Monday, 21 March 2016

በኤርትራ እና በዙሪያዋ ለስለላ ስራ እንዲሁም ለቅኝት የዉጊያ ስምሪት እንዲጠቅሙ ተብለዉ የተሰማሩ የህወሃት ወታደራዊ መረጃ አባላቶች እየታደኑ መታፈናቸዉን የሚያረጋግጡ መረጃዎች አፈትልከዉ ወጥተዋል።

በተልይም ሞላ አስገዶም ከኤርትራ ወደ ህዉሃት ከፈረጠጠ ወዲህ በኤርትራ እና በኢትዮጵያ ነጻነት ሐይሎች የደህንነት ክትትል ምክንያት በህወሃት መረጃ ሰንሰለት ስር የነበሩ ሰላዮች በሙሉ መረሸናቸዉን የወያኔ ወታደራዊ ደህንነት በማረጋገጥ ለመከላከያ ሚኒስቴሩ እና ለሚመለከታቸዉ የደህንነት ክንፎች አሳዉቋል። ወታደራዊ ደህንነቱ ሌሎች በተለያየ ምክንያት ወደ ኤርትራ ሰርገዉ እንዲገቡ የተደረጉ የስለላ ሰዎች በተለይም የአርበኞች ግንቦት ሰባትን አጠቃላይ ፖለቲካዊና መሰረታዊ የአደረጃጀት እርከን፣ እንዲሁም ወታደራዊ ኮርሶችና ዲስፕሊኖችን፣ ስልታዊ መዋቅርንና አቀማመጥን ለመሰለል እንዲረዱ ከተሰማሩ ግለሰቦች ዉስጥ አንዳቸዉም የት እንደገቡ ለማወቅ ያለመቻሉን ምንጮቻችን ጠቅስዋል። ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ወደ ዉጊያዉ አምድ ከተቀላቀሉ ወዲህ ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ በፍጥነት እየአሰገሰ በመምጣት ላይ የሚገኘዉን የለወጥ ነዉጥ መቛቋም የተሳነዉ የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን ወታደራዊ ደህንነት የአርበኞች ግንቦት7ን እና የጥምር ሐይሎችን እንቅስቃሴ ማወቅ እንኳ እንደተሳነዉ በወታደራዊ የደህንነት ስልትም መበለጡን በተለይም የተሳሳቱ መረጃዎች እየደረሱት ላም ባልዋለበት... ሲቅበዘበዝ የነጻነት ሐይሎቹ ሽምቅ ዉጊያ ሰለባ እየሆነ መምጣቱን ለተደራቢ አዛዡ ሌተናንት ጄኔራል ዮሃንስ ገብረመስቀል ውይይት እንዲደረግበት ከቀረበው አጀንዳ ለመረዳት ተችሏል። ስርአቱ አሁን ባጋጠመዉ የመረጃ መዳፈን ምክንያት ስጋት ላይ ስለወደቀ ድንገተኛና የተጠናከረ ተመላላሽ ጥቃት እንዲሰነዘር እንዲሁም በጎንደር ዙሪያ የሚገኘዉ የመከላከያ ሰራዊት በእጅጉ እንዲጠናከር ለማድረግ ከሸዋሮቢት የመጡ አዲስ ወታደሮች ወደ ክፍለ ጦሮቹ እንዲካተቱ እና አጥቂዉ የግንባር ሐይል ለመመሪያ ዝግጁ እንዲሆን በአመራሮች ቢወሰንም ከተራ ወታደር አንስቶ እስከ ከፍተኛ አመራሮች መመሪያ ለመቀበል ስጋት ላይ ናቸዉ። ይህን መረጃ አያይዘዉ የላኩልን ምንጮች በኤርትራ የሚገኙ የነጻነት ሐይሎች ከምንዜዉም በበለጠ በንቃትና በመጠናከር እየወደቀ የሚገኘዉን ባለ ሁለት እግር ዝሆን ለመጣል እንዲዘጋጁ መዘናጋትን ፈጽመዉ እንዳያስቡት አስጠንቅቀዋል። ከአራት እግሮቹ ሁለት የፊት እግሮቹን የቆሰለ ዝሆን ለመጣል ዝሆን መሆን አያስፈልግም። ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

