Friday, 22 May 2015
የወያኔ በጉልበት የምረጡኝ ዘመቻ (ከ አዲስ ብርሃኑ)
ንብን ምረጡ ማለት ከጀመሩ ሰነባብተዋል ። ለአገር እድገት፤ ለብለጽግና ፤ለእኩልነት ፤የተጀመረውን እድገት፤ ለማስቀጠል እያሉ...... እያሉ.... መንገድ ተሰራ፤ ህንጻ ተሰራ ፤ስልጣኔ ገባ ፤ይህን ሁሉ በዘመነ ኢህአዲግ ነው ብለው ይናግሩናል። ይህን ማለታቸው ጥሩ። ምንም ተቃውሞ የለኝም ።
አንድ ኢትዮጵያዊ የፈለገውን የመከተል እና የማመን ጉዳይ ነው ። ሌላም ሌላም ይጨምሩ ስለነሱ ማውራት ሳይሆን ለኛም እድል ስጡን እኛም ስለ ኢትዮጵያ የምነለው ነገር አለ ስለ ወያኔም የምንነቅፈው ነገር አለን ይህ ነው ቁምነገሩ ፍርድ እና ውሳኔውን ለሕዝብ በመተው ሕዝብ የመረጠውን እንዲመራው ማድረግ ግድ ይላል።
ወያኔ ኢትዮጵያን ማስተዳደር ከጀመረ የማይታወቁና የማይፈለጉ ሃሳቦች እና ነገሮች ገብተዋል። ያም ህዝብ ወዶ ሳይሆን በግድ የህዝብ ሃሳብ ተጥሶ የአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ሃሳብ እና አላማ እየተንጸባረቀ ነው። ባንዲራው ላይ ከተለጠፈችው ኮከብ ብንጀምር ከ90%
በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን የኮከብ ምልእክት አርማ ያለውን ባንድራ አይቀበለውም ።የኮከቡ ትርጋሜውም ወይም አላማው ሌላ ነው። ኮከባ የምትገልጸው የስይጣንን አምላኪወችን ሲሆን በኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ የተለጠፈው ኮከብ ሶስት ትረጔሜ አለው እነሱም እንደሚከተሉት ናቸው።
1 የኢትዮጵያን ህዝብ በሰይጣናዊ ሃይል ለማፍዘዝ ፦
2 ስይጣን ፍቅር ስለማያውቅ መለያየት እና መጣላት በኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ ለማስረጽ፦
3 የኢትዮጵያ ህዝብ አውቆም ሆነ ሳያውቅ የሰይጣን ምልክት የሆነውን የሰይጣንን ምልክት እንዲያውቅ እና ክፋታዊ የሰይጣንን አሰራር እንዲለማመድ ለማድረግ ነው።
በዚህ ዙርያ ትንሽ ብዬ ወደ ወያኔ ወደሆነችው አርማ እሄዳለው
በኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔ ከገባ ጀምሮ የአገሬ ህዝብ ውስጥ ብዙ ክፋት አብሮ ገብቱአል። ለዚህም ኮከባ የወለደችው ወይም ያፈራችው ፍሬ ስናይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ፍቅር ጠፍታል ። የኢትዮጵያ ህዝብም ብርን እና ጥቅምን አምላኪ ከመሆኑ የተነሳ ወንድም ወንድሙን ፤እህት እህቷን፤ ወላጆች ልጆቻቸውን ፤አሳልፈው ይስጣሉ። ሁሉም ስልጣን ናፋቂወች ሆነዋል። አባት ከልጁ፤ እህት ከወንድም፤ ዘር ከዘር ፤ጎሳ ከጎሳ ፤ሃይማኖት ከሃይማኖት፤ ኢትዮ ጵያ ውስጥ ከእለት ወደ እለት ግጭቶ ች እየተበራቱ ጥላቻወች በሰፊው እየታዩ ነው። እናት ሌባ ልጅ ቀማኘ የሚለው ቢሄል (አባባል) በአሁን በዘመነ ወያኔ እያየነው ነው። መሪዎች ተብዬዎች ሌባ ሎሌዎች ደግሞ ቀማኞች የሆነች ሐገር ከመሰለች ሰነባብታልብ ።የጠፋው ፍቅር እንዲመለስ እና የተወሰድብን ክብር እንዲመጣ የወያኔ አዚም የሆ ነችውን ኮ ከብ ከኢትዮጵያ ምድር ማጥፋት መቻል አለብን። ይህ ኮከብ ቢሄር ቤሄረስቦችን የሚወክል ሳይሆን ጥላቻና መለያየትን የሚያሰፍን ፍቅርን የሚያጠፋ የሰይጣንን ስረአት የመከተል እና የሠይጣንን አርማ ከፍ አድርጎ የማሳየት ስራ ነው።
