Thursday, 31 October 2013
በወያኔ ሎሌነት ከመማቀቅ አንድ ቀን ነፃ ሆኖ መኖር ይሻላል
ከሚያዩ ዜጎች ውስጥ ራሱ ሥርአቱ ለራሱ መገልገያ የሰበሰባቸውና ያሰማራቸው ዜጎች ይገኙበታል። ከእጅ ወደ አፍ እንኳን ለማትሆን ደመዎዝ በሰራዊቱ ውስጥ በተራ ወታደርነትና በበታች ሹማምንት የሲኦልና የጉስቅልና ኖሮ እንደሚኖሩ እናውቃለን።
በየዞኑና በየወረዳው በካድሬነት ወያኔ ለገላጋይነት ያሰማራቸው ሰራተኞችና የድርጅቱ አባሎች ከህዝቡ የጥላቻ ሰለባነት ባልተናነሰ በኑሮአቸው ለራሳቸውም ለቤተሰቦቻቸውም ሳያልፍላቸው እንደሚኖሩ እናውቃለን።
ይልቁንስ የወያኔው የአመራር ጉጅሌ ነገ የት እንደሚያደርሳቸው በማያውቁት ጨለማ ውስጥ ነው የሚዳክሩት ሚስጥርና የዳጎሰ ጥቅም ከነሱ ዘንድ አይደርስም። በቀድሞ ጊዜ የነበሩት የባላባት ሎሌዎች እንኳን ክብር አላቸው።
በዚህ ላይ ሁሉም አስተማማኝ ሎሌ መሆኑን ወያኔ ለማረጋገጫ የሚጠቀምበት ግምገማ አለ። የወያኔ ግምገማ የበታች አባላትና ደጋፊዎቹን በማስፈራራት ያላቋረጠ ድጋፍ እንዲሰጡት የሚያደርግበት በመሰረቱ ከውሻ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የማይለይ ተቋም ነው። የትምህርት እድል የስራ እድገትና የደመወዝ ጭማሪ የወያኔው ጉጅሌ የባርነት መደለያዎች ናቸው።
ግንቦት 7 ከጥቂት ከመንገዳቸው እያወጡ ህዝብ ከሚያሰቃዩት የወያኔ ታዛዥ ሎሌዎች በቀር የሀገርና የወገን ጠላት ናቸው ብሎ አያምንም። ትግላችን ለነሱም ነጻነት ነው። እነዚህ ወገኖቻችን ባገኙት አጋጣሚና እድል ሁሉ ትግሉን ያግዛሉ ብሎም ያምናል። የሚያግዙም አሉ። እርግጥ ነው ባሽከርነት ኑሮ የተንገፈገፉ የሰራዊቱ አባላትና ለህሊናቸው ክብር ያላቸው በርካታ የስርአቱ አገልጋዮች ትግላችንን እየተቀላቀሉ ነው።
ግንቦት 7 ንቅናቄ ዛሬም እንደሁሌው ለነዚህ ወገኖች ኑ ተቀላቀሉን የሚል ጥሪውን ያቀርባል። ሁላችንም ከነክብራችን ሆነን ሰዎችን ሳይሆን ውዲቱን ሀገራችንና ህዝባችንን በፈቃደኝነት በነጻነት የምናገለግልበት ጊዜ እየቀረበ ነው፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
Tuesday, 29 October 2013
የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ አስተዳደር ከተማሪዎች አመጽ ጀርባ ኢሳት እና ሌሎች ሀይሎች እንዳሉበት ገለጸ
ኢሳት ዜና :- ተማሪዎች የርሃብ አድማ በማድረግ ላይ ሲሆኑ ዩኒቨርስቲው ትክክለኛነቱን አረጋግጦዋል፡፡
የተማሪዎች አመጽ የተነሳው መንግስት ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አዲስ የአለባበስ ፤ የአመጋገብ እና የአምልኮ ስርዓት ህግ ማውጣቱን ተከትሎ ነው። ” ተማሪዎች እምነታችሁ ተው ፣ ማተባችሁን በጥሱ” ተብለናል ይላሉ።
በ2004 እና በ2005 ዓም ተማሪዎች ህጉን እንዲተገብሩ ሙከራ ቢደረግም ተማሪዎች ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ህጉ ሳይተገበር ቀይቷል ሲሉ የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ንጉሴ ምትኩ ከክልል አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይት ተናግረዋል።
ተማሪዎች ለዘጋቢያችን እንደነገሩት ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ለመመገብ በሀገሪቱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የተፈቀደው የቀን በጀት 12 ብር ብቻ ነው፡፡ በደብረ ማርቆስ ከተማ 12 ብር አንድ ሻይ እና ዳቦ የመግዛት አቅም የሚሉት ተማሪዎች፣ መንግስት እየመገበን ሳይሆን የርሃብ አድማ ውስጥ እያስገባን ነው ይላሉ።
የተማሪዎችን ጥያቄ ትክክለኛነት የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ንጉሴ ምትኩ ያረጋግጣሉ፡፡ ተማሪዎች የሚቀርብላቸው የምግብ አቅርቦት የበጀት አነስተኛነት ከፍተኛ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ከመንግስት ፈቃድ ውጭ በሚልየን የሚቆጠር የበጀት ድጎማ እያደረግን ተማሪዎችን ለመመገብ ጥረት አድረገናል የሚሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ሁኖም ግን መንግስት በገመገመውና በተቸው መሰረት የዳቦ ግራማቸው ከ80 ወደ 45 ግራም ዝቅ እንዲል መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ተማሪዎች በ45 ግራም ዳቦ እና ከዚያ ባነሰ ሁኔታ ቁርሳቸውን እንዲመገቡ ተገደዋል፡፡ የዳቦው መጠን ግን ተማሪዎች አውጥተው ባስመዘኑት መሰረት ከ25- 30 ግራም የሚመዝን ሲሆን አንድ ጉራሻ የመሆን አቅም ብቻ ነው ያለው፡፡
በምግብ እጥረት ትምህርት በተጀመረ በወር ጊዜ ውስጥ 32 ተማሪዎች ታመው ወደ ህክምና ተቛማት መወሰዳቸውን ከጤና ጥበቃ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ንጉሴ ምትኩ የተማሪዎች አመጽ የአመጋገብ እና የአምልኮ ስርዓት የወጣውን ህግ ለማስተግበር በተካሄደው አሰገዳጅ ህግ እና በምግብ ማነስ ምክንያት በተነሳ ርሃብ ላይ ብቻ የተመሰረት ሳይሆን ኢሳት እና ሌሎች ሃይሎች ያደራጁት ሊሆን እንደሚችል፣ ኢሳት ዘገባውን ያቀረበበትን ሰአት አይቶ መናገር እንደሚቻል ገልጸዋል።
በአመጹ ሙሉ በሙሉ የስድስት ህንፃዎች መስታውቶች ወድመዋል፤ ሶስት የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አምቡላንሶችን ጨምሮ ከአገልግሎት ውጭ ሁነዋል፡፡
አመጹን የፌደራል ፖሊስ ለመቆጣጠር በወሰደው እርምጃ በተማሪዎች ላይ ድብደባ ፈጽሟል፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎች ለአመጹ ድጋፍ በመስጠታቸው ዬዩኒቨርስቲው መሪዎች ወቀሳ ሰንዝረዋል፡፡ነዋሪዎች በበኩላቸው ተማሪዎች እየራባቸው ሲወድቁ መመልከታቸውን ለደብረ ማርቆሱ ወኪላችን ነግረውታል፡፡ ተማሪዎቹ በተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርበው መልስ በማጣታቸው በአጸፋው የወሰዱት እርምጃ አስተማሪ መሆኑንም ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
ESAT
“ከ40 ግድብ አንድ የቀይ ባሕር ወደብ!
“ከ40 ግድብ አንድ የቀይ ባሕር ወደብ!”የኢትዮሚዲያ ድረገጽ የወቅቱ መፈክር ነው።ከመፈክሩ ጋር ወይም በመፈክሩ ላይ ምንም ችግር የለብኝም።ይልቁንም ወያኔ ከሌሎች ክፉ ነገሮች በተጨማሪ ወደባችንን አስበልቶ በምድር ብቻ ተቀርቅበን የቀረን አገር ስላደረገን እስከ ዛሬ ድረስ ከሚንገበገቡት ኢትዮጲያውያኖች አንዱ ነኝ።የባሕር በር ባለቤትነታችን በእኔ እድሜ እንኳ ባይመለስ ቢያንስ የባሕር በር እንድናጣ ባደረጉን ዋና ዋና ከሃዲዎች ላይ በአገር ክህደት ወንጀል ክስ ሲመሰረት በሕይወት ዘመኔ ለማየት ከፍተኛ ጉጉት አለኝ።በነገራችን ላይ በዚህ ክስ በቀንደኛነት እንዲካተቱ ከምፈልጋቸው ሰዎች ውስጥ አንዱ መንግስቱ ኃይለማሪያም ወልዴ ነው።ስለምን?በዋናነት የተበላነው እሱ የ”አብዮታዊ ጦር ጠቅላይ አዛዥ”በነበረ ጊዜ ነውና።
ከላይ የጠቀስኩትን የኢትዮሚዲያን ወቅታዊ መፈክር ተንትርሶ አንድ ራሱን ጋሻው አባተ ብሎ የሚጠራ አንባቢ ከፕሪቶሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ በጻፈው ደብዳቤ ኢትዮሚዲያን አስተማማኝ የመረጃ ምንጭ ብሎ ካሞካሸና እነተስፋዬ ገብረአብን (ገብረ እባብ–ጋሻው እንዳሰቀመጠው) ጭምብላቸውን ገሽልጠሕ ስላጋለጥክልን እናመሰግናሃለን ገለመሌ ካለ በኋላ፤ ግን “ወደባችንንም አጥተን ግድብ አይኑራችሁ ነው ወይ የምትለው?” ብሎ መፈክሩ ችግር እንዳለበት በሻዕቢያዊ መሰሪነት ይሁን ወይም ስለ”ልማት” በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፕሮፓጋንዳ ሆዱ እንደተነፋ “ልማታዊ”ደንቆሮ ይሁን የመሰለውን ብሏል።
“Remove Assab! What? Reader vs Ethiomedia”በሚል ርዕስ ድረገጹ የለበደውን ፅሁፍ ይመልከቱ።
የኢትዮሚዲያ ዋና አዘጋጅ ለአስተያዬት ሰጪው “ጋሻው” ከሰጠው ምላሽ ውስጥ አንዳንዶቹ ነጥቦች ትኩረቴን በመሳብ ሌላ ቦታ ያነበብኩትን እንዲሁም በሕይወት ዘመኔ ያስተዋልኩትን እንዳስታውስ ስላደረጉኝ ይህን ለመጫር ተነሳሁ።ኢትዮሚዲያ በመፈክሩ ላይ የጸና አቋም እንዳለውና መፈክሩም በድረገጹ አናት ላይ ጎልቶ መታየቱን እንደሚቀጥል ካተተ በኋላ “በህዋሃት ውስጥ እውነተኛ ስልጣን በትግራይ ልጆች ሳይሆን እንደ መለስ ዜናዊ፣ስብሃት ነጋ ወዘተ በመሳሰሉ የለየላቸው ኤርትራውያን ቅጥረኞች እጅ”እንደነበረና ከሻዕቢያ ጋር የነበረውን መሞዳሞድ የተቃወሙ አንዳንድ የህዋሃት አባላት ምናልባትም እንደዋና አዘጋጁ አገላለጽ አንድምታ “ንጹህ የትግራይ ልጆች”በ”ለየላቸው ኤርትራዊያኖች”እጅ ተገድለዋል፤ወይም ተገልለዋል።