Sunday, 20 March 2016

በኦሮሚያ በየቦታው የአጋዚ ጦር አባላት እየተገደሉ እየተገኙ ነው – ግብር ሰብሳቢዎች “ህዝቡን ፈራን” አሉ

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የአጋዚ ጦር አባላት እየተገደሉ እየተገኙ እንደሚገኙ ከተለያዩ ሥፍራዎች ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች አመለከቱ:: ታክስ ሰብሳቢዎችም እንዲሁ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውረው ግብር ለመሰብሰብ ሲሞክሩ በሚደርስባቸው ጥቃት የተነሳ ሥራ መስራት እንደተቸገሩም ለማወቅ ተቻለ::የዘ-ሐበሻ የመረጃ ምንጮች እንዳመለከቱት በ አርሲ በባሌ በምስራቅ እና ም ዕራብ ሐረርጌ, በምስራቅ ሸዋ; በ ም ዕራብ ሸዋ የተለያዩ ቦታዎች በየቀኑ የአጋዚ ጦር አባላት ባልታወቁ ሰዎች እየተገደሉ በየጫካው ሥር እንደሚገኙ ታውቋል””በም ዕራብ ሸዋ አምቦ; አመያና ግንደበረት ባለፉት 3 ሳምንታት ብቻ ከ6 በላይ የአጋዚ ጦር አባላት ተገድለው ተገኝተዋል:: እንደ አይን እማኞች ገለጻ በግንደበረት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን አካባቢ የአጋዚ ጦር አባላት ላይ ህዝቡ እርምጃ እንደወሰደም ታውቋል::ከግንደበረት አካባቢ የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለከቱትም ህዝቡ ተፈትሮዋዊ ያልሆኑ ገደሎችን በመሥራት የአጋዚ ጦር መኪኖች ሲሄዱ እንዲገለበጡ በማድረግ ላይ እንዳለም ታውቋል:በአሪሲ ሮቤ; መርቲ; ገደብ; እና ኮፈሌም እንዲሁ የአጋዚ ጦር አባላት እየሞቱ እየተገኙ ሲሆን መንግስት ግን ይህን ደብቆ እንደሚገኝ ታውቋል::ይህ በ እንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ የተለያዩ ቦታዎች ግብር ለመሰብሰብ የሚንቀሳቀሱ የመንግስት አካላት ላይ ሕዝቡ ጥቃት በማድረሱ የተነሳ ግብር ሰብሳቢዎች “ህዝቡን ፈራነው ስለዚህ ሄደን ግብር ክፈሉ ማለት አንችልም” በማለት ሥራ እንዳቆሙ ለመረዳት ተችሏል:: ግብር ክፍሉ እያሉ በም ዕራብ ሸዋና በምስራቅ ወለጋ የተንቀሳቀሱ የመንግስት አካላትን ሕዝቡ በቆመጥ ቀጥቅጦ እንዳባረረም ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች አመልክተዋል::ከም ዕራብ ወለጋ የደረሱን መረጃዎች እንደሚያመለከቱትም በተለይም በነጆ; በጃርሶና ጊምቢ አካባቢም ህዝቡ አድብቶ በመጠበቅ በአጋዚ ወታደሮች ላይ ጥቃቶችን እየፈጸመ ይገኛል::

