Friday, 28 February 2014

‘‘ፋሽዝም’’ በኢትዮጵያ!

ኢትዮጵያ በወያኔ ፈላጭ ቆራጭ ቡድናዊ አገዛዝ ስር ከወደቀችበት እነሆ ሁለት አስርተ ዓመታት ነጐዱ። ወያኔ ስልጣን ላይ ሲወጣ ካለፈው የተሻለ የዲሞክራሲ ለውጥ ይመጣል የሚል በብዙ ሰዎች ዘንድ የተስፋ ጭላንጭል ተጥሎለት ቢኖርም “ጅብ እስኪነክስ ያነክስ” እንዲሉ ስልጣናቸውን ካደላደሉ በኋላ ግን ተስፋ የተጣለለትን ዲሞክራሲ ደብዛውን በማጥፋት “ከፋፍለህ፣ በሆዱ ይዘህ፣ አሸብረህ፣ አደናግረህ፣ አናቁረህና አደንዝዘህ ግዛ” የሚለውን ሌሎች አምባገነን መንግስታት የሚከተሉትን የጡንቻ አገዛዝ ዘይቤ የዲሞክራሲ ሽፋን በመስጠት ዘላለማዊ ስልጣናቸውን ለማጠናክር ሲሉ በበለጠ ሲጠቀሙበት መቆየታቸው የአደባባይ ሚስጢር ሆኖ ቆይቷል። በአገራችን ኢትዮጵያ በሥልጣን ላይ ያለው የወያኔ አገዛዝ በዓለም ዙሪያ በተለያየ ዘመን ወደ ሥልጣን ከመጡት መሰል ፀረ-ሕዝብ መንግሥታት ቢብስ እንጂ በምንም መልኩ የተሻለ አይደለም። ፋሽዝምን እንቃወማለን፣ እናወግዛለን እያለ በጫካ ያናፋ የነበረው ወያኔ ዛሬ በዲሞክራሲ ድባብ ሥር እየተገበረው ያለ አገርና ሕዝብን ማዋረድና መዝረፍ፣ መቀጣጫ እያለ በግፍ ማሰርና መግደል ምን ተብሎ ሊጠራ ነው? በአዲስ አበባ ፣ በጋምቤላ ፣ በአዋሳ ፣ በወለጋ ፣ በሰሜን እና በአራቱም ማእዘን የኢትዮጵያ ክልሎች በየእለቱ በወያኔ ታጣቂዎች እየተካሄደ ያለውን የጅምላ ጭፍጨፋ ምን ብለው ይጠሩታል? ወያኔ ኢትዮጵያን ሲቆጣጠር ተሸክሞት የመጣውን በቀል አማራው፣ ኦሮሞው፣ ጋምቤላው፣ አፋሩ፣ ኦጋዴኑ ወዘተ. ዘር የማጥፋት ተግባሩን ፈጽሞታል፤ አሁንም እያጠፋ፣ እየገደለ በየወህኒ ቤቶቹ እየማገደው ነው። ይዞት የመጣው ድህነትና በሽታን ብቻ ነው። ፖሊሲው የኢትዮጵያን ሕዝብ ከዓለም ሃገሮች በድህነት ከወለል በታች ያደረገ ስርዓት ነው። የኢትዮጵያ ገበሬ የመሬቱ ባለቤት በነበረበት ወቅት እራሱን እና ቤተሰቡን አብልቶ ቀሪውን ለገበያ በማቅረብ ሕዝቧ እንደ አቅሙ በልቶና ጠጥቶ ያድር ነበር። የወያኔ መንግስት መሬት የመንግሥት ነው ብሎ በማወጁ የኢትዮጵያ ሕዝብ በገጠሩም በከተማም መሬት አልባ ሆኗል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በገዛ ሃገሩ ሁለተኛ ዜጋ ከመሆኑ የተነሳ ሲሞት እንኳን የሚቀበርበት ቦታ ያጣ ሕዝብ ሆኗል። የዚህ ጽሁፌ ዋና አላማ የወያኔ መንግስት የፋሽስት አገዛዝ ስለመሆኑ ምሳሌዎችን አንድ ሁለት በማለት ነቅሸ በማሳየት ማስረገጥ ሲሆን ወያኔ ከምስረታው ጀምሮ ያካሂድ የነበረውን የንፁሃን ወገኖቻችንን ጭፍጨፋ ለማስረጃነት በማንሳት ለማሳየት እሞክራሉ። • ወያኔ በ1969 መጀመሪያ በትግራይ ሰላማዊ ዜጋ ላይ ግድያ በመፈፀም ፋሽስታዊ ጉዞውን ሀ ብሎ ጀመረ። ግድያው ሳያንሰው የንፁሃን ዜጐችን ሃብትና ንብረትም ወረሰ። ከደደቢት በረሃ የጀመረውን አማራ የትግራይ ሕዝብ ጠላት ነው በማለት በተለያዩ ጊዜያትና ቦታዎች አማራውን በመጨፍጨፍ የዘር ማጥፋት ወንጀልም ፈጽመዋል። ለሴቶች በግዳጅ የማምከኛ መድሃኒት በመስጠት የአማራው ቁጥር እንዳይጨመር አድርገዋል። ከኖረበት ቀየውና መሬቱ በግዳጅ እንዲፈናቀል አድርገዋል። • ወያኔ ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ በ1984/5 መጀመሪያ ጀምሮ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ መጠነ ሰፊ የጥቃት ዘመቻ በመክፈት የግድያ፣ የቤት ማቃጠል፣ ንብረቱን መዝረፍና ከፍ ያለ ሰቆቃ አደረሰ። እንደ አማራው ሁሉ ከመኖሪያ ቦታውና ከመሬቱ ላይ ተፈናቅሏል። የኦነግ አባል ናችሁ እየተባሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ያለምንም የፍርድ ውሳኔ ወደ ወህኒ ወርደዋል። በየቦታው በከፍተኛ ትምህርት ተቋሟት የሚማሩት የኦሮም ልጆች ከትምህርታቸው ተባረዋል። የተባረሩትም፣ መባረራቸው አልበቃ ብሎ ለእስር ተዳርገዋል፤ የተገደሉትንም ቤት ይቁጠራቸው። ደጉና ሩህሩሁ የኦሮሞ ሕዝብ ከእርሻው ተፈናቅሎ የረሃብና የበሽታ ሰለባ በመሆን የፋሽስቱ ወያኔ የግፍ ፅዋ ገፈት ቀማሽ ከመሆን አላለፈም። • ወያኔ በጋምቤላ አኝዋኮች ላይ የፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀልን ማንም ይረሳልዋል ብየ አላስብም? ሕዝቡ ከመሬቱ ተፈናቅሎ አብዛኛው በጎረቤት ሃገሮች ስደተኛ ሆነው በየሃገሩ እየተንከራተተ በችግር ላይም ይገኛሉ። • የኦጋዴን ሕዝብም የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበታል። ቤት ንብረቱ በወያኔ ወታደሮች ተቃጥሎበታል፤ ሴት ልጆቹና ሚስቶቹ ተደፍረውበታል። በተጨማሪም ከመሬቱ ላይ ተፈናቅሎ ለስደት ተዳርጓል። • የአፋር ሕዝብም በሌሎቹ የኢትዮጵያ ጎሳዎች የደረሰው ደርሶበታል፣ እየደረሰበትም ይገኛል። የኢትዮጵያን ሕዝብ ከማሰቃየት ባለፈ ደግሞ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለሱዳን መንግሥት ሸጠዋል። ሃገሪቱን ካለባህር በር አስቀርተዋል። የሃገር ሃብትና ታሪካዊ ቅርሶችን አውደመዋል፣ ሸጠዋል። እንደው በደፈናው በአገራችን ታሪክ ውስጥ በሕዝባችን ከቶም እንደ አሁኑ ሳንጃ በአንገቱ ላይ ተወድሮ ጦር ተሰብቆበት የሚገኝበት የፋሽስታዊ አገዛዝ ጊዜ የለም። ፋሽዝም ዛሬ በወያኔ/ህወሃት ጊዜ ነግሷል ሥርም ሰዷል። በሥልጣን ላይ ለመቆት፣ ሃብቷን በዝብዞና ሽጦ ለማፈራረስ በታቀደው የአገዛዝ ሽብር ተግባር፣ ፋሽዝም በዴሞክራሲ ታዛ ሥር ወያኔ በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ እየፈጸመው ያለ ለመሆኑ ሁሉም አገር ወዳድ ዜጋ ይረዳውል ብየ አምናለሁ። ፋሽስት ሕዝብ ይጨፈጭፋል፣ ያስፈራራል፤ ፋሽስት የማደናገሪያ ፕሮፓጋንዳን ያስፋፋል፣ ውሽት ይዋሻል፤ ፋሽስት ትምክህተኛና ጦርነት ፈላጊ ነው። ፋሽስት ራስ ወዳዶችን፣ ሆዳሞችን፣ ግብዞችን፣ ዱርየዎችን መሳሪያ ያደርጋል፤ ፋሽስት ድርጅቶችን ያስፋፋል፣ ተለጣፊ ያበዛል ወዘተ። እንግዲህ የፋሽስት አገዛዝ ባህርያትን ማንሳቴ ወያኔን በነዚህ ባህሪያትም መዝነን ፍረጃችንን ለማጠናከር ይረዳን ዘንድ በማሰብ ነውና መዝኖ ፍርድ መስጠቱን ለእናንተው ትቻለሁ። ወደ ሥልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ እጁን በንፁኃን ዜጎች ደም የታጠበው የወያኔ አገዛዝ ሕጋዊ የአምልኮት ነፃነታቸው ያለምንም የአገዛዙ ጣልቃገብነት እንዲከበር የጠየቁ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያንን በጅምላ በሃይማኖት አክራሪነትና አሸባሪነት ወንጅሎ የግድያ ወንጀል ፈጽሟል። በክርስቲያን እምነት ተከታይ ወገኖቻችንም ተመሳሳይ ግፍ ሲፈፀምባቸው ተመልክተናል። ገዳማትን ማፍረስና መነኮሳትን ማሳደድና መግደል የወያኔ መለዮው ሆኗል። ወያኔ ንፁኃን ዜጎችን ከማሰቃየት፣ ከማሰርና ከመግደል የታቀበበት ወቅት ከቶውንም የለም፤ አልታየምም። ድብደባው፣ ማሰሩና ግድያው እየተፈጸመ ያለው በሁሉም የሃገሪቷ ክፍሎች በሚኖሩ ንፁሃን ዜጐች ሲሆን በግፍና በገፍ ወደ እሥር ቤት የማጎር እርምጃዎች ያልርኅራሄ ተፈጽመዋል፤ እየተፈጸሙም ነው። ውድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ በኢትዮጵያዊ ትዕግሥትና አርቆ አስተዋይነት በፋሽስቱ ወያኔ ወገን ሲደበደብ፣ ሲባረር፣ ሲገደል፣ ሃብት ንብረቱ ሲዘረፍ፣ ዳር ድንበሩ ሲወሰድ፣ በቋንቋ ልዩነት ሲመደብ፣ የተማረ ወገን ሲገደልና ሲሰደድ፣ አገር ለውጭ ባለሃብት ስትሽጥ፣ ይህ ሁሉ ሲሆን እስከ አሁን በደልን ተሸክመህ በዝምታ ታግሰሃል። ዛሬ በፋሽስቱ ወያኔ ኢትዮጵያ ተደፍራለች፣ ሕዝቧ ተዋርዷል፣ የታሪክ ክብሯ ተንቋል። ለብዙ ሺህ አመታት የኛ ቀደምት ትውልዶች አጥንትና ደማቸውን በማፍስስ ታፍራና ተፈርታ የኖረች አገር ዛሬ በዚህ ወቅት የትውልድ መካን ሆና ጥቃቱና ጥፋቱ እጅግ ተነባብሯል። ኢትዮጵያዊ ወገኔ ሆይ! ፍርሃት ከአደጋ የመከላከያ ባህሪ እንጂ እየሸሹ ለመጥፋትና ለመሞት አይደለም። ይህ ጭቆናና ጥቃት ሊያበሳጭ፣ ሊያናድድህና ሊያስቆጣህ ይገባል። ሰው ነህና ለመብትና ለነፃነት መታግልና ለመጭውም ትውልድ ለልጆችህ አገር ማቆየት ይኖርብሃል። የኛ ቀደምት አባቶችና እናቶች እኛ ሞተን አገር ትኑር ብለው ለኢትዮጵያ ታላቅ መስዋዕትነት ከፍለዋል። ታሪክ ምስክርነትዋን መዝግባለች። ዛሬም የኢትዮጵያዊያን ወኔና ጀብዱ፣ አትንኩኝ ባይነት ይደገም። ወያኔ ኢትዮጵያዊነት የሌለው አረመኔ ፋሽስት ነውና፤ መወገድ አለበት። ስለዚህ ለትዕግሥት ገደብ እንስጥ፣ አንዋረድ ፣ ትውልድ እንጠብቅ፣ አገርና ሕዝብ እናድን። ድል ለጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ!

Thursday, 27 February 2014

የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረዕት ነጻ ፕሬሶችን አስጠነቀቀ !

