኸው ነው፡፡ ኢሕአዴግም ‹ነገረ መለኰት›ን ለሲኖዶሱና ለመጅሊሱ እስከ ማስተማር ድረስ የደፈረው የእነርሱ ለሁለት ጌታ መገዛት ነው – ለገንዘብ እና ለጌታ፡፡ የሲኖዶሱ እና የመንግሥት ፍጥጫ በኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ሕገ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ከፍተኛውን ሥልጣን የሚይዝ ሲኾን ፓትርያርክንም የመሾምና የመሻር ሥልጣን አለው፡፡ ኾኖም ይህ የላዕላይ መዋቅር እስከ አቡነ ጳውሎስ ኅልፈት ድረስ ለእርሳቸውም ኾነ ለሥርዐቱ ሰጥ ለጥ ብሎ የሚገዛ ጥርስ የሌለው አንበሳ በመኾኑ ለትችት ከመዳረጉም በላይ በምእመናን ዘንድ ለመንፈሳውያን አባቶች የሚሰጠው ክብርም ተነስቶት ቆይቷል፡፡ ይኹንና በያዝነው ዓመት ጥቅምት ወር መጀመርያ በተካሄደው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ፴፪ኛ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ከመንግሥት የተወከሉ ሓላፊዎች÷ ‹‹የብዝኃነት አያያዝ አክራሪነት/ጽንፈኝነት ዝንባሌዎቹና መፍትሔዎቹ›› በሚል ርእስ ያቀረቡትን ጥናት ተከትሎ ስድስት ጳጳሳት ቀድሞ ባልታየ መልኩ ጠንካራ ተቃውሞ ማቅረባቸው፣ በብዙዎች ዘንድ የሃይማኖት መሪዎች ለመንፈስ ልዕልና ሊገዙ ይኾን? ከምድራዊው ይልቅ ሰማያዊውን ሊመርጡ ይኾን? ‹‹እመን እንጂ አትፍራ›› የሚለውን አስተምህሮአቸውን ሊተገብሩ ይኾን? የሚል ጥያቄ አጭሯል፡፡ በዕለቱ የመጀመርያው ተናጋሪ የነበሩት የሰሜን ወሎና ዋግ ኽምራ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቄርሎስ በጥናቱ ላይ መቻቻል አስመልክቶ የቀረበውን ድምዳሜ እንዲህ ሲሉ ነበር ያጣጣሉት፡- ‹‹ይኼ አክራሪነት፣ ጽንፈኝነት የሚለውን ቋንቋ እናንተው ናችኹ ያሰማችኹን፤ ከዚህ በፊትም አይታወቅም፣ በደርግም ይኹን በሌላ፡፡ እንደገና ደግሞ ብዙ ጊዜ ጽንፈኝነት፣ አክራሪነት እያላችኹ ዕድሜ ሰጥታችኹ ያበለጸጋችኋቸው እናንተው ናችኹ፡፡›› በርግጥም አቡኑ የተቹት ሥርዐቱ የፕሮፓጋንዳው ፋሽን ያደረገውን ‹‹መቻቻል››ን ብቻ አይደለም፤ ‹‹በመቃብሬ ላይ ነው የሚሻሻለው›› የሚለውን የመሬት ፖሊሲንም ነው፡፡. . . ‹‹በፊት መሬትም ሕዝብም የነገሥታቱ ነበር፤ አሁንስ የማን ነው? ይልቁንም ከአንድ ቤት ‹ግድግዳው የቤቱ ባለቤት ነው፤ ሳሎኑ የመንግሥት ነው› የሚለው ዐዋጅ የአሁን አይደለም እንዴ? ለኢትዮጵያዊነቱ ዋስትና የለውም፤ ይኼ የእኔ ነው የሚለው ከሌለ ምንድን ነው? ይህች የእኔ የኢትዮጵያዊነቴ መገለጫ ናት ካላለ ምንድን ነው ኢትዮጵያዊነት? አሁንም መሬቱም ሕዝቡም የእናንተው ኹኖ ሳለ ለፊቱ፣ ለነገሥታቱ መስጠታችኹ በምን ተመልክተውት ነው?