Wednesday, 30 September 2015

አገር የምትኖረው በ3 ነገር ነው በወታደር በገበሬ እና በመምህር ። – ከአዲስ ብርሃኑ ፡

ethiopiaአገር ለማፍረስ ቆርጦ የተነሳው ወያኔ ኢትዮጵያ የምትባለው አገር እንድትኖር በመሰሪ ሃሳቡ ሌት ተቀን የማይቆፍረው ግድጓድ የለም የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። ነገር ግን እንደ አሳቡ ሊሆንለት አልቻሉም ዘር ከዘር ሊያጋጭ ብዙ ጣረ አልተሳካለትም፤ ሐይማኖት ከሃይማኖት ሞከረ ይሄም አልሰራ አለው ሃሳቡ ሁሉ መና ሲቀርበት እራሱ ከሳሽ እራሱ ፈራጅ በሆነበት ፍርድ ቤት የብዙሃን ነጽሃን ሰው መሰቃያ ወደ ሆነው ወህይኒ እየወረወረ ባልሰራበት ወንጀል ባላደረጉት ድርጊት ንጽሐኑን ማሰቃየት ከጀመረ ድፍን 24 አመት አለፈ። -
መምህር….. አንድ አገር ከሚያስፈልጋት ዋናው መሰረታዊ ነገር መምህር ነው። መምህር ከሌለ የተማረን ህብረተሰብ ማግኝት አይቻልም። መምህር በጠመኔው ለአገር የሚሆን ፍሬ ለህዝብ የሚጠቅም ዘር በሰው አእምሮ ውስጥ የሚዘራ እና ብዙ ጥበቦች ባለ ብዙ እውቀት ባለቤት አገርን በጥበብ የሚመራ ላገሩ በእውቀት የሚያገለግል ለአገር የሚጠቅመውን ካመነበት የሚሰራ ካላመነበት ደግሞ እንቢ የሚል ማንኛውንም ነገር ሰለ ህዝብ ብሎ ስለ አገር ብሎ ማድረግ የሚቻል ዜጋን የሚቀርጹት መምህራናን ናቸው። ዛሬ ወያኔ እያደረገ ያለው እኔ የምላቹሁን አድረጉ እኔ የምላቹሁን አስተምሩ እኔ የምላቹሁን መመርያ ተቀበሉ ብሎ አገርን የሚያጠፋ ሆኖ ሰላገኙት የወያኔ ደጋፊ ባለመሆናቸው ብቻ አገርን የሚያቀኑን መምህራን ትውልድን የሚቀርጹ መምህራን በካድሬ በመተካት የተማረ እንዳይበቅልባት ያወቀ እንዳይወጣባት ትምህርት ቤቶችና ዪንቨርስቲዎች ያቃጣሪወች መናህርያ አድርጓታል። እንግዲህ ወገኔ የመምህራን መነካት የኢትዮጵያ አንዱ መሰረቱ እየተናጋ ነውና ልትነቃ እና የወያኔ አገር አጥፊነቱን አውቀን በቃህ ልንለው ይገባል። ገበሬ…… አገር የምትኖረው ገበሬው አምርቶ በሚያበቅለው ምርት ነው ገበሬው ጠንክሮ በማረስ አገርን በመመገቡ ሂደት የአገርን መሰረት ነው። ዛሬ ገበሬው ከመሬቱ በማፈናቀል ለውጪ ባለሃብት ለኢንቬስተር በመስጠት እንዲሁም በግድ ማደበርያ እንዲወስድ እያደረጉት ባለ እዳ በማድረግ እዳውን መክፈል ሳይችል ሲቀር መሬቱን ጥሎ እንዲሄድ በማድረግ ተሳዳጅ አድርገውታል። ገበሬ የለም ማለት አገር የለችም ማለት ነው ።