ኢዜአ የነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች ማህበር ሊቀመንበርን ጠቅሶ ባስተላለፈው ዜና የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ዳግም በነጻ ፕሬሶች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጦል። እንደ ዜናው ዘገባ በአሸባሪነት ተፈርጀው በህግ ቁጥጥር ስራ በሚገኙ ዙሪያ አንዳንድ ጋዜጦች የተዛባ ውዥንበር በህዝብ መሃል በመንዛት ድብቅ አጀንዳቸውን ያራምዳሉ ብሏል። የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ሰሞነኛ ፉከራ መጪውን ሃገራዊ ምርጫ ተከትሎ የተቃዋሚ ሃይሎች በህዝብ ዘንድ ድጋፍ እያገኙ እና እያንሰራሩ መመጣታቸው እንዳስደነገጠው የሚናገሩ ወገኖች ከብሄራዊ ምርጫ በፊት የህዝብ ልሳን የሆኑትን የነጻ ፕሬስ ጋዜጦችን በማጥፋት የህዝብን ድምጽ፡ለማፈን እያደረገ ያለው ዘመቻ አንዱ አካል መሆኑንን ይስማሙበታል ። በ1997 እ.ኢ.አ በኢትዮጵያ የተካሄደውን ብሄራዊ ምርጫ ተከትሎ በተነሳው ውዝገብ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መግስት ኮሮጆ ገልብጦ ጠንካራ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን በማጥፋት ብቻውን እሩጦ በዴሞክራሲ ሽፋን አለም አቀፉን ማህበረሰብ ሲያደናገር የነበር ስረአት መሆኑንን የሚገልጹ የፖለቲካ ተንታኞች ሀግሪቱን ያለተቀናቃኝ ለ20 አመታት ረግጦ መግዛቱን በመጥቀስ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለሰ ዜናዊ ሞት በሃላ በአባልቱ መሃከል የነበሩ አለመግባባቶች ፈር እይለቀቁ መምጣታቸውን ተከትሎ ድርጀቱ ከእንግዲህ እንደ መንግስት መቀጠል እንደማይችል ይናገራሉ። ይህ በዚህ እንዳለ የነጻውን ፕሬስ አባላት በመግደል እና በማፈን የሚታወቀው ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መግስት ኢትዮጵያ ውስጥ አቋጥቁጦ የነበርን ዲሞክራሲያዊ ስረአት በመቀልበስ በአለም አቀፍ ደረጃ ከለየላቸው አንባ ገነን መንግስታቶች ግንባር ቀደም መሆኑ ይታወቃል። አቶ ታምራት ይህደጎ ከቨርጅኒያ

Monday, 24 February 2014

በብአዴን አመራሮች እና በካድሬዎቹ መካከል ከፍተኛ አለመግባባት ተፈጠረ

“ዩኒፎርሙን አውልቆ ካልሸጠው አንድ ጉራጌ ጄነራል አድርገን ሾመናል።” ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ከሳምንታት በፊት ራሱን የአማራ ክልል ብሎ በሚጠራው የክልል አምባገነን ጁንታ አስተዳዳሪ ነኝ የሚለው የብኣዴን የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ አለምነህ መኮንን በድርጅቱ የውይይት መድረክ ላይ የአማራውን ህዝብ ለሃጫም እና ልጋጋም እንዲሁም መርዝ ብሎ መሳደቡን ተከትሎ በከፍተኛ ደረጃ የውጪ እና የውስጥ ተቃውሞ በየአቅጣጫው እየተነሱ መሆኑን መረጃዎች ጠቁመዋል:: ሰሞኑን በብአዴን አመራሮች እና በካድሬዎቻቸው መካከል ግለሰቡን የተመለከተ አለመግባባት መከሰቱን እና ጥያቄዎች ከአባላቱ በስፋት እየመጡ መሆናቸውን የውስጥ ምንጮች ጠቅሰው የአዲስ አበባ እና አከባቢው የድርጅቱ ካድሬዎች ግለሰቡ እና ሁኔታው እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል እስከማለት ደርሰዋል:: ይህንን ለመናገር የፈለገው ለምንድን ነው ተልእኮውስ ምንድነው? በሌላው ብሄር ላይ ይህ ነገር ቢነገር የድርጅታችን እርምጃ ምን ይሆን ነበር? ግለሰቡ በህግ ሊጠየቅ ይገባል::የሚሉ እና ተመሳሳይ ጥያቄዎች የተጠየቁ ቢሆንም አመራሮቹ እስካሁን መልስ ከመስጠት ይልቅ ኢዲሞክራሲይዊ በሆነ መንገድ አለመግባባቶችን ከመፍታት ይልቅ በማስፋት መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ጸረ-… እያሉ ጠያቄዎችን በመወንጀል እና ዋናውን ክትትላቸው ያደረጉት ድምጹን ቀድቶ ማን አውጣው የሚለውን የማይመለስ ጥያቄ ይዘው አደና ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል:: ከድርጅቱ አንዳንድ ካድሬዎች እንደሚሰማው የድምጹን ቅጂ ያወጡት የሕወሓት ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ የሚሉ እና ሕወሓትን በጥርጣሬ የሚይስቡ እንዲሁም ግንቦት ሰባት ናችሁ ብለው እርምጃ ሊወስዱባቸው የሚፈልጉትን የብኣዴን ካድሬዎች ለመዋጥ የተደረገ ሴራ ነው::በድርጅታችን ውስጥ የማይበጁትን አንጠባጥቦ የራሱን ለመሰግሰግ ያሰረው ሕወሓት መንገድ አገኘ ቢሉም በለላ ወገን ደግሞ በድርጅቱ የተማረሩ እና የለውጥ ፍላጎት ያላቸው የብአደን አመራሮች አሹልከው ያወጡት እንደሆነ ይነገራል።ካድሬዎቹ ክፉና ደጉን እንድንለይ ላደረገን ኢሳት ቴሌቭዥን ምስጋና እናቀርባለን ሲሉ ተደምጠዋል:: በአመራሮቹ እና በካድሬዎቹ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በዚሁ ከቀጠለ አቶ አለምነህ የድርጅት ስራ ብቻ እንዲሰሩ ወደ አዲስ አበባ ለማምጣት እና በክልሉ ላይ የተሰጣቸውን ስልጣን ለስም ብቻ እንዲቀመጥ የሚደረግ እንደሚሆን እና ቀስ በቀስ ከድርጅቱ ገፍቶ በማስወጣት አምባሳደር አድርጎ መሾም የሚሉ አስተያየቶች ከድርጅቱ አከባቢ ተደምጠዋል:: ============================================= ይህ በእንዲህ እንዳለ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የብሄር ተዋፅኦን እና የመኮንኖች ቅነሳን በተመለከተ ከፍተኛ የሆነ ክርክር መነሳቱን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ተናግረዋል:: እንደምንጮቹ ከሆነ በዚህ ሰሞን በተካሄዱ ተከታታይ ምስጢራዊ ስብሰባዎች ላይ የመከላከያ ሰራዊቱ በአንድ ብሄር በተሰበሰቡ ጄኔራሎች የተሞላ ነው: የመኮንኖች ቅነሳ ለምን አስፈለገ? ለምንስ አማራው እና ኦሮሞው ላይ አተኮረ ?ሰራዊቱ እና ቤተሰቡ በኑሮ ውድነት እየዋተተ ነው ከፍተኛ መኮንኖች በሙስና ተዘፍቀዋል ህገመንግስቱ አልተተገበረም የሚሉ የህዝብ አቤቱታዎች ተበራክተዋል … የሚሉ በሰራዊቱ ውስጥ ተጠንቷል ተብለው በቀረቡ ጥያቄዎች ዙሪያ ክርክር እና ውይይት የተደረጉ ቢሆንም በሕወሓት ጄኔራሎች ማስፈራሪያ እና ዛቻ እንዲሁም ሞራልም ያልጠበቁ ስድቦች ካለውጤት እንደተበተኑ ምንጭኦቹ ገልጸዋል:: የአንድ ብሄር የበላይነት የምትሉት ለሕወሓት ያላችሁን ጥላቻ ለመግለጽ ነው ያሉት ጄኔራል ሳሞራ ጥያቄውን የፓርቲ ስብሰባ እስኪመስል ድረስ ጮኽውበታል::በትግል የከፈልነው መስዋትነት ውጤት እንጂ ከጎዳና ላይ መጥተን ማእረግ አልተሰጠንም::ከየብሄሩ አስፈላጊ ያልነውን ሊሰራልን የሚችለውን ጄኔራል እያደረግን እየሾምን ነው:: ዩኒፎርሙን አውልቆ ካልሸጠው አንድ ጉራጌ ጄነራል አድርገን ሾመናል። ሲሉ በመከላለያ ኢንዱስትሪ ምክትል አዛዥ ብርጋዴል ጄኔራል ጠና ላይ ተሳልቀውባቸዋል:: የሰራዊቱ መኮንኖችን ቅነሳ በተመለከተ የማይታጠፍ እቅድ ስለሆነ ተግብርዊ ይሆናል ያሉት ሳሞራ ብሄር ለይተን ያደረግነው ሳይሆን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እና የመከላከያ ሰራዊቱ ተጠንቶ የሚወሰድ ኢርምጃ ነው ብለዋል::ለሰራዊቱ የምናደርገው ድጎማ የለም::ያልተመቸው ካለ ሰራዊቱን መሰናበት ይሽላል ሲሉ በቁጣ የመለሱ ሲሆን ሙስና የሚባለው ማስረጃ ያለው ሄዶ ሊከስ ይሽላል ከዚህ ውጭእ ስም ማጥፋት ነው ሲሉ ተደምጠዋል :;ህገመንግስቱን እና መንግስታዊ ስርኣትን በተመለከተ መልካም አስተዳደር እና ልማት ስለሰፈነ ቢዚህ ልይ ምተኮር ስፈላጊ አይደለም ብለዋል:: ከሰራዊቱ አባልት መሃል ገብተን ያስጠናነው ጥያቄ ነው እየተወይየንበት ያሉትን ሰነድ በተመለከተ ማንም የጦር መኮንን አስተያየት ያልሰጠበት እና ያልጠየቀ ሲሆን ሁሉም በዝምታ በማዳመጥ ሳይወያይ መስማማት አለመስማማቱን ሳይገልጽ የተነገረውን እንደ መመሪያ ተቀብሎት መውጣቱን ምንጮቹ ተናግረዋል::

Thursday, 20 February 2014

የኢትዮጵያ መንግሥት፡- በኮምፕዩተር ስለላ ተከሰሰ፤ እንዲህ ዓይነቱን ውንጀላ አስተባበለ

የኢትዮጵያ መንግሥት የተራቀቁ የስለላ ሶፍትዌሮችን እየለቀቀባቸው የኮምፕዩተሮቻቸውን ይዘት እንደሚሠርቅ እና የግል ግንኙነቶቻቸውንም እንደሚከታተል በውጭ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስሞታዎችን እያሰሙ መሆናቸው እየተነገረ ነው፡፡ አንድ የዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ነዋሪ በዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል ፍርድ ቤት በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ክሥ መመሥረታቸው፤ ሌላ አንድ ሰው ደግሞ ለእንግሊዝ ፖሊስ አቤቱታ ማስገባታቸው ታውቋል፡፡ ከትናንት በስተያ ማክሰኞ ዋሽንግተን ዲ.ሲ. ውስጥ በሚገኝ አንድ ፌደራል ችሎት የተከፈተ ዶሴ ከዚህ የስለላ አድራጎት ጀርባ ያለችው ኢትዮጵያ እንደሆነች ጠቁሞ ከሣሹ የአሥር ሺህ ዶላር የጉዳት ካሣ እንዲከፈለው ጠይቋል፡፡
እንግሊዝ ዋና ከተማ ለንደን ላይ በቀረበ ሌላ ክሥ እዚያ በስደት የሚኖሩትና የግንቦት ሰባት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል መሆናቸውን የተናገሩት ታደሰ ኬርስሞ ሰኞ ዕለት ባስገቡት ማመልከቻ ፊንፊሸር የሚባለውን ሶፍትዌር የሚቀምረው ዋና ተቀማጭነቱ እንግሊዝ ውስጥ የሆነ ጋማ ግሩፕ እንዲመረመርላቸው ጠይቀዋል፡፡ ኢትዮጵያን ከእንዲህ ዓይነቱ የኢንተርኔት ስለላ ጋር የሚያያይዙ ማስረጃዎች የተሰባሰቡትና የተደራጁት ካናዳ ውስጥ በሚገኝ ሲቲዘን ላብ በሚባል ድርጅት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ “የኢትዮጵያ መንግሥት የኮምፕዩተር ጠለፋ ወይም የስለላ ተግባር አያካሂድም” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ ቃል አቀባይ አምባሣደር ዲና ሙፍቲ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡ ተጨማሪና ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡ http://amharic.voanews.com/audio/Audio/378801.html

ESAT Focus on Ethiopia: Surveillance/Cyber Spying on US Citizens and residents by foreign governments

http://ethsat.com/video/esat-focus-on-ethiopia-surveillancecyber-spying-on-us-citizens-and-residents-by-foreign-governments/

