Thursday, 25 December 2014

በነ ሀብታሙ አያሌው የክስ ጉዳይ የተሰየመው ችሎት ‹አስገራሚ› ውሎ

∙ተከሳሾቹ ‹‹ዘረፋ›› ተፈጽሞብናል ብለዋል ∙‹‹ለማን አቤት ይባላል?›› ሀብታሙ አያሌው በላይ ማናዬ ዛሬ ታህሳስ 15 ቀን 2007 ዓ.ም በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮችን ጨምሮ 10ሩም ተከሳሾች በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛው ወንጀል ምድብ ችሎት ቀርበው ነበር፡፡ የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና አቶ አብርሃ ደስታ እንዲሁም አንደኛ ተከሳሽን ጨምሮ ስድስት ተከሳሾች ተሟልተው ፍርድ ቤት ተገኝተዋል፡፡ ችሎቱ የተሰየመው ታህሳስ 9 ቀን 2007 ዓ.ም በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ ወቅት ተከሳሾች በቀረበባቸው የሽብር ክስ ላይ የሰጡትን መልስ በተመለከተ 7ኛ ተከሳሽ መልስ በዕለቱ ባለማቅረባቸው አሟልተው እንዲቀርቡ ነበር፡፡ በተጨማሪም ተከሳሾች በእስር ላይ ባሉበት ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሊጎበኟቸው የሚሄዱ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው ወደ እስር ቤቱ ሲገቡ በተለየ መዝገብ እንዲመዘገቡ እየተደረጉ መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበው ስለነበር ይህን በተመለከተ ማረሚያ ቤቱ ማብራሪያ እንዲሰጥ በታዘዘው መሰረት ማብራሪያውን ለመስማት ነበር፡፡ የተከሳሾች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች በጥየቃ ወቅት በተለየ መዝገብ ይመዘገባሉ የተባለውን አቤቱታ በተመለከተ፣ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በደብዳቤ መልስ መስጠቱ የተገለጸ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ‹‹ማረሚያ ቤቱ በሰጠው መልስ እስረኞች ከሌሎች በተለየ የደረሰባቸው ችግር የለም›› ማለቱን ገልጾ ይህንኑ መልስ ሙሉ ለሙሉ መቀበሉን አስታውቋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን በዛሬው የችሎቱ ውሎ ላይ ተከሳሾች ለየት ያለ አቤቱታ በጠበቆቻቸው በኩል አቅርበዋል፡፡ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ለችሎቱ እንዳስረዱት ደንበኞቻቸው ከሌሎች በተለየ መልኩ ከፍተኛ በደል እየተፈጸመባቸው ነው፡፡ አቶ ተማም አባቡልጉ በታህሳስ 12 ለ13 ቀን 2007 ዓ.ም አጥቢያ ሌሊት ስምንት ሰዓት ጀምሮ ደንበኞቻቸው ላይ ድንገተኛ ፍተሻ ተደርጎ የግል ማስታወሻዎቻቸው፣ ገንዘብ እና በተከሰሱበት ጉዳይ ላይ እያዘጋጁት የነበረው መቃወሚያና መከራከሪያ ተወስዶባቸዋል ብለዋል፡፡ ‹‹ደንበኞቼ ላይ እየተደረገ ያለው ጉዳይ ለህይወታቸውም የሚያሰጋቸው ነው፡፡ በማረሚያ ቤቱ በሌሊት ፍተሻ ያደረጉባቸው ሰዎች ቀደም ሲል በምርመራ ወቅት ‹ህገ-ወጥ› ተግባራት ሲፈጽሙባቸው የነበሩ የፌደራል ፖሊስና የደህንነት አባላት ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህን ሰዎች ደንበኞቼ ያውቋቸዋል፡፡ ስለሆነም ፍተሻው የተከናወነው በማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች አልነበረም ማለት ነው፡፡ ድርጊቱ የተፈጸመው የተለየ የስም ዝርዝር ተይዞ ከሌሎች በተለየ መልኩ ነው፡፡ ለአብነት ደንበኞቼ አቶ አብርሃ ደስታና በሌላ የክስ መዝገብ የተከሰሰው አብዱራዛቅ አክመድ ላይ የሆነው ከሌሎቹ በተለየ መልኩ ነው፡፡ ፍተሻው ስለት ነገር አልያም ሌላ ህገ-ወጥ ቁሳቁስ ለመያዝ የተደረገ አለመሆኑን ከተወሰዱት ንብረቶች ማየት ይቻላል›› ሲሉ አቶ ተማም ለፍርድ ቤቱ በደንበኞቻቸው ላይ የተፈጸመውን ድርጊት አስረድተዋል፡፡ ይህን በተመለከተ አስተያየት የሰጡት የፌደራል አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ በበኩላቸው፣ ‹‹ማረሚያ ቤቱ መንግስት ዜጎች ታንጸው እንዲወጡ ያሰራው ነው፡፡ ይህን አሰራር ለመጠበቅም የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር የተለያዩ ስራዎችን ሊሰራ ይችላል፡፡ እየቀረበ ያለው አቤቱታም ከዚህ አኳያ መታየት ያለበት ነው›› ብለዋል፡፡ ጠበቃ ተማም የደንበኞቻቸውን አቤቱታ ከህግ አንጻር ያስረዱ ሲሆን፣ ‹‹በመሰረቱ ፍተሻ ሊካሄድ መቻሉ ላይ አይደለም አቤቱታው፡፡ የተካሄደው ፍተሻ ግን ህገ-ወጥ ነው፤ ምክንያቱም ፍተሻው የተከናወነበት ሰዓት ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ባለው ጊዜ ሳይሆን ሌሊት 8 ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡ ይህ ህገ-ወጥ ነው፡፡ በሌላ በኩልም ፍተሻው በማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች አይደለም የተከናወነው፡፡ በደህንነቶችና የፌደራል ፖሊሶች ነው ፍተሻው የተደረገው፡፡ ይህም ማረሚያ ቤቱ ደንበኞቼን ለመጠበቅ ፍላጎቱም ሆነ ብቃቱ እንደሌለው ያሳያል፡፡ ስለሆነም ፍርድ ቤቱ ይህን መሰል ድርጊት የፈጸሙት አካላትና በማን ትዕዛዝ እንደተፈጸመ ምርመራ እንዲካሄድ ትዕዛዝ እንዲሰጥልን እንጠይቃለን›› ብለዋል፡፡ ጠበቃ ተማም በተጨማሪ ከደንበኞቻቸው ላይ በፍተሻው ወቅት የተወሰዱባቸው ንብረቶችና ማስታወሻዎች እንዲመለሱላቸው ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው አመልክተዋል፡፡ ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ ‹‹የተለየ ከፍተኛ በደል ደርሶብኛል›› በሚል ለፍርድ ቤቱ እንዲያስረዱ ዕድል እንዲሰጣቸው ጠይቀው የነበሩት 3ኛ ተከሳሽ አቶ ዳንኤል ሺበሺ የጠየቁት የመናገር እድል ሳይፈቀድላቸው ቀርቷል፡፡ በጠበቆቹ አማካኝነት የቀረበው አቤቱታን በተመለከተ ችሎቱ አስተያየት የሰጠ ሲሆን በተለይ ጠበቃ ተማም አቤቱታውን ባቀረቡበት ወቅት ‹‹ማረሚያ ቤቱ ደንበኞቼን ለመጠበቅ ፍላጎትም ብቃትም የለውም›› ያሉት አገላለጽ ተገቢ ስላልሆነ እንዲታረሙ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡ ይህንኑ ጉዳይ በቃል የገለጹት የመሐል ዳኛው፣ ‹‹እንዲህ አይነት አገላለጽ ማረሚያ ቤቱ የበቀል እርምጃ እንዲወስድ የሚገፋፋ እንዳይሆን…›› በማለት ሌላ አስገራሚ መነጋገሪያ ከፍተዋል፡፡ ይህን የዳኛውን ንግግር ተከትሎ 2ኛ ተከሳሽ አቶ ሀብታሙ አያሌው የመናገር እድል ከተደጋጋሚ ጥያቄ በኋላ ለአጭር ጊዜ ተፈቅዶለታል፡፡ እናም፣ ‹‹እርስዎ እያሉት ያለው ነገር ተገቢ አይደለም፡፡ በህይወቴ ላይ የደህንነት ስጋት አለብኝ ነው እያልኩ ያለሁት፡፡ ይህንን ስጋቴን ለችሎት እያስረዳሁ ነው፡፡ ግን እርስዎ ‹የበቀል እርምጃ› እንዲወሰድብን ማሳሰቢያ እየሰጡ ነው፡፡ ይህ ተገቢ አይደለም፡፡ በእርግጥ አሁንም የበቀል እርምጃ እንደማይወሰድብን ማረጋገጫ የለንም፡፡ እሺ ለማን አቤት ይባላል? የደረሰብንን በደል ለፍርድ ቤት ከማስረዳት ውጭ ለማን አቤት እንላለን….አሁን እኮ ፍርድ ቤቱ ከማረሚያ ቤቱ ጋር መወገኑን ነው እያየን ያለነው፡፡ ፍርድ ቤቱ የእኛን አቤቱታ እየሰማ አይደለም፡፡ ከፍርድ ቤት ውጭ ለማን አቤት እንበል?›› ሲል አቤቱታውን በስሜት ውስጥ ሆኖ አስረድቷል፡፡ የሀብታሙን ንግግር አዳምጠው አንደኛ ዳኛ ‹‹እኛ ሳንሆን ህጉ ነው ይህን እንድንል የሚያደርገን›› በማለት አጭር መልስ ሰጥተዋል፡፡ በዚህ መልኩ ቀጥሎ የዋለው ችሎት በተከሳሾች በኩል የቀረበውን አቤቱታ መርምሮ ፍርድ ቤቱ ይህን ጉዳይ የማየት ስልጣን አለው ወይስ የለውም በሚለው ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት፣ እና መደበኛ ክሱን ለማየት ለታህሳስ 24 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተጥቷል፡፡

Monday, 1 December 2014

ከ40 በላይ የአንድነት አባላትና አመራሮች በቃሊቲ እስር ቤት ታገቱ

የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አስራት አብርሃን ጨምሮ ከአርባ በላይ የሚሆኑ የፓርቲው አባላት ቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ ታገቱ፡፡ አንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለህሊና እስረኞች በሚል መሪ ቃል ከህዳር 14 ጀምሮ እያካሄደያለው የማህበራዊ ሚዲያ ንቅናቄ አካል የሆነውን የህሊና እስረኞችን የመጎብኘት መርሀ-ግብር ለመሳተፍ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ያቀኑት የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አስራት አብርሃ እና የፓርቲው የአዲስ አበባ ሰብሳቢ አቶነገሰ ተፋረደኝን ጨምሮ 40 የአንድነት ፓርቲ አባላት ለግዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሰበብ በእስር ቤቱ ግዜያዊ ማቆያ እንዲገቡ መደረጋቸውን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ከስፍራው ዘግበዋል፡፡ አንድነት የሚሊዮኖች ድምፅ ለህሊና እስረኞች በሚል መሪቃል በዚህ ሳምንት እያካሄደ ያለው ንቅናቄ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን ትኩረት ማግኘቱ ገዢውን ቡድን ማስቆጣቱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ዘግይቶ የደረሰን ዜና እንዳመለክተው ከሆነ ደግሞ; የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ነገሰ ተፈረደኝ፣ ንዋይ ገበየሁ፣ ዳንኤል ሙላትና አቶ ብርሐኑና ትግስት ክራውን ሆቴል አካባቢ አሁንም ታስረው እንደሚገኙ ምንጮች ገለጹ፡፡ ስማቸው ከላይ የተጠቀሱት ግለሰቦች የታሰሩ የህሊና እስረኞችን ለመጠየቅ ወደቃሊቲ አምርተው ከነበሩት ሰዎች መካከል ይገኛሉ፡፡

Wednesday, 26 November 2014

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አመራሩ ድብደባ እንደተፈጸመበት ገለፁ።

አንድ ወር የትግል መርሃ ግብር ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎችና ህዝባዊ የለውጥ ንቅናቄዎችን በገዥው ፓርቲ አፈና እና ማስፈራሪያ እንደማይቆም ትብብሩ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡ ህዳር 7/2007 ዓ.ም የትብብሩ ህዝባዊ የአደባባይ ስብሰባ በኃይል መበተኑን፣ ይህንኑ አስመልክቶ ህዳር 7/2007 ዓ.ም ለሰማያዊ ፓርቲ ማስጠንቀቂያ መጻፉን እና ለህዳር 21 ለሚደረገው ስብሰባ የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ደብዳቤ በፖስታና በአካል ቢላክለትም ማሳወቂያ ክፍሉ አልቀበልም ማለቱን የገለጸው መግለጫው ስርዓቱ የትብብሩን የትግል መርሃ ግብር ለማስቆም እየጣረ መሆኑን ገልጾአል፡፡ በተጨማሪም የትብብሩ አንድ አባል እና ትብብሩ ህዳር 21/2007 ዓ.ም የሚያደርገውን የአደባባይ ስብሰባ የሚያስተባብረው መኢዴፓ ሊቀመንበርና የትብብሩ ገንዘብ ያዥ የሆኑትን አቶ ኑሪ ሙደሲር ላይ የድብደባ ወንጀል እንደተፈጸመባቸው አመራሩ ገልጸዋል፡፡ ትብብሩ በዛሬው ዕለት ‹‹ማስፈራራትና አፈና የዴሞክራሲ ጥያቄዎችንና ሠላማዊ ሕዝባዊ የለውጥ ንቅናቄዎችን አይቀለብስም›› በሚል በሰጠው መግለጫ የተገኙት አቶ ኑሪ ሙደሲር ከሁለት ሳምንት በፊት ጀምሮ ወከባ እንደተፈጸመባቸው ገልጸዋል፡፡ አቶ ኑሪ ‹‹መኪናችን ገጨህብን ባሉ 10 ሰዎች ነው የተደበደብኩት፡፡ ከአሁን ቀደምም ፖሊሶች ምንም አይነት ችግር ሳላደርስ ገጨህብን ብለው አዋክበውኛል፡፡ ሰሞኑን መኪናዬን ቢሰብሩብኝም በስህተት የተመታ መስሎኝ ነበር፡፡ አሁን ከደበደቡኝ መካከል ተክለኃይማኖት አካባቢ የሚገኙ ካድሬዎችና ደንብ አስከባሪዎች ይገኙበታል፡፡ መጀመሪያ ላይ ፖሊሶች ‹ቢገጭስ እንዴት 10 ሆናችሁ አንድ ሰው ትደበደርባላችሁ?› ካሉ በኋላ እንደገና ካድሬዎች መሆናቸውን ሲያውቁ እነሱን ትተው እኔን ይወቅሳሉ፡፡ ይህም የሚያሳየው ሆን ተብሎ የተደረገ ነገር መሆኑን ነው›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ህዳር 21/2007 ለሚደረገው የአደባባይ ስብሰባ በአካልም ሆነ በፖስታ ደብዳቤ ቢላክም የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍሉ ባለመቀበሉ የትብብሩ ደብዳቤ በፋክስ እንዲደርሰው እንደተደረገ የትብብሩ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ገልጸዋል፡፡ ሆኖም በፋክስ የተላከውን ደብዳቤ አልቀበል ካለ የትብብሩ አመራሮች በጋራ ደብዳቤውን ለማድረስ እንደሚሄዱ፣ የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍሉ ይህንም አልቀበልም ካለ ሁነቱን በቪዲዮና በፎቶ በመቅረጽ ለህዝብ በማሳወቅ ስብሰባውን እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡ በሂደቱም የሚከፈለውን መስዋዕትነት ሁሉ ለመክፈል እንደተዘጋጁ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ገልጸዋል፡፡

Friday, 14 November 2014

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ፖሊስ ጣቢያዎችን እንዲሰሩ ተጠየቁ

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በየ አካባቢያቸው ለሚሰሩት አዳዲስ ፖሊስ ጣቢያዎች ገንዘብ እንዲያዋጡ መጠየቃቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ በየ አካባቢው የሚገኙት የፖሊስ ጣቢያዎች ነዋሪዎች ገንዘብ እንዲያዋጡ በየ ቤታቸው ደብዳቤና የገንዘብ መክፈያ ቅጽ እየሰጡ ሲሆን ነዋሪዎቹ ገንዘብ እንዲከፍሉ የተጠየቁበትን ቅጽ ሳይሞሉ መመለስ አይችሉም ተብሏል፡፡ ደብዳቤው ላይ ባለው የፖሊስ ጣቢያው ስልክ ቁጥር ደውለን ያነጋገርናቸውና ስማቸውን ለመግለጽ ፈቃደኛ ያልሆኑ አንድ የፖሊስ አባል ‹‹ህዝቡን ለምን ፖሊስ ጣቢያ እንዲሰራ ታስገድዳላችሁ?›› በሚል ላነሳነላቸው ጥያቄ ‹‹ህዝቡኮ ራሱ ነው ሴት ልጆቻችን በሰላም መግባት አልቻሉም እያለ ያለው፡፡ ፖሊስ የህዝብ እስከሆነ ድረስ ህዝብ ፖሊስ ጣቢያ ቢያሰራ ምን ችግር አለው? ህዝቡ አልከፍልም ካለ ሊቀር ይችላል፡፡ እናንተ ግን ይህን እንደጥያቄ የምታነሱት ስብሰባው ላይ ስላልነበራችሁ ነው፡፡›› ብለውናል፡፡ ከወራት በፊት ‹‹ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ›› በሚል አደረጃጀት ህዝቡ በየቤቱና ከጎረቤት ጋር 1ለ5 በመደራጀት ከፖሊስ ጋር ግንኙነት እንዲኖረው የሚያዝ ህግ መውጣቱና ነዋሪዎቹንም ማደራጀት መጀመሩን ነገረ ኢትዮጵያ መዘገቧ ይታወቃል፡፡

Wednesday, 12 November 2014

የፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ልዩ አማካሪ አቶ አሰፋ ከሲቶ ተነሱ፡፡

የፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) ልዩ አማካሪ አቶ አሰፋ ከሲቶ ተነሱ፡፡ አቶ አሰፋ የተነሱት በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ፊርማ በተጻፈ ደብዳቤ ነው፡፡ በአቶ ኃይለ ማርያም ፊርማ የወጣው ደብዳቤ፣ አቶ አሰፋ ከኃላፊነት የተነሱበትን ምክንያት ያልጠቀሰ ሲሆን፣ አቶ አሰፋም በምን ምክንያት እንደተነሱ እንዳላወቁ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ‹‹ወደፊት የሚተገበሩ አዳዲስ ፕሮግራሞችን እየቀረፅኩ ነበር፤›› በማለት ከኃላፊነት መነሳታቸው ያላሰቡትና ያልጠበቁት እንደሆነ አቶ አሰፋ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ደብዳቤው በጥቅሉ፣ አቶ አሰፋ ከኅዳር 2001 ዓ.ም. ጀምሮ የፕሬዚዳንቱ ልዩ አማካሪ በመሆን ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋናውን ገልጿል፡፡ በሥራ አፈጻጸምም ሆነ በሙስና እንዳልተገመገሙ አቶ አሰፋ ለሪፖርተር ገልጸው፣ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር አዲስ የሥራ መደብ እንዲሰጣቸው ደብዳቤ መጻፉን ተናግረዋል፡፡ የሸካ ዞን፣ የኪ ወረዳ፣ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ተመራጭ የነበሩት አቶ አሰፋ፣ የክልሉ ፀረ ሙስና ምክትል ኮሚሽነርና የደቡብ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሠርተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለአምስት ዓመታት የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር ሆነው ሠርተዋል፡፡ አቶ አሰፋ የፕሬዚዳንቱ ልዩ አማካሪ ከመሆናቸው በፊት፣ የፍትሕ ሚኒስትር ሆነውም ሠርተዋል፡፡ አቶ አሰፋ የፍትሕ ሚኒስቴርን ለሦስት ዓመታት ከመሩ በኋላ ከቦታው ተነስተው የፕሬዚዳንቱ ልዩ አማካሪ ሆነው ተሰይመዋል፡፡ አቶ አሰፋ ላለፉት ስድስት ዓመታት የቀድሞውን ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስንና በቅርቡ ፕሬዚዳንት ሆነው የተሰየሙትን ዶ/ር ሙላቱ ተሾመን ሲያማክሩ ቆይተዋል፡፡

Tuesday, 11 November 2014

ግልጽ ደብዳቤ ”ለጠቅላይ ሚኒስትር” ኃይለማርያም ደሳለኝ : ከታሳሪ ዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሕገ መንግስታችንን ያክብሩ! ሠላም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር!? እንዴት ነዎት? ያስታውሱ ከሆነ የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢከፊሉ የዚህ ማስታወሻ ፀሃፊዎች ‘ግልፅ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ’ “ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እባክዎትን የተለያዩ የመንግስት አካላት የሕገ መንግስታችንን ድንጋጌዎች እየጣሱ ነውና እርስዎም በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 74/13/ መሠረት ሕገ መንስቱን የማስከበርና የማክበር ግዴታ ስላለብዎት ሕገ መንግስቱን ያክብሩ” በማለት አንዲት አጭር ደብዳቤ ፅፈንልዎት ነበር፡፡ ድንገት በተለያዩ ምክንያቶች የጻፍንልዎትን ደብዳቤ ካላነበቡት ወይም ማስታወስ ካልቻሉ ዛሬ ይሄን ማስታወሻ ስለምንፅፍልዎት ግለሰቦች አንድ ሌላ ማስታወሻ እንስጥዎ፡ ከ6ወራት በፊት /በሚያዚያ 2006 ዓ.ም/ ሶስት ጋዜጠኞችንና ስድስት ጦማሪያንን ‘ሕገ መንግስቱንና ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ በመሞከር ወንጀል ጠርጥሬያችኋለሁ’ በማለት መንግስትዎ ልማታዊ ርምጃ (አብዮታዊ ርምጃ እንደሚባለው) ወስዶ ነበር፡፡ እኛም የዚህ ማስታወሻ ፀሃፊዎች የዚህ ‘ልማታዊ ርምጃ’ ሰለባ የሆንን ግለሰቦች ነን፡፡በርግጥ ከሁለት ዓመታት በፊት ‘ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሕገ መንግስቱን’ ያስከብሩልን በማለት ጥያቄ ያቀረብንልዎት ግለሰቦች ‘ከ6 ወራትበፊት ሕገ መንግስቱን ለመናድ ሞክራችኋል’ በማለት መንግስትዎ ሲያስረን ሕገ መንግስቱ እንዲከበር ጠይቀን ሕገ መንግስቱን ለመናድ በመሞከር ወንጀል ተጠርጥረን ስንታሰር እስሩ በጣም ግራ አጋብቶን ነበር፡፡በዚህ ያልቆመው መንግስትዎ ክሱን ‘ሕብረተሰቡንና ሀገሪቱን ለማሸበር አቅዳችኋል ሞክራችኋል አሲራችኋል…’ በማለት ወደ ‘ሽብርተኝነት’ያሳደገው ሲሆን እርስዎም ከዚህ ጋር በተያያዘ ሃሳብዎትን ሲሰጡ ስለተመለከትንዎ ትንሽ ቅሬታ ይዘን መጣን፡፡ በቅድሚያ አሁን ያለንበትን ሁኔታ በትንሹ ብናስረዳዎት ቅሬታችንን ለመረዳት ያስችልዎታልና አንዳንድ ጉዳዮችን እንንገርዎት፡፡ ይሄን ማስታወሻ በምንፅፍልዎት ወቅት ከታሰርን ከ 200 ቀናት የተቆጠሩ ሲሆን፣ነገር ግንጉዳያችን ገና በቅድመ ክስ (Pre Trial) የክርክር ሂደት ላይ ይገኛል፡፡ ይሄ የሆነበት ዋነኛ ምክንያትም መንግስትዎ እንኳን ለእኛ ለተከሳሾች ለከሳሽ አካልም ግልፅ ያልሆነ ክስ በማቅረቡ ነው፡፡ ይሄንንም ስንል ልትፈፅሙት ነበር የተባለው ‘የሽብርተኝነት ድርጊት’ ሳይጠቀስ ‘በቃ የሽብርተኝነት ድርጊት ልትፈፅሙ ነበር’ በማለት በጨበጣ ስለመጣብን ነው፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እንግዲህ የብዙ ድብደባ፣ ዛቻ እና ስድብ ሰለባዎች ከሆንን በኋላምየቀረበው ይሄ ክስ ነው ከ6 ወራት በኋላም ተከሳሾች ከሳሾቻችንምሳንረዳው በየቀጠሮው እየታሸ ነው የሚገኘው፡፡ ‘የተፋጠነ ፍትህ’ ሕገ መንግስትዊ መብት ነውና የተፋጠነ ፍትህ ይሰጠን፣ እርስዎምይሄን ሕገ መንግስታዊ መብት ያክብሩ እያልንዎት አይደለም ‘ሕገ መንግስቱ ተከብሮ እያለ ሕገ መንግስቱ ይከበር በማለቴ ጥፋተኛ ነኝ’በማለት ‘ጥፋት የሚያሳምን’ ( አንዱ የዚህ ደብዳቤ ጸሃፌ ጦማሪ ጥፋት ብሎ አንዲፈርም የተገደደው ህገ መንግስቱ ተከብሮ እያለህገመንግስቱ ይከበር ማለቴ ጥፋት ነው ብሎ መሆኑ መንግስትዎን መልክ ግልጽ አድርጎ ያሳያል) መንግስት አለዎትና ይህ ጥያቄ አንደሚበዛብዎትእናውቃለን፡፡ ይልቁንም ቀላልና ግልፅ ቅሬታን ነው ይዘን የመጣነው፡፡ ይሄውም የኢፌድሪ ሕገ መንግስትበአንቀፅ 20/3/ ላይ ‘የተከሠሡ ሰዎች[…] በፍርድ ሂደት ባሉበት ጊዜ በተከሰሱበት ወንጀል እንደ ጥፋተኛ ያለመቆጠር[…]መብት አላቸው::’ በማለት የደነገገ ሲሆን፣ ይሄንን ሕገ መንግስታዊ መብትም ማንኛውም የመንግስት አካል እንዲሁም ግለሰብ የማክበር ግዴታ አለበት፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር እርስዎና መንግስትዎም በተደጋጋሚ ‘ሕገ መንግስቱ ሳይሸራረፍ እናስከብራለን’ ይላሉና ይሄን ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌ የምታውቁት ይመስለናል፡፡ ነገር ግን ከታሰርን ወዲህ ስለእኛ የእስር ጉዳይ በተጠየቁባቸውጊዜያት ይሄን ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌ በመጣስ ‘ፍርድዎትን’ በተደጋጋሚ ሲሰጡ ታዝበናል፡፡ እናስረዳዎ፡- ሐምሌ 12/2006 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣሚ መግለጫ ላይ ስለእኛ እስር ጉዳይ ለቀረበልዎት ጥያቄ ሲመልሱ፡- ‘ከአስመራ እስከ ሞቃዲሾ የተዘረጋው የሽብር ሰንሰለት ውስጥ አንዴከገቡ በኋላ ብሎገር ነኝ፣ ጋዜጠኛ ነኝ ማለት ዋጋ የለውም’ በማለት ብዙ ነገሮችን ተናገሩ፡፡ ይሔውልዎት ስህተትዎ፡- 1. የክሳችን ዋነኛ ጭብጥ በሃገርውስጥ ‘የሽብርተኛ ድርጅት በማቋቋም ‘የሽብርተኝነት’ ተግባራትን ለመፈጸም አሲረዋል፡ አቅደዋል… የሚል እንጂ፣ እርስዎም እንደሚሉት ‘ሰንሰለት’ ምናምን አይደለም፣ 2. እሺ አሸባሪዎችም ይበሉን፣ነገር ግን ሕገ መንግስቱ እንደሚደነግገው በፍርድ ቤት ‘ጥፋተኝነታችን’ እስሚረጋገጥ ቢጠብቁስ ምናለበት? ይህ የሚያመለክተው እርስዎም እንደ ማእከላዊ መርማሪዎች ነፃ ሆኖ የመገመት (presumption of innocence) መብታችንን እያከበሩልን እንዳይደለ ነው፡፡ ይሄ ነገር የሆነው በድንገት ሊሆን ይችላል ብለንዝም ብንልም እርስዎ ግን በድጋሚ ጥቅምት 6/2007 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ከምክር ቤቱ አባል ለቀረበልዎ ጥያቄሲመልሱ፡- “የብሎገር ጭምብልአጥልቆና በጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ ተሸሽጎ ከተከሳሽነት ማምለጥ አይቻልም፡፡ ሽብርተኝነትን መዋጋታችን ይቀጥላል…” እያሉ እርስዎ ያሉትን የብሎገር ጭምብል አውልቀውና ተሸሸጉበት ያሉትን የጋዜጠኝነት ሙያመሸሸጊያ አፍርሰው ባንዴ ‘የአሸባሪነት’ ካባ ደረቡልን፡፡ ክቡር ጥቅላይ ሚኒስቴር፣ እያልን ያለነው የአንድ ሰው ‘አሸባሪነት/ወንጀለኝነት’ የሚረጋገጠው በፍርድ ቤት እንደሆነ ሕገ መንግስቱ ደንግጎ እያለ፣ እርስዎ ግን ነፃ ሆኖ የመገመት መብታችን ወደ ጎን ብለው እንደ ከሳሽም እንደፈራጅም በመሆን ‘አሸባሪዎች’… እያሉን ይገኛሉ ነው፡፡ ምናልባት ‘ስራ አስፈጻሚው ከሳሽ ነውና እኔም የስራ አስፈጻሚው አካል መሪ ስለሆንኩ የፈለኩትን አስተያየት የመስጠት መብት አለኝ’ ብለው ከሆነ፣ ሕገ መንግስቱን የማክበር ጉዳይ ‘ርስዎን ጨምሮ ሁሉም ዜጎች ላይ የተጣለ ግዴታነው፡፡ እርስዎ ‘L’e’tat, c’est moi’ ይሉት አይነት የራስ ግምት ውስጥዎ ከሌለ በስተቀር እንዲህ በግልፅ እየጠየቅንዎት ‘ሕገ መንግስትቱን አላከብርም’ በማለት ገና ዋነኛ ክርክሩ እንኳንያ ልተጀመረ ክስን (ዋነኛ ክርክር ካለው) መሠረት በማድረግ ከዚህ በኋላ እኛን ‘አሸባሪዎች’ አይሉንም ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ይህን ተመሳሳይ ምላሽ “በእርግጠኝነት አሸባሪ ናቸው” በሚል ቃና ለቢቢሲ ለኢንቢሲ ለመሳሰሉት አለም አቀፍ ሚዲያ ተቋማትም መስጠትዎን ሰምተናል፡፡ ሌላው ልናስታውስዎ የምንፈልገው ጉዳይ እንደኛ አይነት የተራገበ( በሰፊው በታወቀ የአደባባይ)የፍርድ ጉዳይ ([un] popular case) ላይ የመንግስት አካላት አስተያየት (say) ያለውን ተፅእኖ እንዲያስቡት ነው፡፡እርስዎ በምክር ቤት ቀርበው የአሸባሪነት ፍርድ ከበየኑብን (አሁን እያደረጉት እንዳሉት) ፍርድ ቤትም ሆነ ሌሎች የመንግስትዎ አካላትምን ሊያስቡ እንደሚችሉ አስተውለውታልን?! ይሄን ሁሉ ስንልዎ እንዲያው ሕጉን ያክብሩልን ለማለት ያክል ነው እንጅ፣ ከሽብርተኝነትጋር የሚያገናኘን ቅንጣት ያክል እውነት /A segment of fact/ እንደሌለና የሰው ልጆች መልካምና ደስተኛ ሕይወት እንዲኖራቸውከመመኘትና ለአገራችን ያገባናል ከማለት ያለፈ ሕይወትም ፍላጎትም እንደሌለን እኛም እናውቀዋለን እርስዎና መንግስትዎም ያውቁታል፡፡ነገር ግን ካለፉት ስድስት ወራት አንስቶ ጨዋታውን በግድ ካልተጫወታችሁ ተብለናልና እየተጫወትን ነው፡፡ የአሁኑ ጥያቄያችን ግን በጣም ቀላል ነው፣ ጨዋታው ገና በደንብ እንኳን ሳይጀመር ውጤቱን እይወስኑት ነው፡፡ እርስዎ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት የስልጣን ደረጃ በወጡ ሰሞን አብዛኞች የዚህ ማስታወሻፀሃፊዎች መጠነኛ ለውጥና ማሻሻዎች ያደርጋሉ የሚል ተስፋ ሰንቀን “The First 100 Days” ወዘተ እያልን ብዙ ጠብቀንዎት ነበር፡፡ ከሁለት ዓመት በሚበልጥ ግዜ እንደተመለከትንዎ ግን ተስፋችን ፍሬ ሊያፈራልን አልቻለም፡፡ አሁንም አዲስ ተስፋ ሰንቀን ግን ፡-“ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር እባክዎትን ሕገ መንግስቱን ያክብሩ! የእኛንም መብት ያክብሩልን” እንላለን፡፡ ‘’የብሎገር ካልሲ አድርጎ፣ የጋዜጠኝነት ጫማ ተጫምቶ የሽብረተኝነት ሰንሰለት ውስጥ ከገቡ በኋላ ሕገ መንግስቱን ያክብሩልኝ ማለት ዋጋ የለውም!’’በማለት ተስፋችን ዋጋ እንደማያሳጡት ተስፋ አለን፡፡ ከአክብሮት ጋር ጦማርያን ጋዜጠኞች ዘላለም ክብረት ኤዶም ካሳዬ ናትናኤል ፈለቀ ተስፋለው ወ/የስ በፍቃዱ ሃይሉ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ አጥናፍ ብርሃኔ አቤል ዋበላ ማህሌት ፋንታሁን