ገበሬው በማሰቃየት እረፍት በመንሳት እስመርረውት ያሉት ወያኔወች ሃሳባቸውም ራያቸውም ሰለ ኢትዮጵያ እና ሰለ ሕዝቧ ስላልሆነ ስለሚያደርጉት ነገር መጸጸት እንኳን አያሳዩም ስለዚህ ገበሬው ሲነካ የአገር መሰረት መነካት ነውና ወገኔ እንግዲህ ንቃ። ወታደር….. አገር የምትጠበቀው በወታደር ነው አንድ አገር ጠንካራ የወታደር ከሌላት ጠላት በቀላሉ ይዳፈራታል። ስለዚህ ጠንካር የወታደር ተቋም ለአገር አጥርም መሰረት ነው። ዛሬ ግን ወያኔ እየሰራ ያለው የወታደር ተቋም በወታደራዊ ስልጠና እንዲሁም ትምርት በብቃት የሚበልጣቸው እያሉ ትግሬ በመሆኑ ብቻ አዛዥ ቦታ ላይ እንዲቀመጥ ይደረጋል ይሄ አካሄድ ለወያኔወች የአገር ማፍረስ አላማቸው ስለሆነ ምንም አይሰማቸው ለትግሬወች ግን ጊዚያዊ ሹመት ሲሰጣቸው ሁሉንም ቦታ ያለ እውቀታቸው ቦታውን እንዲይዙት ሲደረግ ለምን ብላቹ መጠየቅ ሲገባቹሁ የተሰጣችሁን ስልጣን ተቀብላቹ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ላይ በደልና ጫና የምትፈጥሩ እንግዲህ እዳው በእጃቹ ነው። የወያኔ ባለስልጣን ባንተ ስም የአገርን ንብረት እየዘረፉ እያሸሹ ይገኛሉ አንተ ግን ከህብረተሰቡ ጋር የትም አትሄድም ያኔ በሰፈሩት መስፈርያ እንዳይሆንባቹሁ የትግሬ ተወላጆች በወታደር ላይ የምታደርጉትን በደል ታቆሙ ዘንድ ያስፈልጋል። እንተም ከጥቂት የአገር አጥፊ እና ዘረፊ ጋር ባለመወገን አንድነታቹሁን የምታሳዩበት ጊዜ በጣም አጭር ነውና ይታሰብበት። ካለበለዚያ ግን ወደ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ደምና ጉልበት እንዲሁም በኢትዮጵያ ሕዝብና ሃብት እንደፈለጋቹ እየሆናቹ የምትኖሩበት ጊዜ ማብቂያው ይመጣል። ወታደሩም እራሱንና አገሩን ሕዝቡን የመጠበቅ ነጻ የማውጣት ሃላፊነት እንዳለበት ወያኔ የሚያውቅበት ጊዜ ቅርብ ነው። ወያኔወች የመከላከያ ሰራዊት የሃገር መሰረት ስለሆነ ይህንም ለማፍረስ እና ለመበተን ሌት ተቀን እየሰሩ ነው። እውነት ነው መምህሩም ወደቀድሞ ቦታቸው ተመልሰው ባላቸው እውቀት ጠመኔን ይዘው ያለምንም ተጽእኖ ዜጋን የሚያፈሩበት ጊዜ ቅርብ ነው። እውነት ነው ገበሬው ሞፈሩን አንስቶ እርሻውን አስፍቶ በትራክተር አርሶ ሕዝቡን የሚመግብበት ቅርብ ነው ። እውነት ነው ወታደሩ ወያኔን የተባለ ወንበዴን አጥፍቶ ለሕዝቡና ለአገሩ ዘብ የሚቆምበት ጊዜ ቅርብ ነው ። ሞት ለወያኔ!!! አዲስ ብርሃኑ -

