Monday, 31 March 2014

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ምሬታቸውን ለፓርላማ አሰሙ

‹በሕይወቴ ያለምቾት የሠራሁበት ወቅት አሁን ነው›› የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሀብትና ንብረትን ለመጠበቅና ለማስተዳደር ሲባል ‹‹ራሳችንንና ቤተሰቦቻችንን ችግር ውስጥ ከተናል›› በማለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ለፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ ምሬታቸውን ገለጹ፡፡ የኦዲት አገልግሎት ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢና በሥሩ የሚገኙ ተቋማት ላይ ከ1999 እስከ 2002 ዓ.ም. ባለው ሒሳብ ላይ ያካሄደውን ኦዲትና የኦዲት ግኝቶችን አስመልክቶ ማብራርያ እንዲሰጡ፣ ባለፈው ዕለት በፓርላማው የመንግሥት ወጪ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተጠርተው በተወቀሱበት ወቅት ነው አመራሮቹ ምሬታቸውን የገለጹት፡፡ በዋናው ግቢ ከልዩ ልዩ የተሰብሳቢ ሒሳብ መሰብሰብ የሚገባው 80.7 ሚሊዮን ብር ለረዥም ጊዜ መንከባለሉን፣ የሚሰበሰብ ከሆነም ከማን እንደሚሰበስብ አለመታወቁ፣ በዋናው ግቢ በግዥ ቅድመ ክፍያ ተከፍሎ የመጀመርያው ሳይወራረድና ሳይረጋገጥ ድጋሚ የግዥ ቅድሚያ ክፍያ በተለያዩ አቅራቢዎች ተመዝግቦ መገኘቱና ለረዥም ጊዜ ያልተወራረደ ሒሳብ በድምሩ 29.8 ሚሊዮን ብር መገኘቱ፣ በአንዳንድ ሒሳብ መደቦችና አካውንቶች ጭራሹኑ የባንክ ማስታወቂያ ሒሳብ ያልተሠራላቸው መኖራቸውና የሒሳቡ ትክክለኝነትን ማረጋገጥ አለመቻሉን የኦዲት ሪፖርቱ ይገልጻል፡፡ ለአብነት ያህል ከተጠቀሱት ውስጥ በዋናው ግቢ በጥሬ ገንዘብ በባንክ ሒሳብ 28 ሚሊዮን ብር መኖሩ የጥሬ ገንዘብ ቆጠራና የባንክ ሒሳብ ባለመዘጋጀቱ ስለትክክለኛነቱ ማረጋገጥ አለመቻሉ፣ እንዲሁም በገንዘብ ያዥ እጅ 10.4 ሚሊዮን ብር በጉድለት መታየቱና ምክንያት ሊቀርብለት አለመቻሉ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ አቶ እሸቱ ተሾመና ሌሎች የቋሚ ኮሚቴው አባላት እንዲሁም የዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት ባለሙያዎችና ዋና ኦዲተሩ አቶ ገመቹ ዱቢሶ የኦዲት ግኝቱን አስመልክቶ የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርበውላቸዋል፡፡ ‹‹የአገሪቱን የፋይናንስ ሕግ፣ ደንብ፣ መመርያና አሠራር ለማክበር ችግራችሁ ምንድነው? ዩኒቨርሲቲው ሒሳቡን በወቅቱ ዘግቶ ኦዲት አለማድረጉና ችግሩን በወቅቱ አለማረሙ ምክንያቱ ምንድነው? ተጠያቂነቱን እንዴት ትዘነጋላችሁ›› በማለት ጠይቀዋቸዋል፡፡ በቀረቡት ጥያቄዎች ላይ የማጠቃለያ ምላሽ የሰጡት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አድማሱ ፀጋዬ፣ ‹‹በዋናነት መታወቅ ያለበት ችግሩን የማስተካከል ኃላፊነት እንጂ እኛ ተጠያቂ አይደለንም፡፡ ምክንያቱም አሁን ያለው አመራር ከመምጣቱ በፊት የተከሰተ ችግር ነው፤›› በማለት ግንዛቤ እንዲወሰድ ጠይቀዋል፡፡ ‹‹ይህ ማለት ግን ኃላፊነቱ አይመለከተንም ማለት እንዳልሆነ፣ አሁን ያለው አመራር ሚና የተፈጠሩትን ችግሮች ማረም፣ ማስተካከልና በዛላቂነት ለመፍታት ሲስተም መፍጠር ነው፤›› ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ያሉትን ችግሮች ለመፍታት ከተጀመሩ የሲስተም ዝርጋታዎች አንዱ ሕግን በተከተለ መንገድ አሥራ አምስቱን የዩኒቨርሲቲው ግቢዎች የንብረት ቆጠራ ማካሄድና የሀብት ግምታቸውን ማወቅ ነው ብለዋል፡፡ ከዚህ ቀደም የዩኒቨርሲቲው ንብረቶች የሚመዘገቡት በእርሳስ እንደሆነ፣ የንብረት ክፍል ኃላፊዎች ሲቀየሩና አዲስ ኃላፊ ሲመጣ በላጲስ ጠፍቶ የአዲሱ ኃላፊ ስም እንደሚመዘገብ አስታውቀዋል፡፡ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴርን አስፈቅዶ ዩኒቨርሲቲው ገንዘብ ሲሰበሰብ የነበረው ራሱ በሚያሳትመው የገንዘብ መሰብሰብያ ሰነድ መሆኑን ያስታወሱት ፕሬዚዳንቱ፣ አሁን ግን ገንዘብ ሚኒስቴር በሚያውቀው ሰነድ መሰብሰብ አለበት በመባሉ ወደዚህ ሥርዓት እየተገባ ነው ብለዋል፡፡ ኦዲት መደረግና መሰብሰብ ባልቻሉት ሒሳቦች ላይ ዕርምት ተወስዶ በርካታ ሚሊዮን ብሮች ተሰብስባዋል ሲሉ አስረድተዋል፡፡ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ዶ/ር ጄሎ ዑመር፣ ‹‹ዩኒቨርሲቲው ከ50 ሺሕ በላይ ተማሪዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ከ20 ሺሕ በላይ በግቢው ውስጥ ነው የሚኖሩት፡፡ እነሱን በቀን ሦስቴ መመገብ አለብን፡፡ ግቢው ውስጥ ኮሽ ሳይል የመማር ማስተማሩ ሒደት መቀጠል አለበት፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የፋይናንስም ሆነ የግዥ ሕጉን ማስተናገድ መቻል አለብን፡፡ እነዚህን አጣጥሞ መሄድ ምን ያህል ፈተና እንደሆነ ካልገባን በስተቀር አስቸጋሪ ነው፤›› በማለት ያለውን ሁኔታ ለማሳየት ሞክረዋል፡፡ በተለይ ደግሞ ችግሩ በቀድሞዎቹ አመራሮች ጊዜ የተፈጠረና ሥር የሰደደ በመሆኑ አስቸጋሪ ያደርገዋል ብለዋል፡፡ ‹‹እውነት ለመናገር ራሴንም ቤተሰቦቼንም ለችግር አጋልጬ ነው የምሠራው፡፡ ታመኖብን ከገባን አይቀር ብለን እንጂ ምቾት ተሰምቶን አይደለም፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹እኔ በሕይወቴ ምቾት ሳይሰማኝ ሥራ የምሠራበት ወቅት ቢኖር ባለፉት ሦስት ዓመታት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ከተቀላቀልኩ በኋላ ነው፤›› በማለት ምሬታቸውን አሰምተዋል፡፡ የሚቻለውን ያህል ሕግ ለማስከበር እየሠሩ መሆናቸውን የተናገሩት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ የዩኒቨርሲቲውን መኖሪያ ቤቶች ተረክበው የነበሩ መምህራን ከዩኒቨርሲቲው ቢለቁም መኖሪያ ቤቱን ግን ለቤተሰቦቻቸው ሰጥተው ቤተሰቦቻው አከራይተው እየኖሩ መሆኑ እንደተደረሰበትና ሕገወጥነቱን ለማስቆም ግብግብ ውስጥ መግባታቸውን ጠቁመዋል፡፡ ፕሮጀክቶች ከተጠናቀቁ በኋላ ለዩኒቨርሲቲው መመለስ የሚገባቸው ተሽከርካሪዎች አሁንም በመምህራን ንብረትነት እየተቆጠሩ በመሆናቸው፣ ይህንን ሁኔታ ለመቀየር ንትርክ ላይ መሆናቸውን በማስረዳት ጥረታቸው በፈተና የታጀበ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

Saturday, 29 March 2014

ኢህአዴግ የእምነት ተቋማትን በጥብቅ የሚቆጣጠርበት ህግ ሊያጸድቅ ነው

ህጉ ጣጣ እንዳያመጣ የሰጉ ኢህአዴግን እየመከሩ ነው
ኢትዮጵያን ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ እየገዛ ያለው ኢህአዴግ የሃይማኖት ተቋማትንና ምዕመናኑን በጥብቅ የሚቆጣጠርበትን ህግ ለማጽደቅ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተሰማ። የህጉ ረቂቅ የደረሳቸው ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ኢህአዴግን አበክረው እየመከሩና በሚያመጣው አጠቃላይ መዘዝ ዙሪያ እያስጠነቀቁ ነው። ጎልጉል ከዲፕሎማት ምንጮቹ ባገኘው መረጃ መሰረት ኢህአዴግ በእምነት ተቋማት ላይ ቁጥጥሩን የሚያጠብቅበትንና ከሃይማኖት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውጭ መሰብሰብን፣ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግንና የተቃውሞ ድምጽ ማሰማትን የሚከለክል ህግ አዘጋጅቷል። የዜናው ምንጮች ዝርዝር ህጉን ለጊዜው ይፋ ከማድረግ እንደሚቆጠቡ አስታውቀዋል። ይሁን እንጂ የሚደነገገውን አዲስ ህግ ጥሰዋል በሚል የሚከሰሱ ምዕመኖች እስከ እድሜ ልክ በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ የሚያዝ አንቀጽ አለበት። አዲሱ ህግ ከሽብርተኞች ህግ ጋር የሚጣቀስ እንደሆነም የጠቆሙት ክፍሎች ኢህአዴግ “ከእምነት ነጻነት” ጥያቄ ጋር በተያያዘና በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ውስጥ ውስጡን እየነደደ ያለው ችግር ስላስጨነቀው ይህንን ህግ ለማውጣት መገደዱን አስረድተዋል። በሌላ በኩልም እስካሁን መፍትሔ ያላገኘው የሙስሊሞች ጥያቄ ከዚያም ጋር ተከትሎ የተከሰተው ደም መፋሰስ ወደፊት ሊያመጣ በሚችለው ጉዳይ ላይ ኢህአዴግን በብርቱ አሳስቦታል፡፡ ኢህአዴግ ከቀን ወደ ቀን ቀውስ እየተደራረበት እንደሆነ የተረዳችው አሜሪካ በከፍተኛ ባለስልጣኖቿ አማካይነት ኢህአዴግን እየመከረች እንደሆነ ከዲፕሎማቶች የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ከፖለቲካው ቀውስና በቀጠናው ካለው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ አሜሪካ በተደጋጋሚ የህወሃትን ሰዎች በተናጠል እያነጋገረች እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል። ዲፕሎማቶቹ እንደሚሉት አሜሪካ መለስ “ከተሰዉ” በኋላ አገሪቱን ማን እየመራት እንደሆነ በቅጡ ለመረዳት በሚያስቸግር ሁኔታ የስልጣን መዛነፍና ደረጃን የጠበቀ የስልጣን ተዋረድ አለመኖሩም አሳስቧታል። ኢህአዴግ ለህልውናዬ ያሰጋኛል በሚል መንግሥታዊ ባልሆኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች /መያዶች/ ላይ ያወጣውን አፋኝ ህግም ጠቅሰዋል። ዲፕሎማቶቹ በጉዳዩ ዙሪያ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ወቅቱ አሁን እንዳልሆነ አመልክተዋል።

Friday, 28 March 2014

በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ደማቅ የተቃውሞ ትእይንት ተደረገ::

በታላቁ ኣንዋር መስጂድ የሰላም ምልክት የሆነው ነጭ ወረቀት በህዝበ ሙስሊሙ እየተውለበለበ ነው! በአዲስ አበባ ታላቁ አንዋር መስኪድን ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ ዋናዋና ከተሞች ‹‹ሰላታችንን በመስጂዳችን!›› በሚል መሪ ቃል ህዝበ ሙስሊሙ እያካሄደው ያለው መስጂድ ተኮር የዘመቻ እንቅስቃሴ አካል የሆነው እና የዘመቻው ማጠናቀቂያ የጁምኣ የተቃውሞ ትእይንት በደመቀ መልኩ ተካሂዷል:: ህዝቡን ከመስጂዱ ለመነጠል በመንግስት በኩል እየተሰራ ያለውን ህገ ወጥና ኢ-ህገ መንግስታዊ ስራም ለራሱ ተረድቶ ላልሰሙት ሁሉ በማሰማትና መስጂዶቹን በዒባዳ በማድመቅ ላይ ነው የሚገኘው፡፡ ይህ ወቅታዊና አንገብጋቢ የመስጂድ ባለቤትነትን የማረጋገጥ እንቅስቃሴ የመንግስትን እና የመጅሊስን ሴረኞች እንቅልፍ ማሳጣቱንም ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡ የውስጥ መረጃዎች እያጋለጡ ነው፡፡ ‹‹ሰላታችንን በመስጂዳችን!››ዘመቻ የዛሬው ጁሙአ ድረስ ቀጥሎ የቆየ ሲሆን በአዲስ አበባና በተመረጡ የክልል መስጂዶች ላይም አስቀድሞ የነበሩንን ቋሚ ትዝታ ጥለው ያለፉ ግዙፍ ተቃውሞዎችን በሚያስታውስ መልኩ የደመቀ የተቃውሞ ስነስርአት በማድረግ በሰላማዊ ሁኔታ ዘመቻው መጠናቀቁ ታውቋል:: በዚህም መሰረት ከቀኑ ስድሰት ጀምሮ በአዲስ ወደ አዲስ አበባ አንዋር መስኪድ እና በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ የተቃውሞ ወደተመረጡ መስኪዶች የተመመው ህዝበ ሙስሊሙ የመስኪዶችን ውስጥ እና ደጅ በመሙላት መስኪዶቹ የራሱ ሃብት መሆናቸውን እና ሙስሊሙ ህዝብ ሰላም ፈላጊ መሆኑን በደመቀ ተቃውሞ ነጭ ምልክቶችን በማውለብለብ ገልጿል:: ህዝበ ሙስሊሙ ዘመቻውን በተሳካ መልኩ በማድረግ ሰላማዊ ተቃውሞውን አሰምቶ ከኮሚቴው ጎን ዛሬም ቃሉን አክብሮ እንደቆመ በማሳየት በሰላም መመለሱን ለማረጋገጥ ተችሏል::

Wednesday, 26 March 2014

HRW: Foreign Technology Used to Spy on Ethiopian Opposition inside Country, Abroad

Ethiopia: Telecom Surveillance Chills Rights Foreign Technology Used to Spy on Opposition inside Country, Abroad (Berlin, March 25, 2014) – The Ethiopian government is using foreign technology to bolster its widespread telecom surveillance of opposition activists and journalists both in Ethiopia and abroad, Human Rights Watch said in a report released today. The 100-page report, “‘They Know Everything We Do’: Telecom and Internet Surveillance in Ethiopia,” details the technologies the Ethiopian government has acquired from several countries and uses to facilitate surveillance of perceived political opponents inside the country and among the diaspora. The government’s surveillance practices violate the rights to freedom of expression, association, and access to information. The government’s monopoly over all mobile and Internet services through its sole, state-owned telecom operator, Ethio Telecom, facilitates abuse of surveillance powers. “The Ethiopian government is using control of its telecom system as a tool to silence dissenting voices,” said Arvind Ganesan, business and human rights director at Human Rights Watch. “The foreign firms that are providing products and services that facilitate Ethiopia’s illegal surveillance are risking complicity in rights abuses.” The report draws on more than 100 interviews with victims of abuses and former intelligence officials in Ethiopia and 10 other countries between September 2012 and February 2014. Because of the government’s complete control over the telecom system, Ethiopian security officials have virtually unlimited access to the call records of all telephone users in Ethiopia. They regularly and easily record phone calls without any legal process or oversight. Recorded phone calls with family members and friends – particularly those with foreign phone numbers – are often played during abusive interrogations in which people who have been arbitrarily detained are accused of belonging to banned organizations. Mobile networks have been shut down during peaceful protests and protesters’ locations have been identified using information from their mobile phones. A former opposition party member told Human Rights Watch: “One day they arrested me and they showed me everything. They showed me a list of all my phone calls and they played a conversation I had with my brother. They arrested me because we talked about politics on the phone. It was the first phone I ever owned, and I thought I could finally talk freely.” The government has curtailed access to information by blocking websites that offer any independent or critical analysis of political events in Ethiopia. In-country testing that Human Rights Watch and Citizen Lab, a University of Toronto research center focusing on internet security and rights, carried out in 2013 showed that Ethiopia continues to block websites of opposition groups, media sites, and bloggers. In a country where there is little in the way of an independent media, access to such information is critical. Ethiopian authorities using mobile surveillance have frequently targeted the ethnic Oromo population. Taped phone calls have been used to compel people in custody to confess to being part of banned groups, such as the Oromo Liberation Front, which seeks greater autonomy for the Oromo people, or to provide information about members of these groups. Intercepted emails and phone calls have been submitted as evidence in trials under the country’s flawed anti-terrorism law, without indication that judicial warrants were obtained. The authorities have also detained and interrogated people who received calls from phone numbers outside of Ethiopia that may not be in Ethio Telecom databases. As a result, many Ethiopians, particularly in rural areas, are afraid to call or receive phone calls from abroad, a particular problem for a country that has many nationals working in foreign countries. Most of the technologies used to monitor telecom activity in Ethiopia have been provided by the Chinese telecom giant ZTE, which has been in the country since at least 2000 and was its exclusive supplier of telecom equipment from 2006 to 2009. ZTE is a major player in the African and global telecom industry, and continues to have a key role in the development of Ethiopia’s fledgling telecom network. ZTE has not responded to Human Rights Watch inquiries about whether it is taking steps to address and prevent human rights abuses linked to unlawful mobile surveillance in Ethiopia. Several European companies have also provided advanced surveillance technology to Ethiopia, which have been used to target members of the diaspora. Ethiopia appears to have acquired and used United Kingdom and Germany-based Gamma International’s FinFisher and Italy-based Hacking Team’s Remote Control System. These tools give security and intelligence agencies access to files, information, and activity on the infected target’s computer. They can log keystrokes and passwords and turn on a device’s webcam and microphone, effectively turning a computer into a listening device. Ethiopians living in the UK, United States, Norway, and Switzerland are among those known to have been infected with this software, and cases have been brought in the US and UK alleging illegal wiretapping. One Skype conversation gleaned from the computers of infected Ethiopians has appeared on pro-government websites. Gamma has not responded to Human Rights Watch inquiries as to whether it has any meaningful process in place to restrict the use or sale of these products to governments with poor human rights records. While Hacking Team applies certain precautions to limit abuse of its products, it has not confirmed whether and how those precautions applied to sales to the Ethiopian government. “Ethiopia’s use of foreign technologies to target opposition members abroad is a deeply troubling example of this unregulated global trade, creating serious risks of abuse,” Ganesan said. “The makers of these tools should take immediate steps to address their misuse; including investigating the use of these tools to target the Ethiopian diaspora and addressing the human rights impact of their Ethiopia operations.” Such powerful spyware remains virtually unregulated at the global level and there are insufficient national controls or limits on their export, Human Rights Watch said. In 2013, rights groups filed a complaint at the Organization for Economic Co-operation and Development alleging such technologies had been deployed to target activists in Bahrain, and Citizen Lab has found evidence of use of these tools in over 25 countries. The internationally protected rights to privacy, and freedom of expression, information, and association are enshrined in the Ethiopian constitution. However, Ethiopia either lacks or ignores judicial and legislative mechanisms to protect people from unlawful government surveillance. This danger is made worse by the widespread use of torture and other ill-treatment against political detainees in Ethiopian detention centers. The extent of Ethiopia’s use of surveillance technologies may be limited by capacity issues and a lack of trust among key government ministries, Human Rights Watch said. But as capacity increases, Ethiopians may increasingly see far more pervasive unlawful use of mobile and email surveillance. The government’s actual control is exacerbated by the perception among many Ethiopians that government surveillance is omnipresent, resulting in considerable self-censorship, with Ethiopians refraining from openly communicating on a variety of topics across telecom networks. Self-censorship is especially common in rural Ethiopia, where mobile phone coverage and access to the Internet is very limited. The main mode of government control is through extensive networks of informants and a grassroots system of surveillance. This rural legacy means that many rural Ethiopians view mobile phones and other telecommunications technologies as just another tool to monitor them, Human Rights Watch found. “As Ethiopia’s telecom system grows, there is an increasing need to ensure that proper legal protections are followed and that security officials don’t have unfettered access to people’s private communications,” Ganesan said. “Adoption of Internet and mobile technologies should support democracy, facilitating the spread of ideas and opinions and access to information, rather than being used to stifle people’s rights.” “‘They Know Everything We Do’: Telecom and Internet Surveillance in Ethiopia,” is available at: http://hrw.org/node/123977 For more Human Rights Watch reporting on Ethiopia and the Anti-Terrorism Proclamation, please visit: http://www.hrw.org/africa/ethiopia For more Human Rights Watch reporting on Internet freedom, please visit: http://www.hrw.org/topic/free-speech/internet-freedom

ከአምቦ ተፈናቅለው በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት የተጠለሉ የአማራ ተወላጆችን አስመልክቶ በፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል የተቀነባበረ ዘጋቢ ፊልም

Monday, 24 March 2014

ለዜጎች ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ አፈናና እስራት ምላሽ አይሆንም! (ሰማያዊ ፓርቲ)

ከሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት የወጣ የአቋም መግለጫ የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት መጋቢት 14 ቀን 2006 ዓ.ም ባካሄደው ሁለተኛ ዓመት አራተኛ መደበኛ ስብሰባው የካቲት 30 ቀን 2006 ዓም የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው ሩጫ ላይ በተገኙ የሰማያዊ ፓርቲ ሴት አባላት ላይ ፖሊስና ፍርድ ቤት በመተባበር የፈጸሙትን ሕገ መንግስት የጣሰ ተግባር፣ እንዲሁም ከአሜሪካ መንግስት በደረሳቸው ግብዣ መጋቢት 12 ቀን 2006 ዓም ምሽት ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ቦሌ አውሮፕላን ማረፈያ በተገኙት የፓርቲያችን ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ላይ ራሳቸውን ከህግ በላይ ያደረጉ የደህንነት ኋይሎች የፈጸሙትን አሳፋሪና ሕገ ወጥ ተግባር በመመርመር የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥቷል፡፡Statement from Semayawi party of Ethiopia, regarding Nile issue. 1. የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው ሩጫ ላይ የተገኙ የሰማያዊ ፓርቲ ሴት አባላት በሩጫው ከተሳተፉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች የሚለዩት የነጻነትን ቀን ሊያከብሩ በተገኙበት ቦታ ስለ ነጻነት፣ስለ ፍትህ፣ስለዴሞክራሲ፣ስለ ሰብአዊ መብት ወዘተ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው በማሰማታቸው ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 29/2 «ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሀሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው» ተብሎ የተደነገገውን ከምንም ያልቆጠረውና ሕጉን ሳይሆን ጠመንጃውን ተማምኖ፣ የሙያውን ሥነ ምግባር ሳይሆን የአለቆቹን ትዕዛዝ አክብሮ እንደሚሰራ በተግባሩ ያረጋገጠው ፖሊስ እነዚህን የሰማያዊ ፓርቲ ሴት ወጣቶች አፍሶ ሲያስር አንዳችም ህጋዊ ምክንያት አልነበረውም፣ የፖሊስ ሕገ ወጥ ተግባር በዚህ ሳያቆም የታሰሩ የትግል አጋሮቻቸው የሚገኙበትን ቦታና ሁኔታ ለማወቅ ወደ ፖሊስ ጣቢያ የሄዱ የፓርቲው አመራር አባላትንም አሰረ፡፡ ዋስትና ለማስከልከል አይደለም ለክስ የሚያበቃ ምንም ምክንያት ሳይኖረው ለፍ/ቤት ምርመራየን አልጨረስኩም የግዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ በማለት አባላቱ ለአስር ቀናት በጣቢያ እስር እንዲጉላሉ በማድረግ ሕግን ለማስከበር ሳይሆን የፖለቲከኞችን ፍላጎት ለማስፈጸም የቆመ መሆኑን በተግባር አረጋግጠ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ይህንን ሕገ መንግሥቱን በግልጽ የጣሰ የፖሊስ ተግባር በጽኑ እያወገዘ፣ፖሊስ የግለሰቦች ሥልጣን ጠባቂ ሳይሆን ሕግ አስከባሪ መሆኑን በተግባር እንዲያሳይ ይጠይቃል፡፡ 2. የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 19/4 «የያዛቸው የፖሊስ መኮንን ወይም ህግ አስከባሪ በጊዜው ገደብ ፍርድ ቤት በማቅረብ የተያዙበትን ምክንያት ካላስረዳ ፍርድ ቤቱ የአካል ነጻነታቸውን እንዲያስከብርላቸው የመጠየቅ ሊጣስ የማይችል መብት አላቸው፡፡» ተብሎ የተደነገገውንእንዲያቀርቡ አዟል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምር ፍርድ ቤቱ ለህግ የበላይነት የሚሰራና በመተላለፍ ታሳሪዎቹን የዋስትና መብት ከልክሎ ለሁለት ግዜ ለፖሊስ የግዜ ቀጠሮ የፈቀደው ፍርድ ቤት፣ የእኔ ሥልጣን አይደለም መደበኛ ፍርድ ቤት አቅርቡዋቸው በማለት ካሰናበት በኋላ የምርመራ መዝገቡ ለክስ አይበቃም ተብሎ በአቃቤ ሕግ ውድቅ የተደረገበት ፖሊስ መልሶ እዛው ፍርድ ቤት ሲያቀርባቸው እያንዳንዳቸው 1300 ብርና የሰው ዋስ በጣምራ ለፍትህ መከበር የቆመ አለመሆኑን በተግባር ያረጋገጠበትን ይህን ተግባር እያወገዘ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 79/2 «በየትኛውም ደረጃ የሚገኝ የዳኝነት አካል ከማንኛውም የመንግሥት አካል፣ከማንኛውም ባለሥልጣን ሆነ ከማንኛውም ሌላ ተጽዕኖ ነጻ ነው» እንዲሁም በአንቀጽ 79/3 ዳኞች የዳኝነት ተግባራቸውን በሙሉ ነጻነት ያከናውናሉ፣ከሕግ በስተቀር በሌላ ሁኔታ አይመሩም »ተብሎ የተደነገገው በተግባር እንዲገለጽ አጥብቆ ይጠይቃል፡፡ 3. የፓርቲያችን ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ወደ አሜሪካ የሚያደርሳቸውን አስፈላጊ የጉዞ ሰነድ አሟልተው ሻንጣቸው አውሮፕላን ላይ ካስጫኑ በኋላ ፓስፖርታቸው በደህንንት ኋይሎች ተቀዶ ጉዞአቸው እንዲስተጓጎል ተደርጓል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ይህን ሕገ ወጥ ብቻ ሳይሆን እጅግ አሳፋሪ የሆነና የደህንነት ክፍሉን ብቻ ሳይሆን የአየር መንገዱንም ስም የሚያጎድፍ ተግባር በጽኑ እያወገዘ ድርጊቱን በፈጸሙት ማን አለብኝ ባዮች ላይ ከሕግ በላይ ሊሆኑ እንደማይችሉ የሚያሳይ ሕጋዊ ርምጃ አንዲወሰድ እንጠይቃለን፡፡ 4–መንግሥት ለዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብት ጥያቄ እስራት አፈናና ማስፈራራት ምላሽ እንደማይሆን ከታሪክ በመማር ለዜጎች የመብት ጥያቄ ትክክለኛውን ምላሽ እንዲሰጥና ትግሉ ሰላማዊ፣ ዓላማው ሕዝባዊ ግቡ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን እውን ማድረግ ከሆነው ሰማያዊ ፓርቲ ላይ የጥፋት እጁን እንዲያነሳ አጥበቀን እንጠይቃለን ፡፡

Friday, 21 March 2014

በአዲስ አበባ “የእሪታ ቀን” በሚል ስያሜ በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ሠላማዊ ሠልፍ ለማድረግ ወሰነ!! ከአዲስ አበባ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ!!

ከአዲስ አበባ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ! ኢህአዴግ አገር የመምራት ብቃት እንደሌለው አዲስ አበባ ማሳያ ናት!! ሌሎች አገሮች ለዋና ከተሞቻቸው ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የየአገሮቻቸው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ማሳያ በማድረግ አለም አቀፍ ተቋማትንና ጎብኝዎችን በመጋበዝ የከተሞቻቸውን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ያደርጋሉ፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ ግን በብዙዎች የአፍሪካ አገራት የአህጉሪቱ መዲና ተደርጋ የምትጠቀሰው አዲስ አበበባችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ኋላ አየተጎተተች ለኑሮ ምቹ ከሆኑ ከተሞች ምድብ መቀላቀለ ተስኗት ለነዋሪዎቿ የማትመች የፈተና ምድር ሆናለች፡፡ ኢህአዴግ ራሱን ልማታዊ መንግሥት በማድረግ ከሰየመበት ቅጽበት አንስቶ በልማት ሰበብ ዜጎች ከመኖሪያቸውና ቤተሰቦቻቸውን ከሚያስተዳድሩበት የንግድ ቦታ እንዲፈናቀሉ ተደርገዋል፡፡ በከተማይቱ እንዲነሱ የተደረጉት የንግድ ሱቆች በአብዛኛው በኪራይ ቤቶችና በቀበሌ ስም የተመዘገቡ በመሆናቸውም በሱቆቹ በመነገድ ይተዳደሩ የነበሩ ቤተሰቦች ባዶ አጃቸውን እንዲቀሩ ተደርገዋል፡፡ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለውን የመንገድ ዝርጋታ የተነሳ የተጠና ሥራ ባለመሰራቱ ከፍተኛ የህዝብ ገንዘብ የወጣባቸው መንገዶች ለምረቃ በበቁ በጥቂት ቀናት ልዩነት እንዲፈርሱ ተደርገዋል፡፡ የከተማው ነዋሪ ለሚጠቀምባቸው የመጓጓዣ አውታሮች ተለዋጭ መንገድ ባለመዘጋጀቱም ለተጨማሪ ወጪ ተዳርጓል፡፡ ትራንስፖርት ማግኘት በሁሉም አካባቢዎች አስቸጋሪ በመሆኑ የከተማይቱ የሥራ እንቃስቃሴ ተዳክሟል፡፡ መንግሥት ‹‹የምትታለብ ላም›› በማለት የሚጠራው የኢትዮ ቴሌ ኮም አገልግሎት የለም የሚባልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ጭምር በኢትዮጵ ቴሌኮም የተንቀራፈፈ አገልግሎተ የተነሳ ባንኮችና የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ለደምበኞቻቸው ተገቢውን ግልጋሎተ ማበርከት አልቻሉም፡፡ የከተማይቱ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር የተወሰኑ ሠራተኞች ችግር እንደሆነ ተጠቁሞ ሠራተኞች ለስንብት ቢዳረጉም የኤሌክትሪክ መቆራረጥና ለረጅም ግዜ መጥፋት የከተማይቱ ኢንዱስትሪዎች ፤ንግድ ተቋማትንና ነዋሪውን እያማረረና ህይወቱን እያመሰቃቀለ ከመሄድ ውጭ ምንም አይነት ለውጥ አልታየበትም፡፡ በከተማይቱ ውሃ ማግኘት እንደ ትልቅ እድል መቆጠር ጀምሯል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የከተማይቱ 75% ነዋሪ ውሃ እንደሚያገኝ ቢናገሩም መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን በተቃራኒው ሆኗል፡፡ ጊዜያቸውን በትምሀርት ገበታቸው ላይ በመገኘት ማሳለፍ ይገባቸው የነበሩ ተማሪዎች ውሃ ለመቅዳት ረዥም መንገድ ለመጓዝ በመገደዳቸው የትምህርት ጊዜአቸው እየተበደለ ይገኛል፡፡ በአጠቃላይ ከተማይቱን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ የከተማይቱ ነዋሪ ለሚገፋው አስቸጋሪ ህይወት ተጠያቂ ነው፡፡ ድርጅቱ አገሪቱን የመምራት ብቃት እንደሌለውም የወቅቱ የአዲስ አበባ ሁኔታ አይነተኛ ማሳያ ነው፡፡ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የከተማይቱ ነዋሪ እየገፋው የሚገኘውን ፈታኝ ህይወት በማጥናት ህዝቡን በተለይም የከተማውን እና የዙሪያ አካባቢዋን ነዋሪ በማደራጀት በቅርቡ ‹‹የእሪታ ቀን›› በማለት ሰይሞ በ1ወር ጊዜ ውስጥ ሠላማዊ ሠልፍ ለማድረግ የወሰንን መሆኑን እየገለፅን የአዲስ አበባና አካባቢዋ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፉ በሚደረግበት ቀን በነቂስ በመውጣት በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ለመግለፅ እንዲዘጋጁ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ድል የህዝብ ነው መጋቢት 11 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም

Thursday, 20 March 2014

የአዳማ ከተማ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ ወጣት ምርቱ ጉታ ታሰረ

በአዳማ ከተማ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ የሆነው ወጣት ምርቱ ጉታ ዛሬ መጋቢት 10 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ገደማ በተለምዶ ዠቅአለ ተብሎ በሚጠራው ገበያ አካባቢ መታሰሩን የከተማዋ የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጣት ተስፋዬ ዋቅቶላ ለፍኖተ ነፃነት ገለፀ፡፡ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው እንደገለፀው ዠቅአለ ተብሎ በሚጠራው ገበያ አካባቢ የሚገኙ አነስተኛ ነጋዴዎች የገበያ ስፍራው እንዲለቁ መጠየቃቸውን ተከትሎ ሲያሰሙ የነበረውን ብሶት እንደዜጋ ለማዳመጥ ከሞከሩ የአንድነት አባላት መካከል ወጣት ምርቱ ጉታን አስረውታል፡፡ ወጣት ምርቱ ጉታ በአሁኑ ሰዓት በአዳማከተማ ፖሊስ መንሪያ የወረዳ4 ፖሊስ ጽ/ቤት ውስጥ እንደሚገኝ የታወቀ ሲሆን በአዳማ ከተማ የአንድነት ጽ/ቤት ለማሰራጨት የተዘጋጀውን በራሪ ወረቀትና “ግጥም ለነፃነት” በሚል መሪቃል በአዳማ የአንድነት ጽ/ቤት በወሩ መጨረሻ ለሚዘጋጀው የኪነጥበብ ምሽት የተዘጋጀውን የፖስተር ንድፍ በእጁ ይዞ በመገኘቱ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑ ታውቋል፡፡ የአዳማ ከተማ የአንድነት ፓርቲ “ግጥም ለነፃነት” በሚል መሪ ቃል በጽ/ቤቱ በወሩ መጨረሻ የሚያደርገውን የኪነጥበብ ምሽት የከተማው ተወላጅ ለሆነችውና በህገወጥ እስር ለምትገኘው ለርዕዮት አለሙ መታሰቢያ እንደተሰየመ የከተማዋ የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጣት ተስፋዬ ዋቅቶላ ለፍኖተ ነፃነት ጨምሮ ገልጧል፡

Wednesday, 19 March 2014

1000 Days in Jail for Ethiopian Journalist Reeyot Alemu

March 16, 2014 marked the 1000th day of imprisonment for Ethiopian journalist Reeyot Alemu. She is serving a five-year sentence after she was found guilty on terrorism charges in January 2012.
Jailed Ethiopian journalist Reeyot Alemu. Photo via Facebook page of Free Reyoot Alemu campaign. Reeyot, an English teacher, is the recipient of the UNESCO-Guillermo Cano World Press Freedom Prize, the Hellman/Hammett award, and the International Women’s Media Foundation Courage in Journalism Award. According to the Committee to Protect Journalists, the Ethiopian government has convicted 11 independent journalists and bloggers including Reeyot and Eskinder Nega under a sweeping anti-terrorism law since 2011. Among those jailed are two Swedish journalists who are serving an 11-year sentence for allegedly supporting an ethnic Somali rebel group. In this blog post, blogger BefeQadu Z Hailu described the plight of imprisoned Ethiopian journalists: If the objective of imprisonment is to correct the convicted ones, then to encourage reading and education should be one of the tools to meet the objective. In Kality prison both are allowed but not easily to these journalists and others who are convicted in relation to ‘terrorism’. These prisoners are not allowed to get books. Eskinder says, “Especially those kinds of books that have titles combining words of ‘Ethiopia’ and ‘history’ are not allowed in.” The same is true to the ward of Reeyot Alemu and others such as Wubshet Taye, Bekele Gerba, etc. Local independent newspapers and magazines are not also allowed in; Eskinder further explained it to me that even News TV channels like BBC and Al Jazeera are not allowed to be viewed in zones where he and others are imprisoned. Reeyot Alemu, after a tough struggle with the prison admins and after the media revealed the story, is now allowed to get distance education. But, it is still difficult for her to get supplementary books other than the books directly sent to her from the College. Twitter users sent out tweets using the hashtag #ReeyotAlemu to express their support for the jailed journalist. Below are a sample of tweets: Read More :HERE

በኩዌት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ አሳሳቢ ሆኗል

በዚህ ሳምንት አትክሮት ማግኘት ከሚፈልጉ ወገኖቻችን በዋነኝነት በኩዌት የሚኖሩ እና በስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ናቸው:: ባሳለፍነው ቀናት በዋና ዜናነት በአገሪቱ የስፖርት ሚኒስትር መኖሪያ ቤት ውስጥ የምትሰራ ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ የአሰሪዋን ሴት ልጅ ገላለች ተብሎ የተዘገበውን ዜና ተከትሎ ኢትዮጵያውያን በስጋት ላይ ሲሆኑ እንዲሁም ተከራካሪ የዜግነት መብታቸውን የሚያስከብር ኤምባሲ መጥፋቱ እና በኤምባሲው የሚፈጸመውን ደባ በከፊል ለማየት እንሞክራለን:: በአሁኑ ወቅት በኩዌት ለኢትዮጵያውያን ነገሮች ሁሉ አስቀያሚ እና አስቸጋሪ እየሆኑ እንደሆን ለኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ቅርብ የሆነ ኢትዮጵያዊ ገልጿል::ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደረጉ በደሎች ተከራካሪ የመንግስት አካል እና የኤምባሲ ሰው መጥፋቱ ለአሁኑ ወንጀል መፈጸም እና ስጋት መንስኤ እንደሆነ ጠቁሟል::በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሱ በደሎች እና ከአሰሪዎቻቸው እና ከቀጣሪ ድርጅቶች ጠፍተው የሚመጡ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሃገራቸው መመለስ ሲገባው ከደላሎች ጋር በመመሳጠር ሌላ ስራ በማስገባት ችግሩ እንዲሰፋ ያደረገው እምባሲው እና ሆዳም ዲፕሎማቶቹ ናቸው ሲል ይኸው የኮሚኒቲው ሰው ገልጿል:: ኢትዮጵያውያን በኩዌት እስር ቤት እየተሰቃዩ ከፍተኛ ወጪ ከኤምባሲው እና ከኮሚኒቲው በማውጣት ደግሰው በመጨፈር ላይ በነበሩበት ሰአት ከዚህ ቀደም ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠማቸው ሲሆን ወገኖቻችን በእስር ቤት እየተሰቃዩ ለምን እንዲህ አይነት ድግስ ይደገሳል:: አስፈላጊውን ወጪ በማድረግ ወደ ሃገራቸው የሚመለሱ ይመለሱ ያሉ ወገኖችን የተለያየ የኤምባሲ ትብብር በመከልከል ወደኤምባሲው በር እንዳይደርሱ በማገድ ከፍተኛ የሆነ የግል ጥቅምን ያማከለ በደል እየተፈጸመ መሆኑን የኮሚኒቲው ሰው አጫውቶናል::ለማንም ተደግሶ የማያውቅ ኮሚኒቲው የኢትዮጵያ ሆኖ እያለ ለሌሎች ኢትዮጵያውያን እና ግለሰቦች ሳያገለግል የትግራይ ልማት ማህበር አላማን ሲያስተምር ይውላል ሲሉ አባላቱ ይተቹታል:: የታሰሩትን ለጊዜው ተወት አድርጓቸው እና የሃገራችንን መልካም ገጽታ እናስተዋውቅ እያሉ ለዜጎች አትኩሮት በመንፈግ አሁን ላለንበት ስጋት አብቅተውናል ሲሉ ኢትዮጵያውያን በማማረር ይናገራሉ:: ኮሚኒቲው ሲቋቋም ለታሰሩ እና ለተቸገሩ መፍትሄ ይሆናል ተብሎ የነበረ ቢሆንም በስሙ መካከል ህዳሴ የሚል ቃል በመጨመር ቢሮውን ከነበረበት ቦታ ወደ ኤምባሲው ውስጥ በማዘዋወር ፖለቲካ እየሰበከ ኢትዮጵያውያንን ረስቷል ሲሉ ይናገራሉ::ሌላው ነገር ይላሉ ኢትዮጵያውያኑ ማንኛውንም ደብዳቤ በኤምባሲውም ይሁን በኮሚኒቲው ማህተም ተደግፎ ቢጻፍ በኩዌት ውስጥ ተቀባይነት የለውም ሲሉ ይገልጻሉ::የመኖሪያ ፈቃድ ለማሳደስ በእጃችን ፓስፖርት እያለ ፓስፖርቱን ለመቀበል የኩዌት መኖሪያ ፈቃድ የሚያድሰው አካል ብዙ መጉላላት እና ወከባ እንደሚፈጽምባቸው እና ይህንንም ለኤምባሲው ሪፖርት ቢደረግ የራሳችሁ ጉዳይ የሚል ዘለፋ አዘል መልስ እንደሚሰጡ ታውቋል:: በግድያ ወንጀል ተጠርጥራ የተያዘችው ኢትዮጵያዊት ተከትሎ የመኖሪያ መታወቂያዎች እንዲታደሱ መደረግ የጀመረ ሲሆን ካሁን በፊት NON KUWAITI የሚል ሲጻፍ የነበረ ሲሆን በኣሁን ሰአት ለኢትዮጵያውያን በተለየ መልኩ Ethiopian ኢትዮጵያዊ የሚል መጻፍ የተጀመረ መሆኑ ታውቋል:: የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ምንም መከራከር የማይችል እና በመኪና ተገጭተው የሞቱ ታንቀው ራሳቸውን ከፎቅ ወርውረው የሞቱ ኢትዮጵያውያን ደብዛቸው እና የሞት ጉዳያቸው እንዳይነሳ ኮሚኒቴው በመሸፋፈን ለችግር እየዳረገን ነው ሲሉ በኮሚኒው ላይ አማረዋል::በ17 አመቷ ወደ ኩዌት የገባችው እና በአሁን ሰአት የ22 አመት ወጣት የሆነችው በግድያ ተጠርጥራ የተያዘችው ኢትዮጵያዊት በአሰሪዎቿ ልጆች የተደፈረች መሆኗን ለኤምባሲው ቅርብ የሆነ ግለሰብ ተናግሯል::ግድያውን ከመፈጸሟ በፊት በልጁ የተደፈረች እና ይህንን ጉዳይ ለሴት ልጂቷ ብትናገር የሚሰማት ያጣት እና የደበደቧት መሆኗን እና ይህንን ተከትሎ ወንጀሉን ፈጽማው ይሆናል የሚሉ ግምቶች በስፋት ይነገራል:: በኢምባሲው ውስጥ የሚደረገው ከፍተኛ በደል በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ሲሆን በኤምባሲው ውስጥ ከ400 እስከ 500 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን የሚገኙ ሲሆን: ከፍተኛ የሆነ መጉላላት እየደረሰባቸው ለኣእምሮ ጉዳት ለጭንቀት ለድብርት እና ለእብደት መዳረጋቸውን የገለጹ ሲሆን በኤምባሲው ውስጥ ከፍተኛ የምግብ እጥረት ያለ ሲሆን ኤምባሲው ግን በድግስ እየተንበሸበሸ ኮሚኒቲው በየድህረገጹ የፌሽታ ፎቶዎችን በመርጨት ከፌሽታው ጀርባ ግን የኢትዮጵያውያን ሞት እና ሰቆቃ ለእይታ እንዳይበቃ እያደረገ ሲሆን አንድም ቀን የሞቱ እና የተበደሉ ኢትዮጵያንን ቦታ ሳይሰጥ የኢትዮጵያውያን መብት እና ነጻነት ሳያስከብሩ በአደባባይ ስንገላታ እያዩን ያላግጡብናል ያመናጭቁናል ከፖሊስ ጋር ይተባበሩብናል በማለት አቤቱታቸውን የሚሰማ አካል እንዳላገኙ እና በስጋት አጣብቂኝ ውስጥ መግባታቸውን ኢትዮጵያውያን ተናግረዋል:: ተጨማሪ ዘገባዎች ካሉ እንመለሳለን::

YOUTH AGAINST INJUSTICE!

It should not take more than three youths who take personal injustice. On 1 March invited Andrew Selvig Odegaard, Juliane Therese Godager Thorbjørnsen and Darya Owren youth between 13 and 19 years to a workshop where freedom of expression and the case of the Ethiopian journalist Eskinder Nega were central. On the 13th March takes the next step with a solidarity action. Youth is again invited to turn ring on freedom of expression, literally. Andreas attending Amnesty's project management program . He will conduct a akjson where he focuses on journalists' freedom of expression and the unfair treatment of Eskinder Nega . The Ethiopian journalist has been given a prison sentence of 18 years for having made speeches criticizing the government, and to have required a greater protection of the right to freedom of expression. 1 March total Andreas, Juliane and Darya 30 enthusiastic youngsters to workshop to make alternative newspaper front pages to focus on Eskinder Nega his case. 13 March organized solidarity action where 30-40 young people to stand in a circle with their own "special paper" outside VG-house. The aim is to create awareness about the importance of freedom of expression and shed light on how fatal it can be when critical voices are silenced. The demonstration will take place on 13 March at 17.00 in front of VG-house, where you too can join in! In our meeting with Andreas tells him why this case engages him, and why he encourages everyone to join wanted to support the freedom of expression. Tell me about the first time you let yourself inspire by injustice? I've always had strong opinions and was particularly involved in the events around the world. But it was only in high school that I really realized that I could make that commitment and my strong opinions about the action. Therefore I joined Amnesty International. What inspires you to use your "voice"? What inspires me most is all the people around the world who have so much to lose by opening your mouth and say anything, but that still does. All those who sacrifice life and limb for what they believe in and and struggling against oppressive regimes and dictators. Here in Norway we are so protected, we live so well and safely. Of course, I use my voice when people without this protection and safety of dry doing it. What makes you passionate about this issue? The case of Eskinder Nega is a typical example of someone who has opened his mouth and meant something, in spite of the consequences it would get. Something that also fascinates me Eskinder is his endurance. He has now been jailed eight times but it does not seem to discourage him. It is so incredibly important that we can show him that there's more that believe on his wishes and dreams for Ethiopia. What made ​​you chose this particular form of expression? As a journalist, I think Eskinder would agree to free speech effect. The desire is to show that we in Norway are also incredibly addicted to this freedom. We can not turn the ring about Eskinder and his newspaper in Ethiopia, but we can turn the ring about a Norwegian newspaper and hope that people become aware. To use the newspapers to this campaign refers to Eskinder work as a journalist, but it is also about what is not in Norwegian newspapers. We have had to create new cover pages where freedom of speech and Eskinder Nega is at the center because the Norwegian newspapers simply do not write about issues that Eskinder her. What do you take personal injustice? For me it comes naturally, I realize just why I should accept the atrocities taking place in the world. I have grown up in a society based on openness, trust and fairness. Not a perfect society, but a good starting point. I see that there are infinitely large improvement in the world, and know that it is so small it takes that many could be better. Much of the world's population can not decide for themselves, they are bound to the will of a dictator or a corrupt regime. I had not accepted this, why am I accepting that others suffer the same fate?