Tuesday, 4 November 2014

ጦማርያንና ጋዜጠኞቹ ለሳምንት ቀጠሮ ተሰጠባቸው

ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2007 ዓ.ም በልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ለ10ኛ ጊዜ ችሎት የቀረቡት የዞን ዘጠኝ ጦማርያንና ሶስቱ ጋዜጠኞች ለሳምንት (ህዳር 3/2007 ዓ.ም) ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠባቸው፡፡ ፍርድ ቤቱ ዛሬ በጦማርያንና በጋዜጠኞቹ ቀደም ሲል የቀረበውን የክስ ማሻሻያ አቤቱታ መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም፣ ምርመራው አላለቀም በሚል ምክንያት አጭር ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በዛሬው ችሎት ላይ ከተሰየሙት ዳኞች መካከል ሁለቱ አዲሶች በመሆናቸው ምክንያት ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱን ጠበቃ አምሃ መኮንን ገልጸዋል፡፡ ዳኞች ብቻ ሳይሆን ችሎት ክፍሉም በመቀየሩ ክፍሉ ጠባብ ነው በሚል፣ የተከሳሽ ቤተሰቦችና ጋዜጠኞች ችሎት መግባት አለመቻላቸውም ታውቋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በነገው ዕለት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተከሳሾች ዋስትና ጉዳይ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ መያዙን አቶ አምሃ ጨምረው አስረድተዋል፡፡ በተከሳሾች በኩል ደግሞ፣ ሁለቱ ሴት ተከሳሾች (ኤዶም ካሳዬ እና ማህሌት ፋንታሁን) በቃሊቲ ማረሚያ ላይ ያነሱትን የመብት ጥሰት አቤቱታ በተመለከተ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር በቀጣይ ቀጠሮ ድጋሚ ቀርቦ እንዲያስረዳ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ ሁለቱ ተከሳሾች በቀን ለ10 ደቂቃ ብቻ ስማቸው ቀድሞ በተመዘገቡ ሰዎች ብቻ እየተጎበኙ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

Friday, 31 October 2014

አብርሃ ደስታ, ሀብታሙ አያሌዉ, የሽዋስ አሰፋ, ዳንኤል ሺበሺ, በይፋ ክስ ተመሰረተባቸው

• አብርሃ ደስታ የሁለት ድርጅቶች አባል ነው የሚል ክስ ተመስርቶበታል • ወደ አዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወሩ ታዟል በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር በልደታ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ምድብ ወንጀል ችሎት ዛሬ ጥቅምት 21/2007 ዓ.ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ በተሰየመው ችሎት 10 ተከሳሾች በፌደራል አቃቢ ህግ በይፋ ክስ ተመሰረተባቸው፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከ100 ገጽ በላይ የክስ ቻርጅ የተነበበላቸው ሲሆን ከክስ ቻርጁ ጋር ከ300 ገጽ በላይ የምርመራ ሰነድ ቀርቦባቸዋል፡፡ የክሱ መዝገብ የተከፈተው ዘላለም ወርቃገኘሁ በተባለውና ‹‹የግንቦት 7 አመራር ነው፡፡›› ተብሎ ክስ በተመሰረተበት ግለሰብ ሲሆን በዚህ የክስ መዝገብ የተካተቱትም፡- 1ኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ 2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው 3ኛ ተከሳሽ ዳንኤል ሺበሺ 4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታ 5ኛ ተከሳሽ የሽዋስ አሰፋ 6ኛ ተከሳሽ ዮናታን ወልዴ 7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሰለሞን 8ኛ ተከሳሽ ሰለሞን ግርማ 9ኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ደጉ 10ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ተፈሪ ናቸው ለሁሉም ተከሳሾች ከዛሬ በፊት ክስ እንዳልደረሳቸውና ዛሬ ፍርድ ቤት ውስጥ እንደተሰጣቸው ታውቋል፡፡ በችሎቱ 6ኛ ተከሳሽ ከሆነው ዮናታን ወልዴ በስተቀር ሁሉም ያለ ጠበቃ የቀረቡ ሲሆን ጠበቃዎቹ ያልቀረቡበት ምክንያትም ጠበቆቹ ደምበኞቻቸው የሚቀርቡበት ቦታና ጊዜ ስላልተነገራቸው እንዲሁም ቀደም ብለው እንዳይገናኙ በመደረጋቸው መሆኑን አቶ ኃብታሙ አያሌው ችሎቱ ላይ ተናግሯል፡፡ ከሳሹ የፌደራል አቃቢ ህግ በ1996 የወጣው የወንጀል ህግ እና የጸረ ሽብር ህግ ጠቅሶ ክስ ያቀረበ ሲሆን ክሶቹ በሁለት ዋና ዋና ጭብጦች ቀርበዋል፡፡ የመጀመሪያው ጭብጥ ‹‹ከሽብርተኛ ቡድኖች ጋር በጋራ በመስራት›› የሚል ሲሆን ‹‹ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ፣ የመንግስትን መሰረተ ልማት በማፈራረስ፣ ህዝብን ለአመጸ በማነሳሳት መንግስትን መለወጥ አላማው አድርጎ ከሚሰራውና ራሱን ግንቦት 7 ብሎ ከሚጠራው ቡድን ጋር አባል በመሆንና በወንጀል ድርጊቶች በመሳተፍ›› በሚል ቀርቧል፡፡ ሁለተኛው የክስ ጭብጥ ‹‹የሽብር ቡድን አመራር በመሆን›› የሚል ሲሆን በተለይም የአንደኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ ‹‹የሽብር ቡድኑ አመራር በመሆንና አባል በመመልመል›› በሚል የክስ ጭብጥ ቀርቦበታልል፡፡ ከ2-5ኛ የክስ መዝገብ የሚገኙት ማለትም ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሽ፣ አብርሃ ደስታና የሸዋስ አሰፋ ‹‹ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲን ከለላ በማድረግ ግንቦት 7 የተባለውን የሽብር ቡድን አላማ ለማሳካት ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ፋሲል የኔ ዓለምና ሌሎች የሽብር ቡድኑ አባላት ጋር በስልክ በመነጋገርና በማህበራዊ ድህረ ገጸ የተለያዩ መልዕክቶችን ተለዋውጠዋል›› የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡ አብርሃ ደስታ ከግንቦት 7 በተጨማሪ ‹‹ደምኢት የተባለ ቡድን አባል ነው፡፡›› የሚል ክስ ቀርቦበታል፡፡ በስተመጨረሻም ፍርድ ቤቱ ሁለት ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ አንደኛው ረቡዕ ጥቅምት 26/2007 ዓ.ም 3 ሰዓት ተከሳሾቹ ዋስትና ይሰጣቸው አይሰጣቸው በሚለው ጉዳይ ላይ ፍርድ ቤቱ ከተከሳሾቹ ጠበቆች ጋር ተማክሮ ውሳኔ ይሰጣል ተብሏል፡፡ በሁለተኛነት ተጠርጣሪዎቹ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ቀደም ሲል ለአራት ወራት ወደቆዩበት ማዕከላዊ እስር ቤት እንዳይመለሱ ፍርድ ቤቱን ስለጠየቁ ፍርድ ቤቱ በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት (3ኛ) እንዲቆዩ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ ተከሳሾቹ ትናንት ጥቅምት 20/2007 ዓ.ም አራዳ ምድብ ችሎት ይቀርባሉ ተብሎ የነበር ቢሆንም ሳይቀርቡ ቀርተዋል፡፡ በተመሳሳይ ዛሬ ጥቅምት 21/2007 ዓ.ም ጠዋት ወደ ልደታ ፍርድ ቤት ተወስደው የነበረ ቢሆንም እንደገና ወደማዕከላዊ ተመልሰው ከሰዓት እንዲቀርቡ ተደርገዋል፡፡