Wednesday, 19 February 2014

በሃገሪቱ የተነሰራፋው ዘረኝነት፣ የደህንነት ሥጋትና አድልዎ አውሮፕላን እንዲጠለፍ አድርጓል

ከምኒልክ ሳልሳዊ በሃገሪቱ የተንሰራፋውን የደህንነት ስጋት በመልካም አስተዳደር እና በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ አድልዎ ተከትሎ የተደረገው የአይሮፕላን ጠለፋ ህዝቦች በገዛ አገራቸው በደህንነት ላይ ምን ያህል ስጋት እንዳጠላበት እና በመኖር ህልውናቸው ላይ ኢትዮጵያውያን የስርአቱ ፖሊሲዎች እያሸማቀቋቸው እንደሚገኙ አለም ካለፈው ጊዘ በተሻለ እውነታውን ፍንትው አድርጎ እየመሰከረ ነው። የሕወሓት መራሹ ጁንታ ወደ ስልጣን በጠበንጃ ሃይል ከመጣ ጀምሮ በአለም አቀፍ ደረጃ የተደነገጉ የሰብኣዊ መብት ህጎችን ካለምንም ማርቅርቅ እና ድካም ከሌሎች በመገልበጥ በወረቀት ላይ ከማስፈሩም በተጨማሪ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በአለም ላይ የሰው አገር ህግን እና አለማቀፍ ድንጋጌን ከሃገራችን ሁኔታ ጋር ሳይገናዘቡ በስፋት በደመነፍስ ለፍጆታ የተጻፈበት ሃገር ኢትዮጵያ ብቻ ሲሆን በየትኛውም አለም ሃገራት ያልተከሰተ የአለም አቀፍ ህጎችን ግልባጭ በከፊል በህገመንግስት እንዲሁም የገዢ ፓርቲን የፖለቲካ ፕሮግራም በከፊል ደባልቆ በጋር እንደ አውራ ህግ የወጣባት ሃገር ብትኖር ኢትዮጵያ ብቻ ናት::ኢትዮጵያ በታሪኳ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የመብቶች ሕጋዊነት በተጨበጨበለት ሁኔታ እና ይህ በማይባል ደረጃ የተደነገጉባት አገር ነች፡፡ እንግዲህ ይህ ሆኖ እያለ ነው በአገሪቱ የመብቶች ጥሰት ጉዳይ ከአገሪቱ ብሔራዊ አነታራኪ ፖለቲካዊ አጀንዳነት አልፎ ዓለም አቀፍ አጀንዳ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ጥላቻ በፈጠረው ፍርሃት ብቻ የሃገሪቱን ህጎች ዜጎች ለመጥለፍ እያዋሉት ነው:: የቀድሞ መንግስትን ሽንፈት ተከትሎ በኢትዮጵያ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች የፍፃሜ ምዕራፍ ይሆናል ተብሎ ተስፋ ተደርጎ ነበር፡፡ ነገር ግን ጭራሽ ብሶበት ቁጭ አለ፡፡ የሕወሓት ወንበሩን መቆጣጠር ተንተርሶ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በተለይም ሒዩማን ራይት ዎችና አምነስቲ ኢንተርናሽናል የወያኔን ጁንታ በሰብዓዊ መብት ጥሰት በማብጠልጠል ነበር የተቀበሉት፡፡ ባለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት የሰብኣዊ መብት ጥያቄዎች አቤቱታ ማሰማታቸውን አላቆሙም፡፡ ጋዜጠኞችን የሃሳብ ነጻነት ከሚገድብ ጥቃት በመከላከል ላይ የተሰማሩ የመብት አስከባሪ ድርጅቶችም ወያኔ በሚፈጥረው ከባድ የሰብኣዊ መብት ጥሰት በየጊዜው መክሰስ ሥራቸው ሆኗል::የአሜሪካው ስቴት ዲፓርትመንት በየጊዜው በሚያወጣው ዓመታዊ መግለጫው ወያኔን በሰብዓዊ መብት ጥሰትና የፖለቲካ መብቶችን ማፈን ይከሰዋል፡፡ ባሁን ወቅትየእነኚህን አካላት መግለጫዎች የታወቁ ዓለም አቀፍ መገናኛ ድርጅቶች በመቀባበል ኢትዮጵያ የዜጎቿን መብቶች በመጣስና በማፈን ወደር የሌላት አገር እንደሆነች ዓለም እንዲረዳው እያደረጉ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ በአስከፊ ድርቅና ረሃብ ለመታወቅ እንደበቃችው ሁሉ ወያኔ የዜጎችን መብቶች በመጣስና በማፈን እንዲሁም በሰብዓዊነት ላይ በሚፈጽመው ወንጀል በዓለም ላይ ታዋቂነትን እያተረፈ ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም;ወያኔ የፖለቲካ ተቀናቃኞችን መብቶች ለመጣስ ስለሚጠቀምባቸው ዘደዎች የሚቀርቡ ማስረጃዎች እና ማብራሪዎች እጅግ ዘግናኝ ናቸው፡፡የወያኔ መሪዎች የፖለቲካ ተቀናቃኖችን ለማዳከም ሲሉ ንፁኃንን ወንጀለኛ የሚያደርግ ዘዴዎችን ሥራ ላይ እንደሚያውሉ በተለያዩ ይፋዊ ሪፖርቶች ላይ ሁሉ ከነማስረጃው እየተነገረ ይገኛል:: የህ የሰብኣዊ መብጥ ጥሰት እየተባባሰ የሚሄድበት ምክንያት ወይኔ በአብዛኛው ካድሬዎች ዘንድ በስፋት ሰርጾ እንዲገባ ያደረገው የተቃዋሚዎች ጥላቻ እና እንዲሁም የተቃዋሚው ቡድን የትግል አቅጣጫው በተመሳሳይ መልኩ በጥላቻ ላይ የተመረኮዘ መሆኑ ነው::ተቃዋሚዎች የታጠቁ ሃይላት ባለመሆናቸው የመርሃቸው እንቅስቃሴ የተገደበ እና ለፖለቲካ እና ለሚዲያ ፍጆታ የዋለ ተዳፍኖ የሚገኝ ሲሆን የወያኔው ግን በታጠቁ የጸጥታ ሃይሎች እና በፖለቲካ ማጭበርበሮች ላይ ስለተመረኮዘ ካድሬዎቹ በተሰጣቸው የጥላቻ ተግዳሮት እና ወያኔያዊ ስልቶች የፈጠሩትን ጥቅማጥቅሞች ጠብቀው ለማቆየት ሲባል ጥላቻ በፈጠረው ፍርሃት ብቻ የሃገሪቱን ህጎች ዜጎች ለመጥለፍ እያዋሉት ነው:: ይህ ፍርሃት እና ጥላቻ በወያኔ ከትልቅ እስከ ትንሽ ካድሬዎች አናት ውስጥ ስር ለስር በመስደድ የፈጠረው ነገር ቢኖር ማንኛውም ዜጋ ተቃውሞ ካሰማ በወንጀለኛነት በመፈረጅ በማሳደድ በማጥፋት እረፍት ለማግኘት እና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲራወጡ የህዝብን የበላይነት አፈር ከተውታል::ማእከላዊ የወያኔ ጁንታ በዲሞክራሲ ባለመወቀጣቸው የህጎችን የበላይነት ማረጋገጥ ካለመቻሉም በተጨማሪ በህዝብ እና በዲሞክራሲ ላይ በደሎችን የሚያደርሱ ባለስልጣናት የሚጠየቁት በሃገሪቱ የበላይ ህጎች ሳይሆን በወያኔያዊ የፓርቲ መመሪያዎች በመሆኑ በጥቅም መተሳሰር በፈጠርው ዝግ መንገድ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች እየተብራከቱም ከመሆኑ አልፎ የእለት ተእለት ተግባራት አካል ሆነዋል:: የአይሮፕላን ጠለፋዉም ከላይ ከገለጽኩት ጉዳዮች ጋር ቁርኝት ያለውና በሃገሪቱ እየተተገበረ ያለውን የቡድን አምባገነንነት በማጋለጥ ረገድ ትልቁን ሚና ተጫውቷል። ምንጭ ዘ-ሐበሻ

Monday, 17 February 2014

አቶ አለማየሁ አቶምሳ በገዛ ፍቃዳቸው ከሥልጣናቸው ለቀቁ (በጽዮን ግርማ)

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳ በገዛ ፈቃዳቸው ከኦሕዴድ ሊቀመንበርነታቸው ለቀቁ፡፡በዛሬው ዕለት በተካሄደው የኦሮሞ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ መልቀቂያቸውን ያስገቡት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቶ ከሥልጣን መነሳታቸው ታውቋል፡፡አቶ አለማየሁ ቀድሞውንም ሥልጣን ሲይዙ በከባድ ሕመም የሚሰቃዩ መኾናቸው እየታወቀ ሲኾን ምንጮች እንዳረጋገጡት አቶ አለማየሁ ወደ መንፈቅ ለሚጠጋ ጊዜ በውጭ አገር በሕክምና ላይ ነበሩ፡፡ በተደጋጋሚ ኮማ ውስጥ ይገቡም ነበር ተብሏል፡፡ በዚህ ጊዜ የፕሬዝዳንትነቱን ቦታ ተክተው ይሠሩ የነበሩት አቶ አብዱላዚዝ አህመድ ሲኾኑ የኦሕዴድ ሊቀመንበርነታቸውን ሥልጣን ደግሞ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩና የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙክታር ከድር እንደነበሩ ምንጮች ጨምረው አረጋግጠዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ጋር ከመደራደር ይልቅ ሌሎች አማራጮችን መውሰድ እንፈልጋለን›› የግብፅ የውኃ ሚኒስትር

-ግብፅ ከኢትዮጵያ ጀርባ ቱርክ አለች ማለት ጀመረች ባለፈው ሰኞ በአዲስ አበባ ለውይይት መጥተው ስብሰባው ተቋርጦ ወደ አገራቸው የተመለሱት የግብፅ የውኃና መስኖ ሚኒስትር መሐመድ አብዱል ሙታሊብ ካይሮ ሲደርሱ በሰጡት መግለጫ፣ ከኢትዮጵያ ጋር መደራደር እንደበቃቸው ከገለጹ በኋላ ‹‹ሌሎች አማራጮችን መውሰድ እንፈልጋለን፤›› ብለዋል፡፡ ሚኒስትሩ በደፈናው ሌሎች አማራጮችን ከማለት ውጪ ማብራሪያ አልሰጡም፡፡ ይሁን እንጂ ንግግራቸውን በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ያነበቡ ኢትዮጵያውያን ንግግሩን ፀብ አጫሪነት ነው ብለው፣ ‹‹ኢትዮጵያውያን ግድቡን እንገነባለን፣ ግብፆች ያላቸው ሌላ አማራጭ ምን እንደሆነ እናያለን፤›› በማለት በቁጣ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ የመንግሥት ባለሥልጣናት ግብፅን የመጉዳት ፍላጎት የለንም እያሉ ነው፡፡ ይህንን ግን በወረቀት አስቀምጡልን ብለን ስንጠይቅ አይቀበሉም፤›› ያሉት ሚኒስትሩ፣ በህዳሴው ግድብ ምክንያት በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለማጥበብ በግብፅ በኩል የሚደረጉ ጥረቶችን ኢትዮጵያ እያደናቀፈች ነው በማለት በአገራቸው ቴሌቪዥን ወቀሳ አቅርበዋል፡፡ ከዚህ በኋላ ውጤት ለሌለው ድርድር ጊዜ ማጥፋት ተገቢ እንዳልሆነ የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ ‹‹ሌሎች አማራጮች አሉ፣ እነርሱን ወደ መተግበር እንሸጋገራለን፤›› በማለት የአማራጮቹን ምንነት ሳያብራሩ በደፈናው አልፈዋል፡፡ በቅርቡ ኢትዮጵያን የጎበኙት የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን በተመለከተም፣ የግብፅ የውኃና መስኖ ሚኒስትር በዚሁ መግለጫቸው ላይ አስተያየት ሰጥተውበታል፡፡
ሚኒስትሩ አብዱል ሙታሊብ፣ ‹‹ግብፅን የማይወዱ ወገኖች ከኢትዮጵያ ግድብ ጀርባ ይገኛሉ፤›› በማለት የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአዲስ አበባ ጉብኝትን ተችተዋል፡፡ የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአዲስ አበባ በተገኙበት ወቅት ኢትዮጵያ ለምትገነባው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ባለሙያዎችን ለመላክ ፈቃደኛ ሆነዋል ሲሉም ወቀሳ አቅርበዋል፡፡ ‹‹ቱርክ፣ አታቱርክ የተባለውን ግድቧን ስትነገባ ሶሪያና ኢራቅ ተቃውሞ ነበራቸው፡፡ ቱርክ የሶሪያና የኢራቅ ተቃውሞን ቸል በማለት ሁለቱን አገሮች ለውኃ ጥም ዳርጋና ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ጥሳ ግንባታውን አከናውናለች፡፡ አፅንኦት ሰጥቼ ማለት የምፈልገው ኢትዮጵያ ቱርክ አይደለችም፡፡ ግብፅም እንደዚሁ ሶሪያ ወይም ኢራቅ አይደለችም፤›› በማለት ዛቻ መሰል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ እስካለፈው ዓርብ ምሽት ድረስ የቱርክ መንግሥት ለሚኒስትሩ አስተያየት ምላሽ አልሰጠም ነበር፡፡ የግብፅ ሚኒስትር በይፋ በአገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ የተናገሩትን ተርጉመው የዘገቡ የተለያዩ ድረ ገጾችን የተመለከቱ በርካታ ኢትዮጵያውያን፣ ‹‹ሚስተር ሙታሊብ ኢትዮጵያ አሁንም ግብፅን የመጉዳት ፍላጐት የላትም፡፡ የእርስዎ ንግግር ግን የተለመደው የግብፅ ባለሥልጣናት ድንፋታ ነው፡፡ ሌሎች አማራጮች ያሉትን እስኪ እንያቸው፡፡ ከንግግርና መግባባት የተሻለ በዚህ ጉዳይ ላይ አማራጭ የለም፤›› የሚሉ አስተያየቶችን አንፀባርቀዋል፡፡ እኚሁ የግብፅ ሚኒስትር ባለፈው ሰኞ በኢትዮጵያ ተገኝተው ከኢትዮጵያ አቻቸው አቶ አለማየሁ ተገኑ ጋር ተገናኝተው የነበረ መሆኑን፣ ሚኒስትሩ ግን የህዳሴው ግድብ ግንባታ ቆሞ እንወያይ በማለታቸው ስብሰባው መቋረጡን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ከዚህ ስብሰባ ማግሥት ጋዜጠኞችን በመሰብሰብ በሁለቱ አገሮች መካከል ስላለው ወቅታዊ ጉዳይ በኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ማብራርያ ተሰጥቶ ነበር፡፡ በዚህ ስብሰባ ላይ ከጋዜጠኞች ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል፣ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ጦርነት በዚህ ዘመን ሊሆን አይችልም በማለት ግብፅ በአማራጭነት እንደማትመርጠው እየተናገሩ ቢገኝም፣ ጦርነት ሊፈጠር ቢችልስ ሲሉ የኢትዮጵያን አቋም ጠይቀዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጡት የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን፣ ‹‹አለመግባባቱን በጦርነት ለመፍታት ኢትዮጵያን መውረርና መቆጣጠር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ይህ ግን መሆን አይችልም፤›› በማለት ምላሽ ሰጥተው፣ ‹‹ማንኛውም አገር ጐረቤቱን ነቅነቅ ለማድረግ የሚፈልገው የጐረቤቱ እግር ወልከፍከፍ ያለ እንደሆነ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ደረጃ ግን ይህንን ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ የለም፤›› ሲሉ አረጋግጠዋል፡፡ የኢትዮጵያን ደኅንነት የበለጠ ለማረጋገጥ ቀዳዳዎችን መድፈን እንደሚገባ ያከሉት ሚኒስትሩ፣ ‹‹የጐረቤት አገሮችን ሰላምና ደኅንነት ማረጋገጥ፣ ከጐረቤቶቻችን ጋር ጥብቅ ቁርኝት መፍጠር፣ ለውጭ ኃይሎች ያደሩ የራሳችንን ሰዎች ነቅሶ ማውጣት፤›› ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ በመቀጠልም፣ ‹‹ጦርነት መክፈት ይቻላል ኢትዮጵያን ማሸነፍ ግን የማይቻል ነው፤›› ብለዋል፡፡ ግብፆች ኢትዮጵያን ብድር የማስከልከል እንቅስቃሴያቸውን አሁንም አጠናክረው መቀጠላቸውን የተናገሩት አቶ አለማየሁ ተገኑ በበኩላቸው፣ የህዳሴው ግድብ ግን የውጭ ኃይሎችን ዕርዳታ አይፈልግም ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ አውሮፕላን በገዛ ረዳቱ ጠለፋ ተደረገበት… ለምን… ?