ትልቁ ችግሬ እዚህ ጋር ነው።ማነው ንጹሕ የትግራይ ልጅ? ማነው ንጹሕ የኤርትራ ልጅ?ሁለቱም ቡድኖች ወይም ከሁለቱም ክፍለሃገሮች ተወላጅ ነን የሚሉ የዚያን ጊዜ ልሂቃን በጎሳ ወይም በክፍለሃገር ጠባብ ስሜት ተከታትለው በመነሳትና በመደጋገፍ ጎሳን ወይም ክፍለሃገርን ብቻ “ነፃ” ሊያወጡ ነው የተነሱት እንጂ የኢትዮጲያን ሕዝብ በማስተባበር በኢትዮጲያ የግፍ ስርዓት እንዲቀር አልታገሉም።እነሱ የጀመሩትና የሰበኩት የክህደትና የጎሳ በሽታ ዛሬ ስር ሰዶ ከዘር ወይም መንደር ነፃ አውጪነት በላይ ማሰብ በኢትዮጲያ “ፖለቲካ” እጅግ አዳጋች ሆኗል።በበኩሌ ለኢትዮጲያ ባህር በር ማጣት ከሻዕቢያ እኩል ወያኔን እንዲሁም ላይ እንደጠቀስኩት የደርጉን ቁንጮ መንግስቱን ኃ/ማሪያምንም ጭምር በኃላፊነት እይዛለሁ።በእኔ መጽሃፍ በተለይ በዚያን ጊዜ በጎሳ “ነፃ አውጪነት”የተሰባሰቡት ሁሉ በአገር ክህደት የሚፈረጁ ናቸው።በተቀር ትግሪኛ ተናጋሪ ወገኖቻችንን በተመለከተ አንዱ የአገራችን ክፍል በፋሺስት ጥልያን ተቆርሶ ስለተወሰደብን ግማሾቹ ከኛ ጋር ሲቀሩ ሌሎቹ ከመረብ ወንዝ ወዲያ ማዶ በፈረንጅ ባላንጣ እጅ በመክረማቸውና በዚህና በሌላ ውሉ በደንብ ባልለየ ምክንያት እርስ በርስ ከሚናናቁ በቀር በመካከላቸው በደግም ሆነ በክፉ ብዙ ልዩነት በበኩሌ አይታየኝም።
በትግራይና በኤርትራ የሚገኙ ትግሪኛ ተናጋሪዎችን አንድ መሆንና ግራ የሚያጋባ ስር የሰደደ መናናቅ እና መጠላላት በአምባሳደር ዘውዴ ረታ ‘በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት የኤርትራ ጉዳይ ‘መፅሃፍ ላይ በገጽ 376-377 ላይ የሰፈረው የተድላ ባይሩና የወልደአብ ወልደማሪያም የከረረ ንግግር አመላካች ነው።ከብዙ በጥቂቱ ልጥቀሰው።
“አንድ ጊዜ በአስመራና በምፅዋ መካከል በሚገኘው “ቤተ ጊዮርጊስ”በተባለ ሥፍራ፤ጥቂቶች ያገር ፍቅር ማህበር መሪዎችና አባሎች ተሰብሰበው ሲወያዩ፣ተድላና ወልደአብ የተለዋወጧቸው ቃላቶች የሁለቱን ሰዎች በሀሳብ መራራቅ ብቻ ሳይሆን፣መጠላላታችውንም በትክክል ያሳያል።እንደተለመደው ወልደአብ ወልደማሪያም፣ኤርትራ ከኢትዮጲያ ጋር የምትቀላቀለው በሕግ በተደነገገ ውል መሆን አለበት፣የሚሉትን ሀሳብ እየደጋገሙ ይናገራሉ።የአንድነት ማህበር ዋና ጸሐፊ ደግሞ፣ተለያየተው የኖሩ እናትና ልጆች ብዙ እፍዳ ደርሶባቸው፣ከብዙ ዓመታት በኋላ ሲገናኙ ምን ውል ያስፈልጋቸዋል?በማለት ለማስረዳት ሲሞክሩ፣ወልደአብ ፊታቸውን አጥቁረው ለማዳመጥ የማይጥማቸው መሆኑን ያሳያሉ።በዚህ ጊዜ ተድላ ግልፍ ይላቸውና፣ኧረ ለመሆኑ መሠረተትውልድዎ የት ነው?ብለው ይጠይቋቸዋል።ትውልዴ አክሱም አጠገብ ከምትገኝ “ዓዲ ክልተ”ከምትባል ቀበሌ ነው ብለው፣ወልደአብ ይመልሳሉ።አቶ ተድላ ቀጠል ያደርጉና፤ትውልድዎ አክሱም ከሆነ፣ታዲያ የኤርትራ ጉዳይ ምን ይመለከትዎታል?ይሏቸዋል።ወልደአብ በገነፈለ ስሜት “—–እንኳንእኔአክሱምአገሬ፤በኩረሎሚየሚሸተውትውልዴቀርቶ፤ከናይጄሪያየመጣጀዓሊ፣ከየመንየመጣጀቦሊ፣
በኤርትራኖሬአለሁብሎ፣ስለኤርትራእድልለመናገርችሎየለምወይ?—ብለው መለሱላቸው።”
ወልደአብ ወልደማሪያም የመጀመሪያውና አንጋፋው የኤርትራ ግንጠላ አራማጅ እንደሚሉት “ንጹሕ”የአክሱም ተወላጅ ከሆኑ ኢትዮጲያን ያለ ባህር በር ባስቀረው የአገር ክህደት ወንጀል ላይ ከመረብ ወዲያ ማዶ ብቻ ተወለዱ የምንላቸውን “የለየላቸውን”የኤርትራ ልጆች ብቻ ለመወንጀል አይመችም።የጉዳዩ ውስብስብነት ሰለሞን ዴሬሳ እንዳለው የጦርነትና የፍልሰት ታሪክ ባጥለቀለቃት ኢትዮጲያ ውስጥ “የጠራሁ አማራ፤የጠራሁ ኦሮሞ፤የጠራሁ ትግሬ ማለት ጥጋብ ነው”ሲል የተናገረውንም ያስታውሰናል።ያውም ሰማይን በማሽቀንጠር እግዜሩን ካራቀብን የበቅሎ እርግጫ የባሰና አሁን በቀድሞ ኢትዮጲያውኖች ወይም በኤርትራውያኖች ላይ መዓት እንዳመጣው አይነት ሌላ መዓት የሚያስከትል ጥጋብ።
የመዋዠቅ መብት
የኢትዮሚዲያን የወቅቱን መፈክር ሳነሳ እስከ ቅርብ ጊዜ የነበረው የቀድሞ መፈክሩ ትክዝ አለኝ።“ህዋሃትሊታደስ አይችልም።ልክ እንደ አፓርታይድ መፍረስ ነው ያለበት።“የሚል ነበር።ታዲያ በቅርቡ ኢትዮሚዲያ ከዚህ መፈክሩ በተጻራሪ ሁኔታ ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ ደብረፅዮን የመሳሰሉትን አይነት ሰዎች የህዋሃት አዳሽ አድርጎ በማቅረብ ወያኔዊው አገዛዝ የመታደስ ተስፋ እንዳለው በርዕሰ አንቀፅ መልክ በማስቀመጥ ያሳየው የአቋም መዋዠቅ አግራሞትን ፈጥሮም እንደነበር ትዝ ይለኛል።
ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው እጅግ አድርጎ መርገምት የተጠናወተው የኢትዮጲያ “ፖለቲካ” እንዲህ ያለ መዋዠቅ ቢያስከትል ሊያስገርመንም ሊያናድደንም እንደማይገባ፤ይልቁንም ኢትዮጲያ የተባለችውን መሰረታችንን እስካለቀቅን ድረስ በዚያው መሰረት ላይ ሆነን በተስፋ እና በተስፋ መቁረጥ መካከል ብንዋዥቅ ሊበረታታ እንደሚገባ፤መዋዠቃችንም ተስፋ ባደረግን ጊዜ እንደ ስዬ፣ብርሃኑ፤ነጋሶ፤ልደቱ፤እስክንድር፤ዳዊት ወዘተ የመሳሰሉ ግለሰቦችንም ጭምር እስከማምለክ ወይም ሰማይ ድረስ እስከ መቆለል ሊወስድን እንደሚችል፤ ተስፋ ስናጣ ደግሞ እርስ በርስም ሊያዘረጣጥንም እንደሚችልና ይህም በኛ ብቻ የሚታይ ሳይሆን በሌሎችም አገር ሕዝቦች ላይ የሚታይ መሆኑን በማወቅ የ”መዋዠቅ መብታችንን”ተጥቅመን ከስህተታችን ትምህርት እየወሰድን መቀጠል እንችላለን።ዋናው ቁም ነገር ግን መረጃ በመስጠት ተግባር ላይ ተሰማርተናል የምንል ሰዎች ከመዋዠቃችን በፊት–ምንም እንኳ ሰዎች እንደመሆናችን ባንዳንድ ጉዳይ እኛም ከመዋዠቅ ባናመልጥም—በጥንቃቄ ማሰብና መመርመር ይጠበቅብናል።ከዚህ አንጻር ኢትዮሚዲያ ልክ ህዋሃት ሊታደስ አይችልም ባለበት አንደበቱ በህዋሃቱ ውስጥ ጥርሳቸውን የነቀሉና ሌላ ሕይወት የማያውቁ ሰዎችን ከመለስ ሞት በኋላ ሊያድሱን ይችላሉ እንዳለው አይነት መዋዠቅ ነገ ተነስቶ ወደብ ባይኖረንም ግድብ ይበቃናል እንደማይል ተስፋ አለኝ።
እኔም ዋዠቁ መሰለኝ። መሰረታችን ኢትዮጲያ እስከሆነች ድረስ በኢትዮጲያ ጉዳይ የመዋዠቅ መብት የማይጠበቅበት ምን ምክንያት አለ?ቅንነቱ እስካለ ድረስ ዋዥቀን ዋዥቀን ረግተን መቆማችን አይቀር።
Monday, 28 October 2013
Norway: Bergen streets in the fight against torture
We demonstrate in order to put pressure on the Norwegian government and the international community, so they can put pressure on the regime in Ethiopia , says EBSS Tesema to BA.
He explains that many of them are asylum seekers from the region of Oromia in Ethiopia , where the systematic injustice taking place.
WHIPPED AND HUNG
Opposition politicians , journalists and regime critics are subjected to systematic torture at a police station in Addis Ababa , according to a Human Rights Watch report that was presented last week.
The police station is located in the heart of the capital Addis Abbeba in Oromia region .
Torture methods used include blow to the body with hard objects and flogging . Prisoners are also hung from the ceiling in very painful positions, writes Aftenposten.
Merciless
Ethiopia’s ruling party , Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front ( EPRDF ) , has ruled the country for over 20 years. Following the disputed elections in 2005 , the authorities have turned down hard on the opposition.
Anti -terror laws since 2009 have been used to imprison both journalists and dissidents .
It is these conditions Ethiopians in Bergen will have an end.
With banners with slogans like ” Stop the torture of Oromo ” and ” Stop lavishing “, and the use of megaphones , spread the message to people in the downtown streets.