Wednesday, 29 October 2014

ፕሬዚዳንት ኦባማ ስለኢትዮጵያ ምርጫ ምን ያህል “ያውቃሉ”? ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ ፕሬዚዳንት ኦባማ እ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው “ምርጫ” ምን ያህል ያውቃሉ? ባለፈው ሳምንት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በኢትዮጵያ ካለው የገዥው አካል የልዑካን ቡድን አባላት ጋር በዚህ በዋሽንግተን ዲሲ ላይ በመገናኘት እንዲህ የሚል ንግግር አሰምተው ነበር…”በዚህ ዓመት ጠቅላይ ሚስትር [ኃይለማርያም ደሳለኝ] እና መንግስታችሁ በኢትዮጵያ ምርጫ ለማካሄድ የዝግጅት እንቅስቃሴ በማደረግ ላይ ትገኛላችሁ፡፡ ስለዚያ ጉዳይ ጥቂት ነገሮችን አውቃለሁ…እናም ስለሲቪል ማህበረሰቡ እና ስለመልካም አስተዳደር እንደዚሁም ኢትዮጵያ እስከ አሁን ድረስ ያስመዘገበችውን አንጸባራቂ እድገት እና ተምሳሌትነት እንዴት አድርጎ ወደ ሲቪል ማህበረሰቡም ማሸጋገር እንደሚቻል ለመነጋገር ጥሩ አጋጣሚ ይፈጥርልናል…“ ገና ከመጀመሪያው ጀምሬ አስተያየቴ ምን ላይ አንዳተኮረ ግልጽ ላድርግ፣ ይህ የአሁኑ ትችቴ ትኩረት አድርጎ የሚያነጣጥረው ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በተለየ መልኩ በፕሬዚዳንት ኦባማ ላይ ነው፡፡ ለዚህም ዋናው ምክንያቴ እርሳቸው በፈቃዳቸው በኢትዮጵያ የምርጫ ፖለቲካ ውስጥ በተለይ “የማውቃው ነገሮች አሉ” በማለት እመር ብለው ዘለው ገብተውበታል፡፡ እንደዚህ ልዩ በሆነው መግለጫቸው ስለዚያ ምርጫ ጉዳይ የማውቃቸው ጥቂት ነገሮች አሉ በማለት በይፋ በማወጃቸው ስለዚያ ምርጫ ጉዳይ የሚያውቋቸው “ጥቂት ነገሮች” ምን እንደሆኑ በይፋ ለህዝብ ግልጽ ማድረግ እንዳለባቸው ለመጠየቅ እፈልጋለሁ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዚያች አገር በየጊዜው ምርጫ እየተባለ የህዝብ እና የመንግስት ሀብት ያለአግባብ እየባከነ ለይስሙላ የሚካሄደውን ምርጫ በማስመልከት እኔም የማውቃቸውን “ጥቂት ነገሮች” ለእርሳቸው ግንንዛቤ እንዲረዳቸው ላካፍላቸው እፈልጋለሁ፡፡ በፕሬዚዳንቱ ያልተጠበቀ የቃላት አመራረጥ እና አጠቃቀም ግራ ተጋብቻለሁ፣ በትክክል ምን ለማለት እንደፈለጉም ለማወቅ ጉጉት ያደረብኝ ሲሆን ይህ ፈሩን የለቀቀ የሸፍጥ አነጋገር ግን ሳልተች አንደአላልፍ ተገድጃለሁ፡፡ ፕሬዚዳንቱ ስለቀጣዩ የኢትዮጵያ ምርጫ “ጥቂት ነገሮችን” አውቃለሁ ሲሉ እንደ ስለላ ተቋም በሚስጥር የማውቀው ነገር አለ ማለታቸው ነውን? ፕሬዚዳንቱ ስለምርጫው ጥቂት የማውቃቸው ነገሮች አሉ ሲሉ ከዚህ ቀደም የተደረጉ የተጭበረበሩ እና በቀን ብርሀን የምርጫ ኮሮጆዎች እየተገለበጡ በሸፍጥ የተካሄዱ የይስሙላ ምርጫዎች ነበሩ ለማለት ፈልገው ነውን? እ.ኤ.አ በ2015 ስለሚካሄደው የኢትዮጵያ ምርጫ ፕሬዚዳንት ኦባማ የሚያውቋቸውን ጥቂት ነገሮች ግልጽ እንዲያደርጉልኝ በእርግጠኝነት ለማወቅ እፈልጋለሁ፣ ምክንያቱም የንግግራቸው ዳህራ አቀራረብ ጆርጅ ኦርዌል እንዳሉት “በቅጥፈት የታጀበን አንደበት እውነት ማስመሰል“ ከሚለው ጋር መሳ ለመሳ አስመስሎታል፡፡ ፕሬዚዳንቱ የሚያውቋቸውን ጥቂት ነገሮች ለማወቅ በዛር እንደተለከፈ ሰው መንቀጥቀጥ አለብን እንዴ? እ.ኤ.አ በ2010 በኢትዮጵያ በተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ በህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ሕወሀት) የበላይነት የሚመራው ገዥው ፓርቲ በጠራራ ጸሐይ የድምጽ ኮሮጆ እየገለበጠ በመዝረፍ እና ምርጫ በማጭበርበር 99.6 በመቶ የመራጮችን ድምጽ በማግኘት ጠቅላላ የፓርላማውን መቀመጫ እንደተቆጣጠረ ያውቁ ነበርን? ይህ የምርጫ ውጤት መቶ በመቶ (100%) ለመሆን የቀረችው የአንድ ፐርሰንት አራት አስረኛ ብቻ ነበረች፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 የፕሬዚዳንት ኦባማ ብሄራዊ የደህንነት ምክር ቤት እንዲህ የሚል መግለጫ አወጣ፣ “የኢትዮጵያ ምርጫ ዓለም አቀፍ የምርጫ መስፈርትን የማያሟላ መሆኑን ዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች ያረጋገጡት ስለሆነ ይኸ ጉዳይ አሳስቦናል…ከምርጫው ዕለት በፊትም እንኳ ለነጻ እና ፍትሀዊ ምርጫ የሚሆን የተስተካከለ የምርጫ ሜዳ በስራ ላይ አልዋለም ነበር፡፡ ከቅርብ ዓመታት ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ መንግስት የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በማስፈራራት እና በማሸማቀቅ የፖለቲካ ምህዳሩን በማጥበብ የሲቪል ማህበረሰቡን እና የነጻውን ፕሬስ እንቅስቃሴ ገድቧል…“ ብለው ነበር፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ ይህንን ሲሉ በአሁኑ ጊዜ የተቃዋሚ ፓርቲዎች እና አመራሮች በገዥው ፓርቲ አምባገነናዊ ማንአለብኝነት ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው፣ እየተሸማቀቁ፣ እየታሰሩ፣ እየተሰቃዩ እና በሸፍጥ የፍርድ ቤት ክስ እየተጉላሉ መሆናቸውን ያውቃሉ? ፕሬዚዳንት ኦባማ ለመሆኑ እ.ኤ.አ በ2010 በተካሄደው የመጨረሻ አገር አቀፍ ምርጫ የምርጫ ዘገባ በማቅረባቸው ምክንያት ምርጥ እና የብሩህ አዕምሮ ባለቤት የሆኑት የኢትዮጵያ ጀግኖች ጋዜጠኞች ከሰብአዊነት በወረደ መልኩ በየእስር ቤቶች እየታጎሩ በመማቀቅ ላይ እንደሚገኙ ያውቃሉ? ክቡር ፕሬዚዳንቱ እ.ኤ.አ በ2010 የዓለም የፕሬስ ቀንን ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ተጣብቆ የሚገኘውን ገዥ አካል በስም እየጠሩ በተለይም በነጻ ፕሬሱ ላይ እያካሄደ ያውን ጭቆና በማውገዝ እንዲህ የሚል ንግግር አሰምተው አልነበረምን?፣ “በአሁኑ ጊዜ ህዝቦች ከምንጊዜውም በላይ በኢንተርኔት አገልግሎት፣ በተንቀሳቃሽ ስልክ እና በሌሎች ተገጣጣሚ የቴክኖሎጂ ውጤቶች አማካይነት አስፈላጊውን መረጃ እያገኙ ባለበት ሁኔታ እንደ ቻይና፣ ኢትዮጵያ፣ ኢራን እና ቬንዙዌላ የመሳሰሉ አገሮች የህዝቦቻቸውን ሀሳብን በነጻ የመግለጽ ነጻነትን በመገደብ እና እነዚህን ዘመኑ ያፈራቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች እንዳይጠቀሙ በማድረግ ላይ ናቸው“ አላሉም ነበር እንዴ? በኢትዮጵያ ባለው ገዥ አካል ቀያጅ የሆነው የበጎ አድራጎት እና ማህበራት አዋጅ መውጣት ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት ቁጥር እ.ኤ.አ በ2010 የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ብቻ ከነበረበት 4,600 ወደ 1,400 አሽቆልቁሎ መውረዱን ሊያስታውሱ ይችላሉን? እነዚህ የተረፉት ጥቂት ድርጅቶች ህልውናቸውን ለማቆየት ሲሉ የሰራተኞቻቸውን ቁጥር ከ90 በመቶ ወይም ከዚያ በላይ በሆነ መጠን የቀነሱ መሆናቸውን አያውቁምን? እ.ኤ.አ በ2009 “ስህተት እንዳትሰሩ፣ የሲቪል ማህበረሰቡ–የሲቪል ቡድኖች መንግስቶቻቸው በተሻለ የማስተዳደር ብቃት እና መስፈርት ላይ እንዲሆኑ ያግዛሉ“ በማለት የሲቪል ማህበረሰቡን ሁኔታ በማስመልከት ያደረጉትን ንግግር ሊያስታውሱ ይችላሉን? በኢትዮጵያ ውስጥ እ.ኤ.አ በ2009 ወይም በ2010 ከነበረው ቁጥራቸው እጅግ በጣም ባነሰ ሁኔታ ጥቂት ብቻ የሆኑ ድርጅቶች በ2014 በሀገሪቱ ውስጥ ሁሉም በሚባል መልኩ የገዥው አካል ደጋፊ እና ታዛዥ በሆኑ ጥቃቅን የጎጆ ኢንዱስትሪ መሰል ድርጅቶች ባለቤትነት፣ ተግባሪነት እና አመራር ሰጭነት የሚንቀሳቀሱ ብቻ ናቸው ያሉት ብለው የተናገሩትን ሊያስታውሱ ይችላሉን? ፕሬዚዳንት ኦባማ ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ እድሚያቸው በ20ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ የሆኑ ወጣት ወንዶች እና ሴቶች በፌስ ቡክ እና በሌሎች የማህበራዊ ድረ ገጾች አማካይነት ሀሳባቸውን በመግለጻቸው ብቻ አሸባሪ የሚል ታፔላ ተለጥፎባቸው በቀጥጥር ስር ውለው ወደ ዘብጥያ ተወርውረው በእስር ቤት በመማቀቅ ላይ እንደሚገኙ ያውቃሉን? በኢትዮጵያ ያለው የነጻው ፕሬስ በጭቆና ውስጥ ያለ መሆኑን፣ መታፈኑን እና እየተዘጋ መሆኑን አያውቁምን? ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ ስድስት ታዋቂ ነጻ ህትመቶች ማለትም አፍሮ ታይምስ፣ አዲስ ጉዳይ፣ እንቁ፣ ፋክት፣ ጃኖ እና ሎሚ የተባሉ መጽሔቶች እንዲዘጉ ተደርገዋል፣ በደርዘን የሚቆጠሩ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞችም ወደ እስር ቤት እንዲወረወሩ እና ከሀገር እንዲሰደዱ ተደርገዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2012 የዓለም የፕሬስ ቀንን በማስመልከት “የጋዜጠኞችን፣ የጦማሪያንን እና የሰላማዊ አመጸኞችን በነጻ የመጻፍ እና የመናገር አቅም እንዳይገደብ ለመጠበቅ እና ምንም ዓይነት የበቀል እርምጃ እንዳይወሰድ እንዲሁም የጉዞ እቀባን ለማስቆም እና ሌሎች ቀጥተኛ ያልሆኑ የሳንሱር ስራዎችን አለማድረግ እና ዜጎች ዓለም አቀፋዊ የሆኑ መብቶቻቸውን ያለምንም ገደብ መጠቀም እንዲችሉ ማድረግ“ ብለው የተናገሩትን ሊያስታውሱት አይችሉምን? የተከበሩ ፕሬዚዳንት ኦባማ በኢትዮጵያ ከዜጎች ፈቃድ እና ፍላጎት ውጭ በኃይል ተፈናጥጦ በማተራመስ ላይ ላለው ገዥ አካል መሪዎች “ወጣት የኢትዮጵያ ጦማሪያንን እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆኑትን ጋዜጠኞች በስም እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ እና ውብሸት ታዬ ከእስር ይፈቱ“ በማለት እስከ አሁን ድረስ ያቀረቡት ጥሪ የሌለ መሆኑን ያውቃሉን? ፕሬዚዳንት ኦባማ ለመሆኑ የፕሬስ ነጻነት፣ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በከፍተኛ ጭቆና ውስጥ እየተሰቃዩ ባሉበት እና የፖለቲካ ምህዳሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ እየጠበበ በመጣበት ሁኔታ የሚደረግ የይስሙላ እና የሸፍጥ ምርጫ ከስም የዘለለ ፋይዳ ሊኖረው እንደማይችል ሊገነዘቡት ይችሉ ይሆን? እ.ኤ.አ በ2009 በጋና አክራ ላይ ለአፍሪካ ህዝቦች ያደረጉትን እንዲህ የሚለውን ንግግራቸውን “…ይህ ምርጫ ከማካሄድ በላይ ነው፣ እንደዚሁም ደግሞ በምርጫዎች መካከል ምን እንደሚደረግ የማወቅም ጉዳይ ነው፡፡ የጭቆና መገለጫዎች ብዙ ናቸው፣ በዚህም መሰረት ብዙ መንግስታት ምርጫ በማካሄድ ላይ ያሉትም እንኳ ህዝቦቻቸው በረሀብ አደጋ ችግር እየተሰቃዩ በህዝቦቻቸው ይወገዛሉ፡፡ የሀገር መሪዎች የሀገሮችን ሀብት ለግል ጥቅማቸው እያዋሉ እና ኢኮኖሚውን እየመዘበሩ ባሉበት ሁኔታ አንድ ሀገር ሀብት ማፍራት አትችልም…የትርፉን 20 በመቶ እና ከዚያ በላይ የሚሆነውን የአገር ሀብት የሚመዘብር መንግስት ባለበት ሀገር ማንም ቢሆን ከውጭ ሀገር ሄዶ መዋዕለ ንዋዩን ሊያፈስ አይችልም፣ የህግ የበላይነት ቀርቶ ጭካኔ እና የባርነት አገዛዝ በተንሰራፋበት ማህበረሰብ ውስጥ ለመኖር የሚፈልግ ማንም ሰው የለም፡፡ ያ ዴሞክራሲ አይደለም፣ ይልቁንም አንዳንድ ጊዜ ለይስሙላ ምርጫ እየተዘጋጀ ቢቀርብም ያ የለየለት አምባገነናዊነት ነው፡፡ እናም እንደዚያ ዓይነቱን የግፍ አገዛዝ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ለማስወገድ ጊዜው አሁን ነው፡፡“ በማለት የተናገሩትን አስመሳይ ንግግር ፕሬዚዳንት ኦባማ ሊያስታውሱት ይችሉ ይሆን? በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ እስከ አንገታቸው ድረስ በሙስና በተዘፈቁ አስመሳይ አምባገነን መሪዎች እና የእነርሱ ጋሻጃግሬዎች ኢኮኖሚውን በብቸኝነት አንቀው ይዘው እየመዘበሩ እራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን በማበልጸግ ላይ እንዳለሉ እንዲሁም አልፎ አልፎ የይስሙላ ምርጫ እያሉ በአገሪቱ ውስጥ ዴሞክራሲ እንዳለ በማስመሰል በዓለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚሰጠውን እርዳታ እና ብድር በማጋበስ ለግል ጥቅማቸው በውጭ አገር በሚገኙ ባንኮች የሂሳብ አካውንት እየከፈቱ በማጨቅ ያሉ ዘራፊዎች እና ማፊያ ጭልፊቶቸ መሆናቸውን ፕሬዚዳንት ኦባማ ሊያውቁ ይችላሉን? እ.ኤ.አ በ2008 እጩ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ታውቃላችሁ፣ ለማቆንጀት ሲባል የዓሳማን ከንፈር ቀለም መቀባት ትችላላችሁ፣ ሆኖም ግን ዓሳማው አሁንም ቢሆን ያው ዓሳማ ነው፣ ዓሳማነቱን አይቀይርም፡፡ አንድን የጠነባ ዓሳ በወረቀት ጠቅልሎ ለውጥ ማለት ይቻላል፡፡ ከስምንት ዓመት በኋላም ቢሆን ያው መጠንባቱን አይተውም፡፡“ እንደዚሁም ሁሉ ቆንጆ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማስመሰል ምርጫ የሚባል የጠነባን ቀለም በምርጫ ካርድ በመጠቅለል የዘራፊዎችን ከንፈር መቀባት ይቻላል፣ ሆኖም ግን የሚደረገው የይስሙላ ሽርጉድ ምርጫ ውጤት ከ23 ዓመታት የሸፍጥ ምርጫም በኋላ ያው በዘራፊዎች ከንፈር ላይ ሆኖ መጠንባቱን የማይለቅ መሆኑን ፕሬዚዳንት ኦባማ በውል ተገንዝበውት ይሆን? ወሮበላነትን ምርጫ በሚባል የጠነባ ነገር በምርጫ ካርድ ወረቀት መጠቅለል ይቻላል፣ ሆኖም ግን ከ23 ዓመታት በኋላም ቢሆን ያው መጠንባቱን እንደማይተው ፕሬዚዳንት ኦባማ አልተረዱም ይሆን? ስለምንናገረው ነገር ማወቅ፡ እ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ምርጫ ሊኖር ይችላልን? “ፖለቲካ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ“ በሚል ርዕስ ባዘጋጁት በባለ 1946 ገጽ ድርሰታቸው ጆርጅ ኦርዌል እንዲህ በማለት ጽፈው ነበር፣ “ሀሳብ ቋንቋን የሚያሻግት ከሆነ ቋንቋ እራሱም ሀሳብን ያሻግታል፡፡“ መጥፎ አጠቃቃም በህዝቦች መካከል በዘልማድ ይተላለፋል፣ የተሻለ እውቀት ባላቸው ሰዎችም ቢሆን እንኳ፡፡ ኦርዌል እንዲህ የሚል የመከራከሪያ ጭብጥ አቅርበው ነበር፣ “የፖለቲካ የቃላት አጠቃቀም ውሸትን እውነት ለማስመሰል ተብሎ የሚዘጋጅ ነው፣ እናም የተከበረን ነገር እውነት በማስመሰል ይገድላል፣ ባዶ ነፋስን ጠንካራ እና ጠጣር በማስመሰል፡፡“ እ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ፕሬዚዳንት ኦባማ የሚያወሩት ሁሉም ነገር ባዶ ነፋስ/ውሸት ነው፣ ሸፍጥ የተሞላበት ምርጫ ለማካሄድ የሚነገር ቋንቋ እውነት ሊመስል ይችላል እናም ወሮበላነት የተከበረ ዴሞክራሲ ይሆናል፡፡ በአሁኑ የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ “ምርጫ” የሚለው ቃል መሰረተቢስ እና እርባናቢስ ነው፡፡ “እ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ምርጫ ይካሄዳል” ማለት ወይም ደግሞ “እ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው ምርጫ ጥቂት የማውቀው ነገር አለ” የሚለው አባባል የፕሮፌሰር ኖአም ቾምስኪን አባባል እንዳለ የሚደግም እና ትርጉመቢስ እና እርባናየለሽ የሆነ ሆኖም ግን በሰዋስዋዊ አግባቡ ትክክል የሆነ ዓረፍተ ነገር ማለት ሲሆን “ቀለም የሌላቸው አረንጓዴ ሀሳቦች በብስጭት ይተኛሉ” እንደማለት ነው፡፡ በኢትዮጵያ “ምርጫ” ማለት በሶስት ቀለበት የሰርከስ ላይ ተውኔት የሚተወን ምርጫ የሚባል የህዝቡን ድምጽ በተቀነባበረ ሌብነት እና ዝርፊያ የሚነጠቅበት ከመሆን የዘለለ ፋይዳ የለውም፡፡ እንደዚህ ዓይነቱነን የተጭበረበረ የዘረፋ እና የውንብድና ሂደት ምርጫ ነው ማለት ውሸት ማለት እውነት ነው እንደማለት ነው፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ እ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው ምርጫ ጥቂት የማውቀው ነገር አለ ብለው ከማወጃቸው በፊት ጥቂት ኢትዮጵያወያን/ት እና የተወሰኑ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሀን ስለዚሁ ጉዳይ ሲነጋገሩበት ነበር፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩ እ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ የሚካሄደው ምርጫ የምርጫ ዘዋሪ ቀበኛው ልዩው መሀንዲስ ያለፈው መለስ ዜናዊ በሌለበት በዚህ ወቅት እውነት ነጻ እና ፍትሀዊ ምርጫ የሚካሄድ ስለመሆኑ ወይም አለመሆኑን አስመልከቶ ትንሽም ቢሆን ተስፋ ስለመኖሩ እና አለመኖሩ ሙያዊ ትንታኔ እንድሰጥ ጥያቄ ቀርቦልኝ ነበር፡፡ ተስፋ በቆረጠ መልኩ “የምን ምርጫ?” ነበር ያልኩት፡፡ ወያኔ ምርጫውን አሁንም በድጋሜ ይሰርቃል፡፡ ጥቂቶቹ የዘረፋውን እርግጠኛ እውነትነት ባረጋገጠ መልኩ የምጸት ሳቅ ነበር የሳቁት፡፡ ጥቂቶቹ ደግሞ የምርጫ ቅስቀሳ ተብየው በዘራፊው የገዥ አካል በይፋ ሲጀመር የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት በተቀናጀ እና በተደራጀ መልኩ ዘርፈ ብዙ የሆነ የሰላማዊ አመጽ እና እንቢተኝነት ዘመቻ ሊያካሂዱ እና የምርጫውን እርባናየለሽነት ለአገር ውስጥ እና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሊያጋልጡ ይችላሉ በማለት ነግረውኛል፡፡ እንዲህ የሚል ጥያቄ ተጠየቅሁ፣ “የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች እራሳቸውን ከምርጫው ሊያገልሉ ይችላሉን?“ በሚሊዮን ዶላሮች የሚያወጣ በአንድ ወይም በሌላ መልኩ የተጠየቅሁት ጥያቄ ደግሞ “የወያኔው የፖሊት ቢሮ አባላት ኃይለማርያም ደሳለኝን (የይስሙላ ጠቅላይ ሚኒስትር) አሽቀንጥሮ በመጣል በሌላ አሮጌ እና ነባር በሆነ የጫካ ዘብ ይተኩ ይሆን“ የሚል ነበር፡፡ (የወያኔ አለቆች በ2015 በሚደረገው አገር አቀፍ ምርጫ ኃይለማርያም ዳሳለኝን በማስወገድ በቀጥታ ወደ ቅርጫት ይጥሉታል የሚል ግምት አለኝ!) እ.ኤ.አ በ2015 ስለሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ኃይለማርያም ደሳለኝ ምን ይህል ያውቃሉ? እ.ኤ.አ ጁን 11/2014 ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አፍሪካ ዘገባ/Africa Report ለተባለ የዜና ወኪል በሰጡት ቃለመጠይቅ ነጻ እና ፍትሀዊ ምርጫ ይካሄዳል የሚል የሀሰት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ለማንኛውም የሰጡት ቃለመጠይቅ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ እ.ኤ.አ በ2015 በሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተወካዮች ምክር ቤት ብዙ መቀመጫዎችን ያገኛሉ ብለው ያስባሉን? ምርጫዎች እስካሉ ድረስ ትኩረት ማድረግ የምንፈልገው በሂደቱ ላይ ነው፡፡ የምርጫ ሂደቱን በህዝቦቻችን ፊት ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻ፣ ፍትሀዊ እና ታማዕኒነት ያለው ማድረግ አለብን፡፡ ከዚያ በተረፈ ውጤቱ የህዝቡ ነው፡፡ እነዚህ ብዙ መቀመጫዎች ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ወይም ደግሞ ለኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህዴግ) ይሰጣሉ ብየ ለመገመት አልችልም፡፡ የምርጫ ሂደቱ ዴሞክራሲያዊ ይሆናል ብለው ያምናሉ? ተቋማዊ ሂደታችን፣ ህጎቻችን እና ደንቦቻችን ሙሉ በሙሉ እንከን የላቸውም፡፡ ህጉ በእራሱ አይደለም እንቅፋት የሚሆነው፣ ሆኖም ግን እነዚህን ህጎች ከመተግበሩ ላይ ነው፡፡ ስለሆነም ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚመሩበት የምርጫ መመሪያ ህገ ደንብ/Cod of Conduct አዘጋጅተን በስራ ላይ አውለናል፡፡ በማያወላውል መልኩ ለዚህ ህገደንብ ተገዥ መሆን ምርጫውን የበለጠ ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻ፣ ፍትሀዊ እና ለህዝብ ታዕማኒነት እንዲኖረው ያደርገዋል፡፡ ከ2010ሩ አገር አቀፍ ምርጫ ጋር ተመሳሳይ ውጤት የሚኖረው ከሆነ እና አንድ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ዕጩ ብቻ አሸንፎ ወደ ፓርላማ የሚገባ ከሆነ ይኸ ሁኔታ በመንግስት ላይ የሚኖረውን ታዕማኒነት ከጥርጣሬ ላይ ሊጥለው ይችላል ብለው ያስባሉን? ይህንን አላስብም ምክንያቱም ውሳኔው በህዝቡ የሚወሰድ ከሆነ ሁላችንም በዚያ ውሳኔ ላይ መስማማት አለብን፡፡ የምርጫው ውጤት አንዳንድ ጊዜ ለአንዳንዶቻችን ቢመቸንም ባይመቸንም ምንም ይሁን ምን ውጤቱን መቀበል አለብን፡፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ኃይለማርያም ደሳለኝ የእርሳቸውን (ይቅርታ የህወሀትን ማለቴ ነው) የ2015ን ምርጫ እና እንዴት አድርገው የ2010ን የምርጫ ውጤት እንዳለ በመድገም በዝረራ በማሸነፍ ድልን ሊቀዳጁ እንደሚችሉ እና በእንዴት ዓይነት ማጭበርበር ዝርፊያውን ለማስኬድ እንዳቀዱ ባለሶስት ምላስ አጠቃላይ የምርጫ ስትራቴጂ ነድፈዋል፡፡ ይኸውም፣ 1ኛ) እ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ የሚካሄደው አገር አቀፍ የምርጫ ሂደት ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻ፣ ፍትሀዊ እና በህዝብ ዘንድ ታዕማኒነት ያለው እንዲመስል የመንግስት የመገናኛ ብዙሀንን እና ሀብትን በመጠቀም የኢትዮጵያን ህዝብ ማታለል፤ 2) ፍጹም እና እከንየለሽ የሆኑ ተቋማዊ ሂደቶቻችንን፣ ህጎቻችንን እና ደንቦቻችንን ወደ ተግባር በማሸጋገር፤ 3ኛ) ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የፈረሙትን እና የተቀበሉትን የምርጫ ህገ ደንብ እንዲቀበሉት እና እንዲተገብሩት ማስገደድ የሚሉት ናቸው፡፡ የወያኔ ባለሶስት ጣት የምርጫ ስትራቴጂ በእርግጠኝነት እንከን ለሌለው የተጭበረበረ ምርጫ እንከንየለሽ የምርጫ ጨዋታ ዕቅድ ነው፡፡ አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ እንከንየለሽ የሸፍጥ የምርጫ ጨዋታ ህግ መጽሐፍ እ.ኤ.አ በ2010 ጽፎ ተግባራዊ አድርጓል፡፡ በዚህም መሰረት የእርሱ ፓርቲ እንከንየለሹን ምርጫ 99.6 በመቶ የፓርላማ መቀመጫዎችን በማግኘት አሸናፊነቱን አረጋግጧል፡፡ ከዚህ የበለጠ እንከንየለሽ የምርጫ ውጤት ማግኘት ሰብአዊነት ነውን? (አሁን በህይወት የሌለው ሳዳም ሁሴን ብቻ ነው እ.ኤ.አ በ2002 በተካሄደው አገር አቀፍ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከ11,445,638 ድምጽ ሰጭዎች መቶ በመቶ ድምጽ በማግኘት እከንየለሽ የድምጽ ውጤት በማግኘት በመፎከር ላይ የነበረው፡፡) የሸክስፒርን አባባል በመዋስ፣ የመለስ ሙት መንፈስ እ.ኤ.አ በ2015 በሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ላይ ለማጥላት “በጨላማው የሲኦል ቦታ ላይ እንደ እሬሳ ሳጥን“ ትንጠለጠላለች፡፡ “ስለህዝቦች አገዛዝ/አስተዳደር ሳይሆን ህዝቦችን ለመግዛት ያፈጠጠ” “ምርጫ”፣ የበከተ አስተሳሰብን በመያዝ እና እና የሞራል ስብዕና በሌላው መልኩ እ.ኤ.አ በ2014 የኃይለማርያም አለቆች ከእርሳቸው በስተጀርባ ሆነው እንከንየለሽ ተቋማዊ ሂደት፣ ህጎችን እና ደንቦችን በመጠቀም ተግባራዊ አድርገው ምርጫ ማሸነፍ እንዳለባቸው ብቻ አይደለም እምነታቸው ሆኖም ግን ኢትዮጵያን ለዘላለም ለመግዛት ባላቸው መብት የኢትዮጵያ ህዝቦች እንከንየለሽ ገዥዎች መሆናቸውን ለማረጋገጥ ጭምር እንጅ፡፡ በእነርሱ እና በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አስተሳሰብ በቀጣይ ኢትዮጵያን የሚገዛት ማን ነው የሚለው ከጥያቄ ውሰጥ የሚገባ ጉዳይ አይደለም፡፡ ይኸ ጉዳይ ለውይይት የሚቀርብ አይደለም፣ የሚያከራክርም አይደለም፣ እናም ለድርድር የሚቀርብ አይደለም፡፡ በእርግጥ መለስ እ.ኤ.አ በ2010 በተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ የተጎናጸፈውን የምርጫ ድል አስመልክቶ ባደረገው ንግግር እንዲህ የሚል ግለጽ መልዕክት አስተላለፎ ነበር፣ “…በዚህ ምርጫ የህዝቡን የምርጫ ድምጽ ድጋፍ ላላገኛችሁት እና ስኬታማ ላልሆናችሁት ፓርቲዎች በዚህ ፓርላማ ወንበር ይኑራችሁም አይኑራችሁም የህዝቡን ፍላጎት፣ የአገሪቱን ህገመንግስት እና ሌሎችን የአገሪቱን ህጎች እስካከበራችሁ ድረስ ከእናንተ ጋር በመቀራረብ እናንተን በታላላቅ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በማሳተፍ እየተመካከርን አብረን እንሰራለን” ነበር ያለው፡፡ የውሸት እና የሸፍጥ ፈጣጣ ንግግር! በቀላል አነጋገር ማንም ቢሆን እ.ኤ.አ በ2015 የሚካሄደውን እንከንየለሽ የምርጫ ውጤት አልቀበልም የሚል ልቡ ያበጠበት ወጠጤ ካለ በኃይለኛው ጡንቻ የመደምሰስ አደጋ ይገጥመዋል፡፡ አራት ነጥብ! ሆኖም ግን ምንም የማይሉ ሆኖም ግን የተባሉትን ብቻ የሚቀበሉ ዓላማቢስ እና ስሜት አልባ በመሆን አንገታቸውን ደፍተው ጫማ የሚልሱ ወንዶች እና ሴቶች ከሆኑ ያለምንም ችግር የመሸለም ዕድልን እየተጎናጸፉ በታላላቅ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በማማከር እና እንዲያውም በማሳተፍ ይህችን በእድገት ጎዳና ላይ እንደ እሮኬት ጥይት በመምዘግዘግ ላይ ያለች ሀገር የበለጠ እንድትተኮስ ያደርጓታል፡፡ እንዲያውም ባለሁለት አሀዙ የኢኮኖሚ ዕድገት እጅግ በጣም ከመጦዙ የተነሳ ወደ ባለሶስት አሀዝ ሳይገባ ይቀራል ጎበዝ! ከዚህ በላይ በአገር እና በህዝብ ላይ ከመቀለድ የከፋ እና የከረፋ ከቶውኑ ምን ነገር ሊኖር ይችላል! እ.ኤ.አ በ2015 የሚካሄደውን እንከንየለሽ አገር አቀፍ ምርጫ ውጤት አልቀበልም የምትሉ ዕደለቢሶቹ ሁሉም የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች (ውይ! ለምስክርነት ካላችሁ ማለቴ ነው)፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አመራሮች ካላችሁ በምርጫው ወቅት አንድም እንደ አህያ ዱላውን ተቀበሉ አለያም ደግሞ በእስር ቤት ውሰጥ በመግባት እየማቀቃችሁ የአህያውን ኑሮ መኖር ነው የሚጠብቃችለሁ፡፡ ሌሎቹስ ስለኢትዮጵያመ ምርጫ ምን ያህል ያውቃሉ? እ.ኤ.አ ኦክቶበር 2009 “የ2010 የኢትዮጵያ ምርጫ እብድነት” በሚል ርዕስ የሚከተለውን ጥያቄ በማንሳት ትችት ጽፌ ነበር፣ “የፖሊስ መንግስት በተንሰራፋበት ሀገር ፍትሀዊ እና ነጻ ምርጫን ማካሄድ ይቻላልን?“ (ይህ ጥያቄ የፕሬዚዳንት ኦባማን የከንፈር ቀለሙን እና የዓሳማውን ጉድኝት የሚያመሳስል ቀላል የተመሳስሎ አቀራረብ ነው፡፡) ያ ትችት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እ.ኤ.አ በ2001 ከኢትዮጵያ ከስልጣናቸው መንበራቸው እስከለለቀቁበት ድረስ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት የነበሩት ባቀረቡት የምርጫ ዘመቻ ዘገባ ላይ መሰረት ያደረገ ነበር፡፡ ዶ/ር ነጋሶ በምዕራብ ኢትዮጵያ የምትገኘውን ደምቢዶሎን ወክለው ለተወካዮች ምክር ቤት ለመወዳደር ለምርጫ ቅስቀሳ በተንቀሳቀሱበት ወቅት በገዥው ፓርቲ የበታች አካላት ልክ የድሮዎቹ የኮሙኒስት ፍልስፍናን ሲያራምዱ የነበሩ አገሮች ሲያደርጉት እደነበረው ሁሉ ህዝቡን አስጨንቀው በመያዝ የአዛዥ እና የቁጥጥር ስርዓት/Command and Control በመዘርጋት ሲያደርጉት የነበረውን የአፈና አሰራር ነው፡፡ እርሳቸውም ተዘዋውረው በተመለከቱት መሰረት በደምቢዶሎ የገዥው ፓርቲ የታችኛው እርከን ድርጅቶች የደህንነት፣ የፖሊስ እና ሌሎች በታችኛው የስልጣን መዋቅር ላይ ያሉት የሲቪል ማህበረሰብ መሰል ድርጅቶችን ሁሉ ሳይቀር በቁጥጥር ስር በማዋል አንድ ወጥ የሆነ የቁጥጥር መዋቀር በዞኖች፣ በከተሞች፣ በወረዳዎች፣ በመንደሮች፣ በጎጦች እና በቤቶች ሳይቀር ተጠርንፈው የተያዙ መሆናቸውን ግልጽ አድርገው ነበር፡፡ ዶ/ር ነጋሶ የመረጃ ሰጭዎች፣ የወኪሎች እና የሚስጥር ፖሊስ መሰል አደረጃጀቶች ሆነው እነዚህም የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን ለማሸማቀቅ፣ ለማስፈራራት፣ የስለላ መረጃ ለመሰብሰብ እና ተቃዋሚዎችን በማዳካም ሰርስሮ ለመግባት የተዋቀሩ አደረጃጀቶች እንደነበሩ እጀ እረጅም በመሆን ህሉን አድራጊ ፈጣሪ እንደነበሩ ግልጽ አድርገው ነበር፡፡ በደምቢዶሎ በፖለቲካ ፓርቲው እና በህዝብ ደህንነቶች መካከል ምንም ዓይነት የስራ ክፍፍል ልዩነት የለም በማለት ሲሞግቱ ነበር፡፡ ሁለቱም በአንድ የፖለቲካ ጥላ ስር የተዋቀሩ እና የአካባበኒውን የፖለቲካ እና የማህበራዊ ሁነት በጅምላ የተቆጣጠሩ እና የበላይነትን የያዙ ነበሩ ብለዋል፡፡ የመንግስት ሰራተኞች፣ አርሶ አደሮች፣ የአካባቢው ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የአነስተኛ ብድር እና ቁጠባ ድርጅቶች እና ሌሎችም በግዳጅ በሚስጥራዊው የፓርቲ መዋቅር ስር እንዲሆኑ ይገደዳሉ፡፡ የቁጥጥር ስርዓቱ መጥበቅ ሁሉን ነገር የሚያሽመደምድ ነበር በማለት ዶ/ር ነጋሶ እንዲህ በማለት ጽፈው ነበር፣ “እያንዳንዱ ቤተሰብ በየዕለቱ ወደ ቤቱ የሚመጡትን እንግዶች እና ጎብኝዎች የመጡበትን ምክንያት፣ ምን ያህል ጊዜ እንደሚቆዩ፣ በቆይታቸው ጊዜ ምን እንደተናገሩ እና እዳደረጉ እንዲሁም በምን ስራ ላይ እንደቆዩ ዘገባ ማቅረብ ይጠበቅበታ”:: እንግዲህ ያ ነበር የመለስ የደህንነት ዋስትና በመሆን በ2010 እንከንየለሽ ምርጫ በማካሄድ 99.6 በመቶ ድምጽ በማግኘት የቅጥፈት የድል ከበሮ ሲደልቅ የነበረው፡፡ አሁን ከኃይለማርያም በስተጀርባ ያሉት ስምየሾች፣ አረመኔዎች እና ራዕይየለሾች በተመሳሳይ መልኩ እንደገና በ2015 ለሚደረገው ምርጫም ተመሳሳዩን የሸፍጥ ስራ ለመስራት እና ለማግኘት ደፋ ቀና ይላሉ፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 በተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ የምርጫ ውጤት ላይ ትችት በማቅረብ ፕሮፌሰር ቶቢያስ ሐግማን የተመለከቱትን እንደሚከተለው አስፍረዋል፡፡ “የኢትዮጵያ መንግስት እ.