የኢትዮጵያ አውሮፕላን በገዛ ረዳቱ ጠለፋ ተደረገበት… ለምን… ? (ከአቤ ቶክቻው) ዛሬ ወደ ሮም ሲበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን መጠለፉን ሰማን። ማነው እንዲህ የደፈረን ብለን አቶ ሬደዋንን ብንሰማቸው ጊዜ “አውሮፕላኑ ሱዳን ላይ አርፎ ነበር ምናልባት ጠላፊዎቹ ያኔ ይሆናል የገቡት” ብለው ተናገሩ። ኋላ ላይ ሲጣራ ግን ጠላፊው የአውሮፕላን አብራሪው ረዳት መሆኑ ተሰማ፤ ረዳቱ ጠለፋውን የፈፀመው ዋናው አብራሪ በአውሮፕላኑ መፀዳጄ ቤት ጎራ ባለበት ሰዓት ነው። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ… መላ ምት አንድ፤ ዋና አውሮፕላን አብራሪው ፓይለት በሰላም እየበረረ ሳለ መንገድ ላይ የመፀዳዳት አምሮቱ መጣበት እና ረዳቱን፤ “በሰማይ የሰጠውህን በሰማይ እቀበልሃለሁ” በሚል፤ አደራ በሎት መፀዳጃ ቤት ወገቡን ሊፈትሽ ገባ። ይሄን ጊዜ ረዳቱ ሆዬ “ይሄ ሰውዬ ከመፀዳጃ ቤቱ ሲመለስ ሮም አድርሶ ከዛምም ወደ ፍትህ አልባዋ ሀገሬ ከሚመልሰኝ አሁን መሪውን እንደጨበጠኩ የራሴን እድል በራሴ ለምን አልወስንም” አለ እና … መሪውን አለቅም አለ። ሰዊስ ጄኔቭ ላይም ጥገኝነት ትሰጡኝ እንደሆን ስጡኝ ብሎ አሳረፈው። መላ ምት ሁለት፤ ዋና አብራሪው እና ረዳቱ ቀድሞውኑ ተነጋግረው ነበረም ይሆናል። (ምንም እንኳ ይቺ ዋና አብራሪውን የምታስፎግር መላ ምት ብትሆንም ከጠረጠርን ጠረጠርን ነውና እንናገራለን) ገና ከኢትዮጵያ ሰማይ ላይም ሳይወጡ፤ ረዳቱ እና ዋናው ኢትዮጵያ መሬት ላይ እያሉ ምሬቶቻችውን ሲያወጉ ነበር አሉ። በተለይ ረዳቱ የደረሰበትን አስተዳደራዊ በደል ሁሉ ዘረዝሮ ለዋናው አብራሪ በነገረው ጊዜ ዋና አብራሪውም በረዳቱ የደረሱ በደሎች በሙሉ በሱም እንደ ደረሱ ነግሮት ስቀሰቅ ብለው ተላቀሱ። ከዛም ረዳቱ አለው፤ “ላንተ እና ለሀገሬ እግዜር መላ እንዲያበጅላችሁ እፀልያለሁ ለእኔ ግን አንድ መላ አብጅቻለሁ” አለው። ቀጠለናም አንተ የምትተባበረኝ አንድ ነገር ብቻ ነው… ሲል ነገረው። “አንተ የሁነልህ እንጂ ችግር የለም ምን ለተባበርህ…” አለው ዋናው አብራሪ… በነገው በረራ የሆነው ቦታ ላይ መፀዳጃ ቤት ገብተህ ትንሽ ቆይታ አድርግ…! አለው አደረገም የሆነው ሁሉም ሆነ። ከዚህ ምን እንገነዘባለን፤ አንድ ወዳጃችን በፌስ ቡክ ገፁ “ነገ ከነገ ወዲያ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ አውሮፕላን ጠለፈው ጥገኝነት ጠየቁ የሚል ዜና መስማታችን አይቀርም” ብሎ እንደጠረጠረው በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የደላው ማንም እንደሌለ በቅጡ እንረዳለን። ከአውሮፕላን ረዳት እስከ ታክሲ ረዳት እና ቤተሰብ ረዳት በሙሉ በፍትህ እጦት “የተማረረበት ሁኔታ ነው ያለው” በመጨረሻም፤ ያማንማረርባት እና የማንባረርባት ኢትዮጰያ ትመጣ ዘንድ እንፀልያለን።

Sunday, 16 February 2014

ወያኔን ካላጠፋነዉ ዘረኝነቱና ዉርደቱ ይቀጥላል

ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች በራሳቸዉ እጅ የጻፉት ማኒፌስቶ በግልጽ እንደሚያሳየን እነዚህ ዘረኞች ጫካ ገብተዉ የትጥቅ ትግል እንዲጀምሩ ያነሳሳቸዉ በአማራ ህዝብ ላይ ያላቸዉ ጥላቻና መሰረተ ቢስ ቂም በቀል ነዉ። ይህ ጥላቻቸዉ ደግሞ አማራዉን በመግደልና ግዛቱን ሲያሻቸዉ ከራሳቸዉ ክልል ጋር በመቀላቀል አለዚያም ለጎረቤት አገሮች በመሸለም ብቻ ሊቆም ወይም ሊገታ አልቻለም። እነሆ የአማራው ህዝብ የወያኔ ዘረኞች ዋነኛ ዒላማ ሆኖ የአገዛዙን የግፍ ፅዋ ያለማቋረጥ መጋት ከጀመረ ድፍን 23 አመታት ተቆጠሩ። ፋሽስቱ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ብሔራዊ ስሜት በማምከን ፣ የዘመናት ተገዥነቱን ለማረጋገጥ በቅድሚያ የአማራን ሕዝብ ማንነት ማጥፋት ፣ የአማራን ሕዝብ ስነ ልቦናዊ ጥንካሬ መስለብ እና አንገቱን ማስደፋት አስፈላጊ መሆኑን በጽናት ያምናል። ይህ በመሆኑም ፣ በአማራ ህዝብ ላይ በወያኔ የሚፈፀመው ግፍ እና በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ስር እየሰደደና እየከፋ በግልፅም በስውርም በተቀነባበረ መንገድ ቀጥሏል። ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ብሔራዊ ስሜት በማዳከም፣ ለዘመናት ሥልጣን ላይ ለመቆየት ያገለግለኛል ብሎ ዘመቻ ከከፈተባቸው ብሄረሰቦች አንዱና ዋንኛው የሆነው የአማራ ህዝብ በራሱ ማንነት እንዲያፍርና ብሄራዊ ኩራቱ እንዲሟሽሽ ላለፉት 23 አመታት በግብር ከፋዩ ህዝባችን ገንዘብ በሚተዳደሩ የመንግሥት መገናኛዎች ሳይቀር ከፍተኛ የስነ ልቦና ዘመቻ ተካሂዶበታል። በአማራ ሥም አማራውን የወያኔ አገር የማፍረስ አጀንዳ አስፈጻሚ ለማድረግ የተሾሙበት ተላላኪዎች በህወሃት አለቆቻቸው የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለመፈጸም በተለያዩ አጋጣሚዎች አማራውን የሚያዋርድና የሚዘልፍ አስተያየት በአደባባይ ሲሰጡ ሰምተናል አይተናል። ይህ ተግባራቸው ለአማራ ህዝብ ቅንጣት ታህል ክብርና ፍቅር ያልነበረው ዘረኛው አለቃቸው መለስ ዜናዊ ከዚህች አለም በሞት ከተሰናበተ ቦኋላም ተጠናክሮ ቀጥሎአል። የህወሃት መሪዎች አማራው ላይ ያላቸው ጥላቻ ወደሥልጣን ከመጡ ቦኋላ የተፈጠረ ሳይሆን ገና በጫካ ትግል ላይ በነበሩበት ወቅት በጻፉት የድርጅታቸው የፖለቲካ መረሃግብር በግልጽ እንደተቀመጠው ለትግል ያነሳሳቸውም አማራ ብለው የሚጠሩት ብሄረሰብ እንወክለዋለን በሚሉት ብሄረሰብ ላይ አድርሰዋል በሚሉት የፈጠራ በደልና ቂም እንደሆነ አረጋግጠዋል። ላለፉት 23 አመታት አማራው ከሚኖርበት የራሱ ክልሉ ሳይቀር እንዲፈናቀል ተደርጎ እየደረሰበት ያለው በደል የዚህ የቆየ የወያኔ ቂም በቀል ውጤት መሆኑ ግልጽ ነው። ሰሞኑን አለምነው መኮነን የተባለ ሆድ አደር የባንዳነት ተግባሩን በመፈጸም በአለቆቹ ፊት ግርማ ሞገስ ለማግኘት እመራዋለሁ የሚለውን የአማራ ህዝብ እጅግ በወረደና ጸያፍ በሆነ ቃላት ያን ያህል ሲዘባበትበት መደመጡ አማራውን ብቻ ሳይሆን መላውን የአገራችንን ህዝብ አስቆጥቶአል። በእርግጥ አለምነው መኮንን አማራን በማዋረድ የመጀማሪያው የወያኔ ተላላኪ አይደለም። የህወሃቶቹን ቁንጮዎች ስድብና ዘለፋ ወደ ጎን ትተን በወያኔ የዘር ፖለቲካ አማራውን እወክለዋለው የሚለው ብአዴን ከፍተኛ አመራር እነ እነታምራት ላይኔ ተፈራ ዋልዋና በረከት ስሞን በተለያየ ወቅት ንቀትና ስድባቸውን አሰምተውናል። አለምነህ መኮንን እንደዚያ በወረደ ቃላት አማራውን ሲያዋርድ በስብሰባው አዳራሽ የነበሩ ህወሃት የፈጠራቸው የብአዴን ልጆች በሳቅ ካካታ ሲያጅቡት እንደነበረ እድሜ ለኢትዮጵያ ሳታላይት ቴለቪዥን ከአዳራሹ ሾልኮ ለህዝብ ጀሮ የደረሰው የኦዲዮ ድምጽ አጋልጦአል። ሁላችንም፤ እንደምንገነዘበው ወያኔ የገዛ ብሄረሰባቸውን ረግጠው በመግዛት የጥፋት አላማውን እንዲያስፈጽሙለት በራሱ አምሳል ከፈጠራቸው ድርጅቶች አንዱ የሆነው ብአዴን በታሪኩ አንድም ለህዝቡ የቆመ መሪ አፍርቶ አያውቅም። ለራሳቸውና ከአብራኩ ለተገኙት ህዝብ ምንም አይነት ክብር የሌላቸው የብአዴን መሪዎች ጣሊያን አገራችንን በወረረችበት ወቅት ለሆዳቸው ሲሉ ከባዕድ ጋር ተሻርከው ህዝባቸውን ካስጨፈጨፉት ባንዳዎች የከፋ ተግባር በህዝባቸው ላይ እየፈጸሙ ነው። ወያኔ ለም የሆነውን የአማራ ግዛት እንዳለ የኔ ነው ወደሚለው የትግራይ ከልል ሲወስድ፤ በአማር ክልል ወስጥ በቀሩት ለም ቦታዎች የህወሃት ታማኝ ካድሬዎችን ከያሉበት እያጓጉዘ ሲያሰፍር፤ የአገሬውን አርሶ አደር እያፈናቀለ ለራሱ ታማኞች ለም መሬት እየሸነሸነ ለሰፋፊ እርሻ አገልግሎት ሲያድል አማራውን እወክለዋለው የሚለው ብአዴን አንድም የተቃውሞ ድምጽ አሰምቶ አያውቅም። የብአዴን መሪዎች የወያኔን ተልዕኮ ከማስፈጸም አልፈው በሟቹ አለቃቸው በመለስ ዜናዊ ሥም እየማሉ በአገራችን ኢትዮጵያና በሚያስተዳድሩት የአማራ ህዝብና ክልል የሚፈጽሙት በደል ብዙ ነው። ልክ እንደ ብአዴን የዘረኛውን ወያኔ የጥፋት ፖሊሲ ለማስፈጸም ከሚተጉት አንዳንዶቹ አማራውን ከክልላቸው ለማጽዳት በቤኒሻንጉል፤ በቤንች ማጅና ጉራፈርዳ ወረዳ እርምጃ ሲወስዱና ንብረታቸውን ቀምተው ባዶ እጃቸውን ሲያባርሩዋቸው ብአዴን ቁጭ ብሎ ተመልካች ነበር። ከአማራ ክልል ጋር የሚዋሰነው ዳር ድንበራችን ላይ በተነሳው የባለቤትነት ጥያቄም ላይ የወሰደው አቋም በህዝብና በታሪክ ፊት ውሎ አድሮ የሚያስጠይቀው ነው። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንደሚገነዘበው ፋሽስቱ ወያኔ በአገራችንና በህዝባችን ላይ እየፈጸመው ያለው አንዱን ዘር ከሌላው ጋር የማጋጨትና በተናጠል ደግሞ እያንዳንዱን ለይቶ የማዋረድና የማጥፋት ተግባር አሁን የተጀመረ ክስተት አይደለም። የቆየና ወያኔ ህዝባችንን ከፋፍሎ ለመግዛት ከመነሻው ሲጠቀምበት የነበረ ስልት ነው። ስለዚህ ወያኔ በራሱና በተላላኪዎቹ አማካይነት ላለፉት 23 አመታት በህዝባችን ላይ እየፈጸመ ያለውና የፈጸመው ግፍ፤ ውርደትና መከራ እንዲያበቃ ሁላችንም እጅ ለ እጅ ተያይዘን መነሳት ይኖርብናል። በወያኔ ከፋፋይ አጀንዳ እርስ በርስ እየተናቆርን የጥቃት ሰለባ የመሆናችንን እንቆቅልሽ ለማስቀረት ከኛ በላይ ሃይል ያለው አይኖርም። በተለይ ግንባር ቀደም የወያኔ ሰለባ የሆነው የአማራ ህዝብ ወጣት በጫንቃው ላይ ተፈናጠጠው የወያኔን የጥላቻና የበቀል እርምጃ የሚያስፈጽሙትን ከአብራኩ የተገኙ ባንዳዎች ላይ የጥቃት ክንዱን መሰንዘርና ለክብሩ መቆሙን ማሳየት ያለበት ጊዜው አሁን ነው። በብአዴን ሥር የተሰባሰቡ የአማራ ተወላጆች፤ በመከላኪያ ሠራዊቱ፤ በፖሊስና በደህንነት፤ በወጣት ማህበር፤ በሠራተኛ ማህበርና በተለያየ ሙያ ማህበር ብአዴን ራሱ ያደራጃቸው ሁሉ ለክብራቸውና ለኢትዮጵያዊ ማንነታቸው ሲሉ ከትግሉ ጎን በመሰለፍ የወያኔን ዕድሜ ለማሳጠር ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የሚያካሂደውን ትግል እንዲቀላቀሉ ንቅናቄው ጥሪውን ያቀርባል። ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