ወደ ንብ ስንመጣ ደሞ ንብን ምረጡ... ንብን ምረጡ ...እያሉ መለፍለፍ ከጀመሩ ሰንብተዋል መረዟን ብቻ እንጂ ማሯን የማናየውን ንብን ፤በየአገሩ እየዞረች እሾኴን የምታራግፈዋን ንቧን፤ ማሯን ለንጉሶቻ ብቻ የምታበላዋን ንቧን ፤ህብረተሰባን ማሯን ታበላን ይሆን ብሎ የሚጠብቃት ተስፈኘዋን ንቧን ፤ይችን ንብ ነው ምረጡ የሚሉን።
የንብ በሀሪ የአንድ ቀፎ ንብ ከሌላ ቀፎ ንብ ጋር በፍጹም አይሰማማም ተሳስታ አንዷ ንብ ወደሌላ ቀፎ ከሄደች ይገድሏታል። ወያኔም ልክ የንብ በሀሪ ነው ያለው። ከወያኔወች ድርጅት ውጪ የሌላ ድርጅት የሆነ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲኖር አይፈለግም ።
ንቦች ማራችውን የሚሰሩት ለራሳችው እና ለንጉሳ ቸው ብቻ ነው። ወያኔዎችም የሚሰሩት ለራሳችው እና ለሹማምቶቻችው ብቻ ነው።
ንቦች ለማር መስሪያ እንዲሁም ለቀፎ አገልግሎት የሚሆነውን በሙሉ የሚጠቀሙት ክቀፎአቸው ወጥተው በሰአት 100 ኪ. ሜ ያህል
በመብረር ከአካባቢያችው ስብሰበው ወደቀፎአቸው የገባሉ። ወያኔዎቸም የኢትዮጵያን ንብረት በሙሉ በሁሉም አቅጣጫ በመዘዋወር እየዘረፉ ለራሳቸው ያክማቻሉ። ንቦች የራሳቸው ባልሆነ ነገር ማራቸውን እየሰሩ የሌላ ቀፎ ንብ ግን ወደነሱ ቀፎ እንድትገባ አይፈልጉም ወያኔም ምንም ቅሬታ በሌላችው ስዎች የሌላውን ህብረተሰብ ሃብት ለመጠቀም ይስበሰባሉ። ሊላው ህብረተሰብ ወደ እነሱ ሲጠጋ ግን ያጠፉታል ።ስለዚህ የንብን ማር መብላት የሚችለው የቀፎወቹ ንቦች ብቻ ናቸው። የኢትዮጵያንን ሃብት እየበላ እና እየተጠቀመ ያለው ብቻውን ወያኔ ነው።
ኢትዮጵያ ማር ነች ማርን ደግሞ ሁሉም ይፈልጉታል አንድም ለመብላት አንድም ለመድሃኒት። ማር መብላት ካማሮት ወደ ንብ ቀፎ ባዶ እጅ አይኬድም እንደጭስ ያለ መከላከያ እና ማሩን መቁረጫ ቢላ ያስፈልጋል። ካለበለዝያ ግን በመርዝ ተወግተው ይሞታሉ። ወያኔም እንደዚሁ ነው የኢትዮጵያን ሃብትና ንብረትን የብቻው አድርጎ ማስተዳደር ከጀመረ ሰንብታል ስለዚህ ኢትዮጵያ የምትባለው አገር የወያኔ ብቻ መስሎ ከታያቸው ሰንብታል። የኢትዮጵያ ሃብት የኢትዮጵያን እንጂ የጥቂቶች ብቻ አይደለችም ብሎ ለመጠቀም እና ለሁሉም ለማዳረስ ባዶ እጅ ተኪዶ አይሆንም ።በባዶ እጅ ከተኬደ በመረዛቸው ወግተው ስለሚገሉ መከላከያ አድርገን ኢትዮ ጵያን ማዳን ግድ ይለናል። ስለዚህም ምርጫ ..ምርጫ.... የሚለው የወያኔ የማደናገርያ ዘዴ ነው እና ይህ ምርጫ አልጫ እንደሆነ እና ትርጉም የሌለው መሆኑን ልንረዳው ይገባል። አልጫ የሆነው ምርጫ የሚለወጠው አልያም የጣፈጠ የሚሆነው የሁሉም ኢትዮጵያዊ የነቃ ተሳትፎ ሲያደርግ ነው። ንብን በማጥፋት በመርዙ ከመወጋት እና ከመሞት የኢትዮጵያ ሕዝቡ ነጻ ሁኑ። ባንዲራው ላይ ያለችውን ኮከብ በማስወገድ የሰይጣንን መንፈስ የኢትዮጵያ አርማ ከመሆን እንከላከል እላለው።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!!!!