ኤ.አ በ2005 በተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ውርደትን ባከናነበ መልኩ ሽንፈትን ከተጎነጨ ወዲህ አ.ኤ.አ በ2010 በተደረገው አገር አቀፍ ምርጫ መንግስት የመጨረሻ የፖለቲካ ስተራቴጂ ነድፎ የገባበት ነው፡፡ ይህ የአካሄድ እስትራቴጂ ዱላ እና ካሮትን ሁለቱንም አካትቶ የያዘ ነበር፡፡ ዱላው የሚያካትተው ማስፈራራትን፣ ማሸማቀቅን እና የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን እና የእነርሱ ደጋፊ ይሆናሉ ብለው የሚያምኑባቸውን በቁጥጥር ስር እያዋሉ ወደ እስር ቤት መወረወወር ሲሆን ካሮቱ የሚያካትታቸው ደግሞ ገዥው ፓርቲ አዲስ የፓርቲ አባላትን በገፍ መመልመል እና አዲስ የትንታኔ ዘገባ እንደሚጠቁመው ጠንካራ የተቃዋሚ አባላት በሚገኙባቸው ወረዳዎች በቀጥታ ከፌዴራል ወደ ወረዳዎቹ ገንዘብ እንዲላክ በማድረግ በጣም ጠንካራ የሆኑትን በገንዘብ መደለል እና በገንዘብ የምርጫ ድምጽ በመግዛት ዓላማቸውን ማሳካት ነበር… በምርጫ 2010 የተገኘው 99.6 በመቶ የምርጫ ድምጽ ውጤት ሲታይ ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ ለህዝብ አስተዳደር ሳይሆን ህዝቡን ለመግዛት የሚያመላክት ጠንካራ ምልክት ነው… ከ20 ዓመታት በላይ በስልጣን ላይ ከቆየ በኋላ የኢትዮጵያ ህዝቦቸች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) በፖለቲካ ውክልናው እና በውሳኔ ሰጭነቱ ህጋዊነትን ያልተላበሰ አድራጊ ፈጣሪ ጠቅላይ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲ ማለት ምን ማለት እንደሆነም በእራሱ አረዳድ እና ዓላማ ጠቅልሎ የያዘ ህጋዊነትን ያልተላበሰ ድርጅት ነው፡፡” የፕሮፌሰር ሄግማን ምልከታዎች በተጨማሪም የወያኔ አመራሮች (እና የእነርሱ ጋሻ ጃግሬዎች) በእብሪተኝነት እና ሊለወጥ በማይችል ቀኖናዊ አመለካከት ወጥመድ ውስጥ የተያዙ በመሆናቸው ምክንያት እድሜልካቸውን ለመግዛት ሀሳብ አላቸው፡፡ ከዚህ አንጻር በኢትዮጵያ ምርጫ ማካሄድ ምንም ዓይነት እርባና የሌለው እና ከንቱ ነገር መሆኑን ፕሮፌሰሩ አጽንኦ በመስጠት አስቀምጠውታል፡፡ የምልከታቸውን ተጨባጭነት ይበልጥ ለማረጋገጥ እንዲህ ይላሉ፣ “ይህ ሁኔታ ኢህአዴግ እራሱን በሚያይበት መነጽር ላይ በግልጽ ሲንጸባረቅ ይታያል – በስም እራሱን አውራ ፓርቲ/Vanguard party እና የመንግስትነት ስልጣንን ጨብጨ የመምራት መብት የእኔ መብት ሆኖ ልማት ማለት ምን ማለት እደሆነ እና ዴሞክራሲ እንዴት መደራጀት እና መዋቀር እንዳለበት የምወስነው እኔ ነኝ፡፡ ስለሆነም ማንም ይሁን ማን ከኢህአዴግ አመለካከት ውጭ የሆነ ሁሉ ጸረ ልማት ወይም ደግሞ ጸረ ሰላም ነው፣ እናም ማንም ማን ይሁን የእርሱን ፖሊሲ የሚቃወም ሁሉ ጸረ መንግስት ነው“ በማለት የድርጅቱን (የጠቅላዩን እና ዘላለማዊ ገዥውን) ከንቱነት በማያሻማ መልኩ አስቀምጠውታል፡፡ እ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ምን ያህል አውቃለሁ? በ2015 በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ እኔ የማውቀው ይልቁንም የበለጠ የተወሳሰበ ነገር ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ በርካታ ጥያቄዎችን እጠይቃለሁ፣ እነዚህም ለእኔ የሚታወቁ ታዋቂዎች፣ ታዋቂ የማይታወቁዎች፣ እና የማይታወቁ የማይታዎቁዎች ናቸው፡፡ ይቅርታ አድርጉልኝ አንዳንድ ጊዜ እንቆቅልሽ ማውራት ይቀናቸው እንደነበሩት እንደ ቀድሞው የዩኤስ አሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ዶን ሩምፌልድ ዓይነት አቀራረብ ተከትየ ከሆነ፡፡ ዶን እንዲህ ብለው ነበር፣ “የምናውቃቸው የሚታወቁ ነገሮች አሉ፣ እንደዚሁም የምናውቃቸው የማይታወቁ ነገሮች አሉ፣ ይህም ማለት የማናውቃቸው ጥቂት ነገሮች አሉ፡፡ ሆኖም ግን የማናውቃቸው የማይታወቁ ነገሮች አሉ፣የማይታወቁ እና እኛም የማናውቃቸው፡፡“ ሙሉ በሙሉ ግልጽ ላድርገው፡፡ በእርግጠኝነት ጥቂት ነገር አውቃለሁ፡፡ የወያኔ ገዥ አካል እ.ኤ.አ በ2015 የሚካሄደውን አገር አቀፍ ምርጫ እንደ ቁማር ጨዋታ ሻጥር ይሰራበታል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ የምርጫው ዕለት የድምጽ ቆጠራ ገና ሳይጠናቀቅ እና የቆጠራ ጣቢያዎች ገና ሳይዘጉ የወያኔ ገዥ አካል በዝረራ አሸንፎ ድልን እንደተቀዳጀ በማስመሰል በህዝብ ግብር በሚተዳደረው መገናኛ ብዙሀን ማናፋቱን ይቀጥላል፡፡ ይኸ እንግዲህ ታዋቂው የማውቀው ነገር ነው፣ ምንም ዓይነት ሊያስረዳኝ የሚችል ሌላ ጭንቅላት አያስፈልገኝም፡፡ ሆኖም ግን የሚታወቁ የማላውቃቸው ነገሮች አሉ፡፡ ይህም ማለት እ.ኤ.አ በ2015 በሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ የወያኔ ገዥ አካል ቢያንስ በ99.6 በመቶ ያሸንፋል፣ ሆኖም ግን ይህ እንደ እስስት ተለዋወጭ የሆነው ገዥ አካል በ99.7፣ በ99.9፣ በ100 ወይም ደግሞ በ110 በመቶ ለማሸነፍ ዕቅድ ይዞ ይሆናል (ይህም እንግዲህ ከ2010 ጀምሮ የሞቱ ድምጽ ሰጭዎችን ቆጥረው ማለት ነው)፡፡ ሆኖም ግን በ2015 የሚደረገው ምርጫ የመራጮች ድምጽ ውጤት ከ99.6 በመቶ ያነሰ የድል ውጤት ተመዝግቦ ከሆነ መለስ ከመቃብር ውስጥ ሆኖ ለዚህ የሸፍጥ ምርጫ ስኬታማነት ተንቀሳቅሶ ሊሆን ስለሚችል የማይታወቅ የማላውቀው ነገር መሆኑ ነው፡፡ ለእኔ እ.ኤ.አ በ2010 በተደረገው አገር አቀፍ ምርጫ የወያኔ ገዥ አካል 99.6 በመቶ የመራጮች ድምጽ ውጤት አመጣሁ ብሎ የድል ከበሮ ሲደልቅ ፕሬዚዳንት ኦባማ በውስጠ ታዋቂነት ይህንን ተቀብለው ቡራኬ በመስጠት ማጽደቅ መቻላቸው የሚታወቀው የማውቀው ነገር ነው፡፡ ፕሬዚዳንቱ ለዚህ ጉዳይ ጆሮዳባ ልበስ፣ አላየሁም አልሰማሁም ነው ያሉት፡፡ (ሆኖም ግን እ.ኤ.አ በ2013 በዚምባብዌ በተደረገው አገር አቀፍ ምርጫ ሮበርት ሙጋቤ የፕሬዚዳንትነት ወንበሩን በ61 በመቶ ድምጽ በማግኘት አሸንፊያለሁ ብለው ድንፋታ ሲያሰሙ ፕሬዚዳንት ኦባማ ለወያኔው ገዥ አካል እንዳደረጉት ሁሉ በዝምታ አላለፉም፡፡) እንዲያውም እንደህ ነበር ያሉት፣ “ዚምባብዌያውያን/ት አዲስ ህገመንግስት አላቸው፡፡ ኢኮኖሚው በማገገም ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ወደፊት በእድገት የመገስገስ ዕድሉ ይኖራል፣ ሆኖም ግን ይህ ተፈጻሚነት ሊኖረው የሚችለው ነጻ፣ ፍትሀዊ እና ሰላማዊ ምርጫ ሲካሄድ ብቻ ሲሆን በዚህም መሰረት ዚምባብዌያውያን/ት የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውን እራሳቸው ምንም ዓይነት የማስፈራራት ፍርሀት እና የብቀላ እርምጃ ሳይወሰድባቸው ሲወስኑ ነው፡፡ 61 በመቶ የመራጮች ድምጽ በማግኘት አሸናፊ የሆነ ምርጫ ነጻ እና ፍትሀዊ አይደለም፣ ስለሆነ ህዝባዊ ውግዘት ሊደርስበት ይገባል“ ነበር ያሉት፡፡ ሆኖም ግን 99.6 በመቶ የመራጮችን ድምጽ በማግኘት አሸናፊ የሆነ ምርጫ እንደ ክቡር ፕሬዚዳንቱ መንታ ምላስ ሁኔታ ነጻ እና ፍትሀዊ ነው፣ እናም ታላቅ የሆነ የግል ሙገሳ ያስፈልገዋል! ፕሬዚዳንት ኦባማ እ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ስለምርጫው ጥቂት የማውቀው ነገር አለ ሲሉ የማይታወቀው እኔም የማላውቀው ነገር ማለት ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ምናልባት ፕሬዚዳንቱ የሚያውቁት ሆኖም ግን ማንም ኢትዮጵያዊ የማያውቀው ነገር ሊኖር ይችላል፡፡ እ.ኤ.አ በ2015 በኢትዮጵያ በሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ የተለያዩ የህወሀት ተስፈንጣሪ ቡድኖች የጠቅላይ ሚኒስትርነቱ ቦታ ለእኔ ይገባል፣ ለእኔ ይገባል በሚል የንግስና ጦርነት ለማካሄድ ዝግጅት ሊያደርጉ የሚችሉበት የማይታወቅ እኔም የማላውቀው ነገር ሊሆን ይችላል፡፡ ከኢኮኖሚያዊ ጥቅም አንጻር የተለያዩ የህወሀት ተስፈንጣሪ ቡድኖች አሮጌ ብር በማጣበቂያ ታሽጎ አንድ እንደሚሆነው ሁሉ እነርሱም ለጥቅም ሲሉ ብቻ አንድ ሊሁኑ የሚችሉበት የማይታወቅ እኔም የማላውቀው ነገር ሊኖር ይችላል፡፡ ሆኖም ግን የሚታወቅ እና እኔም የማውቀው ነገር አለ፣ ይኸውም የምርጫ ዘራፊዎች የሚከባበሩበት እና የማይከባበሩበት ያልተጻፈ ህግ አለ፣ እርሱም፣ “በምርጫ ወቅት አንድ ዘራፊ በሌላው ዘራፊ የምርጫ ጓደኛው ላይ ጦርነት አይከፍትም፣ ምክንያቱም በምርጫ ጦርነት የሚያሸንፉ የምርጫ ዘራፊዎች የሉምና፡፡“ ስለወያኔ ውስጣዊ ባህሪያት እና አሰራር በርካታ የማይታወቁ እና የማናውቃቸው ነገሮች አሉ፡፡ አጋጣሚ ሆኖ ስለወያኔ የማይታወቁ የማናውቃቸውን የሚያውቁ ንግግር አያደርጉም፣ እናም ንግግር የሚያደርጉት ስለወያኔ የማይታወቁትን የማናውቃቸውን አያውቁም፡፡ ኦ! በጣም አደናጋሪ ነገር ነው! የነጻ እና ፍትሀዊ ምርጫ ትክክለኛ ትርጉም እና ተሞክሮ፤ ምርጫዎች እና ምርጫዎች አሉ፡፡ በሸፍጥ የተሞሉ እና የተጭበረበሩ ምርጫዎች እራሳቸው ማለት ናቸው፡፡ አንድ ምርጫ ነጻ እና ፍትሀዊ ነው ወይም አይደለም “የተቋማዊ የአሰራር ሂደቱ፣ ህጎቻችን እና ደንቦቻችን እንከንየለሾች ናቸው“ ብሎ በመወሰን የማወጅ ያህል አይደለም፣ ችግሩ እንከንየለሽ የተቋማዊ የአሰራር ሂደት፣ ህጎች እና ደንቦች ያለመኖር አይደለም፣ ይልቁንም እነዚህ እንከንየለሽ ተቋማዊ የአሰራር ሂደቶች፣ ህጎች እና ደንቦች ተፈጻሚነት የማይኖራቸው እንከን በእንከን በተሞሉ ሰዎች ስር በመሆናቸው ብቻ ነው፡፡ ችግሩ ያለው እነዚህን እንከንየለሽ ህጎች በሚጽፉት ሰዎች እጅ እና በትክክል ቅን ልቦና ኖሯቸው ወደተግባር አምጥተው በቅንነት መተግበር በማይችሉ እንከን በእንከከኖች ነው፡፡ ከሁሉም በላይ እንከን በእንከን የተሞሉ ሰዎች እንዴት እንከንየለሽ የአሰራር ሂደቶችን፣ ህግችን እና ደንቦችን ያወጣሉ? እነርሱ እራሳቸውን እንከንየለሾች ነን ብለው የሚያምኑ በቀላሉ ነገሮችን የመረዳት ወይም ደግሞ የግንዛቤ ችግር ያለባቸው ናቸው፣ እናም ያ ዓይነት አመለካከት ያላቸው አጠቃላይ የጅምላ እንከን በእንከን ቁልሎች ናቸው፡፡ ከኃይለማርያም ደሳለኝ በስተጀርባ ያሉት ኃይሎች እንከን በእንከን የሆነችውን ኢትዮጵያ ለመግዛት ከላይ ተቀብተው የመጡ እና በክልል፣ በሙስና እና የጅምላ ሰብአዊ መብትን እየጣሱ በእነርሱ የእንከንየለሽ መስፈርት ለማድረስ እየዳከሩ ያሉ ለመሆናቸው በእርግጠኝነት እምነቱ አለኝ፡፡ በእርግጥ በኢትዮጵያ እንከንየለሽ ደንቦችን፣ ህጎችን እና ሂደቶችን በማውጣት ብቻ እንከንየለሽ ምርጫ ይካሄዳል ብሎ የሚጠብቅ ሰው የለም፡፡ ነጻ እና ፍትሀዊ ምርጫ ጥቂት እንከኖች ያሉበት፣ ቁስሎች እና ህጸጾች መኖራቸው ተፈጥሯቂ ነው፡፡ እንደዚህ ያሉት ምርጫዎች የመከሰታቸው ሁኔታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስምምነት የተደረሰባቸው መስፍርቶች እና መርሆዎች ያሉ ሲሆን መፍትሄዎችም ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች መክፈት እና ማስፋት፣ የተቃዋሚ አባላትን ማስፈራራት እና ማሸማቀቅ ማስወገድ፣ በሲቪል ማህበረሰቡ ላይ ያለውን የቁጥጥር ደረጃ ማላላት እና የነጻውን ፕሬስ መብት በማረጋገጥ ለዜጎች መረጃ እንዲሰጥ እና ዘገባ እንዲያቀርብ መፍቀድ ናቸው፡፡ ፍትሀዊ እና ነጻ ምርጫዎች ህዝቡ በዕለቱ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመሄድ የምርጫ ካርዱን ጥሎ በመምጣቱ ብቻ የሚከሰቱ አይደሉም፡፡ ይልቁንም ከምርጫው ዕለት በፊት የመከወኑ ነገሮች ናቸው፡፡ ፕሬዚዳንት አቦማ ጋና ላይ እንደተናገሩት፣ “ይህ በአጠቃላይ ምርጫ ከማካሄድ በላይ ነው፡፡ እንደዚሁም ደግሞ በምርጫዎች መካከል ምን ተከናወነ የሚለውም መታየት አለበት“ ነበር ያሉት፡፡ ከሁሉም በላይ በመጀመሪያ ነጻ እና ፍትሀዊ ምርጫ ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው የህግ የበላይነት ባለበት እና መሰረታዊ የሆኑ የሰብአዊ መብቶች በተከበሩበት ሁኔታ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህግመንግስት “የሀገሪቱ የህጎች ሁሉ የበላይ” ለድምጽ ሰጭዎች እና ለዕጩዎች (በአጠቃላይም ለዜጎች) ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብትን ያጎናጽፋል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ፖለቲካዊ የሆኑ መልዕክቶች እና መረጃዎችን ከምርጫው በፊት እና ከድህረ ምርጫ በኋላ ወደ ህዝብ ለማሰራጨት እና መረጃ ለመለዋወጥ የሚያስችለውን የፕሬስ ነጻነትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ በህገመንግስቱ የማይገዙት ለምንድን ነው? ህገመንግስቱ ለሁሉም ድምጽ ሰጭዎች፣ ፓርቲዎች እና እጩ ተወዳዳሪዎች፣ ነጻ፣ ከማንም ጋር ያልወገነ የምርጫ ሂደቱን የሚያስፈጽም የምርጫ ቦርድ እንዲኖር ዋስትና ይሰጣል፡፡ በዜጎች የፖለቲካ ፓርቲዎችን እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ለመመስረት በሚያደርጉት ጥረት የመደራጀት እና የመሰብሰብ መብት ላይ በዘፈቀደ የሚደረግ ጣልቃገብነት መኖር የለበትም፡፡ እንደዚሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰላማዊ ሰልፍ እና የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ለማድረግ ሲፈልጉ ያለምንም ችግር በነጻ መንቀሳቀስ እንዲችሉ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ዜጎች የፖለቲካ አመለካከታቸውን በነጻ የማራመድ እና ከማንኛውም ተጽእኖ ነጻ ሆነው መግለጽ እንዲችሉ መብታቸው ሊጠበቅ ይገባል፡፡ ዜጎች መረጃ የመፈለግ፣ የመቀበል እና የማካፈል መብታቸው ሊረጋገጥ ይገባል፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ የዘመቻ ቅስቀሳ ለማድረግ እና ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ከገዥው ፓርቲ ጋር ጭምር እኩል በሆነ መልኩ የመንቀሳቀስ መብታቸው ሊጠበቅ ይገባል፡፡ የፖለቲካ አመለከካከታቸውን ለማራመድ እና በህዝብ ዘንድ ለማስረጽ እንዲችሉ ማንኛውም እጩ ተመራጭ ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ለሚዲያ በተለይም ለብዙሀን መገናኛ እኩል እድል ሊያገኙ ይገባል፡፡ ከምርጫ እና ከፖለቲካ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ መልኩ የሚነሱ ውዝግቦችን በሰላማዊ መልኩ ለመዳኘት እንዲቻል ነጻ እና ከማንም ያልወገኑ ተቋማት ያስፈልጋሉ፡፡ የህገመንግስቱን ትዕዛዛት ለምን አይከተሉም? የተቃዋሚ ፓርቲ እጩዎች እና ፓርቲዎች ለህዝብ ቀርበው ሀሳቦቻቸውን እና ፕሮግራሞቻቸውን ሊያስረዱ የሚቸችሉበት መንገድ ሊቀየስ ይገባል፡፡ ገዥው ፓርቲ ፖሊስን፣ ወታደሩን፣ የፍትህ አካላቱን፣ የመንግስት ሰራተኛውን፣ የምርጫ አስፈጻሚ ባለስልጣኖችን ከህግ አግባብ ውጭ ወገንተኝነት እንዲያሳዩ እና እራሱ እንዳይጠቀምባቸው ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ማድረግ እና መረጋገጥ አለበት፡፡ የመንግስት ገንዘብ እና የማስፈጸሚያ ቁሳቁሶች በምንም ዓይነት መንገድ ለፓርቲ ስራ ገዥውን ፓርቲ ጨምሮ መዋል የለባቸውም፡፡ ጥብቅ በሆነ መልኩ መከልከል አለባቸው፡፡ የምርጫ ሂደቱ ምንም ዓይነት ችግር የሌለበት የመራጮች ምዝገባ፣ ሊደረስባቸው የሚገባ የምርጫ ቦታዎች፣ የምርጫ አስፈጻሚ ኃላፊዎችን ክብር ያረጋገጠ አያያዝ ማድረግን፣ ለሁሉም ክፍት የሆነ እና ግልጽነትን የተላበሰ የመራጮች ድምጽ ቆጠራ እና የማረጋገጥ ስራ ሂደት፣ ምርጫዎችን በሰለጠነ እና ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ነጻ በሆኑ ኃላፊዎች ታዛቢነት እንዲኖር ማድረግ እና የምርጫ ማጭበርበር ያለመኖሩ መረጋገጥ አለበት፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 በኢትዮጵያ ለተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ የአውሮፓ የምርጫ ታዛቢ ቡድን የመጨረሻ ዘገባ፣ የምርጫው ሂደት በተለይም የሂደቱን ግልጽነት እና ለሁሉም ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች እኩል ምህዳር ባለመስጠቱ ዓለም አቀፍ የምርጫ መስፈርትን አያሟላም፡፡ የበለጠ ፍትሀዊ እና ወካይነት ያለው የምርጫ ሂደት እንዲኖረው ተደረጉት ጥረቶች አናሳ ሆነው ተገኝተዋል…በመሆኑም ሙሉ፣ አድሎአዊ ያልሆነ እና መሰረታዊ የሆኑ መብቶችን ለመጠቀም ባለመቻሉ የምርጫው ሂደት በችግር ተተብትቧል… የገዥው ፓርቲ በመላ አገሪቱ ባሉ የምርጫ ጣቢያዎች ከመገኘቱ አንጻር ሲገመገም በተለይም የገጠሩ አካባቢ 80 በመቶ የሚሆነውን ህዝብ የሚሸፍነው የህብረተሰብ አካል የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተወካዮች እና ተወዳዳሪዎች አልነበሩም፡፡ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት በተለይም የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ባካተተ መልኩ የመሰብሰብ ነጻነቶች፣ ሀሳን በነጻ የመግለጽ፣ በነጻ የመንቀሳቀስ መብቶች ወጥ በሆነ መልክ አልተከበሩም…በመንግስት ቁጥጥር ስር ያለው የብዙሀን መገናኛ ለሁሉም እኩል በሆነ መልኩ ሽፋን አልሰጠም፣ በተለይም ለገዥው ፓርቲ ከ50 በመቶ በላይ የህትመት እና የብሮድካስት ሽፋን ሰጥቷል…በብዙዎቹ የአገሪቱ ዝቅተኛ የመንግስት አስተዳደራዊ መዋቅሮች ዘንድ በገዥው ፓርቲ እና በመንግስት መዋቅር መካከል የጠራ ልዩነት አልነበረም፡፡ የአውሮፓ የምርጫ ታዛቢ ቡድን በቀጥታ የመንግስት ሀብቶች ለገዥው አካል የምርጫ ዘመቻ ቅስቀሳ አገልግሎት መዋላቸውን አረጋግጧል፡፡ በስልጣን ላይ ያለው ገዥው ፓርቲ በግልጽ ጠቀሜታ ያለው መሆኑ በግልጽ የሚታይ ቢሆንም የምርጫ ቡድኑ የ2010ሩ አገር አቀፍ ምርጫ በብዙ መልኩ የምርጫ ምህዳሩ ፍትሀዊ አልነበረም፣ በብዙ የምርጫ ጣቢያዎች በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ገዥው ፓርቲ ያደላ ነበር… አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ የአውሮፓ ህብረት የታዛቢዎችን ቡድን የምርጫ ዘገባ “ለምንም የማይውል ወደ ቆሻሻ ቅርጫት መጣል ያለበት“ በማለት በአደባባይ አጣጥሎታል፡፡ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “የምርጫ ዘገባው ስለእኛ ምርጫ አይደለም፡፡ ይኸ ጉዳይ በገዥው ፓርቲያችን መጠናከር ደስተኞች ያልሆኑት የምዕራቡ ዓለም ኒዮሊበራሎች አመለካከት ነው፡፡ ማንም ወረቀት እና ብዕር የያዘ ሰው የፈለገውን ነገር መሞነጫጨር ይችላል፡፡“ በእርግጥ መለስ በፖለቲካ መድረክ ላይ እንደዚህ ያለ አስቀያሚ ቋንቋ ማስተላለፍ መቻሉ አፈታሪክ ነበር፡፡ መለስ በአፍሪካ አህጉር ማንንም የፖለቲካ ሰው መሳደብ፣ የጭቃ ጅራፉን ማጮህ፣ መበጥበጥ፣ መዘለፍ፣ ጥላሸት ሲቀባ የቆየ ሰው ነበር፡፡ መለስ የአውሮፓ ህብረት የታዛቢዎች ቡድን የምርጫ ዘገባን “በውሸት ቁልል የታጨቀ“ ብሎታል፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ ስለ2015 ምርጫ ማወቅ እና ማድረግ ያለባቸው ነገሮች፣ ፕሬዚዳንት ኦባማ እያወቁ ያላወቁ በመምሰል የሚያደርጉትን ትተው የምርጫ 2010 ስህተት በ2015ም እንዳይደገም ለመከላከል ማወቅ እና ማድረግ የሚኖርባቸው ጥቂት ነገሮች እንደሚከተለው ቀርበዋል፣ ቅድመ ምርጫ ከባቢ፡ የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን በ2010 እንደተመለከተው “ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻዎቻቸውን ነጻ እና ለሁሉም እኩል በሆነ የምርጫ ምህዳር ሜዳ ላይ የመወዳደር መብት እንዳለቸው ህጉ ይፈቅዳል”፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ የወያኔ ገዥ አካል የፖሊስ መንግስት ሆኖ የቀጠለ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከምርጫው በፊት በሚኖሩት ወራት ሰላማዊ ሰልፎች ለማካሄድ እና በአገሪቱ በሙሉ የፖለቲካ ከባቢ አየሩ ከማስፈራራት እና ከማሸማቀቅ ነጻ በመሆን እኩል የምርጫ ጨዋታ ምህዳር እንዲኖር ያላቸውን የፕሬዚዳንትነት ስልጣን ተጠቅመው እውን እንዲሆን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡ የመንግስት ሀብትን መጠቀም፡ ለአንድ ለፖለቲካ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ስራ በሚል የህዝብን ወይም የመንግስት ሀበት መጠቀም በህግ የተከለከለ ነው፣ ሆኖም ግን በ2010 በተካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ የአውሮፓ የምርጫ የታዛቢዎች ቡድን እንደዚህ ያሉ ሀብቶች በስፋት በስራ ላይ ውለው እንደነበር ምስክርነቱን ሰጥተቷል (ተሽከርካሪዎች፣ በስራ ላይ ያሉ የመንግስት ሰራተኞች ለገዥው ፓርቲ ለምርጫ ቅስቀሳ መሰማራት፣ በየአካባቢው ያሉ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ለምርጫ ቅስቀሳ ማዋል፣ ወዘተ) ፕሬዚዳት ኦባማ የህወሀት ገዥ አካል የመንግስት ሀብቶችን እና ተቋማትን ለእራሱ የፖለቲካ ስራ የሚጠቀምበት መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ እንደዚህ ያሉ የተሳሳቱ አሰራሮች ሊወገዱ እንደሚገባ ፕሬዚዳንቱ ጥረታቸውን ሊያደርጉ ይገባል፡፡ የሜዲያ ከባቢ፡ የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ተዛቢ ቡድን በ2010 በደረሰበት ድምዳሜ መሰረት በመንግስት በሞኖፖል የተያዘው የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት በአገሪቱ ያለውን ብቸኛ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቆጣጥሮታል፡፡ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ ይደረጋል፣ እንደዚሁም አንዳንድ በዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን የሚንቀሳቀሱ ድረ ገጾች ይሰለላሉ፡፡ የወያኔ አገዛዝ በአገሪቱ የሚገኙ ሁሉንም ነጻ ጋዜጦችን እና መጽሔቶችን የዘጋ መሆኑን፣ እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎትን መዝጋቱን መቀጠሉን እና የሳቴላይት እና የሬዲዮ ስርጭቶችን በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ወጭ እያደረገ እያፈነ መሆኑን ፕሬዚዳንት ኦባማ ሊያውቁት ይገባል፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ ያላቸውን ስልጣን በመጠቀም ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ እስከ ምርጫው ዕለት ድረስ በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉት ሚዲያዎች እኩል በሆነ መልክ እንዲያገልግሉ ብቻ ሳይሆን ጋዜጠኞች እንዲፈቱ እና ሜዲያው በነጻ እንዲያገለግል እና ሁሉን ዓይነት መረጃ ማቅረብ እንዲችል እንዲያደርጉ፡፡ ሲቪል ማህበረሰብ፡ የአውሮፓ የምርጫ ታዛቢ ቡድን በ2010 ምርጫ ዘገባው የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በበጎ አድራጎት እና ማህበራት ቀያጅ አዋጅ ምክንያት የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በምርጫ ሂደቱ ስራ በእጅጉ ስራቸው ተደናቅ ፎነበር፡፡ ይህ ህግ ከ10 በመቶ በላይ የሚሆነውን ገንዘብ ከውጭ ምንጭ የሚያገኙ ከሆነ የአገር ውስጥ ድርጅቶች እንዲባሉ ተደረገ፡፡ በሀገር ውስጥ ያሉ ደርጅቶች ብቻ ናቸው በሰብአዊ መብት እና በዴሞክራሲ ላይ መስራት የሚፈቀድላቸው፡፡ ከአንድ ሳምንት ገደማ አካባቢ በኒዮርክ ከተማ በክሊንተን ግሎባል ኢኒሼቴቭ ባራክ ኦባማ እንዲህ የሚል ንግግር አሰምተው ነበር፣ “የሲቪል ማህበረሰቡ መሪዎች ብቻ ናቸው በብዙ መልኩ ዘለቄታዊነት ያለው ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉት፡፡ ምክያቱም አባባሉ ሲነገር በነበረበት ጊዜ በጣም ጠቃሚው ርዕስ “ፕሬዚዳንት” ወይም “ጠቅላይ ሚኒስትር” አይደለም፣ በጣም ጠቃሚው ርዕስ “ዜግነት”… ዜጎች ሲቪል ማህበረሰብ ለምን በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ያስታውሰናል፡፡ ህዝቦች ሀሳባቸውን በነጻ መግለጽ ሲችሉ እና መሪዎቻቸው ተጠያቂ እንዲሆኑ ሲደረጉ መንግስት መልስ ሰጭ እና ውጤታማ ይሆናል፡፡“ ፕሬዚዳንት ኦባማ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት ተብሎ የታወጀውን ቀያጅ አዋጅ እንዲወገድ ወይም ደግሞ ጠቃሚነት ያለው ማሻሻያ እንዲደረግበት ጥረት እንዲያደርጉ በአጽንኦ እጠይቀዎታሉ፡፡ የሲቪል ማህበረሰቡ ለዴሞክራሲያዊ ሂደቱ ዋናው እምብርት በመሆኑ ላይ ሙሉ እምነት ስላላቸው ፕሬዚዳንት ኦባማ ያላቸውን ኃላፊነት ተጠቅመው የ2015 አገር አቀፍ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት የሲቪል ማህበረሰቡ ስራውን እንዲጀምሩ እና ነጻ ሆኖ እንዲሰራ እንዲደረግ እንዲያደርጉልን፡፡ የፕሬዚዳንት ኦባማ ኃይል ምንድን ነው? የእርዳታ ገንዘብ፡፡ በጥረት የተገኘ የአሜሪካ የዶላር ግብር ከፋይ ህዝብ፣ አፍሪካውያንን/ትን በመርዳት ሰበብ የአሜሪካንን ዶላር ለአፍሪካ አምባገነኖች መስጠት ሆኖም ግን የአፍሪካ አምባገነኖችን የሂሳብ አካውንት ማቆም፣ የእርዳታ ገንዘብ ይናገራል፣ እናም በወያኔ ደንቆሮ አለቆች አንደበት በከፍተኛ ደረጃ ይሰማል፡፡ ዳምቢሳ ሞዮ በመጽሐፏ ላይ የሞተ እርዳታ/Dead Aid ብላ ባሰፈረችው መሰረት የወያኔ ገዥ አካል 97 በመቶ የሚሆነውን በጀት የሚያገኘው ከውጭ እርዳታ ነው፡፡ በቀላል አነጋገር የወያኔ ገዥ አካል ከአሜሪካ ጠንካራ ሰራተኛ ግብር ከፋዮች የሚሰበሰብ እርዳታ እስካላገኘ ድረስ ለአንዲት ቀን እንኳ መቆየት እንደማይችል እና ህልውና እንደሌለው ግልጽ ሊሆን ይገባል፡፡ ፕሬዚዳት ኦባማ ዓመታዊውን የደህንነት እርዳታ ለለማኞቹ የወያኔ ተመጽዋቾች ለመስጠት እጅዎን ሲዘረጉ እ.ኤ.አ በ2009 በጋና አክራ ለአፍሪካውያን/ት ምን የሚል ንግግር አድርገው እንደነበር ያስታውሱ፡፡ ልማት በመልካም አስተዳደር ላይ የሚወሰን ነው፡፡ የእራሳቸውን ህዝቦች ፍላጎት የሚያከብሩ፣ በስምምነት የሚገዙ እና በጭቆና የማይገዙ መንግስታት በጣም ሀብታሞች ናቸው፣ የተረጋጉ ናቸው እናም ከሌሎች የዚህ ዓይነት ባህሪያት ከሌላቸው መንግስታት የበለጠ ስኬታማ ናቸው፡፡ መንግስታት የህዝቡን ሀብት እየመዘበሩ የእራሳቸውን ኪስ የሚያዳብሩ ከሆነ ማንም አገር ቢሆን ሀብት ሊፈጥር አይችልም፡፡ የህግ የበላይነት ቦታውን ለጨካኝነት እና ባርነት የሚለቅ ከሆነ በዚህ ዓይነት ማህበረሰብ ውስጥ መኖር የሚፈልግ የለም፡፡ ያ ዴሞክራሲ አይደለም፣ ይልቁንም ያ አምባገነናዊነት ነው፡፡ እናም በአሁኑ ጊዜ የዚያ ዓይነት መንግስት መወገጃው ጊዜው አሁን ነው… የ2015 የኢትዮጵያ ምርጫ ከነፋስ ጋር አብሮ ይሄዳል፣ እ.ኤ.አ በአስራ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አራት ኦር ዌል እንዲህ ብለው ጽፈው ነበር፣ “የወደፊቱን ስዕል የምትፈልግ ከሆነ በሰው ፊት ላይ ለዘላለም ማህተም የተደረገ የቦት ጫማ በህሊናህ ውስጥ አስብ፡፡“ የ2015ን የኢትዮጵያን ምርጫ ስዕል ለማየት ከፈለግህ በጠራራ ጸሐይ በቀን ብርሀን የተሰረቀን የምርጫ ውጤት እና በምርጫ ቦት የምርጫ ሌቦችን እና ዘራፊዎችን የሚያባርሩትን ፊቶች፣ ግን ለብዙ ጊዜ አይቆይም፣ ግን በጣም ለረዥም ጊዜ አይቆይም፡፡ በ2015 በኢትዮጵያ ስለሚደረገው ምርጫ የፕሬዚዳንት ኦባማ ንግግር “ባዶ ነፋስ” ነው፣ (“የውሸት ቁልሎች” ከመለስ ዜናዊ ዘለፋ በመጥቀስ) ውሸትን እውነት የሚያስመስል ፖለቲካዊ ቋንቋ፡፡ ታሪክ ብዙ ነገሮች “ከነፋስ ጋር እንደሚሄዱ” ያሳያል፡፡ “እርሱ የእራሱን ቤት የሚያስቸግር ነፋስን ይወርሳል፡ እናም ቂል የብልህ አሽከር ይሆናል የሚለውን ሁላችንም ልናውቀው ይገባል”፡፡ አሁን በህይወት የሌለው መለስ እና የእርሱ ደቀመዝሙሮች በአሁኑ ጊዜ አስቸጋሪ በሆነ መልኩ የኢትዮጵያን ቤት በማስቸገር ላይ ይገኛሉ፣ እናም ነፋስን ይዘግናሉ! አውሎ ነፋስም በቅስፈት ይዞዋቸው ይሄዳል። በ2015 በኢትዮጵያ ምርጫ አለ፡፡ ምርጫው ሰዎችን እንዴት በብር መግዛት እንደሚቻል ነው፣ እናም ስለሰዎች አስተዳደር አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ በ2015 ምርጫ አይኖርም፣ ሆኖም ግን ሸፍጥ ለመስራት የሚቆይ ምርጫ አለ፡፡ ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!