Tuesday, 18 March 2014

የፈረሰው ቅንጅት ሶስት አራተኛው እንደተመለሰ ይሰማኛል፤ (የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ)

በአንድነት እና መኢአድ የዉህደት እንቅስቃሴ ላይ አስተያይተ የሰጡት የፓርላማ እና የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት አባል አቶ ግርማ ሰይፉ ምክር ቤቶቹ ይሄን ታሪካዊ ዉሳኔ ባሳለፉበት ወቅት የሚከተለውን ብለዋል።
«ዛሬ በመኢህአድ ፅ/ቤት የመኢህአድ እና የአንድነት ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት የጋራ ስብሰባ አድርገው አንድ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል። ይህውም ለቀጣይ ሐሙስ መጋቢት 11/2004 ዓ/ም የቅድመ ውህደት ሰምምነት እንዲደረግ እስከ አሁን ውህደቱን ለማዘግየት የተወሰደው ጊዜ ከበቂ በላይ በመሆኑ አጅግ አጭር በሆነ ጊዜ ውስጥ ይህን ጉዳይ አጠናቆ የጋራ ጉባዔውን የሚያመቻች ኮሚቴም በእለቱ ይፋ እንዲደረግ ከስምምነት ተደርሶዋል። እነዚህ ሁለት ፓርቲዎች ውህድ በሚሆኑበት ወቅት ፈታኝ ይሆናሉ የተባሉ የፕሮገራም እና የደንብ ልዮነቶች የሚባሉት ውሕዱን ፓርቲ የተሻለ ደንብና ፕሮግራም እንዲኖረው ከማድረግ የዘለለ ውህደቱን ለማዘግየት ምክንያት እንዳይደሉ መግባባት ላይ ተደርሶዋል። የውህዱን ፓርቲ ስያሜ በተመለከተም ተሳታፊዎቹ በአዲስ መሆን እንዳለበት እና ይህም ተጠንቶ ለጠቅላላ ጉባኤ ቀርቦ የሚወሰን እንደሆነ ግንዛቤ ተይዞዋል። ትልቁ ነጥብ የነበረው በሁለቱም ፓርቲዎች በኩል አመራሮች በምንም ሁኔታ ውህደቱን ለማዘግየት ቢሞክሩ አባላት ተዋሕደው አመራሮች ተንጠልጥለው እንደሚቀሩ በተደጋጋሚ የገለፁ ሲሆን ይህም በከፍተኛ ጭብጨባ ድጋፍ አግኝቶዋል። እውነት እውነት እላችኋለው ይህ ጉዳይ ከሁለት ወር ባልበለጠ ጊዜ እውን ይሆናል የሚል እምነት አለኝ። ይህ ከሆነ ደግሞ የፈረሰው ቅንጅት ሶስት አራተኛው እንደተመለሰ ይሰማኛል። ቸር ወሬ ያሰማን። የመጋቢት 11 ሰው ይበለን።»

Monday, 17 March 2014

የኦህዴድ አባላት በአቶ አለማየሁ ሞት ጉዳይ ጥያቄ እያቀረቡ ነው

የኦሮሚያ ክልል እና የኦህዴድ ፕሬዚዳንት የነበሩትና ሰሞኑን ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የአቶ አለማየሁ አቶምሳ የሞት መንስኤ እንዲጣራ የኦህዴድ መካከለኛና ዝቅተኛ ካድሬዎችና አባላት በየመድረኩ ጥያቄ እያነሱ መሆኑ ከፍተኛ አመራሩን ጭንቀት ውስጥ እንደጣለው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ፡፡ አቶ አለማየሁ ለሞታቸው መንስኤ የሆነው ከምግብ ጋር የተሰጣቸው መርዝ ነው የሚሉ መረጃዎች ኢሳትን ጨምሮ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ይፋ መሆኑን ተከትሎ አብዛኛዎቹ መካከለኛና ዝቅተኛ የድርጅቱ አባላትና ካድሬዎች የአቶ አለማየሁ ሞት በገለልተኛ ወገን ተጣርቶ እንዲቀርብ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ጥያቄ ማቅረብ ጀምረዋል፡፡ በተለይ ከአቶ አለማየሁ ሞት ጀርባ የቀድሞ የኦሮሚያ ፕሬዚደንት አቶ አባዱላ ገመዳ እጅ አለበት መባሉና ጉዳዩም ሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነትን ጠራርጎ ለማጽዳት አቶ አለማየሁ የጀመሩት እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ ሆን ተብሎ የተፈጸመ ነው በሚል መገለጹ አብዛኛውን የድርጅቱን አባላት ቁጭት ውስጥ ጥሏል፡፡ በዚህም ምክንያት አቶ አለማየሁ የጀመሩትን የኪራይ ሰብሳቢነትና የሙስና ትግል አጠናክረን እንቀጥላለን የሚሉ መፈክሮች በየወረዳውና በየቀበሌው በስፋት በመስተጋባት ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡ አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ላቸው የኦህዴድ አባል ለዘጋቢያችን እንደገለጹት የአቶ አለማየሁ ሞት እንዲጣራ ጣያቄ ሲቀርብ ከፍተኛ አመራሩ ይሄ የጸረ ሰላም ሃይሎች አሉባልታ ነው በሚል ምላሽ ለመስጠትና ለማጣጣል ሙከራ እንደሚያደርጉ አስታውሰው የሁሉን አመኔታ ለማግኘት ግን ፍረጃ ውስጥ ከመግባት ይልቅ ነገሩን በገለልተኛ ወገን ማጣራቱ ይቀል ነበር በማለት ነቀፌታውን አጣጥለውታል፡፡ አብዛኛው አባላት የአቶ አለማየሁ ሞት መንስኤ እንዲጣራ እየወተወተ መሆኑንና የዚህ ጥያቄ መመለስና አለመመለስ በድርጅቱ ቀጣይ ህልውና ላይ የራሱ የሆነ አዎንታዊም ሆነ አሉታዎ ሚና እንደሚኖረው አመልክተዋል፡፡ ይህ የኦህዴድ አባላትና ካድሬዎች ጥያቄ በተለይም የኦህዴድ ስራ አስፈጻሚ ኮምቴ አባላትን አስጨንቋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በቅርቡ የሰልጣን ሽግሽግና አዲስ ሹመት ያገኙትን ጨምሮ ኦህዴድን በመምራት ላይ የሚገኙት ስራ አስፈጻሚዎች አቶ ሙክታር ከድር ሊቀመንበር፣ወ/ሮ አስቴር ማሞ ምክትል ሊቀመንበር፣አቶ ዘላለም ጀማነህ፣አቶ ግርማ ብሩ፣አቶ አባዱላ ገመዳ፣አቶ ኩማ ደመቅሳ፣አቶ ሶፊያን አህመድ፣አቶ ድሪባ ኩማ፣አቶ አብዱልአዚዝ አህመድ አባላት መሆናቸው ይታወቃል፡፡

TPLF Security Agent Points Gun at Arrested Female Activist

Semayawi Party (Blue Party) updated its supporters and the world about the arrested party leaders and female activists prison experience. Semayawi Party- Ethiopia Some updates on arrested Blue Party’s members and leaders Lets share you some of the news from the prison we are disgusted with! A day before one of the girls called out late at night, the security guard took her to a room where there was a man namely Sami (Samson I think) who claim to be from security force and ordered her to sit. The talk was started with threatening and tricking. She reported to us that he told her they cannot be successful with peaceful struggle and asked what the Blues are trying to do if that does not work.
Emebet Girma, turned 18 this year was quite smart one, she explained to him “all the Blue members and supporter would not do such an act and we stand and struggle peacefully all the way till we are all arrested or killed for freedom with love and truth that for sure will set them free”… the replay that he got from the young girl irritates him and took out his gun and put it on the table… “I wasn’t disturbed,” she said. After a pause he pointed the gun at her and threatened her. She said, “he asked me what if he shoots me, and I told him to go ahead.” The brave young women told us this in the narrow window that ables visitors communicate with while the guards are watching every move and hear every word. While we talk one of the police was looking at us repulsively trying to warn us to stop with a scary facial expression. Yet she remained still and continued. “After some filthy threatening he started to talk to me as young girl who must act like the rest of the girls out there,” she said… and added he even asked her phone number after trying to sweetly talk to her. Past the drama she was returned to her cell hearing partially begging and somehow threatening speeches behind her, followed by the so called security force member ‘Sami’ and the same guard that took her out. We will keep you updated for more!

ሚሊየነች ድምጽ – ሸንጎና የኢትዮጵያ የሽግግር ምክር ቤት ለሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ አጋርነታቸውን ገለጹ !

ወደ ስድስት የሚጠጉ የፖለቲካና የየሲቪክ ማህበራት ስብስበ የሆነው የኢትዮጶያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት፣ በዚህ ሳምንት በዳያስፖራ ለተቋቋመው የሚሊዮኖች ድምጽ ግብረ ኃይል በጻፉት ደብዳቤ ፣ ድርጅታቸው፣ በአገር ቤት ከፍተኛ መስዋእትነት እየከፈሉ ላሉ ታጋዮች ያላቸዉን አድናቆትና አክብሮት በመገጽል፣ አገር ቤት እየተደረገ ያለዉን የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ ጎን እንደሚቆሙ አረጋገጡ። ድርጅቶቹ በደብዳቤ ድጋፋቸውን ከመግለጽ ባሻገር ፣ በግብረ ኃይሉ የሚሳተፉ ተወካዮችን የላኩ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ መሰረታዊ ለዉጥ እንዲመጣ ከተፈለገ የኢትዮጵያዉያን መሰባሰብ አስፈላጊ እንደሆነም አስምረዉበታል። ሸንጎም ሆነ የሽግግር ምክር ቤቱ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ አጀንዳዎችን በመያዝ ሕዝቡን ለትግል ለማነሳሳት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ የቆዩ፣ በተለያዩ ጊዜያትም አገር ቤት የሚደረገዉን ትግል ሲደግፉ የነበሩ ድርጅቶች እንደሆኑ ይታወቃል። በዳያስፖራ የተቋቋመው የዳያስፖራ ድምጽ ንቅናቄ ከሸንጎ እና የሽግግር ምክር ቤቱ በተጨማሪ በርካታ ድርጅቶችን በማሰባሰብ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ የሚሊዮኖችን ድምጽ በመደገፍ አንጻር ከፍተኛ መነሳሳት እየታየ ነው። ግብረ ኃይሉ ከአዲሲቷ ኢትዮጵያ ሶሊዳሪቲ ንቅናቄ፣ ከማርች ፎር ፍሪደም ሲቪክ ማህበር፣ ከኢትዮጵያዊነት ሲቪክ ማህበር፣ ሎስ አንጀለስ ከሚገኝ የኢትዮጵያ የዲሞክራሲኦና ሰብአዊ መብት ሲቪክ ማህበር ፣ ከቃሌ፣ ከደብተራዉ እና ከረንት አፌር ፓልቶክ ክፍልም አዎንታዊ ምላሽ እያገኘ ነው።

Sunday, 16 March 2014

በሕወሓት ጄኔራሎች እና በብኣዴን የጦር መኮንኖች መካከል ውጥረት ነግሷል::

ጄኔራል አበባውን ወደ ሲቭል ባለስልጣንነት የመቀየር እቅድ ተይዟል: ህገመንግስታዊ ጥያቄ ባነሱ ከጄኔራልነት እስከ ሻምበልነት ማእረግ ባላቸው የቀድሞው የኢሕዴን ታጋዮች እና የአሁን የብኣዴን የጦር መኮንኖች እና በሕወሃት ጄኔራሎች መካከል ከፍተኛ የሆነ የመብት ጥያቄዎችን ያማከለ እና ህገመንግስታዊ ስርኣትን ተከትሏል የተባለለት ጥያቄዎችን ተከትሎ ከፍተኛ ውጥረት መከሰቱን የመከላከያ ምንጮቻችን ጠቁመዋል:: ባለፉት ሰሞናት የተደረጉት ስብሰባዎች በከፍተኛ አለመግባባት የተበተኑ ሲሆን በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ በስፋት የፓርቲ ስራዎች እንጂ ሃገራዊ ስራዎች እየተሰሩ አይደለም የሚሉ እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊቱ ለህገመንግስቱ መከበር ተገኢ መሆን አለበት በአሁን ወቅት ለአንድ የፓርቲ አመራር እና ለፕሮፓጋንዳ ተገኢ ሆነናል የሚሉ ተመሳሳይ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በሰራዊቱ ውስጥ ያለውን የእድገት የትምህርት እና የደምወዝ መብትን በተመለከተም ከፍተኛ ክርከር ቢደረግም ካለመግባባት መኮንኖቹ ጥርስ እንደተነካከሱ ወደየመጡበት ተበታትነዋል:: የሰራዊት አባላትን ለመቀነስ በተደረገው ጥናት መሰረት ለምን ሁለት ብሄር ላይ አተኮረ የሚሉ ጥያቄ እንዲሁም የስኮላርሺፕ አድሏዊነት በተመለከተ ጠንከር ያሉ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን እንዲሁም ከአንድ ብሄር ለትምህርት ተመርጠው የሚላኩ መኮንኖች በዛው ሳይመለሱ ይቀሩና ነገሩ ይድበሰበሳል የሚሉ አስጨናቂ ጥያቄዎች ተከታትለው ቢነሱም ከመድረኩ መልስ ሳይሰጥባቸው ተድበስብሰው አልፈዋል::ከአንድ ብሄር ብቻ ተመርጠው ለትምሕርት አውሮፓና አሜሪካ ከሄዱት መኮንኖች 80 ከመቶ ያልተመለሱ ሲሆን ይህ ጉዳይ ተድበስብሶ ሌላው ብሄር ስኮላሺፕ እንዳያገኝ ምክንያት እየተፈጠር በዚያው ስለምትከዱ ሃገር ውስጥ በቂ አካዳሚ ስላለ እዚህ እንድንማር ይደረጋል::ስኮላሺፕ የሚሰጣቸው ለማይመለሱ መኮንኖች ነው የሚሉ አቤቱታዎች ተሰምተዋል:: በሕወሓት ጄኔራሎች እና በብኣዴን ከፍተኛ የጦር መኮንኖች መካከል የተነሳውን ፍጥጫ ተከትሎ ጄኔራል አበባውን ወደ ሲችል ባለስልጣንነት ለማዘዋወር የታቀደ መሆኑን የገለጹት ምንጮሽች በአሁን ሰአት ጄኔራሉ እንደ ቁም እስረኛ አብዛኛው ጊዜያቸውን በመኖሪያ ቤታቸው እንደሚያሳልፉ እና ወደ ቢሯቸው አልፎ አልፎ እንደሚገቡ ታውቋል:: የሳሞራ የኑስን ስልጣን ይረከባሉ ተብሎ የሚጠበቀው ጄኔራል አበባው ጄኔራል ዮሃንስን ወደ ሳሞራ ሕወሓት በሹመት አቅርቦ ካመጣቸው በኋላ ይተለያየ ተጽእኖ እየተደረገባቸው ቢሆንም የብኣዴን ፓርቲ አመራሮች ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተሉ ነው ቢባልም ምንም አይፈጥሩም የአሽከርነት ሚና ካልሆነ በስተቀር ሲሉ ምንጮሹ ገልጸዋል::የጄኔራል አበባው ስልጣን ማቆም እና ወደ ሲቭል ባለስልጣንነት መቀየር በሃገሪቱ የፖለቲካ ሂደት ላይ የሚያመጣው ለውጥ እንዳይኖር ሁኔታዎች እየተገመገሙ መሆኑ ታውቋል::ከዚህ ቀደም በተለያየ ወቅት ወደ ውጪ ለእረፍት ለመሄድ ጥያቄ ያቀረቡት ጄኔራል አበባው በተለያየ ምክንያት ሲሰናከልባቸው የቆየ ሲሆን እሳቸውን እና መሰላቸውን ከሰራዊቱ በዘዴ እና በብልሃት ገፍቶ ለማስወጣት በስፋት እየተሰራ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል::ካሁን ቀደም ሜጄር ጄኔራል የነበሩት አባዱላ ገመዳ አቶ ተብለው ወደ ሲችል ባለስልጣንነት ሲዘዋወሩ ሁለት ከፍተኛ የጦር ጄኔራሎች ደግሞ ወደ እስር ቤት መወርወራቸው አይዘነጋም:: ምንሊክ ሳልሳዊ

በጎንደር አድማ መርታችኋል የተባሉ 6 ታክሲ ሹፌሮች በእስር ቤት እየተንገላቱ ነው

ክሱን ከፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ለማገናኘት የሞከረው ፖሊስ አልተሳካለትም ምንሊክ ሳልሳዊ :- በጎንደር ከተማ የታክሲ ሹፌሮች የስራ ማቆም አድማ ላይ ተቃውሞ አሰምታችኋል አድማውን መርታችኋል በሚል ሰበብ የታሰሩ 6 ሰዎች እንዳሉ ከአከባቢው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል:: ከአንድ ወር በፊት የጎንደር ከተማ የታክሲ ሹፌሮች አዲሱን የትራፊክ የቅጣት ደንብ በመቃወም የስራ ማቆም አድማ መምታታቸውን ተከትሎ አድማውን አስተባብረዋል በሚል ሰበብ ተፈጥሮ ከየመንገዱ ከስራቸው እና ከየቤታቸው ታፍነው የተወሰዱ የታክሲ ሹፌሮች በእስር ቤት ውስጥ እየተሰቃዩ መሆኑን ለወሕኒ ቤት ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል:: ባለፈው ሳምንት ፍርድ ቤት ቀርበው የዋስትና መብታቸው ሳይከበር ወደ እስር ቤት የተመለሱት የታክሲ ሹፌሮች ከሰማያዊ ፓርቲ የመጣ ትእዛዝ ነው የስራ ማቆም አድማ ያደረጋችሁት በሚል ጉዳዩን ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር በሃሰት ለማገናኘት በፖሊሶች በሃይል ለማሳመን ጥረት ቢደረግም እንዳልተሳካ ምንጮቹ ገልጸው እስካሁን ምንም አይነት መረጃም ሆነ ማስረጃ መርማሪዎች በማጣታቸው በስራ ማቆም አድማ ላይ የተሳተፉ የታክሲ ሹፌሮችን በታሰሩት ላይ እንዲመሰክሩ በጥቅም እያግባቧቸው መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል:: በአድማው ወቅት የታክሲ ባለንብረቶችም የታሪፍ ማስተካከያ አለመደረጉን በመቃወም የታክሲ ሹፌሮቹን ተቀላቅለው የነበር ሲሆን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ባለስልጣናት ሾፌሮቹና ባለንብረቶቹ ወኪል ልከው እንዲነጋገሩ በጊኤው የጠየቁ ቢሆንም ሹፌሮቹ “የክልሉ መንግስት ወከሎችን በተደጋጋሚ የማሰር ልምድ ስላለው ወኪል አንልክም” ብለው እንደነበር ይታወሳል::

Thursday, 13 March 2014

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ግምገማ

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ያተኮረ ውይይት ጄኔቭ ስዊትዘርላንድ ውስጥ ዛሬ ተካሂዷል ። የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ባዘጋጁት በዚሁ ውይይት ላይ በኢትዮጵያ ይፈፀማሉ የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በዝርዝር ቀርበዋል።
መንግሥት የሰብዓዊ መብት አያያዙን እንዲያሻሽል ያግዛሉ የተባሉ ሃሳቦችም ተሰንዝረዋል ። በስበሰባው ላይ የተካፈሉት የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች ለተሰነዘሩት ወቀሳዎች የበኩላቸውን መልስ መስጠታቸው ተገልጿል ።በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ያተኮረው ውይይት ዛሬ የተደረገው ከ25,ተኛው የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጉባኤ ጎን ለጎን ነው ። የውይይቱ ዓላማም በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ያተኮረ ዝርዝር ዘገባ ለተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በመጪው ግንቦት ከመቅረቡ አስቀድሞ ስለሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው ። ስበስባውን ካዘጋጁት ዓለምዓቀፍ ድርጅቶች አንዱ መቀመጫውን ጆሃንስበርግ ደቡብ አፍሪቃ ያደረገው ሲቪኩስ የተባለው ድርጅት የፖሊሲና የጥብቅና ጉዳዮች መኮንን ቶር ሆድንፌልድ ስብሰባው በተለይ በሶስት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መወያየቱን ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።
ከነዚህም እጎአ በ2009 ዓም የወጣው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራት ህግ አንዱ ነው ። ህጉ ከባድ ተፅዕኖ ማሳደሩና መዘዞቹም በውይይቱ መነሳታቸውን ሆድንፌልድ ገልፀዋል ። « በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ መብት ለሚታገሉ ድርጅቶች በሚለገሰው ዓለም ዓቀፍ የገንዘብ እርዳታ ላይ በተጣሉትን ገደቦች ላይ ተነጋገግረናል በዚህ ህግ ምክንያት በኢትዮጵያ ዓለም ኦቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች አይሰሩም ። በርካታ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶችም ከሰብዓዊ መብት ጋር የተገናኙ ሥራዎች ማካሄድ አቁመዋል ወይንም ከነጭራሹ ተዘግተዋል » መድረኩ ትኩረት ሰጥቶ የተወያየበት ሌላው ጉዳይ ደግሞ ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት ላይ ያደርጋል የተባለው ጫና ነበር ። «ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከተገቢው የህግ ሂደት ውጭ እንዲሁም በልዩ ደንቦች ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት ላይ የተጣሉትን ገደቦችም በውይይቱ ተነስተዋል ። በተለይ ስብሰባው በኢትዮጵያ 12 ጋዜጠኞች በቨረ ሽብሩ ህግ ምክንያት መከሰሰሳቸውኢትዮጵያ ውስጥ በህጋዊ መንገድ የጋዜጠኝነት ተግባራቸውን ሲያከናውኑ ርዕዮት ዓለሙና እስክንድር ነጋ የመታሰራቸውም ጉዳይ ላይም ትኩረት ሰጥቶ ተነጋግሯል ። ሆድንፌልድ እንደሚሉት በውይይቱ በኢትዮጵያ የነጻ ሚዲያ መገደብም ተነስቷል ። በጎርጎሮሳውያኑ 2012 5ጋዜጦች መዘጋታቸው በአሁኑ ሰዓትም ኢንተርኔ ት ከሚጠበቀው በላይ ቅድመ ምርመራ ይካሄድበታል ዓለም ዓቀፍ መገናኛ ብዙሃንንና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችን የሚያነሱ ድረገፆች በኢትዮጵያ እንዳይሰሙና እንዳይታዩ በመንግሥት ይታገዳሉ ሲሉ ተወያዮቹ መገለፃቸውን ተናግረዋል ሆድንፌልድ የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ መብት አያያዙን እንያሽሽልም ሃሳቦች ተሰንዝረዋል ። « የ2009 ዓም የበጎ አድራጎት ና የሲቪክ ማህበራት መተዳደሪያ ደንብ እንዲሰረዝ ወይም እንዲሻሻል ሁለተኛ የፀረ ሽብር ህግ በደል መፈፀሚያና ጋዜጠኖችን ማፈኛ እንዳይሆን እንዲሰረዝ በፀረ ሽብሩ ሕግ ምክንያት የታሰሩ ጋዜጠኞችና የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች በሙሉ እንዲፈቱ እንዲሁም ተቃዋሚዎችና ሰላማዊ ሰልፈኞች ከሚቀጥለው ዓመት ምርጫ በፊት የመሰብሰብ መብታቸውን እንዲጠቀሙ እንዲደረግ ሃሳብ ቀርቧል ።» ዶቼቬለ ስለ ውይይቱ ና ስለተሰጡት አስተያየቶች የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮችን ለማነጋገር ያደረገው ሙከራ አልተሳካም ። ሆኖም በውይይቱ ላይ የተካፈሉት የሰብዓዊ መብት ተመራማሪው አቶ ያሬድ ኃይለ ማርያም ያኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮችለመድረኩ የሰጡትን አስተያየት አጋርተውናል ። ሂሩት መለሰ

