Thursday, 30 January 2014

የኢትዮጵያ መንግስት የግንቦት7 መሪዎችን ኮምፒዩተሮች በዘመናዊ የስለላ መሳሪያዎች ሲሰልል እንደተደረሰበት አንድ አለማቀፍ ተቋም አጋለጠ

ጥር ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህዝቦችን ደህንነት ከመንግስታት ጥቃት ለመከላከል የተቋቋመው ፕራይቬሲ ኢንተርናሽናል የተባለው ተቋም ለእንግሊዝ መንግስት የገቢዎቸና ጉምሩክ መስሪያ ቤት በጻፈው ደብዳቤ “ጋማ ኢንተርናሽናል የተባለው የእንግሊዝ ኩባንያ በአለም ላይ የሰብአዊ መብቶችን በመጣስ ለሚታወቁ አገሮች ኮምፒይተሮችን፣ የሞባይልና የስካይፕ የስልክ ግንኙነቶችን እንዲሁም የኢሜል ልውውጦችን በርቀት ሆኖ ለመከታተል የሚያስችለውን ፊን ፊሸር ወይም ፊን ስፓይ በሚል ስም የሚጠራውን የመሰለያ መሳሪያ ከአውሮፓ ህብረት ውጭ ላሉ አገሮች በመሸጥ ዜጎች እንዲሰለሉና ደህንነታቸው አደጋ ላይ እንዲወድቅ በማድረጉ ምርመራ እንዲጀመር” ሲል ጠይቋል። የግንቦት7 ከፍተኛ አመራር በሆኑት በ ዶ/ር ታደሰ ብሩ የግል ኮምፒዩተር ላይ የመሰለያ ቫይረሱ መገኘቱን በቶሮንቶ ዩኒቨርስቲ የሙንክ ስኩል ግሎባል አፌርስ የምርምር ተቋም የሆነው ሲትዝን ላብ ማረጋገጡን ፕራይቬሲ ኢንተርናሽናል በደብዳቤው ገልጿል። የመሰለያ መሳሪያው የሰብአዊ መብቶችን በሚጥሱ 36 አገራት ላይ መሸጡን የገለጸው ፕራይቬሲ ኢንተርናሽናል፣ በተለይም በቬትናም፣ ማሌዚያና ኢትዮጵያ የፖለቲካ ተቀናቃኞችን ለመሰለያነት እየዋለ ነው ብሎአል። በኢትዮጵያ የግንቦት7 ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶ/ር ታደሰ ብሩ ኮምፒተራቸው ሲሰለል መቆየቱን የገለጸው ፕራይቬሲ ኢንተርናሽናል፣ በአንድ የብሃሬን የሰብአዊ መብት ተማጓች ኮምፒዩተር ላይም ተመሳሳይ የስለላ ሶፍት ዌር መገኘቱን ገልጿል። ዶ/ር ታደሰ ብሩ ለፕራይቪሴ ኢንተርናሽናል ጠበቃ የምስክርነት ቃላቸውን መስጠታቸውን ተናግረዋል። ፕራይቪሲ ኢንተርናሽናል የስለላ ቫይረሱን የሸጠውን ጋማ ኢንተርናሽናልን የተባለውን ድርጅት ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድ ማቀዱን ዶ/ር ታደሰ ገልጸዋል፡ ከዶ/ር ታደሰ ጋር የተደረገው ቃለምልልስ ከዜናው በሁዋላ ይቀርባል።

Wednesday, 29 January 2014

መንግስታት ፈለጉት ኣልፈለጉት በኤርትራና በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል ለወደፊት ትውልዶች የሚቀጥል የመዋሃድ ዝምድና መኖር ኣለበት” ኢሳያስ ኣፈወርቂ

ኣቶ ኢሳያስ ኣፈወርቂ ከኣሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ጣቢያ ያማርኛው ክፍል ከጋዜጠኛ ኣዳነች ፍስሃየ ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ ጋዜጠኛ ኣዲሱ ኣበበ፥ እየተገባደደ የነበረውን የኣውሮጳውያን የ1992 ዓ.ም. ምክንያት በማድረግ በተገባደደው ዓመት ከተከስቱ ጉዳዮች መካከል ዋና ዋናዎቹን ሲያስተናግድ፤ “1993 ዓ.ም. ላይ ደርሰናል፤ እንደ ኣውሮጳ ኣቆጣጠር። ኣቶ ኢሳያስ ኣፈወርቂ ስለ ኤርትራ ሬፈረንደም፥ ማለትም ህዝበ ውሳኔ፥ ይህን ብለው ነበር።” በሚል መክፈቻ የስራ ባልደረባው የሆነቺው ጋዜጠኛ ኣዳነች ፍስሃየ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ኣፈወርቂ ጋር ቀደም ሲል በድምፅ ያደረገችውን ቃለመጠይቅ ይለቃል። ጋዜጠኛ ኣዳነች ፍስሃየ፤ በግዴታም ይሁን በውዴታ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ተሳስስራ ቆይታለች። እና፥ እንግዲህ፥ የነፃነት ጥያቄ፥ የመገንጠል ጥያቄ ከማን? የሚለው [መልሱ] ከኢትዮጵያ ነው። እንግዲህ፥ [ኤርትራ] ከኢትዮጵያ ጋር ተሳስራ ስለቆየች። እና፥ ይህ የሬፈረንደሙ ነጥብ ራሱ ምንድንነው የሚለው፤ “ነፃነት ትፈልጋለህ? ኣዎን ወይም ኣይደለም” ዓይነት ነው። እና፥ ለምንድነው እንደዛ የጠበበው? ትንሽ ሰፋ ብሎ ወይም ደግሞ ከኢትዮጵያ ጋር ኣንድነት ወይም ኮንፌደረሽን ወይም ፌደረሽን ወይም ሰፋ ያለ የራስ ገዝ ኣስተዳደር ወይንስ ነፃነት ነው የምትመርጠው? በሚል ሰፋ ባለ ይዘት ለምን ኣልቀረበም? ፕሬዚዳንት ኢሳያስ፤ በመጀመሪያ ኤርትራ ከኢትዮጵያ እየተገነጠለች ነው የሚለውን ጥያቄ እኛ በበኩላችን ከመጀመሪያውም ኣልተቀበልነውም። የምንቀበለው ነገርም ኣይደለም። በኛ ኣስተያየት ጥያቄው ምንደንነው? ህጋዊ ያልሆነ ጋብቻ ወደ ፍች በሚያመራበት ወቅት ወደ ህግ መልሶ ለማረጋገጥ የሚቻል ኣይመስለኝም። የኤርትራ ህዝብ ከኢትዮጵያ ጋር ስለመዋሃዱ ጉዳይ በህጋዊ መንገድ የተደረገ ኣልነበረም። ስለዚህ ለኤርትራዊያን የሚቀርበው ጥያቄ ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ትፈልጋለህ? ወይንም ኣትፈልግም? የሚል ሳይሆን፥ ነፃ ኣገር እንድትሆን ትፈልጋለህ? ኣትፈልግም? የሚለው መሆኑ ባህሪያዊ የሆነ ነገር ይመስለኛል። ይህ ማለት ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ትጠላዋለህ፥ ኣትወደውም፥ ከኢትዮጵያ ጋር ዝምድና የለህም፥ ኣይኖርህምም ማለት ኣይደለም። ጋዜጠኛ ኣዳነች ፍስሃየ፤ ያኔ፥ ጋዜጣዊ መግለጫ በተደረገበት ጊዜ፥ የኤርትራ ህዝብ ወይም መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር የኤኮኖሚ ውህደት ወይም ኢንቲግሬሽን እንደሚፈልግ፥ ከዛም ኣልፎ እንዳውም እስከ በኮንፌደርሽን የመዋሃድ ደረጃ ሊደርስ እንደሚችል ጠቅሰው ነበረ። እና ይህ ኣባባል ምን ያህል እውነትነት ኣለው? ምን ያህልስ የሚገፋበት ነገር ይመስለዎታል? ፕሬዚዳንት ኢሳያስ፤ ከዚያም በኋላ ደጋግሜ እንደገለፅኩት ሁሉ፥ ጥያቄው ስለቀረበ፥ ለረጅም ጊዜ በቆየው ኣመለካከታችን መሰረት በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ለያድግ ስለሚችል ዝምድና በሚመለከት ጭንቅላታችን ምን ጊዜም ቢሆን ክፍት ነው። በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ሊኖር ስለሚችል ማንኛውም ዓይነት ገንቢ መረዳዳት ገደብ የሚደረግበት ነገር ኣይሆንም። በኮንፌደረሽን መዋሃድ የሚፈለግ ከሆነ፥ ለምን ኣይሆንም እንላለን። መንግስታት ፈለጉት ኣልፈለጉት በኤርትራና በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል ለወደፊት ትውልዶች የሚቀጥል የመዋሃድ ዝምድና መኖር ኣለበት። በፍላጎትና በምኞት ላይ ብቻ ሳንወሰን በተጨባጭ ወደ መዋሃድ ወደሚያመሩን እቅዶች መግባት ኣለብን። እንዲህ ሲባልም ምንልባት ኣንዳንዶቹ፥ እነዚህ ችጋራሞች የሚበላና የሚጠጣ ስለሌላቸው ሊጠቀሙብን ፈልገው ነው ኣሁን ውህደት የሚሉት፤ ለጥቅማቸው ሲሉ ነው፤ ይሉ ይሆናል። ይህ ግን ገንቢ ኣይሆንም።” ታሪካዊ ምክንያቶች በመነሳት የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብ ኣንድነት ከራሳችን ኣልፎ ለኣካባቢያችንና ለመላው ኣፍሪካ የሚሰጠውን ጠቀሜታ በውል በመገንዘብ የኢትዮጵያና የኤርትራ ፌደራላዊ ኣስተዳደር እንድንመሰርት ያለንን ፍላጎት ቀደም ኣድርገን ለወያነ መንግስት ኣቅርበናል። የወያነ መንግስት በማናውቀው ምክንያት ሃሳባችንን ካለመቀበሉም ሌላ ይህንን ሃሳብ ካቀረብንበት ጊዜ ኣንስቶ በሁለቱም ኣገሮች ለነበረው መልካም ግኑኝነት ሳንካ ለመፍጠር እንደተንቀሳቀሰ ኣስተውለናል። ለወደፊትም ቢሆን ስርዓት በተከተለና ኣግባብ ባለው መንገድ ከህዝባችን ጋር መክረን በህዝባችን ፍላጎትና ውሳኔ ተመስርተን ይህንኑ ሃሳብ የምናራምድ መሆናችንን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን። · በብሄር ከተደራጁ ድርጅቶች ብቻ ግንኙነት ታደርጋላችሁ ለተባለው ቅስቀሳው የወያነ ቅስቀሳ ከመሆኑ ባሻገር ትክክለኛ መረጃ ኣይደለም። እኛ የምናደርገው ግንኙነት ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብና በብሄርም ሆነ በህብረ-ብሄራት ከተደራጁ ድርጅቶች ጋር እንደሆነ ለማንም ግልፅ ሊሆንለት ይገባል። ከዚህ ውጭ ኣንተ በብሄር ኣንተ ደግሞ በህብረ-ብሄር ተደራጅ እያልን መመሪያ የመስጠት መብት የለንም። ድርጅቶች በህብረት እንዲሰሩ ለማድረግ ሙሉ ፍላጎታችን ቢሆንም እጅ ኣየጠመዘዝን ድርጅቶችን እንዲያብሩ ማድረግ ግን በድርጅቶቹ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ከመሆኑም በላይ ስራው የኢትዮጵያዊያኖች እንጂ የኛ ሊሆን 11 ኣይገባም። የኛ ዕቅድና ፍላጎት ኢትዮጵያን ለመበተን ቢሆን ኖሮ በደርግ ውድቀት ማግስት ልናደርገው እንችል ነበር። የተበታታነች ኢትዮጵያ ደግሞ ለራሷ ብቻ ሳይሆን ለኛም ጠንቅ እንድምትሆን ኣጠያያቂ ኣይደለም። እኛ ግን በተቃራኒው በሽግግሩ ጊዜ በኢትዮጵያ መረጋጋት እንዲሰፍን ያበረከትነው ኣስተዋፅኦ ወዳጅም ጠላትም በሚገባ ያውቀዋል። በኢትዮጵያ መበታተን የኤርትራ ህዝብ ተጠቃሚ ይሆናል ብሎ የሚያስብ ካለ የታመመ ሰው ብቻ መሆን ኣለበት። ስለዚህ ወያነ ለራሱ ህልውና ሲል የሚለፍፈውን የውሸት ፕሮፓጋንዳ ሰለባ ከመሆን በመታቀብ ታጋይ ኢትዮጵያዊያንና ባጠቃልዩም የኢትዮጵያ ህዝብ የኤርትራ ችግር የተከሰተበትን ምክንያትና ለሰላሳ ዓመታት ያህል የተካሄደው ትግል ምንነት በማጤን ሁላችንም ከስህተቶቻችን ተምረን ስህተቶች እንዳይደገሙ በውይይትና በመግባባት ህዝባችንን ለተሻለ ህይወት ለማብቃት ከመታገል ሌላ ኣማራጭ የሌለን መሆኑን ጠንቅቀን ማወቅ ይገባናል። · በኢትዮጵያ ውስጥ ኣሳሳቢ ችግር ያለ መሆኑን እንገነዘባለን። ችግሩን በሚገባ ተረድቶ ዘላቂ መፍትሄ መሻት ደግሞ የሁላችን ተሳትፎ እንደሚጠይቅ እናምንበታለን። ኣሁን የገባንበት የኢትዮጵያና የኤርትራ ችግር በኣንድ ተጨባጭ ፎርሙላ ማስተካከል ከተቻለ ደግሞ ሌላው የውስጥ ችግር ህይወት ኖሮት ሊቀጥል ስለማይችል ወዲያውኑ እንደሚፈታ ለመገንዘብ ኣስቸጋሪ ኣይደለም። ስለሆነም ችግሩ በተናጠል የኢትዮጵያ የውስጥ ችግር ተብሎ የሚቀርብ ሳይሆን የጋራ ችግር መሆኑን ተረድተን መፍትሄውን በጋራ ለማስገኘት በኤርትራ መንግስትና ህዝብ በኩል ይህ ቀረው የማይባል ትብብር እንዳለና ለወደፊቱም በዚሁ እንደሚቀጥል ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።

