Friday, 27 March 2015

የኛ የኢትዮጵያውያን ጥያቄ ስር ነቀል አብዮታዊ ለውጥ ጥያቄ ነው

ኢትዮጵያውያን ለነጻነታችን ዋጋ መክፈል የጀመርነው ከጥንት ጀምሮ መሆኑ ይታወቃል:: በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶየሚገኘው የዘረኛውና ቡድናዊው አገዛዝ በዜጎች ላይ ከፍተኛ በደል በማድረስ ላይ ይገኛል:: ከዚህ ጨቋኝ አገዛዝ ለመገላገልበአንድነትና በመተባበር ለነጻነታችን መታገል አለብን:: ላለፉት 24 አመታት በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተቀመጠውንዘራፊውን እና ጨቋኙን የወያኔ ጁንታን ለመቅበር የአንድነት እና የለውጥ ሃይሎች ልዩነቶቻችንን በማቻቻል በጋራ ልንታገልየሚገባና ለውጥ ልናመጣ የሚገባ ችላ የማይባል ዋነኛ ጉዳይ ነው። በህዝባችን ላይ ከፍተኛ እንግልት፣ እስር፣ ሰቆቃ፣ ግድያወዘተ እየፈጸመ የሚገኘው የህዝባችንና የሃገራችን ጠላት ወያኔ እና ወያኔ ብቻ ነው:: ባሳለፍናቸው መራር የትግል አመታት ውስጥ በቅርቡ እንዳየነው የተቃዋሚዎች በመዋሃድና አንድነትን ከመፍጠር ይልቅ እርስበእርስ መፈራረጅና መወነጃጀል ለስልጣን መሮጥ እንዲሁም ለስም እና ለዝና መትጋት ነው:: ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተረፈው ነገርቢኖር ከጭቆና ወደ ባሰ ጭቆና ማቅ ውስጥ ከመዘፈቅ ውጪ ፍጹም የናፈቀውን የነጻነት አየር እንዲተነፍስ አላደረግነውም።የተቃዋሚ ሃይሎች ጥንካሬ እንዲጎለብት በየድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እንከኖች በማጥራት በጋራ እና በተመቻቸ የሃሳብ መግባባትተቻችሎ እና ተግባብቶ የትግል ስትራቴጂን ከግብ ለማድረስ ህብረ-ብሄር የሆኑት የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር እና ግንቦት7 እንዳደረጉት ለአንድነትና ለትብብር ተግቶ መስራት ይጠበቅብናል። በአሁኑ ወቅት ይህንን ዘረኛ ስርዓት ለማውረድ በውስጥምሆነ በውጭም ትግሉ በስፋት ቀጥሎ ይገኛል:: ወያኔ እስኪወድቅና ህዝባችን ድል እስኪቀዳጅ ድረስ ሊቀጥል የሚገባው ትግልእንደመሆኑ መጠን ከበፊቱ በተሻለ ሁኔታ የተያዘው ትግል በአሁኑ ሰአት ወያኔን እያፍረከረከ በፍርሃት እንዲሸበር አድርጎታል:: የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል! የኛ የኢትዮጵያውያን ጥያቄ አብዮታዊ የለውጥ ጥያቄ ነው። የፖለቲካ አስተዳደር ለውጥ ፣የኑሮ ውድነት የሚያላቅቅ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ለውጥ፣ በጋራ ህብረተሰባዊነትና እኩልነት ላይ የተመሰረተ አገዛዝ ወይንም መንግስትእንደምናገኝ የሚያረጋግጥልን ለውጥ እንፈልጋለን፡፡ የማህበራዊና ፍትህ እኩልነት ለውጥ፣ የነጻነት እና የመብት ማግኘት ጥያቄ፣ከመንግስት ነጻ የሆነ ፍርድ ቤት፣ በሃገራችን ተዘዋውረን በፈለግነው ቦታ የመስራት እና የመኖር ጥያቄ የሚያረጋግጥልን ለውጥእንፈልጋለን፡፡ በሃገራችን ላይ የሃገራችን ባለቤቶች ስንሆን የሚገኘው ብልጽግና እና እድገት ባለቤት መሆናችንን የሚያረጋግጥልንለውጥ እንፈልጋለን፡፡ ይህ ሳይታለም የተፈታ እና የሁሉም የነጻነት ፈላጊ ሃይሎች ጥያቄ ነው። ሰብአዊ መብቶች ለዲሞክሪያሲያዊስርአት ግንባታና ለአንድ ሀገር ልማትና ብልፅግና መሰረታዊ ነገሮች ተደርገው የሚወሰዱ ናቸው፡፡ ዜጎች የሃገራቸው ሃብትባለቤትና የመጠቀምም መብት እንዲሁም ሃሳባቸውን በነጻነት የመግለጽ መብት ሊኖረን ይገባል:: በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉትን ፓርቲዎች መዋቅሮቻቸውን በማጠናከር የውስጥ ድክመቶቻቸውንም በመቅረፍእንዲጠነክሩ የማድረግ ግዴታ ከሁላችንም ከለውጥ ፈላጊ ሃይሎች ይጠበቃል።ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Sunday, 15 March 2015