Ethiopia: Hackers Without Borders

March 11, 2014 by Joshua Kopstein The New Yorker Photograph: Raphael Satter/AP Before Edward Snowden sparked a global debate about government surveillance, it was a fact of life for Tadesse Kersmo. During Ethiopia’s national elections, in 2005, he and his wife campaigned for the country’s pro-democracy party, the Coalition for Unity and Democracy, which achieved a sweeping victory in the capital of Addis Ababa. But, when the results were overturned and protests broke out amid allegations of fraud, the ruling party quickly began cracking down on the opposition. Observers from the European Union reported extensive human-rights violations in the months that followed, including nearly two hundred demonstrators killed by security forces and tens of thousands more imprisoned. Kersmo evaded arrest and moved to the countryside, but his ties to the opposition subjected him to continued threats, harassment, and intense monitoring long after the election. “It is common wisdom that the phones are tapped,” he told me, in a tired baritone, over Skype. “People would call me and tell me, ‘We are following you, we know what you’re doing, we know where you are.’ ” On three separate occasions between 2005 and 2007, Kersmo was detained and beaten. At one point, he was told that his family would find his dead body in the streets, because the prisons were filled to capacity. When that seemed imminent, in 2009, Kersmo and his wife fled to the U.K., where they were granted asylum. There he continued his work as a university lecturer and a senior member of Ginbot 7, an exiled pro-democracy party that the Ethiopian government labelled a terrorist group in 2011, under a vague and widely condemned proclamation. Kersmo and his wife thought that their new life in the U.K. would take them out of the government’s sights. But, in April of last year, Kersmo read a report from the University of Toronto’s Citizen Lab, a nonprofit research group that scans the Internet to expose government-sponsored spyware and cyberattacks, showing evidence of a malware campaign targeting Ethiopian dissidents. The report describes a malicious file that, when opened, silently installs monitoring software on the victim’s computer. When Kersmo noticed that the malware “baited” its victims using photos of Ginbot 7 members, including those of himself, he decided to have his machine examined by Citizen Lab. The group found traces of FinSpy, part of an “intrusion” software suite known as FinFisher, which first made headlines in 2011, after a sales contract was discovered inside the headquarters of the Egyptian secret police, following the ouster of President Hosni Mubarak. The spyware was capable of stealthily transmitting Kersmo’s chats, Web searches, files, e-mails, and Skype calls to a server somewhere in Ethiopia. “The feeling was shock—that they are still following us, even here,” Kersmo told me. “It goes beyond my personal security. All Ethiopians living in the U.K., United States, and elsewhere are unsafe now.” The other week, Privacy International, a U.K.-based human-rights organization, filed a criminal complaint on Kersmo’s behalf, making him the first U.K. resident to challenge the use of hacking tools by a foreign power. “This case would be important to all refugees who end up in countries where they think they are safe,” Alinda Vermeer, a lawyer with Privacy International, who filed Kersmo’s complaint, told me in a phone interview. That sense of safety is illusory, she said, because countries armed with tools like FinSpy insure that refugees “can be spied on in an equally intrusive way as they were back at home.” Worse, the surveillance also reveals with whom the victims have been communicating, potentially endangering the lives of contacts and relatives still residing in their home country. Kersmo’s dilemma is becoming more common, particularly among journalists and activists seeking political freedoms beyond their country’s borders. The Electronic Frontier Foundation recently filed a suit similar to Kersmo’s against the Ethiopian government, on behalf of a U.S. citizen living near Washington, D.C., where most of the country’s Ethiopian-American population lives. (Fearing government reprisal, the plaintiff asked to use a common Ethiopian name, “Kidane,” as a pseudonym during the proceedings.) In a different report, released last month, Citizen Lab revealed evidence of an attack on Ethiopian Satellite Television, a news service with offices in the U.S. that serves as an alternative to state-controlled media in Ethiopia. A mysterious source had made three attempts to send malicious files to employees, claiming that they were news articles; the files contained a small program that exploits a security flaw in Microsoft’s Windows operating system, allowing it to silently install Remote Control System, a spyware tool similar to FinSpy. The growing surveillance-technology industry—including the companies Gamma International and Hacking Team, the European developers of FinSpy and Remote Control System—has been valued at five billion dollars. Proponents defend such commercial spyware by noting that it helps authorities catch terrorists and other serious criminals. But Gamma will not disclose which countries it sells its products to, nor is it particularly eager to take responsibility for how they are used. In 2012, Martin J. Muench, the company’s founder, told Bloomberg News that his company has “no control; once it’s out there it’s basically with the country” to use the tools ethically. (Gamma did not respond to a request for comment.) The Milan-based Hacking Team claims that it monitors its software, and has the ability to disable functionality if it believes that clients “have used Hacking Team technology to facilitate gross human rights abuses.” According to its customer policy, the company’s sales are reviewed by “an outside panel of technical experts and legal advisors,” which looks for “red flags,” including “credible government or non-government reports reflecting that a potential customer could use surveillance technologies to facilitate human rights abuses.” Like Gamma, Hacking Team also refuses to name which countries use its products, but it denied allegations in a recent report by Citizen Lab that claimed Remote Control System was used in twenty-one countries, including Azerbaijan, Uzbekistan, Saudi Arabia, and Sudan. A spokesperson, Eric Rabe, told Mashable that the Citizen Lab report is “not an accurate list of nations where Hacking Team clients are located,” but refused to elaborate on the company’s vetting process. Regardless, the increased scrutiny of commercial spyware has led some countries to tighten regulations regarding its sale, particularly across national borders. In 2012, the U.K. government informed Gamma, which has offices in Andover, England, that it needs to obtain licenses to sell FinSpy outside the country, citing laws that control the export of cryptography. Alinda Vermeer, of Privacy International, explained that, while export controls under the Wassenaar Arrangement—which regulates weapons and technologies with potential military applications within forty-one nations—were recently updated to restrict spyware, the new terms haven’t yet been adopted by all participating countries. This means that, while future deals will be regulated in some countries, past purchases and current efforts from spyware companies around the world have relatively few rules to follow—and more people like Kersmo are bound to get caught in the crosshairs. “There is a social obligation for corporations,” Kersmo said. “Selling this kind of software to irresponsible governments is irresponsible.” Joshua Kopstein is a cyberculture journalist from New York City.

Wednesday, 12 March 2014

የአውሮፓ ሕብረት በአዲስ አበባ መንግስትን እና ተቃዋሚዎችን እያነጋገረ ነው

የፖለቲካ ምህዳር መስፋት፣ የ2007 ምርጫ፣ የታሳሪዎች ጉዳይ በአጀንዳነት ተነስቷል ከዘሪሁን ሙሉጌታ በአውሮፓ ኅብረት የአፍሪካና የኢትዮጵያ ቋሚ አምባሳደር የኢትዮጵያ መንግስትንና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን እያነጋገረ ነው። የኅብረቱ ቋሚ አምባሳደር አማካኝነት መካሄድ የጀመረው ውይይት በሀገሪቱ የፖለቲካ መህዳር መስፋት፣ በ2007ቱ ምርጫ፣ ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች እንዲሁም በሀገሪቱ ስላለው የሰብአዊና የዴሞክራሲ መብቶች ዙርያ መሆኑ ታውቋል። ባለፈው ዓመት የኅብረቱ ቋሚ አምባሳደር በመሆን የተሾሙት አምባሳደር ቻንታል ሔብሪች ኅብረቱን በመወከል በኢትዮጵያ ውስጥ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የበለጠ የሚከበሩበትን ገንቢ አማራጭ እያፈላለጉ ነው። በዚህም የአምባሳደሯ እንቅስቃሴ መሠረት የካቲት 26 ቀን 2006 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በመገኘት ከሌሎች የአውሮፓ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር በመሆን በሀገሪቱ አጠቃላይ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ዙሪያ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ውይይት አካሂደዋል። አምባሳደሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ውይይት ካካሄዱ ከአምስት ቀናት በኋላ በሀገሪቱ ካሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አንዱ ከሆነው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራር አባላት ጋር በጽ/ቤታቸው ውይይት አካሂደዋል። በአውሮፓ ኅብረት የአፍሪካና የኢትዮጵያ አምባሳደር ቻንታል ሔብሪች ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ጋር በተወያዩበት ወቅት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳሩ ዴሞክራሲያዊ ሕጋዊ መሠረት የተከተለ እንዲሆን የኢትዮጵያ መንግስት በርካታ ስራዎችን እየሰራ ላይ ቢሆንም፤ የበለጠ መሻሻል በሚገባቸው ቀሪ ስራዎች መወያየታቸው መዘገቡ ይታወሳል። በተጨማሪም በመጪው ዓመት የሚካሄደው ብሔራዊ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ በሚሆንበት ጉዳይ ላይ መወያየታቸው አይዘነጋም። በተመሳሳይ ባለፈው ሰኞ መጋቢት 1 ቀን 2006 ዓ.ም በአውሮፓ ኅብረት ጽ/ቤት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራውና የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ከኅብረቱ አምባሳደር ቻንታል ሔብሪች እንዲሁም በአውሮፓ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድና የህንድ ውቅያኖስ ክፍል ኃላፊ ጋር ውይይት አካሂደዋል። በውይይቱም በአጠቃላይ ፓርቲው እያደረገ ስላለው እንቅስቃሴና “የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት” በሚለው የፓርቲው ክፍል ሁለት ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ላይ ማብራሪያ መጠየቃቸውን፣ የገዢው ፓርቲ የመሬት ፖሊሲ በሀገሪቱ መሬት የጥያቄ የኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ጥያቄ በመሆኑ በጥቅሉ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ጤናማ እንዳይሆንና መንግስታዊ የሙስና ሥርዓት እንዲጎለብት መደረጉን አርሦ አደሩም ከድህነት እንዳይወጣ በማድረግ ዋነኛ የዴሞክራሲ ማፈኛ መሆኑን ማስረዳታቸውን በውይይቱ የተሳተፉት አቶ ሀብታሙ አያሌው ለሰንደቅ ጋዜጣ ገልፀዋል። ከዚህ ጎን ለጎን በእስር ስለሚገኙ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች የፓርቲው አመራሮችን በተመለከተ ማብራሪያ መስጠታቸውን፣ አቶ አስራት ጣሴ ስለታሰሩበት ምክንያት፣ ምርጫ 2007 ላይ ፓርቲው ስላለው አቋም፣ በኢትዮጵያ የመብት ጥሰቱ በምን ደረጃ ላይ እንዳለና በስቴት ዲፓርትመንት ሪፖርት፣ የሚዲያ ሞኖፖሊና የግል ፕሬሱ ወዳከም ጋር የተያያዙ ችግሮች ዙሪያ ውይይት ማካሄዱን ከአቶ ሀብታሙ ገለፃ መረዳት ተችሏል። በመጪው ሚያዚያ ወር ብራስልስ ላይ የአውሮፓ ኅብረትና የአፍሪካ ኅብረት በሚያካሂዱት የግራ ስብሰባ ላይ የአንድነት ፓርቲ ተወካይ ተገኝቶ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ንግግር እንዲያደርግ ጥያቄ መቅረቡንም አቶ ሀብታሙ አያይዘው ገልፀዋል። የአውሮፓ ኅብረት በገዢው ፓርቲ እና በተቃዋሚዎች መካከል ገንቢ ውይይት ተደርጎ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱ ከፍ ማድረግ አለበት ያሉት አቶ ሀብታሙ፣ ይህ ካልሆነ ግን በምስራቅ አፍሪካ አደገኛ ወደሆነ የፖለቲካ አለመረጋጋት ሊፈጠር እንደሚችል ገልፀዋል። የአውሮፓ ኅብረት ከተለያዩ ሀገራት ጋር ሰፊ የልማት፣ የቴክኒክ ድጋፎች እንደሚያደርግ ይታወቃል። በምትኩ ሀገራቱ የዜጎቻቸውን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲያከብሩ ከፍተኛ ግፊት ያደርጋል። ኢትዮጵያም የሎሜ ኮንቬንሽንን እ.ኤ.አ በ1975 ዓ.ም ከፈረመች ጊዜ አንስቶ ከኅብረቱ ጋር የልማት ትብብር መስርታለች፤ ኅብረቱም በአውሮፓ የልማት ፈንድ (European Development Fund) (EDF) እገዛ ያደርጋል። በተለይ በትራንስፖርት፣ በገጠር ልማት፣ ባልተማከለ የማኅበራዊ አገልግሎት ድጋፍ፣ በንግድ፣ በጾታ በሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ እና በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ ሀገሪቱን ይደግፋል። የድጋፍ መጠኑም በቅርቡም ወደ 600 ሚሊዬን ፓውንድ ይደርሳል። አዲሲቷ የኅብረቱ ቋሚ አምባሳደር በመንግስትና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል የተካረረውን ግንኙነት በማለዘብና ወደ ገንቢ ውይይት እንዲመጡ ማበረታታታቸው በበጎ ዓይን እየታየላቸው ነው። አምባሳደር ቻንታል ባለፈው ዓመት የሹመት ደብዳቤአቸውን ከማስገባታቸው በፊት በአውሮፓዊቷ ኪርጊስታን ሀገር የኅብረቱ ቋሚ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል። የቤልጂየም ተወላጅ የሆኑት አምባሳደር ቻንታል በኢትዮጵያ የኅብረቱ ቋሚ አምባሳደር የነበሩትና ባለፈው ግንቦት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን የሀገራቸውን ልጅ አምባሳደር ቫቪየር ማርሻልን ተክተው ወደ ኢትዮጰያ መምጣታቸው ይታወሳል። (ዜናው የተገኘው ዛሬ በአዲስ አበባ ከታተመው ሰንደቅ ጋዜጣ ነው) Ze-Habesha
Tadesse Kersmo Before Edward Snowden sparked a global debate about government surveillance, it was a fact of life for Tadesse Kersmo. During Ethiopia’s national elections, in 2005, he and his wife campaigned for the country’s pro-democracy party, the Coalition for Unity and Democracy, which achieved a sweeping victory in the capital of Addis Ababa. But, when the results were overturned and protests broke out amid allegations of fraud, the ruling party quickly began cracking down on the opposition. Observers from the European Union reported extensive human-rights violations in the months that followed, including nearly two hundred demonstrators killed by security forces and tens of thousands more imprisoned. Kersmo evaded arrest and moved to the countryside, but his ties to the opposition subjected him to continued threats, harassment, and intense monitoring long after the election. “It is common wisdom that the phones are tapped,” he told me, in a tired baritone, over Skype. “People would call me and tell me, ‘We are following you, we know what you’re doing, we know where you are.’ ” On three separate occasions between 2005 and 2007, Kersmo was detained and beaten. At one point, he was told that his family would find his dead body in the streets, because the prisons were filled to capacity. When that seemed imminent, in 2009, Kersmo and his wife fled to the U.K., where they were granted asylum. There he continued his work as a university lecturer and a senior member of Ginbot 7, an exiled pro-democracy party that the Ethiopian government labelled a terrorist group in 2011, under a vague and widely condemned proclamation. Kersmo and his wife thought that their new life in the U.K. would take them out of the government’s sights. But, in April of last year, Kersmo read a report from the University of Toronto’s Citizen Lab, a nonprofit research group that scans the Internet to expose government-sponsored spyware and cyberattacks, showing evidence of a malware campaign targeting Ethiopian dissidents. The report describes a malicious file that, when opened, silently installs monitoring software on the victim’s computer. When Kersmo noticed that the malware “baited” its victims using photos of Ginbot 7 members, including those of himself, he decided to have his machine examined by Citizen Lab. The group found traces of FinSpy, part of an “intrusion” software suite known as FinFisher, which first made headlines in 2011, after a sales contract was discovered inside the headquarters of the Egyptian secret police, following the ouster of President Hosni Mubarak. The spyware was capable of stealthily transmitting Kersmo’s chats, Web searches, files, e-mails, and Skype calls to a server somewhere in Ethiopia. “The feeling was shock—that they are still following us, even here,” Kersmo told me. “It goes beyond my personal security. All Ethiopians living in the U.K., United States, and elsewhere are unsafe now.” The other week, Privacy International, a U.K.-based human-rights organization, filed a criminal complaint on Kersmo’s behalf, making him the first U.K. resident to challenge the use of hacking tools by a foreign power. “This case would be important to all refugees who end up in countries where they think they are safe,” Alinda Vermeer, a lawyer with Privacy International, who filed Kersmo’s complaint, told me in a phone interview. That sense of safety is illusory, she said, because countries armed with tools like FinSpy insure that refugees “can be spied on in an equally intrusive way as they were back at home.” Worse, the surveillance also reveals with whom the victims have been communicating, potentially endangering the lives of contacts and relatives still residing in their home country. Kersmo’s dilemma is becoming more common, particularly among journalists and activists seeking political freedoms beyond their country’s borders. The Electronic Frontier Foundation recently filed a suit similar to Kersmo’s against the Ethiopian government, on behalf of a U.S. citizen living near Washington, D.C., where most of the country’s Ethiopian-American population lives. (Fearing government reprisal, the plaintiff asked to use a common Ethiopian name, “Kidane,” as a pseudonym during the proceedings.) In a different report, released last month, Citizen Lab revealed evidence of an attack on Ethiopian Satellite Television, a news service with offices in the U.S. that serves as an alternative to state-controlled media in Ethiopia. A mysterious source had made three attempts to send malicious files to employees, claiming that they were news articles; the files contained a small program that exploits a security flaw in Microsoft’s Windows operating system, allowing it to silently install Remote Control System, a spyware tool similar to FinSpy. The growing surveillance-technology industry—including the companies Gamma International and Hacking Team, the European developers of FinSpy and Remote Control System—has been valued at five billion dollars. Proponents defend such commercial spyware by noting that it helps authorities catch terrorists and other serious criminals. But Gamma will not disclose which countries it sells its products to, nor is it particularly eager to take responsibility for how they are used. In 2012, Martin J. Muench, the company’s founder, told Bloomberg News that his company has “no control; once it’s out there it’s basically with the country” to use the tools ethically. (Gamma did not respond to a request for comment.) The Milan-based Hacking Team claims that it monitors its software, and has the ability to disable functionality if it believes that clients “have used Hacking Team technology to facilitate gross human rights abuses.” According to its customer policy, the company’s sales are reviewed by “an outside panel of technical experts and legal advisors,” which looks for “red flags,” including “credible government or non-government reports reflecting that a potential customer could use surveillance technologies to facilitate human rights abuses.” Like Gamma, Hacking Team also refuses to name which countries use its products, but it denied allegations in a recent report by Citizen Lab that claimed Remote Control System was used in twenty-one countries, including Azerbaijan, Uzbekistan, Saudi Arabia, and Sudan. A spokesperson, Eric Rabe, told Mashable that the Citizen Lab report is “not an accurate list of nations where Hacking Team clients are located,” but refused to elaborate on the company’s vetting process. Regardless, the increased scrutiny of commercial spyware has led some countries to tighten regulations regarding its sale, particularly across national borders. In 2012, the U.K. government informed Gamma, which has offices in Andover, England, that it needs to obtain licenses to sell FinSpy outside the country, citing laws that control the export of cryptography. Alinda Vermeer, of Privacy International, explained that, while export controls under the Wassenaar Arrangement—which regulates weapons and technologies with potential military applications within forty-one nations—were recently updated to restrict spyware, the new terms haven’t yet been adopted by all participating countries. This means that, while future deals will be regulated in some countries, past purchases and current efforts from spyware companies around the world have relatively few rules to follow—and more people like Kersmo are bound to get caught in the crosshairs. “There is a social obligation for corporations,” Kersmo said. “Selling this kind of software to irresponsible governments is irresponsible.” Joshua Kopstein is a cyberculture journalist from New York City. Photograph: Raphael Satter/AP

frontline club oslo in the Name of Democracy . Land Grabbing ....