Sunday, 26 January 2014

የወያኔ የውሸት ዘገባዎች ሲጋለጡ

“ኦክስፋም” በመልካም ሥራቸው ከታወቁ ትላልቅ ዓለም ዓቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አንዱ ነው። በቅርቡ አንድ መቶ ሀያ አምስት አገሮችን ያካተተ ከምግብ አቅርቦትና አጠቃቀም ጋር የተያያዘ ጥናት ውጤት ይፋ አድርጓል። ጥናቱ አራት ዝርዝርና አንድ አጠቃላይ አመላካቾች አሉት። 1. አመላካች አንድ: የምግብ እጥረት ይህ አመላካች “በየአገሮቹ ምን ያህል ለበላተኛው የሚበቃ ምግብ አለ?” የሚለውን ይለካል። በጥናቱ ውጤት መሠረት በምግብ እጥረት እጅግ የተጎዱ የመጨረሻዎቹ አስር አገሮች የሚከተሉት ናቸው: – ቡሩንዲ፣ የመን፣ ቻድ፣ ኢትዮጵያ፣ ማዳጋስካር፣ ናይጄሪያ፣ ላኦስ፣ ባንግላዴሽ፣ መካከለኛዉ አፍሪካ ሪፑብሊክ እና ህንድ። ኢትዮጵያ አገራችን ከመጨረሻ አራተኛ ናት። 2. አመላካች ሁለት: ለምግብ የመክፈል አቅም (Affordability) ይህ አመላካች “የአገሩ ሕዝብ በአገሩ ዋጋ ምግብ ገዝቶ ለመብላት ምን ያህል አቅሙ ይፈቅድለታል?” የሚለውን የሚመልስ ነው። አሁንም ከመጨረሻ እንጀምር። አንጎላ፣ ዚምባቡዌ፣ ቻድ፣ ጉያና፣ ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ፣ ኮንጎ፣ ኬንያ፣ ጋምቢያ እና ኢራን የየአገሩ ሕዝብ ምግብ መሸመት የሚቸገሩባቸው አገሮች ናቸው። አገራችን ኢትዮጵያ ከመጨረሻ አምስተኛ ናት። 3. አመላካች ሶስት: የምግብ ጥራት ይህ የምግብ ይዘትንና የአያያዝ ንጽህናን የሚመለከት ሲሆን ኢትዮጵያ፣ ማዳጋስካር፣ሞዛምቢክ፣ ቻድ፣ ቶጎ፣ ዛምቢያ፣ ማሊ፣ ናይጄሪያ፣ ባንግላዴሽ፣ ሌሶቶ ከመጨረሻው እስከ አስረኛ ደረጃ ይዘዋል። ኢትዮጵያ በምግብ ጥራት የመጨረሻዋ አገር ናት። 4. አመላካች አራት፡ የሰውነት ውፍረት እና የስኳር በሽታ ይህ አመላካች ከልክ ያለፈ ውፍረት ዓለም ዓቀፍ የጤና ችግር እየሆነ በመምጣቱ የገባ አመልካች ነው። ኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥሩ ውጤት ያመጣችሁ በዚህ አመላካች ብቻ ነው። ኢትዮጵያ አብዛኛው ሕዝቧ ቀጫጫ ነው፤ የስኳር በሽታም እንደሌላው አገር የተስፋፋባት አገር አይደለችም። 5. አማካይ ውጤት የእነዚህ አራት አመላካቾች ድምር ውጤት አጠቃላይ ውጤትን ይሰጣል። በአጠቃላይ ውጤት: ቻድ፣ ኢትዮጵያ፣ አንጎላ፣ ማዳካስካር፣ የመን፣ ቡሩንዲ ናይጄሪያ፣ ሞዛምቢክ፣ ዚምባቡዌ፣ ሴራሊዮን ከመጨረሻ እስከ አስረኛ ወጥተዋል። ኢትዮጵያ ከመጨረሻ ሁለተኛ ነች። ይህ ምንን ያመለክታል? ወያኔ ባለፉት አስር ዓመታት በተከታታይ ከ11% በላይ ኢኮኖሚውን አሳድጌዋለሁ ሲለን ነበር። እድገቱ ያተኮረው ገጠር፤ ምንጩም ግብርና ነው ብሎን ነበር። ሐቁ ግን ከላይ የተመለከተው ነው። እርግጥ ነው የወያኔ ሹማምንት በከተሞች ሕንፃዎችን ይገነባሉ፤ በገጠሮች በመቶዎች ሄክታር የሚለካ ለም መሬት ይዘው ፈጣን ገንዘብ በሚያስገኙ የአበባ፣ የጫትና የቃጫ ምርት ላይ ተሰማርተዋል። ከራሳቸውም አልፈው ሀብታም የውጭ አገራት ሸሪኮቻቸውን በአገራችን ለም መሬት ይበልጥ ያበለፅጓቸዋል። የእነሱ የግላቸው፣ የቤተሰቦቻቸው፣ የዘመዶቻቸው እና የሸሪኮቻቸው ኢኮኖሚ እየተመነደገ መሆኑን እናውቃለን። ይህን በገዛ ዓይኖቻችን የምናየው ሀቅ ነው። ሆኖም ግን የእነሱ ኢኮኖሚ ማደግ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማደግ አለመሆኑ እናውቃለን። አገራችን ከጓረቤት አገሮች ጋር ስትነፃፀር ወደ ኋላ እየቀረች መሆኑ ያንገበግበናል። በቅርቡ አክስፋም በጥናት ያረጋገጠዉ የኢትዮጵያ ገበሬዎች በየቤታቸው ከወዳጆቻቸው ጋር በምስጢር የሚያወሩትን እውነት ነው። ከሳምንት በፊት ደግሞ “ኢኮኖሚክ ኢንተለጀንስ ዩኒት” የተሰኘው ታዋቂ የምርምር ተቋም አንድ የጥናት ውጤት ይፋ አድርጎ ነበር። በዚህ የጥናት ውጤት መሠረት በዓለም በከፍተኛ ፍጥነት እያደጉ ያሉ አስር አገሮች በቅደም ተከተል ሞንጎሊያ፣ ሴራሊዮን፣ ቱርክሜንስታን፣ ቡታን፣ ሊቢያ፣ ኢራቅ፣ ላኦስ፣ ቲሞር-ሊስቲ፣ ኤርትራ እና ዛምቢያ ናቸው። በዝርዝሩ ውስጥ ኢትዮጵያ አገራችን የለችበትም። በዓለም አቀፍ መድረኮችም የወያኔ መረጃዎች ውሸትነት እየተጋለጡ መሆናቸው በጎ ምልክት ነው። የሚያሳዝነው ግን ይህንን ሀቅ የሚያዉቁ ምዕራባዉያን ለጋሽ አገሮች አሁንም ወያኔን እየረዱና እየደገፉ ሥቃያችን የሚያራዝሙብን መሆኑ ነው። ለዚህም ነው ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዘላቂ መፍትሔ ሊመጣ የሚችለው በአገራችን መሠረዊ የሆነ የአስተዳደር ለውጥ ሲኖር ነው ብሎ የሚያምነው። የወያኔ አገዛዝ በዲሞክራሲያዊ አስተዳደር እስካልተተካ ድረስ የኢትዮጵያ አብዛኛው ሕዝብ መደህየቱ፤ ጥቂት ሀብታሞች ደግሞ በብዙሀኑ ድህነት መበልፀጋቸው አይቀርም። የወያኔ ውሸቶች ለኢትዮጵያ ድሀ ምግብና መጠለያ አይሆኑለትም። ለኢትዮጵያ ዘላቂ ጥቅም ማምጣት የምንችለው ወያኔን አስወግደን በምትኩ ለሕዝብ ሁለተናዊ እድገት የሚጨነቅ መንግሥት መምረጥ ስንችል ብቻ ነው። ስለሆነም ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በውሸት እድገት እያደናቆረን፤ በተግባር ግን እያደኸየን ያለውን ዘራፊውን ወያኔን አስወግደን በሕዝብ ነፃ ምርጫ የተመረጠ መንግሥት እንዲኖረን ትግላችን እናጠንክር ይላል። ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Sunday, 19 January 2014