›› የደቡብ ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ እንድርያስም በሚያስተዳድሩት አካባቢ ያለውን የመንግሥት ጣልቃ ገብነትና ተጽዕኖን ከዘረዘሩ በኋላ ለተሰነዘረው ፍረጃና ማሸማቀቂያ እንዲህ የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡- ‹‹የተበደለ ሰው ሲናገር ‹ፖሊቲካ ተናገረ› እየተባለ የውሸት ውሸት ሲያተራምሱን የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው፡፡. . .እንዴ! የመንግሥት ሥልጣን የተረከቡ ወንድሞች የእኛን አፍ፣ የእኛን አንደበት ብቻ ነው እንዴ የሚጠብቁት፤ ለሌሎች ሞራል ይሰጣሉ ማለት ነው?. . .ለምንድን ነው ግን በሽፋንነት የምትጠቀሙብን? መንግሥት እኛን ሽፋን አድርጎ ነው ሲበዘብዘን የምንኖረው፡፡ ሌባውም ቀጣፊውም ሰርጎ ገቡም ሲያጭበረብረን ሲያታኩሰን መንግሥትን ሽፋን አድርጎ ነው፡፡›› የወላይታ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅም በተመሳሳይ መልኩ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን ቤተ ክርስቲያኗ ስትቃወም ጉዳዩን ወደ ፖሊቲካ እየቀየሩ ማስፈራራቱ እንደተለመደና ለቀብር ማስፈጸሚያ የሚኾን መሬት ከመስተዳድሩ በሚጠየቅበት ጊዜ የሚሰጠው መልስ በሐሰት መወንጀል እንደኾነ ከገለጹ በኋላ ጉዳዩ መፍትሔ ካላገኘ ሊከተል ስለሚችለው ስጋታቸውን ተናግረዋል፡- ‹‹ ‹የፖሊቲካ ጉዳይ ነው፤ ሕዝብን በሃይማኖት ሽፋን ታንቀሳቅሳላችኹ› እየተባልን እየተሸማቀቅን ያለንበት ኹኔታ ነው ያለው፡፡ ይህን እንዴት ታዩታላችኹ? መቻቻልስ የሚመጣው ከምን አኳያ ነው? ዝም ብለን የምንቀመጥ ከኾነ ምናልባት ሓላፊነት ለመውሰድ ስለሚከብደን ይህን ወርዳችኹ እንድትፈትሹ ለማለት ነው፡፡›› (በነገራችን ላይ የአጠቃላይ ጉባኤው ዓመታዊ ስብሰባ በተጠናቀቀ ማግሥት ከማኅበረ ቅዱሳን አመራር ሦስት አባላት ወደ ፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ተጠርተው ዶ/ር ሽፈራውን ጨምሮ ከሚመለከታቸው ሓላፊዎች ጋራ ውይይት ማድረጋቸውን ከመሥሪያ ቤቱ ምንጮቼ ሰምቻለኹ፡፡ ሚኒስትሩ ከማኅበሩ አመራሮች ጋራ ለመወያየት የተገደዱት ካልተጠበቀው የሲኖዶሱ አባላት ድፍረት ጀርባ ‹የማኅበረ ቅዱሳን እጅ አለበት› የሚል ጥርጣሬ በመያዙ ነው፡፡ በውይይቱም ላይ የተንጸባረቀው የአባላቱ መለሳለስ፣ ማኅበሩን አክራሪ ብለው እንደማያምኑና ከዚህ ቀደም የተሰራጩት ወንጃይ ሰነዶችን ሳይቀር ‹አናውቃቸውም› እስከማለት የደረሰ እንደነበር አረጋግጫለኹ፡፡ ይኹንና ይህ እሳት ማጥፊያ ስልት ከሥርዐቱ ጋራ የቆየ መኾኑ ይታወቃል፤ የማኅበሩ አመራርም ይህ ይጠፋዋል ብዬ ባላስብም፤. . .) የኾነው ኾኖ [በአጠቃላይ ጉባኤው ዓመታዊ ስብሰባ] ከፌዴራል ጉዳዮች ከመጡት ሦስት ተወካዮች