)

Monday, 10 March 2014

ኢህአዴግ ዳግም በክፍፍል ጎዳና...? (ተመስገን ደሳለኝ)

ከዚህ ቀደም በተለያየ ጊዜ በተዘጋጁ ሁለት ፅሁፎች፣ የድህረ መለስን ኢህአዴግ የኃይል አሰላለፍ ለማመልከት መሞከሬ የሚታወስ ቢሆንም፤ ዛሬም ያልተጠበቁ ክስተቶችን ማስተዋላችን አልቀረም፡፡ በርግጥ «አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ ፪» በሚል ርዕስ ቀርቦ በነበረው ተጠየቅ ከሞላ ጎደል ሀገሪቷን እንደንጉስ ሚካኤል ከጀርባ ሆነው የሚያሽከረክሯት ህወሓት እና ብአዴን መሆናቸው የተጠቀሰበት አውድ ብዙም አልተቀየረም፡፡ ይሁንና በኦህዴድ እና ደኢህዴን ውስጥ እየታየ ያለው የእርስ በእርስ መተጋገል መደምደሚያ ምናልባት ወቅታዊውን መልከአ ኢህአዴግ ሊለውጠው የሚችልበት አጋጣሚ እንዳለ እገምታለሁ፤ ማን ያውቃል? ...እነዚህን ኩነቶች ታሳቢ አድርገን የገዢው ፓርቲ አክራሞትን በአዲስ መስመር ጨርፎ ወደመመልከቱ እንለፍ፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ «ብላቴኖች» ክልሉን የሚያስተዳድረው የደኢህዴን የአመራር አባላት በስርዓቱ ልሂቃን የፖለቲካ ግምገማ ገና «ብላቴና» ተደርገው የሚወሰዱበት የትምክህት ዘመን አላከተመም፡፡ በርግጥ ድርጅቱ ደርግን ለመጣል በተደረገው የትጥቅ ትግል ላይ የተሳተፈ ባለመሆኑ፣ ዛሬም ፖለቲካን (ሀገር ማስተዳደርን) በበረሃው ትግል ተፈትኖ ከማለፍ ጋር ከሚያጋምዱት የግንባሩ ጉምቱ መሪዎች ዘንድ፣ ይህን መሰል ማጣጣያ የሚጠበቅ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለደኢህዴን ደካማነት በምክንያትነት የሚነሳው ጉዳይ ከአወቃቀሩ ጋር የሚያያዝ ነው፤ ይኸውም በክልሉ የሚገኙ 56 የተለያዩ ዘውጎችን ማቀፉ ለመከፋፈል አደጋ በቀላሉ የሚጋለጥበትን ዕድል የማስፋቱ እውነታ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ከክልሉ ነዋሪዎች በቁጥር የሚልቁት የወላይታና የሲዳማ ተወላጆች፣ በደኢህዴን ውስጥ ያላቸው ተሰሚነት (ተፅዕኖ) የገዘፈ መሆኑን ለመረዳት፣ ሕገ-መንግስቱ ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ የፓርቲውን ሊቀ-መንበርነትም ሆነ የክልሉ ፕሬዚዳንትነት ከሁለቱ ብሔሮች በቀር፣ ለሌሎቹ የሰማይ ያህል የራቀ ያደረገውን «ዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት» መጥቀሱ በቂ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የፓርቲው ሊቀ-መንበር ኃይለማርያም ደሳለኝ የያዘውን መንግስታዊ ስልጣን የሚመጥን ተሰሚነት ለማግኘት ድርጅታዊ ድጋፍ ማሰባሰብ ላይ ያተኮሩ የሚመስሉ ክስተቶችን ሲከውን ታዘብናል፡፡ ኩነቱን በስነ-አመክንዮ ለማጠናከር ጥቂት ማሳያዎችን ላቅርብ፡- በጠቅላይ ሚኒስትርነት መንበር ላይ ከተቀመጠ በኋላ፣ በደኢህዴን ውስጥ ያሉ የተወሰኑ ተገዳዳሪዎቹን ከኃላፊነታቸው ከማንሳትም አልፎ፣ ደጋፊዎቹ (ታማኞቹ) እንደሆኑ የሚነገርላቸውን በከፍተኛ ሥልጣን ላይ አስቀምጧል የሚያስብለው፣ ከወራት በፊት በፓርቲውም ሆነ በደቡብ ክልል ከእርሱም የበለጠ ተሰሚነት የነበረውን ሽፈራው ሽጉጤን አንስቶ፤ ትጉህ አገልጋዩ እንደሆነ የሚነገርለትን ደሴ ዳልጌን ተክቶታል፤ በቅርቡ ደግሞ ሌላኛው ‹የደኢህዴን ቁልፍ ሰው› የሚባለው የፖለቲካ (የድርጅት) ጉዳይ ኃላፊ እና የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አለማየሁ አሰፋን ያለአንዳች ኮሽታ «በትምህርት ስም» ከቦታው አንስቶታል (ይህ ጉዳይ እስከአሁን ድረስ መንግስታዊው ሚዲያ የዜና ሽፋን አላገኘም)፡፡ በግልባጩ ታማኝነታቸውን ያስመሰከሩ፣ ከሲዳማ ብሔር ውጪ ያሉ ጓዶቹን በፌደራል መንግስቱ ወሳኝ የስልጣን እርከኖች ላይ አስቀምጧል፡፡ ለማሳያ ያህልም አሰፋ አብዩ /ሀድያ/፣ ወርቅነህ ገበየውን ተክቶ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር፤ ደበበ አበራ /ከፋ/፣ የኢህአዴግ ዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ፤ ውዱ ሀቶ /ሸካ/፣ የፀረ ሙስና ምክትል ኮሚሽነር፤ አማኒኤል አብርሃም /ወላይታ/፣ በሚኒስቴር ዴኤታ ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕዝብ አደረጃጀት አማካሪ፤ ሰለሞን ተስፋዬ /ጉራጌ/፣ በተመሳሳይ ማዕረግ የፕሬስ አማካሪ፤ ካይዛ ኬ (ጂንካ) በገቢዎች ባለስልጣን የገብረሀዋድን ቦታ ተክቶ የገባ እና የፌደራል ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት ምክትል ኃላፊ ተደርጋ የተሾመችውን የወላይታዋ ተወላጅን መጥቀስ ይቻላል (ከደኢህዴን የሥራ-አስፈፃሚ አባላት መካከል የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትሩ ሬድዋን ሁሴን እና መከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈጌሳም የሲዳማ ተወላጅ አለመሆናቸውን ልብ ይሏል) ይህንን ጉዳይ እንዲህ በብሔር ደረጃ ቁልቁል አውርደን እንድንመለከተው የሚያስገድደን ስርዓቱ ከሚያራምደው የፖለቲካ ፍልስፍና እና በክልሉ እየተነሱ ካሉ የማንነት ጥያቄዎች ጋር የመቆራኘቱ አንድምታ ነው፡፡ በተለይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሲዳማዎች ራሳቸውን ችለው በክልል ደረጃ ለመዋቀር ተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርበው አያሌ መስዋዕትነትን መክፈላቸው ይታወሳል (በኢህአዴጋዊ የክልል አሰያየም ቀመር ሕገ-መንግስታዊ ድጋፍ ያላቸው መሆኑ ሳይዘነጋ)፡፡ ይሁንና ጥያቄው ተቀባይነት ቢያገኝ የክልሉ አስተዳደር መቀመጫ የሆነችውን አዋሳን ከመውሰዳቸውም በላይ፣ ሊያስከትል የሚችለው አለመረጋጋት ሲታከልበት፣ ህዳጣን ልሂቃኑን የኢኮኖሚ ጥቅመኝነት ያሳጣቸዋል፡፡ ይህ ስጋትም በደኢህዴን ውስጥ ከሲዳማ ተወላጆች ውጪ ካሉ የአመራር አባላት ድርጅታዊ ድጋፍ ለማግኘት ብርቱ ትግል ከሚያደርገው ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር በወሳኝ ሰዓት፣ መሀል መንገድ ላይ ቢያስተቃቅፋቸው የማይታመን አይሆንም፡፡ የእነዚህ አዳዲስ ኩነቶች (ሹም ሽሮች) መግፍኤ፣ በሁለት የቢሆን ሃሳቦች ተነጣጥለው ሊታዩ ይችላሉ፡፡ የመጀመሪያው ኃይለማሪያም ደሳለኝ የጠቅላይ ሚንስትርነት ሹመቱን ተከትሎ ‹በዚህ ላይ ፈርም›፣ ‹ይህንን ተናገር›፣ ‹እንዲህ አይነት አስተያየት ስጥ!!› ወዘተ የሚሉ ከጀርባ ሆነው የሚሾፍሩት የአለቆቹ ቀጭን ትዕዛዛትን የሚገዳደርበት ፖለቲካዊ ጉልበት ለማሰባሰብ እና በቁርጥራጭ ጨርቅ በተጣጣፈው እናት ድርጅቱ ውስጥ ያሉ ችግሮችን ስልታዊ በሆነ መልኩ አስወግዶ ቅቡልነቱን ለማጠናከር እንቅስቃሴ ጀምሯል የሚል ሊሆን ይችላል፡፡ ሌላኛው ደግሞ ከኢትዮጵያውያንም አልፎ በውጪ ዜጎች ሳይቀር ‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሻንጉሊት ነው› የሚለውን እምነት ለማስቀየር በህወሓትና ብአዴን እየተደረገ ያለ ፖለቲካዊ ጨዋታ ሊሆን የመቻሉ ጉዳይ ነው፡፡ ኦህዴድ ባለፉት የህወሓትም ሆነ የአቶ መለስ ዜናዊ የበላይነት በገነኑባቸው ዘመናት፣ ኦህዴድ ምንም እንኳን ስርዓቱን ካነበሩ የግንባሩ አባል ድርጅቶች አንዱ መሆኑ ባይካድም፣ በስጋት መታየቱ የአደባባይ እውነታ ነው፡፡ እንዲያውም በአንድ ወቅት አቶ መለስ ራሱ «ኦህዴድ ሲፋቅ ኦነግ ነው» ማለቱ አይዘነጋም፡፡ ከሶስት ያላነሱ የስራ አስፈጻሚ አባላቱ፣ ድርጅቱን ከድተው ኦነግን መቀላቀላቸውም የውንጀላው ማሳያ ተደርጎ እስከመወሰድ ደርሶ ነበር፡፡ ይህ ሁኔታም ኦህዴድን የተረጋጋ አመራር እንዳይኖረው ከማደናቀፉም ባሻገር፣ በተቀነባበረ ማኪያቬሊያዊ ሴራ እርስ በርስ በማይተማመኑና በተከፋፈሉ ሰዎች ስር እንዲቆይ አስገድዶታል፡፡ ግና፣ ኩነቱን ምፀት የሚያደርገው ህወሓት በረሃ እያለ ያሳትመው በነበረው ልሳኑ «የኦሮሞ ጥያቄና የኢትዮጵያ አብዮት» በሚል ርዕስ ባሰራጨው ፅሁፍ ኢህአፓን «የኦሮሞ ሕዝብ በነፍጠኛው ላይ የነበረውን ተገቢ ጥላቻ በማራገብ ፋንታ ለማብረድ በተጨባጭ ተንቀሳቅሷል» («የትግል ጥሪ» 3ኛ ዓመት ቁጥር 10፣ 1979 ዓ.ም) ሲል ይከስሰው እንደነበረ ማስተዋላችን ነው፡፡ በአናቱም አቶ መለስ እስከ ህልፈቱ ድረስ በኦህዴድ ደስተኛ እንዳልነበረ ይነገራል፡፡ ይህ ግን ‹የኦሮሞን ሕዝብ በአግባቡ አላገለገለም› ከሚል ቁርቆራ የተነሳ አይደለም፤ እንዲህ አይነቱ ስሜት ሌላውን ክልል ቀርቶ ትግራይንም የሚመለከት ቢሆን አሳስቦት አያውቅምና፡፡ የእርሱ ቅሬታ ‹ህዝቡን አሳምነውም ሆነ ጠርንፈው ከድርጅቱ ጎን አላሰለፉትም›፣ ‹ሁላችንንም በሚያሳጣ መልኩ ዘረፋ ውስጥ ገብተዋል›፣ ‹ዲሲፕሊን የላቸውም...› የሚሉና ሌሎች መሰል መነሾዎች ናቸው፡፡ እንዲህ ያለ የድርጅቱ «እንዝህላልነት» ደግሞ የህዝቡ ልብ ይበልጥ ኦነግን እንዲናፍቅ ማስገደዱን መለስ ዜናዊ ጠንቅቆ ያውቅ ነበር፡፡ ለዚህም ይመስለኛል የክልሉን ባለስልጣናት ሁሉ ወደ ጎን ብሎ እታች ድረስ በመውረድ የወረዳ አመራሮችን ቀጥታ ያለ ሥልጣን ተዋረድ በስልክ እስከማናገር የተገደደባቸው ቀናት የበዙት፡፡ በርግጥ በድርጅቱ ስብሰባዎች ላይ መተላለፍ ያለባቸውን ውሳኔዎች በፅሁፍ መስጠት እና ለአመራርነት የሚመረጡ ሰዎችን መመደብ ድረስ ባሉ ጉዳዮች ጣልቃ የመግባቱ ነገር ማንም አሌ የማይለው በግልፅ ይታይ የነበረ ክስተት ነው፡፡ የሆነው ሆኖ ከምንጮቼ እንዳረጋገጥኩት አባዱላ ገመዳ ዕድሜውን ሙሉ ሲፈራ የኖረው መለስ ዜናዊን ብቻ ነበር፤ መለስ ደግሞ ይህችን ምድር ለመጨረሻ ጊዜ ከተሰናበታት አንስቶ የተቆጠሩት በርካታ ወራት ፍርሃቱን ጥሎ ነፃነቱን እንዲጎናፀፍ ለመርዳት ያስችሉታል ብዬ አስባለሁ፡፡ እናም በዚህ መልኩ ተፈጥሮ ያመቻቸለትን ታሪካዊ አጋጣሚ ተጠቅሞ ይደቆስ የነበረውን ኦህዴድ ከወደቀበት ለማንሳት ሙከራዎችን እያደረገ ይመስለኛል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኦህዴድ በሚያደርጋቸው ስብሰባዎች ላይ የሚቀርቡ አንዳንድ አጀንዳዎችና አቋሞችን የአባዱላ ግፊት እንዳለባቸው ስናስተውል፣ «ጄነራሉ» ወሳኝ ሰው ለመሆን እያደረገ ያለው የጥንጣን ጉዞ ምን ያህል እየሰመረለት እንደሆነ ለመረዳት ያስችላል፡፡ ይህንን መከራከሪያ ከለጠጥነው ደግሞ፣ ከህወሓት/ብአዴን ጋር ትከሻ መገፋፋት ጀምሯል ወደሚል ጠርዝ ይገፋናል፡፡ ይህም ባይሆን እንኳ ከኃይለማርያም ደሳለኝ የተሻለ ተሰሚነት እንዳለው ለመናገር የሚያስደፍሩ ማስረገጫዎች አሉ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ቀን የከዳ ዕለት በተናጠል በኃላፊነት ሊያስጠይቁት የሚችሉ ጉዳዮችን ሳይቀር፣ በያዘው ሕገ-መንግስታዊ ሥልጣን ከመወሰን ይልቅ በቡድን እንዲያልቅ ሲስማማ፤ በግልባጩ አፈ-ጉባኤው ከዚህ ቀደም በምክር ቤቱ ውስጥ ተነስተው ለአቶ መለስ ይቀርቡ የነበሩ ጉዳዮችን ወዲያውኑ መፍትሔ እንዲያገኙ በማድረግ ሲቋጫቸው ተደጋግሞ ተስተውሏል፡፡ ኦህዴድንም በሚመለከት ‹በድርጅታዊ መደጋገፍ› ስም ማንም ጣልቃ መግባት እንደማይችል በይፋ እስከ መናገር መድረሱን ምንጮች ጠቅሰውልኛል፡፡ በቀጣይ አመት የሚደረገውን አምስተኛ ዙር አገር አቀፍ ምርጫን አስመልክቶም እየተደረገ ባለው ዝግጅት በሃሳብ አመንጭነት እየተሳተፈ ነው፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት ለምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ ከሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤት ለተወከሉ እና ምርጫ ቦርድ ሀላፊዎች /ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እና ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሔር በተገኙበት/ «የአውራ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ባህሪያት» በሚል ርዕስ ጥናታዊ ፅሁፍ ማቅረቡ አስረጅ ሆኖ ሊወሰድ ይችላል (በነገራችን ላይ ስርዓቱ በምርጫ ስም የሚፈፅመውን ደባ ፍንትው አድርጎ የሚያሳየው፣ ሁለቱ የቦርዱ ኃላፊዎች የዚህ አይነቱ ውይይት ላይ ተሳታፊ መሆናቸው ነው)፡፡ እንዲሁም ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ በአዳማ ለክልል አፈ-ጉባኤዎች ሰፊ ትንተና ሰጥቷል፡፡ የአባዱላ ገመዳንና የበረከት ስምኦንን መገፋፋት በጨረፍታም ቢሆን ሊያሳይ የሚችለው ሌላኛው ሁነት ደግሞ ወ/ሮ አና ጎሜዝን አስመልክቶ ሊነሳ የሚችለው ነው፡፡ በረከት «የሁለት ምርጫዎች ወግ» በሚለው መጽሐፉ «የቅኝ-ገዥነት መንፈስ ያልለቀቃት» ብሎ የገለፃትን አና ጎሜዝ (የመለስ በስድብ የተሞላ የኢትዮጵያን ሄራልድ ጋዜጣ መጣጥፍ ሳይዘነጋ)፣ ከሁለት ወራት በፊት አዲስ አበባ በመጣችበት ወቅት አባዱላ በጓዳዊ ስሜት እንዳስተናገዳት ራሷ ከመመስከሯም በዘለለ፣ እነርሱም በአዲስ ዘመን ጋዜጣቸው «እየተመካከርን ነው» የሚል የወዳጅነት መንፈስ የረበበበት የፎቶ ዘገባ ማቅረባቸውን እናስታውሳለን፡፡ ይህች ተራ የምትመስል ሁነት ለበረከት የምታስተላልፈው መልዕክት ቢኖር ‹እናንተ እንደሰይጣን የረገማችሁትን ሁሉ እየተከተልን አንረግምም» የምትል እኩዮች ነን አይነት ትከሻ መጋፋት ትመስለኛለች፡፡ በአናቱም አባዱላ አብዛኛው የኦህዴድ አመራርን በዙሪያው ማሰባሰብ ስለመቻሉ ይነገራል፡፡ ከዚህ ቀደም በአደባባይ እስከመዘላለፍ የተደራረሱትን አቶ ሙክታር ከድርንም ከጎኑ ማሰለፍ ችሏል፡፡ በአንድ ወቅት የግል ጠባቂው የነበረውና አሁን የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆነው አብይ አህመድ በእንዲህ አይነቱ ጊዜ ውለታ ለመመለስ የሚያደርገው ተጋድሎ የማይናቅ ጠቀሜታ አስገኝቶለታል፡፡ የሰሞኑ ሹም ሽርም የራሱ የሆነ አንድምታ አለው፡፡ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ በማዕከላዊ ኮሚቴ ድምጽ ከስልጣኑ የተሻረው የክልሉ ፕሬዚዳንት አለማየሁ አቱምሳ (እርሱን ማንሳት የሚችለው ጠቅላላ ጉባኤው ብቻ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ በርግጥ ሰውየው አሁን አልፏልና በባህላዊ ልማዳችን መሰረት ነፍስ ይማር ብለን እናልፋለን) በ2002ቱ ምርጫ ማግስት አቶ መለስ ከካድሬዎቹ ይሁንታ ውጪ አባዱላን ለመተካት ያመጣው እንደነበር ይታወሳል፡፡ (በነገራችን ላይ በወራት እድሜ ውስጥ በመለስ የተሾሙ የክልል ፕሬዚዳንቶች ከኃላፊነታቸው ሲነሱ ከሽፈራው ሽጉጤ እና አያሌው ጎበዜ ቀጥሎ አለማየሁ አቱምሳ ሶስተኛው ሰው መሆኑ ነው) የድርጅቱ ሊቀ-መንበር እና ምክትል ሆነው የተመረጡት ሙክታር ከድርና አስቴር ማሞም የአባዱላን የበላይነት ለመቀበል ግለ- ሂሳቸውን ውጠዋል፡፡ ይህም ሆኖ የክልሉ አስተዳዳሪ ማን ይሆናል? የሚለው ጥያቄ ገና መልስ አላገኘም፡፡ ምናልባት (ከስራ አስፈፃሚዎችም መካከል መምረጥ እንደሚቻል ታሳቢ ተደርጎ) በሌሎች አካባቢዎች እንደታየው ከድርጅቱ ሊቀ-መናብርት (ሙክታርና አስቴር) አንዳቸውን መሾም ቢፈልጉ እንኳ ዕውን የሚሆንበት ዕድል የለም፡፡ ምክንያቱም እነርሱ የህዝብ ተወካዮች እንጂ የጨፌ ኦሮሚያ ም/ቤት አባል አይደሉምና፡፡ በእኔ ግምት እስከሚቀጥለው የምርጫ ዘመን ድረስ ቦታው አዲስ ሰው ሳይሰየምበት በምክትል ፕሬዚዳንቱ አብዱል አዚዝ ስር እንዳለ የሚቆይ ይመስለኛል፡፡ ከምርጫው በኋላስ? ....አፈ-ጉባኤው በኦህዴድ ውስጥ ለማስፈን እየሞከረ ካለው «አምልኮ አባዱላ» ተነስተን «ተገፈተርኩበት!» የሚለውን ያደረ ቁጭቱን ስንደምርበት ወንበሩን ራሱ ይይዘው ይሆናል ከሚል ጠርዝ ያደርሰናል፤ አሊያም ከሽርኮቹ ሙክታር ከድር እና ወርቅነህ ገበየው አንዳቸውን አሾሞበት በጨፌ ኦሮሚያም የሚካኤል ስሁልን መንፈስ ማንበሩ አይቀርም ብሎ ቅድመ ግምት ማስቀመጥ ይቻላል (ይህ መላምት የህወሓት-ብአዴን ጥንካሬ በዚሁ ከቀጠለ እና የእነርሱ ፍላጎት ደግሞ የተለየ ከሆነ ከህልም ሊዘል አለመቻሉን በማመን ላይ የተመሰረተ ነው) ኦህዴድን ካነሳን የሌንጮ ለታን ኦዴግን መፃኢ እድልም መመልከት ግድ ይለናል፤ ምክንያቱም ኦዴግ አገር ውስጥ ገብቶ በሰላማዊ መንገድ መታገል ወስኖ ጨርሷልና፤ ሂደቱንም ለማመቻቸት ከግንባሩ መሪዎች አቦ ሌንጮ ለታ፣ ዶ/ር ሌንጮ ባቲ፣ ዶ/ር ዲማ ነጎዎ፣ ዶ/ር ታደሰ ኤባ እና ዶ/ር በየነ አሰቦ ጋር ከስምምነት ለመድረስ፣ ኢህአዴግ በውጪ ሀገር ከሚገኙት የጄኔራል ታደሰ ብሩ ልጆች በተጨማሪ፣ ፕ/ር እንድሪያስ እሸቴ፣ ፕ/ር ኤፍሬም ይስሃቅ፣ ፓስተር ዳንኤል፣ ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ፣ ሻለቃ ደራርቱ ቱሉ፣ አባቢያ አባጆቢር፣ አቶ በቀለ ነዲ (የአዋሽ ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩ)፣ ወ/ሮ ሙሉ ሰለሞንን የመሳሰሉ አደራዳሪዎችን ማሳተፉ ይነገራል፡፡ ይህም ሆኖ ድርድሩ በስኬት ተቋጭቶ ኦዴግ ሀገር ቤት መግባት ቢችል እንኳ፣ ኦህዴዶች ‹አያሰጋንም› የሚል እምነት እንዳላቸው ሰምቻለሁ፡፡ ግና፣ ያለፉት ሁለት አስርታት ዘግናኝ ክስተቶች አሻራ ዛሬም በረዣዥሞቹ የባሌ ተራሮች በጉልህ ተቸክችኮ የመታየቱ እውነታ፣ በስርዓቱ ላኮረፈው የኦሮሚያ ህዝብ፣ ኦዴግን አማራጭ የሚያደርግበት «አኪር» ሸሽጎ ይዞ እንደሆነ ማን ያውቃል? ይህ እንግዲህ እነ ሌንጮ «ካዳሚ» ለመሆን አይመጡም በሚል ስሌት ከተቃኘ ነው፡፡ ይሁንና ከድርድሩ ጀርባ ያለውን እንቆቅልሽ ለመፍታት ጊዜ የሚጠይቅ ቢሆንም፣ ጉዳዩን ውስብስብ የሚያደርጉ ክስተቶችን ግን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ይኸውም በአፈ-ጉባኤ አባዱላ ፊት አውራሪነት ስር ለመጠናከር እየሞከረ ያለው ኦህዴድ፣ ከሰዎቹ ሀገር ቤት መግባት ምን ያተርፋል? ምንስ ያጣል? ከሚለው ጋር ይያያዛል፡፡ መቼም የኦዴግን መምጣት፣ ኦቦ ሌንጮ «እንጮቴ» (ተወዳጅ ባሕላዊ ምግብ ነው) በአይኑ ላይ እየተመላለሰ እንደሆነ ከሰነዘረው ቀልድም ሆነ «ከሌሎች የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ዘመናዊ ፌደራሊዝምን እመሰርታለሁ» ብሎ በደምሳሳው ከገለፀው ዓላማው ጋር አያይዞ ማለፍ አይቻልም፡፡ አሊያም ያኔ እርሱ ሸገርን ተሰናብቶ ሲወጣ ገና ያልፀደቀውን አንቀፅ 39ን «አስፈፅማለሁ» በሚል ቀቢፀ-ተስፋ ተገፍቶ ነው ማለትም አይቻልም፡፡ በግልባጩ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ‹የኦዴግ መሪዎች በኦነግ ዘመን ለእስር የዳረጓቸውን በሺ የሚቆጠሩ የኦሮሚያ ተወላጆችን ለማስፈታት ሲሉ፣ በታማኝ ተቃዋሚነት ለመታገል ወስነው ነው የሚመጡት› የሚለውን መከራከሪያቸውን ለመቀበል የሚቸግረው ደግሞ፣ እስረኞቹን መፍታት ለሃያ አመታት ያህል በክልሉ ላይ ሰላማዊ ዜጎችን በማሰር የሚታወቀውን ኦህዴድን ሊያሳጣ የመቻሉ ነገር ነው፡፡ ያም ተባለ ያ፣ «ለሁሉም ጊዜ አለው» እንዲል ጠቢቡ ሰለሞን ሁሉም ቋጠሮ ጊዜ የሚፈታው ይሆናል፡፡ አሁን ላይ እርግጠኛ መሆን የሚቻለው በኦህዴድ ውስጥ አባዱላ ገመዳ ወሳኝ እየሆነ የመምጣቱ እውነታ ብቻ ነው፡፡ ህወሓት-ብአዴን በዋናነት ሀገሪቷን እንደሚያሽከረክሯት የሚነገርላቸው ህወሓት እና ብአዴን፣ በመጪዎቹ ጊዜያት ‹ኢህአዴግ ለዳግም ክፍፍል ሊዳረግ ይችላል› በሚል ፍርሃት ድርና ማግ ሆነው እየሰሩ ስለመሆኑ እየሰማን ነው፡፡ በርግጥ ‹መለስ ህወሓትን አዳክሞ ነው ያለፈው› የሚል የትግርኛ ተናጋሪዎች ድምፅ መሰማት ከጀመረ ሰነባብቷል (በነገራችን ላይ ከ2000 ዓ.ም ወዲህ የህወሓትን የምስረታ በዓል የካቲት 11ን በብሔራዊ ደረጃ ማክበር መቅረቱን በይፋ ከማወጃቸውም በላይ፣ መለስ ራሱ ለመጨረሻ ጊዜ በመቀሌው የሰማዕታት አዳራሽ የተገኘው 35ኛው ዓመት በተከበረበት ወቅት ነበር፡፡ ይሁንና ከህልፈቱ በኋላ ድርጅቱ የደረሰበትን ድክመት ለመሸፋፈን በደመቀ መልኩ እያከበረው ይገኛል፤ ለዚህም ይመስለኛል በአምናውም ሆነ በዘንድሮው በዓል ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ መቀሌ የሞቀ ተገኝቶ ንግግር ከማድረግም አልፎ ከሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኡመር ሀሰን አልበሽር ጋር በትግሉ ዘመን በተቀነቀኑ ዜማዎች ሲደንስ በቴሌቪዥን መስኮት ተመልክተን ሦስተኛው ሚሊንየም ገባ እንዴ? ብለን ግራ የተጋባነው፡፡ አልበሽርስ አንድ ቻርተር አውሮፕላን ለክልሉ በስጦታ ያበረከተው ዕውን በዓሉን አስመልክቶ ነው? ወይስ በምትኩ የተሰጠው ነገር ኖሮ? መቼም የህወሓት የምስረታ በዓል እንዲህ ሊያስፈነጥዘው እይችልም) ‹ህወሓት ተዳክሟል› የሚለውን ቅሬታ የሚያሰሙ የቅርብ ሰዎች፣ ድርጅቱ አቅምና ልምድ በሌላቸው መሪዎች ስር ማደሩን ይጠቅሳሉ፡፡ ተስፋ የጣሉበት ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤልም ቢሆን ከአምባገነንነቱም በላይ ሀሳቡን አፍታቶ የማስረዳት ችሎታው ደካማ መሆን መፍትሄውን አርቆ ሰቅሎታል፡፡ እንደ ድርጅቱ የቅርብ ሰዎች አገላለፅ የ«ጠንካራ ተተኪ» አልቦነትን ለመረዳት፣ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ኃላፊነቱ በተነሳው አቶ ዘርዓይ አስገዶም ቦታ ላይ የዋልታ ስራ አስኪያጅ መመደቡ እና ራሱ ዘርዓይም በጓሮ በር የብሮድካስት ባለስልጣን ሆኖ መሾሙን (አዲስ ፊት አለመታየቱን) መመልከቱ በቂ ነው፡፡ በቅርቡ የዶክትሬት ዲግሪውን ያገኘው አርከበ እቁባይም ለአመራርነት ለቀረበለት ጥያቄ እያንገራገረ እንደሆነ ተሰምቷል፤ አቦይ ስብሃት ነጋም ኢ-መደበኛ በሆነ የጠረጴዛ ወግ ህወሓት «በግብር በላ» መሪዎች እጅ መውደቁን በቁጭት መናገራቸው ይጠቀሳል፡፡ ይሁንና በዚህ ቀውጢ ወቅት ሁለት ተቋማት ድርጅቱን ለጊዜውም ቢሆን ፖለቲካዊ ጉልበቱን እንዳይነጠቅ ታድገውታል፡፡ ደህንነቱ እና ሰራዊቱ፡፡ የሆነው ሆኖ ህወሓት ዛሬም ከብአዴን ጋር በማበር (በአባይ ፀሐዬ እና በበረከት ስምኦን የፊት መሪነት) የፖለቲካው አሽከርካሪነቱን እንዳስከበረ ይገኛል፡፡ ሁለቱ ሰዎች የስርዓቱን ርዕዮተ-ዓለምንም (በተለይም አብዮታዊ ዲሞክራሲን) ከሌሎች ጓዶቻቸው በበለጠ ማብራራት እንደሚችሉ ይነገራል፡፡ በጅጅጋ ከተማ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በተከበረበት ወቅትም ሆነ ከሳምንታት በፊት በመቀሌ ከተማ በተዘጋጀ መድረክ አባይ ፀሐዬ የርዕዮተ-አለሙ «ተንታኝ» ሆኖ የቀረበው ከዚህ አኳያ ነበር፡፡ በአናቱም አባይ እና በረከትን ጨምሮ ከኦህዴድ ኩማ ደመቅሳ፤ ከደኢህዴን ዶ/ር ካሱ ኢላላ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር አማካሪ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡ በዋናነት ለኢህአዴግ የስልጣኑ መሰረት (ከታጠቀው ኃይል እና ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬው በተጨማሪ) ‹በልማታዊ መንግስት፣ በጥርነፋ፣ ሳር-ቅጠሉን በማደራጀት፣ የብሔር ጉዳይን በማጎን እና መሰል ጭብጦችን በማስጮኽ የሚያምታታበት ርዕዮተ-ዓለሙ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የእነ በረከት የተሰሚነት ምስጢርም ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በርግጥም የካቲት 14 ቀን 2006 ዓ.ም. የተሰበሰበው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከልን ለማቋቋም የሚያስችል ደንብ ማፅደቁን እና የአራቱም ድርጅት የአመራር አባላት የተወከሉበት ከመሆኑ አኳያ፣ ቦታው ከማማከር የዘለለ የስራ ድርሻ እንዳለው መገመት አያዳግትም (በነገራችን ላይ የመለስ ፖለቲካ ሰለባ የሆነው የብአዴኑ ተፈራ ዋልዋ ድምፁን አጥፍቶና ከውጥንቅጡ አርባ ክንድ እርቆ በእንጦጦ ተራራ እና በረዣዥም ህንፃዎች አናት በመፈናጠጥ ቴሌስኮፑን ግራና ቀኝ እያዟዟረ ከዋክብት ሲመለከት መዋልን አይነት ፀጥተኛ ህይወት፣ አንዳንድ የቀድሞ ጓዶቹም ለተረፈቻቸው እድሜ የሚመኙት ይመስለኛል) ለውጥ ይኖር ይሆን? የስርዓቱ ልሂቃን ብሔሮቻቸውን ማዕከል ባደረገ መልኩም ይሁን፣ በሥልጣን ከፍታ ከሚያገኙት ግላዊ ጥቅማ-ጥቅም በመነሳት፣ ከላይ ለመተንተን እንደሞከርኩት ባለ የመከፋፈል መሰል ሂደት ውስጥ እንኳን ቢያልፉ በቀጣይ ጊዜያት ‹የፖለቲካ ማሻሻያ ያደርጋሉ› ብሎ ለማመን ነገሮች በእጅጉ አስቸጋሪ ናቸው፡፡ ለዚህም ሶስት ነጥቦችን እናንሳ፡- የመጀመሪያው የሀገሪቱ የደህንነት መዋቅር አደረጃጀት ባህሪ ነው፡፡ እንደሚታወቀው በእነ ጌታቸው አሰፋ የሚመራው የደህንነት ተቋም በሚታዩና በማይታዩ ድርጊቶች ለህወሓት የተገዛ ነው፡፡ ከዚህች ሀገር ጀርባ ለተፈፀሙም ሆነ ገና ለሚፈፀሙ ድርጅታዊ እና ግለሰባዊ (ባለሥልጣናዊ) ወንጀሎች አስፈፃሚና በደል አንፂ ነው፡፡

Sunday, 9 March 2014

ህዝብን በመጨቆን ሀገርን መምራት አይቻልም!

በአሸናፊ ንጋቱ የፖለቲካ ስርአትና የአንድ ሀገር እድገት ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት አላቸዉ። አንድ አገር ትክክለኛ ባልሆነ የፖለቲካ አገዛዝ ይበለፅጋል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። ሃገራችን ኢትዮጵያም የወያኔ መንግስት ባነገሰው የተዛባ አገዛዝ ሳቢያ ህዝባችን ለከፋ ችግር መዳረጉ በገሃድ የሚታይ ሃቅ ነው። ታዲያ በዚህ ወያኔያዊ የተዛባ አገዛዝ እንዴት ከችግር ልንወጣ እንችላለን? አገራችን ኢትዮጵያ ምንም እንኳ የጥንት ስልጣኔ ባለቤት ብትሆንም በአየር ንብረትም ሆነ በተፈጥሮ ሀብት ጥሩ ከሚባሉት ሀገሮች አንዷ ብትሆንም እንደ እድል ሆኖ መሪዎች ግን አልተሳኩላትም። ለምን ኢትዮጵያ የረሃብ አገር ተባለች ለምን ዜጎቿ ተደስተው በነጻነት መኖርን እንደተመኙ ህልማችዉ ከንቱ ሆነ? ብዙዎች የሞቱላት አገር አንገታቸዉ ለሰይፍ ደረታቸዉ ለጥይት የሰጡላት አገር ኢትዮጵያ በህዝቦቿ ታታሪነት አለም ያደነቃት ለምን ተዋርዳ ተገኘች!? እውቀትን፣ ስልጣኔን፣ ጥበብን ለአለም ያበረከተች ሃገር ዛሬ ላይ በቤተ መንግስቱም ይሁን በቤተ ክህነቱ የተማሩ ሰዎችን ናፊቂ ሆናለች፡፡ ምክንያቱም ምሁራኑ በሃገራቸው ሊኖሩ የሚያስችላቸው እድል ስላልተመቻቸላቸው ሁሉም ጉዟቸው ወደ ውጭው አለም ስደት በመሆኑ ነው፡፡ በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህዝቦች በረሃብ አለንጋ የሚገረፍባት ሲኦልም ከሆነች ዘመናትን አስቆጥራለች፡፡ እንዲሁም መለያየትን ወይም ዘረኝነት በግልፅ የምትሰብክ የዘረኞችና የጎሰኞች መሰማሪያ ሜዳ ሆና ክፉ አድራጊዎች እንደፈለጉ እየዘፈኑባት ትገኛለች፡፡ በቃል ከሚወራ ዲሞክራሲ፣ እድገት፣ ብልፅግና በስተቀር በተግባር የሚታይ አንዳችም መልካም ነገር የማናይባት አሳፊሪ ሃገር ሆናለች፡፡ በደልና ጭቆና በዝቷል ድህነትና ጉስቁልና ከመቼዉም በባሰ ተንሰራፍቷል እስርና ሰቆቃ ተራ ነገሮች ሆነዋል። በአሸባሪዎች ስም እራሳቸዉ ቦንቦች አጥምደው ህዝቦች እየፈጁ ሰላማዊ ዜጎች በአሸባሪነት እየተፈረጁ ለስቃይ እየተዳረጉ ነዉ። ዛሬ በሃገራችን አርሶም ሆነ ነግዶ መኖር አይቻልም። መኖር የሚቻለዉ ኢሕአዴግ ልማት ነዉ የሚለዉን መዝሙር በመዘመር ብቻ ነዉ። የሁሉም ነገር መሰረት እንደሆነ የሚታመንበት ትምህርትን ብንመለከት እንኳ ትምህርት በኢትዮጵያ ሞቷል ለማለት በሚያስደፍርበት ጀረጃ ደርሷል። ከተለያዩ ሀገሮች ያለምንም ጥናት በኩረጃ የሚያመጧቸዉ የትምህርት ፖሊሲዊች ምንም እንኳን ብዙ ወጭ ቢወጣባቸዉም የሚሰራባቸዉ ለአንድ የትምህርት መንፈቀ አመት ብቻ ነዉ። በኢትዮጵያ ወያኔ ልማት ነዉ በሚል አባዜ የተለከፈ ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል። ልማታዊ መንግስት፣ ልማታዊ፣ ዘፋኝ፣ ልማታዊ አስተማሪ፣ ልማታዊ የእምነት ዘርፍ፤ ወዘተ… በማለት ከወያኔ ጎን ካልተሰለፉ ኢ-ልማታዊ/ ሽብርተኛ የሚል ስም ይሰጣቸዋል ይህንንም ተመርኩዞ ለእንግልትና ለእስራት ይዳረጋሉ። ‘‘ዶሮ ጭንቅላቷ ላይ ስጋ ተሸክማ ወይ አትበላዉ ወይ አታስበላዉ‘‘ እንደተባለዉ ማንንታቸዉና እዉቀታቸዉን ትተዉ የወያኔ መዝሙር ብቻ በመዘመር የሚኖሩ ጥቂት ሰዎች በኢትዮጵያ ዉስጥ የማይጠበቅ ኑሮን ሲኖሩ ይታያሉ። የሚላስ የሚቀመስ በጠፋበት በአሁኗ ኢትዮጵያ ዘይትና ሽንኩርት ለመግዛት እንኳ አንድ ግለሰብ የወር ደሞዙ በቂ አልሆን ባለበት ግዜ እንዴት ጥቂት ባላባቶች ፎቆችና ቪላዎች ይገነባሉ? የህዝብ ንብረት ካአልተዘረፈ በቀር እነሱ ከየት አመጡት? ወይስ ኢትዮጵያ ሲባል እነሱን አይጨምርም? ከአዉሮፓ መንግስታት የሰዉ ፍጥረት በረሃብና በህክምና እጥረት ህይዎቱን ለማዳን ተብሎ የሚላከው ገንዘብ እነሱ ዉስኪ ሲራጩበት ሊሞዚንና አሉ የተባሉ ምርጥ በአለም ከታወቁ ካምፓኒዎች የተሰሩ መኪናዎች ሲገዙበት ለህዝቡ ድህነት ባህላችን መሆኑን ዘላለም በመተረክ ይኖራሉ። በስብሰባ ፍቅር ብቻ የተለከፉ ባለስልጣናቶቻችን ስብሰባዉን እንደጨረሱ አበል በሚል ስም ገንዘብ ይከፋፈላሉ። ይህንን እንስሳዊ የሆነ አስተሳሰብ አልደግፍ ያሉት ደግሞ ፀረ ልማትና አሸባሪ በሚል ስም ለእንግልት ይዳረጋሉ። አሸባሪነት ለምን የፖለቲካ መጠቀሚያ ሆነ? አሁን የታሰሩት ዉብ የኢትዮጵያ ልጆች አሸባሪዎች እንደሆኑ የሁል ግዜ ለጆሮ የሰለቸ ንዝንዝ ነዉ፤ ስለዚህ አሸባሪነት ለአምባገነናዊ መንግስት አለመዘመር ከሆነ ወደድክም ጠላህም መኖርም ሆነ መስራት የሚቻለዉ ይህንኑ ስትዘምር ብቻ ነዉ። ለዚችው በሺህ የሚቆጠሩ የነፃነት ታጋዮች የታሰሩባት; ረሃብ፣ ጦርነት፣ሞትና ግድያ መለያየት የሰፈነባት፤ ዜጎችዋ በሰላም ወጥተው በሰላም ለመግባት ለሚሸማቀቁባት ሃገር ለታሪኳ ሁለ መበላሸት ተጠያቂው ወይም ተወቃሹ ገዳዩ የወያኔ አገዛዝ ነው፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ የድንቁርና ፣ የመለያየት፣ የጦርነት፣ ያለማወቅ፣ የግድያ ጭለማ እንዴት ይወገድ ወደሚለው መፍትሄ ሃሳብ ስንመጣ፤ በኢትዮጵያ ያለው የክፉ ነገሮች ሁሉ ጨለማ የሚወገደው በወለደቻቸው እና ባሳደገቻቸው ኢትዮጵያውያን ሃገር ወዳድ ልጆቿ ነው፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላም ናፍቋት የሰላም ያለህ እያለች ነው፡፡ ውድ ልጆቿም አረመኔው የወያኔ መንግስት በየጊዜው እየቀሰፈባት እረፍትን ትሻለች፡፡ በመሆኑም ይህን አምባገነናዊ የወያኔ ስርዐት በማስወገድ ; በሃገራችን የእውቀትና የሰላም ብርሃን እንዲፈነጥቅ ; ዜጎቿም በሰላም ወጥተው በሰላም እንዲገቡ; መብቶቻቸውም ሊጠበቁ የሚችሉበትን እንዲሁም የምንፈልገውን ነፃነት፣ እድገት፣ፍትህ፣ ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ ለማምጣት የራሣችንን ቁርጠኝነት ማሣየት ይጠበቅብናል!!! ድል ለጭቁኑ ህዝብ!!!

Friday, 7 March 2014

ወያኔ በግንቦት 7 ስም ሠላማዊ ዜጎችን ማሰቃየቱን ባስቸኳይ ማቆም አለበት

ባለፉት አራትና አምስት አመታት በግልጽ እንዳየነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እኩልነቱን፤ መብቱንና ነጻነቱን ለማስከበር የሚያደርገዉ ትግል ጫና በፈጠረበት ቁጥር ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ የራሱን ህገመንግስት የሚደፈጥጡ ህጎች አርቅቆ አያጸደቀ ሠላማዊ ዜጎችን አስሯል፤ ገድሏል ከአገር እንዲሰደዱም አድርጓል። ለምሳሌ በ2003 ዓም የኢትዮጵያ ፓርላማ ከቤተመንግሰት የተላለፈለትን ትዕዛዝ አክብሮ ለኢትዮጵያ ህዝብ መብትና ነፃነት መከበር የሚታገለዉን የግንቦት 7 ንቅናቄ ሽብርተኛ አድርጎ ፈርጇል። ይህ ፈር የለቀቀ ፍረጃ ደግሞ ወያኔ የሱን ዘረኛ ስርዐት የሚቃወሙ ግለሰቦችን፤ ሀሳባቸዉን በነፃነት የሚገልጹ ዜጎችን፤ ጋዜጠኞችን፤ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና ከወያኔ ጋር አናብርም ያሉ ወጣት ኢትዮጵያዉያንን “ግንቦት ሰባቶች” ናችሁ እያለ በጅምላ እያሰረ እንዲያሰቃይ ህጋዊ ሽፋን ሰጥቶታል። ለምሳሌ ከፍትህና ከነጻነት ጥማት ዉጭ ከግንቦት 7 ንቅናቄ ጋር ምንም አይነት ግኑኝነት የሌለዉን የፖለቲካ ፓርቲ መሪዉን አንዱአለም አራጌን፤ ታዋቂዉን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና መምህርት ርኢዮት አለሙን የግንቦት 7 አባላት ናቸዉ የሚል ሰንካላና መሠረተ ቢስ ክስ መስርቶ ለረጂም ዘመን እስራት ዳርጓቸዋል። ወያኔ እንደ ዛሬዉ ከተማ ዉስጥ ሆኖ ሥልጣን ሳይቆጣጠር ገና ጫካ ዉስጥ እያለ ጥርሱን ከነከሰባቸዉና ከተቻለ አጠፋቸዋለሁ ካለዚያም አሽመደምዳቸዋለሁ ብሎ አስራ ሰባት አመት ሙሉ ከተዘጋጀላቸዉ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ የአማራ ብሄረሰብ ነዉ። በለስ ቀንቶት ሥልጣን ከጨበጠ ማግስት ጀምሮም በወሎና በጎንደር በኩል ከትግራይ ጋር የሚያዋሰኑ ሰፊ የሆነ ለም መሬቱን ጠቅልሎ በመውሰድ ዘረኛ ሥርዓቱን ዕድሜ ሊያራዝሙልኛል ይችላሉ ብሎ የሚተማመንባቸውን የቀድሞ የትግል አጋሮቹንና ካድሬዎቹን አስፍሮበታል:: ይህ በደልና ግፍ አልበቃ ብሎትም ቀደምቶቹ የኢትዮጵያ ገዥዎች ለፈጸሙት ግፍና የአስተዳደር በደሎች ሁሉ አማራዉን በጅምላ ተጠያቂ የሚያደርግ ፕሮፖጋንዳ እነሆ እስከዛሬ በመርጨት ለዘመናት በሠላም ከኖረው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር በጠላትነት እንዲተያይ አድርጎታል:: በወያኔ አጋፋሪነት በበደኖ ፡በአርሲ በአረካና ሌሎች አካባቢዎች አማራው ላይ በግፍ የተፈጸመው ጭፍጨፋና ከ2004 እስከ 2005 ዓም አማራዉን ከጉራፈርዳና ከቤንሻንጉል ለማፈናቀል የተወሰደው እርምጃ የዚህ የወያኔ የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ ውጤት መሆኑን የምስት የለም:: ሟቹ መለስ ዜናዊና በህይወት የሚገኙ ቀንደኛ የወያኔ መሪዎች የተጠናወታቸው የአማራ ጥላቻ በጸረ ፋሽስት ዘመቻ ወቅት ባንዳ ከነበሩ አባቶቻቸዉና አያቶቻቸዉ የተወረሰ ፋሽስት ጣሊያን ለደረሰባት ሽንፈት በዘርና በሃይማኖት ተከፋፍለን እርስ በርሳችን እንድንጠፋፋ ተክላብን የሄደቺው ተንኮል አካል ነው :: የዚህ የጥፋት አጀንዳ አስፈጻሚ የሆነው ወያኔ የጀመረውን አገር የማፍረስና ህዝብ የመከፋፈል አጀንዳ ለማሳካት በየክልሉ የተኮለኮሉ ምስሌኔዎች እንወክለዋለን በሚሉት ህዝብና ክልል ላይ እየፈጸሙት ያለው በደልና ሰቆቃ አዲስ ምዕራፍ በያዘበት በአሁኑ ወቅት እራሳቸዏን ለባርነት አዋርደው ህዝባቸውን በማዋረድ ላይ የሚገኙት የብአዴኑ አለምነህ መኮንንን የመሳሰሉ ሆድ አደሮች ውርደት በቃን ዘረኝነት በቃን ብለው በተነሱ ዜጎች ላይ እየወሰዱ ያለው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ እጅግ አሳሳቢ ሆኖአል:: ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና ሞክራሲ ንቅናቄ ከሰሞኑ በደረሰው መረጃ ወያኔ ከአማራው ቀምቶ በትግራይ ክልል ባስገባቸው ወረዳዎች ላይ የሚኖሩ ንጽሃን ዜጎች ለምን በወያኔ የግፍ አገዛዝ ትማረራላችሁ እየተባሉ በወያኔ ታማኝ ሚሊሻዎች እስር እንግልትና ድብደባ እየተፈጸመባቸው መሆኑን አረጋግጦአል:: በዚህ በአዲስ መልክ በተጀመረዉ የወያኔ የጥቃት ዘመቻ መሳሪያ ያነገቡ የህወሃት ሚሊሻዎች ከክልላቸዉ ዉጭ ወደ ተለያዩ የአማራ ከተማዎችና ወረዳዎች ሰርገዉ እየገቡ የእነሱን ቋንቋ የማይናገረዉን ሁሉ የግንቦት 7 ተላላኪዎች ናችሁ በሚል እያሰሩ በመደብደብ ላይ ናቸዉ። ይህ በመሆኑ ዛሬ አትዮጵያን ከሱዳንና ትግራይን ከጎንደር ጋር በሚያዋስኑ የአማራ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ገበሬዎች እጃቸዉ እርፍ ከሚጨብጥበት ግዜ በወያኔ ሰንሰለት የሚታሽበት ግዜ ይበልጣል፤ የመንግስት ሰራተኛዉና የከተማ ነዋሪዉም ቢሆን አብዛኛዉን ግዜ የሚያጠፋዉ ከወያኔ ካድሬዎች ጋር ግምገማ በመቀመጥ ሲሆን ተማሪዉና ወጣቱ ህብረተሰብ ደግሞ “መጡ አልመጡም” እያለ ሌሊቱን የሚያሳልፈዉ በየጫካዉ እየተሸሸገ ነዉ። የዚህ አይነት አስከፊ ግፍና መከራ በአፋር ፡ በጋምቤላ በኦጋዴንና በኦሮሚያ በሚኖሩ ዜጎቻችን ላይ ሲፈጸም ቆይቶአል:: ? ወያኔ እራሱ አርቅቆ ባጸደቀውና በሐምሌ ወር 1987 ዓም በስራ ላይ የዋለዉ የወያኔ ህገ መንግስት ኢትዮጵያ በዘጠኝ የፌዴራል ክልሎች መከፈሏንና እያንዳንዱ ክልል እራሱን በእራሱ የማስተዳደር መብቱ የተረጋገጠ እንደሆነ ይደነግጋል። በዚህ ህገ መንግስት መሠረት እያንዳንዱ ክልል የራሱ ቋንቋ፤ የአስተዳደር ማዕከልና እንዲሁም የክልሉን ሠላምና ጸጥታ የሚያስከብር የፖሊስ ኃይል ይኖረዋል ይላል። ታድያ ለምንድነዉ እያንዳንዱ ክልል የራሱ ፖሊስ ኃይል አያለዉ ከትግርኛ ቋንቋ ዉጭ ሌላ ቋንቋ የማይናገሩ የህወሃት ታማኝ ሚሊሻዎች አማራ ክልል ዉስጥ እየገቡ አማራዉን የሚያሰቃዩት? መልሱ ቀላል ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ ህዝባዊ አምቢተኝነቱ እያየለ በመጣና የነጻነት ኃይሎች ጡንቻ በፈረጠመ ቁጥር ወያኔ አንገቷ ላይ ቀጭል እንደታሰረባት በቅሎ ይደነብራል። የደነበረ ደግሞ መራገጡ አይቀርምና መሳሪያ ያነገቡ ኃይሎችን እንቅስቃሴ እገታለሁ በሚል ከንቱ ጥረት ደንባራዉ ወያኔ የፈሪ በትሩን በድንበር አካባቢ በሚኖሩ የአማራ ክልል አርሶ አደሮች፤ ወጣቶችና ሠራተኞች ላይ ማሳረፍ ጀምሯል። ወያኔ እንደ ግንቦት ሰባት የኮነነዉና የህዝብና የአገር ጠላት አድርጎ የሳለዉ ድርጅት የለም፤ የወያኔ የዜና ማሰራጫዎችም ይህንን የአገዛዙን አቋም በተደጋጋሚ ለኢትዮጵያ ህዝብ አሰምተዋል።የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ማን ለመብቱና ለነጻነቱ እንደቆመና ማን መብቱና ነጻነቱ ላይ እንደቆመበት ለይቶ የሚያዉቅ ህዝብ ነዉ። ስለዚህም ግንቦት ሰባት ወያኔዎች አላፊዉንና አግዳሚዉን “ግንቦት ሰባት” ነህ እያሉ ከሚያሰቃዩ፤ ህዝብንና ግንቦት ሰባትን ያስተሳሰረዉ ነጻነት፤ ፍትህና ዲሞክራሲ ነዉና የኢትዮጵያን ህዝብ ጥያቄ ቢመልሱ ለእነሱም፤ ለእኛም ለአገርም ይበጃል የሚል የጸና እምነት አለዉ። ወያኔ በኢህአዴግ ስም ያሰጠጋቸዉን ምሰለኔዎች ጨምሮ ከራሱ ዉጭ ሌላ ማንንም አያምንም፤ ስለዚህም ነዉ የአገሪቱን የመከላከያ፤ የደህንነትና የፖሊስ ተቋሞች በራሱ ሰዎች ቁጥጥር ስር ያደረገዉ። ዛሬ በግልጽ እንደምንመለከተዉ ወያኔ በጉልበት ለያዘዉ ስልጣን ያሰገኛል ብሎ በሚጠረጥረዉ ቦታ ሁሉ የራሱን ልዩ ሚሊሺያ እየለላከ የኢትዮጵያን ህዝብ መኖሪያ ቤቱ ድረስ አየሄደ እያጠቃ ነዉ። ግንቦት ሰባት ወያኔና የፈጠረዉ ዘረኛ ስርዐቱ የቆሙት በፍጹም ማንሰራራት የማይችሉበትት የመጨረሻ መቀበሪያ ጉድጓዳቸዉ ጫፍ ላይ ነዉ የሚል ጽኑ እምነት አለዉ። ሆኖም ጉድጓድ ጫፍ ላይ የቆመ ጠላት በራሱ ተወርዉሮ ጉድጓዱ ዉስጥ አይገባምና ይህንን የተዳከመ ጠላት እተፈራገጠ ጉዳት ከማብዛቱ በፊት ለመደምሰስ ክንዳችንን አጠናክረን በህብረት እንደ አንድ ሰዉ እንነሳ ይላል። ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Thursday, 6 March 2014