ልጓም ያልተገኘለት የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ

መንግስት የነዳጅ ዋጋን ማረጋጋት አለበት” (ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ ብሩህ ተስፋ) ባለፉት 8 ዓመታት የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ከአራት እጥፍ በላይ አድጓል የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መንግስት ለዜጎቹ ግድ ማጣቱን አመላካች ነው፡፡(የከተማዋ ነዋሪ) የስምንት ዓመት የዋጋ ንረት 1998 2006 ቤንዚን 6.57 20.47 ነጭ ጋዝ 3.45 15.75 ታክሲ (አጭር ርቀት) 0.60ሳ 1.50 ታክሲ (ረዥም ርቀት) 1.25 3.00 አንበሳ አውቶብስ 0.50ሳ 300% ጭማሪ አቶ መስፍን ወርቅነህ በመንግስት መ/ቤት የንብረት አስተዳደር ክፍል ውስጥ ተቀጥረው መስራት ከጀመሩ ወደ 18 ዓመት ገደማ አስቆጥረዋል፡፡ ሥራ ሲጀምሩ የወር ደመወዛቸው 720 ብር ነበር፡፡ በሥራ ዘመናቸው ለሦስት ጊዜ ያህል የደረጃ ዕድገቶችና የደመወዝ ጭማሪ ዕድሎችን አግኝተዋል፡፡ በ18 ዓመት ጊዜ ውስጥ ደሞዛቸው 1690 ብር ደርሷል፡፡ ከ15 ዓመት በፊት ትዳር የመሰረቱት በ280 ብር ከግለሰብ በተከራዩት ቤት ውስጥ ሲሆን ሦስት ልጆቻቸው የተወለዱትም እዚሁ ቤት ውስጥ ነው፡፡ የዛሬ 10 ዓመት ገደማ አከራያቸው ድንገተኛ የሃምሳ ብር ጭማሪ ሲያደርጉባቸው ክው ብለው ደነገጡ፡፡ የከተማው ዳርቻ አካባቢ አነስተኛ የኪራይ ቤት ማሰስ ጀመሩ። በመጨረሻም አየር ጤና የተባለው ሰፈር በ200 ብር የኪራይ ቤት አገኙና ቤተሰባቸውን ይዘው ገቡ፡፡ አቶ መስፍን ከከተማ ወጣ ብለው ቤት የተከራዩት፣ወጪያቸውን በመቀነስ የሚያገኟትን ደሞዝ አብቃቅተው ሦስቱን የአብራካቸውን ክፋዮች ሳይርባቸው ሳይጠማቸው አሳድጋለሁ በሚል ነበር፡፡ ጊዜው ግን ከእሳቸው ጋር እልህ የተጋባ መሰለ፡፡ ከዓመት ዓመት ኑሮው ወደ ላይ ይተኮስ ጀመረ ይላሉ፤ አዛውንቱ፡፡ ከአየር ጤና ካዛንቺስ ሱፐር ማርኬት አካባቢ እሚገኘው መ/ቤታቸው ለመድረስ ሁለት አንበሳ አውቶቡሶችን መጠቀም ነበረባቸው፡፡ የአንድ ቀን የደርሶ መልስ ወጪያቸው 3 ብር ሲሆን በወር 80 ብር ገደማ ለትራንስፖርት ያወጣሉ፡፡ አንዳንዴ ከረፈደባቸው ወይ ከቸኮሉ ከ5-6 ብር ለማውጣት ይገደዳሉ – በታክሲ ለመሄድ፡፡ የቤታቸውና የመሥሪያ ቤታቸው ርቀት ለምሣ ወደቤት መሄድን ፈፅሞ የሚያሳስብ አይደለም፡፡ መ/ቤታቸው አቅራቢያ ባለች አነስተኛ ምግብ ቤት ከ8-10 ብር እያወጡ ምሳቸውን የሚመገቡት አቶ መስፍን፤ የምሳ ወርሃዊ ወጪያቸው ከ180-200 ብር ይደርስ እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡ በልጆች ት/ቤት በኩል የተገላገሉ ይመስላሉ። ሁሉም በመንግስት ት/ቤት ነው የሚማሩት፡፡ እንዲያም ሆኖ ግን በአመቱ መጀመሪያ ላይ ለትምህርት መሳሪያዎችና ለዩኒፎርም ማሰፊያ የሚጠየቁት ገንዘብ ወገብ ይቆርጣል። የቱንም ያህል ፈተናና ውጣ ውረድ ቢበዛባቸውም ሁሉን ተቋቁመው ወደፊት እንዲጓዙ የሚያደርጋቸው ተስፋቸው ነበር፡፡ መቼም ቢሆን የተሻለ ነገን ከማለም ቦዝነው አያውቁም፡፡ አስደንጋጩ የኑሮ ውድነት ግን ህይወታቸውን አጨለመባቸው፡፡ ህልምና ተስፋቸውን ነጠቃቸው፡፡ ለኑሮ ውድነቱ መባባስ፣ ለሸቀጦች ዋጋ መናር፣ ለትራንስፖርት ዋጋ በሁለትና ሦስት እጥፍ መጨመር፣ ለነዋሪው ኪስ መራቆት፣ ለችግርና ጉስቁል መጋለጥ፣ ወዘተ… ሰበቡ ልጓም ያጣው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ነው። ሌላው ቀርቶ መንግስት እንኳ በሰፊ እጁ ስላለቻለው “ድጎማውን ትቼ አለሁ” ብሎ በይፋ እጅ ሰጥቷል። ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በነዳጅ ዋጋ ላይ የተደረገው ተከታታይ የዋጋ ጭማሪ የአቶ መስፍንን ህይወት ብቻ አይደለም ያናጋው፡፡ እንደሳቸው ያሉ ሚሊዮኖችን ኑሮ አቃውሷል፡፡ የሚሊዮኖችን ከእጅ ወደ አፍ ኑሮም አዛብቷል፡፡ አቶ መስፍን፤ ከ10 ብር በማይበልጥ ዋጋ ምሳቸውን ይበሉበት የነበረው ምግብ ቤት፤ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ዓይናቸው እያየ 40 እና 50 ብር ገባ፡፡ የዛሬው ብቻ ሳይሆን የነገው ጭምር ያሳስባቸው ጀመር፡፡ “አንዳንዴ የምንኖረው በተአምር ነው የሚመስለኝ፤ ምኑ ተምኑ ተደርጐ ከወር ሊደርስ እንደሚችል ማሰቡም ከባድ ነው፡፡ ተዉኝ እባካችሁ… ለዜጎች ግድ ያጣ መንግስት ነው ያለን፡፡ ብናልቅስ ምን ገዶት ብላችሁ!” ይላሉ አቶ መስፍን – የኑሮ ውድነቱ የወለደውን ብሶታቸውን ሲተነፍሱ፡፡ የአለማቀፉን የነዳጅ ዋጋ ውጣ ውረድ ተንተርሶ፣ የንግድ ሚኒስቴር በወሩ መጨረሻ የሚያወጣው የነዳጅ ዋጋ ክለሣ፣ በ8 አመት ውስጥ ከሶስት እጥፍ በላይ መጨመሩን ያመለክታል፡፡ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ ከግንቦት 1998 ዓ.ም ጀምሮ በፍጥነት እየጨመረ የመጣው የአለማቀፉ የነዳጅ ዋጋ፣ በኢትዮጵያ የነዳጅ አቅርቦትና የዋጋ ተመን ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ አሳርፏል፡፡ በአለማቀፍ ደረጃ የበርሜል ነዳጅ ዋጋ መጨመሩን ተከትሎ በዚያው ዓመት በተደረገው የዋጋ ክለሣ፣ የአዲስ አበባ የተራ ቤንዚን መሸጫ ዋጋ፣ በሊትር 6 ብር ከ57 ሣንቲም ገደማ የነበረ ሲሆን ታሪፉ አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንደገና ተሻሽሎ በታህሳስ 1999 ዓ.ም 7 ብር ከ75 ሳንቲም ሆነ፡፡ በ8 ወር ጊዜ ውስጥ በሊትር እስከ 1ብር ከ20 ሣንቲም የሚደርስ ጭማሪ ተደርጓል ማለት ነው፡፡ በወቅቱ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው በህብረተሰቡ የእለት ተእለት ኑሮ ላይ የጐላ ጫና አሳርፏል ለማለት ባያስደፍርም፣ ጭማሪው ቀደም ካሉት አመታት አንፃር ሲታይ ከፍተኛ ነበር፡፡ ከአመት በኋላ በንግድ ሚኒስቴር በተደረገው ክለሳ፣ የነዳጅ ዋጋ ወደ 9 ብር ከ60ሣ. አድጓል፡፡ ከቀድሞው ዓመት 1 ብር ከ85 ሣንቲም ጭማሪ በማሳየት ማለት ነው። የ2001 ዓ.ም የነዳጅ ዋጋ ደግሞ ቀደም ካለው ዓመት 1 ብር ከ40 የሚደርስ ቅናሽ እንዳሳየ የሚኒስቴር መ/ቤቱ መረጃ ይጠቁማል፡፡ ሰኔ 2001 የተከለሰው የነዳጅ ዋጋ እንደሚያመለክተው፤ ቤንዚን በሊትር 8 ብር ከ95 ሣንቲም ገደማ ሲሆን ከሁለት ወር በኋላ በጳጉሜ 2001 በተደረገው ክለሳ፣ አዲስ አበባ ላይ በሊትር የ2 ብር ገደማ ጭማሪ በማሳየት ወደ 10 ብር ከ93 ሣንቲም ተመነደገ፡፡ ከአንድ አመት በኋላ በህዳር 2003 ዓ.ም በከፍተኛ ሁኔታ ያሻቀበው የቤንዚን ዋጋ፣ 14 ብር ከ87 ሣንቲም የደረሰ ሲሆን ከአምስት ወር በኋላ በአብዛኛው የክልል ከተሞች በሊትር ከ22 ብር በላይ ሲሸጥ፣ በአዲስ አበባ የ6 ብር ጭማሪ ተደርጐበት በሊትር 20 ብር ከ94 ሣንቲም ገባ። ይህም በ8 አመት ውስጥ በጥቂት ወራት ልዩነት ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ የታየበት ወቅት መሆኑን ያመለክታል፡፡ 2004 እና 2005 ዓ.ም ከሌሎቹ አመታት በንፅፅር የነዳጅ ዋጋ የተረጋጋበት ወቅት ነበር፡፡ መጠነኛ ቅናሽም አሳይቷል፡፡ በዚህ ጊዜ ከ18 ብር ከ75 ሣንቲም እስከ 19 ብር ከ45 ሣንቲም ባለው ዋጋ መካከል ሲዋልል ቆይቷል፡፡ ዘንድሮ በ2006 ዓ.ም የየካቲት ወር የቤንዚን ዋጋ በሊትር 20 ብር ከ47 ሣንቲም ተተምኗል፡፡ በዝቅተኛ ኑሮ ላይ የሚገኘው የህብረተሰብ ክፍል፣ እንደ እለት ተእለት ፍጆታው የሚጠቀምበት ነጭ ጋዝ (ላምባ)፤ በ1998 አዲስ አበባ ላይ በሊትር 3 ብር ከ45 ሲሸጥ፣ በየካቲት 2006 ዓ.ም 15 ብር ከ75 ሣንቲም እየተሸጠ ነው፤ በአምስት እጅ ጨምሮ፡፡ የንግድ ሚኒስቴር ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ በየወሩ መጨረሻ ላይ የሚያደርገውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ተከትሎ የመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣንም የትራንስፖርት ዋጋ ማሻሻያ እያደረገ ነው፡፡ የታሪፍ ጭማሪው በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ሃይገር ባሶች፣ የከተማ አውቶቡሶችና ታክሲዎችን የሚመለከት ሲሆን አንበሳ አውቶቡሶች ከ0.50 ሳንቲም ታሪፍ ተነስተው እንደየርቀታቸው ከ300% በላይ ጭማሪ አድርገዋል፡፡ በ1998 ዓ.ም የአጭር ርቀት የታክሲ ተመን 65 ሳንቲም፣ የረዥም ርቀት 1.25 ሳንቲም የነበረ ሲሆን አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ክፍያው ወደ 95ሣ. እና 1.65 ሳንቲም ከፍ ብሏል፡፡ በየጊዜው በሚደረገው የዋጋ ማሻሻያ መሠረትም ታሪፉ እየጨመረ ሄዶ፣ በያዝነው የካቲት ወር የአጭር ርቀቱ 1.50 ሳንቲም፣ ረዥም ርቀቱ 3.00 ብር ሆኗል፡፡ በከፍተኛ ደረጃ እያሻቀበ የመጣው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ በአገሪቱ ኢኮኖሚና በህብረተሰቡ የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ በተመለከተ ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም መምህር የሆኑት ዶክተር ቆስጠንጢኖስ ብሩህ ተስፋ፤ በየጊዜው በሚጨምረው የነዳጅ ዋጋ በይበልጥ የሚጐዳው በቋሚ ደመወዝ የሚተዳደረው የህብረተሰብ ክፍል ነው ይላሉ፡፡ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ከአለም የነዳጅ ዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ እንደሚከሰት የጠቆሙት ዶክተሩ፤ መንግስት ሌላውን ዘርፍ እየጎዳ በነዳጅ ላይ ድጎማ ያደርግ እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡ የነዳጅ ዋጋ በጨመረ ቁጥር በሁሉም ሴክተር ላይ የዋጋ ጭማሪ መታየቱ እንደማይቀር ጠቁመው፤ በዚህ ተጎጂ የሚሆነው በተለይ በቋሚ ደመወዝ የሚተዳደረው የህብረተሰብ ክፍል እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ “በዓለም የነዳጅ ዋጋ ስለጨመረ እኛም መጨር አለብን በማለት መንግስት በየጊዜው በነዳጅ ዋጋ ላይ የሚያደርገው ጭማሪ አያዋጣም” የሚሉት ባለሙያው፤ የነዳጅ ዋጋው በጨመረ ቁጥር የዋጋ ግሽበቱ እየጨመረ መሄዱ በህብረተሰቡ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ምን ያህል እንደሆነ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ተሰብስበው እንዲመክሩበትና መፍትሄ እንዲፈልጉለት ማድረግ ተገቢ ነው” ሲሉም ይመሰክራሉ፡፡ በዋናነት የነዳጅ ዋጋን የማረጋጋት ኃላፊነት የመንግስት መሆኑንም ያሰምሩበታል፡፡ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአብዛኛው ህብረተሰብ አቀፍ ዘርፍ በመሆኑ መንግስት ሊቆጣጠረው የሚችለው ነው ያሉት ዶክተሩ፤ የነዳጅ ዋጋ በጨመረ ቁጥር ነጋዴው በሚሸጠው ዕቃ ላይ ዋጋ ጨምሮ በመሸጥ ጭማሪውን ሊቋቋመው እንደሚችል ጠቅሰው፣ ሸማቹ በተለይም ቋሚ ገቢ ያላቸው የመንግስት ሰራተኞችና ጡረተኞች ግን ለጉዳት እንደሚጋለጡ ተናግረዋል፡፡ የመንግስት ሰራተኞች ሲባልም የጦር ኃይሎችና የፖሊስ አባላትን እንደሚያካትት፣ እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎችም በዋጋ ንረቱ እንደ ሚጎዱ በመግለፅ ጉዳዩ ትኩረት ተሰጥቶ ሊታይ ይገባዋል ብለዋል፡፡ አገሪቱ በዓመት ወደ ሶስት ቢሊዮን ዶላር የሚፈጅ ነዳጅ እንደምታስገባ የጠቆሙት ዶክተር ቆስጠንጢኖስ፤ በነዳጅ ዋጋ ላይ የሚደረገውን ጭማሪ ለመግታት ሌላው አማራጭ የነዳጅ ፍጆታን መቀነስ እንደሆነ ጠቁመዋል። በከፍተኛ መጠን ነዳጅ የሚጠቀሙት የመንግስት መስሪያቤቶች ሲሆኑ መኪኖች፣ ጄኔሬተሮች፣ ግድቦችና መሰል ነገሮች የሚሰሩት በነዳጅ በተለይም በናፍጣ በመሆኑ ይህንን ፍጆታ መቀነስ የሚቻልበት መንገድ ሊታሰብበት ይገባል ሲሉም አሳስበዋል፡፡ ሌላው ምሁሩ አማራጭ ነው ያሉት ጉዳይ የነዳጅ ፍለጋውን አጠናክሮ መቀጠል ሲሆን ነዳጅን እየደጎሙ መቀጠሉ አዋጪ ነው የሚል እምነት እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡ የነዳጅ ዋጋ ማሻቀቡ ሌላው ምክንያት ነው ያሉት የፍጆታ መጠን መጨመሩ ሲሆን አሁን አገሪቱ ውስጥ ባለው ሁኔታ እየተሰሩ ያሉት መሰረተ ልማቶች፤ ማሽኖችና መሳሪያዎች የሚወስዱት የነዳጅ ፍጆታ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ አገራችን በአብዛኛው ነዳጅ የምታስገባው ከኩዌት መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር ቆስጠንጢኖስ፤ በአሁኑ ወቅት የሚታየውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ለመግታት መንግስት ሊያስብበት ይገባል ይላሉ። የልማት ስራዎች ሲሰሩም የህዝቡን ጥቅምና ፍላጎት ሳይነኩ መሆን እንዳለባቸው ጠቁመው፤ “ከአቅም በላይ የሚሰራ ልማት ጫናው በህብረተሰቡ ጫንቃ ላይ ያርፍና ህብረተሰቡ ይበልጥ እየተቀየመ ከመጣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀውሶችን ይፈጥራል” ብለዋል፡፡ በእሳቸው ዘመን ከንጉሱ ጊዜ ተቃውሞ ለለውጡ ዋንኛ መንስኤ የነበረው የታክሲ ነጂዎች በነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ምክንያት ያስነሱት ተቃውሞና ያደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ መሆኑንም ዶክተር ቆስጠንጢኖስ አስታውሰዋል፡፡