Sunday, 27 October 2013
የጀነራል መኮንኖች የምደባ ለውጥ ተካሄደ
ሜጀር ጀነራል አደም መሀመድ የአየር ሀይል አዛዥ ሆነው መሾማቸውንና የአዛዥ ጄነራሎች ላይም የምደባ ለውጥ መደረጉን ምንጮቻችን አመለከቱ፡፡ በአየር ሀይል አዛዥ በነበሩት ሜጀር ጀነራል ሞላ ሀይለማርያም ምትክ የተሾሙት ሜጀር ጀነራል አደም የአየር ሀይል ፓይለት የነበሩና በሱዳን አቢዬ ግዛት የሠላም አስከባሪ ሀይል ምክትል አዛዥነት ያገለገሉ እንዲሁም የመከላከያ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ነበሩ፡፡
በሌሎች የመከላከያ የስራ ምድብ ቦታዎች ላይ የአዛዦች የምደባ ለውጥ መደረጉን የተናገሩት ምንጮች፣ አዲስ የሀላፊነት ምደባ ከተሠጣቸው ውስጥ ሌተናል ጀነራል ሠአረ መኮንን፣ ሌተናል ጀነራል አበባው፣ ሜጀር ጀነራል ዮሀንስ ወልደጊዮርጊስ፣ ሜጀር ጀነራል ገብራት አየለ እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡
ባለፈው አመት እና ዘንድሮ ከ60 በላይ ለሚሆኑ መኮንኖች የጀኔራልነት ሹመትና እድገት መሰጠቱ ይታወሳል፡፡
addis admas
Saturday, 26 October 2013
የጀነራል መኮንኖች የምደባ ለውጥ ተካሄደ
ሜጀር ጀነራል አደም መሀመድ የአየር ሀይል አዛዥ ሆነው መሾማቸውንና የአዛዥ ጄነራሎች ላይም የምደባ ለውጥ መደረጉን ምንጮቻችን አመለከቱ፡፡ በአየር ሀይል አዛዥ በነበሩት ሜጀር ጀነራል ሞላ ሀይለማርያም ምትክ የተሾሙት ሜጀር ጀነራል አደም የአየር ሀይል ፓይለት የነበሩና በሱዳን አቢዬ ግዛት የሠላም አስከባሪ ሀይል ምክትል አዛዥነት ያገለገሉ እንዲሁም የመከላከያ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ነበሩ፡፡
በሌሎች የመከላከያ የስራ ምድብ ቦታዎች ላይ የአዛዦች የምደባ ለውጥ መደረጉን የተናገሩት ምንጮች፣ አዲስ የሀላፊነት ምደባ ከተሠጣቸው ውስጥ ሌተናል ጀነራል ሠአረ መኮንን፣ ሌተናል ጀነራል አበባው፣ ሜጀር ጀነራል ዮሀንስ ወልደጊዮርጊስ፣ ሜጀር ጀነራል ገብራት አየለ እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡
ባለፈው አመት እና ዘንድሮ ከ60 በላይ ለሚሆኑ መኮንኖች የጀኔራልነት ሹመትና እድገት መሰጠቱ ይታወሳል፡፡
addis admas
ስብሃት ህወሃት ጠቦ ታሪኩን እንደሚቋጭ አረጋገጡ
ስብሃት ነጋ የኢህአዴግ አባትና ፈጣሪ የሆነው ህወሃት የመጨረሻው ታሪኩ ጠቦ እንደሚቋጭ ይፋ አደረጉ። ችግር የህወሃት ልዩ በረከትና ስጦታ እንደሆነ በማመልከት ህወሃት ውስጥ ልዩነትና መፈርከስ አደጋ ተከስቶ እንደማያውቅ ሸመጠጡ።
አቶ ስብሃት ጠቦ የሚጠናቀቀውን የህወሃት ስውር አጀንዳ የገለጹት ከጋዜጠኛ ደረጃ ደስታ ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ በሰጡበት ወቅት ነበር። በኢህአዴግ የመከላከያ መዋቅር ውስጥ ከፍተኛ መከፋፈልና የኩዴታ አደጋ ሊያስከትል የሚችል አደጋ እንደተረጋገጠ ተጠቅሶ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ስብሃት “አዲስ አበባ መንግስት ገልብጠው የክልሎችን ድጋፍ ቢጠይቁ ማን እሺ ይላል” በማለት ነበር የመለሱት። አንዴ በመከላከያ ውስጥ የመከፋፈልና የመበታተን አደጋ ሊያጋጥም የሚችልበት አግባብ እንደሌለ፣ ጠያቂው እንዳለው የመፈንቅለ መንግስት አደጋ ቢያጋጥም እንኳ የህወሃት ስጋት እንዳልሆነ አስመስለው አቶ ስብሃት የመለሱት የክልሎችን ስም በመጥራት ተቀባይት እንደማይኖረው ነው። ይህም አባባላቸው እኛን ገልብጦ አገር አንድ አድርጎ መምራት አይቻልም የሚል እንደምታ ያለው ቢመስልም፤ “ሪፑብሊክ” ለመመሥረት የተነሳውና እስካሁን በነጻአውጪ ስም አገር እየገዛ ያለውን ህወሃት የመጨረሻ የመጥበብ ዓላማ በማስረጃ የገለጹበት ነው፡፡
ህወሃት “ኢህአዴግ” የሚባለውን ድርጅት ሲያበጀው የአገልግሎት ዘመን መድቦለት እንደሆነ ስለ ድርጅቱ የወደፊት መድረሻ ድንበሩ ከሚያወሱ የድርጅቱ የተለያዩ ማረጃዎችና ነባር አባሎቹ መጠቆሙ ይታወሳል። ህወሃት 40ና 50 ዓመት ኢትዮጵያን በብሔር ፖለቲካና በዘር እያጋጨ ለመግዛት የሳለው ስዕል እንዳሰበው ካላዘለቀው እንዴት ጠቦ እንደሚጠናቀቅ የጠቆሙት ስብሃት፣ አስተያየታቸው አካሄዱ የገባቸውን በሙሉ አበሳጭቷል።
በ1997 የምርጫ ወቅት ተፈጥሮ በነበረውና በራሱ በቅንጅት ሰዎች ሽኩቻ በተኮላሸው ህዝባዊ ድል ግለት ወቅት ኢንዲያን ኦሽን የተሰኘው ጋዜጣ “ህወሃት ወደ ትግራይ የማፈግፈግ እቅድ ይዟል” በማለት የዘገበውን ዘገባ በማስታወስ በአቶ ስብሃት መልስ ላይ አስተያየት የሰጡ፤ በቅድሚያ አቶ ስብሃትን “አቦይ ብላችሁ አትጥሩት። አባታዊ አንደበትና ምግባር የለውም” በሚል ማሳሰቢያ ከሰጡ በኋላ “የስብሃት ንግግር ህወሃት ታሪኩ ሲጠናቀቅ ጠቦ እንደሚቋጭ ነው። ለዚህ ሲል ነው ህዋሃት ከአንቀጽ 39 ጋር ቅበሩኝ የሚለውና የአማራ ክልል መሬትን እየዘረፈ የመውጫ ቀዳዳ ፍለጋ ሌት ከቀን መሬት እየቆረሰ አዲስ ካርታ የሚያመርተው፤ ዓለምአቀፋዊ ድንበርም ለትግራይ እንዲኖራት ያደረገው” ብለዋል።
“ህወሃት ካለውና ከተፈጠረበት ክፉ ዓላማ አንጻር በቀጣይዋ ኢትዮጵያ ‘ቦታ አይኖረኝም’ የሚል ድምዳሜ ላይ ስለደረሰ ሁልጊዜ ሲጨንቀው ኢትዮጵያን የማፈራረስ ስዕል ያሳያል። የስብሃትም ንግግር ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነው” በማለት ምልከታቸውን የተናገሩት የጎልጉል የዘወትር አስተያየት ሰጪ “ውሳኔውና ህልሙ ስኬት የናፈቀው የቅጥረኞቹ የህወሃት ሰዎች ጭንግፍ ምኞት ቢሆንም መላው የትግራይ ህዝብ በዚህ ጉዳይ ላይ ጥርት ያለ አቋም በመያዝ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የሚቆም መሆኑን ማሳየት እንደሚገባው” አመልክተዋል።
ከህወሃት ሊቀመንበርነታቸውና ከስራ አስፈጻሚነታቸው አራት ጊዜ ማመልከቻ በመጻፍ በፈቃዳቸው እንደለቀቁ ያመለከቱት ስብሃት ነጋ በኤፈርት ጉዳይ ከወ/ሮ አዜብ ጋር ስምምነት እንዳልነበረቸው ፍንጭ ሰጥተዋል። አያይዘውም ህወሃት የመከፋፈል አደጋ አጋጥሞት እንደማያወቅ፣ እንዲያውም በየጊዜው የሚነሱ የሃሳብ ልዩነቶች የድርጅቱ ልዩ ስጦታውና በረከቱ አንደሆነ ተናግረዋል። ልዩነትና በልዩነት ጥግ ድረስ ደርሶ መፋጨት የህወሃት የጥንካሬው መሰረት እንደሆነ ያመለከቱት አቶ ስብሃት በድህረ ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ህወሃት ለሁለት ተከፍሎ አደጋ ላይ የወደቀበትን ጊዜ አስተባብለዋል። እነ አቶ ስዬንም “የተባረሩ” ሲሉ አቅመ ቢስ አድርገው ስለዋቸዋል።
ኤርትራ ራሷን በወጉ መከላከል እንኳ የማትችል አገር እንደሆነች የጠቆሙት ስብሃት ኤርትራን ተማምኖ የሚከናወን የተቃውሞ ትግል የጤና ነው ብለው እንደማያምኑ “እብደት ነው” በማለት ኢህአዴግም ሆነ እሳቸው በእንቅስቃሴው ላይ ስጋት እንደሌለባቸው ለመግለጽ ሞክረዋል። ስብሃት በአሜሪካ ከተለያዩ ወዳጅ ሚዲያዎች ጋር እየተወደሱ ጥያቄና መልስ ያካሄዱ ሲሆን በተለይም ስለ መለስ ቅንድብ ከዘፈነው ሰለሞን ተካልኝ ሲቀርቡላቸው የነበሩት ጥያቄዎች የሚያዝናኑ ነበሩ። ጥያቄና መልሱን የተከታተሉ “ጠያቂው መልሱን አስቀድሞ ጥያቄ ማስከተሉ ጥሩ ተማሪ መሆኑንን በማረጋገጥ የምስክር ወረቀት የፈለገ አስመስሎታል” ሲሉ የለበጣ አስተያየት በማህበራዊ ገጾች ላይ አስፍረውበታል። አቶ ስብሃት በአሜሪካ ከጠባቂዎቻቸው ጋር በመሆን መደባደባቸውና በፖሊስ ይፈለጉ እንደነበርም መዘገቡ ይታወሳል። አቶ ስብሃት ከፖለቲካው ፈላጭ ቆራጭነት ወጥቻለሁ ቢሉም የሚሰጡዋቸው አስተያየቶችና ትንቢቶች አሁንም “የህወሃት የኋላ ዘዋሪ” እንደሆኑ አመላከች እንደሆነ ተጠቁሟል።
Friday, 25 October 2013
ሕዝባዊ እምቢተኝነት በውጭ አገር፤ እንዴት?
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በሁለገብ ትግል ወያኔ ማስወገድ ይገባል ብሎ የሚያምና ለዚህም የሚታገል ድርጅት ነው። “ሁለገብ ትግል” ሲባል ሰላማዊም ሰላማዊ ያልሆኑም የትግል ስልቶችን መጠቀም ማለት ነው። “ሁለገብ ትግል” ሲባል በአገር ውስጥም ከአገር ውጭም የሚደረጉ ትግሎች ማለት ነው።
ከዚህ አንፃር በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሚና ምን ሊሆን ይገባል?