ሀገር ማለት በትልቁ ሰዉ ነዉ (ከአዲስ ብርሀኑ )

ሀገር ማለት በትልቁ ሰዉ ነዉ እንጂ ብቻዉን አፈሩ፤ ምድሩ፤ ተራራ፤ ወንዝና ሸንተረሩ አይደለም፡፡እንደሚታወቀዉ ኢትዮጵያ የብዙ ብሄረሰቦች ሀገር፤ብዙ ቓዋንቓዋ፤ እምቅ ባህል እና ሀይማኖቶች ያላቸዉ ህዝቦች የሚኖርባት ሀገር ነች፡፡ የዚህ ሁሉ ጥቅል አንድን ሀገር ሀገር ያሰኛታል፤ የዚህ ሁሉ ራስ የሆነዉ ሰዉ ነዉ፡፡ ይህንን ያልኮበት ምክንያት በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ እነዚህን በኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉ ህዝቦች ሲመሩ የነበሩ መንግስታት ወይም ነገስታት የሰሩወቸዉ አሉታዊ የሆኑ የታሪክ ጠባሳዎች አሉ፡፡ እነዚህ ጉዳት ደርሶብናል ብለዉ ጥያቄ ለሚያነሱ ወገኖች መብቶቻችንን ተነፈግን ኖረናል፤ እንደሰዉ ያልተቆጠርንበት ዘመን ነበር ብለዉ አሁን ለሚያነሱት ጥያቄ ጆሮ መስጠት እና ማዳመጥ ልዩንትን ለማጥበብ ኢትዮጵያቂነትን አንዲፈልጉ፤ አንደሚቀበሉና የባለቤትነት ስሜትን ለመፍጠር ተገቢ ይመስለኛል፡፡ ያለበለዚያ ግን በማፈን ወይም በማግለል መፍትሄ ማምጣት አይቻልም፡፡ እኛ ዜጎች እንደ ሰለጠኑት ሀገራት የመደማመጥ የመከባበር እና የመደናነቅ ባህል ልናዳብር ይገባል፡፡ ሌላዉ የቀደሙት መሪዎች የሰሩዋቸዉ አወንታዊ የሆኑ በጎ ለሀገር የሚጠቅም ተግባራትን ከዉነዉ አልፈዋል፡፡ ስለዚህ አሁን ያለዉ ትዉልድ እነዚህን በጎ ጎኖች በማዳበር ስለወደፊት እጣፋንታችን ለመወሰን በጋራ በመወያየት የተሻለች ሀገር መገንባት የዚህ ትዉልድ ሀላፊነት ነዉ፡፡ የወያኔ መንግስት በዘራዉ መርዝ ተያይዘን እንዳንጠፋ በልዩነት የሚነሱትን ወገኖች ማዳመጥ ጥያቄያቸዉን ማክበር ለምንመኛት ወይም እንድትኖር ለምንፈልጋት ኢትዮጵያ ህልዉና ጉልህ አስተዋፆ ይኖረዋል፡፡ ምክንያት ብጠቅስ ኢትዮጵያ የተገነባችዉ በዉሰጧ በሚኖሩ ብሄሮች በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ህብረት ነዉ፡፡ ስለዚህ በዚች ሀገር ዉስጥ የሚኖሩ ህዝቦች እኩል በቅንልቦና ላይ የተመሰረተ የሁሉንም መብት የሚያስጠብቅ የጋራ ስርዓት መመስረት አሌ የማይባል ሀቅ ነዉ፡፡ ያለበለዚያ ግን መብቴ ይጠበቅልኝ፤ ማንነቴ የታወቅልኝ ብለዉ የሚነሱ የብሄር ጥያቄዋች ማፈን ዉጤቱ ለመለያየት፤ ለእርስ በእርስ ግጭት ምክንያቶች ከሚሆኑት ዉስጥ አንዱ እና ዋነኛዉ ነዉ፡፡ ስለአንድ ኢትዮጵያ ስናወራ ስለብዙሀኑ ብሄር ፍላጎት ማሰብ እና የመብት ጥያቄያቸዉን መመለስ የግድ መሆን አለበት፡፡ እንዲህ ስናደርግ የምንፈልጋትን ኢትዮጵያ ሁላችንንም በአለም ፊት እኩል እና በልዩነታችን ዉስጥ አንድ እንደሆንን የምናሳይበትን እና ለቀጣይም ትዉልድ ሀላፊነታችንን ተወጥተን ከታሪክ ተወቃሽነት ልንድን እንችላለን፡፡ ያለበለዚያ ግን ”ዉሻ በቀደዳ ጅብ ይሾልካል” እንደሚባለዉ ይህንን ልናስወግድ ካልቻልን ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ለተነሳዉ የጋራ ጠላታችን ወያኔ እንዲያፈራርሰን እና የምንኮራበት ማንነታችን እንዲጠፋ መሆኑ አይቀርም፡፡ ይህንን ሀላፊነት የማይሰማዉ የወያኔ መንግስት ከስልጣን ማስወገድ እና በወያኔ የጭቆና አገዛዝ እየተረገጠ ያለዉን ህዝባችንን ነፃ ማዉጣት ተቀዳሚ ተግባራችን አንዲሆን እግ/ር ይርዳን፡፡ ፍትህ ፈትህን ለተጠሙ ይሁን!!!

የፀረ-ሽብር፣ የፕሬስና የሲቪል ማኅበረሰብ ሕጎቹ ማወዛገባቸውን ቀጥለዋል

“መፈክር በተሰማ ቁጥር መፈክሩን ተከትለን አንነጉድም” አቶ ጌታቸው ረዳ የጠቅላይ ሚኒሰትሩ ቃል አቀባይ የ2013 የስቴት ዲፓርትመንት ሪፖርት መውጣትን ተከትሎ ባለፉት አምስት ዓመታት ሲያወዛግቡ የነበሩት የፀረ-ሽብር፣ የመገናኛ ብዙሃን እና የበጎ አድራጎትና ማኅበራት (የሲቪል ማኅበረሰብ) ሕጎች ማወዛገባቸውን ቀጥለዋል። የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መ/ቤት (ስቴት ዲፓርትመንት) በየዓመቱ በሚያወጣው ሪፖርት ላይ በሕጎቹ የሀገሪቱን ሕዝቦች ስብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ላይ ጫና እንደሚያደርጉ ሲጠቅስ መቆየቱ ይታወሳል። መንግስት በበኩሉ የፀረ-ሽብር ሕጉ በሀገሪቱ ላይ ያንዣበበውን የሽብር አደጋ ለመግታት አስፈላጊ መሆኑን፣ የፕሬስና ሕጉም ሀሳብን የመግለፅ ነፃነትን ለማስፋት እንዲሁም የሲቪል ማኅበረሰብ አዋጁም በሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ የውጪ ጣልቃ ገብነትን ለመግታትና ሀገር በቀል የሲቪል ማኅበራትን ለማበረታታት መሆኑን ሲገለፅ ቆይቷል። ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሕጎች የሀገሪቱን ዴሞክራሲያዊ ሂደት እያሽመደመደና የፖለቲካ ዓላማ ያዘሉ፣ የገዢውን ፓርቲ የስልጣን ዘመን የሚያረዝሙ በማለት ሲቃወሙ ቆይተዋል። ከሰሞኑንም ይሄው ጉዳይ እንደ አዲስ ተነስቶ እያወዛገበ ነው። በመንግስት በኩል ሕጎቹን የማሻሻል ሁኔታ በራሱ መንገድ የሚያየው መሆኑን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ ገልፀዋል። “በእኛ እምነት ሕጎቹን መቀየር የሚያስፈልግ ከሆነ በሂደት ከታለመላቸው ዓላማ አንፃር ያመጡት ስኬት ተመዝኖ፣ የኢትዮጵያ መንግስት በራሱ መንገድ (Organic Process) መልሶ የሚያያቸው ይሆናል” ያሉት አቶ ጌታቸው ከዚህ ውጪ ሕጎቹን በደፈናው ከመቃወም በስተቀር በዝርዝር የመጣ ጉዳይ የለም ብለዋል። ከዚህ ይልቅ ሕጎቹን ለማስቀየር መፈክር ማሰማቱ እንደማይጠቅም ገልፀዋል። አቶ ጌታቸው “መፈክር በተሰማ ቁጥር መፈክሩን ተከትለን የምንነጉድበት ምክንያት የለም” ብለዋል። በአንድነት ለዴሞክራሲ ለፍትህ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው በበኩላቸው ፓርቲያቸው ገዢው ፓርቲ በሕጎቹ ላይ በጠረጴዛ ዙሪያ ለመነጋገር ፈቃደኛ ከሆኑ በደስታ እንደሚቀበሉት ተናግረዋል። ምንም እንኳ ፓርቲያቸው ለስርዓት ለውጥ የሚታገል ቢሆንም፤ ኢህአዴግን ጨምሮ በውጪ ሀገር በሚገኙ በሕግ ካልተከለከሉ በስተቀር ከማንኛውም የዴሞክራሲ ኃይል ጋር ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ገንቢ ውይይት ማድረግ እንፈልጋለን። ኢህአዴግም በማንኛውም የሕግና የፖሊሲ የሀሳብ የበላይነት ለማግኘት ፍረጃውን በመተው፣ ፓርቲዎችን በማናናቅና ሕዝባዊ መሠረታቸውን ሳይክድ እስከመጣ ድረስ በሕጎቹ ላይ ለመወያየት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ለመነጋገር እንዲያመችም ሕጎቹን በጅምላ ከመቃወም ባለፈ በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ለመነጋገርም እንደሚፈልጉ ገልፀዋል። ሕጎቹን በጅምላ የሚቃወሙትም አዋጆቹ የወጡበትን መሰረታዊ ፍላጎት (Intention) ዴሞክራሲንና ሕገ-መንግስቱን የሚጥሱ በመሆኑ ነው ብለዋል። አስተያየቶች (0)አስተያየትዎን ይተዉልን

Wednesday, 5 March 2014

ኣፍሪካ ሃገራት የሚነሱ መሪዎች ስልጣን ላይ ከመጡ በሁዋላ ሁለት ነገር በጣም ይወዳሉ።

የሃገራቸው ነገር ሲነሳ የሚከነክናቸው ወገኖቻችን ኢትዮጵያ ላለባት ችግር መፍት ሄው ምንድነው?? እያሉ ኣጥብቀው ሲጠይቁ ይደመጣል። መፍትሄውም ብቻ ሳይሆን ችግሩ ማለትም እውነተኛው ችግር የት ላይ ነው ያለው??? ብለውም ኣጥብቀው ሲደመሙ ይታያል። በርግጥም ሁላችን ኢትዮጵያዊያን የሆንን ችግሩ ምንድነው? ብለን ከጠየቅን ኣንዳንዶች ሊገረሙብን ይችላሉ። የችግሩ ተካፋይ ሆነን ሳለ፣ እየተጉላላን ያለነው እኛው ሆነን ሳለ፣ እንደገና መልሰን የሃገራችን ችግር የት ጋር ነው??? ብለን ስንጠይቅ የምናወጋቸው ሰዎች ምናልባትም ግራ ሊጋቡ ቢችሉ ኣይደንቅም። ነገር ግን መጠየቃችን ትክክል ነው። በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ትንቢተ ዳንዔል ላይ ኣንድ ናቡከደነጾር የተባለ ንጉስ ኣንድ ጊዜ ጠቢባንን ጠርቶ የህልም ፍቺ ይጠይቃል። ጥበበኞቹም ህልሙን ንገረንና ፍቺውን እንነግርሃለን ሲሉት ህልሙ ጠፍቶብኛል ስለዚህ ህልሙንም ፍቺውንም ውለዱ ብሎ ጉድ እንዳፈላ እናነባለን። እኛ ኢትዮጵያዊያን የዋናው ችግር ተጽእኖዎች የየእለት ኑሮኣችንን ሲያምሱት ብናይም ዋናውን የችግሩን ምንጭ መፈለጋችን ግን ኣሁንም ትክክል ነው። የሃገራችንን ዋና ችግር የት ጋር ነው ብለን ኣጥብቀን ከጠየቅን በርግጥ የስርዓት ችግር ነው ወይ? ስርዓት በማጣታችን ነው ወይ የከፋ ችግር ላይ የወደቅነው? ብለን እንጠይቃለን። በዚህ ኣገባብ ስርዓት ስንል የኣይዲዮሎጂውን ጉዳይ ሳይሆን ፍትህና ተጠያቂነት፣ ግልጽነትና የህዝብ የበላይነት የሚንሸራሸርበት ሲስተም ተዘርግቷል ወይ ብሎ የመጠየቅ ያህል ነው። ስለ ስርዓት ስናነሳ ደግሞ በዋናነት የሚታየው ህገ- መንግስታዊ ስርዓቱ ነው። ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ ምን ያህል ለዜጎች ይጨነቃል፣ ምን ያህል ለፍትህና ለነጻነት ለህዝቦች ጥቅም መንሸራሸሪያ ይህናል? ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል። በዚህ ረገድ በርግጥ መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች ቢኖሩም በዋናነት ግን ችግራችን የስርዓት ችግር ሆኖ ኣናይም። ለኣብነት የ1955ቱን ህገ መንግስት ስናይ የፕሬስ ነጻነትን ይሰጣል፣ እኩል የህግ ከለላ ይሰጣል፣ የመሰብሰብ፣ ሰልፍ የማድረግ መብትን ሁሉ ይሰጣል። የደርጉም ቢሆን ለዜጎች የሚጨነቅ ኣይነት ነው። “ኢትዮጵያዊያን በህግ ፊት እኩል ናቸው” ይላል። ከሁሉ በላይ ደግሞ የ1995ቱን ስናይ “ሰብዓዊ መብቶችና ነጻነቶች ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የሚመነጩ የማይጣሱና የማይገፈፉ ናቸው” ብሎ እጅግ ኣጠንክሮ ለዜጎች መብት መቆሙን ይደነግጋል። በውነቱ ይህ ኣንቀጽ ብቻውን ለኛ ለኢትዮጵያዊያን ዋስትና ይሆን ነበር። ይሁን እንጂ ተግባራዊው እውነት ደግሞ ለብቻው በተቃራኒው ተንሰራፍቶ ይታያል። ይህ ለምን ሆነ? እንዴት እንዲህ ሊሖን ይችላል? ብለን ነው መጠየቅ ያለብን። እንዲህ ስንጠይቅ የችግሩ ዋና ጉዳይም የስርዓት እጦት ሳይሆን ሌላ ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን። በርግጥ ለወደፊቱዋ ኢትዮጵያ የተሻለ ስርዓት ማምጣት ያስፈልጋል። በተለይም ብዙህነቱዋን ተንከባክቦ የሚይዝ ማህበራዊ የፖለቲካ ስርዓት ያሻናል። ያ ማለት ግን ከችግራችን እንድንወጣ ብቻውን ዋስትና ነው ማለት ኣይደለም። የቱንም ያህል ጥሩ ስርዓት ዘርግተን ከችግራችን ሳንወጣ ልንቆይ እንችላለን። ርግጥ ነው የማንነት ፖለቲካ ማህበራዊ ቀውስን ያመጣ ችግሮች የበለጠ እንዲነዱ የሚያደርግ ጉዳይ በመሆኑ ከዚህ መንግስት ውድቀት በሁዋላ ከዚህ የፖለቲካ መዋቅር መውጣታችን ለመፍትሄ ትልቅ በር ኣለው። ይሁን እንጂ ኣሁንም ቢሆን የቱንም ያህል ቆንጆ ስርዓት እናምጣ ኢትዮጵያን ከመከራና ከርሃብ የሚያወጣት እሱ ብቻውን ኣይደለም። ታዲያ ምንድነው? የሚል ጥያቄ መምጣት ኣለበት። ኣዎ፣ ዋናው የሃገራችን ችግር ያለው የፖለቲከኖች ስብእና ተክለሰውነት ወይም ፐርሰናሊቲ ጋር የተገናኘ ነው። ሃገራችን ከችግር እንድትወጣ ከተፈለገ የፖለቲካ ቁርጠኝነትን ይጠይቃል። የችግሮቻችን ቁንጮም የፖለቲካ ቁርጠኝነት እጦት ነው ብሎ መደምደም ይቻላል።የፖለቲካ ቁርጠኝነት ስንል ኣንድ ፓርቲ ስልጣን ከያዘ በሁዋላ የፍርድ ቤቱን ልጓም ለቀን መልሶ ከበላንም ይብላን፣ በራሳችን ላይ ይፍረድብን፣ ብሎ በራስ ላይ የመወሰን ኣቋም ነው። ወታደሩን ኣገርህን ጠብቅ የፓርቲ ጠባቂ ኣይደለህም ኣንተ ኣገር ጠባቂ ነህ ለማለት የፖለቲካ ሰዎችን ቁርጠኝነት ይጠይቃል። ፖሊሱን፣ ባንኩን፣ ሚዲያውን ሁሉ ልጓሙን ለቆ በሙያህ ኣገልግል ብሎ መወሰን ሲቻል ነው ከገባንበት ኣረንቋ የምንወጣው። የናፈቀንን ዴሞክራሲ በህይወት የምናየው። ጥያቄው ይህ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እንዴት ሊመጣ ይችላል ነው። የፖለቲካ ቁርጠኝነት ከጥቂት የፖለቲካ መሪዎች ከራስ ጥቅምና ዝና በላይ የህብረተሰብን ዝናና ጥቅም በተጠሙ ሰዎች ሊነቃነቅ ይችላል። ኣንድ ቁርጠኛ መሪ ኣገር ሊለውጥ ይችላል። በታሪክ የታዩ ኣንዳንድ ቁርጠኛ መሪዎች በየሃገሩ ተነስተው ጥሩ መሰረት እየጣሉ ኣልፈዋል። በሃገራችንም የተጠማነው ይህንን ነው። በኣሁኑ ጊዜ ተቃዋሚው ክፍል መንግስትን ኣጥብቆ ማውገዙ ትክክል ነው። የህዝቡም ልብ ነጸብራቅ ነው። ይሁን እንጂ ይህ መንግስት በማንኛውም መንገድ ሲወድቅ ስልጣን ይዞ ጥሩ ስርዓት መዘርጋቱ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ቁርጠኝነት (political commitment) ያላቸውን ሰዎች ይዘዋል ወይ? ብለን እንድናስብ ያደርገናል። በዚህ ረገድ ተቃዋሚው ጥቃቅን በሆኑ ፖሊሲዎች ከመከፋፈል ይልቅ ወደ ጋራ እያመሩ ከሁሉ በላይ የፖለቲከኞችን ስብእና የመገንባቱ ላይ ማተኮር ለነገይቱ ኢትዮጵያ ዋስትና ይሆናል። ይህን ስብእና ወይም ተክለሰውነት የመገንባት ስራ ፓርቲዎችን ቢዚ የሚያደርግ ወቅታዊ ስራ መሆን ኣለበት። ኢትዮጵያ በኣሁኑ ደረጃዋ ጥቃቅን ፖሊሲዎችን በማነጻጸር የምታማርጥበት ጊዜ ላይ ኣይደለችም። መሰረታዊ የሆኑ ጉዳዮችን ያጣች በመሆኑዋ የስካንዲኒቪያው ኣይነት ዴሞክራሲ ይሻልሻል የኣሜሪካው ኣይነት? ማለቱ ያልበላትን የማከክ ያህል ነው። ሁሉቱም ሆኖላትስ ነው? ዋናው በኣሁኑ የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጉዳይ ፓርቲዎች እኔ እሻላለሁ ለማለት ዋናው መመዘኛቸው የተሰባሰቡት በተለይም ኣመራር ላይ ያሉት ግለሰቦች የፖለቲካ ቁጠኝነት ኣላቸው ወይ? ቁርጠኝነት በሞላቸው ሰዎች ቁጥር የትኛው ፓርቲ ያይላል? የሚል ልብ ያለው ድጋፍ ነው በተግባር የሚታየው ወይም መታየት ያለብት። በቲየሪ ደረጃ በኣሁኑዋ ኢትዮጵያ በፍርድ ቤት ጉዳይ መንግስት ጣልቃ ኣይገባም። ይሁን እንጂ በተግባር ይገባል። ይገባል ብቻም ሳይሆን ፍርድ ቤት የፖለቲካ መሳሪያ ነው። ኣሁን እዚህ ጋር የጎዳን የስርዓቱ ወይም የኣሰራሩ ጉዳይ ሳይሆን መከራ ውስጥ የከተተን ጉዳይ የግለሰቦች ስብእና ጉዳይ ሆኖ ነው የምናየው። ለምን እነዚህ ግለሰቦች ስርዓቱን ይጥሳሉ፣ ህጉ ለምን ኣቅም ያጣል? ካልን የፖለቲከኞቹ ላእላይ ስብስብ በተለያየ የግል ጥቅማጥቅም የተተበተበ በመሆኑ ነው። ድህነታችንም ኣንዱ ኣስተዋጾ ያደረገ ይመስላል። የተሻለ ስራ ለማግኝነት፣ ከድህነት ለመላቀቅ፣ ፖለቲካን መሳሪያ ማድረጉ የተለመደ መሆኑና ወደዚያ ጠጋ ያሉ ሃላፊዎች በዚህ ሞቲቭ የተሞሉ ስለበዙበት ስርዓቱ በቁሙ እንዲሞት ኣድርጎታል። በርግጥም በኣሁኑ የነጻነት ትግል ኣሰላለፍ በኩል ጎድሎ የታየው ይሄ ነውና ይህንን ማቋቋም ተገቢ ነው። ይህ ኮሚሽን ፓርቲዎችን እያበራታታ ይህን ተፈላጊ ስብእና በመገንባቱ ረገድ ከፍተኛ ኣስተዋጾ ያደርጋል። ፓርቲዎችን በማቀራረብ ረገድ፣ የመፍትሄ ኣሳቦችን በማጠናቀር ረገድ፣ ለኣዲሲቱዋ ኢትዮጵያ የሚሆነውን ኣዲስ ሰውነት በመጠቆሙ ረገድ ከባድ ሚና ሊጫወት ይችላል። ከዚያ በተረፈ ደግሞ እኛ ተራ ዜጎች መሪዎቻችንን የማጎልበትና ወደ ህብረት የመግፋት እንዲሁም ስብእናቸውን የመገንባት ሃላፊነት ኣለብን። የብዙ ኣፍሪካ ሃገሮች ችግር ይሄ ይመስለኛል። ታግለን በብዙ መስዋእትነት ኣንድ ኣምባገነን ከጣልን በኋላ መልሰን በሌላ ኣምባ ገነን እንተካለን። ሌላው ኣለም እየተሻሻለ ሲሄድ ይሄኛው ክፍለ ኣለም ወደ ኋላ የቀረበት ትልቁ ምክንያት የነጻነት ታጋዮች ራሳቸው በሚገባ ለኣመራር የሚበቃ ስብእና ሳያዳብሩ ወደ ስልጣን ስለሚመጡ ነው።ደቡብ ሱዳን ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ናት። ለብዙ ኣመታት የነጻነት ትግል ታግለው፣ ብዙ ደም በመፍሰሱ ዓለም ሁሉ እነዚህ ሰዎች ቢገነጠሉ ይሻላል ብሎ ፈርዶላቸው ተገነጠሉ። የዳርፉሩን እልቂት የማያውቅ፣ ያልሰማ ያለም ክፍል የለም። ያ ሁሉ ሆኖ ኣዲስ ኣገር ከመሰረቱ በኋላ ገና ኣንድ ጊዜ እንኳን ምርጫ ሳያካሂዱ፣ በህዝብ የተመረጠ መንግስት ሳይመሰርቱ፣ ከሁለት ዓመት ያልዘለለ እድሜ ያላትን ኣገር በጎሳ ከፋፍለው ማመስ ጀመሩ። ያለ መታደል ሆኖብን በኣንዳንድ ኣፍሪካ ሃገራት የሚነሱ መሪዎች ስልጣን ላይ ከመጡ በሁዋላ ሁለት ነገር በጣም ይወዳሉ። ኣንደኛው ዝና ሲሆን ሁለተኛው ገንዘብ ነው። ሁለቱም እጆቻቸው ይዘዋል። ባንዱ ስልጣን በሌላው ገንዘብ። ዝናውን ወደው ገንዘቡን ችላ የሚሉ ቢሆኑ ትንሽ ይሻል ነበር። ነገር ግን ሁለቱንም በሃይል ስለሚወዱና ለዚህ የተሰጠ ስብእናቸው በውስጣቸው ስላልሞተ ክብ በሆነ ችግር ውስጥ እንድንወድቅ ኣድርጎናል።ኢትዮጵያዊያን በዚህ ላይ ልንነቃ ይገባናል። በተለይ የፖለቲካ ሰው መሆን የፈለጉ ወገኖቻችን፣ መሪ መሆን የሚሹ ወገኖቻችን በየጊዜው የባህርይ ለውጥ እያሳዩ በኣመለካከትና በሃላፊነት ስሜት እያደጉልን እንዲሄዱ እንሻለን። ከፍ ሲል እንዳልኩት እኛ ተራ ዜጎች ከውጭ ሆነን መፍረድ ብቻ ሳይሆን መሪዎቻችንን መንከባከብና ፍቅርን ክብርን ማሳየት ለፖለቲካ ቁርጠኝነታቸው ሃይል ይሰጣል።