ከሰማያዊ ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ

ሰማያዊ ፓርቲ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በሕብረተሰቡ ዘንድ የሚነሱ በርካታ መሰረታዊና ወቅታዊ ጥያቄዎችን ጥያቄዎቹ አድርጎ ሲንቀሳቀስ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥም ፓርቲያችን በተለያየ መልኩ የተቻለውን ሁሉ በማድረግ እየታገለ በመንግስት ላይ ጫና ለማሳደርና ችግሮች መፍትሔ የሚያገኙበት አቅጣጫ ሲያመለክት ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ የሀገራችን አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሱና እየከፉ የመምጣታቸውን ያህል ገዢው ፓርቲ ቆም ብሎ ከማሰብ ይልቅ ወደ ማይወጣው አዘቅት ውስጥ ሀገሪቷን ጭምር እያንደረደራት ይገኛል፡፡ ይህም አልበቃ ብሎ ከዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደት ፍፁም በማይጣጣም መለኩ ዜጎችን ለአንድ ሀሳብ ብቻ እንዲገዙ አስገዳጅ መንገዶችን ጭምር በመጠቀም አፋኛ መዋቅሩን በማናለብኝነት እያስፋፋ ይገኛል፡፡ ይህም አልበቃ ብሎ ለማናቸውም አስተዳደራዊም ይሁን ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ሀይልን በመጠቀም ለመደፍጠጥና ለማጥፋት ቆርጦ በመነሳት ፍፁም አምባገነንነቱን ገፍቶበት የበርካቶች ህይወት ተቀጥፏል፡፡ ለዚሁ እንደማሳያም:- ካለፈው ዓመት የክረምት ወራት መጨረሻ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ ዜጎች በተለያየ ዘርፍ በመከፋፈል የግዳጅ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡ በዚህ አስገዳጅ ስልጠናም የምርጫ ቅስቀሳ በሚመስል መልኩ ከህወሓት/ኢህአዴግ ውጪ አማራጭ እንደሌለ ከመስበክ ባለፈም ማናቸውም የተለየ ሀሳብ የሚያራምዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን፣ ድርጅቶችንና ግለሰቦችን ፍፁም ስነ ምግባር በጎደለው መልኩ የጥላቻ ዘመቻ በማካሄድ የሃሳብ ልዩነትን የማስተናገድ ፍላጎቱ ሙሉ ለሙሉ የተዳፈነ መሆኑን አሳይቷል፡፡ ለዚህ ህገወጥ እንቅስቃሴ እና ዓላማም ወደ 1 ቢሊየን የሚጠጋ የህዝብ ሃብት ባክኗል፤ እየባከነም ይገኛል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እነዚህን ስልጠናዎች እጅግ በቅርበት ሲከታተላቸው የቆየ ሲሆን ከጅማሬውም ተቃውሞውን በይፋ ማሰማቱ ይታወሳል፡፡ በሌላ በኩል የሕብረተሰብ የመረጃ ክፍተት ለመሙላት እና ካለበት የፖለቲካ ድብርት ለማውጣትና ለማነቃቃት ሕገ መንግስቱን መሰረት አድርገው ሃሳባቸውን በነፃነት የገለፁ ጋዜጠኞችና የህትመት ውጤቶቻቸው ከገበያ እንዲወጡ በማተሚያ ቤቶች በኩል አስተዳደራዊ ሴራ መስራቱ ሳያንስ ሕገ መንግስቱን በሚፃረር መልኩ በሕትመት ሚዲያዎቹ ባለቤቶች፣ አዘጋጆች፣ በጋዜጠኞቹና ሰራተኞቻቸው ላይ በማስፈራራት ስነ ልቦናዊ ጫና በማሳደር በርካቶች ለስደት ሲዳረጉ ጥቂቶች ደግሞ ለእስር ተዳርገዋል፡፡ ገዢው ፓርቲ ባንድ በኩል ሀሳቡን ለመጫን የግዳጅ ስልጠና እየሰጠ በሌላ በኩል ደግሞ የተለየ ሀሳብን እንዲሁም የህዝብ ብሶትን የሚያሰሙ ጋዜጠኞች ላይ የማሳደድ ዘመቻ መክፈቱ የስርዓቱን መበስበስ እና አፋኝ አምባገነንነትን ብቸኛ አማራጭ አድርጎ መቀጠል መምረጡን ግልጽ አመላካች ነው፡፡ ከላይ ከሰፈሩት ሁነቶች እጅግ የከፋውና እየተባባሰ የመጣው ሌላው ከፍተኛ አደጋ ያዘለ ችግር ደግሞ፤ አስተዳደራዊ እና ፖለቲካዊ ጥያቄ እያነሱ ያሉ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በሀይል ለመገዛት ቆርጦ መነሳቱ ነው፡፡ ባሳለፍናቸው ሁለት ወራት ብቻ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ዜጎች በመንግስት ሀይሎች ተገድለዋል - ቆስለዋል - ተሰደዋል፡፡ በኦጋዴን መንግስትን የተቃወሙ ዜጎች ወደ ግጭት እንዲገቡ በሚገፋፋ መልኩ ጥያቄዎቻቸውን በመግፋት በርካታ ዜጎች በመንግስት ሀይሎች ህይወታቸው መቀጠፉ ሳያንስ ሬሳቸው እንኳን ክብር በሌለው ሁኔታ መሬት ለመሬት እየተጓተተ ባደባባይ ሰብአዊ መብት ሙሉ ለሙሉ ተጥሷል፡፡ በጋምቤላም በተመሰሳይ መልኩ የህወሓት ሰዎች መሬት በሕገ-ወጥ መንገድ መቀራመታቸውን የተቃወሙ ዜጎች ወደ ግጭት የተገፉበት እና በርካታ የሰው ህይወት የተቀጠፈበት ሁነት እጅግ አሳዛኝ እና መንግስት የተያያዘው መንገድ ወደ ከፋ ሁኔታ ሀገሪቷን እየወሰዳት ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ከላይ የተዘረዘሩትንና ከዚህ ያልተጠቀሱትን በተለያየ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚፈፀሙትን በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና አስጊ ሁኔታዎች በቅርብ እየተከታተለ ይገኛል፡፡ በተደጋጋሚ እንደተገለፀውም አሁን ካለንበት ሀገራዊ አዘቅት እና አደጋ መውጫው መፍትሔ በቆራጥነት ሀገርን የማዳን ትግል ማካሄድ እንደሆነ ፓርቲያችን በሚገባ ይገነዘባል - ያምናል፡፡ በስልጠናዎቹ ወቅትም ተማሪዎች እና በርካታ የሕብረተሰብ ክፍሎች በብዛት ሲያነሱት የነበረውን ጥያቄና ስሞታም ከግንዛቤ በማሰገባት ጥያቄዎቹ ምላሽ የሚያገኙበትን የትግል አቅጣጫ በተጠናከረና በተጠና መልኩ አሳታፊ አድርጎ ከግብ ለማድረስ በሙሉ ቁርጠኝነት እና አቋም ላይ እንደሚገኝ ያረጋግጣል፡፡ በመሆኑም የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ከግምት በማሰስገባት መላው የሀገሪቱ ህዝብ፣ በውጪ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ለሀገር ተቆርቋሪ ተቋማት እንዲሁም በገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ስር ሆናችሁ ለውጥን የምትሹ ወገኖች ሀገራችንን ወደ አደጋ እየወሰዳት ያለውን አፋኝ ስርዓት በቻላችሁት ሁሉ በመቃወምና ከስርዓቱ ጋር ባለመተባበር በብሔራዊ ደረጃ የሚደረገው ትግል አካል እንድትሆኑ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር! ጥቅምት 18 2007 ዓ.ም ሰማያዊ ፓርቲ አዲስ አበባ Source ነገረ ኢትዮጵያ/Negere Ethiopia. ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia's photo. ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia's photo.

Tuesday, 28 October 2014

Friday, 24 October 2014

የህዝብ ግንኙነት ካድሬዎች በማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ ሊዘምቱ ነው

ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ ሬድዋን ሁሴን የሚመራው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አሰልጥኖ በፌዴራል የመንግስት ተቋማት በህዝብ ግንኙነት ኃላፊነት ለመደባቸው ካድሬዎች የሁለት ቀናት የማህበራዊ ድረገጾች አጠቃቀም ስልጠና በመስጠት በተለይ በግንቦት ወር ከሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ እንዲሳካ የበኩላቸውን አዎንታዊ ሚና እንዲጫወቱ አደራ ተጥሎባቸዋል፡፡ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን እንደገለጸው የኮምኒኬሽን ጽ/ቤቱ በሚኒስትሮች ምክርቤት ደንብ ቁጥር 158/2001 ሲቋቋም በመንግስትና በሕዝቡ መካከል ቀልጣፋ ውጤታማ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ማስቻል አንዱና ዋና ዓላማው ያደረገ ቢሆንም በተግባር ግን የሰለጠኑና ልምድ ያካበቱ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎችን የአመለካከት ችግር አለባቸው በሚል በማባረርና በማንሳፈፍ ካድሬዎችን በለብለብ ስልጠና ሲመድብ ቆይቷል፡፡ ዘርፉ ልምድና በቂ ስልጠና በሌላቸው ካድሬዎች በመያዙ በመረጃ አሰጣጥ በኩል ያለው ችግር እንዲባባስ ምክንያት ሆኗል፡፡ ጽ/ቤቱ የመደባቸው ካድሬዎች በተለይ በማህበራዊ ድረገጾች አጠቃቀም ደካማ በመሆናቸው ምክንያት ሚኒስትሩ አቶ ሬድዋን በሰበሰቡዋቸው ቁጥር ከፍተኛ ብስጭት የኢህአዴግን አቁዋም እንኩዋን መናገር የማይችሉ በማለት እስከመዝለፍ ደርሰዋል፡፡ የዜና ምንጮቻችን እንደጠቆሙት በአዲስአበባ ቦሌ አካባቢ በሚገኘው ዋሽንግተን ሆቴል ባካሄደው ስልጠና ካድሬዎቹ እንደፌስ ቡክና ቲዎተር ባሉ ማህበራዊ ድረገጾች ላይ እንዴት መጠቀም እንደሚችሉና የመ/ቤታቸውንና የመንግስትን አቋም ከማስረዳት ባለፈም ጸረ መንግስት አቋም ያላቸውን መረጃዎች በማጣጣልና በማስተባበል ረገድ የበኩላቸውን የተከላካይነት ሚና እንዴት እንደሚወጡ በመሰልጠን ላይ ናቸው። በተለይ የማህበራዊ ድረገጾች መንግስትን በሚቃወሙ ሃይሎች ሙሉ በሙሉ ቁጥጥር ስር እንደወደቀ የአቶ ሬድዋን ቢሮ የሚያምን ሲሆን ይህን ለመመከት የሚያስችል ብቃት ያለው የኮምኒኬሽን ባለሙያ ባለመኖሩም ካድሬዎቹ በተደጋጋሚ ወቀሳ ሲሰነዝርባቸው መቆየቱን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ለዘጋቢያችን ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የአንዳንድ የፌዴራል መ/ቤት ተቋማት የህዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ካድሬዎች በተለይ በፌስቡክ ፈራተባ እያሉ መረጃዎችን መልቀቅና በሚጻፉ የተለያዩ ጉዳዮች አስተያየት መሰንዘር በመለማመድ ላይ ናቸው፡፡

Thursday, 16 October 2014

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ወገንተኝነቱን የሚያሳይበት ወቅት አሁን ነው!

ዘረኛውና ፋሽስታዊው የህወሓት አገዛዝ የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት በዘርና በፓለቲካ ወገንተኝነት በመከፋፈል ሹመቱና ጥቅማ ጥቅሙን ለራሱ ወገን፣ ችግሩንና መከራዉን ግን ለሌላው ኢትዮጵያዊ ያደለ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ሳይማሩና ሳይሰለጥኑ የጄኔራልነት ማዕረጎችን በሙሉ ሰብስበው የወሰዱት የህወሓት አባላት መሆናቸው የአደባባይ ሚስጢር ነው። በወያኔ መዳፍ ውስጥ እየተሰቃየች ባለችው ኢትዮጵያችን ውስጥ በዘርም ይሁን በፓለቲካ አመለካከት ከህወሓት የተለዩ ኢትዮጵያዊያን ቢማሩም ቢሰለጥኑም ለከፍተኛ አመራርነት እንደማይበቁ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ያየነው ነው። አገዛዙ ቅራኔ ውስጥ በገባባቸው ቦታ ሁሉ እየዘመቱ ሕይወታቸውን እየገበሩ ያሉት ግን በመካከለኛና ዝቅተኛ ማዕረጎች ያሉ ኢትዮጵያዊያን መኮንኖችና ብዙሃኑ የሠራዊቱ አባላት የሆኑ ወታደሮችናቸው። ብዙሃኑ የሠራዊት ክፍል አለቆቹን ከመጠበቅ ባለፈ ድምጹን ከፍ አድርጎ ለመናገር እንኳን የማይፈቀድለት ሎሌ ተደርጓል። ለኢትዮጵያዊ ወታደር ለህወሓት ሎሌ ከመሆን በላይ የሞት ሞት የለም። ብዙሃኑ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊቱ አባላት በጥቂት የወያኔ ሹማምንት የሚረገጥ መሆኑ የሠራዊቱን አባላት የግል ስብዕና ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የሠራዊቱን ክብር ይነካል። የሠራዊታችን የህወሓት አገልጋይ መሆን የምንወዳት አገራችን ኢትዮጵያን ያዋርዳል። ይህ ዉርደት በዚህ ሁኔታ መቀጠል የለበትም። ከእንግዲህ ጄኔራሎችና ሌሎችም የበላይ አዛዦች ሁሉ የአንድ አካባቢ ተወላጆች በሆኑበት ሠራዊት ውስጥ ተስማምቶ መኖር መቀጠል እያንዳንዱን የመከላከያ ሠራዊት አባል ሊያሰፍር ይገባል። የህወሓት ጄኔራሎች ጮማ በውስኪ ሲያወራርዱ፤ በህንፃዎች ግንባታ፣ በባንኮች ንግድ፣ በግብርናና በኢንዱስትሪ ዘርፍ ተሰማርተው ቢዝነሳቸውን ሲያጧጥፉ፣ ምስኪኖቹ የሠራዊቱ አባላት በኦጋዴን፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በአማራና በሌሎች የአገሪቱ ግዛቶች እየተወረወሩ ወገኖቻቸውን የሚፈጁበት ሥርዓት ማብቃት አለበት። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ብዙሃኑ አባላት ቤተሰቦቻቸው በችጋር እየተቆሉ የአዛዦቻቸው ሀብት ጠባቂ መሆናቸው ማክተም አለበት። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት የጭለማ ዘመን ታሪክ እያበቃ መሆኑን የሚጠቁሙ ምልክቶች እየታዩ ነው። መሣሪያዎቻቸውን እንደያዙ የነፃነት ኃይሎችን የሚቀላቀሉ የሠራዊቱ አባላት ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨረመ መጥቷል። ሠራዊቱ ከሕዝብ ጎን እንደሚቆም ውስጥ ውስጡን የሚላኩ መልዕክቶች እየተበራከቱ መጥተዋል። ይህ አበረታች ዜና ነው፤ ግን በቂ አይደለም። ወያኔን ከውስጥም ከውጭም የምናጣድፍበት ጊዜው አሁን ነው። የነፃነት ኃይሎችን መቀላቀያ ጊዜ አሁን ነው፤ በሠራዊቱ ውስጥም በህቡዕ መደራጃ ጊዜ አሁን ነው። ይህን ጊዜ መጠቀም ብልህነት ነው። ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ጥቂት የህወሓት ጥጋበኞች በብዙሃኑ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ላይ የሚያደርሱት በደል ማብቃት አለበት ይላል። ግንቦት 7፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት በሙስና የደለቡት፣ ትዕቢተኛና ጨካኝ መሪዎቻቸው ፍጹም ኢትዮጵያዊ ባህርይ የሌላቸው ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች እንደሆኑ በመረዳት በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ክንዱን እንዲያነሳባቸው ጥሪ ያደርጋል። ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ሕዝብም የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት አንድ ወጥ እንዳልሆነ እና በመካከለኛና ዝቅተኛ ደረጃ ያሉ መኮንኖችና አብዛኞዎቹ ወታደሮች የሕዝብ ወገን መሆናቸውን እንዲገነዘብ ያሳስባል። “አብረን ነው ዘረኛውና ፋሽስቱን ወያኔን ከኢትዮጵያ ጫንቃ ላይ አውርደን የምንጥለው” ስንል አብዛኛው የመከላከያ ሠራዊታችን ኢትዮጵያዊ ወገናችን እንደሆነ እና በወደፊቷ ኢትዮጵያ ግንባታ ውስጥም ጉልህ ሚና እንዲጫወት የምንፈልግ መሆኑን ግልጽ ማድረግ እንሻለን። የመከላከያ ሠራዊቱም የሕዝብ ወገንተኝነቱ በተግባር እንዲያሳይ ጥሪ እናደርጋለን። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት የሕዝብ አካል ነው፤ የሕዝብ ወገናዊነቱ በተግባር የሚያሳይበት ትክክለኛ ጊዜ ደግሞ አሁን ነው እንላለን። ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!

Sunday, 5 October 2014

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የያዘችውን ፓሊሲ ትመርምር

መስከረም 15 ቀን 2007 ዓም፣ የዩ. ኤስ. አሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦቦማና ባልደረቦቻቸው በአንድ በኩል ኃይለማርያም ደሣለኝና አለቆቹ በሌላ በኩል ሆነው የሁለትዮሽ ስብሰባ ተደርጎ ነበር። በዚህ ስብሰባ ላይ ፕሬዚዳንት ኦባማ ያደረጉት ንግግር የዲፕሎማሲ ጨዋነት ከሚጠይቀው ርቀት በላይ ተጉዘው ሸሪኮቻቸው ባልሠሯቸው ጀብዶች ማሞገሳቸው አሳዝኖናል። ፕሬዚዳንት ኦባማ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ያደረጉት ንግግር ላይ በርካታ ስህተቶች፣ ህፀፆችና ግድፈቶች የያዘ ከመሆኑም በላይ አንዳንዱ አስተያየት የኢትዮጵያዊያንን ክብር የሚነካ ሆኖ አግኝተነዋል። ፕሬዚዳንቱ ንግግራቸውን የጀመሩት “ኢትዮጵያ በዓለም ከሁሉም በላይ በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ያለች አገር ነች“ በሚል ዓረፍተ ነገር ነበር። የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ጽ/ቤት የፈጠራ ቀመሮች በዓለም ባንክ በኩል ዞረው በሚስ ሱዛን ራይስ ተቀነባብረው በባራክ ኦባማ አንደበት መስማት የሚያሳፍር ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ኦባማ የተናገሩትን ዓረፍተ ነገር ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥና ራድዮ ደጋግሞ ሰምቶ ሰልችቶታል። ኦባማ፣ ይህ የተሰለቸ ዓረፍተ ነገር በእሳቸው አንደበት ሲነገር ስለሚሰጠው ትርጉም ጥቂት ቢያስቡ ኖሮ ለእሳቸውም ለአሜሪካም የተሻለ ነበር ብለን እናምናለን። “በአንድ ወቅት ራሷን መመገብ ያቅታት የነበረችው አገር ዛሬ ከፍተኛ እድገት የሚታይባት ሆናለች፤ አሁን የግብርና ብቻ ሳይሆን [የኤሌክትሪክ] ኃይልንም በመሸጥ በቀጠናው ቀዳሚነት ይዛለች” ሲሉ ያሞካሿት ኢትዮጵያን ኢትዮጵያዊያን የማያውቋት መሆኑን፤ እሳቸው የሚያወድሷት ኢትዮጵያ በህወሓት ፕሮፖጋንዳ እንጂ በመሬት ላይ የሌለች መሆኑን ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ማወቅ ነበረባቸው። በአንፃሩ የእውነተኛዋ ኢትዮጵያ 70% ሕዝብ በድህነት ወለል በታች በሆነ ኑሮ ሕይወቱን እየገፋ እንደሆነ፤ የሚሊዮኖች ኢትዮጵያዊያን የእለት ጉርስ ምንጭ የአሜሪካና የአውሮፓ አገሮች እርዳታ መሆኑን ፕሬዚዳንት ኦባማ አያውቁም ማለት ይከብዳል። ፕሬዚዳንት ኦባማ የተናገሩለት የመብራት ኃይልም ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተስፋ ተረት መሆኑን፤ ዛሬም የኢትዮጵያዊው የምሽት ኑሮ የሚገፋው በባትሪ፣ በሻማና በኩራዝ መሆኑን ፕሬዚዳንት ኦባማ አያውቁም ማለት ያስቸግራል። ፕሬዚዳንት ኦባማ ከተናገሩት ውስጥ ትርጉም የሚሰጥ ነገር ቢኖር ስለ “ሰላም ማስከበር” የተናገሩት ነው። የህወሓት አገዛዝ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን ገንዘብ ባለበት እና አሜሪካ ወደ ፈለገችው ቦታ ሁሉ የሚልክ መሆኑ ይታወቃል። ስለሆነም የጦሩ የሰላም ማስከበር ሥራ ማሞካሸታቸው የሚጠበቅ ነው። እንዲያውም የፕሬዚዳንቱ ሙሉ ንግግር የተቃኘው ከዚህ አቅጣጫ ይመስላል። እንደዚያ ባይሆን ኖሮ የራሳቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያወጣውን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሪፖርትን ውድቅ የሚያደርግ ነገር ባልተናገሩም ነበር። አንዳችም ነፃ ተቋማት በሌሉበት አገር ውስጥ ፍትሃዊ ምርጫ የሚባል ነገር ሊኖር እንደማይችል አውቀው ቀዳሚው ጥያቄዓቸው የሰብዓዊ መብቶች መከበር እና የነፃ ተቋማት ግንባታ ጉዳይ ባደረጉት ነበር። ፕሬዚዳንት ኦባማ ስለኢትዮጵያ ተጨንቀው ቢሆን ኖሮ የራሳቸው ስቴት ዲፓርትመን የዘንድሮውን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሪፓርት ያስታውሱ ነበር። ሪፓርቱን በማስታወሳቸው ብቻ በግፍ እየታሰሩ ስላሉት ዜጎች፣ በኦጋዴን፣ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በአፋር እና በአማራ እየተጨፈጨፉ ስላሉ ዜጎች፣ ስለ መሬትና የሀብት ዘረፋ፣ ስለፍትህ እጦት፣ ስለ ተቋማዊ ዘረኝነት እና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮች እንዳነሱ ይቆጠር ነበር፤ ምክንያቱም ያ ሪፓርት የያዘው ይህንን ሁሉ ነው። ፕሬዚዳንት ኦባማ ግን የንግግራቸው ግብ ዘማች ወታደር ማግኘት በመሆኑ የራሳቸውን የስቴት ዲፓርትመንት ሪፓርት ትተው የወያኔን ሪፓርት ይዘው የቀረቡ አስመስሎባቸዋል። ይህ አካሄድ አሜሪካ ወደማትፈልገው የጦር አረንቋ የሚላኩ የሠራዊት አባላት ሊያስገኝ ቢችልም የሚያስከትላቸው ጉዳቶችም መታየት ነበረባቸው። የንግግራቸው ፈጣን አሉታዊ ውጤት ለማየት ቀናትም አልፈጀም፤ እነሆ በኦባማ አይዞህ ባይነት የተነቃቁት የህወሓት ገዳዮች ከኢትዮጵያ አልፈው በአሜሪካ ምድርም በኢትዮጵያዊያን ላይ መተኮስ ጀምረዋል። የኦባማ ንግግር ትኩረት የፀጥታ ጉዳዮች ሆኖ ኢኮኖሚ የግኑኝነት ማሳለጫ ሆኖ ቀርቧል፤ የሰብዓዊ መብት አጠባበቅና የዲሞክራሲ ጉዳዮች ደግሞ ፈጽመው ተገፍተው ወጥተዋል። ይህ ንግግር አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለውን ፓሊሲ አመላካች ነው። ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በፀጥታ ጉዳይም ቢሆን አሜሪካ የያዘችው አቋም በረዥም ጊዜ የኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የአሜሪካን ጥቅም የሚጎዳ ነው ብሎ ያምናል። ኢትዮጵያ ለአሜሪካ ከወታደር ምንጭነት በላይ የምታገለግል አገር ናት። ኢትዮጵያ ውስጥ ከራሱ ሕዝብ ጋር የታረቀ መንግሥት መኖር ለቀጠናው ሰላም እና ብልጽግና ወሳኝ ከመሆኑም በላይ የቀጠናው ሰላምና ብልጽግና የአሜሪካም ስትራቴጂያዊ ጥቅም ነው ብለን እናምናለን። የአጫጭር ጊዜ ጊዜዓዊ ጥቅሞችን ብቻ በመመልከት አምባገነኖችን መደገፍ አሜሪካን ምን ያህል ውድ ዋጋ እያስከፈላት እንደሆነ በዓይኖቻችን እያየነው ያለ ሀቅ ነው። አሜሪካ አምባገነኖችን መደገፏን ከቀጠለች ፈጥኖም ይሁን ዘግይቶ የምታገኘው እስካሁን ስታገኝ የነበረውን ውግዘትና የጽንፈኞች መጠናከር ነው። አሜሪካ የተሳሳተ ፓሊሲ በያዘችባቸው አገሮች ሁሉ ግንባር ቀደም ተጎጂዎች ለዘብተኞችና ዲሞክራቶች ሲሆኑ እየተጠናከሩ የሚመጡት ደግሞ ጽንፈኖች ናቸው። አሁንም አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የያዘችውን ፓሊሲ የአገሪቱን የዲሞክራሲ ኃይሎችን የሚያዳክም እና ጽንፈኛ ኃይሎችን የሚያበረታታ እንደሆነ ከወዲሁ ሊጠን ይገባዋል። ዩ. ኤስ አሜሪካ የምትመራባቸው የነፃነት፣ የእኩልነትና የፍትህ እሴቶች የግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እሴቶችም ናቸው። ኢትዮጵያዊያን እንደ አሜሪካ ዜጎች ሁሉ ፍትህን፣ ነፃነትን፣ እኩልነትንና ዲሞክራሲን ይሻሉ፤ እነዚህ መሻት ደግሞ መብታቸው ነው ብሎ ግንቦት 7 ያምናል፤ ለዚህም ይታገላል። አሜሪካ ይህን ትግል ማገዝ ይገባታል። በተግባር የምናየው ግን የዚህ ተቃራኒ ነው። አሜሪካ ለአጫጭር ጊዜ ጥቅም ስትል ከአምባገነን ኃይሎች ጋር ማበሯ የዓላማ ተጋሪዎቿን እያዳከመ መሆኑ የወቅቱ የዓለም ሁኔታ የሚመሰክረው ሀቅ ነው። በኢትዮጵያ ላይ እየተከተለችው ያለው ፓሊሲው ተመሳሳይ የረዥም ጊዜ መዘዝ እንዳያመጣ ያሰጋል። ይህ እንዳይሆን እርምት የሚገባው አሁን ነው። ስለሆነም፣ ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ዩ. ኤስ. አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የያዘችውን ፓሊስ እንደገና እንድትመረምር እና ዘረኛና አምባገነኑን የህወሓት አገዛዝን መርዳት እንድታቆም አበክሮ ያሳስባል። ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Saturday, 4 October 2014