ከ አዲስ ብርሃኑ
Email.. berhanu.addis@yahoo.com
Friday, 15 May 2015
በፍርሃት ውስጥ ያለው የኢሕአዴግ ሥርዓት የማዕከላዊ ዕዝ ወታደሮች ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ መመሪያ አወረደ!
የኢህአዴግ ስርአት የማእከላዊ እዝ ወታደሮች ከቦታ ወደ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ መምሪያ እንዳወረዱላቸው ምንጮቻችን ገለፁ ሲል የደህሚት ድምጽ ዘገበ:: በአዲ-ኮኮብ የሰፈሩት የማእከላዊ እዝ የበታች አመራር ወታደሮችና ተራ ወታደሮች ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር እንዳይገናኙና ወደ አዲ-ዳዕሮና ሸራሮ እንዳይንቀሳቀሱ ተከልክለው እንደሚገኙ የገለጸው የደህሚት ድምጽ እነዚህ የበላይ አመራሮች ሰራዊቱን በመሰብሰብ በአዲ-ዳዕሮ፤ አዲ ነብሪ ኢድ፤ አዲ-ሃገራይ፤ ሸራሮና አካባቢው በአጠቃላይ በአካባቢው የሚገኝ ህብረተሰብ የትህዴን አባል ሰለሆነ የምናጣራው ነገር አለን መንቀሳቀስ ክልክል ነው በማለት ትእዛዝ እንዳወረዱላቸው ለማወቅ ተችሏል። በተጨምሪም- ወታደሮቹ በአካባቢው ህብረተሰብ ላይ ጥላቻ እንዲያሳድሩና ከሱ ጋር እንዳይወግኑ የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ቅስቀሳ ሲሰጥ የሰነበተ ሲሆን ስርአቱ ከህዝብ ተነጥሎ በጠምንጃ ሃይል ብቻ የቆመ እንደሆነ በሚገባ ሰለሚያውቅ ወታደሮቹ ደግሞ ስርአቱን በመተው ከህዝባቸው ጋር እንዳይወግኑ በመስጋት የመነጨ መሆኑን ወታደሮቹ በሚገባ እንደተረዱት ለመረጃ ምንጩ የደረሰው መረጃ አስረድቷል።
Thursday, 7 May 2015
የቁልቁለቱን ጉዞ እናስቁም፤ ውርደት ይብቃን!!!
የህወሓት አገዛዝ ፋሽስታዊ ባህርያት እያደር መረን እያጣ፤ ነውረኛ እየሆነ መጥቷል። በአሳለፍነው ሣምንት ብቻ እንኳን አስነዋሪ ይዘት ያላቸው ሁለት ፋሽስታዊ ክስተቶችን አስተውለናል።
አንዱ በምርመራ ስም በታሳሪዎች ላይ የሚደረገው አሳፋሪ ሰቆቃ ነው። በገላቸው በሚያፌዙና በሚሳለቁ ተቃራኒ ፆታ መርማሪዎች ፊት ለሰዓታት ተመርማሪዎች ራቁታቸውን እንዲሆኑ የሚደረግበት እና እየተፌዘባቸው የሚደበደቡበት ሥርዓት መኖሩ የጉዳቱ ሰለባዎች ይፋ ሲያወጡ እፍረቱ ለመርማሪዎቹ ብቻ ሳይሆን ይህንን ጉድ ተሸክመን ለኖርነው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ነው። በተለይም ደግሞ እንዲህ ዓይነት ክብረነክ ሰቆቃ በሴቶች ላይ እየተፈፀመ መሆኑን ስንሰማ አገራዊ ውርደቱ ያሸማቅቀናል። እንዲህ ዓይነቶችን በሰው ስቃይና እፍረት የሚዝናኑ ጉዶችን ተሸክመን የምኖር መሆናችን ሁላችንን ያዋርደናል። ይህንን አስነዋሪ “የምርመራ ዘዴ” ያጋለጡት የዞን 9 ብሎገሮች፣ ጋዜጠኞችና ፓለቲከኞች ክብርና ሞገስ የሚገባቸው ጀግኖች ሲሆኑ የተዋረዱት እነሱ ሳይሆኑ እኛ ኢትዮጵያዊያን መሆናችን ሊሰማንና “ውርደት በቃ” ልንል ይገባናል።
ሁለተኛው አሳፋሪ ድርጊት ደግሞ ወገኖቻችንን በግፍ ባረደው አይሲስ በተሰኘው አሸባሪ ድርጅት ላይ የህወሓት አገዛዝ የተለሳለሰ አቋም ወስዷል ብለው ራሱ ህወሓት በጠራው ሰልፍ ላይ ተቃውሞዓቸውን ባሰሙ ወጣቶች ላይ አገዛዙ የወሰደው የኃይል እርምጃና ከዚያም ወዲህ እየተደረገ ያለው ነገር ነው። አገዛዙ ለፕሮፖጋንዳው ይጠቅመኛል ብሎ በጠራው ሰልፍ ወጥተው ተቃውሞዓቸውን የገለፁ ወጣቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተደብድበዋል፤ በጅምላ ወደ እስር ቤቶች ተግዘዋል። የአገዛዙ ካድሬዎች ወገኖቻችንን የፈጀውን አይሲስን በመቃወም