Tuesday, 4 March 2014

ኢትዮጵያ እየከሳች አላሙዲ በሃብት እየወፈሩ ነው፤ የዓለማችን 61ኛው ቢሊየነር ሆኑ

(ዘ-ሐበሻ) ታዋቂው የዓለማችን የቢዝነስ መጽሔት ፎርብስ በየዓመቱ የዓለማችንን ቢሊየነሮች ደረጃ የሚያሳውቅበትን መረጃ ይፋ አደረገ። ባለፈው ዓመት የዓለማችን ሁለተኛው ሃብታም የነበሩት የማይክሮሶፍት ባለቤት ቢል ጌትስ የዓለማችን አንደኛ ቢሊየነር ሲሆኑ የፌስቡክ ባለቤት ማርክ ዙከምበርግ 21ኛው የዓለማችን ቢሊየነር ሆኗል። ኢትዮጵያ ውስጥ በመሬት ነጠቃ የሚከሰሱት ሼህ መሀመድ አላሙዲ የዓለማችን የሃብታምነት ደረጃቸው ከዓመት ዓመት እድገት እያሳየ አምና ከነበሩበት የ65ኛ ደረጃ 4 ደረጃዎችን በማሻሻል የዓለማችን 61ኛው ሃብታም ሆነው በመጽሔቱ ተቀምጠዋል። እንደ ፎርብስ ገለጻ የ8 ልጆች አባት የሆኑት በአባታቸው የሳዑዲ፤ በእናታቸው ደግሞ ኢትዮጵያዊ የሆኑት አላሙዲ $15.3 ቢሊዮን አላቸው። ከሳዑዲ አረቢያ ሃብታሞች መካከል ሁለተኛው የሆኑት አላሙዲ የወያኔ/ኢሕአዴግ ደጋፊ ከመሆናቸውም በላይ፤ ከስር ዓቱ ጋር በፈጠሩት ስር የሰደደ ወዳጅነት በአድልዎ አብዛኛው የኢትዮጵያ ወሳኝ የንግድ ተቋማት በርሳቸው ስር እንዲያዙ ትልቅ ውለታ እንደተዋለላቸው በተደጋጋሚ እንደሚተቹ የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ። ምንም እንኳ ሼኩ በነዳጅ ዘይት ሽያጭ ላይ የተሰማሩ ቢሆኑም በተለይም የኢትዮጵያን ወርቅ በእርሳቸው ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ የሰውዬው ሃብት ከእለት ወደ ዕለት እንዲጨምር አስችሎታል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ። የፕላኔታችን 10ሩ ቢሊነሮች የሚከተሉት ናቸው። 1ኛ. ቢል ጌትስ 76 ቢሊዮን ዶላር 2ኛ. ቻርሎስ ሳሊም ሄሉ 72 ቢሊዮን ዶላር 3ኛ. አማሪኮ ኦርቴጋ 64 ቢሊዮን ዶላር 4ኛ. ዋረን ብፌት 58.2 ቢሊዮን ዶላር 5ኛ. ላሪ ኤልሰን 48 ቢሊዮን ዶላር 6ኛ. ቻርለስ ኮች 40 ቢሊዮን ዶላር 7ኛ. ዳቪድ ኮች 40 ቢሊዮን ዶላር 8ኛ. ሼልደን አንደርሰን 38 ቢሊዮን ዶላር 9ኛ. ክርስቲ ዋልተን እና ቤተሰቦቿ 36.7 ቢሊዮን ዶላር 10ኛ. ጂም ዋልተን 34. 7 ቢሊዮን ዶላር የፌስቡክ ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ በ28.5 ቢሊዮን ዶላር 21ኛ፣ አላሙዲ በ15.3 ቢሊዮን ዶላር 61ኛ፣ ቸልሲ ስፖርት ክለብ ባለቤት ኢብራሞቪች በ9.2 ቢሊዮን ዶላር 137ኛ ሆነዋል። source ze-Habesha

Sunday, 2 March 2014

የዩናይትድ እስቴስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኢትዮያ ዉስጥ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳለ በዘንድሮዉ አመታዊ ሪፖርቱ ይፋ አደረገ

ዋሽንግተን ዲሲ፤ የካቲት 20/2006 (ቢቢኤን) ፦ የዩናይትድ እስቴስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት (State Department) ባወጣዉ የዘንድሮ የሰዓዊ መብት ሪፖርት ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ያከናዉናቸዋል ያለዉን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በመዘርዘር ሰፋ ባለ መልኩ አቅርቦታል። ቀድም ሲል ኢትዮጵያ ዉስጥ በ2003 በተደረገዉ ምርጫ፤ በሟቹና በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስቴር መለስ ዜናዊ ይመራ የነበርዉ ኢ.ህ.አዴ.ግ ከ547 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ 545 መቀመጫዎች አሸንፏል መባሉን ሪፖርቱ እያመላከተ የምርጫ ጣቢያዎች በመንግስት ሐይላት ቁጥጥር ስር እንደነበሩና አለምአቀፍ ታዛቢዎች ስራቸዉን በተገቢዉ መልኩ እንዳያከናዉኑ ገደብ እንደነበረባቸዉ ይገፃል። John Forbes Kerry current United States Secretary of State. በአገሪቱ ዉስጥ ባለዉ ከፍተኛ የመብት ረገጣ ሳቢያ ዜጎች የመሰብሰብ፣የመደራጀት፣የመናገር መብትን በገሃድ እንደሚነፈጉ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ያስደረግቸዉን ጥናቶች ተመርኩዞ ያብራራል። እነዚህን የዲሞክራሲ እሴቶችን ለመተግበር የሚሞክሩም ይታሰራሉ፣ይንገላታሉ፣ይዋከባሉ፣ዛቻ ይደርስባቸዋል፣ ክብራቸዉ ተነክቶ እንዲሸማቀቁምይደረጋሉ በማለት ሪፖርቱ ያትታል።እርዳታን የሚያስተባብሩ፣ እርዳታን ለጋሽ የሆኑ ድርጅቶች፣ ማህበራዊና ትርፍ አልባ የሆኑ ተቋማት (NGO) የግብረ-ሰናይ ተልእኮ አቸዉን እንዳይፈጽሙ የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚከለክል፤ በሰዎች ላይ ህገ ወጥ የሆነ ግድያ እንደሚፈጽም፣ዜጎች ግርፋት-ድብደባ እንደሚደርስባቸዉ፣ ወጥ የሆኑ የማሰቃያ ተግባራት በመንግስት ሐይላት እንደሚፈጽምና በአገሪቱ እስርቤት የሚገኙ ታሳሪዎችን ህይወት ለአደጋ የሚያጋልጹ አሳቃቂ ተግባራትም እንዳሉም በሪፖርቱ ላይ ተገልጿል። ሰዎች በፍርድ ቤት ሳይበየንባቸዉ በጅምላ ተይዘድዉ ይታሰራሉ፤በፍርድ ቤት የአሰራር ዘይቤም ይሁን በፍትህ ሒደቱ ዉስጥ ግልጽ የሆነ ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት አለበት፤ ፍርድ ቤቶችም ደካማ ናቸዉ! ሲል ሪፖርቱ ይደመድማል። መንግስት ሀሳብን በነጻነት ለመግለጽ የሚሞክሩ ያገሪቱ ዜጎች ላይ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ እንደሚወስድ በዝርዝር የተቀመጠ ሲሆን፤ በነሐሴ 2/2005 የኢድ-አልፈጥር በዓል በሚከበርበት ወቅት፤ በሰላማዊ መንገድ ተቃዉሞ ያሰሙ ከነበሩት ሙስሊም ኢትዮጵያዉያን መካከል ከ 1000 በላይ የሚሆኑት በጅምላ ተግበስብሰዉ መታሰራቸዉና ከመካከላቸዉም የሞቱ መኖራቸዉ በሪፖርቱ ላይ አጽንኦት ተሰጥቶታል።የዜጎች ግላዊ መብትን በመግፈፍ፤ በሙስሊሙ ማህበረስብ ላይ ህገወጥ የሌሊት ፍተሻዎችም ተደርገዋል። ግልጽና ስልታዊ በሆነ መልኩም ከቦታ ወደ ቦታ ዜጎችን የማፈናቀል መርሃግብር በመንግስት መፈጸሙን የሚያስረዳዉ ሪፖርት ነጻ መሆን የሚገባዉ የመማርና የማስተማር ሒደት የመንግስት ጣልቃገብነት እንዳለበትም ይገልጻል። ዜጎች ዲሞክራሲያዊ መብታቸዉን ተጠቅመዉ በነጻነት መንግስትን የመቀየር አቅማቸዉ ሆን ተብሎ የተገደበ ነዉ!በፖሊስ፣በፍርድ ቤቶችና በመንግስት አመራር ዉስጥ በስልጣን መባለግ-ሙሰኝነት-ጉቦኝነት በገሃድ ይተገበራሉ። መንግስት በስልጣን የባለጉንና የህዝብን አደራ ያጎሳቆሉ ወንጀለኞች ችላ በማለት ፖለቲካዊ ዉለታን ይዉላል፤ ፖለቲካዊ ምህረትን ለምግባረ ብልሹ የመንግስት አካላት እንደሚያደርግ የዩናይትድ እስቴትስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሪፖርት ያጋልጻል። በኢትዮጵያ ህገ መንግስት የጾታ እኩልነት የተረጋገጠ ቢሆንም በመንግስታዊ የአሰራር መዋቅር ዉስጥ ሴቶች ይጨቆናሉ። ህገወጥ የሆነ የሰዉ ዝዉዉር ይፈሰማል፣ የአካል ጉዳተኞች (የተሳናቸዉ) ማህበራዊ ጭቆና ይደርስባቸዋል፣የ ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ህሙማን ማህበራዊ የሆነን በደል ይጋፈጣሉ፣የሰራተኖች መብት የተገደበ በመሆኑ ህፃናትን አስገድዶ የጉልበት ስራ ማሰራቱ የተለመደ መሆኑ በሪፖርቱ ላይ ተዘርዝሯል። የመንግስት ሐይላት የሰዎችን ደብዛ ያጠፋሉ፤ የሰዎች መሰወር ይስተዋላል! በትግራይ ክልል በአላማጣ ከተማ መንግስት በልማት ስም ቤቶችን በሚያፈርስበት ወቅት አለመግባባት ተፈጥሮ የታሰሩ 12 የአካባዊ ተወላጆች የገቡበት እንደማይተዋቅ እና ተመሳሳይ በሆነ መልኩ በሶማሌ ክልል ያለዉ ልዩ የፖሊስ ሐይል በክልሉ ተወላጆች ላይ ኢሰብዓዊ የሆነ ማንገላታት፣ማሰቃየት፤ ግድያ እደሚፈጽም መታወቁ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ህገመንግስት ቶርቸር (ግርፋት ድብደባ ማሰቃየት)ይከለክላል። ቶርቸርን የመሰሉ የሰዉ ልጅን ክብር ገፋፊ የሆኑ ጭካኔ የተሞላባቸዉ ተግባራት፤በመንግስት የደህነነትና የጥበቃ ሐይላት እንደሚፈጸሙ በማጋለፅ በጥር 9/2005 የተያዘዉ የሙስሊሞች ጉዳይ መጽሔት አምድኛ እና ማኔጂንግ ኢዲተር የነበረዉ ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ በማእከላዊ የምርመራ ማእከል ዉስጥ በተደጋጋሚ የዚሁ ህገወጥና አስከፊ ተግባር ሰለባ እንደነበር በዩናይትድ እስቴት የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሪፖርት ላይ በዋቢነት ተጠቅሷል። በጥቅምት 8/2006 ሁማን ራይትስ ዎች ያወጣዉን ሪፖርት እንደ አብነት በመጥቀስ በመጥቀስ በማእከላዊ የምርመራ ማእከል ዉስጥ መርማሪዎች ታሳሪዎችን በማስገደድ የእምነት ቃል እንደሰጡ እንደሚያደርጉ የዩናይትድ እስቴትስ የዉጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት እየገለጸ፤ በማእከላዊ እስር ቤት ዉስጥ ከፍተኛ የሆነ ቶርቸር (ግርፋት-ድብደባ-ማሰቃየትት)፣ ዛቻ፣ማስፈራራርት፣ እስረኞች ላይ ዉሃ መድፋት፣የእስረኞችን እጅ ጣራ ላይ አስሮ ለረጅም ሰዓታት ማቆም፣እሰረኞችን ነጥሎ ለብቻ ማሰርን የመሳሰሉ ኢሰብዓዊ ተግባራት እንደሚፈጽሙና ዲፕሎማቶች፣ኤንጂኦ (በጎ አድራጊ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ትርፍ አልባ ድርጅቶች) እስረኞችን የመጎብኘት ፍቃድ እንደሚነፈጉ ተገልጿል። በመስከረም 2005 በተገኘዉ መረጃ መሰረት ከ70,000 እስከ 80,000የሚድርሱ እስረኞች መኖራቸዉ ሲታወቅ፤ ከነዚህም መካከል 2500ሴቶች ሲሆኑ 600 ህጻናት ከእናቶቻቸዉ ጋር መታሰራቸዉ እና ታዳጊ ወጣቶች ከአዋቂዎች ጋር አብረዉ እንደሚታሰሩ ተዘግቧል። የአገሪቱ እስር ቤቶች በጣም የተጣበቡ ከመሆናቸዉም ባሻገር ወታደራዊ ተቋማትም እንደ እስር ቤት ማገልገላቸዉ ተዘግቧል። በርካታ እስረኞች ከመጣበብ፣ተነጥሎ ከመታሰር፣ የተማሏ የጤና ግልጋሎት ካለመኖሩ የተነሳ ለአእምሮ ህመም ይዳረጋሉ። ለአንድ እስረኛ የምግብ፣ የዉሃ አቅርቦትን ለመለገስ እና የጤና ግልጋሎት ለመስጠት በቀን ስምንት ብር ከአስር ሳንቲም ብቻ እንደተመደበ የዩናይትድ እስቴትስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አመታዊ የሰዓዊ መብት ሪፖርት ይዘረዝራል። ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ከ2004 ጀምሮ ሰላማዊ የሆነ ተቃዉሞን በአወሊያ የትምርት ተቋም ዉስጥ በመጀመር ከአርብ ስግደት (ከጁመዓ ሶላት) በሗላ በቀጣይነት የተቃዉሞ መርሃግብር እንደሚያከናዉኑና፤ ይህ የቅዋሜ ተግባር ምንም ሰላማዊ ቢሆንም የፖሊስ አካላት ሰዎችን በመያዝ አላስፈላጊ ሐይል እንደሚጠቀሙ ሪፖርቱ ያስረዳል። በሐምሌ 14/ 2004 በሙስሊሞች የተደረገዉን ሰላማዊ ተቃዉሞ ተከትሎ መንግስት “የደህንነት ሰጋት” የሚል ማመካኛን በመፍጠር 28 ሙስሊሞችን አስሮ በጥር 24/2005 ክስ ያቀረበባቸዉ ቢሆንም በታህሳስ 3/2006 አስሩን በነጻ አሰናብቶ በአስራ ስምንቱ ላይ ያቀረበዉን ክስ ዝቅ አድርጓል። መንግስት እነዚህን የሙስሊም ታሳሪዎች በአለማችን ላይ ከሚታወቁ አሽባሪ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አላቸዉ ብሎ በገሃድ ለመፈረጅ መሞከሩም በሪፖርቱ ተገልጿል። የኢትዮጵያ መንግስት የመናገር-የመደራጀት-የመሰብሰብን መብት የሚተገብሩ ፖለቲከኞችናና ጋዜጠኞችን እንደሚያስር፣ እንደሚያሰቃይ፣ እንደሚያንገላታ፣ የሚገልጸዉ ሪፖርት ከፖለቲከኞች የመድረኩ አንዱአለም አራጌ ብሎም የኦሮሞን ማህበረስብ መብት በዲሞክራሲ ለማስከበር ከሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ተወላጆች በቀለ ገርባና ኦልባና ሌሊሳ ታስረዉ እየተሰቃዩ መሆናቸዉን፤ ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ከጋዜጠኞች እስክንድር ነጋ፣ሪዮት አለሙና ሰለሞን ከበደ በእስር ይማቅቃሉ ሲልም ሪፖርቱ ያስረዳል። መንግስት ነጻ-ፕሬስ እንዲከስም በሚያደርገዉ ከፍተኛ ጫና ጋዜጠኞች የእስርና የስደት ሰለባ Source ECADF