Friday, 14 August 2015

በአገራችን በሰሜን ምስራቅ እና በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ መጠኑ እየጨመረ መጥቷል፡፡

በአገራችን በሰሜን ምስራቅ እና በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ መጠኑ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ጉዳዩ ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው ተመሳሳይ ድርቅ በመጪው አመት 2008 ዓ.ም በጥቅምት እና በህዳር ወር ሊከሰት እንደሚችል ባለሙያዎች እየጠቆሙ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ገዥው መንግሰት አሁንም የችግሩን አሳሳቢነት ወደ-ጎን በማድረግ ፤የስራዓቱ ደጋፊ እና አቀንቃኝ ከሆኑ ዲያስፖራ ጋር “አስረሽ ሚቺው” እያለ ከበሮ እየደለቀ ይገኛል፡፡ ሆኖም በአገራችን በተለይ በሰሜን ምስራቅ የተከሰተው ድርቅ እንስሳቶችን በከፍተኛ ሁኔታ እየገደለ የሚገኝ ሲሆን ፣በሰው ሕይወት ላይ ቁጥሩ ቀላል የማይባል የሞት አደጋ እያንዣበበ ይገኛል፤በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎች በሰውንት መዳከም እና እስን ተከትሎ በሚመጣ በሽታ እየተጠቁ ናቸው፡፡ ይህ እውነት ከባለፉት ቀናት ዛሬ ላይ ከኢትዮጵያ አልፎ በአለም ላይ መረጃው እየተሰራጨ ይገኛል፤ ይሄን ተከትሎ ገዥው መንግሰት መረጃውን ደብቆ የመያዝ ፍላጎቶ ሊከሽፍበት ችሎአል ፡፡ የመንግሰት ውጥን ሣይሳካ ሲቀር፣ የመንግሰት ኮሚኒኪሽን ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሬዲዋን ሁሴን “ሰባት ሞቶ ሚሊይን ብር በጀት የያዝን በመሆኑ ችግሩን መቆጣጠር እንችላለን” በማላት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ነገሩን ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው እንደሳቸው ገለፃ “ምንም አይነት የዉጪ እርዳታ አያስፈልገንም፣ የዚህን ያህል አሳሳቢ ደረጃ አልደረሰም” ማለታቸው ነው፡፡ እሳቸው ይሄን ይበሉ እንጂ አሁን ላይ የተከሰተው ድርቅ እና በቀጣይ አመት ይከሰታል ተብሎ የተገመተው ድርቅ፣ ከመንግሰት ቅድመ ዝግጅት ማነስ እና የእርዳታ ድርጅቶች መንግሰት በተለመደው መንገድ እየተከላከለ የሚቀጥል ከሆነ፤ አገራችን አስከፊ ሁኔታ ውስጥ የሚከት ነው፡፡ መንግሰት 7መቶ ሚሊየን ብር መደብኩ ይበል እንጂ፣በመንግስት የአሰራር ብልሹነት እና ስር ከሰደደው ሙሱና አንፃር ችጉሩን የቱንም-ያህል ፈቀቅ እንደማያደርገው እውን ነው ፡፡ መንግሰት በተለያየ ወቅት ኢትዮጵያ በምግብ እራሷን ችልለች ይበል እንጂ፣ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ጾም አዳሪ ነው፡፡ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ድርቅ ተከስቶ መንግስት እርዳታ አያስፈልግም ችግሩን መቋቋም እችላለለው በማለቱ፤ አለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ድጋፍ ማድረጋ ባለመቻላቸው በሰው እና በእንስሳ ላይ ቁጥሩ ቀላል የማይባል ሞት ተከስቷል፡፡ ድርቁ ሊከሰት የቻለበት ዋና ምክንያት ከአለም አቀፍ የአይር ንብረት ለውጥ ጋር በተገናኘ ነው፡፡ በጠንካራ የመንግሰት አስተዳደር እራሳቸውን ላዋቀሩ በሌሎች አገራት፣ ይህ አይነቱ ድርቅ በሚከሰትበት ወቅት ከመንግሰት የመጠባበቂያ በጀት እና የእህል ክምችት በመጠቀም ችግሩን ለመቋቋም ጥረት ይደረጋል፡፡ እንዲህ አይነቱ መሠረት የሌለው መንግሰት እና ሕዝብ ደግሞ በለጋሽ አገራት የገንዘብ ድጎማና የምግብ እርዳታ ይደረጋል ፡፡ በተለይ ደግሞ አምባገነን መንግስታት በሚመሩት አገር የደርቅ ችግር በሚከሰትበት ወቅት ችግሩን አፍኖ መያዝ ዋንኛ መገለጫቸው ነው፡፡ እንደምክንያትነት የሚነገረው “እረዳት አያስፈልገንም እራሳችን ችለናል” የሚል ባዶ ቀረርቶ ነው፡፡

Saturday, 18 July 2015

አሜሪካኖቹ ዲፕሎማቶች የኢትዮጵያ መንግስትን አስጠነቀቁ

**የኦባማ ጉብኝት ለውይይት እንጂ ወንጀለኛን መንግስት ለማጽደቅ እንዳልሆነ አስረዱ ** “የተፈቱት የዞን ዘጠኝ ጋዜጠኞች ፓስፖርታቸው እንኳን እንዳልተመለሰ እናውቃለን:: መጀመርያውኑ መታሰር እልነበረባቸውም:: ሲፈቱም አፈታታቸው ሙሉ አይደለም” ዛሬ እዚህ ዋሺንገተን ዲሲ ላይ ጠንካራ ውይይት ሲካሄድ ነበር:: ውይይቱ የኦባማን የምስራቅ አፍሪካ ጉዞ በተመለከተ ሲሆን : አሜሪካኖቹ መራር መልሶችን ሲመልሱ ተደምጠዋል:: የኦባማ ጉብኝት ለአምባገነኖች ሽፋን መስጠት ሳይሆን ሌሎች በርካታ ዓላማዎች እንዳሉትም አስረድተዋል:: በውይይቱ የዞን ዘጠኝ ጋዜጠኞች አስር ፈጽሞ ያልተገባ መሆኑን ጠቅሰው: ሲፈቱም ሙሉ ነጻነት እንዳልተሰጣቸው ፓስፖርታቸው እንኳን እንዳልተመለሰላቸው አስረድተዋል::ከዚሁም ጋር በተያያዘ ሰሞኑን አቶ ኃይለማርያም ኤርትራን ስለመምታት የተናገሩትን ዛቻ በተመለከተ ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል:: ኢትዮጵያ የኤርትራን ድንበር ጥሳ እንዳትገባና ብትገባ ግን አሜሪካ እንደምታወግዘው ገልጸዋል:: ሌሎችም ሌሎችም ውይይቱ ይህን ይመስል ነበር ::