ዛሬ የሚያስፈሯሯችሁን እስከ ዘላለሙ የማትሰሙበት ግዜ ይመጣልና አትፍሩ

ህወሃት የሚያራምደው የዘረኝነት ፖለቲካና፤ የተዘፈቀበት የሙስና አዘቀት ሊወጣ ከማይችልበት አዙሪት ውስት ከተውታል።ከእንግዲህ ወዲህ ለህወሃቶች የቀራቸው አንድ አማራጭ ብቻ ነው። ሁሉንም ዜጎች በዘረኝነት ሰንሰለት አስሮ ቀጥቅጦ እና አፍኖ መግዛት ቀጣዩ ቅዥታቸው ነው። የዚህ አፍኖ የመግዛት ቅዥታቸው መገለጫም ዜጎች ህወሃት ስለሚፈፅመው ወንጀል ምንም ዓይነት መረጃ እንዳያገኙ ማድረግ አንዱ ነው።ህወሃት የሚፈፅመው ወንጀል ከህዝብ ዓይንና ጆሮ ተሠውሮ እንዲረሳ ይመኛል። ይሄን ምኞቱን እውን ለማድረግም ሌሎች ነፃ ሚዲያዎችን አሸባሪ ማለት ወይም ደግሞ ሌላ የተሰወረ አጀንዳ ያላቸው እያለ ማላዘንን ሥራየ ብሎ ተያይዘውታል። ከሰሞኑ አዲስ አበባ ውስጥ የሚታተሙ ስምንት የግል ህትመቶችን አሸባሪዎች በማለት ክስ መስርተዋል። አስቀድመው ፈርደው ከጨረሱ በኋላ ክስ መመሥረት የህወሃቶች የተለመደ የፍትህ ሥርዓት ነው። በአገሪቷ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ግዜ ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ሁኖ የተቋቋመውን ኢሳትንም አሸባሪ እያሉ ሰሚ አልባ ጩኸት እየጮኹ ነው። የኢሳት ቴሌቭዥንና ሬዲዮንን የሚሰማም በአሸባሪነት ይከሰሳል እያሉ በየዜጎች ደጅ እየተንከላወሱ ለማስፈራራት እየሞከሩ ነው። እኛ ግን እንዲህ እንላለን !!! አትፍሩ ! አትፍሩ ! አትፍሩ ! ኢሳትን ሰምታችኋል ብሎ የሚያስፈራሯችሁን ለዘላለሙ የማትሰሟቸው ግዜ እየመጣ ነው። የነፃነት ጎህ ቀዶ ሁላችን የፈለግነውን ሰምተን፤ ያልፈለግነውንም የምንተውበት ዘመን እሩቅ አይደለም። ግንቦት ሰባት የፍትህ የነፃነት እና የእኩልነት ንቅናቄም የተቋቋመው ዜጎች ያለማንም ጣልቃ ገብነት የወደዱትን ወስደው፤ የጠሉትን መተው የሚችሉበትን መንገድ ለማመቻቸት ነው። ዘረኞቹ በደምና አጥንት ታውረው ጭካኔን ከጀግንነት ቀላቅለው እኛ ብቻ ወንድ ባሉበት መንደር ሌላ ጀግና ኢትዮጵያዊ ወንድ ገስግሶ የሚመጣበት ዕለት እየደረሰ ነውና እንዳትፈሩ እንመክራችኋለን። ህወሃቶች ዜጎችን ከሰው በታች አድርገው ለመግዛት እንዲመኙ ያደረጋቸው እብሪት የሚተነፍስበት ዘመን እሩቅ አይሆንምና አሁንም አትፍሩ። ህወሃቶች ከእነርሱ ቁጥጥር ውጪ ያሉ ነፃ ሚዲያዎችን እንደማይታገሱ የታወቀ ነው። ለምን ቢሉ የወንጀላቸው ብዛት፤ የክፋታቸው ጥልቀት ሳይነገር ተሠውሮ እንዲቀር ስለሚመኙ ነው። ይህን ምኞታቸውን እውን ለማድረግም ራሳቸው የሠረቱን ህግ ውልቅልቁን አውጥተው ያፈራርሱታል። ዜጎች መረጃ የማግኘት መብት አላቸው ተብሎ እነርሱ “ህገ-መንግስታችን” እያሉ በሚጠሩት ላይ በማያሻማ ሁኔታ የተቀመጠ ቢሆንም እነርሱ ግን ለራሳቸው ህግ መታመንን አልመረጡም። እንዲያውም እነርሱ ሞተንለታል የሚሉትን ህግ አፈር አስገብተው ራሳቸው ህግ ሆነው ተፈጥረዋል። እነርሱ ህግ ሁነው በመፈጠራቸውም በየዜጎች ደጅ እየተንከላወሱ ኢሳትን ብትሰሙ ወዮላችሁ እያሉ ያስፈራራሉ። ዜጎች ግን የሞኝ ዘፈናቸውን መልሰው መልሰው ለሚያላዝኑ ኢሕአዴጋዊያን ዛቻ የሚንበረከኩ አይሆኑም። አገራቸውን በተመለከተ ማንኛውንም መረጃ ለመስማት ያላቸውን ነፃነትም ለምናምንቴዎች አሳልፈው የሚሰጡ አይሆኑም። ጎሬቤታችን ኬኒያ ከአስር በላይ የግል ቴሌቭዥን ጣቢያዎች አሏት።በርካታ በአጭር ሞገድና በኤፊኤም ሞገዶች የሚተላለፉ ሬዲዮኖችም አሏት። የኬኒያ መንግስት ለዜጎቹ ክብርና ፍቅር ስላለው የተቻለውን ያክል ነፃ ሚዲያ እንዲኖር ይጥራል። ለህዝቡ ክብርና ፍቅር የሌለው ህወሃት ግን በወረቀት ላይ በፃፈው ህግ ዜጎች መረጃ የማግኘት መብታቸው ያልተገደበ ነው ቢልም በተግባር ግን የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብት ያፍናል። ነፃ ሚዲያ እንዳይፈጠር ለማድረግ፤ የተፈጠሩትንም ለማጥፋት ግዜውንና የአገሪቷን ሃብት በከንቱ ያባክናል። ህወሃት ከድሃ ጉሮሮ እየነጠቀ ኢሳትን ለማፈን በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር አባክኗል። የአገሪቷ የህግ ተቋማትም ሌቦችንና ነፍሰ ገዳዮችን መከታተል ትተው በነፃነት እንፃፍ ብለው የተነሱ ጋዜጠኞችን በማሳደድ የአገሪቷን የሥራ ሠዓትና ሃብት በከንቱ ያባክናሉ። ህወሃቶች ይሄው ናቸው። አገር፤ ወገን፤ ህዝብ የሚባል ነገር በሂሊናቸው ያልተፈጠረ፤ እነርሱ ብቻቸውን ሌላውን ተጭነው መኖር የሚፈልጉ፤ የጨካኞችና የእብሪተኞች ስብስብ መሆኑን መዘንጋት አያስፈልግም። የተከበራችሁ ያገራችን ዜጎች ! አገራችሁን በተመለከተ መረጃ ማግኘት የዜግነት መብታችሁ መሆኑን እንዳትረሱ። ይሄም እነርሱ “ህገ-መንግስት” ብለው በሚጠሩት ላይም በግልፅ ተቀምጧል። ይሄን በህግ ደንግጎ ሲያበቃ ኢሳትንና ሌሎችን ነፃ ሚዲያዎችን መስማት አትችሉም ሲል የማውቅላችሁ እኔ ነኝና የምትሰሙትንና የምታዩትን የምመርጥላችሁ እኔ ነኝ እያለ መሆኑን አስታወሱ። ይሄ ማለት አዋቂው እኔ እንጂ እናንተማ ክፉን ከደጉ ለመለየት ገና አልደረሳችሁም ማለት መሆኑንም መገንዘብ ያስፈልጋል።መንግስት ነኝ ብሎ በአገሪቷ ጫንቃ ላይ የተቀመጠው ህወሃት-ኢሕአዴግ ህዝቡን የማያከብር ብቻ ሳይሆን ለህዝብ ያለው ንቀትም ወሰን የሌለው ሁኗል። ይሄ ዘረኛና ዘራፊ ቡድን ክብራችንን አዋርዶና አንገታችንን አስደፍቶ ሊገዛን አይገባውም። ፍርሃት ይብቃ። ህወሃት እየፈጠረ ያለው ፍራቻን መሸሸ አይገባም፤ ይሄን ፍርሃት መጋፈጥ የጀግና ተግባር ነውና ለክብራችሁና ለነፃነታችሁ ስትሉ ፍርሃቱን ተጋፈጡት እንጂ አትሽሹት። በዚያ በጨካኞች መንደር ሁናችሁ በሠላማዊ ትግል ብቻ ለውጥ እናመጣለን ብላችሁ የተደራጃችሁ የፖለቲካ ድርጅቶችም መረጃ የማግኘት፤ መረጃ የመሰብሰብ እና የማሰራጨት መብታችሁ ነው ብለን ልንነግራችሁ አንዳዳም። በነፃ ሚዲያ መናገርም ሆነ ለማንኛውም ሚዲያ መረጃ የመስጠት ማንም የሚሰጣችሁ መብት እንዳልሆነ ታውቃላችሁ። እኛ እንደምንገምተው ኢሳትም ሆነ ሌሎች ነፃ ሚዲያዎች የእናንተም ሃብት ናቸው። ህወሃት-ኢሕአዴግ አትስሙ ወይም ደግሞ አትናገሩ ሲላችሁ ያንን የእብሪተኛ ትዕዛዝ አለመቀበላችሁን ለነፃ ሚዲያዎች መረጃ በመስጠትና ሃሳባችሁን በነፃው ሚዲያ በመግለፅ እምቢተኝነታችሁን በማሳየት ለምትመሩት ህዝብ አርአያ እንድትሆኑ ብናሳስባችሁ ደፈሩን እንደማትሉ ተስፋ እናደርጋለን። ከዚህ አንፃር ሰማያዊ ፓሪትና አንድነት ያወጡትን መግለጫ በአድናቆት የምንመለከተው መሆኑን ለማስታወቅ እንወደላን። ለህወሃት-ኢሕአዴጎች ! ራሳችሁን ከአሸባሪ ምግባርና መዝገብ ማስፋቅ ሳትችሉ የነፃነት ፍላጎት ያላቸውን ሁሉ አሸባሪ እያላችሁ ማላዘናችሁን የምታቆሙበት ግዜ እየመጣላችሁ ነው። እናንተ ከላይ ሁናችሁ ህዝቡ ከሥር ሁኖ እናንተን ተሸክሞ ለዘላለም እንደማይኖር አበክረን ልናሳውቃችሁ እንወዳለን።በየሰው ደጅ ካድሬዎቻችሁን ልካችሁ ኢሳትን አትስሙ እያላችሁ የማስፈራራት እብሪታችሁ ረገብ የሚልበት ግዜ እየመጣላችሁ ነው። ዛሬ ህዝባችንን የእኛን ብቻ ስሙ፤ የእነርሱን አትስሙ ማለታችሁ ለህዝባችን ያላችሁን ንቀት የሚያመላክት ነው።ህዝባችንን እንደናቃችሁና እንዳዋረዳችሁ አትቀጥሉም። የነፃነትን ፍላጎት አፍናችሁ አታቆሙትም። የፍትህ ጥማታችንን በአፈሙዝ ልትገቱት አትችሉም። የእኩልነትን ጥያቄ በውሸትና በዛቻ አታዳፍኑትም። እውነት እውነት እንላችኋለን ወንጀላችሁ ሳይነገር፤ በስውር የዘረፋችሁት በአደባባይ ሳይገለጥ አይቀርም። እኛም ቀንና ማታ ለዚያ ግብ ሳናገራግር እየሰራን ነው። በአገራችን የነፃነት ጎህ ሳይቀድ ለሽፋሽፎቶቻችን እንቅልፍ፤ ለስጋችንም ዕርፍት አይሆንም። የዘረኞችና የዘራፊዎች ጀንበር ሳትጠልቅ፤ የእኩልነት ናፋቂዎች ጎህ ሳትቀድ አናርፍም። ያነገታችሁት መሣሪያ የሸንበቆ ምርኩዝ እስከ ሚሆን የጀመርነውን ትግል ዕለት ዕለት እያጎለበትነው እንቀጥላለን። ህወሃት-ኢሕአዴጎች ሆይ ስሙ! ይሄን ህዝብ ከሚችለዉ በላይ ገፍታችኋታል። ህዝቡም ሊሸከማችሁ ከሚገባ በላይ ተሸክሟችኋል።እንዲህ ህዝባችንን መፈናፈኛ አሳጥታችሁ እና እስከ ልጅ ልጆቻችሁ ረግጣችሁ ለመግዛት ያለማችሁት ህልም በህልምነቱ ብቻ እንደሚቀር ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ አይግባችሁ። ትግላችን ጥሩ መሠረት ይዟል። ከዚህ በኋላ ወደ ኋላ የሚመልሰን ምድራዊ ኃይል የለም።እውነት እውነት እንላችኋለን ለዘላለም ኢትዮጵያዊያንን አዋርዳችሁ የመግዛት ህልማችሁ ቅዥት መሆኑን ደግመን ልንነግራችሁ እንወዳለን። በህወሃት-ኢሕአዴግ ውስጥ ሁናችሁ የነፃነት፤ የፍትህ እና የእኩልነት ጥያቄያችንን የምትጋሩን ወገኖቻችን እሰክ አሁን የምታደርጉት የውስጥ ትግል ፍሬ እያፈራ ነው። ፍሬውን በራሪ ወፍ እንዳይለቅመው የተለመደው ጥንቃቄ እንዳይለያችሁ ይሁን። አሁን ህዝቡ መረጃ እንዳያገኝና፤ መረጃ እንዳይሰጥ የሚሞከረው ሙከራ ህገ-መንግስት ተብየውን የሚጥስ መሆኑን ታውቃላችሁ። ይሄን ካድሬው ሁሉ እንዲገነዘበው የውስጥ ትግሉ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል። ራሱ ያወጣውን ህገ መንግስት አፈራርሶ ከትቢያ የሚቀላቅል ቡድን በምን ሞራል ብቃት ነው ሌላውን ህገ-መንግስቱን ሊንዱ ነበር እያለ የሚከሰው ? በኢትዮጵያዊያን ላይ የተጫነው ህገ-መንግስት በህወቶች ሲፈርስ ትክክል ፤በሌላው በተግባር እንዲውል ሲጠየቅ ደግሞ ስህተት ሁኖ በአሸባሪነት የሚያስከሥሥ መሆኑን ግንዛቤ መጨበጥ ይጠቅማል። በመጨረሻም በህወሃት-ኢሕአዴግ የጭቆና ቀንበር ሥር ለምትንገላቱ ወገኖቻችን ሆይ ! አትፍሩ። ይህን የሚያስፈራራችሁን አካል እስከ መጨረሻው የማትሰሙበት ዘመን እየመጣ ነው። አሁን ፍርሃታችሁን ግደሉት።የምትሰሙትንና የምታዩትን እኔ ነኝ የምመርጥላችሁ ከሚል እብረተኛ እጅ ራሳችሁን ለማላቀቅ የግንቦት ሰባት ንቅናቄ እያደረገ ያለውን የነፃነት፤ የፍትህና የእኩልነት ትግል ተቀላቀሉ። ድል ለaaaaaaኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Saturday, 18 January 2014

አቶ ጌቱ ገለቴና ሌሎች ተጠርጣሪዎች በጋዜጣ እንዲጠሩ ታዘዘ

‹‹የቀረበብኝ ክስ ብዙ በመሆኑ መቃወሚያ ለማቅረብ ረዘም ያለ ቀጠሮ ይሰጠኝ›› አቶ ገብረ ዋህድ ወልደ ጊዮርጊስ - አቶ ጌቱ ገለቴና ሌሎች ተጠርጣሪዎች በጋዜጣ እንዲጠሩ ታዘዘ በተጠረጠሩበት ከፍተኛ የሙስና ወንጀል፤ በፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ክስ ተመሥርቶባቸው ላለፉት ስምንት ወራት በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ፣ ‹‹ክሴ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ይሁን ብዬ የጠየቅኩት እኔ አይደለሁም፤›› አሉ፡፡ አቶ መላኩ ተቃውሞአቸውን ያቀረቡት ጥር 6 ቀን 2006 ዓ.ም. የተጠረጠሩበትን ክስ እየመረመረው ለሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት ነው፡፡ እሳቸው ሳይጠይቁና ምንም ሳይናገሩ በርካታ የመገናኛ ብዙኃን እሳቸው እንደጠየቁና እንደተከለከሉ አድርገው መዘገባቸውን በመቃወም፣ እንዲስተካከል ወይም ታርሞ እንዲዘገብ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ በበኩሉ በሰጠው ምላሽ እንደገለጸው፣ ጥያቄውን ያቀረበው ፍርድ ቤቱ ነው፡፡ የመገናኛ ብዙኃን ከፍረጃ ጋር በማያያዝ ዘገባ እንዳያስተላልፉ ከማስጠንቀቂያ ጋር የሰጠውን ትዕዛዝ ካስታወሰ በኋላ፣ ሁሉም የመገናኛ ብዙኃን በትክክል ባይዘግቡም ሁሉም ደግሞ ተሳስተዋል ማለት እንደማይቻል ገልጿል፡፡ ፍርድ ቤቱ ከዚህ በላይ የሚለው ነገር እንደሌለ በማሳወቅ ተከሳሾቹ ጠበቆቻቸውን አማክረው የስም ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞብናል የሚሉ ከሆነ፣ የሚመለከተውን አካል መጠየቅ እንደሚችሉ አስረድቷል፡፡ ሌላው ፍርድ ቤቱ በዕለቱ መዝገቡን ቀጥሮ የነበረው የአቶ መላኩን ክስ የማየት ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት የትኛው እንደሆነ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከሕገ መንግሥት አጣሪ ኮሚሽን በደረሰው የምርመራ ውጤት ላይ ውሳኔ ሰጥቶ እንዲያሳውቀው የሰጠውን ትዕዛዝ ለመጠባበቅ እንደነበር ለችሎቱ አስታውቋል፡፡ በመሆኑም ፌዴሬሽን ምክር ቤት ታህሣሥ 24 ቀን 2006 ዓ.ም. ባደረገው ውይይት፣ የአቶ መላኩን ክስ የማየት ሥልጣን ያለው ከፍተኛው ፍርድ ቤት መሆኑን በማሳወቁ፣ በእነ አቶ መላኩ ፈንታ ላይ የተመሠረተው ክስ በመደበኛነት እንደሚቀጥል አሳውቋል፡፡ የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ የክስ መግለጫ እንደሚያስፈልገው በመጠቆም፣ ተከሳሾች የክስ መቃወሚያ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑም በችሎት ተነግሯቸዋል፡፡ ተጠርጣሪ ተከሳሾቹ በክሱ ላይ ቅሬታ እንዳላቸውና መቃወሚያ እንደሚያቀርቡ ተናግረው፣ ከክሱ ስፋት አንፃር ረዘም ያለ ጊዜ እንዲሰጣቸው ሲያመለክቱ፣ የአዲስ ኢንተርናሽናል ካርዲያክ ሆስፒታል ባለድርሻ የሆኑት ተጠርጣሪ ተከሳሽ ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ተቃውሞአቸውን ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል፡፡ ‹‹ጠበቆች እየጠየቁ ያሉት ረጃጅም ጊዜ በመሆኑ እኛ የተፋጠነ ፍትሕ የማግኘት መብታችንን ያጣብብብናል፡፡ የምንፈልገው አጭር ቀጠሮ እንዲሆንልን ነው፤›› በማለት አመልክተዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ተጠርጣሪ ድጋፋቸውን ሰጥተዋቸዋል፡፡ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የሕግ ማስከበር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ገብረ ዋህድ ወልደ ጊዮርጊስ ግን የእነ ዶ/ር ፍቅሩን ተቃውሞ በመቃወም፣ ‹‹እኔ ብዙና ሰፊ ክስ አለብኝ፡፡ ጠበቆቼ በደንብ ተረድተውና አብራርተው የክስ መቃወሚያ እንዲያቀርቡ ረዘም ያለ ቀጠሮ ይሰጠን፤›› በማለት ለፍርድ ቤቱ አመልክተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የተጠርጣሪ ተከሳሾቹን ማመልከቻ ከሰማ በኋላ ብይን ሰጥቷል፡፡ በሰጠው ብይንም፣ በተጠረጠሩበት የተለያየ የሙስና ድርጊት ወንጀል ክስ ቢመሠረትባቸውም በችሎት ሊቀርቡ ያልቻሉት አቶ ጌቱ ገለቴን ጨምሮ ሌሎችም ግለሰቦች በጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግላቸው ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ እንዲሁም በችሎት ተገኝተው ክሳቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙትና የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግን ክስ በሚመለከት መቃወሚያ እንዳላቸው ያመለከቱ ተጠርጣሪዎች ለጥር 29 ቀን 2006 ዓ.ም. ተቃውሞአቸውን እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

Wednesday, 15 January 2014

New report calls on Ethiopia to reform repressive anti-terror law

IPI and partners also call for immediate release of five imprisoned journalists
IPI is urging Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn, pictured here in October 2013, to release imprisoned journalists and to reform the country's anti-terrorism law. Tiksa Negeri/Reuters VIENNA, Jan 14, 2014 - Ethiopia’s use of sweeping anti-terrorism law to imprison journalists and other legislative restrictions are hindering the development of free and independent media in Africa’s second largest country, according to a report published today by the International Press Institute (IPI). Dozens of journalists and political activists have been arrested or sentenced under the Anti-Terrorism Proclamation of 2009, including five journalists who are serving prison sentences and who at times have been denied access to visitors and legal counsel. The report, “Press Freedom in Ethiopia”, is based on a mission to the country carried out in November by IPI and the World Association of Newspapers and News Publishers (WAN-IFRA). “Despite a strong constitutional basis for press freedom and freedom of information, the Ethiopian government has systematically used the anti-terrorism law to prosecute and frighten journalists, which has put a straight-jacket on the media,” IPI Executive Director Alison Bethel McKenzie said. “Our joint mission also found a disturbing pattern of using other measures to control the press and restrict independent journalism, including restrictions on foreign media ownership and the absence of an independent public broadcaster.” The report urges the Ethiopian government to free journalists convicted under the sedition provisions of the 2009 measure. These journalists include Solomon Kebede, Wubset Taye, Reyot Alemu, Eskinder Nega and Yusuf Getachew. Mission delegates were barred access to the journalists, who are being held at Kaliti Prison near the capital Addis Ababa. The report urges the 547-member lower house of parliament to revamp the anti-terror law to ensure that it does not trample on the rights of freedom of speech and assembly provided under Article 29 of the Ethiopian Constitution and further guaranteed under the African Charter on Human and People’s Rights and the U.N. Human Rights Covenant, which Ethiopia has ratified. In addition, the report: Recommends that Ethiopian lawmakers review laws that bar foreign investment in media, measures that inhibit the development of an economically viable and diversified market. Urges the courts to ensure that rulings restrict press freedom only in cases of intentional incitement or clear participation in acts of terrorism, and that judges act independently to protect the public’s right to be informed about political dissent and acts of terrorism. Urges Ethiopia’s journalists and media owners to step up cooperation to improve professionalism and independence, and to form a unified front to defend press freedom. The joint IPI/WAN-IFRA mission was carried from Nov. 3 to 6, just ahead of the African Media Leaders Forum (AMLF) in Addis Ababa. The organisations’ representatives met with more than 30 editors, journalists, lawyers, politicians and bloggers, as well as associates of the imprisoned journalists. The delegation also held meetings with the ambassadors of Austria and the United States, a senior African Union official, an Ethiopian lawmaker and government spokesman Redwan Hussien. The organisations urged Prime Minister Hailemariam Desalegn to free the imprisoned journalists, some of whom are suffering from deteriorating health. In a joint statement issued immediately following the mission, IPI and WAN-IFRA also expressed their commitment to helping improve the professionalism, quality and independence of journalism in Ethiopia. While the report highlights a long history of press freedom violations in Ethiopia, including a crackdown on journalists and opposition politicians following the country’s 2005 national elections, it notes that the 2009 anti-terrorism law has given the government expansive powers. “The 2009 anti-terrorism law gave new powers to the government to arrest those deemed seditious, including journalists who step beyond the bounds of politically acceptable reporting or commentary,” the report says. “Armed with statutory authority, the government has not shied from using the laws to bludgeon opposition figures and journalists. Dozens of journalists have been imprisoned or accused of sedition or fomenting unrest, forcing many to flee the country.” The report notes other forms of pressure by the government. Independent journalists recalled being the target of smear campaigns by state-run media, while editors recounted that managers of the government-run printing press refused to print editions of newspapers containing controversial articles. The report does note positive developments, such as the growth in advertising and readership for some of the country’s leading independent newspapers. Journalists and newspaper publishers also expressed a desire to improve professionalism, quality and solidarity; although they added that government pressure and laws continue to create hurdles to self-regulation and cooperation. “We came away from Ethiopia recognising the tremendous potential for a highly competitive, professional and successful media market in Ethiopia,” Bethel McKenzie said. “But to make this happen, the Ethiopian government must remove the roadblocks, starting with the release of imprisoned journalists and then conduct a thorough review of the laws to ensure that reporting on legitimate criticism or dissent is not grounds for prosecution.” Read the full report here. For more information, contact Timothy Spence, senior IPI press freedom advisor for the Middle East and Africa, at +43 (1) 512 9011 or email tspence[@]freemedia.at.

የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች ከአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዩ

ዝርዝር ዘገባ ———– የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ለአንድነት ፓርቲ ባቀረበው ጥሪ መሰረት የፓርቲው ስራ አስፈፃሚዎችና ከ22 ከሚበልጡ የህብረቱ ሀገራት ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን የአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታወቀ፡፡ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ለፍኖተነፃነት እንዳስታወቁት ትላንት ጥር 6 ቀን 2006 ዓ.ም በተደረገው በዚህ ውይይት የአንድነት ፕሬዝዳንት ፣የህዝብ ግንኙነትና የውጪ ግንኙነት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡ በውይይቱ ወቅት የተለያዩ ሀገራትን የወከሉት የህብረቱ ዲፕሎማቶች አሁን ስለሳለው አጠቃላይ የሀገራችን የፖለቲካ ሁኔታ፣አንድነት እንደ ፓርቲ ያለበትን ሁኔታ በዝርዝር ለማወቅ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የፓርቲው ፕሬዝደንት በፕሮጀክተር የታገዘ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አንድነት ከግንኙነት ስትራቴጂ አንፃር በሀገር ውስጥ እንዲሁም በውጪ ማለትም ከኢትዮጵያ ዳያስፖራና ከአለም አቀፉ ህብረተሰብ ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት የተብራራ ምላሽ ተሰጥቷቻዋል፡፡ ኢንጅነት ግዛቸው አንድነት በሚመለከት ባቀረቡት ገለፃ የፓርቲውን ርዕይ፣ተልዕኮና አላማ በሰፊው አብራርተዋል፡፡በመቀጠልም ስለአንድነት ፖሊሲዎችና መርሆዎች ጥልቅ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ አክለውም የአንድነት ፓርቲን ተቋማዊ አደረጃጀት በሚመለከት ገለፃ ሰጥተዋል፡፡ የሀገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ በሚመለከትም የኢህአዴግ መንግስት ባለፉት አመታት አንዳችም አይነት የለውጥ አዝማሚያ እንዳላሳየ ይልቁኑም ተቋማዊ የአፈና ስርአትን እያጠናከረ እንደሚገኝ ፕሬዝዳቱ ማሳያዎችን በመጥቀስ አብራርተዋል፡፡ የኢህአዴግ መንግስት የተዘፈቀበትን ሙስና ግዝፈት የዘረዘሩት ኢንጅነር ግዛቸው የፀረሽብር ህጉ ከመንግስት የተለየ የፖለቲካ አቋም ያላቸውን ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ለማጥቃት የተቀመጠ መሆኑን በአንድነት አመራሮችና በሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችም ላይ የደረሰውን እስርና እንግልት በማሳያነት አስረድተዋል፡፡ አንድነት ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት ጋር መልካም ግንኙነት እንዳለውና በበርካታ ሀገራትም የተቋቋሙ የአንድነት ድጋፍ ሰጪ ቻፕተሮች እንዳሉጠቁመዋል፡፡ ወደፊትም በተጠናከረ ደረጃ በሀገራቸው ፖለቲካ ላይ በቀጥታ የሚሳተፉበትን መንገድ እንደተቀየሰና የዲያስፖራው አባላትን በአባልነትና በድጋፍሰጪነት በንቃት ለማሳተፍ መታቀዱን ፕሬዝደንቱ ተናግረዋል፡፡ በውይይቱ ላይ ከፓርቲው ፕሬዝደንት ከኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው ጋር የተገኙት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ሀብታሙ አያሌውና የውጪ ግንኙነት ሀላፊው ኢ/ር ዘለቀ ረዲ ተጨማሪ ማብራሪያ መስጠታቸውም ታውቋል፡፡

Monday, 13 January 2014

ማገዶ!