ደቡብ ሱዳን የኢትዮጲያን ተቃዋሚዎች ልትረዳ ነው

Oct 3, 2014(Nyamilepedia) — An insider, from within the inner circle of South Sudan security organ, alleged that he, in a team supervised by Akol Koor, the Director of Internal Security Bureau, met Gen. Thokwaath Pal, the leader of the rebel Ethiopian Unity Patriotic Front (EUPF) in mid September 2014. The insider alleged that the main objectives of the meeting was to seal a new deal that would strengthen the Ethiopian rebels groups to destabilize the SPLA rebels’ main military training centers in Maiwut and Pagak at the eastern corridor of South Sudan – Ethiopia border. According to the insider, Gen.Thokwaath has been tasked to establish links with other rebel groups within Ethiopia to form a coalition that will fight for a regime change and destabilize South Sudan Peace Process in Bahir Dar. According to the insider, director Akol Koor has issued One Million ($1,000,000) US Dollar to Ethiopia Rebel groups to equip and set up their operation centers at South Sudan-Ethiopian border. The intelligence alleged that Juba has promised Gen. Thokwaath a sufficient financial and military supports. He said that military garrisons will be set up at the border to detach any military support from Ethiopian government to South Sudan rebels. Gen. Thokwaath is also expected to cut any supply routs and recruitments from Gambela Refugees camps in Ethiopia to South Sudan. This would allegedly benefits the regime as it expected to lure the Eastern Jikany to support South Sudan government. South Sudan government delegation, according to Michael Makuei Lueth’s interview on BBC focus on Africa, has lost truth in TROIKA, Ethiopia and the Ethiopian Ambassador, Seyoum Mesfin, who leads South Sudan Peace Talks. Hon Makuei recently calls on IGAD to relocate the peace process to Kenya and change the chief mediator. According to Michael Makuei Lueth, Ethiopia and TROIKA partners support regime change in South Sudan. Mr. Lueth fears that unless the mediation is relocated to Kenya and led by the Kenyan Envoy, General Lazarus Sumbeiyo, the peace process may never yield an agreement. Salva Kiir government allied with Ugandan and Sudanese rebels against the insurgents in Greater Upper Nile. Four rebels’ factions that are fighting for regime change in Sudan joined South Sudan civil war in December 2013. The Government of South Sudan signed military cooperation with Egypt amid allegations that Ethiopia support SPLA rebels, under the former vice president, Dr. Riek Machar Teny. The agreement has allegedly given Egypt a green light to set up a military base in South Sudan, a move that is expected to throw off Ethiopia’s mega project, the Grand Ethiopian Renaissance Dam.

Monday, 29 September 2014

የታጋይ አንደርጋቸው ጽጌ ጉዳይ በአውሮፓ ህብረት ምክርቤት ኮሚሽን ውይይት ተደረገበት፤ በአስቸኮይ እንዲፈታም ጠይቀዋል።

ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ በአምባገነኑ ወያኔ እጅ ወድቆ መሰቃየት ከጀመረ 3 ወራት አልፈዋል። ባለፉት ቀናት የአውሮፓ ህብረት የሰበአዊ መብት ም/ቤት በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ ውይይት አደርገዋል ። አንዳርጋቸው የፖለቲካ እስረኛ እና ለዲሞክራሲ፣ ለነጻነት፣ ለመልካም አስተዳደር እና ሰበአዊ መብት መከበር የሚታገል የግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር ሲሆን ባስቸኮይ ተለቆ ወደ እንግሊዝ እንዲመለስ ኮሚሸነር ተናግረዋል፡፡የተከበሩ አና ጎሜዝ አንዳርጋቸው ብቻ አይደለም በርካታ ኢትዮጵያኖች ታስረዋል ብሎግ ዘጠኝ፣ ጋዜጠኞች፤ ፖለቲከኞች ሁሉም ካለ ምንም ምክንያት መፈታት አለባቸው። የኢትዮጵያን ፓርላማ ባለፈው ሂጄ አይቸዋለሁ በጣም የሚገርም ነው የፖለቲካ እስረኛ ሳይሆን ሽብርተኞች ናቸው ያሉን ሲሉ ከአንድ መንግስት የማይጠበቅ ነው። እስክንድር ነጋ ሽብርተኛ ሳይሆን አለም አቀፍ የብእር ተሸላሚ ነው። ብሎግ 9 ጸሃፊያን፣ ጦማሪያን ናቸው። አንዳርጋቸው ጽጌ የፍትህ ታጋይ ነው። ታዲያ እንዴት ነው የኢትዮጵያ መንግስት ህግን የሚተረጉመው ሲሉ ተናግረዋል። ኮሚሽኑ በሁለት ወር ውስጥ ይህን ጉዳይና የኢትዮጵያን ሰበአዊ መብት በተመለከተ እና የአንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ የሚመለከት ኮሚቴ እንዲሰየም እና እንደገና እንደሚወያዩበት የወሰኑ ሲሆን የአቶ አንዳርጋቸውን በተመለከተ አሳሳቢ በመሆኑ ከእንግሊዝ መንግስት ጋር በመሆኑ ለብቻ በሚቀጥሉት እናየዋለን ሲሉ ዘግተዋል። በዚሁ ስብሰባ የኢትዮጵያ መንግስት ተወካይ ቀርበው አሁንም የተለመደ ማስተባበያ ሰጥተዋል። እኛ ምንም አይነት ህግ አልጣስንም ብለዋል።

Friday, 19 September 2014

በህወሓት አገዛዝ በኦጋዴን ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን የጅምላ ግድያ በጽኑ እናወግዛለን!!!

የአገራችን የኢትዮጵያን በትረ ሥልጣን በጠመንጃ ኃይል የተቆጣጠረው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ የሥልጣን እድሜውን ለማራዘም በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየወሰደ ያለውን እሥራትና ግድያ አጠናክሮ መቀጠሉን የሚያጋልጡ ማስረጃዎች በየጊዜው ከራሱ ከአገዛዙ እየሾለኩ በመውጣት ላይ ናቸው። መስከረም 5 ቀን 2007 ዓም በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን በምስል ተደግፎ የቀረበው በኦጋዴን ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ከነዚህ ማስረጃዎች አንዱ ነው ። የወያኔን አገዛዝ ይቃወማሉ የተባሉና በኦጋዴን ክልል ከሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎች ጋር ንኪኪ አላቸው የተባሉ እነዚያ የጅምላ ጭፍጨፋ ሰለባ የሆኑ ምስኪን ዜጎች አስከሬን መሬት ለመሬት እየተጎተተ አንድ ቦታ እንዲከማች ሲደረግ፤ አስከሬኑን ለመሰብሰብ ከታዘዙት የአካባቢው ነዋሪዎች አንዱ የገዛ ወንድሙ አስከሬን ከሚጎተተው መሃል እንደነበረ መስማት ህሊናን የሚሰቀጥጥና የወያኔ የጭካኔ እርምጃ አቻ የሌለው ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያመላክት ነው። በደርግ ዘመን ቤተሰብ የተገደለበትን ሰው አስከሬን ለማግኘት የጥይት ዋጋ ለመክፈል ይገደድ ነበር በማለት ሥርዓቱን በነጋ በጠባ የሚወነጅል አገዛዝ ከሚወነጅላቸው ሥርዓት በባሰ በኦጋዴን የገደለውን ንጹህ ዜጋ አስከሬን የገዛ ወንድሙ መሬት ለመሬት እንዲጎትተው አድርጓል። በዚህም ህወሓት በሰብዓዊነት ላይ ከቀደምቶቹ ሁሉ የከፋ የሚሰቀጥጥ ወንጀል ፈጽሟል። ቀደም ሲል በበደኖ፤ በአርሲ፤ በአርባ ጉጉ፤ በሃዋሳ ፤ በጋምቤላ እና ድህረ ምርጫ 97 በአዲስ አበባና ሌሎች የአገሪቱ ከተሞች ነዋሪዎች ላይ በወያኔ ልዩ ትዕዛዝ ተመሳሳይ የጅምላ ጭፍጨፋዎች ተካሂደዋል። ይህ ሁሉ ወንጀል እየተፈጸመብን አስከዛሬ ወያኔን በጫንቃችን ተሸክመን ለመኖር የተገደድነው እነዚሁ ጥቂት ዘረኞች ሕዝባችንን በዘር፤ በቋንቋና በሃይማኖት በመከፋፈላቸው አንዱ የኅብረተሰብ ክፍል ሲጠቃ ሌላው በዝምታ የሚመለከትበት ሁኔታ በመፈጠሩ ነው። ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ወያኔ በኦጋዴን ሕዝብ ላይ የፈጸመውን ይህንን አረመኔያዊ እርምጃ አጥብቆ ያወግዛል። ጊዜው ሲደርስ የዚህ ወንጀል ፈፃሚዎች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው ብሎ ያምናል። ስለሆነም ወያኔ ሕዝባችንን አቅም ለማሳጣት ላለፉት 23 አመታት በኅብረተሰባችን መካከል የገነባውን የጥርጣሬና የጥላቻ ግንብ በመናድ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በኦጋዴንና በሌሎች የአገራችን ክፍሎች ወገኖቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ሰቆቃና እልቂት ለማስቆም እንዲችሉ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል። ኦጋዴን ውስጥ ለፈሰሰው የንጽሃን ደምና በሰብዓዊነት ላይ እየተፈጸመ ላለው ወንጀል ተጠያቂው ሥልጣንን በኃይል የሙጥኝ በማለት በአገርና በሕዝብ ሃብት ዘረፋ ላይ የተሰማራው ጥቂት የህወሃት አመራር መሆኑ አያጠያይቅም። ይህንን ወንጀለኛ ቡድን ለፍርድ ለማቅረብ ንቅናቄዓችን ግንቦት 7 የሚያደርገውን ሁለገብ ትግል ለፍትህ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ የቆመ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንዲቀላቀል በዚህ አጋጣሚ ጥሪ ቀርቦለታል። ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Sunday, 7 September 2014

የኢህአዴግ አባላት በድርጅታቸው ላይ ጥያቄዎችን ማንሳት ቀጥለዋል

በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለከተሞች በመካሄድ ላይ ባለው የኢህአዴግ አባላት ስብሰባ ፣ አባላቱ ዛሬም በርካታ ጥያቄዎችን ሲጠይቁ መዋላቸውን ከውስጥ ምንጮች የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ዛሬ ከሰዓት በኋላ በአባላቱ ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል፡- ” የኢትዮጵና የኤርትራ ህዝቦች የማይነጣጠሉ የአንድ ሃገር ዜጎች ሆነው ሳለ በመሪዎች አለመግባባትና ሽኩቻ በመለያየታቸው እስከዛሬ ድረስ እየተላቀሱ ይገኛሉ፤ ይህም የሆነው በኢህአዴግም አስተዋፆ ጭምር ነው፤ አሁንም ቢሆን ከኛ ጋር መስማማት ከፈለጉ በራችን ክፍት ነው የምትሉት ከልባችሁ ነወይ?” የሚለው ጥያቄ ሰፊ ሰአት ወስዶ ማከራከሩ ታውቋል። በሃይማት አክራሪነት ጉዳይ ለተነሱት ጥያቄዎች ደግሞ ” ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ ሰልፍ በጠራበት ጊዜ ሰልፈኛው መስኪድ አካባቢ ሲደርስ ሙሉ ለሙሉ ለጸሎት ወደ መስኪድ እንደገባ አረጋግጠናል፤ ስለሆነም ” መንግስት ሁሉንም ሚዲያዎች እንደጥፋተኛ ቆጥሮ ጋዜጦችና መጽሔቶችን እንዳለ ከገበያ ማስወጣቱ እኛ አባሎቹ የኢህአዴግን ክፍተት የምናውቅበት መንገድ ተዘግቷል፤ ኢህአዴግ ለስራ አጥ ዜጎች የስራ ዕድል እፈጥራለሁ እያለ በአንፃሩ ግን የስራ ዕድል የሚፈጠርላቸው ዜጎች በአባልነት ላይ የተመረኮዘ ለምን ይሆናል? በታችኛው ህብረተሰብ አካባቢ በብልሹ አሰራር ውስጥ ገብተው ከፍተኛ ሙስና የሰሩና በህዝቡ የተገለሉ ሰዎች ተሸፍነው ወደ ላይ ሲወጡ ሹመት ይደረብላቸዋል ይህ ተገቢ ነወይ?” የሚሉ ጥያቄዎችም ተነስተዋል። የአዲስ አበባ የመሬት ወረራ ጉዳይም ሰፊ አጀንዳ የነበረ ሲሆን፣ ኢህአዴግ በሰላማዊና ጠንካራ ተቃዋሚዎች ላይ የያዘው አቋምም ትችት አዘል ጥያቄ አስነስቶበታል። የዛሬውን የፕላዝማ ውይይት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው መርተውታል። ትናንት ከሰአት በሁዋላ በነበረው የውይይት ጊዜ ደግሞ ” ኢህአዴግ ለሃገሪቱ ስጋት ብሎ ከለያቸው የፖለቲካ ጉዳዮች ውስጥ ዋነኛ ያላቸው የሃይማኖት አክራሪነት ወይም ጽንፈኝነት እና የመልካም አስተዳደር እጦት ቢሆኑም፣ የ ኑሮ ውድነቱ በስጋትነት ሊካተት ይገባል” የሚል አስተያየት ቀርቧል። የደመወዝ ጭማሪው አርኪ አለመሆኑና እንዳውም የበለጠ ህዝቡንና የመንግስት ሰራተኛውን ለችግር መዳረጉም በአባላቱ ተነስቷል። ሰልጣኞቹን በሚሰለጥኑበት ቦታ ጥያቄዎች ሲነሱ እዚያው በህዋሳቸው በሰልጣኞቹ እንዲመለስ በማሰብ በህዋስ ማደራጀት መጀመሩን፣ ሰልጣኞቹ የመድረኩን የፕሮፓጋንዳ ገለፃ ብዙ ትኩረት ሳይሰጡ የጥያቄና መልስ ክፍለ ጊዜ ሲደርስ ግን በንቃት ጥያቄ የሚያነሱ ሲሆን፣ አንዳንዳ ጥያቄዎችን ከውይይሩ ጋር ግንኙነት የላቸውም ወይም ጥያቄውን ወደ ኋላ ላይ ማንሳት ትችላላችሁ በሚል እንደሚታለፉ የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል። ዘግይቶ በደረሰን ዜና ደግሞ የግንቦት 7 ድርጅት አጀንዳ የነበረ ሲሆን በአንዳንድ አባላት ዘንድ ግንቦት 7 ከውጭ መንግስታት ጋር በማበር በሀገር አብዮት እንዲነሳ እየሰራ ነው ሲሉ ሌሎች አባላት ደግሞ ግንቦት 7 አሸባሪ ከተባለ ለምን የአሜሪካ መንግስት አሳልፎ አይሰጥም? እናንተ እንደምትሉት አሸባሪ ቢሆን ኖሮ ያስሩዋቸው ነበር ብለው ተከራክረዋል፡፡ አወያዮቹም ከአሸባሪዎች ጋር መገናኘት የለባችሁም፣በሀገር የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎች አብረው እየሰሩ እንደሆነ ለአባላቱ የገለጹ ሲሆን ንክኪ እንዳይኖራችሁ ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ በኢህአዴግ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው ግምገማ መነሻ፣ በቅርቡ ኢህአዴግ መዳከሙን የተመለከተ ግምገማ ከተደረሰ በሁዋላ ነው። ይህን ተከትሎ ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ፖሊሶች፣ የህግ ባለሙያዎች በመንግስት ፖሊሲ ዙሪያ ስልጠና ሲሰጥ ቆይቷል። በስልጠናው ላይ የተነሱትን ጥያቄዎች የኢህአዴግ አባላት እንዲመክቷቸው በሚል እየተሰጠ ያለው ስልጠና ያልተጠበቁ ጥያቄዎችን ማስነሳቱ፣ ከፍተኛ አመራሮችን ሳይቀር በእጅጉ ማስገረሙን ምንጮች አክለው ገልጸዋል። “እዚህ የምናደርገው ስብሰባ በኢሳት ይዘገባል ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ ? ” በሚል አመራሩ እየተነጋገረበት መሆኑንም ታውቋል። ብአዴንም መረጃዎች እየወጡ ተቸግረናል በሚል ትናንት በጀመረው ግምገማ ማንም ሰው ሞባይል ስልኮችን ይዞ እንዳይገባ ከልክሏል።

Saturday, 16 August 2014

“አሸባሪነት” በወያኔ አገዛዝ ሥር ባለችው ኢትዮጵያ

በአገራችን፣ በወያኔ አገዛዝ መደበኛ ትርጉማቸውን ከሳቱ በርካታ ቃላት መካከል “የሽብር ድርጊት“ እና ”አሸባሪ“ የሚሉት ግንባር ቀደሞቹ ናቸው። ሰፊ ተቀባይነት ያለው የአሸባሪ ትርጉም “የሽብር ድርጊቶችን የሚፈጽም ሰው ወይም ድርጅት” ማለት ነው። “የሽብር ድርጊቶች” የሚባሉት ደግሞ የተለመዱ ጥቃቶችን ሳይሆን የሀይማኖት፣ የፓለቲካ ወይም የርዕዮተዓለም ግብ ለማሳካት ሲባል በሰዎች ላይ ፍርሀትን ለማንገስ፤ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሱ አስከፊ ጥቃቶችን ነው። የሽብር ድርጊቶችን ሰላማዊውን ሕዝብ ጭዳ የሚያደርጉ በመሆኑ በጥብቅ ሊወገዙ ይገባል። ዓላማን በሽብር ድርጊቶች ማስፈፀም ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው። በወያኔ መዝገበ ቃላት ግን “ሽብርተኛ” እና “የሽብር ድርጊቶች” በዘፈቀደ የሚነገሩ ተራ ቃላት ሆነዋል። ስለአገራቸው እና ስለትውልድ የሚጨነቁ፤ ሀሳባቸው በነፃነት የሚያራምዱ፤ የወያኔን ፕሮፖጋንዳ እንደ በቀቀን የማይደግሙ ዜጎች “አሸባሪዎች” እየተባሉ ወደ እስር ቤቶች እየተወረወሩ ነው። ጋዜጠኞች፣ ጦማርተኞች፣ ፍጹም ሰላምተኛ አማኞች እና ሰላማዊ ፓለቲከኞች በሽብርተኞች ዝርዝር ውስጥ ቀዳሚውን ሥፍራ የያዙ ናቸው። በአንፃሩ ደግሞ እውነተኛው አሸባሪ ህወሓት፣ የመንግሥትን ሥልጣን ይዞ መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ማሸበሩን በስፋት ተያይዞታል። ህወሓት ዘረኛ ርዕዮተ ዓለሙን ለማስፈፀም ሲል ባለፉት ሠላሳ አምስት ዓመታት ውስጥ የፈፀማቸው የሽብር ድርጊቶች ተዘርዝረው አያልቁም። የህወሓት የሽብር ድርጊቶች ዓላማ የኢትዮጵያን ሕዝብ በፍርሀት አደንዝዞ መግዛት ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ “አሸባሪ” የሚለውን ቃል ራሱ በማሸበሪያ መሣሪያነት እያዋለው ነው። ይህ የውስጥም የውጭም ታዛቢዎችን የሚያሳስት በመሆኑ ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ ነው። “የፀረ-ሽብር አዋጅ” የሚባለው ህገ-አልባነትን ህጋዊ ያደረገው ሰነድ የመንደር ካድሬዎች ሳይቀሩ አንድን ሰው በሽብርተኝነት “ጠርጥረው” ማሳሰርና ማስደብደብ አስችሏቸዋል። የአስተሳሰብ ድህነት ያጠቃቸው የህወሓት ካድሬዎች ብቻ ሳይሆኑ ኃላፊነት የጎደላቸው ፓሊሶችም የፀረ-ሽብር ህጉን ጉልበታቸውን ማሳያ እና ተፎካካሪዎቻቸውን ማጥቂያ አድርገውታል። በፀረ-ሽብር ህጉ ተከስሰው ወህኒ የወረዱ ዜጎችን ያጤነ ማንኛውም ሰው ኢትዮጵያ አገራችን በዚህ ህግ ሰበብ ምርጥ ዜጎቿን እያጣች እንደሆነ ይገነዘባል። በሽብርተኝነት ለመጠርጠር የሚያበቁ ምክንያቶች እጅግ አሳዛኝ ናቸው። ለካድሬ ሰበካ እውነተኛነት ጥርጣሬውን የገለፀ አስተዋይ ሰው መሆን ብቻውን እንኳን በሽብርተነት ያስጠረጥራል። በዚህም ምክንያት ነው በእውቀትም በአስተሳሰብም የበሰሉ ዜጎቻን በአሸባሪነት የመፈረጅ እድላቸው ከፍተኛ የሆነው። የንቅናቄዓችን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ በርካታ የሀገራችን ምርጥ ዜጎች የዚህ የተዛነፈ ትርጓሜ ሰለባ ሆነዋል። ተስፋ የሚጣልባቸው በርካታ ወጣቶች በዚህ ህገ-ወጥ ህግ እና የተሳሳተ ትርጓሜ ምክንያት የወጣትነት እድሜዓቸውን በእስር ቤት እንዲያሳፉ ተገደዋል። ከዚያ የበዙት ደግሞ በቃሉ ተሸማቀው፤ በሚያስከፍለው ዋጋ ተሸብረው ራሳቸውን እንዲደብቁ ተደርገዋል። ለመሆኑ ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው ምርጥ ዜጓቿ በአሸባሪነት ስም ወህኒ እየተወረወሩ ሲሰቃዩ ምላሻችን ምን ሊሆን ይገባል? እስከመቼ አስተዋይ፣ አርቆ አሳቢና አመዛዛኝ የሆኑ መሪዎቻችንን ለወያኔ ፋሽቶች እየገበርን እንኖራለን? ሀገራችን ይህን ኪሳራ የመሸከም አቅም አላት? ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ወያኔን ለማስወገድ የተሻለ ነው ብሎ ያመነበት የትግል ስልት – ሁለገብ የትግል ስልት ነው። በዚህ የትግል ስልት መሠረት ሕዝባዊ ተቃውሞ፣ ሕዝባዊ እምቢተኝነት እና ሕዝባዊ አመጽ ተደጋግፈውና ተናበው መሄድ አለባቸው ብሎ ያምናል። ስለሆነም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በአመቸውና በሚያምንበት መንገድ ለትግሉ አስተዋጽኦ የማበርከት እድል አለው። በዚህም መሠረት ለሀገር፣ ለትውልድ ድህንነት ዋጋ ለመክፈል እና ለገዛ ራሳችን ህሊና ታማኝ ለመሆን በወያኔ “አሸባሪ” ለመባል መድፈር የትግላችን አንዱ አካል አድርገን መቁጠር ይኖርብናል። በወያኔ “አሸባሪ” መባል የሚያሸማቅቅ ሳይሆን የሚያኮራ፤ ለታላቅ ኃላፊነት እና ሕዝባዊ አደራ በእጩነት የሚያቀርብ መሆኑን በራሳችንም በማኅበረሰባችንም ውስጥ ማስረጽ ይኖርብናል። “አሸባሪ” የሚለው ቃል በወያኔ ተግባር መሠረት ሲተረጎም “ለሀገርና ለትውልድ ደህነት የሚጨነቅ ምርጥ ዜጋ“ ማለት እንደሆነ ማስተማር ይገባናል። ወያኔ ወደ ሕዝብ የሚወረውረውን ጦር መልሰን ወደ ራሱ መወርወር ይኖርብናል። ወያኔ አሸባሪነት ዜጎችን ለማጥቂያ እያዋለው መሆኑ ተረድተን እኛ በዚህ ስያሜ መሸማቀቅ ሳይሆን፣ መኩራትና መልሰን ወያኔን ማሸማቀቅ ይኖርብናል። በውጭ አገራት እየተስፋፋ የመጣው የወያኔ ሹማምንትን የማሸማቀቅ ዘመቻ በኢትዮጵያ ውስጥም መጀመር ይኖርበታል። ሕዝባዊ ተቃውሞ፣ ሕዝባዊ እምቢተኝነትና ሕዝባዊ አመጽ ሲቀናጁ ድላችንን ያፈጥናሉ። በወያኔ “አሸባሪ” መባል የመልካም ዜግነት ምስክርነት እንደሆነ በሙሉ ልባችን እንቀበል። ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Thursday, 14 August 2014