Friday, 22 May 2015

የወያኔ በጉልበት የምረጡኝ ዘመቻ (ከ አዲስ ብርሃኑ)

ንብን ምረጡ ማለት ከጀመሩ ሰነባብተዋል ። ለአገር እድገት፤ ለብለጽግና ፤ለእኩልነት ፤የተጀመረውን እድገት፤ ለማስቀጠል እያሉ...... እያሉ.... መንገድ ተሰራ፤ ህንጻ ተሰራ ፤ስልጣኔ ገባ ፤ይህን ሁሉ በዘመነ ኢህአዲግ ነው ብለው ይናግሩናል። ይህን ማለታቸው ጥሩ። ምንም ተቃውሞ የለኝም ። አንድ ኢትዮጵያዊ የፈለገውን የመከተል እና የማመን ጉዳይ ነው ። ሌላም ሌላም ይጨምሩ ስለነሱ ማውራት ሳይሆን ለኛም እድል ስጡን እኛም ስለ ኢትዮጵያ የምነለው ነገር አለ ስለ ወያኔም የምንነቅፈው ነገር አለን ይህ ነው ቁምነገሩ ፍርድ እና ውሳኔውን ለሕዝብ በመተው ሕዝብ የመረጠውን እንዲመራው ማድረግ ግድ ይላል። ወያኔ ኢትዮጵያን ማስተዳደር ከጀመረ የማይታወቁና የማይፈለጉ ሃሳቦች እና ነገሮች ገብተዋል። ያም ህዝብ ወዶ ሳይሆን በግድ የህዝብ ሃሳብ ተጥሶ የአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ሃሳብ እና አላማ እየተንጸባረቀ ነው። ባንዲራው ላይ ከተለጠፈችው ኮከብ ብንጀምር ከ90% በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን የኮከብ ምልእክት አርማ ያለውን ባንድራ አይቀበለውም ።የኮከቡ ትርጋሜውም ወይም አላማው ሌላ ነው። ኮከባ የምትገልጸው የስይጣንን አምላኪወችን ሲሆን በኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ የተለጠፈው ኮከብ ሶስት ትረጔሜ አለው እነሱም እንደሚከተሉት ናቸው። 1 የኢትዮጵያን ህዝብ በሰይጣናዊ ሃይል ለማፍዘዝ ፦ 2 ስይጣን ፍቅር ስለማያውቅ መለያየት እና መጣላት በኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ ለማስረጽ፦ 3 የኢትዮጵያ ህዝብ አውቆም ሆነ ሳያውቅ የሰይጣን ምልክት የሆነውን የሰይጣንን ምልክት እንዲያውቅ እና ክፋታዊ የሰይጣንን አሰራር እንዲለማመድ ለማድረግ ነው። በዚህ ዙርያ ትንሽ ብዬ ወደ ወያኔ ወደሆነችው አርማ እሄዳለው በኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔ ከገባ ጀምሮ የአገሬ ህዝብ ውስጥ ብዙ ክፋት አብሮ ገብቱአል። ለዚህም ኮከባ የወለደችው ወይም ያፈራችው ፍሬ ስናይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ፍቅር ጠፍታል ። የኢትዮጵያ ህዝብም ብርን እና ጥቅምን አምላኪ ከመሆኑ የተነሳ ወንድም ወንድሙን ፤እህት እህቷን፤ ወላጆች ልጆቻቸውን ፤አሳልፈው ይስጣሉ። ሁሉም ስልጣን ናፋቂወች ሆነዋል። አባት ከልጁ፤ እህት ከወንድም፤ ዘር ከዘር ፤ጎሳ ከጎሳ ፤ሃይማኖት ከሃይማኖት፤ ኢትዮ ጵያ ውስጥ ከእለት ወደ እለት ግጭቶ ች እየተበራቱ ጥላቻወች በሰፊው እየታዩ ነው። እናት ሌባ ልጅ ቀማኘ የሚለው ቢሄል (አባባል) በአሁን በዘመነ ወያኔ እያየነው ነው። መሪዎች ተብዬዎች ሌባ ሎሌዎች ደግሞ ቀማኞች የሆነች ሐገር ከመሰለች ሰነባብታልብ ።