እውነት ለመናገር ከዬካቲት በፊት በአጭር ጊዜ ላልመለስ ወስኜ ነበር። ብቻ እንዲህ ሆነላችሁ … ተክዤ ቆዬሁ። አፍጥጬም አዬሁት። ባለፉት ሳምንታት ዘሀበሻ ላይ የአንድነት ልዩ ጉባኤ ውጤትን ጀመርኩት። መጀመር ነበረብኝና ውስጤን አናጋርኩት – የግድ። የአዲሱን የአንድነት ልዩ ጉባኤ ተመራጮችን ዝርዝር አዬሁት። አቶ ሸፍጠኛው ሂደት …. አንተ ምን አለብህ ቀልድ። ዬደላህ! መለስህ መላስህ ግራጫ ያሰኛኃል …. ዛሬም አዲስ ትወና ይዘህ ከች … አታካች።
እርግጥ በሂደቱ የቀድሞ የአንድነት ምክትል ሊቀመንበር እሩቅ አሳቢው እስረኛው አቶ አንዱአለም አራጌ በጣም እንደ ተደሰተ ዘሀበሻ ላይም አንብቢያለሁ። በሌላ በኩልም ትናንትና በ07.01.2014 ዝርዝር መረጃ ስለመርጫው ሂደት „ከቃሌ ሩም“ አዳምጫለሁ። የቃሌ ሩም ከአቶ ሃብታሙ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ እንደ አዳመጥኩት ከሆነ ምርጫው ዲሞክራሲ እንደ ነበረ ብቻ ሳይሆን አዲሱ አመራር በቃሊቲ እስር ቤት ከአቶ አንዱአለም አራጌ ጋር የነበረውን ቆይታ ምን ይመስል እንደነበርም በዝርዝር ተገንዝቤያለሁ። ያንገበገበኝ ጥቄ ይነሳል በማለት ጓጉቼም ነበር። የሆነ ሆኖ „አቶ አንዱአለም አራጌ ዘግይቶ ሊታይ የሚገባው የአማራሩ ጥንካሬ ከ15 ዓመት በፊት መቅደሙ እንደ አስደሰተው ከደቡብ አፍሪካ የነፃነት ትግል ጋር በንጽጽር ሲያው በጣምም እንደተደነቀ ተስፋም እንደጣለበት“ ነበር አቶ ሃብታሙ የገለጹት። መልካም ነው … ይህ የበለጠ የገለጸልኝ ነገር ቢኖር የአቶ አንዱአለምን ቅንነትና አውንታዊ ዕይታ አመላክቶኛል። በሌላ በኩል ግን ይህ አዲስ መዋቅር ብቻውን የጥንካሬ መግለጫ ሊሆን ከቻላ ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ እስር ቤት እያለች መሰሉ ተከነውኖ ስለነበር እኔ እመደነቀብት ምንም ጉዳይ የለም። …. ለአድናቆት ወይንም ተስፋን በሙሉ ጥግ ለመስጠት ነገን መጠበቄ ግን ግድ ይላል። በነገራችን ላይ በትናንቱ ቃለ ምልለስ የተደስትኩበት አቶ ኃብታሙ ከወያኔ ጋር በነበረቸው አጭር የቤተኝነት የቆይታ ጊዜ „ በድዬ ከሆነ ይቅርታ የመጠዬቅ ሞራል አለኝ“ ማለታቸው አስተማሪ ነበር። ወጣትነት ሁሉንም ሞክሮ ማዬት በመሆኑ፤ ወጣቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ የወያኔን መሰሪ ሀገርና ህዝብን የመግደል ሴራ መርምረው ይህን መሰል እርምጃ መውስዳቸው አብነት ነው ለእኔ። በቀጣይ የትግል ሂደትም በሚያሳዩት የነቃ ጉልህ ተሳትፎ ውስጣቸውን አንጥሮ ማሳዬት የሚችሉ ከሆነ መልካም ነው። እንዲህ ከወያኔ እጅ እያመለጡ የሚመጡትን ወጣቶች በአግባቡ ይዞ ሞራላቸውንም ጠብቆ የነፃነት ትግሉ ጽኑ ቤተኛ ማደረግ የሁላችንም ግዴታ ነው። ወጣትነት ብዙ ባህሪያት በህብር የሚገኝበት በመሆኑ በጥንቃቄ የአያዛዝ ጥበብን ይጠይቃል። ሰሞኑን ስተኛ መገላበጥ አበዛሁ። ለምን? … ቀኑን አላስታውስም ብቻ „ጠርዝ ላይ ያለ ስጋቴ“ የሚል አንድ ጹሑፍ በአደራ ተርጓሚው፤ በቀጥተኛው፤ በግልጹና በግንባር ሥጋው …. በወጠት አንዱአለም አራጌ ዙሪያ የሆነ ነገር ብዬ ዘሃበሻም አውጥቶልኝ ነበር። ጹሑፌ አጭር ቆይታ ብቻ ነበር የነበረው። የፈራሁት እንሆ ደረሰ። http://alltomypeople.blogspot.ch/2013/12/blog-post_2578.html እኔ እንደሚገባኝ በአደራ ጠበቂው በአቶ አንዱዓለም አራጌ ውስጥ በፍጹም ሁኔታ አንድነት ፓርቲውአለ። በአንድነት ማዕከላዊ አመራር ውስጥ አቶ አንዱአለም ግን……. ቀደም ባለው ጊዜም በክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ውስጥ በፍጹም ሁኔታ አንድነት ነበር። በአንድነት ማዕከላዊ አመራር ውስጥ ወ/ት ብርቱካን ሜዴቅሳ ግን … በተመሳሳይ ብቃት፤ በሙሉዑ ተቀባይነት፤ የህዝብ ፍቅር የነበራቸው ሁለቱምየአንድነት ወጣቶች የነፃነት ቀንበጦች ላይ አንድነት የወስደው ተመሳሳይ እርምጃ ግን አልተመቸኝም።- አንጀቴንም አቃጠለው። ይህቺ እናት ሀገር ኢትዮጵያ ወጣቶቻና ሴት ልጆቿ መቼ ይሆን ቦታቸውን አግኝተው በብቃታቸው፤ በእርግጠኝነታቸው፤ በመሆን መቻላቸው፤ በሙቅና ትኩስ ፍላጎታቸው ትራስነት ከዚህ የመከራ ፍዳ የሚታደጉዋት። ወጣትነት እኮ ገዢ መሬት ላይ ያለ አጥቂ ሰራዊት ማለት ነበር። ወኔውም ልቡም ላለው። ማሸነፍ ማለት ወጣትነት ነው ለ እኔ። በመንፈስም በአካልም። …. ዘመኑም ይሄዳል እየለቀሙ ማፈስስ … እያፈሰሱ መልቀም … ዕጣውም ይፈሳል – ጣጣው ይጎፍራል ….. ወጣቶቹ ለሚከፍሉት መስዋዕትን መታጋያ መድረካቸውን የሚያፈናቅል ተግባር ፊታውራሪ ሂደት እስር ላይ እያሉ ይፈጸማል። ይህ ጥቁር የታሪካችን ጠበሳ በወጣት የፖለቲካ መሪዎቻችን ላይ የተሰነዘረ የተስፋችን ጥቃት ነው። ያማል። የሚጎረበጥ – የጓጎለ ጎብዳዳ – ገጠመኝ። ዛሬ ላይ ሆነን የሰሞኑን ጉሽ ነገር ስንለካ፤ ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ከኃላፊነቷ ላይ ሆና ብትሆን ኖሮ፤ ሚዛን ያለው ምላሽ በተሰጠው ነበር። ኢትዮጵያዊነትን በፈተነው ጠቀራማ ዘመቻ ላይ የግንባር ቀደም ተዋናይ በመሆን የድርሻዋን ትውጣ እንደ ነበረ አልጠራጠረም። ግልጽ አቋምም ትወስድ ነበር። የጌጣችን ፈርጥ ሚስጢር እሷ ውስጥ ነበርና። ምክንያቱም ከነፃነት በላይ ትርጉም ያለው መንፈስ ሊኖር ከቶ አይችልም። የሰብዕናና የማንነት ምንዛሬ ህልውና ነጻነት!። ነፃነት ያለው ህዝብ በራስ የመተማመን መንፈሱ ሙሉዑ ነው። የትም ቦታ፤ በዬትኛውም ጊዜ፤ ማናቸውንም ፈተና የሞቋቋምና በእራስ እንደ ራስ ሆኖ የሚያቆም ዓውራ እሴቱ ነፃነት ብቻ ነውና። ስለሆነም ለአንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ማናቸውም ፈተና ከሀገሩ ሉዕላዊነት በታች እንጂ በላይ ሊሆን ከቶ አይችልም። ሀገር አለኝ ማለት የግጥምጥሞሽ ቃል አይደለም። የመኖር አለመኖር ህግ እንጂ …. በሌላ ሀገር ቅኛ አለመገዛት እኮ ቃላት ሊገልጸው – ሊተነትነው – ሊፈትሽው የማይችል ረቂቅ መንፈስ ነው።አብነቱ አይደለም ለእኛ ዓለምን የናኘ ብቻ ሳይሆን አፍሪካን ለነፃነት ያበቃ በኽረ ጉዳይ ነውና። ከዚህ አንፃር የክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ከፖለቲካ መድረክነት መገለል ጉዳቱ ለዛሬም – ለነገም ነው …. ሚስጢሩ ለሚገለጽላቸው …. በሌላ በኩል ትውልድ ከቶውንም ሊተካው የማይችለው የአፍሪካ የቅኔ ልዑሉ፣ ፓን እፍሪካኒስቱ፣ የሃያሲው፤ የመምህሩ፤ የጸሐፊው፤ የገጣሚው የብላቴ ጌታ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን በህይወት አለመኖርም … ሌላው የልባችን ውጋት ነው። አጅሬ ቢኖር፣ እሱ ቢኖር እንዲህ ያለ ታሪክን ጨለመ የሚያለብስ ዘመቻ፤ ሆነ ድፍረትም ፈጽሞ አይታሰብም ነበር። በአንዲት ዘላላ ቅኔዊ ስንኝ አመጣጥኖ፤ አቻችሎ ቀጥ ያደርገው ነበር። የብዕሩ ደም ፈውስና መዳህኒት ነበርና … እሱም እንደ ብርቴ የኢትዮጵዊነት ልዩ ፈርጥ ቅመም ነበረውና አምላከ – ቅብዕ። አሁን ወደ ቀደመው እንደ አቨው … አዎን! ወያኔ በህዝባዊ ፍቅር ተወዳድረው ያሸንፉኛል የሚላቸውን ወጣት የነፃነት አርበኞችን በነፃነት ትግሉ ማዕዶት አስርጎ ባስገባቸው አባሎቹ አማካኝነት እዬለቀመ ያሰራል፤ አቶ ሂደት ደግሞ መንገዱን ተከትሎ መስዋዕትነታቸውን አፈር ድሜ አስግጦ፤ ለዘር ሳያበቃ የበሬ ግንባር የምታክል የጉልማ መሬት ሳያስቀር ለሌላ አዲስ ሂደት አዲስ አመራር ይመርጣል፤ ይሾማል …. ይሸልማል፤ የድርጅቱ ዋነኛ ዓላማ ተስፋ — ቆራጭነትን ሰንቆ እሱን ያዬ፤ እሷን ያያ እያለ መቀጣጫ ያደርጋል … ቲያትሩ … ድራማው ይሄው ነው የፍታውራሪ ሂደት … ቁስለት! „አንዱአለም የሰላም ታጋይ እንጂ አሸባሪ አይደለም“ በዬሀገሮች የተካሄዱ ሰላማዊ ሰልፎች መሪ መፈክር ነበር። „መንገድ በስሙ ይሰዬም“ ሌላው የህዝበ – ጉባኤ ድምጽ ነበር …. በቃ ይሄው ነው? … ማገዶነት ብቻ። የሰላማዊ ትግልን የሚያስከፍለውን መስዋዕትነት የሚከፍሉ ጀግኖች አሉን፤“ እያሉ በመሰዋዕትነቱ እምነት ጥለው ትግሉን የሚያግዙ፣ የሚረዱም ወንድሞችና እህቶች በርካታ ናቸው። ምልክታቸውን አንዱአለምን አድርገው። … ከአዲሱ መጸሐፉ ውስጥም ጥቅሶችን እያወጡ መንገዳችን ይሄ ነው የሚሉም ወገኖች አሉ። አሁን ይህን መርዶ ሲሰሙ ከቶ ምን ብለው ይሆን? አቶ ሂደት ካስመረጠው አዲሱ ዝርዝር ውስጥ እስረኛው፣ የሰላም መርህ አራማጁ እሩቅ አሳቢው አቶ አንዱአለም የለም። አይገርምም?! በውስጡ እያለ በሩን አቶ ሂደት ቀረቀረበት። …. እና ይሄው ነው በቃ?! … ድራማው ይህ ነው … ማለት ነው። አቶ ሂደት በቦታው ሌላ ሰው አስመርጦበታል። ቢፈታ የተሰዋለትን ፓርቲውን ትቶ ከቶ ዬት እንዲሄድ ነው የተፈረደበት … ስቃይ – የመንፈስ! መቼም ይህ ሂድት የሚባል አንጀተ ደንዳና ርህራሄ የለውም … ለሁለት ምክትል ቦታ ከነበረው ምን አለ አንዱ ቦታ እንኳን ለመንፈሱ ደህንነት፤ ለፈኖቹ ሲል እንኳን ክፍት አድርጎ ቢጠብቀው … ለምን ሁለት አስፈላጊ እንደሆነ ባይገባኝም …. መቼም አቶ ሂደት መተዛዘን ነግ ለእኔ ቢል ጥሩ ነበር። ሌላው በአቶ ሂደት የተገረምኩት ደግሞ የአዲሱ የአንድነት አመራር አካላት ሙህራንና በእድሜያቸውም ከ60% በላይ በወጣቶች ተገነባ የሚባለው ጉድ ነው። …. የትኞቹ ናቸው ወጣቶች ፕሬዚዳንት የሆኑት? …. ቲያትር ነው … ። እርግጥ ነው እኔም እማምንበት አንድ መርህ አለ …. ወጣትና ነበር የፖለቲካ ተመራጮች የሂደት ተከታታይነት ማደረግ ይጠበቃል …. እርሾ። … ይህም ቢሆን በኢጂነር ግዛቸው ከነባሩ አመራር ስላልነበሩ ክፍተት አለው። የሆነ ሆኖ አሁንም እዛው ከአዛውንታት ላይ ነው ያለው የመወሰን፤ የመምራት ቁልፉ …. የዛሬው ትውልድ እጅግ የቀደመና የሰለጠነ ሆኖ ሳለ ግን ተፈራ …. ለምን?! አባቴ መዳህኒተ ዓለም ይወቀው። ….ተከታዩ ካቴና የሚጠብቀው ደግሞ ማን ይሆን? …. አቶ ሂደት ልጆቹን ለካቴና እያመቻቸ ያቀብልና ለአዲስ ትወና ይዘጋጃል …. መስራች – ልዩ – ማሟያ እያለ … ደጃችዝማች ሂደት ካቴና ላይ ለሚገኙ አካሎቹ መንፈስ ቢያንስ ተቆርቋሪ ቢሆን መልካም ነው። ለቤተሰቦቹም ይሰብ። „ነግረንህ ነበር አስታውሰንህ ነበር“ የሚሉ አይጠፉም እንዲህ አይነት ተርጓሚ አጥብቆ የሚሻ ገጠመኝ ሲታይ። ኃላፊነት ያለው ተግባር ቢፈጽም መልካም ነው። የአሁኑ ሆናል። አይተናል ሰምተናል … ይብቃኝ መሰልየተቋጠረን መግል ለማፍሰስ፤ እርገት። የቀድሞው የአንድነት ሊቀመንበር ዶር/ ነጋሶ ጊዳዳ በቃኝ ማለታቸውን በአውንታዊነትና በቅንነት ማዬት ይገባል። በወያኔ ሥርዓት ውስጥ የነባራቸውን የሥም ቦታ በፈቃዳቸው ለቀቁ፤ በአንድ ወቅት የኢትዮጵያን ህዝብም ይቅርታ ጠዬቁ፤ ከጎጥ አስተሳሰብ ወጥትው የአንድነት ኃይሉ ቤተሰብ ሆኑ፤ እኔኑ እሰሩኝ ወጣቶቼን ልቀቁ ብለው የትክክለኛ እረኝነትን አብነትም አሳዩን። አሁንም ከዕድሚያቸው ጋር ሊመጥን የሚችል እርምጃ ወሰዱ። ስለሆነም የሚወስዷቸው እርምጃዎች ሁሉበምሳሌነት ሊያሰመሰግናቸው ይገባል እላለሁ እኔ፡ እንዲያውም እንዲህ የሚል ጠፍቶ ነው ተተኪው አዲስ ወጣት ትውልድ አቅሙን የሚተረጉምበት መድረክ ያጣው – የዘመንም ግጭት ደልቶት የምናዬው። ትንሽ ብትክትክ አልኩ መሰል፤ ያለተመቸኝንም የተመቸኝም አዘናንቄ የምለውን አልኩ።ቸር እንሰንብት።