በግንቦት 7 እምነት በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በድጋፍ ሰጭነት ሳይወሰኑ የትግሉ ቀጥተኛ ተሳታፊዎች መሆን ይኖርባቸዋል። በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በወያኔ ጥቅሞችና ተቋማት ላይ በማመጽ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን አርዓያ መሆን ይኖርባቸዋል።
በዚህ ረገድ የተጀመሩ አበረታች ጥረቶች አሉ፤ ለምሳሌ:
ወያኔ ሙስሊሞችን ከክርስቲያኖች ለማጣላት ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም። በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን “እንቢ አንጣላልህም” ያሉት መሆኑ የሚያኮራ ነው። ወያኔ ከጠበቀው በተቃራኒ የሁለቱም ሃይማኖቶች መሪዎች በጋራ ጉዳዮች ላይ ሲመክሩ መታየቱ ተስፋ ሰጪ ጅማሮ ነው። አብሮነታችንን ማጎልበትና ይህንን በአደባባይ፣ በአዳራሾች፣ በቴሌቪዥን መስኮቶች ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማሳየት እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው። ውጭ የተጀመረው አገር ቤት መዳረሱ የማይቀር ነው። ይህ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርብናል።
ወያኔ በአባይ ግድብ ስም በውጭ አገራት ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በርከት ያለ ገንዘብ እንደሚያገኝ ተስፋ አድርጎ የነበረ ቢሆንም ኢትዮጵያዊያን “ከአባይ በፊት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይገደብ” “ከአባይ በፊት ሙስና ይገደብ” እያሉ ወዋጮዎቹን እንቢ ብለዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን የታየው ጽናት በጣም አበረታች ነው። የወያኔ ሹማምንት በአባይ ጉዳይ እንኳንስ ገንዘብ ስብሰባም ሊሰበሰቡ አልቻሉም። ይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
ኢትዮጵያዊያን በስፖርትና በኪነጥበባት መስኮች የሚያደርጓቸው መሰባሰቦች ለትግሉ ትልቅ እገዛ ይሰጣሉ። የኢትዮጵያ ስፓርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ (ESFNA) ከወያኔና ከወያኔ ሸሪክ ቱጃር ጋር ያደረገው ትንንቅ የሚያኮራ ነው። በርካታ ኢትዮጵያዊያን አገር፣ ነፃነት፣ ክብር ይበልጥብኛል ብለው የቀረቡላቸውን አጓጊ ማባበያዎችን “እንቢ” ብለዋል። ይህ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
ባለፈው ዓመት ጋዜጠኛ አበበ ገላው በመለስ ዜናዊ ላይ፤ ዘንድሮ ደግሞ ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድና አቶ መስፍን የዘረኛው ወያኔ ግንባር ቀደም አስተባባሪ በሆነው ስብሀት ነጋ ላይ ያሰሙት ተቃውሞ በጣም የሚደገፍና በውጭ አገራት የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ባህል ሊሆን ይገባዋል።
በስዊድን የሚገኙ የሕግ ባለሙያዎች የጀመሩት እና በኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ተሳትፎ እየተካሄደ ያለው የወያኔ ወንጀለኞችን ወደ ፍርድ የማቅረብ ሂደት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።
እነዚህ መልካም ሥራዎች ምሳሌቶች ሲሆኑ በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ከዚህ በላይ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። አንዳንዱን ለአብነት ያህል ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል።
በአገራችን ውስጥ መሠረታዊ የሆነ ለውጥ እንዲመጣ ከፈለግን ወያኔን ማስደንገጥ፣ ማሸበር፣ ካስፈለገም ማስወገድ የሚችል የአመጽ ኃይል መኖሩ ወሳኝ ነው። እንዲህ ዓይነት የወገን ኃይል ከጀርባው መኖሩ ሲሰማው ነው ሕዝብ ለእንቢተኝነት የሚነሳሳው። በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ይህንን ኃይል ቢቻል መቀላቀል፤ ካልተቻለም በአባላት ምልመላ፣ በፋይናንስ፣ በሎጂስቲክስና ዲፕሎማሲ መደገፍ ይጠበቅባቸዋል። ይህ ከሁሉ የላቀ የእምቢተኝነት መገለጫ ነው።
ትግሉ እየመረረ መሆኑ በመረዳት በርቀት ሆነን ከመብሰክሰክ በትግል ላይ ያሉትን ድርጅቶች መቀላቀል ሌላው አሁኑኑ ልናደርገው የሚገባ ነገር ነው። ድርጅቶች “አይረቡም” ብለን ስላጣጣልናቸው አይጠናከሩም። ድርጅቶችን ማጠናከርና ማዘመን ያለብን እኛው ነው። መሪዎችን ማውጣት ያለብን እኛው ነው። እስካሁን ድርጅቶችን ያልተቀላቀልን ካለን መቀላቀልና ትግሉን ማጧጧፍ ይኖርብናል።
በየተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ወያኔን “እንቢ” እንበል። “እንቢ” የማለትን አጋጣሚ ማሳለፍ የለብን። “እንቢ” ማለት የምንችልባቸው አጋጣሚዎች ብዙዎች ናቸው። ለምሳሌ: -
ሀ) ወያኔ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታን አዲስ የገንዘብ ማለቢያ ለማድረግ አቅዶ ተነስቷል። ወደ ሚሊዮን የሚጠጉ ቤቶችን በ2 ዓመት ጨርሼ አስረክባለሁ በሚል ማባበያ በውጭ አገራት ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ገንዘብ ለመሰብሰብ ዝግጅቱን አጠናቋል። ይኸንን ነገር አጠንክረን “እንቢ” ማለት ይኖርብናል። “ለኛ ቤት ከመሰጠቱ በፊት፤ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን መወደቂያ ያግኙ” ማለት ካልቻልን በራሳችን ማፈር አለብን። የአውሮፓና የአሜሪካ መንግሥታትን አምባገነኖችን በገንዘብ አትደግፉ እያልን እኛ ራሳችን ወያኔን በገንዘብ የምንደግፈው ከሆነማ ከነሱ ብሰን መገኘታችንን እንወቀው።
ለ) ወያኔ በስደተኛ ስም በመካከላችን የሰገሰጋቸውን ካድሬዎችን የማጋለጥ ዘመቻ ማፋፋም አለብን። የወያኔ ደጋፊዎችን በኤርትራ ስደተኞች ስም እንደሚገቡ መረጃዎች አሉ። በደል ደርሶብናል ብለው መንግሥታትን አሳምነው የመኖሪያ ፈቃድ ካገኙ በኋላ አጠቃን ካሉት አገዛዝ ጋር የሚሠሩ መሆናቸው የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችን አጠናቅረን ለየሀገሩ መንግሥታ ማቅረብ እንደ አቢይ ሥራ መያዝ ይኖርብናል።
ሐ) የወያኔ ባለሥልጣናት የሚገዟቸውን ቤቶች፤ የሚያስተዷድሯቸውን ቢዝነሶች እያደንን ማጋለጥ ይኖርብናል።
መ) የወያኔዎች ሹማምንት በአሜሪካና አውሮፓ በነፃነት ሊዘዋወሩ አይገባም። በሄዱት ሁሉ ተቃውሞና ውርደት ሊከተላቸው ይገባል።
ሠ) የወያኔ ቢዝነሶች ላይ ማዕቀብ ማድረግን (ቦይ ኮት) መልመድ አለብን። ጥረቶቻችንን በፈጠራ ከደገፍን ወደ አገር ቤት የምንልከው ገንዘብ የወያኔ የውጭ ምንዛሬ ረሀብ ማስታገሻ የማይሆንበት መንገድ መሻት አለብን።
ረ) ለወያኔ ባለሥልጣኖች ዲግሪ የሚያድሉ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆችን ማዋረድ መጀመር አለብን። ስምንተኛ ክፍል እንኳን በወጉ ላልጨረሱ ሰዎች የማስትሬት ዲግሪ እንደሰጡ ማሳወቅ የኛ ኃላፊነት መሆን አለበት።
በግንቦት 7 እምነት ትግሉ በሁሉም ሥፍራ ነው። ኢትዮጵያዊያን በያለሉበት ቦታ በተደራጀና በተቀናጀ መልክ ወያኔን ፊት ለፊት ከተጋፈጥን የድላችን ቀን እናቀርባለን።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!
Wednesday, 23 October 2013
ጠ/ሚ ኃይለማርያም ከማስረጃ አልባ ፍረጃ እንዲላቀቁ አንድነት አሳሰበ
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ካለፈው ስህተታቸው በመማር ከአጉልና ማስረጃ አልባ ፍረጃ እንዲላቀቁ አሳሰበ። ፓርቲው ከትናንት በስትያ ባወጣው መግለጫ እንደገለፀው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ባለፈው ሳምንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በመሪ ደረጃ በማይጠበቅ መልኩ የአንድነትን እንቅስቃሴ ስም ለማጥፋት በመሞከራቸው ከዚህ ድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል ብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የራሳቸው አጀንዳ የላቸውም፣የሻዕቢያ መልእክት አድራሾች ናቸው ያሉት የራሳችን አጀንዳ እንዳለን ጠፍቷቸው ሳይሆን ሆን ብለውና አቅደው ስም ለማጥፋት እንዲሁም ህዝቡ ውስጥ ጥርጣሬ ለመጫር በመፈለግ ነው ብሏል።