Ethiopia uses Italian surveillance to hack their own journalists in US and Europe – report

2014 (Voice of Russia) — The Ethiopian government used a new Italian surveillance program to hack into computers of their own journalists located in the US and Europe. A new report by Citizen Lab have confirmed the speculations regarding the Ethiopian government hacking into the computers of Ethiopian journalists in the US and Europe. According to the report, all journalists belonged to the Ethiopian Satellite Television (ESAT). ESAT is a news organization, which consists of mainly Ethiopian expats. In order to get access to their files the authorities used a program, developed in Italy, by Italian company Hacking Team. This update is just another example of various government organizations around the world using local surveillance companies for espionage. According to Morgan Marquis-Boire, a security researcher: “This stuff is sold widely, and as such it is also used widely. This type of targeted surveillance is a common method for tracking journalist in the in the diaspora.” Marquis-Boire, who worked on the project with his colleagues from Citizen Lab, Bill Marczak, Claudio Guarnieri and John Scott-Railton, found proof of tracking two ESAT employees: one located in Brussels and one who is in northern Virginia. The attacks took place on December, 20, 2013 in two hour period. The first attack took place in the Brussels office, when a journalist received a file through Skype from someone named Yalfalkenu Meches. The name of the file was “An Article for ESAT”, which looked like a PDF format file but contained a spyware. The program once opened tries to communicate with the server, using a special encryption system. However, the journalist who has received the file didn’t open it but contacted the sender and said that the file is corrupted and might contain the malware. In response to that, Meches stated that file worked fine for him and instead sent another one, this time in a doc. format. This new file managed to trigger and download another one, which was spying software, known as Remote Control System (RCS). The aim of RCS is to monitor upcoming and outgoing files on the computer as well as steal them along with intercepting the Skype calls and other chat communications. After an hour and a half, the same person who sent files in Brussels, did the same thing to another journalist in Virginia. For now, the main suspects of the hacking are unclear but according to Citizen Lab, the Ethiopian government is on the top of the most suspected. “Hacking Team’s spyware is sold only to governments and it’s hard to imagine that a different government besides the Ethiopian government would target ESAT,” stated Marczak. However, Wahide Baley, head of public policy and communications of the Ethiopian embassy in Washington DC has already announced that his government “did not use and has no reason at all to use any spyware or other products provided by Hacking Team or any other vendor inside or outside of Ethiopia.” Despite the contradiction, it is not the first time that the Ethiopian government was accused of spying. Back in March 2013, the same company found proof of another program, FinSpy, developed by Gamma International being used by Ethiopia. “The Ethiopian government is so interested in surveilling and spying that has apparently resorted to purchasing two different systems for this purpose,” Marczak says. Meanwhile, Eric Rabe, Hacking Team’s Chief Communications Executive, has already officially declined in his statement to reveal whether spying enquiry came from the Ethiopian government. He stated that his company’s software “is used in confidential law enforcement investigations.”

Saturday, 15 February 2014

The Discussion on the Review of Dr. Berhanu’s Book and My Impression

I watched the discussion (review) on Dr. Brehanu Nega’s Book, “Democracy and All-round Development in Ethiopia” (Democracy enna Hulentenawi Limat Ba’-Ethiopia) published in 2013. The discussion (the review) was conducted by ESAT on its Program “Ethiopia Nege” on February 7, 2014. Although the host of the program, Ato Gizaw had the difficulty of how to handle the conversation that sounded derailing from its very clear and specific subject matter, he deserves due appreciation for trying to keep the discussion in its right track. The participants were: Dr. Berhanu, explaining the very aim of his book on one side; and Dr.Tesfaye Demelash and Ato Berhane Mewa as critics of the book on the other side.
As one of those who read the book with sincere interest, I was also one of those who watched the review discussion with great interest and sincere attention. I had to go back and watch it for a couple of times to make sure that I could grasp the very essence (specific objective) of the discussion and to make sure that I could have the right impression, not wrong perception . Has the discussion turned-out to be as inspiring as it should have been? To my understanding, it hasn’t. Why not? I will come back to that. Let me first say that I found the discussion encouraging and interesting from the following perspectives in general: 1) Dr. Berhanu has easily and wisely handled his explanation and he showed a typically good example as far as how to deal with a conversation that sounded difficult is concerned. 2) And I also think that with all the weaknesses of their arguments, the critics (Dr. Tesfaye and Ato Berahne) deserve appreciation for coming forward with their view points about the book. I want to say that some of their concerns sounded genuine and should be treated accordingly. As one of those readers of the book, I have tried my best to get a real sense of understanding about the very purpose of the author, and weather that purpose is well-reflected in the very content of the book. To my understanding, the very specific aim of the book is not to deal with a very comprehensive approach to all the political, economic and cultural history of our country together with what we seriously are lacking in the current political, socio-economic and environmental aspects of our lives. I do not think there is a problem of clarity and simplicity of the book as far as aiming at contributing to the dialogue on the ongoing political struggle is concerned. In other words, the author expresses his views and ideas on the question of what does good governance (good political and economic system) mean in a very clear and concise manner. This very critical question has been fairly dealt with throughout the five chapters of the book: (1) The core criteria for good political system (justice, peace and security, economic opportunities for all citizens and the peaceful transfer of power through democratic election)(2) The challenges related with our political history that we may face in the process of bringing about a desired system (undesirable elements of our history (scars), highly skewed growth/development, the politics of identity, impacts of religious conflicts , the problem of our perception about justice) (3) Good economic system( the fulfilment of basic interest of citizens, economic growth /development , fair and just distribution of wealth, the opportunity to use/utilize the potentialities of the people ) (4)The Structural challenges/problems we face to have in the process of building good economic system ( The impacts and difficult choices due to abject poverty, the negative consequence of unfair level of playing field of the economy, the question of how to balance the conflict between the search for growth/development on the one hand and our culture and our lifestyle on the other hand, the conflicts that may arise in the process of building justice ,history and good economy ) (5) Environmental conservation ( the current status of environmental conservation and its consequences if we ignore it , the population growth and the challenges and the pressure they put on us, the political and social troubles that could be caused by the problem of environmental conservation and population growth). In his conclusion, the author has clearly informed his readers that part two of his work will be dealing with the issues of bringing about genuine democratic political system in our country as a necessity, not as a choice. In other words, he clearly states that his second part tries to make its own contribution to show some problem – solving steps that revolve around the imperativeness of establishing democratic political system in our country. That is my understanding and impression with regard to the whole purpose of the author. I want to make clear that I am not saying that the author should not be challenged and criticized .I strongly believe that this kind of thinking (leave me alone or leave him/her alone attitude) is not only nonsensical but absolutely wrong. What I am trying to say is that the way we criticize and challenge the work of any author should be with a certain level of rationality, clarity and genuineness. Because that is the way we can develop critical, rational/objective, constructive and forward-looking way of thinning if we want to bring about the change we desperately aspire. To my understanding, this first part of Dr. Berhanu’s book deals with the very first question we encounter: what is terribly missing in the current political arena of our country? It is beyond any doubt that what is terribly missing is good governance (political freedom, rule of law, socio-economic development and fair and balanced distribution of wealth). And the next logical and critical question will be what is be done (solution)? Needless to say, the only way is to get rid of a political system that is the very root cause for what is terribly missing and replace it with a genuine democratic system that should essentially be responsible to the people and accountable for any action that is against the will and interest of the people. And that was and is my understanding of the book and of what I listened to Dr. Berhanu had to say during the discussion on his book review. Now, let me come back to my observation / impression about the two critics of the review, Dr. Tesfaye Demelash and Ato Berhane Mewa. Both of them stated that the book deserves due recognition for raising very important issues. And that is appreciable. 1. Ato Berhane’s recommendation to those who might not read the book to read it is genuinely constructive. Yes, he was right that it is one thing to go through the review; but it is quite another thing to read and try to comprehend the whole text, and to develop it with more insightful ideas. The problem I have with his critic is related with making very general statements or lack of clarity and specificity. Let me mention some of the difficulties I had to understand his argument: A. He argued that he believes that there is kind of gap. He tried to explain this statement by saying that the equation should include the geopolitics of the sub region, the Nile issue, the danger from external (the surrounding actors) and the issue of globalization which dictates domestic issues. Of course, all these factors should be taken into account whenever we deal with the political challenges we face domestically. The problem is that he could not clarify why and how all these elements (factors) are directly related to the book which deals with a very specific aim, what we are seriously missing in our current political system? I do not know what was the problem to stay focused on the issues of which the book tries to deal with; the question of what went wrong and is going wrong as far as the absence of universal values of democratic political system are concerned. Is it not a very bitter truth that we continue to suffer from all kinds of crises mainly because of the absence of a democratically representative government? B. He complained that the book mainly focuses on current issues. Yes, it does. But that focus is based on a strong political argument that the very reason why we continue to suffer is nothing, but because of the total non-existence of a political system that promotes and protects the very interests of the country and her people. C. I really did not understand his complaint of “In the past it was socialism; now we are talking about democracy.” If it is to mean that Dr. Berhanu’s book and argument is just simply the theorization of democratic values and principles, I do not think that is a well-substantiated and clarified argument because conceptual analysis based on a given political practice such as ours is an essential part of a struggle in a democratic process. D. We have to talk about why we need democracy before we talk about it was another point of argument. He farther stated that he question of accepting or not democracy is up to the people. I do not know how we should have a discussion on the question why we need something without understanding what we really need. It does not sound a logically meaningful reasoning. E. I really did not understand the argument of “first being tolerant and listen to each other, and thereafter democracy will follow.” I think the very content of the book and the way the author explained has neither excluded nor undermined the value of tolerance and the importance of listening to each other. To sum up, I do not want to question the genuine concerns of Ato Berehane Mewa about his country and his aspiration for the realization of a genuine democratic system in which all citizens could live in peace, freedom, equality and shared prosperity. But, I have to say that the way he argued in this particular discussion of book review suffered from lack of clarity and staying focused on the very subject matter under discussion. 2. Dr. Tesfaye’s argument is not very different from Ato Brhane‘s. I read the six pages of his article titled “Solving the Tension of a Country within a Country themselves /Yageren Wutret Beager Mefitat” (I think it means by the people themselves), and I listened to his view points during the discussion on the review. As I understood it, the article is the detail description of his argument he made during the discussion. Here are some of them and the comment I want to make on them: A. Dr. Tesfaye mentioned repeatedly Eritrea in his argument on the very influence of external factors. No doubt that the Ethio-Eritrean issue matters a lot to our domestic security and stability. It goes without saying that it is a foreign policy that is formulated and implemented in line with the very domestic policy (of national interest) that can bring a meaningful peace/stability, security and development in Ethiopia as well as in the sub region. I think what Dr. Berhanu wants to show is that the very indispensable or determinant factor in dealing with all issues that matters to the fulfillment of national interest is nothing, but essentially the existence of a democratic/ truly representative government in our country. So, the very question I want to pose to both critics (Dr. Tesfaye and Ato Berhane) is: Are we arguing that the very purpose (content) of Dr. Barhanu’s book and his explanation is incomplete because it does not deal with foreign policy, or what? I am not saying their concern about external factor (geopolitics) does not sound great. Absolutely not! What I am saying is that trying to argue that the book should have included foreign policy issues (external state and non-state actors) does not sound strong as far as the very specific aim of the book is concerned. B. Let me add just one passing remark on the questioning of the independence of Eritrea. Dr. Tesfaye expressed his difficulty of accepting Eritrea as a country in his article when he questions, “If Eritrea is said to be a country?” Well, I am one of those Ethiopians who consider the separation of Eritrea from Ethiopia using all highly falsified political games was one of very unfortunate chapters of our political history. But, I do not think being denial of what has already become a reality (the internationally recognized Eretria) is the right thing to do as far as the imperative of dealing with the issue of how to make things that has gone wrong right is concerned. And this kind of attitude of denial becomes difficult to comprehend when it comes from well-educated people such as Dr. Tesfaye. I strongly believe that we have to accept the already given reality and deal with it accordingly. Simply put, we need to work hard how to bring a situation where the two countries could move in a direction of confidence building and subsequently making some sort of economic and political cooperation even to the extent of an arrangement of confederation and so no and so forth. The political culture of denial and avoidance will never serve any desirable purpose. What kind of government or political system is required for this very huge and challenging responsibility? There is no doubt that it is only a political system that should be led by an appropriately structured and democratically representative government. And that has to be our focal point if we are serious enough about designing the way out from the very ugly political vicious circle we found ourselves. C. Dr. Tesfaye tried to make kind of comparative politics of the French revolution and the 1970s of ours. He characterized ours as a left –wing movement started by students and now ended up with the so-called democratic revolution of TPLF. Well, leaving the question of whether the comparison is appropriate or not aside, I want to say that the way Dr. Tesfaye and so many other scholars for that matter look at the 1970s revolution sounds highly generalized and subsequently misleading. Dr. Tesfaye says, “Our revolution was started with a derailed left- wing student movement …. / Yegna abyot ferun belekeke Yetemarewoch gira-kinif enkiskasie tejemiro….” It is one thing to simply be critical of the past wrong doings/mistakes; but it is quite another thing to rationally/objectively be critical and come up with ideas of how we should make things right and move forward. I do not know when and how we have to get out of the politics of simply blaming what went wrong in the past. I do not really understand why and how we look at the political event that took place forty years ago as the result of the then international and domestic political circumstances from our perspective of the this 21st century and blame the generation. D. Dr. Tesfaye complains both in the review discussion and in his article about the “emptiness of concepts such as of democracy, rule of law, liberty, equality, constitution, and …..” I do not think it is arguable that that all governments including the most brutal ones preach about those very values and principles of democracy. The question is how we should respond to these kinds of terribly hypocritical, if not deadly cynical political games. To my understanding, the works of intellectuals such as Dr. Brhanu’s give valuable insights in this regard. So, let’s not mainly stay on leaning on what happened in the past and complain about the tyrannical ruling groups such as TPLF/EPRDF who terribly abuse their political power in the name of democracy and national security . Let’s employ our energy and time mainly on strategic ideas and feasible ways and means that could help shorten the continuation of mere political gangsterism. That is why I do not think that criticizing Dr. Behanu’s approach as too much focus on the current challenges we are facing does sound convincing. E. He tried to justify one of his points of critic by stating that it is not good to have “over-exaggerated concern as Ethiopiawinet is not merely the total sum of problems.” He put his argument in the form of question, “Is there no an opportunity other than problems?” And he tries to answer the question by stating that “this kind of thinking is not good to psychology.” Well, that is true. But, all these points of argument boils down to one and only one issue, the absence of practical democratic principles and values . He says we (Ethiopians) have both national and cultural experiences that should be taken account. True. But, on the other hand, somewhere down in his article, he states that, “Our common national survival (lives) and Ethiopiawinetachin is at the cross-road, the direction of survival or death.” That is exactly the very concern expressed in Dr. Berhanu’s book. Well, his article of six pages (in Amharic) posted on Ethiomedia tries to raise and discuss many issues of concern and that is greatly appreciable. However, as it is true to most of our intellectuals, it is heavily over dominated with background information and description of problems and blaming external actors (Eritrea), the ruling party of Ethiopia (TPLF) and “opposition forces which are being used by both parties as agents of proxy war” without referring who is who. I did not observe any substantive recommendation on the question of what is the way out. Let me conclude my observation by saying that although expressing our views and concerns in any way we believe in should be valued , I have an impression that we most of us still are in short of engaging ourselves in ideas and forward –looking recommendations. And I hope we will move towards that direction!