Sunday, 12 January 2014

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ እና የኢትዮጵያ ምህዳር ጋዜጣ አዘጋጆች ለውሣኔ ተቀጠሩ

በህገመንግስቱ ላይ ህዝብን ለአመጽ በማነሳሳት፣ የህዝብን ሃሳብ በማናወጥ እና “ጨፍጫፊ” በማለት የመንግስትን መልካም ስሙን በማጥፋት የተከሰሰው የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ በመከላከያ ማስረጃነት ያቀረበው የቢቢሲ ዶክመንተሪ ፊልም፣ የቢቢሲ ስለመሆኑ ማረጋገጫ እንዲያቀርብ ሲል ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለውሣኔ ቀጥሯል፡፡ ተከሳሹ ከምርጫ 97 ጋር በተያያዘ ቢቢሲ ያዘጋጀው ነው በሚል በመከላከያ ማስረጃነት የቀረበው የድምጽ ምስል ዶክመንተሪ ፊልም በእርግጥም የቢቢሲ ስለመሆኑ ጥያቄ በማስነሳቱ ከጣቢያው ሃላፊዎች ማረጋገጫ እንዲያቀርብ ቀደም ባለው ቀጠሮ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ የሰጠው፡፡ ከትናንት በስቲያ በዋለው ችሎት የተከሳሽ ጠበቃ ለፍ/ቤት እንዳስረዱት፤ ማረጋገጫውን ለማግኘት ከቢቢሲ ሃላፊዎች ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውን ጠቁመው ለዚህኛው ቀጠሮ ሊደርስላቸው ባለመቻሉ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሠጣቸው ጠይቀዋል፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን ቀደም ሲል በአቃቤ ህግ የቀረበበትን ማስረጃ ይከላከሉልኛል ያላቸውን የሰው ምስክሮች ለፍ/ቤቱ ከማሰማቱም በተጨማሪ የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቦ መከራከሩ ይታወሳል፡፡ ለፍ/ቤቱ ካቀረባቸው የመከላከያ የሰነድ ማስረጃዎች መካከልም 4 ገጽ ያለው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ (ኢሠመጉ) ሪፖርት፣ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ “ኢትዮጵያን አመጽ አያሰጋትም” ሲሉ የሠጡት ቃለ ምልልስ፣ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት እንዲሁም ከምርጫ 97 ጋር በተያያዘ ቢቢሲ በፎከስ ኦን አፍሪካ ያሠራጨውና ፍ/ቤቱ ማረጋገጫ የጠየቀበት ዘገባ ይገኙበታል፡፡ ተከሣሹ ባቀረባቸው የመከላከያ ማስረጃዎች ላይ አስተያየቱን የሰጠውን አቃቤ ህግ በበኩሉ፤ የቀረቡት ማስረጃዎች ከክሱ ፍሬ ሃሳብ ጋር ግንኙት የላቸውም ብሎ የተከራከረ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ሣይቀበለው ቀርቷል፡፡ አቃቤ ህግ በቀረቡት የሰነድ ማስረጃዎች ላይ ያለውን አጠቃላይ አስተያየት በቀጣዩ ቀጠሮ ለማቅረብ ፍ/ቤቱን ጠይቆ ተፈቅዶለታል፡፡ ፍ/ቤቱም የተከሳሽን የቢቢሲ ዘገባ ማረጋገጫ ለመቀበልና የአቃቤ ህግን አጠቃላይ የማስረጃ አስተያየት ሠምቶ ውሣኔ ለመስጠት ለየካቲት 5 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጥሯል፡፡ በሌላ በኩል ሐዋሣ በሚገኘው የሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት፤ የሃዋሣ ዩኒቨርሲቲ የ300ሺህ ብር የፍትሃ ብሔር ክስ ያቀረበባቸው የኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ አሳታሚና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሚሊዮን ደግነው እንዲሁም ዋና አዘጋጅ ጌታቸው ወርቁ ባለፈው ረቡዕ ፍ/ቤት ቀርበው የቃል ክርክር ካደረጉ በኋላ፣ የፍ/ቤቱን ውሣኔ ለመስማት ለጥር 20 ቀን 2006 ተቀጥረዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የፍ/ቤቱን ሂደት ለመከታተልና ስለዘገባው ማብራሪያ ለመስጠት ወደ ሃዋሣ በሄደበት ወቅት የትራፊክ አደጋ የደረሰበት ጋዜጠኛ ኤፍሬም በየነ ስለ አደጋው ፖሊስ አዲስ አበባ ድረስ መጥቶ ቃሉን የተቀበለ ሲሆን፤ እስካሁን ግን ክስ እንዳልተመሠረተ የጋዜጣው ዝግጅት ክፍል ባልደረቦች ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡

Thursday, 9 January 2014

የመንግስት የፕሬስ ተቋማት የግል መጽሄቶችን በጽንፈኝነት ፈረጁ

የመንግስት የፕሬስ ተቋማት የግል መጽሄቶችን በጽንፈኝነት ፈረጁ መንግስታዊዎቹ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እና በሕግ በፈረሰ ድርጅት ስም የሚጠቀመው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በጋራ አስጠንተነዋል ባሉት ጥናት መሰረት በአገር ውስጥ ከሚታሙት መጽሄቶች መካከል አዲስ ጉዳይ፣ፋክት፣ሎሚ፣ቆንጆ፣ጃና፣እንቁ እና ሊያ የተባሉ መጽሔቶች ጽንፈኛ ፖለቲካ አራማጆች መሆናቸውን አረጋግጠናል ብለዋል። አዲስዘመን ጋዜጣ በረቡዕ ታህሳስ 30 ቀን 2006 ዕትሙ መጽሔቶቹ በብዙ ባህርያቸው የጽንፈኛ ፖለቲካ ፓርቲ ልሳናት መሆናቸው፣ በተሳሳቱ መረጃዎች ሕዝቡ በስርኣቱ ላይ እምነት አጥቶ ለአመጽ እንዲነሳሳ የሚያደርጉ ዘገባዎችን ያቀርባሉ ብሏል፡፡ በጥናቱ መጽሔቶቹ የመንግስትን ኃላፊዎች የግል ስብዕና እንደሚነኩ፣የአመጽ ጥሪዎችን እንደሚያሰሙ፣ሽብርተኝነትን እንደሚያበረታቱ፣የፖለቲካ ስርዓቱን እንደሚያጨልሙ፣ኢኮኖሚ ዕድገቱን እንደሚክዱ፣ህገመንግስቱን እንደሚጥሱ በዝርዝር አቅርቧል፡፡ መንግስት መጽሄቶችን በጽንፈኝነት በመፈረጅ ምናልባትም ከ2007 ምርጫ በፊት እንዲዘጉ ሊያደርግ ይችላል ሲል አንድ ያነጋገርነው ጋዜጠኛ ተናግሯል። "መንግስት ምንም አይነት እርሱ ከሚያራምደው አጀንዳ ውጭ የተለየ ድምጽ መስማት አይፈልግም" የሚለው ጋዜጠኛውም፣ መጽሄቶችን በተለያዩ መንገዶች በመፈረጅ ከገበያ ለማውጣት ያሰበ ይመስላል ሲል አክሎአል። ኢትዮጵያ የፕሬስ መብቶችን በማፈንና ጋዜጠኞችን በማሰር ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ናት። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ርእዮት አለሙ፣ ውብሸት ታየ፣ የሱፍ ጌታቸውና ሌሎችም ሀሳባቸውን በመግለጻቸው ብቻ መታሰራቸው ይታወቃል። ከምርጫ 97 በሁዋላ እጅግ ዝነኛ ጋዜጣ ሆነ የወጣው ፍትህ ጋዜጣም በመንግስት ጫና ከገበያ እንዲወጣ ተደርጓል። በጋዜጣው ላይ ሲሰሩ የነበሩት ታዋቂ ጋዜጠኞችም በተለያዩ ክሶች ሲዋከቡ ቆይተዋል።