ፓርቲው ተላላኪነቱ ለኢትዮጵያ ህዝብና ይጠቅማል ብሎ ለቀረፃቸው የፖለቲካ ፕሮግራም ብቻ መሆኑን የገለፁ ሲሆን፤ እንዲህ አይነቱን ስም ማጉደፍም በቸልታ እንደማያልፈው ገልጿል። በተጨማሪም የሙስሊም ወገኖችን ጥያቄ በተመለከተ ፓርቲው በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ይመለስ፣ ዜጎች የመብት ጥያቄ ሲያነሱ መፈረጁ ይቁም እንዲሁም ካለአግባብ የሃይማኖት ነፃነት ጥያቄ በማንሳታቸው ወደ እስር ቤት የተወረወሩ ዜጎች በአስቸኳይ ይፈቱ የሚል ጥያቄ ማንገቡን ፓርቲው ገልጿል። በመሆኑም ፓርቲው ከኢፍትሃዊት ጋር እንደማይደራደር እና እንደማይቀበለው አመልክቶ፣ ፓርቲውን ከሙስሊም ወገኖች ጥያቄ ጋር በማያያዝ ትርፍ ፍለጋ መሯሯጥ ወንጀል ነው ብሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሰላማዊ ሰልፍን በተመለከተ የተናገሩት በህገ መንግስቱ የተቀመጠውን መብት በአደባባይ የጨፈለቀ ነው ብሏል ፓርቲው። ሰላማዊ ሰልፍ ለሚያደርጉ በቂ ጥበቃ የለንም በሚል ተልካሻ ሰበብ የዜጎችን መብት መንጠቅ እንደማይቻል የገለፀው ፓርቲው፤ ጥበቃ ማድረግ ያልቻለ መንግስትም ስልጣኑን ለህዝብ በማስረከብ ይቅርታ ጠይቆ መሄድ እንጂ ከአሁን በኋላ መብታችሁን አታገኟትም ብሎ መዛት ትዝብት ላይ ይጥላል ብሏል።
ፓርቲው አያይዞም የአፍሪካ መሪዎች ተሰብስበው አይ ሲሲ ሊከሰን አይገባም ሳይሆን ማለት ያለባቸው፣ የዜጎቻቸውን እንባ ማበስ እና ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲረጋገጡ መጣር ነው ብሏል። መሪዎች በርካታ መፍትሄ ፈላጊ ችግሮች ባሉባት አፍሪካ ተሰብስበው እንግደል፣ እንሰር፣ እንጨፍጭፍ፣ ዘር እናጥፋ፣ ዜጎቻችንን እናሰቃይ ግን መታሰርም፣ መከሰስም የለብንም የሚለው አቋም አሳፋሪ በመሆኑ ፓርቲው እንደማይቀበለው ገልጿል። በመሆኑም ዜጎች ላይ ግፍና ስቃይ የሚፈፅሙ ሁሉ ሳይውል ሳያድር ወደ ፍርድ መቅረብ አለባቸው በማለት፤ አንዳንድ የአፍሪካ መሪዎች አይሲሲን በተመለከተ የሚያራምዱትን የአትክሰሱን አቋም ፓርቲው እንደማይቀበለውም ገልጿል።
Tuesday, 22 October 2013
ጫልቱ እንደ ሄለን ከቡርቃ ዝምታ የቀጠለው መርዛማ ብዕር
ዳኛቸው ቢያድግልኝ
ተራሮች አንቀጠቀጥኩ ያለው ትውልድ አካል ነኝ ባዩ ወንድማችን በቡርቃ ዝምታው በማር የተለወሰ መርዝ አሰናድቶ አማራና ኦሮሞ ሲተራረድ ዙርያ ከበው በለው! አትማረው! የሚሉትን የአባቱን ሀገር ፖለቲከኞች አስቦ የጻፈው ክታብ መሆኑ ተነግሮ አብቅቶለታል። ተስፋዬ የጦር ሜዳ ዘጋቢነቱን በኢትዮጵያውያን ተምሮ ኢትዮጵያዊ አይደለንም ብለው ለሚወጉን ማገልገሉና በደል መፈጸሙ እውነት ነው። ለዚህ ውለታውም የዘመናት ታሪክ ያለውን ድርጅት ያለምንም ክህሎት በአዛዥነት ይዞ እንዳሻው እንዲፈነጭበት ተሰጥቶት ነበር። ቁንጮ ሆኖም የሚበቃውን መረጃ ከክምችቱ እንዲያገኝ ሆኖ መሰየሙንና ክምችቱንም ለፕሮፓጋንዳ መሳርያነት እንዲጠቀምበት ሙሉ መብት ተሰጥቶት እንደነበረም እናውቃለን። ተስፋዬ አገር የለቀቀበትን ጊዜ መለስ ብለን ብንመለከት ለሻዕብያ ያለው ቅርበት ከወያኔ ጋር ለመቀያየም ምክንያቱ መሆኑን መገመት ይቻላል። በተስፋዬ ስራዎች ውስጥ የኤርትራ ጉዳይ ልዩ ቦታ እንዳለውና ከጻፈም ጀግና ብልህና አስተዋይ እንደሚያደርጋቸው የታወቀ ነው።
Read full story in PDF

Monday, 21 October 2013
“ኢትዮጵያነቴን ይዤው ወደ መቃብር እሄዳለሁ” አቶ ተስፋዬ ገ/አብ
ቀደም ብዬም ተናግሬያለሁ። ማንም ሊከለክለኝ አይችልም። ማንም ሊሰጠኝ አይችልም። አገር ውስጥ እንዳልገባ ልከለከል እችል ይሆናል። የልብ ስሜቴን መንጠቅ የሚችል አንድም ሰው የለም። ይህንን ስሜቴን ነው ባጭሩ ማነገር የምፈልገው።ማንም አይቻለውም። ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቼ ሚሊዮኖች አሉ።በተለያዩ ምክንያቶች አገር ቤት መግባት አይችሉም። ከጥቂት ጊዜያት በሁዋላ ግን እንደጎርፍ ነው ወደ አገራችን የምንገባው።ይህንን ነው ላረጋግጥላችሁ የምፈልገው። / አበባ ይበተንለታል/ ለከለከሉኝ ክፍሎች ማን ነው ያ ከልካይ በመሰረቱ? ከየት ነው የመጣው? ያ ሰው ምን አደረገ ለአገሪቱ?እኔ የቢሾፍቱ ልጅ ነኝ። ኢትዮጵያዊ ነኝ። ይህንን መከልከል የሚችል ማንም የለም።ይዤው ወደ መቃብር እሄዳለሁ። እስከመጨረሻው … (ተስፋዬ ከኢካድኤፍ የመወያያ መድረክ ጋር ካደረገው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ)
ከሰነዱ ከተገኙት መረጃዎች መካከል ተስፋዬ በእጁ የጻፈው ይህ መረጃ ይገኛል፡-
“ኢትዮጵያዊያን የኤርትራ ታሪክ በትክክል እንዲያውቁ ይረዳል። ይህም በአዲሱ የኢትዮጵያ ትውልድ አእምሮ ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል እንዳልነበረችና እንደማትሆንም የአመለካከት ዘር መዝራት ያስችለኛል። ለዚህ ሥራም የናንተ መ/ቤት ሆነ ህገደፍ (ሻዕቢያ) ሰነዶችን እንድመለከት በመፍቀድ ያግዘኝ ዘንድ እመኛለሁ። እነዚህ መጻሕፍትን ጽፌ እስከምጨርስ ሁለት ዓመት ይፈጅብኛል። ቢያንስ በቢሮና በጽሕፈት መሣሪያዎች እንዳልቸገር ብደረግ እመኛለሁ።” …
“በኤርትራ ጉዳይ፣ በሻዕቢያ አላማዎችና አሰራሮች፣ እንዲሁም ኢሳያስን በተመለከተ ያለኝ በጣም ግልጽ ነው። ከነሙሉ ችግራችን ኤርትራ በትክክለኛው ሃዲድ ላይ እየተጓዘች ነው ብዬ አምናለሁ። የሚታረሙ ነገሮች ካሉ ዋናው ጉዞአችን ሳይነካ እየተስተካከለ ሊሄድ ይችላል ብዬ አምናለሁ። የምጽፈውም ሆነ የምሠራው ይህን መሠረት ያደረገ ነው።” …
“አሻግሬ ስመለከት በርቀት ሰማያዊ ተራሮች ይታየኛል። ከተራሮቹ ስር ያለው ለጥ ያለ የእርሻ ሜዳ የአባቴ አገር ነው።” …
“ይህን ታሪክ እጽፈዋለሁ: 3 ተከታታይ መጽሐፍ ሊወጣው ይችላል። ባህረነጋስያን በመጀመር የኤርትራን ታሪክ እጽፈዋለሁ። የሻቢያን የትግል ታሪክ እጽፈዋለሁ። ይህም ኢትዮጵያዊያን ስለኤርትራ ተገቢውን ሃቅ እንዲገነዘቡ ያደርጋቸዋል። በዚህ መጽሐፍ ጠላት አፈራለሁ። ቢሆንም ግን እጽፈዋለሁ። ስለዚህ ከአሁኑ ፍንጭ መስጠቱ ጠቃሚ ነው። በተቃውሞ የምጽፍ የሚመስላቸው ስለሚኖሩ እስከዚያው ድረስ ይዝናኑበት። ኤርትራ ለመመለሴ ምክንያት ይሰጥልኛል።”
golgule.com
የኢህአዴግ ቀጣይ የፖለቲካ ሴራዎች – (ተመስገ ደሳለኝ)
የሁለት ሺህ ስድስት ዓመተ-ምህረት የመጀመሪያ ወር ተጠናቅቋል፤ አዳዲስ ክስተቶችም ታይተዋል፤ ያለፉት አስራ ሁለት ዓመታትንበጃንሆይ ቤተ-መንግስት ያሳለፉት ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ፣ በኦህዴዱ ሙላቱ ተሾመ መተካታቸው አንዱ ነው፡፡ አባይ ፀሀዬና ዶ/ር ካሱ ኢላላም ከበረከት ስምዖንና ኩማ ደመቅሳ በተጨማሪ በሚኒስትር ማዕረግ የኃ/ማሪያም ደሳለኝ ‹‹የፖሊሲና ጥናት ምርምር›› አማካሪ ሆነው መሾማቸው ሌላው ነው (በነገራችን ላይ ሹመቱን እንደተለመደው አይቶ ችላ ብሎ ለማለፍ የማያስችሉ ሶስት ምክንያቶች አሉ፤ የመጀመሪያው በሀገሪቱ ለአንድ የሥራ መደብ አራት ሚንስትር ተሹሞ አለማወቁ ሲሆን፤ ሌላው ተሿሚዎቹ፣ ኢህአዴግን ከመሰረቱት አራት ፓርቲዎች በኮታ የተወጣጡ መሆናቸው ነው፡፡ ሳልሳዊውና አስገራሚው ደግሞ ሰዎቹ ፖለቲከኞች እንጂ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ጥናትና ምርምር ያካሄዱ ምሁራን አለመሆናቸው ነው)
እነዚህ ሁሉ በግልፅ የሚታወቁ የዓመቱ መጀመሪያ ክስተቶች ናቸው፡፡ ለስርዓቱ ቅርበት ካላቸው ምንጮቼ ባገኘሁት መረጃ መሠረት፣ በቅርቡ ‹ሚዲያ›ን እና ‹የይቅርታ ስነስርዓት›ን የተመለከቱ አዳዲስ አዋጆች በተወካዮች ም/ቤት ለመፅደቅ ተዘጋጅተዋል፡፡ በተለይም ‹ሚዲያው›ን የሚመለከተው አዲሱ ህግ፣ ከአምስት ዓመት በፊት ተግባር ላይ የዋለውን የ‹‹ፕሬስ አዋጁ››ን የአፋና ጉልበት ይበልጥ የሚያጠናክር በመሆኑ፣ የነበረው አንፃራዊ ጭላንጭል ጭራሽ ሊዳፈን እንደሚችል መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ‹‹የይቅርታ አዋጁ››ም ቢሆን ጥቂት የአገዛዙ ጉምቱ ባለስልጣናት ‹‹የተቃዋሚ ፓርቲ የአመራር አባላትና አንዳንድ የግል ጋዜጠኞች ብንታሰርም በይቅርታ እንፈታለን በሚል ግንባሩን እየተፈታተኑ ነው›› ሲሉ ደጋግመው መደመጣቸውን፣ ከአዲሱ ‹‹የይቅርታ አሰጣጥ እና አፈፃፀም ሥነ-ሥርአት አዋጅ›› ጋር ካያያዝነው፣ አንቀፆቹ ሊኖራቸው የሚችለውን አንድምታ መገመቱ ብዙ ከባድ አይሆንም፡፡
ለማንኛውም ኢህአዴግ ከመቼውም ጊዜ በላይ ጉልበታም በመሆን ቀጣዩን ምርጫ በስኬት ለማለፍ፣ በያዝነው ዓመት የተለያዩ አፋኝ ህጎችን በማውጣት ፓርቲዎቹን የማዳከም ስራ ለመስራት በተለየ መልኩ መዘጋጀቱ ተሰምቷል፡፡ በአናቱም ኃ/ማርያም ደሳለኝ-ከመንግስት፣ ከፓርቲውና ከውስን የግል ጋዜጠኞች፤ ደመቀ መኮንን-ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ፤ ሽመልስ ከማል -ከኢዜአ ጋር ያደረጓቸው ቃለ-መጠይቆችም ይህንን መረጃ የሚያጠናክር ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ የዚህ ፅሁፍ ተጠየቅም አገዛዙ በቀጣይ ሊኖረው የሚችለውን ባህሪ እና ‹አምስተኛው ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫ›ን አስቀድሞ ለማሸነፍ እየቀመረ ያለውን ሴራ መጠቆም ነው፡፡
የባለስልጣናቱ አንደበት
ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያምና ምክትሉ ደመቀ ሰሞኑን ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃለ-መጠይቅ ላይ፣ በስሱም ቢሆን ከጀርባቸው ያደፈጡትን አንጋፋ ታጋዮች ቀጣይ ‹‹የፖለቲካ ሴራ›› (Political Conspiracy) አርድተውናል ብዬ አስባለሁ፡፡