የአዲስ አበባ መስተዳድር በቤቶች ግንባታ ዙሪያ ለምርጫ እንዲደርስ በሚል አስቸኳይ ትእዛዝ ሰጠ

በ40 በ60 በሚባለው የቤቶች መርሃግብር የታቀፉ የዲያስፖራ አባላት ከቀጣዩዓመት ምርጫበፊት ቤት እንዲሰጣቸው የአዲስ አበባ መስተዳድር መመሪያመስጠቱ ታውቋል። ሆኖምየጠቅላላተመዝጋቢውንየቤትፍላጎትለመሸፈንበትንሹከ16 ዓመታትበላይጊዜን እንደሚወስድ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ የአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ኢንተር ፕራይዝ እስካሁን 13ሺህ 800 ቤቶችን በሰንጋተራ እና ቃሊቲ ክራውን ሆቴል በመሳሰሉ አካባቢዎች ላይ እየገነባ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ፣ እነዚህን ቤቶች እስከሚቀጥለው ዓመት አጋማሽ ድረስ ለዕድለኞች ለማስተላለፍ ታቅዷል። የአስተዳደሩ ምንጮች እንደገለጹት ቤቶቹ ከቀጣይ ዓመት ምርጫ በፊት ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው እንዲተላለፉ ከአስተዳደሩ መመሪያ ተሰጥቷል። ሆኖም ለ40 በ60 የቤቶች ፕሮግራም የተመዘገበው ጠቅላላ ሕዝብ ቁጥር 164 ሺህ 779 ያህልሲሆንአስተዳደሩግን በዓመትከ10 ሺህቤቶችበላይቤቶችን የመገንባት አቅም ባለመፍጠሩ የተመዘገቡትን ብቻ ለማዳረስከ16 ዓመታት በላይ ጊዜን እንደሚፈልግ የአስተዳደሩ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ ይህ ደግሞ ከዛሬ ነገ የመኖሪያ ቤት ባለቤት አስቆራጭ ዜና ነው ብለዋል፡፡ በ20/80 በተለምዶኮንዶሚኒየምፕሮግራምየምርጫ 97ን መቃረብ ታሳቢ አድርጎ ሲጀመርከ 350ሺ በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪ መኖሪያ ቤት እፈልጋለሁ ብሎ መመዝገቡን ያስታወሱትምንጮቹ ፣ ፕሮግራሙ 10 ዓመታት ያህል ቆይቶ መመለስ የቻለው ግን 100 ሺ በታች ቤት ፈላጊዎችን ጥያቄ ነው ብለዋል፡፡በዚህ መረጃ መሠረት የጠቅላላ ተመዝጋቢውን ፍላጎት ለሟሟላት ተጨማሪ ከ20 ዓመታት በላይ ጊዜ ንእንደሚወስድ አፈጻጸሙ በራሱ የሚናገርነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡ የአስተዳደሩ ምንጭ እንደሚሉት መንግሥት በአዲስ አበባበዓመት ለቤቶች ግንባታ ብቻ ከ2 እስከ 3 ቢሊየን ብር እያወጣ መሆኑን አስታውሰው ከዚህ በላይ ለማውጣት የፋይናንስ አቅም ችግር መኖሩን፣ገንዘቡ ቢገኝም በግንባታ አፈጻጸምበኩል የአቅም ችግር በመኖሩ በአጭር ጊዜ የመኖሪያ ቤት ፍላጎትን ለመመለስ የማይችልበት አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም እንደገለጹት ደግሞ ዲያስፖራው በፈለገበት አካባቢ ቤት ለመስራት ይችል ዘንድ ክልሎች መመሪያ እንዲያወጡ መታዘዙን ገልጸዋል። ሁሉም ክልሎች ተመሳሳይ የሆነ መመሪያ ባለማውጣታቸው ለዲያስፖራው ቤት ለማደል የታቀደው እቅድ የተፈለገውን ውጤት አለማምጣቱን ገልጸዋል። ይሁን እንጅ ኢሳት የአዲስ አበባን አዲሱን ካርታ ዝግጅት አስመልክቶ ከወራት በፊት በሰራው ዘገባ፣ የቤት ግንባታ መርሃግብሩ የተሰናከለው በአዲስ አበባ የቤት መስሪያ ባዶ ቦታ በመጥፋቱ ነው። ቀደም ብሎ የኦሮምያን ልዩ ዞኖች ወደ አዲስ አበባ በመጠቅለል የቤት መስሪያ ቦታዎችን ለማግኘት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ የኦሮምያ ክልል አንዳንድ ባለስልጣናትና አብዛኛው የኦሮሞ ተወላጅ በመቃወሙ እቅዱን በቀላሉ ተግባራዊ ማድረግ አልተቻለም። ዲያስፖራው ከአዲስ አበባ ውጭ ያሉ ቦታዎችን እንዲጠይቅ ለማግባባት ኢምባሲዎች የስራ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ለአባይ ግድብ በቦንድ ስም ገንዘብ በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ገንዘብ ለማሰባሰብ የታቀደው እቅድ አለመሳካቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምነዋል። ከፍተኛ ገንዘብ ይገኝበታል የተባለው የአሜሪካ የቦንድ ሽያጭ አምና ጭራሽ አልተካሄደም ብሎ መናገር እንደሚቻል ሚኒስትሩ ገልጸዋል። በሁሉም አገሮች ያለው የቦንድ ሽያጭ ደካማ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ ፣ ለድክምቱ ዝርዝር ምክንያቶችን አላቀረቡም። የዶ/ር ቴዎድሮስ ገለጻ፣ ኢሳት ከዚህ ቀደም የቦንድ ሽያጩ በውጭ አገር አለመሳካቱን ሲዘግብ የቆየውን ያረጋገጠ ሆኗል። በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ገንዘብ ለመሰብሰብ በገዢው ፓርቲ በኩል የሚዘጋጁትን ዝግጅቶች አጥብቆ ሲቃወም እንደነበር ይታወቃል። አቶ መለስ የአባይን ግድብ እቅድ ይፋ ሲያደርጉ በውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ 1 ቢሊዮን ዶላር ያዋጣል የሚል እምነት ነበራቸው፣ ይሁን እንጅ እስካሁን ባለው መረጃ በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ከ20 ሚሊዮን ዶላር በላይ ሊያዋጣ አልቻለም።

Sunday, 3 August 2014

በአንዋር መስጊድ ብጥብጥ ፖሊሶችም መሳተፋቸው ተገለጸ

-ኮማ ውስጥ ያሉ ተጎጂዎች ሁኔታ እስኪታወቅ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም. በመርካቶ አንዋር መስጊድና በአካባቢው ላይ በተፈጠረ ግጭትና ብጥብጥ፣ አራት የፖሊስ አባላት መሳተፋቸው በፍርድ ቤት ተገለጸ፡፡ ፖሊስ ለሦስተኛ ጊዜ ሐምሌ 24 ቀን 2006 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፖሊስ ኮሚሽን ጉዳዮች ምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ማስቻያ ችሎት 14 ተጠርጣሪዎችን ያቀረበ ሲሆን፣ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን እያጣራ መልቀቁን ገልጾ በችሎቱ የቀረቡት ተጠርጣሪዎች ላይ ለሚቀረው ተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ጠይቋል፡፡ ፖሊስ ተጨማሪ ጊዜ የፈለገበትን ምክንያት ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው አንድ ኢንስፔክተር፣ አንድ ምክትል ኢንስፔክተር፣ አንድ ምክትል ሳጂንና አንድ ኮንስታብል ግጭትና ብጥብጥ ከፈጠሩት ጋር በመተባበር ፀጥታ ለማስከበር በወጡ የሥራ ባልደረቦቻቸውና ሌሎች ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት በማድረስ መጠርጠራቸውን መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ ተጎጂዎቹ በጥቁር አንበሳና በፖሊስ ሆስፒታል ኮማ ውስጥ ስለሆኑ በመሆናቸው ቃል አለመቀበሉን ገልጿል፡፡ ተጎጂዎቹን አሁን ባሉበት ሁኔታ ማናገርና ቃል መቀበል ባለመቻሉ፣ በቀጣይ የሚሻላቸው ከሆነ የእነሱን ቃል ለመቀበልና ተጨማሪ የምስክሮችን ቃል የመቀበል ሥራ እንደሚቀረው ለፍርድ ቤት አስረድቷል፡፡ ሌሎች በግጭቱና ብጥብጡ የተሳተፉና የሚይዛቸው ተጠርጣሪዎች እንዳሉት ፖሊስ አስረድቶ፣ በሆስፒታል ውስጥ በሞትና በሕይወት መካከል ያሉት ተጎጂዎች ሁኔታ ሳይለይለት ለተጠርጣሪዎቹ ዋስትና ሊፈቀድ እንደማይገባ አመልክቷል፡፡ የተጎዱት ሰዎች ቢሞቱ ተጠርጣሪዎቹ የሚቀርብባቸው ክስ የመግደል ወንጀል ክስ ሊሆን ስለሚችል፣ በወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 63 መሠረት ዋስትና ሊከለከሉ እንደሚችሉ መርማሪ ፖሊስ በመጠቆም የዋስትና ጥያቄውን ተቃውሟል፡፡ በግጭቱ ወቅት አንድ ተጠርጣሪ ሆዱ አካባቢ በጥይት ተመትቶ የነበረ ሲሆን፣ ቀዶ ሕክምና የተደረገለት ቢሆንም ጥይቱ ከሆዱ ሊወጣ ባይችልም፣ በወቅቱ በግጭቱ በነበረው ተሳትፎ ምክንያት ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡ ግለሰቡ በጥይት እንዴት ሊመታ እንደቻለና ማን እንደመታው ፖሊስ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ለፍርድ ቤት ተናግሯል፡፡ የአዲስ ጉዳይ ፎቶ ጋዜጠኛ አዚዛ መሐመድና የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወ/ት ወይንሸት ሞላ፣ ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ከተጠየቀባቸው ተጠርጣሪዎች መካከል ናቸው፡፡ ፖሊስ ስለነሱ የወንጀል ተሳትፎ ለፍርድ ቤቱ ሲያስረዳ፣ በግጭቱ ወቅት ሕዝቡ ሲሸሽ ‹‹ወንድ ሆነህ የት ነው የምትሸሸው?›› በማለትና ወደ ግጭቱ እንዲመለሱ በማድረግ፣ ግጭቱን ሲያባብሱ እንደነበር የሚያሳይ በቪዲዮ የተደገፈ ማስረጃ እንዳለው በማስረዳት ዋስትናቸውን ተቃውሟል፡፡ እነሱ አደፋፍረው ባባባሱት ግጭት የተጎዱና በሆስፒታል ኮማ ውስጥ ያሉ ተጎጂዎች ጉዳይ እልባት ሳያገኝ ዋስትና እንዳይፈቀድላቸው ፖሊስ አመልክቷል፡፡ የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታልና ፖሊስ ሆስፒታል፣ ተጎጂዎቹ ያሉበትን ደረጃ የሚገልጽ ማስረጃ እንዲልኩ በችሎት በመንገርና ፖሊስ ቀረኝ የሚለውን ምርመራ በአጭር ቀናት እንዲያጠናቅቅ በማዘዝ ለሐምሌ 29 ቀን 2006 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Saturday, 19 July 2014

U.S. State Department deeply concerned about charges on Zone 9 Bloggers

Africa: Zone 9 Bloggers Charged by Ethiopian Court for Terrorism 07/18/2014 06:08 PM EDT Zone 9 Bloggers Charged by Ethiopian Court for Terrorism Press Statement Jen Psaki Department Spokesperson Washington, DC July 18, 2014 The United States is deeply concerned by the Ethiopian Federal High Court’s July 18 decision to press charges against six bloggers and three independent journalists under the Anti-Terrorism Proclamation. We urge the Ethiopian government to ensure that the trial is fair, transparent, and in compliance with Ethiopia’s constitutional guarantees and international human rights obligations. We also urge the Ethiopian government to ensure that the trial is open to public observation and free of political influence. We reiterate Secretary Kerry’s May 1 call on Ethiopia to refrain from using anti-terrorism laws as a mechanism to curb the free exchange of ideas. The use of the Anti-Terrorism Proclamation in previous cases against journalists, activists, and opposition political figures raises serious questions and concerns about the intent of the law, and about the sanctity of Ethiopians’ constitutionally guaranteed rights to freedom of the press and freedom of expression. Freedom of expression and freedom of the press are fundamental elections of a democratic society. The arrest of journalists and bloggers, and their prosecution under terrorism laws, has a chilling effect on the media and all Ethiopians’ right to freedom of expression. The Office of Website Management, Bureau of Public Affairs, manages this site as a portal for information from the U.S. State Department. External links to other Internet sites should not be construed as an endorsement of the views or privacy policies contained therein.

Sunday, 13 July 2014

አብርሃ ደስታ – ከትግራይ አዲስ አበባ ማዕከላዊ እስር ቤት ገባ

(ኢ.ኤም.ኤፍ) በትግራይ የሚደረጉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በመጻፍ እና በመተቸት ይታወቃል – አብርሃ ደስታ። በትጋይ የሚገኙት ሰዎች የአብርሃ ደስታን ሃሳብ – በሃሳብ ማሸነፍ ሲያቅታችው አስረውታል። ከታሰረ በኋላ ወዴት እንደተወሰደ ለማወቅ አልተቻለም ነበር። ዛሬ ያገኘነው መረጃ ግን አብርሃ ደስታ ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ማዕከላዊ እስር ቤት ተዛውሮ እንደሚገኝ ለማወቅ ችለናል።\ ይህ በ እንዲህ እንዳለ፤ በሚቀጥለው ሳምንት እሁድ በራያ እና አዘቦ የሚደረገውን የአረና ፓርቲ ስብሰባ፤ “ዘመቻ አብርሃ ደስታ” ማለታቸውውን አሳውቀዋል። አረና የትግራይ ፓርቲ እንደገለጸው ከሆነ፤ ዓረና-መድረክ እሁድ 06 / 11 / 2006 ዓ/ም በራያ ዓዘቦ ወረዳ ሞኾኒ ከተማ “ዘመቻ ኣብረሃ ደስታ” የሚል መፈክር ያለበት ህዝባዊ ስብሰባ ያካሂዳል። ዓረና-መድረክ ፖሊሲው፣ ስትራተጂውና ኣማራጭ ሃሳቡ ከራያ ዓዘቦና ኣከባቢው ህዝብ ለመወያየትና ለማስተዋወቅ ህዝባዊ ስብሰባ ጠርተዋል። ዓረና-መድረክ የሃገራችን የፍትህ፣ ዲሞክራሲ፣ መልካም ኣስተዳደር፣ ሁላቀፍ ልማት፣ የሚድያ ነፃነት፣ ወዘተ ተግዳረቶች በማቅረብ ለነዚህ ችግሮች መፍትሄ ኣማራጭ ሃሳቦች በማቅረብ ወደፊት ሃገራችን የምትመራበት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ምን መምሰል እንዳለበት፣ ሰለማዊ የስልጣን ሽግግር እውን የሚሆንበት ኣግባብ፣ ባለፈው 17 የትጥቅ ትግል የተከፈለ መስዋእትነትና በኣሁኑ ሰዓት የተገኘው ለውጥ ምን እንደሚመስል ከራያ ህዝ ጋብ እንወያያለን።

Friday, 11 July 2014

አብርሀ ደስታ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ ፍርድ ቤት ቀረበ

ካሳለፍነው ማክሰኞ ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በመንግስት ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር ውለው በማዕከላዊ በእስር ላይ የሚገኙት ወጣቱ ፖለቲከኛ ሀብታሙ አያሌው የአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ፣ ወጣቱ ፖለቲከኛ ዳንኤል ሺበሺ የአንድነት ፓርቲ ድርጅት ጉዳይ ም/ሀላፊ ወጣቱ መምህርና ፖለቲከኛ አብርሃ ደስታ የአረና ፓርቲ አመራር በትላንትው ዕለት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ቢጠበቅም ከምሽቱ 12፡16 ላይ የአረና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አብርሃ ደስታ ብቻውን በ3 ፌደራል ፖሊሶች ታጅቦ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡ ማንም ወደ ፍርድ ቤቱ እንዳይገባ በፀጥታ ሀይሎችና ሲቪል በለበሱ የደህንነት ሀይሎች በመከልከሉ ምክንያት ስለቀረበበት ክስ ለማወቅ ያደረግነው ጥረት ሊሳካልን አልቻለም፡፡ በወጣቱ ፖለቲከኛ አብርሃ ደስታ ፊት ላይ ይታይ የነበረው ጉስቁልና ከፍተኛ የሀይል እርምጃዎች ሳይወሰድበት እንዳልቀረ አመላካች ነበር፡፡ ይህንን ዜና እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ የአንድነትና ሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ፍርድ ቤት አልቀረቡም፡፡

Sunday, 6 July 2014

Ambo University fires one of the detained Zone 9 bloggers, lecturer Zelalem

The letter, dated July 02, 2014, posted on Ambo University’s staff notice board states that Zelalem Kibert Beza, lecturer at the University and a member of the blogging collective, Zone 9, has been officially fired from his post as he “had not responded to two previous calls witten within the past couple of months to report about his absence from the University.” Zelalem was detained on the April 25, 2014 along with eight other bloggers and journalists in Addis Abeba accused of various anti-government plots. He has not been yet charged. Police has been holding Zelalem for the past three months without officially charging him but bringing him to court and seeking further time to conduct investigation. Signed by Dr. Lakew Wondimu Abachri, the Academic and Research Deputy President of Ambo University, the letter (attached below) also orders Zelalem to return all materials and works he has been handling back to the University. The letter has been copied to various administrative offices and departments of the University.

Wednesday, 2 July 2014

የኢትዮጵያ ህዝብ በዝምታ እየተቀበላቸው የሚገኙት በደሎች

ያሳዝናል! በአመት ከ70 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ህፃናት በማደጎነት ሲሸጡ እያየን፣ እየሰማን፤ ከ45 ሺህ በላይ ሴቶቻችን ለሳውዲ አረቢያ በቤት ሰራተኝነት ሲቸረቸሩና፤ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ዜጎቻችን በተመሳሳይ መልኩ ለሌሎች አረብ ሃገራት በሃራጭ ሲሸጡ እያየን፣ እየሰማን፤ ሴቶቻችን በየ አረብ ሃገሩ ለመስማት እጅግ በሚያዳግት ሁኔታ አሰቃቂ በደሎች ባደባባይ ሲፈፀምባቸው እያየን፣ እየሰማን፤ አያሌ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ህይወታቸውን ለማትረፍና ለማሻሻል ወደተለያዩ ሃገራት ተሰደው ስቃይ ውስጥ እንደሚገኙ እያየን፣ እየሰማን፤ ከዚህም በላይ ደግሞ ይህ ሁሉ በደል በዜጎች ላይ ሲፈፀም ቢያንስ ተቃውሞውን ሊያሰማ ፈፅሞ ፍላጎት የሌለው፤ ይባስ ብሎ በደሉን በተቃወሙ ዜጎች ላይ ከበዳዮቹ ሃገራት ጋር በማበር ንፁሃን ዜጎችን የሚደበድብ፣ የሚያስር ጭካኝ ስርዓት በጫንቃችን ተሸክመን፤ አንጀታችን እያረረ፣ ልባችን በሃዘን እየተጎዳ፣ ሞራላችን በውድቀት እየተሰበረ፣ አንገታችንን ደፍተን በዝምታ እየኖርን እንገኛለን። ሁላችንም እንደምናቀው የኬኒያ፣ የሱዳን፣ የጅቡቲና፣ ሌሎች የጎረቤት ሃገራት በወያኔ በደል ምክንያት ሳይወዱ ተገደው ህይወታቸውን ለማዳን ከሃገራቸው በተሰደዱ ኢትዮጵያውያን ላይ በተደጋጋሚ አፈና እየፈፀሙ ይገኛሉ። በቅርቡ በኬኒያ መንግስት ታፍኖ ለወያኔ ከተሰጠ በኋላ ህይወቱ እስክታልፍ ድረስ ለአመታት በወያኔ እስር ቤት በተሰቃየው በወንድማችን ወጣት ተስፋሁን ጨመዳ ላይ የተፈፀመውን አሳዛኝ በደልና በኦብነግ አመራር አባላት ላይ የተደረገው አፈና፤ በደቡብ ሱዳን በአቶ ኦኬሎ አኩአይና ሌሎች የጋምቤላ ንቅናቄ አባላት ላይ በተመሳሳይ መልኩ የተደረገው አፈና ያለምንም ተጨባጭ እርምጃ በዝምታ ታልፈዋል። ዛሬ ደግሞ የየመን መንግስት በአሳዛኝ ሁኔታ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ማገቱ በመገናኛ ብዙሃን ተነግሯል። በዜጎቻችን ላይ እየደረሱ ለሚገኙት አሰቃቂ በደሎች በዋነኝነት ተጠያቂው የወያኔ መንግስት ቢሆንም፤ በስደት የሚኖሩ ዜጎቻችን ላይ ከወያኔ መንግስት ጋር በመተባበር በተደጋጋሚ አፈና እየፈፀሙና አጋልጠው እየሰጡ የሚገኙ የጎረቤት ሃገራት ወደፊት በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ተጠያቂ እንደሚሆኑ ምንም ጥርጥር የለኝም። ነገር ግን ወገኖቼ ይህ አፈና እስከመቼ ይቀጥላል!? ዜጎች ጭቆናን በመቃወማቸው ብቻ በስደት ከሚደርስባቸው ስቃይ በላይ ለምን በየ ጎረቤት ሃገሩ ይታፈናሉ!? እኛ ኢትዮጵያውያን እስከመቼ እየተናቅን እንኖራለን!? ጎበዝ ዝምታውና መነጣጠሉ ይብቃ! የሚደርስብንን አፈና ለማስቆምና ራሳችንን ለመከላከል ሁላችንም በአንድነት ጫና መፍጠርና ማስገደድ ግድ ስለሚለን፤ በምንችለው ሁሉ መረባረብና መተባበር ይኖርብናል እላለሁ። አፈናው ይብቃ!

Thursday, 26 June 2014

በዓለም አቀፉ የሠላም ደረጃ ኢትዮጵያ ከ162 ሀገራት 139ኛ ደረጃን ያዘች

በየዓመቱ የየሀገራትን የሠላም ይዞታ በማጥናት ደረጃን የሚያወጣው ኢኒስቲትዩት ፎር ኢኮኖሚክስ ኤንድ ፒስ የተባለ ዓለም አቀፍ ተቋም የ2014 የዓለም ሀገራት የሰላም ደረጃ ከሰሞኑ የለቀቀ ሲሆን በዚህም ጥናቱ ከ162 ሀገራት ኢትዮጵያን በ139ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧል። ተቋሙ የአንድን ሀገር የሠላም ደረጃ ለማውጣት በርካታ የስኬት ማሳያዎች (Indicators) ግምት ውስጥ ያስገባል። ለዚሁ ልኬት ግብዓትነት ከሚውሉት መመዘኛዎች መካከል የውስጥና የውጭ ግጭቶች፣ አንድ ሀገር ከጎሬበቶቹ ጋር ያለው የግንኙነት ሁኔታ፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ የሽብር ተጋላጭነት፣ የወንጀል መስፋፋት እንዲሁም በእያንዳንድ አንድ መቶ ሺ ሰው በአንድ ሀገር ውስጥ ያለውን የእስረኛ ብዛትንም በመውሰድ ደረጃውን ለማውጣት በልኬትነት ይጠቀማል። ከዚህም በተጨማሪ ከአጠቃላይ ብሄራዊው ምርት አንፃር ለሚሊተሪው ዘርፍ የሚወጣውንም የገንዘብ መጠን ታሳቢ ያደርጋል። እነዚህንና ሌሎች ተጨማሪ ግብዓቶችን በማካተት ነው መረጃዎቹ ተተንትነው ደረጃ ወደ ማውጣቱ ስራ የሚካሄደው። የየሀገራቱ ደረጃ ወጥቶ በድርጅቱ ድረገፅ እንዲሁም በዘ ኢኮኖሚስት መፅሄት ለህትመት የሚበቃ ሲሆን የዘንድሮውም ሪፖርት የ162 ሀገራትን መረጃ በመውሰድ ሰፊ ትንታኔ ከሰጠ በኋላ ኢትዮጵያ በ139ኛ ደረጃ አስቀምጧል። ተቋሙ በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ሰላምም ሆነ ጦርነት የሌለበት ሁኔታ በመግለፅም በይደር የተቀመጠ ጉዳይ መሆኑንም አመልክቷል። ኢትዮጵያ ከፀጥታ ጋር በተያያዘም ከፍተኛ ገንዘብ የምታወጣ መሆኑን መረጃው ጨምሮ አመልክቷል። በዚህ የሀገራት የሰላም ደረጃ አይስላንድ የመጀመሪያውን ደረጃ በመያዝ በዓለም እጅግ ሰላም የሰፈነባት ሀገር ተብላለች። ዴንማርክ ሁለተኛ ስትሆን ኦስትሪያ የሶስተኝነትን ደረጃን ይዛለች። ከ162ቱ ሀገራት 162ኛን ደረጃ በመያዝ በደረጃው ግርጌ ላይ የተቀመጠችው ሶርያ ናት። አፍጋስታን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ኢራቅ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎም በደረጃው የመጨረሻ ግርጌ ላይ የተቀመጡ ሀገራት ናቸው። ግብፅ 148ኛ ደረጃን ይዛለች። ዓለም አቀፍ የሀገራት የሠላም ስኬት ደረጃ (Global peace Index) በኢንስቲትዩት ፎር ኢኮኖሚክስ ኤንድ ፒስ ተቋም በየዓመቱ ይፋ የሚሆን ሲሆን መረጃውን በማሰባሰቡ በኩል በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት ሰፊ ትብብርና ተሳትፎን ያደርጋሉ። ከዓለም አቀፍ ተቋማቱ መካከል የተለያዩ የተባበሩት መንግስታት አካላትም ይገኙበታል። እንደ ኮፊ አናን እና ሊቀጳጳስ ዴዝሞንድ ቱቱን የመሳሰሉና በተለያዩ ጊዜያት ሀገራትን ከመሩ በኋላ የስልጣን ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ መሪዎችም የሙያ አስተዋፅዖችን የሚያበረክቱበት ተቋም ነው። ተቋሙ የሀገራትን የሠላም ደረጃ የሚያወጣው 22 መስፈርቶችን አስቀምጦ በዚያ ልኬት መሰረት ነው።

Friday, 20 June 2014

ቀና ብለን የምንሄድበት ጊዜ አየመጣ ነው! ጎበዝ ተነሳ!