የጠፋው ፍቅር እንዲመለስ እና የተወሰድብን ክብር እንዲመጣ የወያኔ አዚም የሆ ነችውን ኮ ከብ ከኢትዮጵያ ምድር ማጥፋት መቻል አለብን። ይህ ኮከብ ቢሄር ቤሄረስቦችን የሚወክል ሳይሆን ጥላቻና መለያየትን የሚያሰፍን ፍቅርን የሚያጠፋ የሰይጣንን ስረአት የመከተል እና የሠይጣንን አርማ ከፍ አድርጎ የማሳየት ስራ ነው። ወደ ንብ ስንመጣ ደሞ ንብን ምረጡ... ንብን ምረጡ ...እያሉ መለፍለፍ ከጀመሩ ሰንብተዋል መረዟን ብቻ እንጂ ማሯን የማናየውን ንብን ፤በየአገሩ እየዞረች እሾኴን የምታራግፈዋን ንቧን፤ ማሯን ለንጉሶቻ ብቻ የምታበላዋን ንቧን ፤ህብረተሰባን ማሯን ታበላን ይሆን ብሎ የሚጠብቃት ተስፈኘዋን ንቧን ፤ይችን ንብ ነው ምረጡ የሚሉን። የንብ በሀሪ የአንድ ቀፎ ንብ ከሌላ ቀፎ ንብ ጋር በፍጹም አይሰማማም ተሳስታ አንዷ ንብ ወደሌላ ቀፎ ከሄደች ይገድሏታል። ወያኔም ልክ የንብ በሀሪ ነው ያለው። ከወያኔወች ድርጅት ውጪ የሌላ ድርጅት የሆነ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲኖር አይፈለግም ። ንቦች ማራችውን የሚሰሩት ለራሳችው እና ለንጉሳ ቸው ብቻ ነው። ወያኔዎችም የሚሰሩት ለራሳችው እና ለሹማምቶቻችው ብቻ ነው። ንቦች ለማር መስሪያ እንዲሁም ለቀፎ አገልግሎት የሚሆነውን በሙሉ የሚጠቀሙት ክቀፎአቸው ወጥተው በሰአት 100 ኪ. ሜ ያህል በመብረር ከአካባቢያችው ስብሰበው ወደቀፎአቸው የገባሉ። ወያኔዎቸም የኢትዮጵያን ንብረት በሙሉ በሁሉም አቅጣጫ በመዘዋወር እየዘረፉ ለራሳቸው ያክማቻሉ። ንቦች የራሳቸው ባልሆነ ነገር ማራቸውን እየሰሩ የሌላ ቀፎ ንብ ግን ወደነሱ ቀፎ እንድትገባ አይፈልጉም ወያኔም ምንም ቅሬታ በሌላችው ስዎች የሌላውን ህብረተሰብ ሃብት ለመጠቀም ይስበሰባሉ። ሊላው ህብረተሰብ ወደ እነሱ ሲጠጋ ግን ያጠፉታል ።ስለዚህ የንብን ማር መብላት የሚችለው የቀፎወቹ ንቦች ብቻ ናቸው። የኢትዮጵያንን ሃብት እየበላ እና እየተጠቀመ ያለው ብቻውን ወያኔ ነው። ኢትዮጵያ ማር ነች ማርን ደግሞ ሁሉም ይፈልጉታል አንድም ለመብላት አንድም ለመድሃኒት። ማር መብላት ካማሮት ወደ ንብ ቀፎ ባዶ እጅ አይኬድም እንደጭስ ያለ መከላከያ እና ማሩን መቁረጫ ቢላ ያስፈልጋል። ካለበለዝያ ግን በመርዝ ተወግተው ይሞታሉ። ወያኔም እንደዚሁ ነው የኢትዮጵያን ሃብትና ንብረትን የብቻው አድርጎ ማስተዳደር ከጀመረ ሰንብታል ስለዚህ ኢትዮጵያ የምትባለው አገር የወያኔ ብቻ መስሎ ከታያቸው ሰንብታል። የኢትዮጵያ ሃብት የኢትዮጵያን እንጂ የጥቂቶች ብቻ አይደለችም ብሎ ለመጠቀም እና ለሁሉም ለማዳረስ ባዶ እጅ ተኪዶ አይሆንም ።በባዶ እጅ ከተኬደ በመረዛቸው ወግተው ስለሚገሉ መከላከያ አድርገን ኢትዮ ጵያን ማዳን ግድ ይለናል። ስለዚህም ምርጫ ..ምርጫ.... የሚለው የወያኔ የማደናገርያ ዘዴ ነው እና ይህ ምርጫ አልጫ እንደሆነ እና ትርጉም የሌለው መሆኑን ልንረዳው ይገባል። አልጫ የሆነው ምርጫ የሚለወጠው አልያም የጣፈጠ የሚሆነው የሁሉም ኢትዮጵያዊ የነቃ ተሳትፎ ሲያደርግ ነው። ንብን በማጥፋት በመርዙ ከመወጋት እና ከመሞት የኢትዮጵያ ሕዝቡ ነጻ ሁኑ። ባንዲራው ላይ ያለችውን ኮከብ በማስወገድ የሰይጣንን መንፈስ የኢትዮጵያ አርማ ከመሆን እንከላከል እላለው። ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!!!! ከ አዲስ ብርሃኑ Email.. berhanu.addis@yahoo.com