ሁለቱ መሪዎች በዋናነት እንዲያተኩሩ የተደረገው በአራት ጉዳዮች ላይ ነው፡፡ በግንባሩ ውስጥ ክፍፍል መፈጠሩን መካድ፣ አመቱን ሙሉ ‹የመለስ ራዕይ› እየተባለ የተዘመረለትን ‹እሳት ማጥፊያ› ፕሮፓጋንዳ ማስተባበል፣ የሙስና ክሱን ሂደትና ውጤት መሸፋፈን እንዲሁም ተቀናቃኝ ፓርቲዎችን ማስፈራራት የሚሉ ናቸው፡፡ በአዲስ መስመርም እነዚህን አራት አጀንዳዎች ነጣጥለን ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡
ክፍፍሉን በተመለከተ
ከመለስ ህልፈት ማግስት አንስቶ በግንባሩ ግልፅ ክፍፍል መከሰቱ የአደባባይ ሀቅ ቢሆንም፣ ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማሪያም ‹‹ፓርቲዎ ውስጥ ክፍፍል አለ ይባላል፤ የኃይል አሰላለፍ እየተጠበቀ ነው የሚኬደው የሚባሉ አሉባልታዎች ይሰማሉ፣ የፓርቲዎ ጤናስ እንዴት ነው?›› የሚል ጥያቄ ሲቀርብለት፡-
‹‹በፓርቲዬ ውስጥ ክፍፍል አለ የሚለው ጥያቄ የምኞት ነው፤ ብዙ ምኞቶች ሲሰሙ ነበር፤ ምኞት አይከለከልም፡፡ ስለዚህም ምኞት ይኖራል የሚል ሃሳብ ከማቅረብ በዘለለ እውነት ስለሌለው ምኞት ነው ብሎ ማለፍ ነው›› በማለት አስተባብሎ ሲያበቃ፤ ከደቂቃዎች በኋላ ደግሞ ተገልብጦ ‹‹አሁን በቅርቡ እንደደረስንበት አንዳንድ ጊዜ በየቦታው ደባ የሚሰሩ ጥቂት የመሥሪያ ቤት ሰራተኞች አሉ›› ብሎ የራሱ ሰዎች በመንግስቱ ላይ እያሴሩበት እንደሆነ በመግለፅ ከላይኛው ንግግሩ ጋር መጣረሱ፣ በርግጥም የተጠቀሰው ችግር መኖሩን ለመረዳት አያዳግትም፡፡
ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተም ‹‹አዲስ ዘመን›› ጋዜጣ ምክትል ጠ/ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ አጠንክሮ ጠይቆት ያስተባበለበት መንፈስም ለመሸሸግ የፈለገው ጉዳይ እንዳለ የሚያሳብቅ ይመስላል፡፡
‹‹አንድ ግልፅ መሆን ያለበት እንደ አቶ መለስ ያለ ታላቅ መሪ፣ ታግሎ የሚታገል ጠንካራ መሪን ማጣት ትልቅ ጉድለት ነው፡፡ ጉድለቱ እንዲሁ ዝም ተብሎ እዚያና እዚህ በዘመቻ የሚሞላ ጉዳይ አይደለም፡፡ …ስለዚህም ሁለት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ ኃላፊዎችን በመሰየም ክላስተር እንዲያስተባብሩ ማድረግ ያለመተማመን መገለጫ አይደለም፡፡››
የሁለቱ ሚኒስትሮችን ያልተጠበቀ ቃለ-መጠየቅ መግፍኤ ለመረዳት በተለይ ደመቀ መኮንን ለቀረቡለት ጥያቄዎች የሰጠውን ምላሾች በጥልቅ መፈተሽ አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም ተከስቶ የነበረውን መከፋፈልም ሆነ ‹ፓርቲው በጥቂት የህወሓትና የብአዴን ታጋዮች ነው
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
የሚሽከረከረው› መባሉን ለማስተባበል የሄደበት መንገድ፣ ከዚህ ቀደም ኢህአዴግ የሚከራከርባቸውን እምነቶቹን ጭምር እስከመናድ የደረሰ ነውና፡፡ ወይም እንዲንድ ታዝዟል ያስብላል (በነገራችን ላይ ከምንጮቼ ባገኘሁት መረጃ እነአባይ ፀሀዬና በረከት ስምዖንም ከመጋረጃው ጀርባ የሚሰራ ኃይል መኖሩን ማስተባበል ይፈልጋሉ፡፡ በተለይም ‹‹በነፃነት እንዲሰሩ አመቻቹላቸው›› እያሉ የሚወተውቷቸውን ምዕራባውያን ዲፕሎማቶች ማሳመኑ ከባድ ሥራ እንደሆነባቸው ሰምቻለሁ፡፡
የሰሞኑ የቃለ-መጠይቅ ጋጋታም ይህንኑ የሚያጠናክር ይመስላል፡፡ ‹‹አዲስ ዘመን›› ጋዜጣም ለደመቀ መኮንን ያቀረባቸው ጥያቄዎች ከቀደመው ታሪኩ አኳያ ሲመዘን የግል እምነቱ አለመሆኑን መረዳት አያዳግትም፡፡ ‹‹ጋዜጣው እስከአሁን ያልነበረውን ‹የኤዲቶሪያል ነፃነት› ዛሬ አግኝቶ ነው ሰውየውን እንዲህ ያፋጠጠው›› የሚል ተከራካሪ ካልቀረበ ማለቴ ነው፡፡ ምናልባትም ጉዳዩን በሌላ አውድ እንየው ከተባለ ደግሞ የሚያያዘው፣ የድርጅቱ አመራሮች አልፎ አልፎ ህዝብ ዘንድ የደረሱ እውነታዎችን፣ በራሳቸው ጋዜጠኞች እንዲጠየቁ በማድረግ ለማስተባበል ከሚሞክሩበት የቆየ ልማዳቸው ጋር ብቻ ነው፡፡ በመስከረም 22፣ 23 እና 24 ቀን 2006 ዓ.ም በታተመው የ‹‹አዲስ ዘመን›› ጋዜጣ በተስተናገደው የደመቀ መኮንን ቃለ-መጠይቅ ላይ የተነሱትን ጥያቄዎች ብንመለከት ይህንኑ ያረጋግጡልናል፡፡ ‹‹ፓርቲው በጥቂት ሰዎች ስር ስለመውደቁ፣ ከመንግስት ኃላፊነት የተነሱ ባለስልጣናት በፓርቲው ውስጥ ስራ-አስፈፃሚ ሆነው ስለመቀጠላቸው፣ መተካካቱ የቦታ መቀያየር ብቻ ስለመሆኑ፣ ሥራ የማይሰሩ ደካማ መሆናቸውን በተወካዮች ም/ቤት ጭምር የተረጋገጠባቸው ከፍተኛ አመራሮች ዛሬም በኃላፊነት ቦታ ላይ ስለመቀመጣቸው፣ በብልሹ አሰራር /በሙስና/ የተጠየቁ ባለስልጣናት ጥቂት ብቻ መሆናቸው፣ በአቅም ማነስ የሚነሱ ኃላፊዎች ወይ ከነበሩበት የተሻለ አሊያም ተመጣጣኝ በሆነ ደረጃ ስለመመደባቸው፣ አንድ ጊዜ የላይኛውን የስልጣን እርከን የተቆናጠጠ ባለስልጣን ከፓርቲው ቁልፍ አመራሮች ጋር ካልተጋጨ በቀር አቅም ባይኖረውም እንደማይሻር፣ ለፓርቲው መስራቾችና እስከአሁንም ወሳኝ ለሆኑት አመራሮች ታማኝ የሆነ ኃላፊ ምንም አይነት ድክመትና ወንጀል ቢፈፅምም በስልጣን መቆየት መቻሉን፣ የሁለቱ ተጨማሪ ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች ሹመት በአራቱ የብሔር ድርጅቶች መካከል ያለውን አለመተማመን ስለማሳየቱ፣ ሁሉም ፓርቲዎች እኩል አለመሆናቸውን፣ መለስ በሃያ ሁለት የሥልጣን ዓመታቱ ተተኪ ማፍራት አለመቻሉን፣ ‹የመለስ ራዕይ› የሚባል ነገር አለመኖሩን…›› እና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ባልተለመደ ድፍረት የጠየቀው መንግስታዊው ዕድሜ ጠገብ ‹‹አዲስ ዘመን›› ጋዜጣ ነው)
ቃለ-መጠየቁ ከእነዚህ በተጨማሪም ቀጣዩን የኢህአዴግ አቅጣጫ አመላክቷል፡፡ የሆነው ሆኖ ክፍፍሉንና ከጀርባ ሆነው ያሽከረክራሉ የሚባሉትን አንጋፋ የአመራር አባላት አስመልክቶ ለቀረበለት ጥያቄ ከሰጠው ምላሽ ውስጥ እንዲህ የሚል ይገኝበታል፡-
‹‹ፓርቲው አንድ ሰው፣ ሁለት ሰው፣ ሶስት ሰው እጅ ጠምዝዞ ‹ይሄን አድርጉ› በሚል አንዳችም ጉዳይ የሚያስፈፅምበት አይደለም፡፡ …ኢህአዴግ በጥቂቶች የሚመራ ድርጅት አይደለም፡፡ …ጥቂት ግለሰቦችን በተለየ ሁኔታ የሚያይ፣ በእነርሱም ስር የሚሆን አይደለም፡፡ የጥቂቶች ነው የሚለው ከእውነት የራቀ ነው፡፡ …ማንም በራሱ ተቆጥሮ በተሠጠው ሥራ ሊወስን፣ ሊመራና ሊንቀሳቀስ ይችላል፡፡ በድርጅታዊ ዲሲፒሊንና አሰራር፣ የግልና የጋራ አሰራር በሚዛን ተቀምጦ በንቅናቄ የሚመራ እንጂ በግለሰቦች አይደለም የሚለው ቢሰመርበት ጥሩ ነው፡፡››
በርግጥ ይህንን ያነበበ ‹‹ሰውየው ስለየትኛው ኢህአዴግ ነው የሚያወራው?›› ቢል ላይፈረድበት ይችላል፡፡ ምክንያቱም የድርጅቱ የታሪክ ንባብም ሆነ የቀድሞዎቹ ስዬ አብርሃ፣ አለምሰገድ ገ/አምላክ፣ አውዓሎም ወልዱ፣ ገብሩ አስራት፣ አረጋሽ አዳነ፣ ነጋሶ ጊዳዳ፣ ሀሰን አሊ፣ አልማዝ መኩን የመሳሰሉት የአመራር አባላት የነገሩን ‹ድርጅቱ በጣት በሚቆጠሩ ሰዎች ፍቃድ የሚያድር› መሆኑን ነው፡፡ ለነገሩ ራሱ ደመቀም ቢሆን ከኤርትራ ጋር ወደ ጦርነት ለመግባት ህወሓት በር ዘግቶ ብቻውን መምከሩንም ሆነ የግንባሩን አባል ድርጅቶች ነፃነት እንዳሻው መጋፋቱን አምኖ መቀበል ባይፈልግ እንኳን፣ በ1999 ዓ.ም መጨረሻ ከሱዳን ጋር የሚዋሰነው የጎንደር መሬት ላይ የተላለፈው ውሳኔ በምን መልኩ እንደነበረ ሊክደው አይችልም (በነገራችን ላይ በወቅቱ የአማራ ክልል አስተዳዳሪው አያሌው ጎበዜ ምክትል የነበረ በመሆኑ፣ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ጎንደርና ትግራይ አካባቢ፣ የሚወራበትን ውንጀል በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ)
የሰውየው መከራከሪያ ግን እውነት አለመሆኑን ‹ፍትህ›ና ‹ልዕልና› ጋዜጦች፤ ‹አዲስ ታይምስ›ና ‹ፋክት› መፅሄትን ጨምሮ የምዕራብ ሀገራት ብዙሃን መገናኛ እና ድርጅቱን በቅርብ የተከታተሉ ምሁራን በተለያየ ጊዜ ማስረጃ በማጣቀስ ደጋግመው ስላቀረቡ ተጨማሪ ማብራሪያ ያስፈልገዋል ብዬ አላስብምና ወደ ቀጣዩ ጉዳያችን አልፋለሁ፡፡
‹‹መተካካት›› ሲባል…
በአንድ ወቅት አቶ መለስ ብዙ ብሎለት የነበረው የመተካካት ዕቅድ ‹‹ቦታ ከመቀያየር ያለፈ አዲስ ፊት አላመጣም›› መባሉን በተመለከተ፣ ደመቀ መኮንን የሰጠውን ምላሽ፣ ከተለያየ አውድ ካየነው ከላይ የተጠቀሰውን ክፍፍል በሌላ በኩል ይነግረናል፡፡ ምክንያቱም መለስ በህይወት በነበረበት ዘመን ጉዳዩን አስመልክቶ የነገረን ‹መተካካቱ ከላይ ያሉትን ነባር የአመራር አባላት፣ በየተራ በጡረታ በማሰናበት አዲሱን ትውልድ (አዲስ ፊት) ወደመሪነት ማምጣት ነው› የሚል እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ደመቀ መኮንን ደግሞ በግልባጩ እንዲህ ይላል፡-
‹‹አዲስ ፊት ሲባል የማናውቀው ሰው ከጨረቃ ይምጣ? የሚመራው እኮ አገር ነው፡፡ አንድ ሰው አንድ ቦታ ላይ ሆኖ ሥራውን እየተወጣ፣ ሌላውንም እያበቃ ሥርዓቱ መቀጠል አለበት፡፡ በጣም የሚታወቅ ህዝባዊ አገልግሎት ላይ ያለ ሰው፣ ከያዘው ኃላፊነት ሌላ፣ በሌላ ጊዜ ሌላ ተክቶ ሊቀርብ ይችላል፡፡ አዲስ ፊት የለም፤ የማናውቃቸው ሰዎች ይምጡ ማለት፣ ሀገር የሙከራ ቦታ ይሁን ማለት ነው፡፡››