መካከል አቶ ገዛኽኝ ጥላሁን አብዛኛውን ጥያቄ በተመለከተ የሰጡት ምላሽ የወከሉት መንግሥት ዛሬም በተሳሳተ ታሪክ ንባብ እያሸማቀቀ፣ እያስፈራራ፣ ሕግን እየጠመዘዘ፣ እስር ቤት እየከተተ. . . የፖሊቲካ ጥቅሙን ማስከበር ላይ ያተኮረ መኾኑን ያሳያል፡፡ ሓላፊው ማስጠንቀቂያውን ያስተላለፉት እንዲህ በማለት ነው፡- ‹‹መጀመርያ ግንዛቤ ላይ እንሥራ በሚል ርምጃ አልወሰድንም፡፡ ኮሽ ባለ ቁጥር ወደ ቃሊቲ መፍትሔ አይኾንም፡፡›› . . .‹ቃሊቲ›ን ምን አመጣው? መቼም ለጣልቃ ገብነቱ ከዚህ የበለጠ ማሳያ መፈለግ ‹ዐውቆ የተኛን. . .› እንደመኾን ነው፡፡ ‹‹መንግሥት እና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው›› ብሎ መከራከሩም ጊዜ ያለፈበት ፕሮፓጋንዳ ይመስለኛል፡፡ እናም የተሻለው መንገድ ከላይ በጠቀስኹት ሰነድ ‹‹በየማእከላዊ ኮሚቴው በሚካሄደው የስምሪት ተግባር በፀረ አክራሪነት ትግል ላይ ያለው የእያንዳንዱ ግለሰብ ቁመና መፈተሽ አለበት›› ተብሎ የተገለጸውን ማሳሰቢያ በፍጥነት በመተግበር፣ በቅድሚያ ራስን ከአክራሪነትና አሸባሪነት ማራቅ ነው፡፡ ማረጋገጫ የማይቀርብበትን አፈ ታሪክንም እየለቃቀሙ በአንድ ሃይማኖት ላይ መለጠፉ አስተማሪ አይመስለኝም፡፡ ከዚህ ባለፈ ‹‹የሃይማኖት ኮማንድ ፖስት አቋቁመን ለችግሩ እልባት እንሰጣለን›› የምትሉት ጉዳይ በቀጥታ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ እጁን ማስገባቱን በዐደባባይ ከማመን ያለፈ የፖሊቲካ ጠቀሜታ አይኖረውም፡፡ ጳጳሳቱም ኾኑ ሼኾቹ ሓላፊነትና ግዴታቸው ሰማያዊውን መንግሥት መስበክ እንጂ ከሰላይ አለቆችና ከፖሊስ አዛዦች ጋራ ቢሮ ዘግተው የመንፈስ ልጆቻቸውን ‹‹ትምክህተኛ››፣ ‹‹አሸባሪ››፣ ‹‹አክራሪ››. . .እያሉ እንዲፈርጁ መፈታተኑ ያልታሰበ ሕዝባዊ ቁጣ መቀስቀሱ አይቀርም፡፡

Friday, 8 November 2013

የግንቦት 7 መሪዎችን ለመግደል የተጠነሰሰው ሴራ ከሸፈ

የግንቦት 7 መሪዎችን ለመግደል የተጠነሰሰው ሴራ ከሸፈ በኢትዮጵያ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ሃለፊ በአቶ ጌታቸው አሰፋ እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ የብራዊ ደህንነት አማካሪ በአቶ ጸጋየ በርሄ ቁጥጥር የተመራና በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌና በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል መሪዎች ላይ የተቀነባበረው የግድያ ሙከራ ከሸፈ። ESAT የግንቦት 7 መሪዎችን ለመግደል የተጠነሰሰው ሴራ ከሸፈ በኢትዮጵያ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ሃለፊ በአቶ ጌታቸው አሰፋ እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ የብራዊ ደህንነት አማካሪ በአቶ ጸጋየ በርሄ ቁጥጥር የተመራና በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌና በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል መሪዎች ላይ የተቀነባበረው የግድያ ሙከራ ከሸፈ። ከግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው ለግድያ የተላከው ሙሉቀን መስፍን የተባለው ግለሰብ በትናንትናው እለት በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፣ በእየደረጃው ከሚገኙ የደህንነት ሀላፊዎች ጋር በስልክ ሲያደርግ የነበረው የስልክ ለውውጥ በህዝባዊ ሀይሉ የመረጃ ክፍል ሲቀዳ ቆይቷል። ወያኔ-ኦ-ሚሊኒየም በሚል የተመራው የግድያ ዘመቻ -በነገው እለት ጥቅምት 30/2006 ዓም ሊካሄድ ታቅዶ እንደነበር የድምጽ መረጃው ያመለክታል። ( ) የግንቦት 7 ህዝባዊ ሀይል ሰራዊት የምረቃ በአል በነገው እለት የሚካሄድ መሆኑን መነሻ በማድረግ በእለቱ በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል መሪዎችንና የኤርትራ ባለስልጣናትን ለመግደል የታቀደው ዘመቻ ከመነሻው ክትትል ሲደረግበት ቆይቶ፣ በፍጻሜው ዋዜማ ላይ ሲድርስ ሙሉቀን መስፍን የተባለውን ለግድያ የተላከውን ግለሰብ ህዝባዊ ሀይሉ በቁጥጥር ስር በማድረግ ወያኔ-ኦ-ሚሊኒየም የተባለው ኦፕሬሽን ከሽፏል። የድምጽ መረጃውን ኢሳት ዌብሳይት ላይ ተከታተሉ

ኢህአዴግንና ተቋማቱን ለምን ማመን ተሳነን?

በእኛ አገር መንግስትና ፓርቲን መነጠል አይቻልም፡፡ህገ መንግስቱ ሳይቀር በብዙ አንቀጾቹ የገዢው ፓርቲ ፕሮግራም ግልባጭ መሆኑ ትስስሩን ላቅ ያደርገዋል፡፡ስለዚህ መንግስት ሲለወጥ ባንዲራ፣ህገ መንግስት፣ብሄራዊ መዝሙር እንቀይራለን፡፡የመንግስት ስርዓት መዘርጋት አለመቻላችን ያመጣብን ጣጣ ልንለው እንችላለን፡፡ ህዝቡ በፓርቲው እምነቱን አጣ ማለት መንግስትንም አያምነውም ተብሎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ኢህአዴግ በኢትዮጵያ የመንገስታት ታሪክ አመኔታ በማጣት ረገድ ግምባር ቀደሙ ይመስለኛል፡፡እምነት የጠፋበት አጋጣሚም ከኢህአዴግ የትጥቅ ትግል ቆይታ ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ደርግ የያኔዎቹን አማጺያን ወንበዴ፣አገር አስገንጣይ በማለት ይፈርጃቸው ነበር፡፡ከተሜው የደርግን ፕሮፓጋንዳ ሲጋት በመቆየቱ ተጋዳላዮቹ ወደ ከተማ ሲገቡ የተቀበላቸው በፍርሃት ድባብ ታስሮ ነበር፡፡ ትግራይን ነጻ ለማውጣት በረሃ የገቡት የትግራይ ልጆች የህዝቡን አመኔታ ለማግኘት የሐውዜንን ድብደባ ለደርግ የተሳሳተ መረጃ በመስጠት የቪዲዮ ካሜራ በማዘጋጀት የተዋጣለት ፊልም መቅረጻቸውና ለጊዜውም ቢሆን በዚህ ምክንያት የትግራይ ህዝብን ድጋፍ ለማግኘት ቢበቁም እያደር ግን የሐውዜን ምስጢር አፈትልኮ መውጣቱ ተአማኒነታቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ፈጥሯል፡፡በግሌ እምነት የሰጧቸው ዋና ዋና ተግባሮቻቸው የሚከተሉት ናቸው —- በትግራይ መንግስት የወረሳቸውን ቤቶች በመመለስ ለሌሎቹም ይህንን እንደሚያደርጉ ቃል ቢገቡም ቃላቸውን መጠበቅ አለመቻላቸው —- የአልባንያን ሶሻሊዝም ተጋዳላዮቹን ይግት የነበረው ኢህአዴግ አዲስ አበባን ለመቆጣጠር ከጫፍ በደረሰበት ወቅት የምዕራባዊያንን ድጋፍ ለማግኘት ራሱን ነጭ ካፒታሊስት በማድረግ መጥራት መጀመሩ ርዕዮት አልባ አድርጎታል፡፡ይህም በሚከተለው የፖለቲካ ፍልስፍና አቋመ ቢስ ስላደረገው የገዛ ታጋዮቹን እምነት አሳጥቶታል፡፡ —–በበደኖ፣በአርባጉጉና በአሰቦት በተፈጸሙ አንድ ብሄር ላይ ያነጣጠሩ ጭፍጨፋዎች ኦህዴድና/ኦነግ ሃላፊነት በመውሰድ መጠየቅ ይገባቸው የነበረ ቢሆንም ኢህአዴግ የኦህዴድን እጅ እንደ ጲላጦስ በማጠብ የደሙን ዋጋ ኦነግ ላይ መጣሉ በኦሮሚያ አማኝ አሳጥቶታል፡፡ —– የመምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት የነበሩትን መምህር ዶክተር ታዬ ወ/ሰማያትን የ17 ዓመት እስራት ሲያከናንብ በዜና ያስደመጠው ‹‹ታጣቂ ቡድን እያደራጁ ነው››ብሎ የነበረ ቢሆንም በፍርድ ቤት ይህንን ማስመስከር አልቻለም፡፡ —–እነ ርዕዮት አለሙ በታሰረበት ቅጽበት ምሽቱን በኢቴቪ የተደመጠው ዜና ‹‹በመንግስት መሰረተ ልማቶች ላይ አደጋ ለማድረስ ሲያሴሩ ተገኝተዋል፡፡››ተብሏል፡፡ፍርድ ቤት ጋዜጠኞቹ በቀረቡበት ወቅት ግን በኢቴቪ የቀረበው በክሳቸው ውስጥ አልተካተተም፡፡ይህም አመኔታን የሚያሳጣ ድርጊት ሆኖበታል፡፡ —-የ1997 ምርጫን ነጻና ፍትሃዊ አደርጋለሁ በማለት ቃል የገባው ኢህአዴግ ለ200 ሰዎች ዕልቂት መንስኤ የሆነን ኮሮጆ ግልበጣ ፈጽሟል፡፡ —-የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቢሮን ለአመታት ተቆጣጥረውት የነበሩት አቶ ስዮም መስፍን የኢትዮ ኤርትራ የድንበር ኮሚሽን ፍርድን ለኢትዮጵያ ህዝብ ባስደመጡበት ወቅት ‹‹እንኳን ደስ አለን ብዙ ሺህ የህይወት ዋጋ የከፈልንባት ባድመ ለእኛ ተፈረደች››በማለት ህዝቡ ደስታውን በሰላማዊ ሰልፍ እንዲገልጽ ቢያደርጉም እውነታው ግን ባድመ ለኤርትራ መወሰኗ ነበር፡፡ —- በተለያዮ ቦታዎች ስለተፈጸሙ የቦንብ ፍንዳታዎች መንግስት ተቃዋሚዎችን ተጠያቂ ቢያደርግበትም ዊኪሊክስ በቅርቡ በለቀቀው መረጃ መንግስት ሆን ብሎ እንዲህ አይነት ድራማዎችን እነደሚሰራ አጋልጧል፡፡እስከ እናንተ ለምን መንግስትን እንደማታምኑ ምክንያታችሁን አካፍሉን፡፡