ጉጅሌዎቹ አይገባቸውም እንጂ የኢትዮጵያ ከተሞችና ገጠሮች የለውጥን ደመና ኣርግዘዋል። ወንዞችም ተራሮችም የለውጥ ማዕበል ማቆብቆቡን አያበሰሩ ናቸው። የቀደሙት ገዢዎች መረጃ የሚያገኙት እረኛ ምን ይላል ብለዉ እየጠየቁ ነበር። የአሁኖቹ አገር አጥፊ ገዢዎች ምሳሌ ያደረጉት ካድሬዎቻቸውን ብቻ ሆነ እንጂ ዛሬም የአገራችን እረኞች የለውጥን መምጣት በሚያምር ቅላጽያቸው አያንጎራጎሩ እንዲህ አያሉን ነው፣ የሀገሬ ጉብል የሰማውን እንጃ የጎንደሬው ጉብል የሰማውን እንጃ ከብቱን አየሸጠ ገዛ ኣሉ ጠብመንጃ። የወለጋው ጉብል የሰማውን እንጃ ቡናውን ሻሽጦ ገዛ ኣሉ ጠብመንጃ። መልእክቱ ግልጽ ነው። የኢትዮጵያ ወጣቶች አገራቸውን በክቡር ደማቸው ሊታደጓት ቆርጠው በመነሳት ወያኔን በማስወገድ የሀገራቸው ባለቤት ለመሆንና ያልተከፋፈለች ውብ ኢትዮጵያን ማየትን ለማረጋገጥ ጥርጊያውን መጀመራቸው ነው። ላለፉት ፵ አመታት አምባገነኖች ባደረሱብን ጭቆና እና እንግልት የተነሳ የራሳችን የሆነ መንግሥት ሳይኖረን አንገታችንን ደፍተን ጀግኖቻችንን ስንገብር ኖረናል። በተለይም ባለፉት ፪፫ አመታት ጉጅሌዎቹ በአራት ኪሎ ከነገብን ጀምሮ በአንድ ላይ አንዳንቆም በማድረግና እና አርስ በራሳችን በማጋጨት ሲያባሉን ኖረዋል። ዛሬ ሁኔታዎች ተለውጠዋል፤ በውጭም በአገር ውስጥም ለውጥ አየታየ ነው። የእንቅስቃሴው ማእበል አይሎ እየመጣ ነው። ዛሬ ሁሉም የዴሞክራሲ ሀይሎች ማለት በሚቻል ደረጃ በሁለት ነገሮች ላይ ስምምነት አለ፣ ፩. ተቃዋሚዎች በግል ከሚያደርጉት ትግል ይልቅ በጋራ የመሰባሰብን አስፈላጊነት ተረድትው መሰባሰብ መጀመራቸው ፪. በአንድ ላይ መሰባሰብ ካልቻሉም እርስ በራስ ላለመጠላለፍ መስማማት መቻላቸውና አስፈላጊ ሆኖ በተገኘ ግዜ ሁሉ መረዳዳት መጀመራቸውና በግልም ከወያኔ ጋር የሚደረገውን ትግል ማፋፋም የቻሉበት ሁኔታ አየታየ መሆኑ የሕዝብ ወገኖችን እያስደሰተ ይገኛል። በአገር ቤት የሚገኙ የዴሞክራሲ ኃይሎችም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሕዝቡ ከፍርሀት ተላቆ ለመብቱ አንዲነሳ የሚያደርጓቸው አንቅስቃሴዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከሩ መጥተዋል። ለዚህም በቅርቡ በአዲስ ኣበባ መድረክ፣ ኣንድነትና ሰማያዊ ፓርቲዎች የጠሯቸው ሰልፎች ይበል የሚያስብሉ ናቸው። ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ በዚሀ ኣጋጣሚ ለዴሞክራሲና ለነፃነት ታጋዮች ሁሉ ያለውን አክብሮትና ኣድናቆት ይገልጻል። በሌላም በተለያዩ አቅጣጫዎች ወያኔን በኣመጽ ለመፋለም የወሰኑ ኃይሎች ከመቼውም ጊዜ በላይ ወያኔን ለመፋለም ቆርጠው በጋራ ክንዳቸውን ኣቀናጅተው ለመፋለም አየተዘጋጁ ያሉበት ሁኔታ አበራታች ነው። እነዚህ ኃይሎች አዳዲስ የነጻነት ታጋይ አርበኞችን በተከታታይ በማስመረቅ ያሉ መሆናቸውና ከዚህም በተጨማሪ ከመላው የአገሪቱ አካባቢዎች ወጣቶች በገፍ ትግሉን እየተቀላቀሉ መሆኑን ስንሰማ ልባችን በደስታ ይሞላል። በወያኔ ጉያ ውስጥ ያሉ የሕዝብ ወገኖች ደግሞ የቻሉትን በውስጥ ሆነው መቃብሩን እይቆፈሩለት ሲሆን፣ ያልቻሉትም የወያኔን ሚስጢር ይዘው በመውጣት የሕዝብ ወገንተኝነታቸውን አየገለጹ ይገኛሉ። ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ለመላው ሕዝባችንና በተለይም ለወጣቱ ትውልድ በተደጋጋሚ አንደሚለው የሀገራችን ባለቤት ለመሆን የምናደርገውን ትግል ተቀላቀሉ!!! መቀላቀል ያልቻላችሁም በኣካባቢያችሁ ከምታምኗቸው ወገኖቻችሁ ጋር ተሰባሰቡ፣ በህዋስ ተደራጁ። ግንቦት 7 በዚህ ትግል የዳር ተመልካች ሳይሆን መሪ እንድትሆኑ ኣገራዊ ጥሪውን ያቀርባል። ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Saturday, 14 June 2014

በአዲስ አበባ የመሬት አስተዳደር ቢሮና በሌሎች ተቋማት ላይ ፓርላማ ዕርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ

ዋና የሕዝብ ዕንባ ጠባቂዋ ወ/ሮ ፎዚያ አሜን የአሥር ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ሰኔ 3 ቀን 2006 ዓ.ም. ሲያቀርቡ፣ ተቋሙ በምርምራ ውጤት ላይ ተመሥርቶ የተሠሩ ጥፋቶች እንዲታረሙና በደል የደረሰባቸው መፍትሔ እንዲያገኙ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የሥራ ኃላፊዎች ከክልሎች፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር፣ አብዛኞቹ ፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች የሚቀርቡባቸውን አቤቱታዎች እንዲያርሙና የተበደሉ ደግሞ መፍትሔ እንዲያገኙ ማድረግ መቻሉን በበጐ ጐኑ አንስተዋል፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ የመንግሥት አስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በምርምራ ላይ ተመሥርቶ የሚያቀርብላቸውን የመፍትሔ ሐሳብ ተግባራዊ ካለማድረጋቸውም በላይ፣ የማይተገብሩበትን ምክንያት እንኳን አይገልጹም ብለዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የሕዝብ ተዋካዮች ምክር ቤት የሕግና የአስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በልዩ ሁኔታ እንዲከታተላቸው ዝርዝር ሪፖርት እንደተላከለትና ኮሚቴውም በአሁኑ ወቅት አስፈላጊውን ሥራ በመሥራት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡ በዝርዝር ሪፖርት ለቋሚ ኮሚቴው ከተላለፉ ተቋማት መካከል የአዲስ አበባ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስ ኤጀንሲ፣ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአራዳ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ይገኙበታል፡፡ ከአዲስ አበባ ውጪ የተጠቀሱት ተቋማት የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት፣ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የእንስሳት ሰብልና ገጠር ልማት ቢሮ፣ የሐረር ክልል ፍትሕና ፀጥታ ጉዳይ ቢሮ ናቸው፡፡ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በአሥር ወራት ጊዜ ውስጥ 2,948 የአቤቱታ መዝገቦች የቀረቡለት መሆኑን የገለጹት ዋና እንባ ጠባቂ ወ/ሮ ፎዚያ፣ መዝገቦቹ በአጠቃላይ 17,682 አቤቱታ አቅራቢዎችን ይመለከታሉ ብለዋል፡፡

Tuesday, 10 June 2014

“ስለ ….. ሲባል ምርጫ ይቅር” …. ትግሉም ይቁም ወይ? ግርማ ሠይፉ ማሩ

“ስለ …. ሲባል ምርጫ ይቅር” በሚል እንድ ፅሁፍ ፋክት ላይ ወጥቶ አንብቤ ለምን? ብዬ ልፅፍ አስቤ ተውኩት፡ ፡ ምክንያቱም በፋክት መፅሔት ላይ አምደኞች የሃሣብ ፍጭት ማድረግ የተለመደ ቢሆንም ሰሞኑን ግን የበዛ ይመስላል ከሚል ነበር፡፡ ይህ አንድ ዘርፈ ብሉ ጥሩ ጎን አለው፡፡ አንዱ አምደኞቹ ከአንድ ፋብሪካ የወጡ ሳሙና ዓይነት ያለመሆናቸውን ያሳያል፡፡ሌላው የፋክት መንፈስ ብለው ለሚቃዡትም ሆነ፤ ከመሬት ተነስተው ለሚፈርጁት የሚያስተላልፈው መልዕክት አለው፡፡ ጉዳቱ ደግሞ በሳምንት አንዴ ብቅ ለምትል መፅሄት የተወሰነ ሃሳብ በተወሰኑ ሰዎች የሚቧቀሱባት ከሆነች ደግሞ አንባቢን አማራጭ እንዳያሳጣ የሚል ፍርሃት ስለአለኝ፡፡ ይህ ሁሉ ዳር ዳርታ እኔም ተውኩት ወዳልኩት የሃሣብ ፍጭት ለመቀላቀል ሰበብ ፈልጌ ብቻ አይደለም፡፡ በቅርቡ “ሰለ … ሲባል ምርጫ ይቅርብን” በሚል በወዳጄ ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ ያቀረበውን ሃሳብ ባልቀበለውም በፋክት ላይ ሳይሆን በጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት እናደርጋለን ብዬ እያሰብኩ ሳለ በፌስ ቡክ የውስጥ መዘገቢያ እንዲሁም በግል የሚያገኙን ሰዎች ምርጫ እንዳትወዳደሩ የሚል አንዳንዱ ምክር አንድ አንዱ ደግሞ ትዕዛዝ መሰል መልዕክቶች በብዛት ይደርሱኝ ጀምረዋል፡፡ ውሳኔው ልከም ይሁን አይሁን የምርጫ ጉዳይ የሚወሰነው በፓርቲ መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት የግል አስተያየቴን መስጠት እፈልጋለሁ፡፡ ለዚህም ነው “ሰለ … ሲባል ምርጫ ይቅር” ከተባለ እኔም እንደቅድመ ሁኔታ ትግሉም ይቁም ወይ? በሚል ጥያቄ የጀመርኩት፡፡ በእኔ እምነት ምርጫ መወዳድር ያለመወዳደር የሚባል አማራጭ የለም፡፡ የአንድ ፓርቲ ስራ ምርጫ መወዳድር ነው፡፡ የሰው ልጅ ሞት እንዳለ እያወቀ ሞትን ረስቶ በህይወት እንደሚኖረው ማለት ነው፡፡ ለፓርቲዎች ያለመወዳደር የሚባል ነገር እንዳለ ረስተው ለምርጫ ውድድር መዘጋጀት ዋናው ስራቸው መሆን አለበት፡፡ ፓርቲዎች ምርጫ ላለመወዳደር የሚያበቃ ነገር እንዳይኖር ተግተው መስራትን ትተው፤ ላለመወዳድር ሰበብ የሚፈልጉ ከሆነ እንደ አሸዋ የበዛ ሰበብ ማቅረብ አይገድም፡፡ ከዚህ ሰበብ ውስጥ ግን አንድም ተሰፋ አይገኝም፡፡ ምርጫውም የሰነፍ ነው የሚሆነው እንጂ ባስቸገሪ ሁኔታ ጀግና ለመሆን ለሚታትር ታጋይ የሚመጥን አይደለም፡፡ በሀገራቸን ኢትዮጵያ ለምርጫ የእኩል መወዳደሪያ ሰፍራ ሳይኖር ምርጫ መወደዳር አስቸጋሪ እንደሆነ መረዳት ለማንም የሚገድ አይደለም፡፡ ትግል የሚባለው ነገርም የመጣው ይህ አስቸጋሪ ሁኔታ በመኖሩ ነው፡፡ በአሜሪካን ወይም በሌሎች በዲሞክራሲ በዳበሩ አገሮች የሚደረግ የፖለቲካ ተሳትፎ ትግል አይባልም፡፡ ታጋዮች ማድረግ ያለባቸው ታዲያ ይህን አስቸጋሪ ሁኔታ ለማስወገድ የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመክፈል የሚያስፈልገውን ማድረግ ነው፡፡ ክቡር የሆነውን የስው ልጅ ህይወት ከማጥፋትና ንብረት ከማውደም በመለስ ማለቴ ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች ምን ምን ሊሆኑ ይችላሉ ቢባል በምርጫ ሂደት ውስጥ ወሳኝ ናቸው ብዬ የማምናቸውን ዋና ዋና ጉዳዮች በማንሳት ለማብራራት እሞክራለሁ፡፡ የዕጩ ተወዳዳሪ ዝግጅት አንዱ መስረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ በምርጫ ለመወዳድር የወሰነ አንድ ፓርቲ በምንም ዓይነት መልኩ ርጫው ሲደርስ ዕጩ ለማዘጋጀት ደፋ ቀና የሚል ከሆነ ለመሸነፍ መዋጮ ማድረጉን ማመን አለበት፡፡ ለምርጫ ውድድር የሚመለመሉ ጩዎች በሁሉም መልክ በተለይ ከገዢው ፓርቲና መንግሰት ሊደርስባቸው የሚችለውን ጫና ለመቋቋም ዝግጁ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡ በዋነኝነት እነዚህ ዕጩዎች እንደ ገዢው ፓርቲ ወጪያቸው በፓርቲ የሚሸፈን ባለመሆኑ ተገቢውን ፋይናንስ ከደጋፊዎቻቸው ለማግኘት የሚያስችል ስልት መቀየስ የግድ ይላቸዋል፡፡ ውድድሩ በእኩል ሁኔታ ላይ እንዳልሆነ ከሚያስረዱት ሁኔታዎች አንዱ ይህ ነው፡፡ የገዢው ፓርቲ ዕጩዎች በዚህ ጉዳይ ቅንጣት ሃሣብ የለባቸውም፡፡ ይህ ጉዳይ የምርጫ ትግል ከሚደረግባቸው አንዱ መሆኑን ተረድተን መፍትሔ መሻት የእኛ እንጂ አንድ አንድ ተቃዋሚ ፓርቲ ነን የሚሉ ፓርቲዎች እንደሚሉት ለዚህ መፍትሔ ኢህአዴግ/መንግሰት የገንዘብ ድጋፍ ያድርግልን የሚለው አይደለም፡፡ በሀገራችን ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግና መንግሰት የማይለያዩ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ከሚባለው በላይ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ስለዚህ መንግሰት ድጋፍ ያድርግልን ሲባል ኢህአዴግ ያድርግ እንደማለት እየሆነ ነው፡፡ ኢህአዴግ ደግሞ ይህን አድርጎ ለመሸነፍ ዝግጁ አይደለም ሰለዚህ ታግለን ተወዳዳሪ ፓርቲዎች በፍትሃዊነት የሚታዩበት ስርዓት እንዲመጣ በትግል ውስጥ ያለን መሆኑን መረዳት የግድ ይለናል፡፡ ይህ ከባድ ከሆነ አማራጩ ትግሉ ይቅር ወይ? የሚለው ነው፡፡ ከዕጩ ዝግጅት በኋላ በዋነኝነት የሚያስፈልገው በየደረጃው ያሉ ታዛቢዎችን ማዘጋጀት ነው፡፡ የታዛቢዎች ዝግጅት በሁለት ይከፈላል፡፡ የመጀመሪያው በምርጫ ቦርድ አስተባባሪነት የሚዘጋጁት ታዛቢዎች ማለትም “የህዝብ ታዛቢ” የሚባሉት ናቸው፡፡ እነዚህ ታዛቢዎች በሚመረጡበት ጊዜ ኢህአዴግ ቀደም ብሎ በአንደ-ለአምስት፣ በጥቃቅንና አነስተኛ፣ በወጣትና ሴቶች ፎረም ያደራጃቸውን በተለይም የፋይናንስ አቅማቸው ደከም ያሉ የአካባቢ ነዋሪዎችን በማዘጋጀት በህዝብ እንደተመረጡ በማስመሰል ይመድባቸዋል፡፡ ይህ ሲፈፀም ተወዳዳሪ ፓርቲዎች በዝምታ በማለፍ አንድ ደጋፊያቸው እንኳን እንዲገባ ሳያደርጉ ያልፋሉ፡፡ ትግሉን በትክክል ተረድተን ከሆነ በየምርጫ ጣቢያዎች እነዚህ ታዛቢዎች ሲመደቡ እኛም ደጋፊዎቻችን እንዲኖሩ ለማድረግ መስራት ይኖርብናል፡፡ ልክ ነው ይህን ለማድረግ ኢህአዴግ የዘረጋው ዓይነት የመንግሰት መረብና ድጋፍ አናገኝም፡፡ ይህ ነው የውድድር ሜዳው ልክ አይደለም የሚያስብለው እና ትግል የሚያስፈለገው፡፡ ይህን ለመለወጥ ትግል ማድረግ ካለብን የማይቻል አይደለም፡፡ ሁሉተኛው በዕጩ ተወዳዳሪዎች በራሳቸው የሚመደቡ ታዛቢዎች ናቸው፡፡ እነዚህን ታዛቢዎች የመምረጥ መብት የዕጩ ተወዳዳሪው ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ያለው ፈታኝ ነገር ታዛቢዎችን ማስፈራራት፣ በገንዘብ መደለል ሲበዛም አፍኖ መውሰድ የመሳሰሉት ናቸው፡፡ እነዚህ በሙሉ የትግሉን አስፈላጊነት የሚያሳዩ እንጂ እንዲህ ግርማ ሠይፉ ማሩ ከሆነማ ምርጫ ይቅር የሚያስብሉ አይመስለኝም፡፡ የማይፈራ፣ በገንዘብ የማይደለል ታፍኖ ለሚደርስበት ፈተና የተዘጋጀ ታዛቢ ማዘጋጅት ትግሉ የሚጠይቀው መሰዋዕትነት ነው፡፡ ለዚህ የሚመጥን ታዛቢ ማዘጋጀት የዕጩ ተወዳዳሪዎችና የፓርቲዎች ሲሆን ይህን በታዛቢዎች ላይ የሚፈፀም ህገወጥ ድርጊት ማሰቀየር ነው በሀገራችን ፖለቲካ ከሌሎች ዲሞክራሲ ከሰፈነባቸው ሀገሮች ለየት የሚያደርገው እና ትግል ያሰፈለገው፡፡ ምርጫቻን የቱ ነው? ታግለን እንቀይር ወይስ ኢህአዴግ በቃኝ እስኪል እንጠብቅ ነው፡፡ የመራጮች ምዝገባ ዘወትር ተገቢ ትኩረት የማይሰጠው በተወዳዳሪ ፓርቲዎች በኩል ነው፡፡ በ1997 ምርጫ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ቅስቀሳ ተደርጎ ብዙ መራጭ የተመዘገበ ቢሆንም መምረጥ የሚገባቸው ያልተመዘገቡና ባለመመዝገባቸው የቆጫቻ እንደነበሩ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡ የ1997 በተለየ ሁኔታ ትተን በሌሎች ምርጫዎች ተቃዋሚዎች እንዲመርጡን የምንፈልገው ኢህአዴግ ጎትጉቶ ባስመዘገባቸው መራጮች ነው፡፡ ሁሉም ማወቅ ያለበት ኢህአዴግ በመራጭነት እንዲመዘገቡ ቤት ለቤት እየሄደ የሚቀሰቅሰው ባለው መረጃ መሰረት ደጋፊዎች ብሎ ያመነባቸውን ወይም በቀላሉ ደጋፊ ላደርጋቸው እችላለሁ ብሎ የሚገምታቸውን ነው፡፡ በተለይ በትምህርት ደረጃ ዝቅተኛ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች እናቶች ከአባለት ቀጥለው ለምዝገባ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጣቸው ናቸው፡፡ ፓርቲዎች በምርጫ ትርጉም ያለው ለውጥ ማየት የምንፈልግ ከሆነ የመራጭ ምዝገባ ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ ደጋፊዎች እንዲመዘገቡ መቀስቀስ፣ ማበረታት እንዲሁም የመመዝገብን ጥቅም ማስተማር ይኖርብናል፡፡ ፓርቲዎች ላለመወዳደር ቢወስኑ እንኳን ደጋፊዎቻቸው ወደ ምርጫ ጣቢያ እንዳይሄዱ ማድረግ በምርጫው ላይ ትርጉም ያለው መልዕክት ያስተላልፋል፡፡ ያለመወዳደር ምርጫ ከሆነ ማለቴ ነው፡፡ መራጮችን ለማሰመዝገብ በምናደርገው እንቅስቃሴ በአብዛኛው ችግር ባይኖርም መዝጋቢ የለም፣ መታወቂያ አልታደሰም፣ እሰከ ዛሬ የት ነበርክ፣ በቀበሌ ተሳትፎ የለህም፣ የመሳሰሉት የሚጠበቁ የማደናቀፊያ መንገዶች ናቸው፡፡ ይህን ሊቋቋም የሚችል መራጭ እንዲኖር ቅስቀሳ ማድረግ ከትግሉ አንዱ አካል ነው፡፡ መራጮች በወኔ እንዲመዘገቡ ካደረግናቸው ከተመዘገቡ በኋላ መራጭ ብቻ ሳይሆን ቀስቃሽም በመሆን የምርጫ ምዕዳሩ እንዲስተካከል ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡ ህዝብ የተሳተፈበት አፈናን እንቢ የማለት ተግባር ደግሞ በጥቂት ካድሬዎች ቁጥጥር ስር እንዲውል የተውነውን ምርጫ በትግላችን የእኛም ይሆናል ማለት፡፡ ለመምረጥ ያልተመዘገበ መራጫ የምርጫ ምዕዳር ለማስፋት አላፊነት ያለበት አይመስለውም፡፡ ትክክልም ነው፡፡ የምርጫ ምዕዳር የማስፋት አላፊነት ያለበት ዜጋ መፍጠር የትግሉ አካል ነው፡፡ ቆጠራ ሳይጠናቀቅ ካደረ አብረን ስንጠብቅ እናድራለን የሚል መራጭ ማዘጋጀት የግድ ይላል፡፡ ምርጫ 97 ትዝ አይላችሁም፡፡ መራጮች የሰጡትን ድምፅ፣ ታዛቢ ተከታትሎ ቆጥሮ፣ ደምሮ የተቀበለውን፣ ምርጫ ቦርድ ሊለውጠው አይችልም ባይባልም ለመለወጥ የሚገጥመው ፈተና ከባድ ይሆናል፡፡ እዚህ ላይ እንደመፃፍ ቀላል እንዳልሆነ ይገባኛል፣ ኢህአዴግ ሲጨንቀው በታጣቂ ኮሮጆ እንደሚገለብጥ ዘንግቼው አይደለም፡፡ ይህን ድርጊቱን በተደራጀ መከላከል የትግሉ አንድ አካል እንደሆነ አፅዕኖት ለመስጠት ነው፡፡ ፓርቲዎች አሁን ባለው ደረጃ ይህን ለማድረግ ሙሉ ለሙሉ አልተዘጋጀንም የሚሉ ከሆነ ከምርጫ ለመውጣት ሳይሆን በተደራጁበት ልክ ለመወዳደር መዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሀሉም ቦታ ለመሆን ሲከጀል አንድም ቦታ ያለመሆን የሚመጣው በዚህ ምክንያት ነው፡፡ በታዛቢዎች የተፈረመ የምርጫ ውጤትን በምርጫ ቦርድ በኩል በሚፈፀም ሸፍጥ ወይም በጉልበት መሣሪያ ጭምር ተደርጎ በሚደረግ ንጥቂያ ሌላ ፈተና ላይ የሚወድቀው አካል የፍትህ ስርዓቱ ነው፡፡ የተደራጀ መረጃ ይዘን የፍትህ ስርዓቱን መሞገትም አንዱ የትግል አካል እንደሆነ መዘንጋት የለበትም፡፡ ይህን ሁሉ አድርገን ኢህአዴግ እነዚህን የህዝብ ድምፆች ገፍቶ ማነኛውንም ዓይነት ጉልበት ለመጠቀም ቢወስን ህዝብ የተሳተፈበት ስለሚሆን መዘዙ ብዙ ነው፡፡ ምርጫን ተከትሎ ለሚመጣ አብዮትም ጠሪ የሚሆነው የዚህ ዓይነት ድርጊት ነው፡፡ በምርጫ መሳተፍ ሂደት ውስጥ ህዝብ ካልተሳተፈ የተወሰኑ ሰዎች የሚያደርጉት መፍጨርጨር ሰለሚሆኑ ህዝቡ ድምፁ እንዲከበር የሚያደርገው ግፊት እምብዛም ነው፡፡ እነደከዚህ ቀደሙ ኢህአዴግ ወትውቶ ያስመዘገባቸው ሰዎች ለምን አልመረጡንም ብለን መጠየቅ ተገቢ አይደለም፡፡ በሚስጥር ድምፅ ሰጥተውን ቢሆን እንኳ በይፋ ድምፃችን ይከበር ሊሉ ይችላሉ ብሎ መጠበቅ የዋህ መሆን ነው፡፡ በሚስጥር የካዱትን በአደባባይ እንዲያረጋግጡ መጠየቅ ነው የሚሆነው፡፡ በዚህ ደረጃ ሳንዘጋጅ ቀርተን ምዕዳሩ ጠቧል ብለን “ሰለ …ሲባል ምርጫው ቢቀር” የምንል ከሆነ ኢህአዴግ ደስተኛ ነው፡፡ በግልፅ የሚሰብከውን አውራ ፓርቲ ስርዓት ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ ኢህአዴግ ምዕዳሩን በህዝብ ተሳትፎ ሳናስገድደው ያሰፋዋል ብለን የምንጠብቅ ከሆነ በቅርቡ የሚሆን ስለአልሆነ የትግል ስልታችንን መፈተሸ ሊኖርብን ይገባል፡፡ አንዱ አማራጭ አንድ ሺ ትንታግ ታዛቢ ከማዘጋጀት፣ አንድ ሺ ተኳሽ ተዋጊ ሀይል ማዘጋጅት ሊሆን ይችላል፡፡ እንግዲህ ዘመኑ የሚዋጀውን፣ ለሰው ልጅ ከፍተኛ ክብር የሚሰጠውን፣ በወጪ አንፃርም አዋጭ ሊሆን የሚችለውን የትግል ስልት መምረጥ በፓርቲ ውስጥ ያሉ ስትራቴጂሰቶች ሃላፊነት ነው፡፡ በሃላፊነት ሰሜት የሚወሰን፡፡ እርግጠኛ ነኝ “ስለ …. ሲባል ምርጫው ቢቀር” የሚለው ሃሳብ የቀረበው በባርነት እንቀጥል በሚል ወይም የኢህአዴግ አውራ ፓርቲ ፍልስፍና ተስማምቶናል የሚል አይደለም፡፡ በእኔ አረዳድ ሌላ አማራጭ የትግል ስልት እንመልከት የሚል መሆን አለበት፡፡ ለጊዜው የምርጫው መንገድ ገና ብዙ ያልተሄደበት መንገድ ስለሆነ ተሰፋ መቁረጥ ያለብን አይመስለኝም፡፡ ምርጫ መሳተፍ የሰላማዊ ትግል ማሳኪያ አንዱ መንገድ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ይህ ማለት ግን በፍፁም የምርጫ ሰሞን ደርሶ በሚፈጠር ሆይ ሆይታ ውስጥ ውጤት ለማግኘት መከጀል አይደለም፡፡ ከላይ በአጭሩ ለማስቀመጥ እንደሞከርኩት በሁሉም የምርጫ ደረጃዎች በንቃት በመሳተፍ እና ህዝቡን በማሳተፍ ነው፡፡ ቸር ይግጠመን