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲህ የሚደክመው በረከት ስምዖን፣ አባይ ፀሀዬ፣ ኩማ ደመቅሳ፣ ሽፈራው ጃርሶ፣ ካሱ ኢላላ፣ ሙላቱ ተሾመን… የመሳሰሉ አንጋፋ መሪዎች ከዚህ ቀደም ለአባላቶቻቸው የገቡትን ቃል ጠብቀው በክብር ከመሰናበት ይልቅ ስልጣን መቀያየራቸውን ለማስተባበል ይመስለኛል፤ በርግጥ ጉዳዩን ከለጠጥነው ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ከአንጋፋዎቹ መካከልም ሊሆን ይችላል እያለን ይሆናል፡፡ ይሁንና ሰውየው ያስተባበለበት መንገድ ግን በውስጡ ካለው እውነታ ጋር የተቃረነ በሚመስል መልኩ
የመተካካቱ አንድምታ የተቀየረው በመካከል የተፈጠረውን የኃይል ልዩነት አርግቦ፣ ስርዓቱ ከገጠመው መንገራገጭ ወጥቶ በሁለት እግሩ ቀጥ ብሎ ቆሞ እንዲቀጥል ለማስቻል መሆኑን ፍንጭ ይሰጣል፡፡
‹‹መተካካት ግለሰብን አይደለም የሚተካው፤ የስርዓት ቀጣይነትን ማረጋገጥ ነው!››
ይህ ሁናቴ በደንብ የሚፍታታው አቦይ ስብሃት ነጋ በተለይ ህወሓት ውስጥ የተካሄደው መተካካት ከተፈጠረው ልዩነት ጋር ተያይዞ መሆኑን ለ‹‹ውራይና›› መፅሄት የሰጡትን ቃለ-መጠየቅ ስናነብ ነው፡-
‹‹ጉባኤው ከማዕከላዊ ኮሚቴ ለተሰናበቱ ሰዎች ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው፣ አሰራር ለምን እነሱን በሌሎች መተካት እንዳስፈለገ፣ ተራ በተራ እየጠቀሰ አስተያየት (ማብራሪያ) መስጠት ነበረበት፡፡ ይህ ተደርጎ ቢሆን ኖሮ ከተሰናባቾቹ መካከል ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ መቆየት (መቀጠል) የሚገባቸው በተገኙ ነበር፡፡ ከተመረጡት ውስጥ ደግሞ መሰናበት (በሌላ መተካት) የሚኖርባቸው ሊገኙ ይችሉ ነበር፡፡ ስለዚህ አካሄዱ ስህተት ስለሆነ ውጤቱም እንደዚያው ሊሆን ችሏል፡፡ እነማን መሰናበት፣ እነማን መቆየት እንደነበረባቸው በዝርዝር ስም ጠርቼ መናገር እችል ነበር፡፡ ግን ምንም ለውጥ ስለማያመጣ ስም መዘርዘሩ አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡››
የ‹‹ራዕዩ›› ጉዳይ…
በፋክት መፅሄት ቁጥር 5 ላይ ኢህአዴግ ‹የመለስ ራዕይ› እያለ ይደሰኩርለት የነበረውን አጀንዳ በወራት ጊዜ ውስጥ ገልብጦ በማጠቋቆር ሊቀየረው መዘጋጀቱ ተጠቅሶ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ በደመቀ መኮንን ቃለ-መጠይቅ ላይም፣ መለስ ሥልጣን ላይ በነበረበት ዘመን ተገምግሞ መንግስታዊ ተቋማትንና የልማት ዕቅዶችን በአግባቡ መከታተልና መቆጣጠር አለመቻሉ ተገልጿል፡፡
‹‹ያለፉት ዓመታት ሥራዎቻችንን ስንገመግም ጠቅላይ ሚኒስትራችን ብዙ ሥራ ተሸክመው ይሰሩ በነበረበት ዋና ዋና የልማት ሥራዎቻችን ላይ በማተኮር አንዳንድ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና የልማት መስኮችን በሚፈለገው ደረጃ ያለመፈተሽ፣ በዝርዝር ዕቅድ ግምገማና ድጋፍ ያለማድረግ ክፍተቶች እንደነበሩ እንደ ችግር በጋራ ያገኘናቸው ነጥቦች አሉ፡፡››
እንዲያ ሀገር-ምድሩ ‹ካልዘመረለት ተደፍረናል!› ሲሉለት የነበረው ‹‹የመለስ ራዕይ››ም ቢሆን የኢህአዴግ እንጂ የመለስ አለመሆኑን እየነገሩን ነው፡፡ አቶ ደመቀም፣ መለስ የነበረው ‹‹ራዕይ›› ሳይሆን ኃላፊነት ነው ወደ ማለቱ አዘንብሏል፡፡
‹‹ይሄን የዕድገት መንገድ ከኢህአዴግ አባላትና ከመሪዎቹ ጋር በመሆን በግንባር ቀደምነት የመሪነት ቁልፍ ሚና የተጫወቱ መሪ ናቸው፡፡››
በጥቅሉ በወቅታዊው የድርጅቱ ፖለቲካዊ አተያይ ‹‹የመለስ ራዕይ›› የሚለው ሀረግ ከየት እንደመጣ የተተነተነበትን አውድ ለመረዳት ከጋዜጣው ላይ አንድ ተጨማሪ ጥያቄና መልስ እንደወረደ ልጥቀስ፡-
‹‹አዲስ ዘመን፡- በየዘርፉ ራዕያቸው ተብለው የሚነገሩት መልእክቶችና መሪ ቃሎች ጋር በተያያዘ የተለጠፈባቸው ራዕይ እንዳለ ነው የሚነገረው፤ አገሪቱን ከመሩበት 22 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ምናልባት አንድ ጊዜ በንግግር መሀል የተናገሯት ወይም ለጋዜጠኞች የሰጡት ምላሽ ራዕይ ተደርጎ እየቀረበ ነው ስለሚባለውስ?
‹‹አቶ ደመቀ፡- እነዚያ መልዕክቶች ያንን ራዕይ የሚገልፁ፣ የሚያስታውሱ ምልዕክቶች ናቸው፡፡ ከማንኛውም ጉዳይ ጋር የተያያዙ መልዕክቶች ይኖራሉ፡፡ እነዚያ ያንን ትልቁን ራዕይ የሚመግቡ መልዕክቶች እንደሆኑ አድርጎ መመልከት ይቻላል፡፡››
ይኸው ነው፤ በቃ፡፡ መለስ ራዕዩን በጥሩ ቋንቋ ከመግለፅ ባለፈ የብቻው የሆነ ነገር የለውም፡፡ በክፍፍሉ ወቅት ከ‹አዲስ አበባው-ህወሓት› ጎን የተሰለፉት አቦይ ስብሃት ነጋ በጉባኤ፣ በተለያዩ ጋዜጦችና መፅሄቶች እንዲሁም አርከበ እቁባይ በህወሓት ጉባኤ ላይ የመለስ ‹ራዕይ› የሚባል ነገር አለመኖሩን በመግለፅ፣ በወቅቱ በአሰላለፍ የተመሳሰሉት ‹የመቀሌው-ህወሓት› እና ብአዴን በ‹ራዕይ› ስም ኃይል የማጠናከር እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን ለመተቸትና ለማደናቀፍ መሞከራቸው ይታወሳል፡፡ ይህ ሁናቴም ልዩነቱ ከተገለፀባቸው ምልክቶች አንዱ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ ሌላው እዚህ ጋ መነሳት ያለበት ጉዳይ በዚህ ዓመት በዚሁ መፅሄት ላይ ‹‹አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ›› በሚል ርዕስ የቀረበው ፅሁፍም ‹‹የመለስ ራዕይ››ን የማይቀበለው ቡድን እያሸነፈ በመምጣቱ፣ የእነ አዜብ-አባይ ወልዱ ህወሓትን አዳክሞ፣ የእነ በረከት-ብአዴንን ከጎኑ ማሰለፍ መቻሉን የተተነተነበትን ጉዳይ የሚያጠናክር መሆኑን ነው፡፡
የሆነው ሆኖ አሁን መለስን የሚያመልኩት ሄደዋል፤ በቦታውም እርሱ የሚያርቃቸው፣ እነርሱም ይፈሩት የነበረ ተተክተዋል፡፡ እናም በህልፈቱ ማግስት ድጋፍ ማሰባሰቢያ እና ኃይል ማጠናከሪያ ከመሆን አልፎ ሀገሪቱን ወደ ብልፅግና ሰማይ የሚያከንፍ፣ መና የሚያዘንብ ተደርጎ የነበረውን ‹‹የመለስ ራዕይ›› ታሪክ በማድረጋቸው፣ አርቀው መስቀል ይፈልጋሉ፡፡ በሌላ አነጋገር በፋውንዴሽኑ አጥር ክልል ተወስኖ ይቀመጥ ዘንድ በይነዋል (በነገራችን ላይ ይህን ጉዳይ በዚህ ደረጃ ያነሳሁት የስርዓቱ መሪዎች ‹‹እንመራዋለን›› የሚሉትን ህዝብ በአደባባይ ሲዋሹ ቅንጣት ያህል ሀፍረት እንደማይሰማቸው ለማሳየት እንጂ፣ በግሌ መለስም ሆነ ጓደኞቹ ለስልጣናቸው ካልሆነ በቀር ሀገር የሚጠቅም ራዕይ አላቸው ብዬ አላምንም)
የ‹‹ሙስና››ውን ክስ ሂደት መሸፋፈን
የእነ መላኩ ፈንቴን እስር ተከትሎ ‹‹ሙስና›› ዋነኛ አነጋጋሪ አጀንዳ ሆኖ ነበር፡፡ በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማሪያምም ‹ጉዳዩን ራሴ እከታተለዋለሁ› የምትል ፉከራ ብጤም ሞካክራው ነበር (ቀደም ሲል በዚሁ መፅሄት የ‹ሙስና›ው ክስ በፖለቲካው የኃይል አሰላለፍ ላይ የበላይነትን ለመጨበጥ በአዲስ አበባው ህወሓት የተመዘዘ ‹‹ካርድ›› እንደሆነ መገለፁ ይታወሳል)
ባለሥልጣናቱ የታሰሩ ሰሞን ‹‹የመለስ ራዕይ›› ገና አልከሸፈም ነበርና ‹‹የፀረ-ሙስና ኮሚሽን›› ኮሚሽነር አሊ ሱለይማንም ጉዳዩን አቶ መለስ ራሱ ጀምሮት ለሁለት ዓመት ያህል ሲከታተለው ከቆየ በኋላ፣ በመጨረሻ ህይወቱ እንዳለፈ እያለቃቀሰ ነግሮን ነበር፡፡
ይሁንና
ከእስራ አምስት ቀን በፊት ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ባደረገው ቃለ-መጠይቅ፣ የታሰሩትን ሰዎች አስመልክቶ ከጊዜ ቀጠሮ ያለፈ ቁርጥ ያለ ነገር አለመኖሩ፣ በሌሎች ላይ ስጋት ስለመፍጠሩ ተጠይቆ በሰጠው ምላሽ ‹ገድሉ›ን ከመለስ ወደራሱ (ከኋላው ወደአሉ ሰዎች) መልሶታል፡፡
‹‹በቅርቡ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አካባቢ የተፈጠረውን ችግር ለማቃለል በሙስና የተጠረጠሩ የባለሥልጣኑ ኃላፊዎችና በሙስና ተግባሩ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች ተጠያቂ የሚሆኑበት ስርዓት ተዘርግቶ የመንግስት አካል የሆነው የፌደራል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ክስ መስርቷል፡፡››
ጥያቄውም ይህ ነው፡፡ ‹‹የአሊ ሱሊማንን ‹መለስ የጀመረው…› መግለጫንስ ምን እናድርገው?››
…ደመቀ መኮንንም ‹‹እዚያም እዚያም ከኃላፊነት የማውረድ፣ በሕግ የመጠየቅና ሕጋዊ እርምጃዎች ደረጃቸውን ጠብቀው ይቀጥላሉ›› ቢልም በመሬት ያለው ተጨባጭ እውነታ ግን የሚያሳየው ሙስና የተዘጋ አጀንዳ መሆኑን ነው፡፡ የ‹‹አዲስ ዘመን›› ጋዜጣ የፊት ገፆችም ‹‹ሚኒስትር እገሌ…››፣ ‹‹ዳይሬክተር እገሌ… በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ›› ከሚል ዜና በብርሃን ፍጥነት ‹‹በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የዲዛይንና ግንባታ ፍቃድ ጽ/ቤት፣ የግንባታና ዕድሳት ባለሙያ የነበረችው ግለሰብ መስከረም 21 ቀን 2006 ዓ.ም አራት ሺ ብር ጉቦ ስትቀበል በፌደራል የሥነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሠራተኞች እጅ ከፍንጅ ተያዘች›› ወደሚል ቧልት ተቀይረዋል፡፡