Friday, 15 May 2015

በፍርሃት ውስጥ ያለው የኢሕአዴግ ሥርዓት የማዕከላዊ ዕዝ ወታደሮች ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ መመሪያ አወረደ!

የኢህአዴግ ስርአት የማእከላዊ እዝ ወታደሮች ከቦታ ወደ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ መምሪያ እንዳወረዱላቸው ምንጮቻችን ገለፁ ሲል የደህሚት ድምጽ ዘገበ:: በአዲ-ኮኮብ የሰፈሩት የማእከላዊ እዝ የበታች አመራር ወታደሮችና ተራ ወታደሮች ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር እንዳይገናኙና ወደ አዲ-ዳዕሮና ሸራሮ እንዳይንቀሳቀሱ ተከልክለው እንደሚገኙ የገለጸው የደህሚት ድምጽ እነዚህ የበላይ አመራሮች ሰራዊቱን በመሰብሰብ በአዲ-ዳዕሮ፤ አዲ ነብሪ ኢድ፤ አዲ-ሃገራይ፤ ሸራሮና አካባቢው በአጠቃላይ በአካባቢው የሚገኝ ህብረተሰብ የትህዴን አባል ሰለሆነ የምናጣራው ነገር አለን መንቀሳቀስ ክልክል ነው በማለት ትእዛዝ እንዳወረዱላቸው ለማወቅ ተችሏል። በተጨምሪም- ወታደሮቹ በአካባቢው ህብረተሰብ ላይ ጥላቻ እንዲያሳድሩና ከሱ ጋር እንዳይወግኑ የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ቅስቀሳ ሲሰጥ የሰነበተ ሲሆን ስርአቱ ከህዝብ ተነጥሎ በጠምንጃ ሃይል ብቻ የቆመ እንደሆነ በሚገባ ሰለሚያውቅ ወታደሮቹ ደግሞ ስርአቱን በመተው ከህዝባቸው ጋር እንዳይወግኑ በመስጋት የመነጨ መሆኑን ወታደሮቹ በሚገባ እንደተረዱት ለመረጃ ምንጩ የደረሰው መረጃ አስረድቷል።