Friday, 14 February 2014

በርካታ ወጣቶች ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት እየተጋዙ ነው

ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ አሸባሪ ካላቸው ግንቦት ሰባት እና ሌሎች ፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ በርካታ የአዲስ አበባና አማራ ክልል ወጣቶች ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት እየተጋዙ መሆኑን የአይን እማኞች ተናገሩ፡፡ ኢህአዴግ በጀመረው አዲስ አሰሳ በሀገሪቱ አንድንድ ቦታዎች ኢንተርኔትን ጨምሮ ስልክ እንዳይሰራ የተደረገ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎችም የመከላከያ ሀይል ተበትኗል፡፡ የዚህን ዜና ዝርዝር በሌላ ጊዜ ይዘን እንቀርባለን። በሌላ ዜና ደግሞ ብአዴን ከፍተኛ የሞራል ውድቀት የደረሰበት መሆኑን ምንጮች ገለጹ። የብአዴን የጽፈት ቤት ሃላፊ እና የአማራ ክልል ም/ል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ አለመነው መኮንን የሚመሩት ህዝብ ጸያፍ ስድብ መሳደባቸውን ተከትሎ ብአዴን የሞራል ውድቀት እንደደረሰበት ከክልሉ የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የክልሉ ህዝብ ያሳየው ቁጣና በብአዴን የንግድ ድርጅቶች ላይ የጣለው ማእቀብ ያሰጋቸው አቶ በረከት ስምኦን ወደ ባህርዳር በማቅናት ፣ የደረሰውን ኪሳራ ለመቋቋም ያስችላሉ የሚሉዋቸውን አማራጮች ሁሉ ለመጠቀም ከሌሎች አመራሮች ጋር እየመከሩ ናቸው። የብአዴን አመራሮች ባደረጉት የመጀመሪያ ግምገማ “የአማራ ህዝብ ፊት ለፊት የምንናገረውና ከጀርባ የምንናገረው ነገር የተለያየ ነው” ብሎ እንዲያስብና እምነቱን እንዳይጥልብን አድርጓል” ብለዋል። ብአዴን በመጪው ምርጫ ላይ በክልሉ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ኪሳራ ሊደርስበት እንደሚችልም በግምገማው ወቅት ተነስቷል። የክልሉ ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአማራ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፣ በኢሳት የቀረበው የአቶ አለምነው ድምጽ አይደለም ብለው ማስተባበል ሳይችሉ ቀርተዋል። ፕሬዚዳንቱ በባህርዳር ስብሰባ መካሄዱንና ድምጹም በጊዜው የተቀረጸ መሆኑን በተዘዋዋሪ መንገድ ያመኑ ሲሆን፣ መክትላቸው የተናገሩትን በቀጥታ ከማስተባበል ይልቅ አቶ አላምነው ለአማራው ህዝብ ስላላቸው ፍቅር መግለጽን መርጠዋል። አቶ አለምነው እራሳቸው ቀርበው ለምን መግለጫ እንዲሰጡ እንዳልተፈለገ ግልጽ አይደለም። የክልሉ ህዝብ የብአዴን ንብረት የሆነውን ዳሸን ቢራን እንዳይጠጣ የሚደረገው ቅስቀሳ አግባብ አይደለም ሲሉ አቶ ገዱ ተናግረዋል። ድርጊቱን ያወገዙት አንድነትና መኢአድ የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ደብዳቤ ማስገባታቸው ታውቋል። ፓርቲዎቹ በጋራ ባወጡት መግለጫ ” ህዝብ ያዋረዱ አመራሮች በተገቢው ፍጥነት ለፍርድ እስኪቀርቡ ድረስ የተቃውሞ ሰልፉ በሌሎች የሀገራችን ክፍሎችም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል” ብለዋል፡፡ የተቃውሞ ሰልፉ ከጣቱ በሶስት ሰአት ከቀበሌ 12 ( ግሽ አባይ ተነስቶ)፣ በክልሉ መስተዳድር ጽ/ቤት ከቀኑ ስምንት ሰአት ላይ ያበቃል። የባህርዳር እና አካባቢዋ ህዝብ በስፍራው ተገኝቶ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት በህዝቡ ላይ ያወረዱትን ዘለፋ እንዲያወግዝ ፓርቲዎቹ ጠይቀዋል።

Thursday, 13 February 2014

የጋዜጠኛው ጥያቄ ጠ/ሚኒስትሩን አስቆጣ

ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በጽ/ቤታቸው ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከፎርቹን ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር አቶ ታምራት ገብረጊዮርጊስ በቀረበላቸው ጥያቄ በመቆጣት ዘለፋ ሰነዘሩ፡፡ አቶ ታምራት ለጠ/ሚኒስትሩ ያቀረቡት ጥያቄ በአሁን ሰዓት አገሪትዋን የሚመራት ማንነው ነው የሚል ይዘት ያለው ሲሆን ጠ/ሚኒስትሩም ብስጭታቸውን በምላሻቸው ወቅት አንጸባርቀዋል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ ለዚህ ጥያቄ ቀጥተኛ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ጋዜጠኛውን ሂድና እዚያ ሐሜት የምትጽፍበት ገጽ ላይ ጻፈው በማለት መዝለፋቸው በርካታ ጋዜጠኞችን አስደንግጦአል፡፡ አንዳንድ ጋዜጠኞች ስለሁኔታው በሰጡት አስተያየት ጋዜጠኛ ታምራትን በማድነቅ አንድ ጋዜጠኛ በሕዝብ ውስጥ የሚነገርን ጥያቄ አውጥቶ መጠየቁ ተገቢና ሙያዊ ሃላፊነቱ መሆኑን በመጥቀስ ጠ/ሚኒስትሩ ጥያቄው የቱንም ያህል ቢያበሳጫቸው በዚህ መልኩ ምላሽ መስጠታቸው ራሳቸውን ከማስገመት ያለፈ ትርፍ እንደሌለው ተናግረዋል፡፡ ከአቶ መለስ ሞት በሃላ ወደስልጣን የመጡት አቶ ኃይለማርያም ቀደም ሲል በአቶ መለስ ብቻ ሲመራ የነበረውን የጠ/ሚኒስትር ስልጣን የጋራ አመራር በሚል ፈሊጥ ሶስት ቦታዎች በመክፈልና በምክትል ጠ/ሚኒስትር ማዕረግ ለኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ስልጣናቸው ማከፋፈላቸው በሕዝብ ዘንድ ያለስልጣን የተቀመጡ አሻንጉሊት መሪ እስከመባል አድርሶአቸዋል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ በዚሁ መግለጫቸው ብዙ ሲባልበት የቆየውን ኢትዮ ሱዳን ድንበር ማካለል ጉዳይ ከውይይት ያለፈ ነገር እንደሌለ በመናገር የሚደርስባቸውን ትችቶች ያጣጣሉ ሲሆን አጀንዳውንም ከመጪው ምርጫ ጋር በማያያዝ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚደረግ ሙከራ መሆኑን ለመናገር ሞክረዋል፡፡ በኢትዮ ሱዳን ድንበር ማካለል ጉዳይ በስፋት የዘገቡትና ሒደቱንም ያሳወቁት የሱዳን ጋዜጦች መሆናቸውን በተመለከተ ያሉት ነገር የለም፡፡ ከኢህአዴግ ጋር በመደራደር አገር ውስጥ ገብተዋል ስለተባሉትም አቶ ሌንጮ ለታ ተጠይቀው ዋሽንግተን ለሚገኘው ኢትዮጽያ ኤምባሲ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ከመስማታቸው ውጪ ስለመግባታቸው የሚያውቁት ነገር እንደሌለ በመናገር ጉዳዩን አስተባብለዋል፡፡

Tuesday, 11 February 2014

የአዲስ አበባ ከንቲባና ፖሊስ ኮሚሽነር በ“አንድነት” ተከሰሱ

ከንቲባ ድሪባ ኩማና ኮሚሽነሩ መከራከሪያቸውን ለፍ/ቤት ያቀርባሉ አንድነት፣ የመንግስት አካላትን በተከታታይ እከሳለሁ ብሏል አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት)፣ የአዲስ አበባ ከንቲባና የፖሊስ ኮሚሽነራቸው ላይ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 8ኛ ወንጀል ችሎት ክስ የመሰረተ ሲሆን ተከሳሾች መልሳቸውን ይዘው እንዲቀርቡ ለየካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጠ፡፡ አንድነት ፓርቲ፤ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” የተሰኘ አገር አቀፍ የ3 ወር ንቅናቄ ማጠቃለያን በአዲስ አበባ ባካሄደበት ወቅት በከተማ አስተዳደሩና በፖሊስ ኮሚሽን እስርና ወከባ እንደተፈፀመበት ገልፆ፤ በደላቸውን በማስረጃ በመዘርዘር ክስ መመስረቱን አስታውቋል፡፡ በፖሊስ ተፈፀመ በተባለ በደል ከንቲባውን በቀጥታ ለምን እንደከሰሰ ፓርቲው ሲያስረዳ፣ የአዲስ አበባ መተዳደሪያ ቻርተር ከንቲባው የከተማዋን ፖሊስ የእለት ተእለት እንቅስቃሴ የመቆጣጠር ኃላፊነት እንዳለበት ስለሚደነግግ ከንቲባውን በቀጥታ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል ብሏል፡፡ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ የፓርቲው አመራሮችና አባላት በጅምላ በፖሊስ ታስረው መዋላቸውን ፓርቲው ጠቅሶ፣ የቅስቀሳ ቁሳቁስ ተነጥቀናል፤ ፖስተሮችን እንዳንለጥፍ ተከልክለናል ብለዋል። የፖሊስን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ የመከታተል ሃላፊነት የተጣለባቸው ከንቲባውና ኮሚሽነሩ፣ የፖሊስን ህገወጥ ተግባር በቸልታ አልፈውታል ብሏል – አንድነት ፓርቲ፡፡ “በቂ ማስረጃ ከተደራጀ በኋላ ነው ወደ ክስ የሄድነው” ያሉት የፓርቲው አመራሮች፤ ክሱን የመሰረቱት ጠበቃ ተማም አባቡልጉ እና ረዳታቸው መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ከንቲባውና ኮሚሽነሩ የካቲት 24 ቀን መልሳቸውን ካቀረቡ በኋላ መጋቢት 2 ቀን ክርክር ይካሄዳል ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ፍ/ቤት የለም ብለው እንደሚያምኑ የተናገሩት የፓርቲው መሪዎች፤ የመንግሥት አካላት የሚፈፅሙትን አፈና በይፋ ወደ ፍ/ቤት በመውሰድ የፍትህ ስርአቱን መፈተንና ለህዝብ ማጋለጥ አንዱ የትግል አላማችን ነው ብለዋል፡፡ ከሰኔ እስከ ነሐሴ 2005 ለ3 ወራት፣ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል በመላ አገሪቱ የተደረጉት ሰላማዊ ሰልፎችና ህዝባዊ ስብሰባዎች ህዝብን በማነቃቃት ስኬታማ ውጤት አግኝተንባቸዋል ሲሉ የፓርቲው መሪዎች ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል፤ በፀጥታው ኃይል እና በገዢው ፓርቲ ካድሬ መካከል ልዩነት አለመኖሩን አይተናል፤ በአገሪቱ በተዘረጋ የአፈና መዋቅር ከፍተኛ የህግ ጥሰት እንደሚፈፀም አረጋግጠናል ያሉት የፓርቲው መሪዎች፤ የመንግስት ጫና ሳያሸብረው ፓርቲው ተመሳሳይ ንቅናቄዎችን በተከታታይ ያዘጋጃል ብለዋል፡፡ “የፀረ-ሽብር አዋጁን ለማሰረዝ የሰበሰባችሁትን ድምፅ የት አደረሳችሁት” የሚል ጥያቄ ከአዲስ አድማስ የቀረበላቸው አመራሮቹ፤ “የተሰበሰበውን የህዝብ ድምፅ ወደ ፍ/ቤት ለመውሰድ የህግ ባለሙያዎች እየመከሩበት ነው፣ በሁለተኛ ዙር የክስ ሂደት ውስጥ የሚካተት ይሆናል ብለዋል፡፡ በተካሄደው የ3 ወር የህዝብ ንቅናቄም መንግሥት ለጉዳዩ ይበልጥ ትኩረት እንዲሰጥ ፓርቲው ጫና ማሳረፉን የሚያመለክቱ ውጤቶች መታየት መጀመራቸውን የጠቀሱት የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው፤ የፀረ-ሽብር አዋጁ ከመፅደቁ በፊት ለህዝብ ውይይት መቅረብ ሲገባው አዋጁ ወጥቶ ብዙዎችን ሰለባ ካደረገ በኋላ መንግስት ራሱን ለመከላከል የፕሮፖጋንዳና የስልጠና ዘመቻ ጀምሯል ብለዋል፡፡ ይህም ፓርቲያቸው ይዞት የተነሳው ጥያቄ ጫና ማሳረፉንና ትክክለኛ እንደነበር የሚያረጋግጥ መሆኑን አቶ ሃብታሙ ገልፀዋል፡፡ “ማንም ሰው ወይም አካል ከህግ በላይ ሊሆን አይችልም” ያለው ፓርቲው፤ ህግ በሚጥሱ የመንግስት አካላት ላይ በተከታታይ ክስ እመሰርታለሁ፤ በቅርቡም በመንግሥት ከፍተኛ አመራሮችና በገዢው ፓርቲ ላይ ተጨማሪ ክስ ለመመስረት እየተዘጋጀሁ ነው ብሏል፡፡

Wednesday, 5 February 2014

ወያኔ: የነፃው ፕሬስ ፀር!