አቦይ ስብሃት ነጋ ከላይ በጠቀስኩት መፅሄት የሙስናውን ጨዋታ የገለፁት እንዲህ በማለት ነበር፡-
‹‹አሁንም ድረስ ያልተፈቱ የአካሄድ (የአሰራር) ችግሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ ‹ሙስና አለ› ብትል፣ ሙስና በስርዓቱ ላይ በሚያደርሰው አደጋ ላይ ከማተኮር ይልቅ ‹አንተስ ከሙሰኛነት ነፃ ነህ ወይ?› በማለት ዋናው ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ቀዝቃዛ ውሃ የሚቸልሱ ሰዎች ጥቂት አይደሉም፡፡ አሁንም ቢሆን ይህንን የከፋ ድርጅታዊ ጉዳይ (ችግር) በመጋረጃ ሸፋፍኖ ለማለፍ ‹ስብሃት ለምን በጊዜው ጉባኤው ላይ አላቀረበውም ነበር› የሚሉ አይጠፉም የሚል ግምት አለኝ፡፡ በበኩሌ ይህ ነገር በሌላ ላይ ጊዜው ሲደርስ የሚነሳ ይሆናል ነው የምለው:፡››
በርግጥ የአቦይ ወቀሳ እውነት ነው፡፡ ይሁንና ጉዳዩን በጉባኤው ላይ ያላነሱበት ምክንያት ‹‹በሌላ ላይ ጊዜው ሲደርስ የሚነሳ ይሆናል›› በሚል እንደሆነ ለመናገር መሞከራቸው ግን የክፍለ ዘመኑ አስቂኝ ቀልድ ከመሆን የዘለለ ፋይዳ የለውም፤ ባይሆን ‹‹አንተስ ከሙሰኛነት ነፃ ነህ ወይ?› ይሉኛል ብዬ ተውኩት›› ቢሉን፣ ቢያንስ ለግልፅነታቸው ባርኔጣ እናነሳ ነበር፡፡ ምክንያቱም በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የኢህአዴግ ሰዎችን የሙስና ወንጀል በህግ የሚያስጠይቅ ከሆነ አቦይ ስብሃት ከፊት መስመር መሰለፋቸው አይቀርምና፡፡ ሌላው ቀርቶ አርከበ እቁባይ ለጊዜው ገለል እንዲል (ከሀገር እንዲወጣ) የተደረገው ከዚሁ ጋር በተያያዘ እንደሆነ የመረጃ ምንጮቼ ነግረውኛል፡፡ አርከብ፣ አቦይን ጨምሮ ከታሰሩት ባለሀብቶች ውስጥ ጥቂቶቹ በስጋ ዝምድናና በጋብቻ የተሳሰሩት የመሆኑ ጉዳይ ይመስለኛል ‹ማዕበሉ እስኪረጋ› ከዕይታ እንዲርቅ የተደረገበት ምስጥር፡፡ በተቀረ አርከበ ሀገር ጥሎ ኮበለለ፣ ኢህአዴግን ከዳ… ጂኒ ቁልቋል የሚሉት የፒያሳ ወሬዎች፣ አንድም ወቅታዊውን የኢህአዴግ አሰላለፍ ካለመረዳት ሊሆን ይችላል፤ አሊያም የጉዳዩ ባለቤቶች ስራዬ ብለው የተሳሳተ መረጃ በሚያስተላልፉበት በተለመደው ሰርጥ ያሰራጩት ማስቀየሻ ነው የሚሆነው፤ አርከበ የሄደው አቦይ እንዳሉት ‹‹አንተስ ከሙስና ነፃ ነህን?›› የማለቱ አቅም ያላቸውን አጉረምራሚ ሰዎችን ለማለዘብ ነው፡፡ ምናልባት የመቀሌው ህወሓት አሸንፎ ቢሆን ኖሮ እውነትም አርከበ ከቃሊቲ ይልቅ አሜሪካ ይሻለዋል ማለታችን አይቀርም ነበር፡፡ እነርሱም ቢሆኑ በእጁ ላይ ካቴና ለማጥለቅ አያመነቱም፡፡ ግና! የሆነው በተገላቢጦሹ ነው፡፡ …ማን ነበር ‹‹አባቱ ዳኛ…›› ያለው? (በነገራችን ላይ ኢህአዴግ የሙስና አዋጁንም በዚሁ ዓመት የማሻሻል ዕቅድ አለው፡፡)
የአፈናው ዝግጅት
ስርዓቱ በሚቀጥለው ዓመት የሚደረገው አምስተኛ ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫን ከወዲሁ ‹የቤት ስራን በማጠናቀቅ› ካልተዘጋጀንበት፣ ያልተጠበቀ አደጋ ሊያመጣብን ይችላል ወደሚል ጠርዝ የተገፋው አንድነት እና ሰማያዊ ፓርቲ በተለያየ ጊዜ በጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተገኘው ህዝብ ቁጥር አሳስቦት ብቻ አይመስለኝም፡፡ ይልቁንም ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ ያለ መለስ ዜናዊ የሚጋፈጠው የመጀመሪያው ምርጫ በመሆኑም ጭምር ነው፡፡ እንደሚታወሰው አቶ መለስ ሁሉንም የሥልጣን ምንጮች ጠቅልሎ የያዘ ‹ጠንካራ ሰው› (Strong Man) በመሆኑ፣ በእንዲህ አይነት ወቅት የሚመጡ ድንገቴ አደጋዎችን ለመቋቋም ብዙም ሲቸገር አይስተዋልም ነበር፡፡ ይሁንና በቀጣዩ ምርጫ አንድም በድርጅቱ ውስጥ የእርሱ አይነት ተተኪ ሰው አለመኖሩ፣ ሁለትም ምንም እንኳ ከህልፈቱ በኋላ የተፈጠረው ልዩነት በአንፃራዊነት የተረጋጋ ቢመስልም፣ ለሌላ ዙር የክፍፍል አደጋ አለመጋለጡ አስተማማኝ ባለመሆኑ ስጋት መፍጠሩ የሚጠበቅ ነው፡፡ በአናቱም ከእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር የተከሰተው አለመግባት እና በማህበረ ቅዱሳን ላይ ተፅእኖ ለማድረግ የመሞከሩ ጨዋታም ለተቀናቃኞች ያልተጠበቀ ኃይል ሊሆን የሚችልበት ዕድል ቢፈጥርስ የሚል ስጋት አለ፡፡
የባለሥልጣናቱ በአደባባይ የማስፈራራት መግፍኤም ይኸው ነው፡፡ ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማሪያም በቃለ-መጠይቁ ላይ ተቃዋሚዎችን (አንድነትና ሰማያዊን) እና የሀይማኖት ማህበራትን ለማስፈራራት ከሰባት ጊዜ በላይ የመለስን ‹‹ቀይ መስመር›› አገላለፅ ተጠቅሞበታል፡፡ በተለይም ሁለቱ ፓርቲዎች የያዙት በሠላማዊ ሠልፍ ተፅዕኖ የመፍጠር መንገድ ተከታዮቻቸውን እያበዛ እና የፈዘዘውን የፖለቲካ ተሳትፎ እያነቃቃው መሆኑን ግንባሩ ጠንቅቆ የተረዳው ይመስለኛል፡፡ በኃ/ማሪያምም በኩል ያስተላለፈው መልዕክትም ቀጣዩን የፖለቲካ ሴራ አመላካች ነው፡-
‹‹መታወቅ ያለበት አንድ ጥያቄ በተደጋጋሚ የሚጠየቅ ከሆነ፣ እኛም አንድ ቦታ ስንደርስ ‹ለዚህ ጥያቄ ብዙ ጊዜ መልስ ሰጥተናል፤ ጥያቄው ይህ ከሆነ የሠልፍ ትርጉም ምንድነው?› ብለን የምናቆምበት ደረጃ እንደርሳለን፡፡ ምክንያቱም ሠልፍ ለዘላለም የሚካሄድበት ሀገር ያለ አይመስለኝም፡፡››
በተመሳሳይ መልኩ የሃይማኖት ማህበራት የሚያነሱትን የመብት ጥያቄም ወዴት ሊገፋው እንደሚችል ጥቁምታ ሰጥቷል፡-
‹‹የሀይማኖት ግብንም አክራሪዎች በምድር ላይ ሊሰሩ የሚፈልጉትን ግብ ሁለቱን የሚያምታቱ ሰዎች አሉ፤ የሌላውን ግብ በምድራዊ ዓለማዊ ማሳካት ስለማይቻል፣ እነዚህ ፖለቲከኞች ይዘዋቸው እንዳይነጉዱ፣ ከህዝብ እንዲነጠሉ ምክር ማስተላለፍ እፈልጋለሁ፡፡ የሚታወቁ ስላሉ፡፡ በተለይ ወጣቶች፣ ከወጣቶችም ወጣት ሴቶች በአሁኑ ወቅት በዚህ ውስጥ ተሳትፈው የሚጓዙ እንዳሉ በግልፅ ይታወቃሉ፡፡ መንግስት በዚህ ደረጃ ለእነዚህ አካላት መልዕክት ማስተላለፉ ጠቃሚ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡››
የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትን በሚንስትር ዴኤታ ማዕረግ የሚመራው ሽመልስ ከማልም ከ‹‹ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ)›› ጋር ያደረገውና ጥቅምት 3 ቀን 2006 ዓ.ም በታተመው ‹‹አዲስ ዘመን›› ጋዜጣ ላይ በወጣው ቃለ-ምልልስ እንደተለመደው ጉዳዩን በተመለከተ ጠንከር ያለ ማስፈራሪያና ማስጠንቀቂያ ለማስተላለፍ የፈለገ (የታዘዘ) መስሎ አግኝቸዋለሁ፡-
‹‹አንዳንድ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሕጉን እናሰርዛለን፣ ሕጉ ሰብዓዊ መብት የሚጥስ ነው ብለው በአደባባይ የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰሙ የሚታዩና በተዘዋዋሪ መንገድ ከሽብርተኞች ጋር ለሽብርተኞች የሞራል ድጋፍ ሲሰጡና ሲቸሩ የምናያቸው አንዳንድ ወገኖች ሳያውቁ፣ ግንዛቤ ሳይኖራቸው በቀና መንገድ ተሳስተው ነው የሚል ግምት ሊኖር የሚገባው አይመስለኝም፡፡
እነዚህ ወገኖች አውቀው ነው ይህንን ሥራ የሚሰሩት፤ በስሌት ነው ይህን የሚከናውኑት፡፡››
በእርግጥም የስርዓቱ የሴራ ቀማሪዎች ‹‹አንድነት እና ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ የፈጠሩት መነቃቃት፣ በጊዜ ካልተቋጨ በሚቀጥለው ዓመት በሚደረገው ምርጫ ‹ባልታወቀ ስፍራ የተኛ ሰይጣን ቀስቅሶ፣ ድንገቴ ማዕበል ሊያስነሳ ይችላል›› የሚለው ትንተናቸው ይመስለኛል ቀድሞም የጠበበውን ምህዳር ይበልጥ ለማጥበብ (ለመድፈን) ከወዲሁ እላይ-ታች እንዲሉ ያስገደዳቸው፡፡
እንደ መውጫ
ስርዓቱ በብዙ መልኩ ያለ ስኬት ከሃያ ሁለት ዓመታት በላይ መጓዙ እርግጥ ነው፡፡ በተቃውሞ ሰፈርም ይህንን ሁናቴ ለመለወጥ አብዛኛውን ዓመታት የበረዶ ያህል ቢቀዘቅዝም፣ አልፎ አልፎ እየጋመ ለውጥ ለማምጣት ያደረገው ሙከራ፣ አገዛዙ ካከማቸው ኃይል ጋር ባለመስተካከሉ ደጋግሞ መምከን አሳዛኝ ዕድል ፈንታ ሆኖ ቆይቷል፡፡ በዚህ ዓመት የተያዘው ዕቅድም ከቀድሞ በባሰ መልኩ፣ ለመደራጀት የሚውተረተረውን ኃይልም ሆነ ተበታትኖና ተከፋፍሎም ቢሆን ለውጥ የሚጠይቀውን ህዝብ በተለያየ መንገድ ማቀዝቀዝ ላይ የሚያተኩር ነው፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ጉዳዩን በደንታቢስነት ማየቱ ይህ እውን ሆኖ የ2002ቱ የምርጫ ድል፣ በ2007 ዓ.ምም ይደግም ዘንድ ፍቃድ የመስጠት ያህል ነው የምለው፡፡
አሁንም አረፈደም፡፡ ነገር ግን ፈረንጅኛው እንደሚለው ‹‹እውነቱ ግድግዳው ላይ ተፅፏል›› የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ ለውጥ ፈላጊ ዜጎች… ስርዓቱ ለህዝብ ፍላጎት ይገዛ ዘንድ ከዚህ ቀደም ያልተሞከሩ (በሰላማዊ ትግል ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ) አማራጮችን ከመተግበር ውጪ ጠረጴዛው ላይ የተቀመጠ ተጨማሪ ‹የዕድል ቁጥር› አለመኖሩን መቀበል ይኖርባቸዋል፡፡
Sunday, 20 October 2013
Subscribe to:
Posts (Atom)