Thursday, 2 January 2014

ቴዲ አፍሮና የቢራው ፖለቲካ

በጋዜጠኛ ስህተት የወጣች አንዲት ጽሁፍ ምክንያት 18 ሺህ ፊርማ በኢንተርኔት መሰበሰቡን ሰማን። ጽሁፉን ያሳተመው መጽሄት ስህተቱን አረመ። ይቅርታም ጠየቀ። ዘመቻው ግን እንደቀጠለ ነው። ቴዲ አፍሮ ይንን እንዳልተናገረ መግለጫ ቢሰጥም ጉዳዩ እልባት ሊያገኝ አልቻለም። ከቶውንም አንድነታችንን የማይፈልጉ ምእራባውያን ጭምር ይህችን ምክንያት በመያዝ ጉዳዩን ማረገብ ጀመሩ። አንድ የዳች ጋዜጣ አጼ ምኒሊክን ከሂትለር ጋር አመሳስሎ በመጻፍ ጋዜጣውን በዚህ ሳምንት አሰራጭቷል! ያለ አንዳች መረጃ። “ለነጮች እጄን አልሰጥም!” ብሎ አድዋ ላይ ስላዋረዳቸው ምኒሊክን ለማንቋሸሽ ምንም መረጃ አያስፈልጋቸውም። እልፍነሽ ቀኖ የተባለች የኦሮምኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ በአንድ ወቅት በለቀቀችው ነጠላ ዜማ ምክንያት ማእከላዊ እስር ቤት ታስራ ነበር። ምርመራውን የሚያካሂዱት ሰዎች በመጀመርያ የዘፈኑ ግጥም ወደ አማርኛ እንዲተረጎም አደረጉ። በግጥሙ ምንም አይነት የወንጀል ነገር ሲያጡ ግጥሙ “የህግ ትርጉም ይደረግለት” ሲሉ አዘዙ። የህግ ትርጉሙም ብዙ ስላላስኬዳቸው ለግጥሙ የፖለቲካ ትርጉም እንዲሰጠው አደረጉና ሙዚቀኛዋን “ጥፋተኛ ነሽ” ሲሉ ከሰሱ። የፖለቲካ ትርጉሙ “ይህን ያለችው እንዲህ ለማለት ነው…” ከማለት ተነስቶ አቀንቃኝዋ በልቧ አስባው ይሆናል የሚለውንም ያካተተ ነበር። በኢትዮጵያ “የፍትህ ሰዎች” የምናስበውንም ያውቁ ኖሯል። የበደሌ ቢራ አድማ ጠሪዎች ቴዲ አፍሮ በልቡ ያሰበውን የማንበብ ሃይል እንዳላቸው አናውቅም። እሱ ግን የተባለውን ነገር እንዳልተናገረ ገልጾላቸዋል። አጼ ምኒሊክ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ያከሄዱት ጦርነት “ቅዱስ ጦርነት ነው” ወይንም “አይደለም” የሚለውን ሙግት ለግዜው ወደጎን እንተወው። ምክንያቱም የዚህ ውይይት ውጤጥ የኦሮሞ ህዝብ አሁን ላለበት ችግር የሚፈይደው አንዳች ነገር የለም። የህሊና አይኖቹን ክፍት አድርጎ ለሚመለከት ሁሉ፤ የዛሬው የኦሮሞ ህዝብ ችግር የበዴሌ ቢራን ከመጠጣት እና ካለመጠጣት የላቀ ነው። ለነገሩ እንጂ 90 በመቶ የሚሆነው የኦሮሞ ህዝብ የሚተዳደረው በግብርና፤ ኑሮውም ከእጅ ወደ አፍ በመሆኑ የበደሌ ቢራን የመጠጣት አቅሙም ሆነ እድሉ የለውም። የዚህ ዘመቻ መሪ ተዋንያን የሆነው ጃዋር መሃመድ እንደነገረን ከሆነ ደግሞ 90 በመቶው የኦሮሞ ህዝብ የሙስሊም እምነት ተከታይ ነው። በሙስሊም አልኮል “ሃራም” ነው። “እስር ቤቱ ሁሉ ኦሮምኛን ይናገራል!” ያለው ማን ነበር? አዎ! የስርዓቱ ቁንጮ የነበረው ስዬ አብርሃ ነው። ስዬ ስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት ከርቸሌ ታስረን የነበርን ጋዜጠኞች የእነ ኦቦ ባይራን ጉዳይ እያነሳን በኦነግ ስም በግፍ ለታሰሩት ስንጮህ የዝሆን ጆሮ ነበር የሰጠን። አቶ ስዬ አብርሃ አይኑ የተከፈተውና ጆሮው ኦሮምኛን መስማት የጀመረው እጆቹ የኋሊት ታስረው ቃሊቲ ሲወርድ ነበር። በእርግጥ ማየት ማመን ነው። ያየውንና የሰማውን በመመስከሩ ሊመሰገን ይገባዋል። ልብ በሉ። እስረኛው ሳይሆን እስር ቤቱ ነው ኦሮምኛ እየተናገረ ያለው። ሂዩማን ራይትስ ዋች ሰሞኑን በለቀቀው ዘገባ፤ በኦሮሞ ወገናችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን አስከፊ ስቃይ በድምጽና በምስል ጭምር አሰራጭቷል። ይህንን ስቃይ ለማስቆም የፌስቡክ ታጋዮቹ ስንት ሺህ ፊርማ እንዳሰባሰቡ አልነገሩንም። የበዴሌ ቢራን የኦሮሞ ህዝብ እንዳይጠጣ በ24 ሰዓታት ውስጥ 18 ሺ ፊርማ ተሰብስቧል ብለውናል። እርግጥ ነው። “ሰብአዊ መብት ይከበር!” የሚል ዘመቻ ከመጀመር ይልቅ “ቢራ አትጠጡ!” ማለቱ ቀላል ሊሆን ይችላል። በምእራቡ አለም የሚመረተውን ሄነከን ቢራ ራሳቸው እየተጎነጩ ይህንን ቀጭን ትእዛዝ ሲያስተላልፉ ግን በዚያ ትልቅ ህዝብ ላይ እያሾፉበት መሆኑን የዘነጉት ይመስላል። የኦሮሞ ልሂቃን ግራ ያጋቡኛል። ይህን ስል ያለምክንያት አይደለም። በአባ ጅፋር ግዛት ተወልጄ በኦሮሞ ባህል ታንጼ ነው ያደግኩት። በደሙ ብቻ ‘ኦሮሞ ነኝ’ እያለ ከሚመጻደቀው ይልቅ የኦሮሞን ህዝብ ማንነት ጠንቅቄ አውቀዋለሁ። ቋንቋው፣ ባህሉና ስነልቦናው ውስጡ ሰርጎ ሳይገባ በደሙ ብቻ ራሱን እየለካ ከህልም እና ከቅዠት አለም ውስጥ ገብቶ የኋሊት ከሚራመደው በተሻለ መንገድ። … እናም አንድ የኦሮሞ ህዝብ አውቃለሁ። በቋንቋው፣ በባህሉና በታሪኩ የሚኮራ ህዝብ። ታታሪና ሰራተኛ ህዝብ። ከሌላው ጋር ተዋልዶና ተከባብሮ በፍቅር አብሮ የሚኖር ህዝብ። የኦሮሞ ህዝብ ከሌላው ወገኑ ጋር በደም ተሳስሯል። ሃቁ ይህ ነው። ግና ፖለቲከኞቹ ከዚህ ህዝብ በሁለት ሺህ ማይልስ ርቀው በምእራቡ አለም በሚሰሩት ስራ ይህንን ትልቅ ህዝብ እጅግ ትንሽ የሚያደርግ መሆኑን ያስተዋሉት አይመስለኝም። በቅርቡ ሳውዲ አረቢያ በወገኖቻችን ላይ የጸመችውን ግፍ ለመቃወም በአለም ዙርያ ያለ ኢትዮጵያዊ በጋራ በሚጮህበት ወቅት አንድ እንግዳ ክስተት በኢንተርኔት ላይ ወጥቶ አየን። “ሳውዲ አረቢያ ኦሮሞን አትግደሉ፣ ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ አይደለም፣ ኦሮሞ ወንጀለኛ አይደለም።” የሚል መፈክር የሚያሰሙ ሰዎች ለብቻቸው ሰልፍ ወጡ። እነዚህ ሰዎች የተሰለፉት “ኦሮሞን አትንኩ። ሌሎቹ ግን ወንጀለኞች ስለሆኑ ይገባቸዋል” የሚል መልእክት ለማስተላለፍ ነበር። መቼም ከማንም ሰብአዊ ፍጡር እንዲህ አይነት ኢ-ሰብአዊ አባባል አይጠበቅም። ድርጊታቸው ያሳፍራል። አንገትም ያስደፋል። ይህ አሳፋሪ ድርጊት እኔን እንዲህ ካሸማቀቀኝ፤ አፈር ስንፈጭ ያደግነው በኢትዮጵያዊነታቸው የሚኮሮ የኦሮሞ ልጆች ቢያዩት ምን ሊሉ እንደሚችሉ በምናቤ እስል ነበር። በዚያ ትልቅ ሕዝብ ስም አደባባይ ወጥተው፣ ተግባራቸው ግን ማስተዋል የተሳነው ትንሽ ህዝብ ነበር። ያንን ኩሩ ህዝብ እንዲህ … እንዲህ እያሉ ሊያሳንሱት አየን። እ.ኤ.አ. በ1998 ገደማ አቶ ዳዊት ዮሃንስ በሆላንድ ውስጥ ህዝባዊ ስብሰባ ጠርቶ ነበር። ከስብሰባው መሃል አንድ ሰው ከመቅጽበት ተነስቶ ‘ለኦቦ ነጋሶ ጊዳዳ የሚያደርሱልኝ ጥብቅ መልእክት አለኝ’ አለ። ስብሰባውን የሚመራው አቶ ዳዊት ዮሃንስም ሰውዬው ተነስቶ መልእክቱን እንዲናገር ፈቀደለት። ሰውየው ከመቀመጫው ተበሳ። “ፊንፊኔ መሃል ላይ ያለው የምኒሊክ ሃውልት በአስቸኳይ እንዲነሳ ይንገሩልን!” አለ ፊቱን ቅጭም አድርጎ በኩራት እየተናገረ። በስብሰባው የነበርን ሰዎች ግን ለተናጋሪው አፈርን። ያሳፈረን ይህንን መልእክት ማስተላለፉ አልነበረም። ሰውየው ሊናገር ከመቀመጫው ሲነሳ ሌላ አንገብጋቢ ጉዳይ ያነሳል ብለን ገምተን ስለነበር እንጂ። ‘ሰዎች በዘራቸው (በኦሮሞንታቸው) ብቻ የሚታሰሩት፣ የሚሰቃዩትና የሚገደሉት እስከመቼ ነው?’ የሚል መልእክት ነበር የጠበቅነው። ምክንያቱም ወቅቱ በቁጥር 20 ሺህ የሚደርስ የኦሮሞ ተወላጆች የጦር ካምፕ እስረኛ እንዲሆን ካደረጉ በኋላ፤ የኦነግ መሪዎች በባሌ ሳይሆን በቦሌ እየተሸኙ የወጡበት ሰሞን ነበር። የኦነግ መሪዎች ከህወሃት ጋር በጋራ መስርተውት የነበረውን ቻርተር ረግጠው በመውጣታቸው ምክንያት ኦሮሞው ወገናችን የህይወት መስዋእትነት ጭምር ይከፍል የነበረበት ወቅት። ዳዊት ዮሃንስም አግባብ ያለው ጥያቄ መሆኑን ከተናገረ በኋላ መልእክቱን ለርእሰ-ብሄሩ እንደሚያደርስ ቃል ገብቶ ሄደ። መልእክቱን ለዶ/ር ነጋሶ ያድርስ፤ አያድርስ የታወቀ ነገር የለም። ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በዚያን ወቅት የሃገሪቱ ርዕሰ-ብሄር ነበሩ። እንኳንና የተባለውን መልእክት ሊያስፈጽሙ፤ እሳቸውም የዛ ስርዓት ሰለባ ሆነው አየን። የአጼውን ሃውልት ግን ዛሬ በባቡር ሃዲድ ስራ ምክንያት ከነበረበት ስፍራ እንዲነሳ አድርገውታል። የተዛባ ታሪክ ይዘን፣ ጥላቻን ብቻ በምናባችን አርግዘን የት እንደምንደርስ አላውቅም። አሁንም በመፍትሄው ላይ ሳይሆን በችግሮቹ ላይ ተወጥረናል። የምኒሊክ ሃውልት ተነሳም አልተነሳ እንደ እንስሳ ለሚታደነው የኦሮሞ ህዝብ ምን ፋይዳ አለው? “በእስር ያሉ ወገኖቼ ይፈቱ!” ለማለት እንኳን ሞራል ሳይኖረን አእምሯችንን በአፈ-ታሪክ ብቻ ወጥረን አንዲት ኢንች እንኳን ወደፊት መራመድ እንዳልቻልን ለምን አናስተውልም? አጼ ምኒሊክ ኢትዮጵያን ግዛት አንድነት ለማስፋፋት ባደረጉት ጦርነት ወንጀል ፈጽመው ከሆነ አጽማቸው ወጥቶ ለፍርድ ይቅረብ ነው የምትሉት? ወይንስ ይህ ትውልድ የዚያ ወንጀል ውርስ አለበት? ውርስ ካለበትስ ማን ነው ወራሹ? አማራው? ጉራጌው ወይንስ ኦሮሞው? እንደ ዘረኞች፣ ደም መለካት ካለብን እኚህ መሪ ከአማራም፣ ከኦሮሞም፣ ከጉራጌም ይወለዳሉ። ጠለቅ ብለን ከሄድን ደግሞ ራስ ጎበና ዳጬን በዚያ ስእል ውስጥ እናያለን። ምእራብ እና ደቡብ ኢትዮጵያን በሃይል የያዙና ያስገበሩ የአጼው የጦር መሪ። ራስ ጎበናን ልንጠላቸው እንችል ይሆናል። ኦሮሞነታቸውን ግን ልንክደው አንችልም። የወንጀል ውርስ በተዋረድ (guilt by association) ውስጥ ከገባን የኦሮሞን ህዝብም በአእምሯችን ለፈጠርነው ወንጀል ወራሽ ልናደርገው ነው። የቴዲ አፍሮ “ጥቁር ሰው” አልበም የሚያሞግሰው ኢትዮጵያን ከወራሪ ጠላት የታደጉትን ጀግኖች ነው። እነ ፊታውራሪ ሃብተጎርጊስ ዲነግዴን እና እነ ባልቻ አባ ነፍሶ። ቴዲ አፍሮ ለነዚህ ጀግኖች ባያቀነቅንላቸውም ከታሪክ መዝገብ ላይ ልንፍቃቸው አንችልም። የታሪክ ተመራማሪዎች ስለነዚህ ጀግኖች የጻፉት አፈ-ታሪክ ወይንም ድርሰት አይደለም። በጀግኖቹ የምንኮራው በዘራቸው ሳይሆን የሰሩት ገድል ነው። በ’ጥቁሩ ሰው’ የተመራው ይህ የጸረ-ቅኝ ግዛት ገድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው አፍሪካና ለጥቁር ህዝቦች ነጻነት ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል። ይህ ሊዋጥላችሁ የሚገባ እውነታ ነው። በዚያ ገድል የሚያፍሩ ካሉ የራሳቸው ጉዳይ። መላው የአፍሪካ ህዝብ ግን ይኮራበታል። የአለም ጥቁር ህዝብም ሲያስታውሳቸው ይኖራል። ዘር እየቆጠርን ከሄድን ብዙ የሚጎረብጡ ነገሮችን ልናነሳ ነው። በግዛት ማስፋፋቱ ሂደት ግን አንድ ሃቅ አለ። ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ህልቀ መሳፍርት ኢትዮጵያዊ አልቋል። ይህ ደግሞ የድንበር መስፋፋት፤ እድገት እና ስልጣኔ ይዞት የሚመጣው ችግር እንጂ አንድን ህዝብ ለመጨረስ ጥናት ተደርጎ የተሰራ እንዳልሆነ ታሪኩን ከስር መሰረቱ ማየቱ ይበጃል። ችግሩ በእኛ ላይ ብቻ ሳይሆን በአያሌ ሃገሮች እንደተከሰተ የታሪክ መዛግብት ይነግሩናል። በ17ኛው ክፍለዘመን የተከሰተው የኢንዱስትሪ አብዮት ሳብያ እንኳን ከሁለተኛው የአለም ጦርነት የማይተናነስ እልቂት ነበር። አጼ ምኒሊክን ከጀርመኑ ኦቶ ቮን ቢስማርክ ጋር የሚያመሳስሉ ምሁራንም አሉ። እርግጥ ነው ጀርመን አሁን የያዘችውን ግዛት ቅርጽ እንድትይዝ ያደረገው ፕሩሲያዊው ቢስማርክ ነው። ቢስማርክ የጀርመንን አንድ ታላቅ ኤምፓየር ለመፍጠር አንባገነን፣ ሃይለኛና ጦረኛ መሆን ነበረበት። ታዲያ ይህችን ሃያል ሃገር በመመስረቱ ጀርመኖች አልጠሉትም። ይልቁንም የጀግንነት ስያሜ ለግሰውታል። አያሌ የመታሰቢያ ሃውልቶችንም አቁመውለታል። ቢስማርክ የህግ ምሁር ነበር። አጼ ምኒሊክ ግን መደበኛም ሆነ ዘመናዊ ትምህርት የተማሩ ሰው አልነበሩም። ከታሪክ እንደምንረዳው በአጼ ልብነድንግል ዘመነ መንግስት፤ የግራኝ አህመድ ወረራን ተከትሎ የነበረውን መከፋፈልና መተላለቅ ለማስቆም መሪዎች ተነሱ። ሃገርን አንድ የማድረጉን ትግል አጼ ዮሃንስ ጀመሩት፣ አጼ ቴዎድሮስ ቀጠሉበት ከዚያም እምዬ ምኒሊክ ተረከቡት። አጼ ምኒሊክ ለአመታት በኦነግ ሰዎች ተወግዘዋል። ውግዘቱ አሁንም እታገልለታለው የሚሉትን ህዝብ ችግር ሲፈታው አለየንም። በ1991 ከህወሃት ጋር ጋብቻ ፈጽመው የምኒሊክ ቤተ-መንግስት ሲገቡ ይናገሩት የነበረውን ሁሉ ረሱት። ከቶውንም ያነሱት የነበረው የኦሮሞ ህዝብ የመብት ጉዳይ ሳይሆን የስልጣን ጥያቄ ለመሆኑን አረጋገጡልን። የሽግግር መንግስቱን ቻርተር ሲያጸድቁ “ኢትዮጵያዊ አይደለንም” የሚለውንም ሳያውቁ ዘንግተውት ነበር። ከገዢው ፓርቲ ጋር የጀመሩት ግዚያዊ ጋብቻ በፍቺ ሲጠናቅቅ የምኒሊክ ጠላትነት መፈክራቸውን እንደገና አነሱት። የዘር ፖለቲካው ስካር ሞቅ ብሎ በነበረበት በዚያን ወቅት እንደቀልድ ይነገር የነበረ አንድ ቁም ነገር አለ። አንድ የምግብ ቤት በር ላይ በላቲን ፊደል “አማራ መግባት ክልክል ነው!” የሚል ጽሁፍ ሰፍሯል። የጽሁፉ ትርጉም ያልገባው አንድ የአማራ ተወላጅ ጎራ ብሎ ምግብ አዘዘ። አስተናጋጆቹ የሰውየው ድፍረት አስደነገጣቸው። ባለስልጣን ስለመሰላቸው አስተናገደዱት። ዳግም እንዳይመለስም እጥፍ ዋጋ አስከፈሉት። ሰውየው በድጋሚ ሲመጣ ሶስት እጥፍ አስከፈሉት። በሌላ ግዜ ከአምስት ጓደኞቹ ጋር መጥቶ ምግብ አዘዘ። ከተስተናገደ በኋላም አራት እጥፍ ቢል አቀረቡለት። በዚህ ግዜ ቲፕም ጨምሮ ሰጣቸው። የሆቴሉ ባለቤት በነጋታው “አማራ መግባት ክልክል ነው!” የሚለውን ጽሁፍ አንስቶ “ኦሮሞ መግባት ክልክል ነው!” በሚል ቀየረው። በአሁኑ ዘመን ከበድ አለ እንጂ፣ ሰዎችን በጎሳ አደራጅቶ ከማሳደም የቀለለ ትግል የለም። ደም ከውሃ ይወፍራል እንዲሉ፤ ሰዎች በጋራ የሚጋሩትን ነገር እያነሱ ስነልቦናዊ ዘመቻ ማድረግ ስኬት ሊኖረው ይችላል። ዘለቄታ ግን አይኖረውም። የዘር ፖለቲካ ልክ እንደ ስካር ነው። ይሞቃል ከዚያም ይበርዳል። በርግጥ በሞቅታ ግዜ የሚፈጠረው አደጋ ቀላል ላይሆን ይችላል። እ.ኤ.አ. በ1993 በምስራቅና በምእራብ ኢትዮጵያ የተፈጸመው አሰቃቂ ወንጀል ለዚህ ዋቢ ነው። የኦነግ ልሂቃን የ19ኛውን ክፍለ ዘመን ጉዳይ እየደጋገሙ ያነሱልናል። በ21ኛው ክፍለ ዘመን በራሳቸው እጅ የተፈጸመው ግድያ ግን በብሄራዊ ቴሌቭዥን ጭምር እንድናየው ተደርጓል። ነብሰ-ጡር ሴቶች በጩቤ ሆዳቸውን እየተሰነጠቁ ሲገደሉ አየን። ነብስ ያላወቁ ሕጻናትና የ90 አመት አዛውንት ጭምር ከተራራ ላይ እየተወረወሩ ሲጣሉም የአይን ምስክሮች ነን። እነዚህ ሰዎች የምናስታውሰው ይህን በመሰለ ወንጀል ብቻ አይደለም። ድርጊቱ የቂምና የቁርሾ አሻራ ጥሎ አልፏል። ይህ ሁሉ በደል በዘመናችን ተፈጸመ። በዳዮቹ ግን አሁንም በቀልን አርግዘው ይጓዛሉ። የበደሌ ቢራን አለመጠጣት የኦሮሞን ችግር የሚፈታ ከሆነ፤ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ቢራውን መጠጣት ያቁም። የአኖሌን ሃውልት መሰራት ለኦሮሞ ህዝብ ፍትህ የሚያመጣ ከሆነ ደግሞ፤ ሃውልቱ በየከተማው ይገንባ። ግና ይህ ሃውልት ለመጭው ትውልድ ጥሎት የሚያልፈው ቂምና በቀልን እንጂ፤ ለሚታገሉለት ህዝብ የፍትህ ጥያቄ ዋስትናው ምን እንደሆነ ልንረዳው አልቻልንም። አሁን ያለው ትውልድ ያልፋል። ከዚህ ትውልድ በኋላ ለሚወለዱት ልጆች ጥለንላቸው የምናልፈው ቅርስ ጥላቻ፣ ቂም እና በቀል ብቻ ይሆናል። ከዘመናችን ታላቅ ሰው ከኔልሰን ማንዴላ አንድ ነገር እንማር። ማንዴላ የደቡብ አፍሪካን ብቻ ሳይሆን የአለምን ፖለቲካ የለወጠ የፖለቲካ ነብይ ነው። ይህንን ሲያደርግ የፖለቲካ ፎርሙላ አልነበረውም። ክፉን ነገር በበጎ ለማሸነፍ ወሰነ። ጥላቻን በፍቅር ለወጠ። ልክ እንደ ክርስቶስ፣ የበደሉትን ሁሉ ይቅር ብሎ በፍቅር አሸነፋቸው። ታሪክ ሰርቶ አለፈ። ስሙም ከመቃብር በላይ ለዘልአለሙ ይኖራል።