ነፃ- ፕሬስ ለነፃነት፤ ለፍትህና ለእኩልነት የሚኖረውን አስተዋፅኦ የሚገነዘቡ ገዢዎች ፕሬሱ ለአንባገነንነት አገዛዛቸው የሚመች ስለማይሆን ይፈሩታል፤ ይጠሉታል፤ ያጠፉታል። ወያኔም እያደረገ ያለው ይህንኑ ነው። ነፃ ፕሬስ የሀሳብ ነፃነት መብት አልፋና ኦሜጋው ነው ብል ማጋነን አይሆንም። የነፃ ፕሬስ መኖር የሚያረጋግጠው ጋዜጠኞች ያለምንም ጭንቀትና ፍርሃት የሚያስቡትን፡ የሚሰማቸውን፡ የሚሰሙትን እንዲሁም ምርምር አድርገው የደረሱበትን ዜናዎች በነፃ ለመፃፍና ለማሰራጨት ብሎም ሕዝብ እንዲወያይበት ለማድረግ ያላቸው ያልተገደበ መብት ነው። ይህም ጤናማ ሕብረተሰብ ለመፍጠር ብቻ ሳይሆን ለእድገቶቹም ጉልህ ድርሻ አለው። ነፃ ፕሬስ የኃሳብ ነፃነት ተግባራዊ ለመሆኑ ዋስትናም መፈተኛም ነው። ኃሳብን ያለምንም ጭንቀትና ፍርሃት በነፃ ለመግለፅ መቻልና መለዋወጥ እንደ ምግብና መጠጥ፤ ሁሉ ሰብአዊ ክቡርነትን የተላበሰ ሕይወት ለመጎናፀፍም አስፈላጊም ናቸው። ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት መኖርና ዋስታናው ዴሞክራሲያዊ በሆነ ሕግ መረጋገጥ ማለት ዘላቂነት ላለው ዴሞክራሲያዊ እድገት ለማገኘትም ዋና መሰረት ነው። የተሳካ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት የነፃ ፕሬስ አስፈላጊነት ትልቅ ቦታ እንዳለው ከልብ ይታመናል፡፡ ያለነፃ ፕሬስ ዴሞክራሲ አለ ብሎ መናገር ማወናበድ እንጅ እውነት ሊሆንም አይችልም፡፡ የነፃ ፕሬስ መኖር በራሱ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት መኖር መገለጫ ነውና፡፡ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ሲኖርም ነፃ ፕሬስ ይኖራል፡፡ ወደ እኛ ሃገር ስመለስ ግን ነገሮች ሁሉ የተገላቢጦሽ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ወያኔ መንግስት ሆኖ ላለፉት 23 ዓመታት ሃገሪቱን ሲያስተዳድር ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን በወረቀትና በቃል እንጂ ከዚያ በዘለለ በተግባር ሲፈፅም አላሳየንም፡፡ ለመተግበር የሞከራቸውንም እንደ ቀንዳውጣ ቀንድ መልሶ ሸሽጎታል፡፡ ስለዚህ በዴሞክራሲያዊ ስርዓት የማያምን አምባገነን ስርአት ስለሆነ ለነፃው ፕሬስ ፀር በመሆን ተገቢውን ጥበቃና እንክብካቤ በመስጠት ፋንታ አጥፊና ደምጣጭ ሆኖ እየሰራ ይገኛል። ዛሬ በዘመነ ወያኔ በኢትዮጵያችን ነፃ ፕሬስ በአሳሪና አስፈሪ የፕሬስ አዋጅ ተጠፍሯል። ጋዜጠኞች ሰበብ አስባብ እየተፈለገ በየፍርድ ቤቱ እየተጎተቱ ነው። ወደ እስርቤት እየተጣሉ፤ እየተሰደዱም ነው። የጋዜጣ፣ የመጽሔት፣ የመጻሕፍት ማሳተሚያ ዋጋ ሰማይ ጠቅሷል። በሀገሪቱ ሕገመንግሥት ቀርቷል የተባለ ቅድመ ምርመራ (ሳንሱር) በብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት ጓሮ በኩል በእጅ ኣዙር ተመልሶ እንዲመጣ ተደርጔል። ሌሎች በከተማው ያሉ ማተሚያ ቤቶችም ሳንጃ የተከለ ጠመንጃ ወድሮ የሚያስፈራራ ኃይል ያለባቸው ይመስል “የተቃዋሚ ጋዜጣን አናትምም” ብለዋል። በቅርቡ በሰማያዊ ፖርቲ ‘‘ነገረ ኢትዮጵያ’’ ጋዜጣ ላይ የተሰተዋለው ችግር ይሄው ነው። ጋዜጣዋ ተዘጋጅታ ለማተምያ ቤት ብትበቃም ስርአቱ በፈጠረው የማደናቀፍ ተንኮል ለህትመት ሳትበቃ በመቅረቷ በፓርቲው ቀና ትብብር በድህረ ገፃቸው እንድናገኛት ተገደናል። ማተሚያ ቤቶች ሠርቶ የማትረፍና ሀብት የመፍጠር ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን እንዲሁም ሕዝብን የማገልገል ግዴታቸውን በፍርሀት ጨርቅ ገንዘው በየማተሚያ ቤታቸው ጓሮ ቀብረውታል። የሕዝብ ንብረት የሆኑ፣ በሕዝብ ሀብት የሚተዳደሩ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ሃያ አራት ሰዓት በወያኔ በሞኖፖል ተይዘዋል፡ የገዥው ልሳን ብቻ መሆናቸውንም አስመስክረዋል። ሌሎችም የተለያየ ስም እየተሰጣቸው በአየር ላይ አለን የሚሉ ጣቢያዎች ልሳናቸው የበዛ ቢመስልም ከሞላ ጎደል ቋንቋቸው አንድ ነው። ያ ቋንቋ ግን የእውነተኛ ነፃ ፕሬስ ቋንቋ አይደለም። በዚህ ዓይነት የፕሬስ ሁኔታ በሀገራችን ዴሞክራሲ ሊኖር አይችልም። negere ethiopiaይህ ነፃ ፕሬስን ማቀጨጭ ብሎም ለመቃብር ማብቃት ደግም በአለም ላይ በስፋት እንደታየው የአምባገነን መንግስታት መለዬ ካባ ነው። አምባገነኖች የሚገዙትን ህዝብ ለመቆጣጠር ከሚወስዷቸው እርምጃዎች ቀዳሚው ፕሬስን መቆጣጠር ነው። በጉልበት የሚገዙት ህዝብ እነሱ ከሚሉት ውጭ እንዳይሰማ ለማድረግ ወደ ህዝብ ጆሮ የሚደርሱትን ነገሮች ሁሉ የመቆጣጠር ተግባር ይፈጽማሉ። ከዚህም በተጨማሪ ውሸትን ደጋግሞ በማውራት እውነት ለማስመሰል ይተጋሉ። ይህ የአምባገነን ሥርዓቶች ሁሉ የጋራ ባህርይ ነው። ስለዚህ ወያኔም ነፃ ፕሬስን የሚፈራበት ትልቁ ምክንያት በኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት አምባገነንነቱንና የጥፋት ተልዕኮ ሚናውን አጋልጠው በሕዝብ እንዲተፋ ማድረጋቸውን በሚገባ ስለሚያውቅ ነው። ይህም ብቻ አይደለም። ነፃ ፕሬሶች ወያኔን ከሥልጣን ለማስወገድ በሚደረገው ሕዝባዊ ትግል የሚያበረክቱት አስተዋፅዖ ከፍተኛ መሆኑን በማወቁ ጭምር ነው። ወያኔ ለሙያቸው ክብር ያላቸው ጋዜጠኞችን በክሶች ብዛት፤ በእስርና እንግልት እንዲሁም ከአቅማቸው በላይ በሆነ የገንዘብ ቅጣት እንዲሸማቀቁ በማድረግ እውነት ዘጋቢ ስታጣ የኢትዮጵያ የመረጃ አየር በውሸት የተሞላ እንዲሆን አድርጎታል። ወያኔ በፈለገው መልክ ሊተረጉመው በሚችለው አንቀጽ ጋዜጠኞችን እያስፈራራና እያዋከበ ሀሳብን በነጻ የመግለጽ ነፃነት መብትን ይኸው እስካሁን ድረስ እንዳፈነ ይገኛል። ወያኔ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ በኢትዮጵያ ለታሰሩ፥ ለተገደሉ፥ ለስደት ለተዳረጉ በርካታ ጋዜጠኞች ዋና ተጠያቂ ነው። የእስራት ፍርድ ተፈርዶባቸው በመማቀቅ ላይ የሚገኙ አሁንም በርካታ ናቸው። የተወሰኑትም ደግሞ ደብዛቸው እንዲጠፋ ተደርገዋል። በአገር ውስጥ የሚገኙ የመረጃ መረቦችን በማናለብኝነት ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር፤ ከውጭ አገራት የሚተላለፉ የሬድዮና የቴሌቪዥን ሞገዶችን በይፋ በማፈን ኢትዮጵያ አገራችን በመረጃ ከዓለም የተነጠለች ደሴት ለማድረግ ተግቶ እየሰራ ይገኛል፤ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ሃብትንም ለዚህ እኩይ ስራው ያባክናል። ነፃ-ፕሬስ ለነፃነት፤ ለፍትህና ለእኩልነት የሚኖረውን አስተዋፅኦ የሚገነዘቡ ገዢዎች ፕሬሱ ለአንባገነንነት አገዛዛቸው የሚመች ስለማይሆን ይፈሩታል፤ ይጠሉታል፤ ያጠፉታል። ወያኔም እያደረገ ያለው ይህንኑ ነው። በመጨረሻም ወያኔ የነፃ ፕሬስ ጠላትነቱን ያረጋገጠው ሥልጣን እንደጨበጠ በመሆኑ ላለፉት 23 አመታት አንድን አፋኝ ሕግ በሌላ አፋኝ ህግ እየተካና እያጠናከረ የነፃ ፕሬስ ፀር መሆኑን ያስመሰከረ በኢትዮጵያ ላይ የመጣ መቅሰፍት ነው። ስለዚህ ለእውነት የቆመ ነፃ ሚዲያ መወለድና ማበብ በአገራችን እንዲኖር ለምንሻው ዲሞክራሲ የመሰረት ድንጋይ መሆኑን በማመን፤ ለእውነት የቆሙ ነፃ ፕሬሶች እንዲፈጠሩ መታገል የሁላችንንም ርብርብ የሚጠይቅ ሃላፊነት መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል። ራሷ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ያለ ነፃ ፕሬስ ማሰብ አይቻልምና:: መረጃ የተጠማው የኢትዮጵያ ህዝብም ነፃ የሚዲያ ተቋማት እንዲፈጠሩና እንዲጠናከሩ እንቅፋት የሆነውን የአንባገነኑን የወያኔ አገዛዝ ከጫንቃው ለማውረድ በጋራ መታገል ይኖርበታል። በተጨማሪም ነፃ ፕሬስ ለሃገራችን ሁለንተናዊ እድገት የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ በመረዳትና፤ መብትም በትግል እንደሚገኝ በማመን የፕሬስን ነፃነትን ለማምጣት በአንድነት በመነሳት እንቅፋት የሆነውን አገዛዝ በቃህ ልንለው ይገባል። በመረጃ የዳበረ ህዝብ አንባገነኖችን ቀባሪ ነው!

Tuesday, 4 February 2014

ESAT MY

https://www.facebook.com/photo.php?fbid=249629698541293&set=pcb.249630991874497&type=1&theater

Saturday, 1 February 2014

በጎንደር ክ/ሃገር ሳንጃ ወረዳ የልዩ ሃይል አዛዥ ሻለቃ ቀለሙ ክብረት መገደላቸው ተሰማ

(ዘ-ሐበሻ) በጎንደር ክ/ሃገር ሳንጃ ወረዳና አካባቢው ሕዝብን ሲያሰቃይ ነበሩ የተባለት የልዩ ሃይል አዛዥ ሻለቃ ቀለሙ ክብረት መገደሉ ተሰማ። የአርበኞች ግንባር ለግድያው ሃላፊነቱን ወስዶ “ግለሰቡ የተገደለው በጥር 21-2006 ዓ.ም ከቀኑ 12 ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰርጎ ገቦች ማሰሮ ደንብ የተባለ ቦታ በጥይት ተደብድቦ ቆስሎ ወዲያውኑ ወደ ጎንደር ቸቸላ ሆስፒታል ቢወሰድም በማግስቱ ማለትም በጥር 22-2006 ዓ,ም ህይወቱ አልፏል።” ብሏል።
(የአርበኞች ግንባር ወታደር – ፎቶ ፋይል) እንደ አርበኞች ግንባር ገለጻ ከሆነ “ይህ ግለሰብ በወረዳው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የአርበኞች ደጋፊ ናችሁ በሚል ሲያሰቃይ የነበረ ሲሆን፣ ብዙ ንፁሃን ግለሰቦችን በድርጅቱ ደጋፊነት ስም እየፈረጀ እንደገደለ፣ እንዳሰረና እንዲሰደዱ ሲያደርግ የነበረ መሆኑ ይታወቃል ። ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ግለሰቡ ከድርጊቱ ታቅቦ ሰላማዊ ኑሮውን እንዲኖር ካልሆነ ግን አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድበት የፅሁፍ መልዕክት የደረሰው ቢሆንም ሊታረም ባለመቻሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰርጎ ገቦች እርምጃ እንዲወስዱበት ተደርጓል።” ብሏል።
(የአርበኞች ግንባር ሠራዊት በምረቃ ላይ – ፎቶ ከፋይል) “በጎንደር አካባቢ ምንም አይነት ወታደራዊ እርምጃ በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት ሲወሰድ የአካባቢውን ሕዝብ ማንገላታቱ የተለመደ ቢሆንም ሻለቃ ቀለሙ ክብረት ከሞተበት ከትናንት ጀምሮ ግን በህዝቡ ከፍተኛ ስቃይ እያደረሰበትና ገዳዮቹን ታውቃላችሁ እናንተ ናችሁ እየደበቃችሁና ቀለብ እየሰፈራችሁ የምታስጨርሱን በሚል ብዙ ሰዎች እንደታሰሩ ታውቋል።” የሚለው የአርበኞች ግንባር ዜና “የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ወታደራዊ መምሪያ በበኩሉ ወደፊትም ቢሆን ወያኔና ተላላኪዎቹን ከዚህም በከፋ ሁኔታ አይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጣ አስታውቆ ሕዝቡም ከመሬቱና ከንብረቱ እየተፈናቀለ መኖሩ ያበቃ ዘንድ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ጎን በመሰለፍ ይህን አፋኝ ስርዓት ለመገርሰስ የበኩሉን አስተዋፅዖ ማበርከት እንዳለበት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን” ብሏል። በዚህ ዜና ዙሪያ የመንግስትን ምላሽ ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። http://www.zehabesha.com/amharic/archives/12396