ሰማያዊ ፓርቲ ቅስቀሳ እንዳያደርግ እንቅፋት እየተፈጠረበት ነው

ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ቅስቀሳ እንዳያደርግ በፖሊሶች ክልከላና ወከባ እየደረሰበት እንደሚገኝ የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ጉዳይ ኃላፊና ም/ሊቀመንበሩ አቶ ስለሽ ፈይሳ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ዛሬ መጋቢት 5/2007 ዓ.ም ፓርቲው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ቅስቀሳ ያደረገ ሲሆን በባህርዳርና ወላይታ ዞን ፖሊስ የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር ቅስቀሰውን ማደናቀፉን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ ዛሬ ሰማያዊ ፓርቲ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ቅስቀሳ በሚያደርግበት ወቅት የከተማው ፖሊስ ‹‹የምርጫ ቅስቀሳ አልተጀመረም›› ብሎ ያዋከበ ሲሆን የፓርቲው አመራሮችና አባላት ቅስቀሳ መጀመሩን ገልጸው ስራቸውን እያከናወኑ በነበሩበት ወቅት ‹‹ህገ ወጥ ሰላማዊ ሰልፍ›› አድርጋችኋል በሚል ሌላ ክስ 8 የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችንና ሌሎች አባላትን በማሰር ቅስቀሳውን እንዳደናቀፈ የወላይታ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ታደመ ፈቃዱ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ በባህርዳር ከተማ ፖሊስ ‹‹በሞንታርቮ ለመቀስቀስ ፈቃድ ስላላመጣችሁ መቀስቀስ አትችሉም፡፡›› በሚል ፓርቲው ሊያደርገው የነበረውን የምርጫ ቅስቀሳ እንዳደናቀፈ የፓርቲው የምዕራብ ጎጃም ዞን ጊዜያዊ አስተባባሪ አቶ አዲሱ ጌታነህ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ‹ለምን ትከለክሏቸዋላችሁ?› በሚል ህዝቡ ፖሊሶቹን በማፋጠጡ በድምፅ መቀስቀስ ባንችልም በህዝቡ ድጋፍ የቅስቀሳ ወረቀቶችን በማሰራጨት የተሳካ ቅስቀሳ አድርገናል›› ሲሉ አቶ አዲሱ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በዚህ ወቅት ቅስቀሳ ለማድረግ ምንም አይነት ፈቃድ እንደማያስፈልግ የገለፁት አቶ ስለሽ ፖሊስ የሚፈጥረው እንቅፋት ሆን ተብሎ ሰማያዊ ወደ ህዝብ እንዳይደርስ የተቀየሰ ስልት ነው ብለዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም ‹‹የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን በመሰረዝ ፓርቲው ምርጫው ላይ የሚፈጥረውን ጫና ለመቀነስ ጥረዋል፡፡ ይህ አልበቃ ሲልም የቅስቀሳ መልዕክቶቻችን በተደጋጋሚ በሚዲያ እንዳይተላለፉ እያደረጉ ነው፡፡ አሁን ደግሞ ወደ ህዝብ እንዳንደርስ በህገ ወጥ መንገድ በፖሊስ ማስቆም ጀምረዋል›› ብለዋል፡፡ በሌላ ዜና የጅማ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ባልታወቁ ግለሰቦች መዘረፉን የምርጫ ጉዳይ ኃላፊው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹በ02/07/07 ሁለት ሰዓት ላይ አራት ግለሰቦች ጽ/ቤቱን በመስበርና የጽ/ቤቱን ጥበቃ አስፈራርተው በማባረር ለቅስቀሳ የተላከ 6 ሺህ ኦሮምኛ በራሪ ወረቀት እንዲሁም 3 ሺህ አማርኛ በራሪ ወረቀት፣ አንድ የፎቶ ካሜራ፣ አንድ ባነር፣ ለሸካ ዞን ሊላክ የተዘጋጀ 5 ሺህ በራሪ ወረቀት፣ 50 ፖስተር፣ አንድ የእጅ ሜጋ ፎን፣ ሁለት ባነር፣ በርካታ ጋዜጦችና መጽሔቶች ሲዘርፉ የጽ/ቤቱን ኮምፒውተርም ሰብረዋል›› ሲሉ ኃላፊው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡

Wednesday, 4 March 2015

በአገር ሙሉ ጀግና ሞልቶ ወያኔን ጀግና አሉት።

ሀገራችን የጀግና ደሀ አይደለችም ጀግኖች የሞሉባት ሀገር ናት። በየተሰለፍንበት መሰኩ አለምን ያስደመመ ጀግኖች ያፈራች አገር ነች።በትምህርቱ ዘርፍ እስከ ሳይንቲስት የደረሱ የትምህርት ጀግኖች አሉ። በሰዕሉ እስከ የአለም ሎሬት የደረሱ የስእል ባለሞያ ጀግኖች አሉን። በስፖርቱም እስከ ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሌያና የአለምን ክብረ ወሠን የሚሰብሩ ጀግኖች ልጆችን ያፈራች አገር ነች። በኪነ ጥበቡ ጥግ ድረስ የደረሱ የኪነ ጥበብ ጀግኖች አሉን። በምርምሩም አዳዲስ ፈጣሪዎችን የሚፈጥሩ ድንቅዬ እና ብርቅዬ ልጆች አሉን። መቼም ጀግና አጥተን የጀግና ደሀ ሆና አታዉቅም አገራችንን የሚያኮሩዋት ጀግኖች አሉዋት የጀግናም ጀግና። -
ወያኔን ጀግና አሉት! በTPLF የትግል ድርሻ ያለው እና ታጋዮች ጭምር ተወዳጅ የሆነውን ታጋይ ኃየሎም አርአያ በትግል ግዜ ሁሌም ካጠገባቸዉ እንዳይለይ የሚፈልጉት በቆራጥነቱ እና በችሎታዉ ታጋዬች በሙሉ የሚተማመኑበት ሀየሎም አርአያ ቀድሞም የጀኔሪል ማእረግ የተሰጠዉ ሰራዊቱ በጣም ስለሚወደዉ አና ስለሚያከብረዉ የተሸበሩት የTPLF መሪ ተብዬዎች ነገ ትልቅ ቦታ እንደሚይዝ እና የወያኔዎችን ኃሳብ ሊቀበላቸዉ እንደማይችል ስለሚያቁ ያንን ከባድ ጊዜያቶችን አሳልፎ የመጣዉን ታጋይ እየተዝናና ባለበት ሰአት አንድ ተራ የወያኔ ካድሬ በበላዮቹ TPLF ሰዎች ትእዛዝ ተሰጥቶት ሳያስበዉ በመሳሪያ ተኩሶ በመምታት ገደለውታል። ይሄ ነዉ የወያኔ ጀግንነት? በትግሉ ሰአት አብሮአቸዉ የነበሩት የትግራይ ሰዎች ትግሉንም በድል ያጠናቀቁትን የትግራይ ልጆች ከድል በኋላ ከወያኔ ጋር የሀሳብ ልዩነት በመኖራቸዉ ብቻ በድብቅ አየተከታተሉ ከሰላሳ ስድስት ሺህ በላይ ታጋዬችን የገደሉ እንግዲህ እዚህን ገዳዬች ነዉ ጀግኖች የምትሉት? ሀዉዜን ላይ የወረደዉ የቦብ ዝናብ በደርግ ባለስልጣን ዉስጥ ሆኖ ትዕዛዝ ያስላለፈዉ አና ይህንን ምስኪን ሕዝብ ለድብቅ አላማቸዉ የሰዉ ሀይል ለማግኛ ተበዳይ ለመምሰል ወደ ሀዉዜን ገበያ የወያኔ ወታደር በሙሉ ገብተዋል ተብሎ እንዲነገር አስደርገዉ የትግራይን ሕዝብ ዳር ቆመው ያስፈጁትን ወያኔን ጀግና አሉት። አዲስ አበባ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ ምንም የጦር መሳሪያ ባልያዙ ንፁሀን ዜጎጀ ላይ የፈሪ ዱላ አንደሚባለው በያዙት መሳሪያ ያለምንም ርህራሄ ህዝቡን የፈጁት ነዉ እንግዲህ ጀግና የምትሉን? ጋንቤላ ላይ ከመሬታችን አታፈናቅሉን በመሬታችን መኖር እንፈልጋለን ብለዉ መሬታችንን ለባዕዳን አትስጡብን ብለዉ ተቃዉሞ ባሰሙት ንፁሁን የጋቤላ ተወላጆች ላይ ብረት አንስግቶ የፈጀዉና በግዳጅ ከመሬታቸዉ አፈናቅሎ ለባድ የሚሰጠዉን ነው ዉያኔን ጀግና የምትሉት? በአኝዋከ ህዝብ ላይ መሬታቸዉን በመፈለግ የአኝዋከ ህብረተሰብን ዘግናኝ በሆነ መልኩ የዘር ማጥፋት እልቂት ከደረሰ በኋላ በጅምላ ወደ አንድ ጉድጓድ የከተተዉን ነዉ ጀግና ብላቹ የምትጠሩት? በኦጋዴን ዉሰ በሱማሌ ተወላጆች ህብረተሰብ ላይ በአየር ቦምብ በማዝነብ የዘር ማጥፋት የፈፀመዉን እና እንደ ሃውዜን ውስጥ እንዳደረጉት ጭካኔ የተሞላበት ስራቸውን የደገሙትን ነዉ ጀግና ያላችኋተው? አንቦ ላይ በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን መሰረት ተቃዉሞ የወጣዉን የአምቦ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የታጠቀ ወታደር አሰማርቶ ተማሪዎችን መግደል ነዉ እንዴ ወያኔን ጀግና ያሰኘዉ? ባህር ዳር ላይ ስለሀይማኖት ብለዉ የወጡት ሰላማዊ ሕዝብ ላይ አነጣጥሮ ተኩሶ መግደል ነዉ ጀግና ያሰኛቸዉ ታድያ ጀግና ያሰኛቸዉ ምንድን ነዉ? ብዕር የያዘ ጋዜጠኛ አንተ አሸባሪ ነህ ብሎ ወደ እስር መጣል ነዉ ጀግንነት? ወይስ የፖለቲካ ሰዎችን ባላቸዉ የፖለቲካ አቋም በመፍራት ብቻ የአሸባሪ ታፔላ እየለጠፉ ወደ ወይኒ መወርወር ነዉ ጀግንነት? ወይስ የተማረዉንም ያልተማረዉንም ሰዉ በኛ መስመር ግባ ካልገባህ መኖር አትችልም ብለዉ ማዋከብ ነዉ ጀግና ያሰኛቸዉ? ጀግና ማለት በፍቅር ታግሎ በፍቅር የሚያሸንፍ ነዉ። ጀግና ማለት ከባርነት ቀንበር አላቆ ነፃነትን የሚያወርስ እና በነፃነት እንዲኖሩ ማድረግ ነዉ።ጀግና ማለት ስራዉ ከሚናገዉ በበጠ ጏልቶ የሚታይ እና በሰዉም ዘንድ ተቀይነትን ያገኘ ነዉ። ጀግና ማለት እንደ ዉሻ ላበላዉ የሚጮህ ሳይሆን ለእዉነት የቆመ ለእዉነት የተሸነፈ ለእዉነት የሚኖር እሱ ነዉ ጀግና። መሳርያ ስለያዘ ብቻ ከኔ በላይ ማን አለብኝ ብሎ እየተኯሰ ሰላማዊ ሰዉን የሚገል እሱ ጀግና ሳይሆን አረመኔ ነዉ አረመኔን ደሞ ጀግኖች ያጠፉታል። ጀግና ማለት ለነሱ የታጠቀ ኃይል በሰላማዊ ሰዉ ላይ ተኩሶ መግደል ከመሰላቸዉ፡ ጀግና ማለት ለነሱ ብዕር የያዙትን ብዕራዉያንን በብረት አስረዉ ማሰቃየት ከሆነ፡ ጀግና ማለት ለነሱ የፓለቲካ ሰዎችን በአአስከፊ ቅጣት መቅጣት ከመሠላው፡ እኔ ግን እላለዉ እነዚህ ጀግና ሳይሆኑ ፈሪ እና እውቀት የጏደላቸዉ ናቸዉ። እነዚህ ጀግና ሳይሆኑ የጨነቃቸዉ ናቸዉ እላለዉ። ፈሪና የጨነቀዉ ሰዉ የሚያደርገዉን ድርጊት እያደረጉት ያሉት። ጀግናማ ፍቅርን አስተማሪ ነዉ። ጀግናማ ለህዝብ የቆመ ነዉ። ጀግናማ ለሆዱ ያልቆመ ነዉ። ጀግናማ ኢትዮጵያዊው ነው። To Addis Berhanu 03.03.2015 Email- berhanu.addis@yahoo.com - See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/5049#sthash.m7pSsFra.dpuf