ፋንታ የራሱ የህወሓትን ውል አልባ ህግ አክብረው በመንቀሳቀስ ላይ ያሉትን ሰማያዊ ፓርቲ፣ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን እና አረና ፓርቲን እየወነጀሉ መሆኑ አጅግ አሳፋሪ ነገር ነው። የአይሲስን አረመኔአዊ ድርጊት ከኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ጋር ለማገናኘት በህወሓት የደህንነት ቢሮ አማካይነት እንቅስቃሴ መጀመሩ እየተሰማ ነው። ለወጣቱ በብዛት መሰደድ በምክንያትነት የሚያቀርቡት ደላሎችን መሆኑ አላዋቂነት ሳይሆን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ቅራኔው በኢትዮጵያዊያን መካከል እርስ በርስ እንዲሆን ያለመ መሠሪነት ነው። ከዚህም አልፎ የትግራይ ወጣቶችን ነጥሎ በመሰብሰብ “ትምክህተኞች ሊበሉህ ነውና ታጥቀህ ሳይቀድሙህ ቅደም” እያሉ መቀስቀስ በመንግሥት ደረጃ የእርስ በርስ እልቂትን ከማደራጀት ተለይቶ አይታይም። የሥርዓቱ ይሉኝታ ቢስነት የደረሰበት ዝቅጠት ገላጭ ከሆኑ ነገሮች አንዱ “እስከምርጫ መጨረሻ ድረስ ልጆቻችሁን አስረን እናቆይላችሁ” እያሉ ወላጆችን እስከመጠየቅ መድፈራቸው ነው።
ከላይ በአጭሩ የተዘረዘሩት ኩነቶች የሚያረጋግጡት ህወሓት የተማከለ አመራር አጥተው መንገድ የጠፋቸው፤ ሆኖም ግን እጃቸው ውስጥ የገባው ስልጣንና ሀብት ላለማጣት ምንም ነገር ከማድረግ የማይመለሱ አውሬዎች ስብስብ መሆኑ ነው። እንዲህ ዓይነቱን የአውሬዎች ስብስብ የሚገዛው የህግም ሆነ የሥነ-ምግባር ገደብ የለም። ህወሓት እስር በርሳችንን አባልቶ አገራችንንና ሕዝቧን ወደ ማንወጣው አዘቅት ከመክተቱ በፊት ራሱ ህወሓትን ማስወገድ እና በምትኩት ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን መገንባት የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው። ይህ ካላደረግን አሁን በወህኒ ቤቶች የሚደረገው ዜጎችን ልብስን አስወልቆ የማዋረድ አስነዋሪ ተግባር ነገ በአደባባዮች የማይደረግ ስለመሆኑ ምንም ማረጋገጫ የለንም። ይህ ትውልድ ኃላፊነቱ ካልተወጣ ህግን አክብረው ከአገዛዙ የተለየ ሀሳብ እናራምዳለን የሚሉ ወገኖቻችን በሙሉ አደጋ ውስጥ ናቸው። በህወሓት መሠሪ ተግባራት ሳቢያ በክርስትናና እስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን መካከል ያለው መግባባት እንዲሻክር እየተደረገ ነው። ዜጎችን በማዋረድ የሚደሰት አገዛዝና ለመዋረድ የፈቀደ ሕዝብ እስካለ ድረስ የቁልቁለቱ ጉዞ መጨረሻ የለውም። ይህንን ማስቆም ያለብን እኛ ሁላንችንም ነን። በአደባባይ መደራጀት ሲከለከል በምስጢር መደራጀትን መልመድ የኛ ኃላፊነት ነው። የኢትዮጵያ አርበኞች ድል መታሰቢያ በዓልን ስናከብር ከቀደምቶቻችን ልንወርስ ከሚገቡን እሴቶች አንዱ ለክብራችን ዋጋ መክፈል ያለብን መሆኑን ጭምር ነው። የኢትዮጵያዊያን ክብር በወያኔ ሲዋረድ እያየን ዝምታን ከመረጥን ከዚህም የባሰ እንዲመጣ መፍቀዳችንን እንወቀው።
አርበኞች ግንቦት 7:የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የዜጎችና የአገር ውርደት ይብቃ! በተባበረ ክንድ ህወሓት ይወገድ፤ በምትኩም ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመመሥረት መሠረት እንጣል፤ ይህንን ታላቅ ኃላፊነት ለመወጣት በኅብረት እንነሳ ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
Source www.patriotg7.org
Subscribe to:
Posts (Atom)